Thursday, September 1, 2016

ሰበር ዜና! የህወሀት/አህአዴግ አገዛዝ በአማራ ክልል ሕዝብ ላይ ይፋዊ ጦርነት ፣ ይፋዊ የዘር ፍጅት አወጀ!


በአማራ ከልል የህወሀት ጉዳይ አስፈፃሚ የሆነው የብአዴን ኮሚኒኬሽን ሐላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን የስርጭት አድማሱ በአዲስ አበባና ዙሪያ ብቻ በተገደበው ሸገር ኤፍ.ኤፍ.ኤም ራዲዮ ቀርበው ‹‹ሕዝባዊ ንቅናቄ እያደረገ ባለው የአማራ ክልል ህዝብ ላይ የመከላካያ ሰራዊት እርምጃ እንዲወሰድ ታዟል›› ብለዋል!!
ይህ የዘር ፍጅት የታወጀው በምእራብውያን አጋዥነት በቆመው የህወሀት ስርዓት መሆኑ አፅእኖት ሊሰጠው ይገባል!!
በተያያዘ ዜናም ዛሬ ማምሻውን ሀይለማሪያም ደሳለኝ በመላው አማራ ላይ የዘር ፍጅት እንዲደረግ  አውጃል እንዲ ሲል
“በአማራ እና በኦሮምያ ክልሎች ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ማንኛውም በጸጥታ ዘርፉ ላይ ያሉት ሁሉ የህግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ አዝዣለሁ አለ።”
ይህ ማለት መብቱን የጠየቀ ባለው ህዝብ ላይ የጥይት መሃት አውርደው ጨርሳቸው እንደ ማለትነው  በሉ እንግዲህ በደንባራው ትእዛዝ የተላለፈላችሁ ሁሉ ኑና ግደሉን። ለኢትዮጵያ ሽህ ጊዜ እንሞታለን!!!
ወያኔ  በአማራ ህዝብ ላይ እልቂት ሊፈጥም ቆርጦ ተነስቷል ። መሳሪያቸውን ወልውለው « ሃድጊዎችን ትጠርጊልናለሽ!» እያሉ መዛት እንደጀመሩም ሰምቻለሁ ። አያደርጉትም አልልም ፥ ጨካኞች ናቸውና ያደርጉታል ። ታዲያ ይህን የአማራ ህዝብ ላይ የተጋረደበትን መከራ ፥ ወንጀሉ ሲፈጠም ም ሆነ ወንጀል ፈጣሚዎቹ ወንጀሉን ወደሚፈጥሙበት ህዝብ ሲያመሩ የሚያሳዩ ማንኛውም አይነት መረጃዎችን ያዙ ።
እርስ በእርስ ተማከሩ ! ተነጋገሩ ! ልዩነት ያላችሁ ፥ የማትስማሙ ብትኖሩ እንኳ ለአማራ ስትሉ ልዩነቱን ወደ ጎን ትታችሁ ጠላቶቻችሁ ላይ አተኩሩ ! ወያኔ ይወድቃል ፥ ግን መስዕዋቱ እንዳይበዛ ጥበብ የተሞላበት ትግል እንደሚያስፈልግ አትዘንጉ። ጠላቶቻችሁ አይተኙም ስለዚህ እናንተ እንቅልፍ እርሱ!
እግዛብሔር ህዝባንና ሀገራችን ይጠብቅ
ሼር ይደረግ ላልሰማ አሰሙ
Aseged

No comments:

Post a Comment