Saturday, September 17, 2016

በዐማራ ሕዝብ የተጠራ የሥራ ማቆም አድማ የለም!



በዐማራ ሕዝብ የተጠራ የሥራ ማቆም አድማ የለም!
ከመስከረም 9 እስከ 14 ቀን 2009 ዓ.ም በሕዝባዊ እምቢተኛነት ኮሚቴ የቤት ውስጥ የሥራ ማቆም አድማ በባሕር ዳር እና በጎንደር ተጠርቷል እየተባለ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚሰራጨው ወሬ ከዕውነት የራቀ ምናልባትም ወያኔዎች ወጣቱን በየቤቱ ለማፈስ የዘየዱት ሊሆን እንደሚችል በባሕር ዳርና በጎንደር ዛሬ ያነጋገርናቸው ሰዎች ገልጸዋል።
በዚህ ሰዐት የቤት ውስጥ አድማ መጥራት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ያመዝናል። ትግሉ ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት በዚህ ሰዐት የቤት ውስጥ አድማ መጥራት ትግሉን ወደ ኋላ የሚጎትት ይሆናል።
ይህ ጥሪ የዐማራ ሕዝብ የማያውቀው ሲሆን ወያኔዎች በመከላከያ ሠራዊት፣ በብሔራዊ ደኅንነትና በፌደራ ፖሊስ የሚመራ ወጣቶን ማደን በጀመረበት በዚህ ጊዜ የቤት ውስጥ አድማ ተጠርቷል መባሉ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ ተንኮል ወይም የኦፕሬሽኑ አካል ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል።

No comments:

Post a Comment