Tuesday, September 20, 2016

ጎንደር እና ባህር ዳር የስራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው [አቤ ቶኮቻው]

vgonder-567ዛሬ ጎንደር ደውለሃል… ዳሩ ስልክ ሲሰራልህ አይደል፤ እሺ ባህር ዳርስ የደወሉለት ደንበኛ የስራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው…የሚል መልስ አግኝተህ ከሆነ አዎ ደውለሃል… ጎንደር እና ባህር ዳር ዳግም በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማ ከተማቸውን ጭርርር አድርገው ውለዋል። ኢህአዴግ መስማት የተሳናት ብቻ ሳትሆን ማመን የተሳናትም ናት እና እንጂ እንደ እውነቱ ከሆነ የሃገሩ ህዝብ አንቅሮ እንደተፋት የአመ ባሉ ዋዜማ በበርካታ የኦሮሚያ ክልል አሁን ደግሞ በብዙው የአማራ መሬት ተቃውሞው በስራ ማቆም አድማ እንዲህ ተቀጣጥሎ ሲከናወን፤ ”አይ እንግዲህ ህዝብ ጠላኝ… ህዝብ ከጠላኝ ምን አለኝ” ብላ አለመፈለጓን አምና ላሽ ባለች ነበር…
ኧረ ዋሽንግተን ዲሲን አይተህልኛል… ኢትዮጵያውያን ከያሉበት ተጠራርተው አሜሪካን አስደመሟት አይደል እንዴ!? መቼም እንደ ዘንድሮ መንግስት በየአቅጣጫው ተጠብጥቦ እና ነጥብ ጥሎ አላየንም።
ትላንት በምድረ አሜሪካ ለፈይሳ ሌሊሳ እንደዛ አይነት የጀግና አቀባበል እዛው በምድረ አሜሪካ የተደረገለትስ ለምን ይመስልሃ… ? በቃ ሰዉ ኢህአዴግ የምትባል ገዢ ፓርቲ በኢትይጵያ ምድር ላይ ፈላጭ ቆራጭነቷ እንዲያበቃ ይፈልጋል። ፈይሳን ጀግና ያደረገው የብር ሜዳሊያው ብቻ አይደለም፤ ወርቅ የሆነው ድምጻችንን ማሰማቱም እንጂ… (ሰዉ ኢህአዴግ ደብራዋለች ስልህ…!)
እወነት እውነት እላችኋለሁ… እንዲህ በያቅጣጫው ካጣደፍናት ይቺ አሮጊት ፓርቲ በቅርቡ ትጭራለች!!!
(እና እናንተ እንዴት ናችሁ…! ?)
bahir-dar-satenawnews-6785
gonder-545
gonder-567
14370318_10205460943001371_1658531143562552636_n
dc-protest-sept-19-2016-satenaw-news
14355715_10205508967083245_9211171498346852074_n

No comments:

Post a Comment