Monday, September 5, 2016

ፈተና በመሸጥ ስልጣንን ለራስ ጥቅም በማዋል መሐይሙ ሽፈራው ሽጉጤ ከትምህርት ሚኒስትርነት ተባረረ።ኣዲስ ስልጣን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል


ፈተና በመሸጥ ስልጣንን ለራስ ጥቅም በማዋል መሐይሙ ሽፈራው ሽጉጤ ከትምህርት ሚኒስትርነት ተባረረ።ኣዲስ ስልጣን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል
በጉራፈርዳ የሚኖሩ ኣማሮችን በማባረር በመግደል በማፈናቀል የሚታወቀው የቀድሞ የደቡብ ሕዝቦች ክልል ርእሰ መስተዳደር የነበረውና በኋላ የትምህርት ሚኒስትር ሆኖ የተሾመው መሃይሙ ሚኒስትር ሽፈራው ሽጉጤ በልምድ ማነስ በኪራይ ሰብሳቢነት እና በኔትወርኮቹ ኣማካኝነት የተማሪዎች ፈተና በመሸጥ በሚል ተገምግሞ ስልጣንን ለራስ ጥቅም በማዋል ተብሎ ከስልጣኑ ተባሯል።ኣዲስ ስልጣን ይሾማል ተብሎ ይጠበቃል ትልቁ ሌባ ሕወሓት እያለ ትንንሾቹ ከስልጣን ይባረራሉ ባለፈው ሳምንት መኩሪያ ሃይሌ ከሚኒስትርነት ወደ ኣማካሪነት መዛወሩ ይታወሳል ኣንድ የፌስ ቡክ ጦማሪ ይህን ከትቧል።

Image may contain: 2 people , text and closeup
ኢትዮጵያውያን የሚፈልጉት ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ እንጂ የሚኒስትሮች ተባሮ መሾም ኣይደለም።
#Ethiopia #EPRDF #Change #Ethiopiaprotests #Freedom #NOTPLF
Minilik Salsawi – mereja.com ባለፈው መኩሪያ ሃይሌ ተባረረ ሳይሆን ተሾመ ኣሁን ደግሞ መሃይሙ ሽፈራው ሽጉጤ ከሚኒስትርነት ተባሮ ተሾመ ። ወያኔ ድሮ መተካካት የሚለው ኣሁን ኣንስቶ ማስቀመጥ ስራዬ ብሎታል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚፈልገው ስር ነቀል የስርዓት ለውጥ እንጂ የሚኒስትሮች ተባሮ መሾም ኣይደለም።===ሰማቹኝ====መኩሪያ ሃይሌ ሲባረር ወገኖቻችንን ኣናፈናቅል ስላለ ወያኔ ጥርስ ነክሶበት ነው የሚል ታፔላ ተለጠፈለት ሽፈራው ሽጉጠ ደሞ ሲባረር የኦሮሞ ተቃውሞን ደግፎ ፈተናው እንዲሰረቅ ተባብሮ ነው የሚል ታፔላ ተለጥፎለት የሕዝብ ፍቅር እንዲያገኙ ፕሮፓጋንዳ ይሰራላቸዋል።ወያኔ ውሸታም ነች ድብን ያለች ውሸታም ወያኔን ማመን ቀብሮ ነው ተግባባን ስለዚህ የምንፈልገው ኣዲስ ስርዓት እንጂ ኣዲስ ሚኒስቴር ስላልሆነ ሕወሓት በኣስቸኳይ ስልጣን ትልቀቅ ኣራት ነጥብ #ምንሊክሳልሳዊ



No comments:

Post a Comment