Friday, September 30, 2016

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ስብሰባ በከፍተኛ የአመፅ ስሜት ተበተነ፡፡



Image result for gondar university



የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ስብሰባ በከፍተኛ የአመፅ ስሜት ተበተነ፡፡
ከዚህ በፊት እንደሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ሳይካሄድ የቆየዉ እና በዛሬዉ እለት በወያኔ ቡችላ በሆነዉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቦርድ ስብሳቢ በሆነዉ በ ደ/ር ሽንታየሁ ወልደ ሚካኤል የተጀመረዉ እና በሁለት ታላላቅ አዳራሽ ከ2ሺህ በላይ የሚሆነዉ የዩኒቨርሲቲዉ ሰራተኛ የቀረበለትን ሻይ እና መስተንግዶ 95 በመቶ የሚሆነዉ የወንድሜ ደም እና ስጋ ይሁንብኝ ብሎ ምንም ያልቀመሰ ሲሆን በአንፃሩ እጅግ ጥቂት የሆኑ ባንዳዎች እና የህዋት ሆዳም አባላት ሲጠቀሙ ታይተዋል፡፡
በመጨረሻም ምንም ነገር ለእናንተ አፋችን አንከፍትም ብሎ ከቆየ በኋላ ሲጨንቃቸዉ የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ምክትል ዲን የሆነዉ እና ያለብቃቱ በወያኔነቱ ስንት ፕሮፌሰሮች እና ዶክተሮች ባሉበት ዩኒቨርሲቲ ምክትል ዲን እንዲሆን የተደረገዉ ለመናገር ሲዉተፈተፍ ሁሉም በአንድ ላይ አንተ ባንዳ እረፍ ወንድሞቻችን እየተሰቃዩ ባለበት ወቅት አትናገርም በማለት በጩኸት ዝም እንዲል ያደረገዉ ሲሆን አንድ የመረረዉ መምህርም ወያኔን እስከመጨረሻዉ ተናግሮ ከተጨበጨበ በኋላ ሰብሳቢዎቹ ሲጨንቃቸዉ ለመበተን ተገደዋል፡፡

source mereja..com

አቶ እንደሻው እምሻውና ግብረ አበሮቻቸው የሰማያዊ ፓርቲ ንብቶችንና ሰነዶችን በመዝረፍ ተሰውረዋል፡፡



አቶ እንደሻው እምሻውና ግብረ አበሮቻቸው የሰማያዊ ፓርቲ ንብቶችንና ሰነዶችን በመዝረፍ ተሰውረዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የፅ/ቤትና አስተዳደር ኃላፊነትን በሕገወጥነት ይዘው የቆዩት አቶ እንደሻው እምሻው ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ጊዚያት የፓርቲውን ንብረት በድብቅ እያወጡ መሆኑ መረጃ የደረሳቸው የፓርቲው ሊቀመንበር ጊዚያዊ የንብረት አጣሪና ተረካቢ ኮሚቴ በማቋቋም የነገሩን እውነትነት እንዲያረጋግጡና ንብረቶቹና ሰነዶቹ ካሉም በቃለ ጉባኤ መዝግበው እንዲረከቡ አዘዋል፡፡ ኃላፊነት የተሰጣቸው አባላት 1ኛ. አቶ እስክንድር ጥላሁን 2ኛ. አቶ ይድነቃቸው አዲስ 3ኛ. አቶ ማቲያስ መኩሪያ 4ኛ. አቶ ቴዎድሮስ አሰፋ በዛሬው ዕለት መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም በፓርቲው ቢሮ በመገኘት ንብረቶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚፈልጉ መሆኑን በመግለፅ አቶ እንደሻው እምሻውን እንዲያሳዩአቸው ቢጠይቁም ወደ ፓርቲው ፅ/ቤት አልመጣም በማለት ፈፅሞ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
አቶ እንደሻው እምሻው በቅርብ ቀናት ወደ ፓርቲው ፅ/ቤት መጥተው የማያውቁ መሆኑና የፓርቲውን ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታ ለማሳየት ፈቃደኛ አለመሆናቸው የኮሚቴ አባላቱን ጥርጣሬ በማሳደጉ ዋና ዋና ሰነዶችና ንብረቶች የሚገኝበት የፓርቲው የፅ/ቤትና አስተዳደር ኃላፊ ቢሮን ከፍተው ባዩበት ወቅት ሰነዶችና ንብረቶች አለመኖራቸውን አረጋግጠው በምስል ቀርፀውና በቃለ ጉባኤ መዝግበው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ይህ ወንጀል መጣራትና በሕግም መጠየቅ ስለሚገባው ለየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ መረጃው ተልኮ ተመዝግቧል፡፡ በነገውም ዕለት በጣቢያው በመገኘት ክስ እንዲመሰረት ፓርቲው የሚጠይቅ መሆኑን ኢንጅነር ይልቃል አስረድተዋል፡፡
አቶ እንደሻው እምሻው የፓርቲውን ማሕተም ከፓርቲው ፅ/ቤት አውጥተው በመውሰድ በግል ቤታቸው ያስቀመጡት መሆኑ በመታወቁ ከፓርቲው የተለየ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በዚህ የፓርቲው ማህተም ተደርጎባቸው የሚወጡ ማንኛውም ሰነዶች ፓርቲውን የማይወክሉ መሆኑንና በፓርቲው ማህተም ሰነዶችን የሚያሰራጩ አካለት በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

Wednesday, September 28, 2016

የህወሃትን የ minority ቁማር ጫወታ ይጠንቀቁ!! ጀዋር መሀመድ

  


የህወሃትን የ minority  ቁማር ጫወታ ይጠንቀቁ!! ጀዋር መሀመድ
*********
በቅርቡ ብዙዎቻቹ እንደተመለከታቹት፣ ህወሃት ሶማሊዎች ኦነግን ወይም ግንቦት ሰባትን በመቃወም ወጡ የሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው። መታወቅ ያለበት እውነት እንዲህ ዓይነቱን የህወሃት ድራማ እየተጫወቱ ያሉት ክልሉን አስተዳድራለው የሚለው አሻንጉሊት ፓርቲ አባላት ብቻም ሳይሆኑ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከሶማሊ ላንድ እንዲሁም ከኬኒያ የመጡ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች መሆናቸውን ነው። እብደት፣ እንዝላልነትና ስርዓት አልበኝነት የተጠናወተው የክልሉ የህወሃት ቅጥረኛ ፕሬዚደንት አብሲ ኢሌ፣ የቡና ቤት ሰራተኞች ሳይቀር በማስገደድ ሰልፍ አስወጥቷል ዛሬ። የህወሃት መንግስት ይሄን ለምን አደረገ? በመጀመሪያ ይሄ የሚያሳየው ህወሃት በኦሮሚያና በኣማራ ክልሎች ባበጃቸው ታዛዥና አሻንጉሊት የነበሩ ፓርቲዎችም ጭምር ሳይቀር መተፋቱንና ተስፋ መቁረጡን ነው። በነዚህ ሁለት ትልልቅ ክልሎች (ኦሮሚያና አማራ) ስርዓቱ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራም አንድም ወደ ተቃውሞ ይቀየራሉ በሚል ስጋት ሰርዟቸዋል ወይም ደግሞ ማንም ሰው ባለመገኘቱ የድጋፍ ሰልፎቹ ከሽፈዋል።
ጉዳዩ ግን ከዚህም በላይ ክፉ (sinister) እሳቤ ያለበት ነው። ጉዳዩ ህወሃቶች የሞት ሽረት ትግል (existential fight) የሚያደርጉበት የኣናሳዎች ፖለቲካዊ ቁማር ጫወታ አካል ነው። የዚህ ዓይነቱን ቆሻሻ ቁማር ካርድ ከሁለት ሳምንታት በፊት ስዩም መስፍንና አባይ ጸሃዬ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ መዘውት ነበር። ይሄን ለማድረግ ሁለት ተልዕኮ ነበራቸው፥
የመጀመሪያው፣ ካለምዓቀፉ ዳተኛ ማህበረሰብ (liberal international community) ‘ትግሬዎች ላይ በሁለቱ ትልልቅ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች (ኦሮሞና አማራ) አጋርነት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው’ በሚል የድረሱልን ጥሪ ለማስተላለፍ ነው የተፈለገው። ወያኔዎች ላለምዓቀፍ ዲፕሎማቶች ‘ትግሬ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሃገሪቱ አናሳ ቡድኖችም ጭምር ለጥቃት እየጠጋለጡ ነው’ በሚል ከፍተኛ አቤቶታና ውትወታ እያቀረቡ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።
ሁለተኛው ምክኒያት ግን ህወሃት ከትግሉ ዘመንም አንስቶ ሲሰራበት የነበረውና የኦሮሞንና የኣማራን የተባበረ ጫና (concerted impact) ለመቋቋም ሌሎች የሃገሪቱን አናሳ ቡድኖች አደርጅቶና ዶሚኔት አድርጎ ማንቀሳቀስ የሚለው ሸፍጠኛ ፖሊሲው ነው። ይሄ ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ሲያራምዱት የነበረ ስትራቴጂ ነው። ትግራይን ከቤኒሻንጉልና በምዕራብ ታች ጋምቤላ ድረስ ወርዶ እንዲሁም በምስራቅ በኩል በኣፋርና ሶማሌ ላይ የሚያገናኘው ካርታ ተራ ስ ህተት ሳይሆነ ካ1970ቹ ጀምሮ ታቅዶ የተሰራበት ፕሮጀክት ነው። በትግራይ ልህቃን የኢኮኖሚ ስግብግብነት የተነሳ ባይሳካላቸውም፣ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ አናሳ ቡድኖችንም ከጎናቸው ለማሰለፍ ጥረው ነበር ህወሃቶች።
በእርግጥ ግን ህወሃት በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች አጋር ነውን? ስራው የሚያሳየው ግን እንዳልሆነ ነው። ምሳሌዎችን እንጥቀስ፥
-የህወሃት ሰራዊት በሶማሊ ክልል ዘር ማጥፋትን ጨምሮ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሟል። ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል ደግሞ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሰፊው የዘገቡት ሲሆን ያሁኑ የክልሉ ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ በቅጥረኛ ነፍሰገዳይነት እንደተባበረ እልፍ አእላፍ መረጃዎች አሉ።
-በ2003 በጋምቤላ ክልል በኣኙዋኮች ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያካሄደ ሲሆን፣ ይሄንኑ ዓይነት ጭፍጨፋ እስካሁንም ቀጥሎበታል።
-በ2002 ሎቄ ላይ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሲዳማዎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዷል።
-አሁን በዚህ ወቅት እንኳን የኮንሶ ህዝብ ራስን በራስ ለማስተዳደር ስለጠየቀ ብቻ መንደሮቹን በእሳት እያጋየ ነው የህወሃት ሰራዊት።
-ሙርሲዎችን በገፍ ገድሏል፣ የተቀሩትን ደግሞ እንደ ጥንት ዘመን ባሮች አጠላልፎ በማሰር የሰው ልጅ በዚህ ዘመን ሊያየው በማይገባ ሁናቴ አስሮ እያሰቃያቸው ነው።
-የስልጤና ጉራጌ ነጋዴዎችን ከንግድ ስርዓቱ በማስወጣት በትግሬዎች ተክቷል።
-የኣፋርን መሬት ትግሬዎች መቀራመት ብቻም ሳይሆን ሲፈልጉም የሱማሌ ኢሳዎችና ሌሎች እንዲቀራመቱት አድርገዋል።
-ወዘተርፈ……
በምቀጥሉት ሳምንታትና ወራት የኦሮሞና የኣማራ አክቲቪስቶችና የነጻነት ቀንዲሎች የተባበረ ክንዶቻቸውን ማሰረፍ ሲቀጥሉ፣ ህወሃት የኣናሳዎችን ቁማር ካርድ ይበልጥ እንደምትመዝ ይጠበቃል። የዚህ ዓይነቱ አስነዋሪ ቁማር ደግሞ በኢትዮጵያ ባሉት ሌሎች አናሳ በሄረሰቦች እንዲሁም በኦሮሞና በኣማራ መካከል ቅራኔና ቁርሾ ለመፍጠር ያለም ነው የሚሆነው። በዚሁ መሰረት ወያኔ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱትን እኩይ ተግባራት ለመፈጸም ይችላልና እንንጠቀቅ፥
-በዳያስፖራም ሆነ በተወሰኑ ያገር ውስጥ አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆኑ ኦሮሞንና አማራን ለማናደድ (offend) ያለሙ ሰልፎችን ሊያዘጋጅ ይችላል፤
-ተንኳሽና ቆስቋሽ ቃላትን በመጠቀም ፕሮፓጋንዳ የመንዛት ዘመቻው ሊጧጧፍ ይችላል፤
-በሶማሊዎችና በኣማራ እንዲሁም በኦሮሞ መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ግለሰባዊ ትንኮሳዎች እንዲሁም በተቋማት ላይ ሊደረግ የሚችል ጥቃት ሊኖር ይችላል፤
-በክልሎች የድንበር አካባቢዎች መፍጠር የጀመሩትን ግጭት ይቀጥላሉበታል። በኣማራና በቤኒሻንጉል እንዲሁም በኦሮሚያና በሶማሊ ክልሎች መካከል ህወሃት በቅርቡ የፈጠረችውን ግጭት ይበልጥ እንዲባባስ ልታደገው ትችላለች፤
እነዚ የህወሃት ሸፍጦች እንዲከሽፉ ተባብረን ካልሰራን፣ ኢትዮፕጵያ ውስጥ በሚገኙ ብሄሮች መካከል የማይሽር ጠባሳ ሊያሳርፉ ይችላሉ። ስለሆነም ይሄን ለመመከት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብናል፥
-የኦሮሞና የኣማራ ተወላጆች በዚህ ዓይነቱ የህወሃት ወጥመድ ውስጥ ላለመውደቅ፣ ከሶማሊ ክልል ካድሬዎችና የኣብዲ ኢሌ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች ጋር ውይይትም ሆነ ክርክር ወይም ማናቸውንም ዓይነት መሳፈጥ ማድረግ እንደማያስፈልግ መረዳት ያስፈልጋል፤
-ይሄንን ዓይነቱን ጉዳይ ለኣክቲቪስቶችና ለፖለቲካ መሪዎች ተውላቸው። እነሱ እንዳስፈላጊነቱ ያሳጧቸዋል (debunk)፤
-የስርዓቱ ቅጥረኞች እንደ ኦሮሞ፣ አማራ ወይም ሶማሊ በመምሰል ግጭት ለመጫር እንደሚተጉም ማስተዋል ያስፈልጋል።
-ወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቅጥረኞችን ልታሰማራ ስለምትችል የታወቁ አክቲቪስቶች እንዲሁም የፖለቲካ መሪዎች በያሉበት መጠንቀቅ አለባቸው። በኦሮሞም ሆነ በኣማራ ኮሞኒቲዎች ውስጥ ያሉ የስርዓቱ ቅጥረኞች ሶማሊዎችን እንዲያጠቁና ግጭት እንዲፈጥሩ ሙከራዎች ሊደረጉ ይችላሉ። የኦሮምና የኣማራ ሰዎች ላይም ጥቃት ሊቃጣ ይቻላል። ምንም ሆነ ምን ግን ምላሹ የጋርዮሽ (communal) ሆኖ በሶማሊ ወይም በሌላው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ላይ ያነጣጠረ መሆን አይገባውም። አካሄዳችን የዚህ ዓይነቱን የወንጀል ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች ነጥሎ በማውጣት ለህግና ፍትህ ማቅረብ መሆን ይኖርበታል።
የዚህ ዓይነቱ ያረጀና ያፈጀ የወያኔ ክፉ የከፋፍለህ ግዛ አባዜ የስርዓቱን እድሜ ሊያራዝመው አይችላም።

ጸረ ነፍጠኛ ግንባር?! (የነስብሐት ነጋ የጥፋት ድግስ!)



ጸረ ነፍጠኛ ግንባር?!
(የነስብሐት ነጋ የጥፋት ድግስ!) Image result for sebhat nega



አንድ የማከብራቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ፖለቲከኛ ወያኔ በአማራ ሕዝብ እምቢተኝነትና አይበገሬነት ስለተርበተበተ፣ ይህን ሕዝብ ከሌሎች የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለመነጠል መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ ነው በማለት በቅርቡ የታዘቡትን አጫውተውኛል፡፡ እኚህ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ኅብረትና ለአገራችን አንድነት ፍጹም ቀናኢ የሆኑ የፖለቲካ ሰው እንደገለጹልኝ፣ ሰው በላው ስብሐት ነጋና ሌሎች የወያኔ መሪዎች የተለያዩ የደቡብ ኢትዮጵያና የኦሮሞ ፖለቲከኞችን እየቀረቡ፣ ከአማራ ውጪ ያሉት ሕዝቦች ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ካልፈጠሩና የአማራውን እንቅስቃሴ ካልመከቱት በስተቀር የድሮው ሥርዓት ተመልሶ አስፈሪ መልክ ይዞ እየመጣ ነው በማለት እየቀሰቀሱ ነው፡፡ እነስብሐት ነጋ ጸረ ነፍጠኛ ሲሉ ጸረ አማራ ማለታቸው መሆኑን ማንም ይስተዋል ብለን አናምንም፡፡ ስለሆነም እነዚህ ነብሰ ገዳዮች ጸረ አማራ ግንባር ለመፍጠር ላይ ታች እያሉ ነው!!!
እንደሚታወሰው ወያኔ በምርጫ 97 አስደንጋጭ ሽንፈት በገጠመው ማግስት፣ ትምክህተኛው አንሰራርቶ ተነስቷል፤ ይህ ኃይል ሥልጣን ከያዘ አገራችን ወደትርምስ ትገባለች፤ በሕዝቦች መካከል የለየለት መተራረድ ይከሰታል ወዘተ. በማለት ከአማራ ውጪ ያሉት የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ በተለይ ደግሞ ወያኔና የኦሮሞ ድርጅቶች ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ሊፈጥሩ እንደሚገባ ለነዶ/ር መረራ ጉዲና ጥሪ ቀርቦላቸው ነበር፡፡ መረራ በመጽሐፋቸው ላይ እንደገለጹት በቅርቡ የሞተው ፕሮፌሰር ዓለም ሀብቱ (የታላቋ ትግራይ ፕሮጀክት አራማጅ) እና ዘላለሙን የአማራ ሕዝብ ጠላት ሆኖ የኖረው አብዱል መሐመድ (ወርጂ) ወያኔንና እነዶ/ር መረራን ለማግባባት ሞክረው ነበር፡፡ እነመለስ በተለመደ ከሃዲነታቸው ‹‹ጸረ ነፍጠኛ ግንባር ፈጥረን፣ የተደቀነብንን ፈተና ካስወገድን በኋላ፣ እኛ ለአምስት ዓመታት ብቻ መርተን ለእናንተ እንለቅላችኋለን›› ወዘተ. የሚል ከንቱ ሙከራ ማድረጋቸውንና እነዶ/ር መረራ ይህንን የነመለስ መሰሪ አካሔድ ተረድተው ጥሪውን ውድቅ ማድረጋቸውን ሰምተናል፡፡ ዝርዝሩ ብዙ ነው፡፡
ዋናው ነገር፣ የወያኔ መሪዎች በሥልጣን ላይ ለመቆየት የማያደርጉት ምንም ዓይነት ነገር እንደሌለ ግልጽ ነው፡፡ እነዚህ ጸረ ሕዝቦች፣ ወያኔን በሥልጣን ላይ እስካቆየ ድረስ እንኳን ከኢትዮጵያውያን ከባዕዳን ጋርም መተባበራቸው አይቀርም፡፡ ባለፉት 25 የግፍ ዓመታት በግልጽ እንደታየው፣ በሥልጣን ላይ ለመቆየት ሲሉ ሕዝብ ይጨፈጭፋሉ፤ በገፍ እያሰሩ ዘግናኝ ቶርቸር ይፈጽማሉ፤ እጅግ ርካሽ በሆነ መልኩ ሴት ፖለቲከኞች እንዳይኖሩ፣ ተስፋ የሚጣልባቸውን ሴት ፖለቲከኞችና የሰብአዊ መብት ተከራካሪዎች አስረው ይጫወቱባቸዋል፤ ወንዶች ብልታቸውን እየተቀጠቀጡ ከሰው ተራ እንዲወጡ ይደረጋል፤ እሳት እየጫሩ አንዱን ሕዝብ ከሌላው ጋር ያጋጩና ገላጋይና ዳኛ መስለው ይገባሉ፤ አሁን በቅርቡ በአማራ  መተማ  ውስጥ በግልጽ እንደታየው ጽረ ሕዝብ በሆነው የደኅንነት ተቋማቸው አቀነባባሪነት ትግሬዎችን እስከነጓዛቸው ጭነው አስወጥተውና የቀሩ አማሮችን አርደው ሲያበቁ፣ ትግሬ ተባረረ፣ በትግሬ ላይ ያነጣጠረ የዘር ጥቃት ተፈጸመ ብለው የትግራይ ሕዝብና ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ከጎናቸው እንዲሰለፍ ለማድረግ የፋሽስት ተግባር ይፈጽማሉ፤ ሕዝብ በሚሰበሰብባቸው የገበያ አዳራሾችና በሕዝብ ትራንስፖርት ላይ ቦንብ ጥለው በሌሎች ላይ ያሳብባሉ፤ ግለሰቦችን በገቡበት ሁሉ እየገቡ እየተከታተሉ ያሸማቅቃሉ፤ ያስፈራራሉ፤ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከፍለው የሎቢ ቡድን ቀጥረው የዲፕሎማሲ ሥራ ይሠራሉ፤ ለዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ባልደረቦች ገንዘብ ይከፍላሉ ወዘተ. ወዘተ.፡፡ እኩይ ተግባራቸው ማለቂያ የለውም፡፡ ተግባራቸው ሁሉ አገር ከሚመራ ድርጅት ሳይሆን ከማፊያዎች የሚጠበቅ የተራ ዱርዬና የማጅራት መቺ ተግባር ነው!! እንብላ ብቻ ሳይሆን ስንበላ አትዩን፣ ከዚያም አልፈው ሌላው አይብላ የሚሉ፣ ያዩትን ሁሉ በብቸኝነት ለማግበስበስ የሚጣደፉ ስግብግቦችና ጸረ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ደግነቱ ሁሉን እንብላ፣ ያየነው ሁሉ አይቅረን ሲሉ የያዙትንም የሚተፉበት ጊዜ መጥቶባቸዋል!!!
እንግዲህ፣ የአማራ ሕዝብ እየተደገሰለት ያለውን የወያኔ መሪዎች የጥፋት ድግስ ነቅቶ መጠበቅ ይኖርበታል፡፡ ለሁለተኛ ጊዜ እየተሞከረ ያለው ጸረ አማራ ግንባር ምን ውጤት እንደሚያስከትል እና ሕዝባችን ከሚደገስለት የሞት ወጥመድ ራሱን ለማዳን ምን ማድረግ እንደሚገባው መወያየት ይኖርብናል፡፡ በእርግጥ እኚህ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ከ40 ዓመታት በላይ የቆዩ ምሁርና ፖለቲከኛ እንደነገሩኝ ከሆነ፣ ሁሉም ድርጅቶች ለዚህ የወያኔ የጸረ አማራ ግንባር ጥሪ ያላቸው ምላሽ አሉታዊ ነው፡፡ ዛሬ ማንም የፖለቲካ ሀ ሁ የሚያውቅ ሰውና የድርጅት መሪ ወያኔ እንዳበቃለት ይገነዘባልና የዚህ የወያኔ የጥፋት ግንባር ተባባሪ የሚሆን አካል ይገኛል ማለት ያስቸግራል፡፡ ስለሆነም ይህ በአማራ ሕዝብ ላይ የተደገሰ የጥፋት ግንባር ሊፈጠር የሚችልበት ዕድል የመነመነ ነው፡፡ ሆኖም ዕድሉ የመነመነ ቢሆንም ዜሮ ነው ማለት ግን አይቻልም፡፡ ሁልጊዜም ግንባር ቀደም ጠላታችን የሆነው ወያኔ የሚደግስልንን የሞት ወጥመድ ነቅተን መከታተልና ማክሸፍ ይኖርብናል፡፡ የወያኔና የእኛ ግንኙነት የአጥፊና ጠፊ ግንኙነት ነውና ወያኔ እንዲጠፋ ያለእረፍት መሥራት፣ ያለእረፍት መታገልም ግዴታችን ነው፡፡ ወያኔ እስካለ ድረስ እኛ ሰላም አናገኝም፡፡ ለእኛ፣ ሰላም ማለት ከወያኔ ነጻ መሆን ማለት ነው!!!!
ወዳጄ የነገሩኝን ነጥብ ጠቅሼ ጽሑፌን ልቋጭ፡፡ ምሁሩና ፖለቲከኛው አዛውንት፣ ‹‹በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ነፍጠኛም ትምክህተኛም ጠባብም ራሱ ወያኔ ነው፡፡ ስለሆነም የወያኔ መሪዎች የሚሉት ጸረ ነፍጠኛም በለው ጸረ ትምክህተኛ ወይም ጸረ ጠባብ ግንባር ጸረ ወያኔ ግንባር በመሆኑ፣ የዚህ ዓይነት ግንባር ከተመሠረተ ከመሥራች አባላት ውስጥ ወያኔ መኖር የለበትም፡፡ ግንባሩ ጸረ ወያኔ ነውና፡፡ ይህን ሐቅ ከያዝን በኋላ፣ ጸረ ነፍጠኛም በለው ጸረ ትምክህተኛ ወይም ጸረ ጠባብ ግንባር መመሥረት አለበት በሚለው ነጥብ ላይ መስማማት ይቻላል፤ እየተመሠረተም ነው›› በማለት አስደምመውኛል፡፡ የነስብሐት ነጋ ቀን መጨለሙን አያመለክትም ትላላችሁ? ለእኔ እንደዚያ ነው የሚታየኝ!

Tuesday, September 27, 2016

በዘ-ህወሀት የውሸት ምድር የማወንበጃ መረጃ ዘመቻ፡ ቀጣፊው በኢትዮጵያ ዉሸትን እዉነት ነው እያለ ሲሰብክ?



ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ
የጸሐፊው ማስታዋሻ፡ በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ እየተጠናከረ የመጣውን የዘ-ህወሀት (ዘራፊ ህወሀት) የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ለማጋለጥ ሲባል በተከታታይ እያቀረብኩ ካለሁት ትችት ይህ ሶስተኛው ክፍል ነው፡፡ እ.ኤ.አ መስከረም 5/2016 አቅርቤው በነበረው ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ ተንሰራፍቶ የሚገኘውን የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እየተስፋፋ እና እየተጠናከረ የመጣውን ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጽ አሳንሶ እና አኮስሶ ለማቅረብ በሚል እኩይ ምግባር ዘ-ህወሀት በቅርብ ጊዜ ውስጥ የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻውን ይጀምራል በማለት አሳስቤ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ መስከረም 18/2016 አቅርቤው በነበረው ሁለተኛው ትችቴ ዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ አስፈሪ እና የማይቀር የዘር ማጥፋት ዘመቻ እውን ይሆናል በማለት አቅርቦት የነበረውን የቅጥፈት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ መሰሪ ፕሮፓጋንዳ ሀሰት እና ተራ ቅጥፈት መሆኑን አጋልጫለሁ፡፡
በመስከረም መጀመሪያዎቹ አካባቢ አቅርቤው የነበረው የዘ-ህወሀት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ በአሁኑ ጊዜ ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ እና በተሟላ ቁመና ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ትችቴ ደግሞ የዘ-ህወሀት ዋና የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ/ዋና ኃላፊ (መማቆ) የሆነውን የደብረጽዮን ገብረሚካኤልን የተዛባ እና መሳቂያ የሆነ የቅጥፈት ፕሮፓጋንዳ በማጋለጥ አቀርባለሁ፡፡ “እራሱን በራሱ ዉሸት ካሳመነ ሰው ጋር በፍጹም አትከራከር“ የሚለውን ጥንታዊ አባባል በሚገባ እገነዘባለሁ፡፡ ጭራ የቀራቸዉን ቀጣፊ ውሸታሞች በፍርድ ቤት በፍትሕ አደባባይ በመስቀለኛ ጥያቄ ማፋጠጡን የምመርጥ ቢሆንም ቅሉ ያ የፍትሕ አደባባይ የሚለው ነገር በሀገሪቱ ውስጥ ከቶውንም የሌለ እና ዳብዛው የጠፋ በመሆኑ ምክንያት በዓለም ህዝብ ህሊና ዳኝነት ክርክሬን ቀጥላለሁ።
በእኔ ዘመን ሳሙና የሆኑ አእምሮአቸው በዉሸት የተበከለ ቀጣፊዎችን  አጋጥመዉኛል፡፡ እናም አንድ ቁልጭ ያለ እና በግልጽ የማስታውሰው ነገር ቢኖር እነዚህ አእምሮአቸው የታመመ ቀጣፊዎች እራሳቸዉን  እንጂ ሌላ ሰው ስያታለሉ አላየሁም፡፡ ይልቁንም እነርሱ የቅጥፈት ባለሞያዎች የሆኑት እራሳቸውን በማታለል ነው፡፡ ሆኖም ግን ውሸት በሚነሳበት ጊዜ የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ (መማቆ) የሆነው ደብረጽዮን እና ሌሎች የዘ-ህወሀት ወሮበሎች የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ፡፡ እነዚህ ፍጡሮች የውሸት፣ የቅጥፈት እና የተራ አሀዛዊ ቅጥፈት ቀፍቃፊ ጌቶቸ ናቸው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ለበርካታ ሳምንታት የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ በመክፈት ማወናበድን በመቀጠል ረገድ 3ኛው ትልቅ ጠብመንጃ ነው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ የዘ-ህወሀትን የጭቆና አገዛዝ በመቃወም እንደ ሰደድ እሳት ተቀጣጥሎ በሚገኘው ሕዝባዊ አመጽ እና መገዳደር ከጥቂት ሳምንታት በፊት አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን ከዘ-ህወሀት የአውሬዎች ዋሻ መካከል በድንገት ብቅ ብለው በመውጣት በሕዝብ ላይ የዘር ፍጅት ያወጁ እና የጮኹ ተኩላዎች ናቸው፡፡
የዘ-ህወሀት የመረጃ ማወናበጃ ጨዋታ ግልጽ ይመስላል፡፡ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የቁማርና ካራምቦላ (እያጋጩ  ማለት) ጨዋታ በመጫወት ላይ ይገኛሉ፡፡
አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን ፍጹም በሆነ መልኩ ምክንያታዊ ያልሆነ እና እርባናቢስ የሆነ የዘር ማጥፋት ወንጀል ይፈጸማል በማለት ፍርሃት ለመፍጠር ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛሉ፡፡ “ሰማይ ይወድቃል” እያለ በሕዝብ ላይ ምዕናባዊ ፍርሀት በመልቀቅ እንደሚባለው በተመሳሳይ መልኩ አባይ ጸሀይ እና ስዩም መስፍን በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ማጥፋት ድርጊት ይፈጸማል በማለት ሕዝቡን በማስፈራራት እና በማደናገር ላይ ይገኛሉ፡፡
እንዲያው ለመሆኑ ይህንን አዲስ ነገር አድርገው እንደበቀቀን እየደጋገሙ የሚለፈልፉት ባለፉት 25 ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ምን ሲያደርጉ ነው የቆዩት? በአማራው፣ በኦሮሞው፣ በጋምቤላው፣ በሶማሊው፣ በሲዳማው፣ በአፋሩ፣ በቤንሻንጉሉ፣ ወዘተ ሲፈጽሙት የቆዩትን የዘር ማጥፋት ወንጀል እስቲ ዘወር ብለው ይመልከቱት፣ ዘወር ብሎ የሚያይ አንገት ካላቸው፡፡ ምኑ ነው አሁን አዲስ የሚሆነው፡፡ ይልቁንስ አሁን የእነርሱ ማብቂያ እና መውደሚያ መሆኑን ስለተገነዘቡት ይሆናል የአቦን ቅጠል እንደቀመሰች ፍየል በመለፍለፍ ላይ የሚገኙት፡፡
ነው? ወይስ ያብየን ለምዬ?
መማቆ ደብረጽዮን የዘር ማጥፋት ወንጀል አይኖርም ይላል፡፡ በእርግጥ የራሱ ቃላት እንዲህ የሚሉ ሆነው ይገኛሉ፣ “በኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝብ ለሕዝብ ግጭት (የዘር ማጥፋት ወንጀል) ሊኖር አይችልም፡፡ በጥቂት ወንጀለኞች እና ችግር ፈጣሪዎች ሊቀሰቀሱ የሚችሉ የተነጣጠሉ ሁከቶች እና ግጭቶች (አመጾች ሳይሆኑ) ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እነዘህ ደግሞ የዘር ማጥፋት ወንጀሎች አይደሉም“ በማለት ሳያውቀው አምኗል፡፡
እንግዲህ ወገኖቼ ከነዚህ ባለመንታ ምላስ እባቦች የትኛውን እንመን? አባይ ጸሀይን፣ ስዩም መስፍንን ወይስ ደግሞ ደብረጽዮን ገብረሚካኤልን?
መማቆ ደብረጽዮን በመጠኑም ቢሆን ተቀባይነት ያለው ለማስመሰል እና እራሱን ከሌሎቹ አስበልጦ እንዲታይ የማድረግ ቁመናን ለመላበስ ሙከራ አድርጓል፡፡ በስተቀኙ በኩል የዘ-ህወሀትን ባለኮከብ እርማ ሰንደቅ ዓላማ በማንጠልጠል የዘ-ህወሀት መልካም አድራጊ መስሎ መቅረብ ሞክሯል። ግን ያለው አስተሳሰብና ያደርገው ድርጊቶች ለኢትዮጵያ ህዝብ  አርሱም ዘ-ህወሀትም  ደንታ እንደሌላቸው አረጋግጧል። መማቆ ደብረጽዮን  የኢትዮጵያ ህዝቦች በዓለም ላይ ታይተው የማያውቁትን ነገሮች ቀይ እና ሰማያዊ ላም እንዲሁም ቀይ ዝሆን አየን እያሉ ይናገራሉ፡፡ ዝም ብለው ይቀባጥራሉ እናም እንዲሁ በፈጠራ ወሬዎች ጭንቅላታቸውን ሞልተው ይገኛሉ ነበር ያለው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ሁሉም ነገር አንዳለ ሳይሆን አንደተመለከቱቱ ነው ይላል። ሲያስረዳም ፣ “አንድ ሰው የጠራውን ቀን ጨለማ ነው  ደጋግሞ ካለ ሕዝቡ ያንን የጠራ ቀን ጨለማ ነው የሚል ሀሳብን ይይዛል ማለት ነው“ ነበር ያለው፡፡
ከዚህ አንጻር በዘፈቀደ አመንኩ፡፡ እጄን ሰጠሁ!
ስለጨለማ እራሱ የጨለማው  ልዑል ከሆነው አስመሳይ ፍጡር በላይ ማን ሊያውቅ ይችላል?
ስለጨለማ የጨለማው ጌታ ከሆነው ከንቱ ፍጡር በላይ ማን የበለጠ ሊያውቅ ይችላል?
ስለጭለማ መማቆ ደብረጽዮንን የመሞገት ችሎታ የለኝም።
ስለጨለማ በብርሀኑ በኩል ያሉት ሰዎች ሳይሆኑ የጨለማው ጌታ የበለጠ ያውቃል።
በሚያስገርም ሁኔታ መማቆ ደብረጽዮን የእርሱን የጨለማ ተመሳስሎ የተዋሰው እንዲህ ከሚለው እና የናዚ ጀርመን የፕሮፓጋንዳ ሚኒስትር ከነበረው ከጆሴፍ ጎቤልስ ነው፣ “ታላቅ ውሸት ከዋሸህ እና ይህንንም ውሸት ደግመህ እና ደጋግመህ ተግባራዊ ካደረግኸው በመጨረሻ ሕዝብ እውነት ብሎ ያምናል፡፡
ሆኖም ግን መማቆ ደብረጽዮን እንዲህ የሚሉትን የጎቤልስን አብረው የነበሩትን ቃላት ሆን ብሎ ዘሏቸዋል፡
“መንግስት ሕዝቡን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና/ወይም ወታደራዊ የሆኑ ውሸቶች ከሚፈጥሯቸው እንቅስቃሴዎች ለመከላከል ሲል ውሸቶች ለእንደዚህ ላለ ጊዜ ብቻ ሊቆዩ ይችላሉ፡፡ በዚህም መሰረት እውነት የሚሞተው የውሸት ጠላት በመሆኑ እና የዚህም ተቀጽላ እውነት የመንግስት ታላቁ ጠላት በመሆኑ መንግስት ሁሉንም ኃይሉን ሰላማዊ ሰዎችን ለመጨቆኛነት የሚጠቀምበት ዋናው አስፈላጊው መሳርያ ነገር ነው፡፡“
እውነት የመንግስት የመረጃ ማወናበጃ ዋና ጠላት ነው፡፡
የመማቆ ደብረጽዮን ቃለመጠይቅ፣
Debretsion Gebremichael
ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
በቪዲዮ በተቀረጸው ቃለመጠይቅ መማቆ ደብረጽዮን በበርካታ ጉዳዮች ላይ በተደጋጋሚ ሲደነፋ ( ሲንተባተብ አላልኩም) እና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ስለዘ-ህወሀት እውነተኛ ምንነት መግለጽ የማይችሉ ደንቆሮዎች እና ደደቦች መሆናቸውን ተናግሯል፡፡ በቁስል ላይ እንጨት እንዲሉ በውሸት ላይ ያሉ ሕዝቦች በማለት እራሱን ከፍ ከፍ እያደረገ መሰረተቢስ የሆነውን የማታለል ንገግር አድርግዋል ፈጽሟል፡፡ ለመማቆ ደብረጽዮን ኢትዮጵያ ሕዝቦች በምዕናባዊ ሀሳብ እና በእውነት መካከል ያለውን ልዩነት ለይተው የማያውቁ የዋሀን ናቸው፡፡ በእርሱ ድሁር አስተሳሰብ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሚያዩት ነገር በተጨባጭ የሚያዩት እና የሚመለከቱት ነገር አይደለም፡፡ ሆኖም ግን ምንም ዓይነት እውነታነት የሌለው በድድብና የተሞላ ምዕናባዊ ነገር ነው፡፡ እውነታውን እንዲያውቁት እንዲመለከቱት ተደጋጋሚ የሆነ ትምህርት ሊሰጣቸው ይገባል፡፡ ይህንን ትምህርት እንዲሰጥ እና ስራውን እንዲሰራ ለብዙሀን መገናኛ ጥሪ መቅረብ አለበት ነው ያለው መማቆው !
የመማቆ ደብረጽዮን ቃለመጠይቅ እንዲህ የሚሉ በርካታ የሆኑ የፕሮፓግንዳ እና የፖለቲካ ዓላማዎችን ለመጎናጸፍ በግልጽ የተዘየደ ዕቅድ ነው፡
1ኛ) በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ተቀጣጥሎ የሚገኘው መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞ በጎንደር ላይ ተወስኖ የሚገኝ ትንሽ ነገር ነው፡፡
2ኛ) በጎንደር ውስጥ የተፈጠረው ሁከት ጥቂት የውጭ ኃይሎች እና ወንጀለኞች ስራ ነው፡፡ በጎንደር ውስጥ ወይም ደግሞ በሌላ በማናቸውም ቦታ እና አካባቢ ውስጥ ምንም ዓይነት ሕዝባዊ አመጽ የለም፡፡
3ኛ) በጎንደር የተቀሰቀሰው ሁከት ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ባልተወጡ የስራ ኃላፊዎች እና  በአካባቢው አመራር ብቃትየለሽነት እና የአስተዳደር ጉድለት የተፈጠረ ነው፡፡ ስለዚህ እነዚህ ሰዎች ተወግደው በሌላ መተካት ይኖርባቸዋል፡፡
4ኛ) በኢትዮጵያ ሕዝቦች ፖለቲካ እና ማህበረሰብ ውስጥ የትግራይ የበላይነት የሚለው ነገር አውዳሚ የሆነ የሰዎች የተሳሳተ ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የትግራይ የበላይነት በልብወለድ ውስጥ ያለ በምዕናባዊ ሀሳብ የሚኖር እንጅ በነባራዊ እውነታ በተጨባጭ የሌለ ነገር ነው፡፡
5ኛ) የኢትዮጵያ ሕዝብ የትግራይ የበላይነት የሌለ መሆኑን እንዲያውቅ ትምህርት ያልተሰጠው በመሆኑ ከግንኙነት ውድቀት የመነጨ ነው፡፡ የእራሳቸው የግንዛቤ ምዕናባዊ እሳቤ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በብርሀን እና በጨለማ መካከል ያለውን ልዩነት መናገር የማይችሉ እንደዚህ ያለ የትግራይ የበላይነት የሚባል ነገር ያለ መሆኑን መናገር የማይችሉ እና ትምህርት የሚያስፈልጋቸው ደንቆሮዎች ናቸው፡፡
6ኛ) ትግራውያን በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ የጎሳ የበላይነት እየተገበሩ ላለመሆናቸው ሊያስገነዝብ የሚያስችል የመረጃ የማወናበጃ ዘመቻ ታላቅ የብዙሀን መገናኛ ፍላጎት አለ፡፡
7ኛ) የኢትዮጵያ ፖለቲካ ነባራዊ እውነታ የሚያሳየው ነገር ቢኖር እያንዳንዱ የጎሳ ቡድን በእራሱ ክልል (ባንቱስታን) የበላይ ነው፡፡
8ኛ) ለጎሳ ታላቅነት እና የበላይነት የጎሳ ፌዴራሊዝም የመጨረሻው ጠባቂ ኃይል ነው፡፡
9ኛ) ብቸኛው እውነታ የዘ-ህወሀት እውነታ ብቻ ሲሆን ሌላው ግን ተራ ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ስለኢትዮጵያ ሕዝቦች መልካም ነገር እና ጥቅም ተልዕኮው ተነግሮ ስለማያልቀው ስለዘ-ህወሀት የተሳሳተ ግንዛቤ አለው፡፡
10ኛ) የኢትዮጵያ ሕዝቦች ዘ-ህወሀት ደም የተጠማ ወንጀለኛ የወሮበሎች ስብስብ እንደሆነ አድርገው የሚነግሯቸውን የሚዋሹ ዓይኖቻቸውን እና ጆሮዎቻቸውን ማመን የሚያቆሙ ከሆነ የዘ-ህወሀትን ደግ፣ ጓዳዊ፣ የተረጋጋ፣ ለጋሽ፣ አፍቃሪ እና ሰብአዊ ፍጡርነት ይገነዘባሉ፡፡“
በሰጠው ቃለመጠይቅ መማቆ ደብረጽዮን በቅርቡ በጎንደር የተፈጠረውን ሁከት (ሕዝባዊ አመጽ) እና ትግራውያንን ማፈናቀል እየተባለ የቀረበውን ውንጀላ ጨምሮ የትግራይ የበላይነት የሚለው መሰረተቢስ ውንጀላ እንደሆነ እና የጎሳ ፌዴራሊዝም የኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ቀውሶች ሁሉ ፈዋሽ መድኃኒት አድርጎ በርካታ ጉዳዮችን እንደሚከተለው አቅርቧል፡
መማቆ ደብረጽዮን አንደተናገረው (ከእንግሊዘኛው አንደተተረጎመ)
“በጎንደር ስለተከሰተው “ግጭት”፣ “ሁከት” ሁኔታ፣
…እንደ ቁንጮ አመራር እኔ ብቻ ስለሁኔታው አውቃለሁ፡፡ የግጭቱን ዝርዝር ሁኔታ የሚያውቁ የተለያዩ አካላት ናቸው፡፡ ያንን ሁኔታ በቅርበት አልከታተልም…በሱዳን እና ከሱዳን በተመለሱት መካከል ግጭት እንዳለ አውቃለሁ፡፡
ይህንን እንዴት መመልከት እንዳለብን፡ በተለየ መልክ እንደተገለጸው ዋናው ነገር ይህ ሁኔታ የሕዝብ ለሕዝብ ጉዳይ (ግጭት) አይደለም፡፡ ከትግራይ ጥቂት የእኛ ሰዎች እና ከሌሎች ቦታዎች በጎንደር ውስጥ በተፈጠረው አመጽ እየተሰቃዩ እና ጉዳት እየደረሰባቸው ይገኛሉ፡፡ የተቀጣጠለውን እሳት (ግጭት) ለማስፋፋት የሚፈልጉ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ በጎንደር የሚኖሩ የአማራ ሕዝቦች ናቸው፡፡ ሌሎችን (አማራ ያልሆኑትን) እንደሚከላከሉላቸው እና ጉዳት እንደማይደርስባቸው እንገነዘባለን፡፡ የተፈጸሙ በርካታ ድርጊቶች (ወንጀሎች) አሉ፡፡ በጣም ጥቂት የሆኑ ሰዎች በጎንደር በሚኖሩ ትግራውያን ንብረቶች ላይ ጉዳት ለማድረስ ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም እነዚህ ድርጊቶች የአብዛኛው የጎንደር ሕዝብ ድርጊቶች አይደሉም፡፡ በየትኛውም ቦታ ትግራውያንን ለማጥቃት ተብሎ የሚደረግ እንቅስቃሴ የለም፡፡ ሆኖም ግን በትግራውያን ላይ ወንጀሎችን ለመፈጸም የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች እንዳሉ እናውቃለን፡፡ ጥቂት ግለሰቦች በትግራውያን ላይ የወንጀል ድርጊቶችን እንደፈጸሙ እናውቃለን፡፡ ይህ ሁኔታ የጥቂቶች ድርጊት እንደሆነ እናውቃለን፡፡ ከእራሳቸው ዓላማ ጋር የሚደረግ እንቅስቃሴ አለ፡፡ የፌዴራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ይህንን ሁኔታ በቅርብ በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡
ሆኖም ግን ይህ ጥያቄ መጠየቅ ያለበት ጥያቄ አይደለም፡፡ ከትንታኔው መገንዘብ እንደሚቻለው መፍትሄው በግጭቱ (መጋፈጥ) ላይ በማተኮር ብቻ ሊገኝ አይችልም፡፡ በአካባቢው አመራር፣ ለሕዝቦች መልካም አስተዳደር ማቅረብ ያልተቻለበትን፣ ለሚቀርቡት ጥያቄዎች ሁሉ በወቅቱ ምላሽ ያልተሰጠበትን፣ ችግሮች ያሉ መሆናቸውን ያለማስተዋል እና ሌሎችን እንደዚህ ያሉትን ሁኔታዎች ሰፋ ባለ መልኩ መመልከት አለብን፡፡ እናም በዚህ ጉዳይ ዙሪያ እንቅስቃሴዎች ይኖራሉ፡፡ ይህ በእራሱ ችግሮችን ፈጥሯል፣ እናም በዚህ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች የምንፈታ ከሆነ ሌሎችን ችግሮችም አብረን እንፈታለን፡፡ ሌሎች አስተዳደራዊ ችግሮችን፣ የልማት ጥያቄዎችን እንፈታለን ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የፖለቲካ ጥያቄዎችን ማንሸራሸር እና መፍታት እንችላለን፡፡ እኛ እንግዲህ የምንመለከተው በዚህ ዓይነት መንገድ ነው፡፡ 
በጎንደር የተከሰተው ግጭት አንድ ውሱን ጉዳይ ነው፡፡ ሁሉንም አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳየን አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በተለያዩ መድረኮች ላይ እየተካሄዱ ባሉት ውይይቶች ላይ በጣም አዝነዋል፡፡ ይህ ኢህአዴግ ያመጣው ነገር አይደለም፡፡ የጎንደር እና የትግራይ ሕዝብ ለበርካታ ጊዚያት አብረው ኖረዋል፡፡ በአንድ ላይ መኖር ብቻ አይደለም ሆኖም ግን እርስ በእርስ በመጋባት እንደ አንድ ቤተሰብ ሆነዋል… ሆኖም ግን ሕዝብ ለሕዝብ ግጭት (የጎሳ ግጭት) ለመፍጠር ዓላማ አድርገው የሚንቀሳቀሱ ጥቂት ሰዎች አሉ፡፡ ይህ ህገወጥ ተግባር ነው፡፡ ጉዳቶች ተፈጥረዋል…እንግዲህ በቅርብ ጊዜ ውስጥ እየተደረገ ያለው ውይይት ስለዚህ ጉዳይ ነው፡፡ 
የሕዝብ ለሕዝብ (የጎሳ) ግጭት ሊኖር አይችልም… በጎንደር ስለተፈጸመው ትንሽ ግጭት የተለየ ልዩ የሆነ መፍትሄ የለንም፡፡ በአንድ በትግራውያን ላይ ለደረሰ ጉዳት መፍትሄ የለም፡፡ ዋናው ነገር ስለሰላም እና መረጋጋት ጉዳይ ነው፡፡ ይኸ ጉዳይ በሚገባ ከተመለሰ ሌላው (የጎሳ ግጭት) ጉዳይ በእራሱ ይፈታል፡፡ 
በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ ስለትግራይ የበላይነት ሁኔታ፣ 
አልጋ በአልጋ የሚሆን ነገር የለም፡፡ ውጣ ውረድ አለ፡፡ እውነታ የማይመስል አንድ  ምዕናባዊ አስተሳሰብ እውነት ይሆናል፡፡ ለምሳሌም ያህል አሁን በዚህ ክፍል ውስጥ ብርሀን አለ፡፡ ነገር ግን አሁን በዚህ ክፍል ያለው ጨለማ ነው የሚባል እና የሚደገም ከሆነ ሕዝብ ጨለማ ነው ብሎ ያምናል፡፡ ብርሀን መኖሩ የሚታወቅ ቢሆንም እንኳ ጨለማ ነው፡፡ ምዕናባዊው ሀሳብ ወደ ተጨባጭ እውንነት ተለወጠ ማለት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ዋና ምክንያት አንድ የተረሳ ነገር አለ ማለት ነው፡፡ ይህም የሆነበት ምክንያት ትክክለኛው ምላሽ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አልተሰጠም ማለት ነው፡፡ ከዚህም የተነሳ በብዙሀን መገናኛዎች ውጤታማ የሆነ ስራ አልተሰራም ማለት ነው፡፡ ማንኛውም እውነት ሆኖ ያልተገኘ ነገር ሁሉ (ምክንያቱም ስለትግራይ የበላይነት እየተነገሩ የቆዩ ውሸቶች እስከ አሁን ድረስ ተግዳሮት ስላልገጠማቸው) አሁንም እውነት አይደለም፡፡ 
እውነት በእራሱ አይናገርም፡፡ እውነታውን በተለያዩ መንገዶች በብዙሀን መገናኛ እና በሌሎች መግለጽ ይቻላል፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት ሜዲያ ተገቢ የሆነ ስራ መስራት አለበት፡፡ ድክመት፣ እድገት ወይም ደግሞ ወደኋላ የመንሸራተት እና ሌሎችም ጉዳዮች ካሉ የመንግስት ሜዲያ ነው እውነታውን ማቅረብ ያለበት፡፡ ሆኖም ግን ሜዲያው እውነትን ማንጸባረቅ (ማሰራጨት) አለበት፡፡ 
በፌዴራሊዝም መኖር ምክንያት የትግራይ የበላይነት ሊኖር አይችልም፡፡ ፌዴራሊዝም ማለት ሁሉም ሕዝቦች እኩል ናቸው ማለት ነው፡፡ እያንዳንዱ ሕዝብ እራሱን በእራሱ ያስተዳድራል፡፡ አንድ ጎሳ የበላይ ወይም የበታች የሚባል ነገር የለም፡፡ የጎሳ ቡድኖች ትልቅ ወይም ትንሽ አባላት ስለመኖር ጉዳይ አይደለም፡፡ ትግራውያን እራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ኦሮሞዎች እና የደቡብ ሕዝቦች እንዲሁም የሶማሊ ሕዝቦች እራሳቸውን በእራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ይህም ማለት የእራሳቸውን መንግስት በባለቤትነት ይይዛሉ ማለት ነው፡፡ መሰረቱ እኩልነት ነው፡፡ ይህ ማለት የእራስህን አስተዳደር አስተዳድር ማለት ነው… 
በአማራ ክልል ውስጥ ትግራውያን አስተዳዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በጋምቤላ ውስጥ አስተዳዳሪው ትግራዊ ሊሆን አይችልም፡፡ እንደዚህ ያለው የጎሳ ፌዴራሊዝም አወቃቀር አንዱ ጎሳ በሌላው ላይ የበላይ እንዲሆን አያደርግም፡፡ አንድ ዓይነት የጎሳ ማንነት ያላቸው እራሳቸውን ያስተዳድራሉ፡፡ ትግራውያን እዚህም እዚያም የበላይ (አለቆች) ናቸው የምትል ከሆነ መሰረትየለሽ ነገር ነው፡፡ ሆኖም ግን በየቦታው እስከ ቀበሌ መዋቅር ድረስ ሁሉም ነገር እውነትነት የሌለው ምዕናባዊ ሀሳብ ነው፡፡ የትግራውያን የበላይነት እውነታነት የለውም፡፡ እንደዚህ ያለ ውንጀላ ማቅረብ መሰረተቢስ ነው፡፡ ብርሀን እየበራ እያለ ባለበት ሁኔታ ጨለማ ነው እንደማለት ያህል ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህንን በደጋገምከው ጊዜ ሌሎችም አዎ ጨለማ ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ በፌዴራሊዝም ሀገሪቱ እንዴት መተዳደር እንዳለባት ስለፌዴራሊዝም የኢትዮጵያን ሕዝቦች አላስተማርናቸውም፡፡   
ያ እውነታ ለህዝቡ እንዲተላለፍ አልተደረገም፡፡ ትግራውያን በየቦታው የበላይ ናቸው ማለት እውነታ አይደለም፡፡ ያ ዜሮ ነው፡፡ ዜሮ፡፡ ከትግራይ ክልል ውጭ ትግራውያን ሰው ካለ የመዋዕለ ንዋይ አፍሳሽ ኢንቨስተር ሆኖ እንደማንኛውም ሰው ይኖራል፡፡ ስለሆነም ሕዝቡን ያለማስተማር የግንዛቤ ችግር አለብን፡፡ የትግራይ የበላይነት እውነት አይደለም ሆኖም ግን የእኛ ብዙሀነን መገናኛዎች ጉድለት አለባቸው፡፡ የትግራይ የበላይነት እንደሌለ ብዙሀን መገናኛዎች እውነቱን የማሰራጨት ኃላፊነት አለባቸው…
መማቆ ደብረጽዮን ገብረሚካኤል፡ መንታ ምላስ እና ሁለት ተጻራሪ እምነቶችን በመያዝ የመረጃ ማወናበጃ ዘመቻን ማካሄድ፣
ጆርጅ ኦርዌል “ፖለቲካ እና የእንግሊዝኛ ቋንቋ“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው ድርሰቱ እንዲህ በማለት ጽፏል፡
በእኛ ጊዜ የፖለቲካ ንግግር እና መጻፍ በአብዛኛው መከላከል ለማይደረግላቸው መከላከያዎች ናቸው፡፡ የፖለቲካ ቋንቋ… ውሸቶችን ለመፈብረክ እና እውነት ለማስመሰል የተዘጋጀ እና የተከበሩትን ለመግደል ምንም ዓይነት ጥንካሬ በሌለበት በባዶ ነፋስ ውስጥ ጥንካሬ እንዳለ አድርጎ የማቅረብ ድርጊት ነው…“ ነበር ያለው፡፡
ከደብረጽዮን መንታ ምላስ የሚወጡ ዉሸቶችና እና ተጻራሪ እምነት የሚብሱ ብዙ የሉም፡፡
የአዞ እንባ አንቢው ደብረጽዮን በመንግስት ላይ መንግስት ላዋቀረው እና ማንኛውንም ነገር የሚቆጣጠረው የዘ-ህወሀት ፖለቲካ አጧዛዥ አድራጊ ፈጣሪ ነው፡፡ በዘ-ህወሀት አገዛዝ ውስጥ በርካታ የኃላፊነት ቦታዎችን ይዞ ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ሚኒስቴር ኃላፊ (በትክክለኛ አጠራር የመረጃ ማወናበጃ ቆሮ (መማቆ)/ Chief Disinformation Officer (CDO) እና ከሶስቱ የዘ-ህወሀት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች አንዱ በመሆን በማገልገል ላይ ይገኛል ይባላል፡፡ እንደዚሁም ሁሉ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የቦርድ ሊቀመንበር እና የቀድሞው የኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ልማት ኤጀንሲ/Ethiopian Information and Communication Development Agency (EICTDA)፣ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን የብሮድባንድ ኔትዎርክ ለመገንባት እና የአካዳሚክ እና የምርምር ኔትወርኮችን ለመደገፍ፣ የኢንፍርሜሽን ኮሙኒኬሽን ኔትዎርክ እና ልማትን በማሳደግ  የአካዳሚክ ተቋማትን የግል ዘርፉን ለማሻሻል ተቋቁሞ የነበረው ድርጅት ዳይሬክተር ጀኔራል ነበር ይባላል፡፡
በአዋጅ ቁጥር 691/2010 ድንጋጌ መሰረት የተቋቋመው የኮሙኒኬሽን እና የኢንፎረሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የEICTDA፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙኒከኬሽን አጀንሲ/ETA እና የዘ-ህወሀት የትራንስፖርት እና ኮሙኒኬሽን ሚኒስቴር ጥምረቶች ነው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን የዘ-ህወሀት ተቃዋሚ በሆኑት በኢትዮጵያ ዲያስፖራዎች ላይ ስለላ ለሚያካሂደው እና ከጣሊያን አገር የሳይበር ደህንነት ድርጅት ምርመራ ቡድን/cybersecurity firm Hacking Team የተገዛው ሶፍት ዌር በስለላ ተግባር ላይ እንዲውል እና ለኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ድፍጠጣ ዕኩይ ምግባር ዋና መሀንዲስ ሆኖ ሲያገልግል የነበረ ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2014 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሬፐብሊክ ከዩኤስ አሜሪካ የቴሌፎን መስመር ጋር በማገናኘት የስለላ ተግባራትን በማካሄድ ሕግን መጣስ የሚል ውንጀላ በዩኤስ ፌዴራል ፍርድ ቤት ተመዝግቦ በፋይል ተያዘ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ጉዳዩ በሕግ ማሻሻያ ሂደት ውስጥ ሲሆን በቀጣዮቹ ጥቂት ዓመታት ውስጥ ለዩናይትድ ስቴት አሜሪካ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ይደርሳል፡፡
እንደ አንድ ዘገባ ከሆነ መማቆ ደብረጽዮን በጫካ ውስጥ የዘ-ህወሀት ሬዲዮ ጣቢያ የነበረውን ድምጺ ወያኔን ከመሰረቱ ግለሰቦች መካከል አንዱ ነው ይባላል ፡፡ ሚኒያፖሊስ አም ኤን እየተባለ ከሚጠራው የድረገጽ ዩኒቨርስቲ የዶክትሬት ዲግሪውን እ.ኤ.አ በ2011 እንዳገኘ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡ “በኢትዮጵያ ድህነት ላይ የአይሲቲ ማዕከል ተጠቃሚዎችን የአይሲቲ ውጤታማነት መፈተሽ/Exploring the perception of users of community ICT centers on the effectiveness of ICT on poverty in Ethiopia“ በሚል ርዕስ ባዘጋጀው የዶክትሬት ዲግሪው የጥናት መሟያ የመመረቂያ ጽሁፍ ምናልባትም ኢንፎርሜሽን እና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) የልማት መገልገያ መሳሪያ እንደሆነ መርምሮ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በሚያስገርም ሁኔታ በድህነት ላይ ያለውን የህልዮት ግንዛቤ በተመሳሳይ መልኩ ለፕሮፓጋንዳ እና ለመረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ስራ እንደሚውል አድርጎ እምነት ያሳደረ ይመስላል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን አሁን በህይወት እንደሌለው እንደ ወሮበላ ዘራፊው መለስ ዜናዊ (ወዘመዜ) ሁሉ የኦርዌልን ባህሪ የተላበሰ ገጽታ ያለው ሰው ነው፡፡ እንደ ወዘመዜ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ በኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ በአበዳሪዎች፣ በለጋሽ ድርጅቶች እና በዓለም አቀፍ የድህነት አቃጣሪዎች ላይ የቁማር ጨዋታን መጫወት ይወዳል፡፡
እንደ ታላቅ ወንድሙ እንደ ወዘመዜ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ እርሱ እና የእርሱ ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች በእውነት እና በእውነታዋ ዓለም ላይ የሚኖሩ እና እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ደግሞ በህልም እና በጨለማ ምዕናባዊ ዓለም እንዲሁም በሀሳብ እና በቅዠት ዓለም ውስጥ የሚኖር ነው በማለት ያምናሉ፡፡
በዘ-ህወሀት የኦርዌሊያን ፕላኔት “ጦርነት ሰላም ነው፡፡ ነጻነት ባርነት ነው፡፡ ድንቁርና ጥንካሬ  ነው፡፡ አምባገነንነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ የጎሳ ፌዴራሊዝም የጎሳ እኩልነት ነው፡፡ የጎሳ የበላይነት ሕገወጥ ሴራ ነው፡፡ የዘ-ህወሀት ባለሀብቶች አገዛዝ ማለት ሁሉም ሕዝቦች እኩል የፖለቲካ ስልጣን አላቸው ማለት ነው፡፡“
መማቆ ደብረጽዮን የኢትዮጵያን ሕዝቦች እንደሚያታልሏቸው፣ ጆሮዎቻቸው እንደሚዋሹባቸው እንዲያምኑ እና ጉድለት ያለው አእምሮ እንዳላቸው አድርገው እንዲያምኑ ይፈልጋል፡፡
ስለዘ-ህወሀት ፕላኔት መረጃ ማወናበጃ ዘመቻ ከብዙ ጊዜ ጀምሬ ስጽፍ ቆይቻለሁ፡፡
እ.ኤ.አ ወደ 2009 መለስ ብለን ስንቃኝ ከ3.6 ሚሊዮን የአካባቢ ምርጫዎች መቀመጫዎች ባለፈው ዓመት (2008) ከሶስት መቀመጫዎች በስተቀር ሁሉንም ማሸነፍ ፍጹም የሆነ ዴሞክራሲያዊ ነው፣ እናም ዴሞክራሲ ስለሂደት ነው፣ ስለውጤት አይደለም… ሂደቱ ንጹህ ከሆነ ስህተት ዜሮ ነው ነበር ያለው መለስ ዜናዊ ፡፡
ዛሬ መማቆ ደብረጽዮን እንዲህ ይላል፣ “የጎሳ ፌዴራሊዝም እኩልነት ነው፡፡ የዘ-ህወሀት የበላይነት ምንም ዓይደለም ግን ዱለታ ነው፡፡ ትግራውያን በየቦታው የበላይ ናቸው ማለት እውነታን የሚያመላክት አይደለም፡፡ ያ ዜሮ ነው፡፡
የሚያስገርመው ነገር መማቆ እና ወዘመዜ ስለዜሮ አንድ ነገር አላቸው፡፡
ዘሮን በጣም ይወዱታል፡፡ በተለይም የዜሮ ድምር ምርጫ ጨዋታዎችን (ሁልጊዜ ሁሉንም ነገር እንደሚያሸንፉ እና ሌላው እያንዳንዱ ሰው ግን ሁሉንም ነገር እንደሚያጣ እና እንደሚሸነፍ) በጣም ይወዷቸዋል፡፡ ላለፉት 25 ዓመታት ከአንድ የዜሮ ድምር ጨዋታ ሌላ የዜሮ ድምር ጨዋታ እየተገለባበጡ በመጫወት ሁልጊዜ በተከታታይ ሲያሸንፉ ኖረዋል፡፡
እስቲ ጉዳዩን ግልጽ ላድርገው፡፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2015 በዘ-ህወሀት ፓርላማ መቀመጫዎችን መቶ በመቶ ያሸነፈው ማን ነው? ይኸ ነው እንግዲህ የዜሮ ድምር ጨዋታ ማለት!
ቀደም ሲል እ.ኤ.አ በ2008 ተካሂዶ እንደነበረው የአካባቢ ምርጫዎች ወዘመዜ ኢትዮጵያውያን ስለዘ-ህወሀት የተሳሳት ግንዛቤ አላቸው እንዳለው ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ መማቆ ደብረጽዮን ዛሬ እንደዚሁ በማለት ላይ ይገኛል፡፡
ወዘመዜ ኢትዮጵያውያን ስለዴሞክራሲ የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው ብሏል፡፡ ስለምርጫዎች፣ የሕግ የበላይነት፣ መልካም አስተዳደር እና ስለፌዴራሊዝም የተሳሳተ ግንዛቤ አላቸው፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ስለዘ-ህወሀት ዴሞክራሲ፣ ፌዴራሊዝም፣ ስለትግራይ የበላይነት፣ ስለልማት፣ ስለመልካም አስተዳደር እና ስለዴሞክራሲ የተሳሳት ግንዛቤ አላቸው ይላል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ኢትዮጵያውያን ከእንቀልፋቸው ተነስተው የፈላዉን ቡና ያሽትቱ ይላል፡፡
በዘ-ህወሀት ፕላኔት ውስጥ የተጻራሪ እምነቶች እና መንታ ምላሶች ውጤት፡ “ጦርነት ሰላም ነው፡፡ ነጻነት ባርነት ነው፡፡ ድንቁርና ጥንካሬ ነው፡፡ አምባገነንነት ዴሞክራሲ ነው፡፡ ድህነት ባለጸግነት ነው፡፡ ረሀብ ጥጋብ ነው፡፡ የመንግስት ስህተቶች የሰብአዊ መብቶች ናቸው፡፡ የተጭበረበሩ እና የተዘረፉ ምርጫዎች የሕዝቦች ምርጫዎች ናቸው፡፡ ሕዝቦችን ማስፈራራት ለእነርሱ የደስታ ምንጭ ነው፡፡ እናም የተደራረቡት የውሸቶች ቁልሎች የእውነት ማዕበሎች ናቸው፡፡“
የዘ-ህወሀት መንታ ምላስ እና ተጻራሪ እምነቶች ምርጫዎች ስለሂደት የሚዘግቡ ናቸው፡፡ የሕግ የበላይነት ማለት በዘፈቀደ የዜጎችን ህይወት የመቅጠፍ፣ የነጻነት እና ንብረት ክልከላ ሂደት ነው፡፡ አስተዳደር ስለተጠያቂነት እና ግልጸኝነት አይደለም፡፡ በላም ጡት ላይ ተጣብቆ እንደሚኖር መዥገር በስልጣን ኮርቻ ላይ ተጣብቆ መኖር ማለት ነው፡፡ ሕገ መንግስት ስለሕግ የበላይነት አይደለም፡፡ ስለሕገወጥ አገዛዝ ነው፡፡ ፌዴራሊዝም ስለግልጽ ሕገመንግስታዊ የስልጣን ክፍፍል አይደለም፡፡ ሆኖም ግን አምባገነናዊ አገዛዝን ለማጠናከር ጥልቅ የሆነ የጎሳ፣ ባህላዊ እና ክልላዊ የጎሳ ፌዴራሊዝም እየተባለ ስለሚጠራው ምዕናባዊ ሂደት ነው፡፡
መንታ ምላስ እና ተጻራሪ እምነቶች እንደ መረጃ ማወናበጃ ስልቶች፣
እ.ኤ.አ በ1984 ኦርዌል እንዲህ በማለት ጽፏል፡
ተጻራሪ እምነት ሁለት ተጻራሪ እምነቶች በአንድ ሰው አእምሮ ውስጥ በአንድ ጊዜ የሚያዙበት እና ሁለቱንም መቀበል ማለት ነው… በቅንነት የሚያምኑበትን ሆን ብሎ ውሸቶችን ለመናገር እና የማይመቹ የሚመስሉትን እንዲረሱ የማድረግ እና አስፈላጊ ከሆነም ብዙ ጊዜ የቆየ እና የተረሳ ቢሆንም ነባራዊውን እውነታው መካድ እና አንድ ሰው የካደውን እንዲይዝ የሚደረግበት ሁኔታ ነው- ይኸ ሁሉ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ተጻራሪ እምነቶች የሚለውን ቃል መጠቀም ቢኖርም ተጻራሪ እምነቶችን መጠቀም አስፈላጊ ነው፡፡ ቃሉን ለመጠቀም አንድ ሰው ከእውነታው ጋር መጋፈጥ ይኖርበታል፡፡ አዲስ በሆኑ ተጻራሪ እምነቶች ይህንን እውቀት ለማጥፋት እና ወሰን በሌለው መልኩ ሁልጊዜ ውሸቱ ከእውነቱ በአንድ እርምጃ ወደፊት ይሄዳል፡፡
 መማቆ ደብረጽዮን እና የእርሱ ዘ-ህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች ሁሉንም ነጻ ጋዜጠኞች በማሰር እና እነርሱን ለመተቸት ድፍረቱ ያላቸውን ፕሬሶች እንዲዘጉ አድርገዋል፡፡ አሁን ደግሞ የመገናኛ ብዙሀኑ የዘ-ህወሀትን እውነተኛ አፈጻጸም ለሕዝቡ በመዘገቡ ረገድ ደካማ አፈጻጸም ነው ያስመዘገቡት በማለት ቅሬታውን በመግለጽ ላይ ይገኛል፡፡ ስለዘ-ህወሀት የብዙህን መገናኛ ደካማ ስራ ቅሬታ የሚያቀርብ ከሆነ የተሳሳተ የአስተሳሰብ መስመርን መከተል ማለት ነው፡፡ አሁን ማንም ኢትዮጵያዊ (ምናልባትም ከዘ-ህወሀት ታዛዥ ሎሌዎች በስተቀር) ለዘ-ህወሀት መገናኛ ብዙሀን ትኩረት አይሰጥም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች በዘ-ህወሀት ውሸቶች፣ ቅጥፈቶች እና ተራ አሃዛዊ አሀዛዊ ቅጥፈቶች ታመዋል፣ ደክመዋልም!
መማቆ ደብረጽዮን ምንም ዓይነት አዲስ ነገር እየተናገረ አይደለም፡፡ የእርሱ ቀደምት የሆነው አስቂኙ በረከት ስምኦን ማንም ቢሆን የዘ-ህወሀትን ቴሌቪዥን ወይም ሌሎችን መገናኛ ብዙሀን አይመለከትም በማለት በየጊዜው ቅሬታውን ያቀርብ ነበር ፡፡
የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኢሳት ጋር ተጣብቀዋል፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦች ከኢሳት ሬዲዮ ጋር እራሳቸውን አዋህደዋል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ኢሳትን በገንዘብ እና በሌላም መደገፍ እንዲችሉ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
መማቆ ደብረጽዮን በጎንደር እና በሌሎች ሁከቱ በተቀሰቀሰባቸው አካባቢዎች ያለው ችግር  ስር የሰደደ ሙስና፣ ስልጣንን ከሕግ አግባብ ውጭ የመጠቀም እና ክልሎችን (ባንቱስታን) የሚያስተዳድሩ ባለስልጣኖች የአስተዳደር ጉድለት አለባቸው ይላል፡፡ ከዘ-ህወሀት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የላቸውም፡፡
እውነታው ፍርጥርጥ ተደርጎ ሲታይ ግን  እንደ እንግሊዝ የቅኝ ግዛት ጌቶች እና እንደ ደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች ዘረኛ የአፓርታይድ አገዛዝ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ዘ-ህወሀት በክልሎች (ባንቱስታንስ) ውስጣዊ ቅኝ ግዛትን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡ ዘ-ህወሀት ለእርሱ ታማኝ የሆኑ ብቸኛ የክልሉ ኗሪ የክልል ባለስልጣናትን ፈጥሯል፡፡ ዘ-ህወሀት የእርሱን ወኪሎች፣ አሻንጉሊት የአካባቢ መሪዎች በስልጣን ላይ ያስቀምጣል፣ እናም ምዕናባዊ የእራስ ገዝ እና የእራስ አስተዳደር መብት ይሰጣቸዋል፡፡ ሆኖም ግን በክልል መንግስታት ላይ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር ያደርጋል፡፡ የክልል ባለስልጣኖች የእራሳቸውን መንግስት በነጻነት መምራት ይቅር እና ከዘ-ህወሀት ፈቃድ ውጭ ከቢሯቸው እንኳ መንቀሳቀስ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን መማቆ ደብረጽዮን በክልል የሚገኙትን ባለስልጣናት በማባረር ዘ-ህወሀትን ነጻ ሊያደርግ ይፈልጋል፡፡
መማቆ ደብረጽዮን ዘ-ህወሀት በጣም ወሳኝ እና አስፈላጊ በሆኑ የፖለቲካ እና የማህበራዊ ተቋማት ውስጥ ዘ-ህወሀት ትንሽ ወይም ደግሞ ምንም ዓይነት ቁጥጥር እንደማያደርግ ይክዳል፡፡
ይህንን ጉዳይ እንዲህ በማለት በሌላ መንገድ ላስቀምጠው፡ እ.ኤ.አ ግንቦት 2016 ተካሄደ የተባለውን የይስሙላ የፓርላሜንታሪ የቅርጫ ምርጫ መቶ በመቶ ያሸነፈው ማን ነበር? በኢኮኖሚው ላይ የበላይነት ያለው ማን ነው? በወታደራዊ ኃይሉ ሙሉ በሙሉ ቁጥጥር ያለው ማን ነው? በሲቪል ሰርቪሱ ላይ ፍጹም የሆነ ቁጥጥር ያለው ማን ነው? የደህንነት አገልግሎቱን እና የፍትህ ሂደቱን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ማን ነው? የአበዳሪ እና የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶችን እንዲሁም የዓለም አቀፍ የደህንነት አቃጣሪዎችን ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ማን ነው?
ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚቀርብ ጥያቄ ቢኖር አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ለማቅረብ እና በማንኛውም ጊዜ ለመከራከር እርግጠኞች ነን፡፡
በመማቆ ደብረጽዮን የተደረገ አስደናቂ የእምነት ቃል፣
ለአስር ዓመታት ያህል የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት እና የእርሱ የክልል መንግስታት ሸፍጠኞች እና ስለደቡብ አፍሪካ (ባንቱስታን) ስርዓት የጭብጥ ክርክሬን ሳደርግ እና መረጃዎችን ሳቀርብ ቆይቻለሁ፡፡
በአሁኑ ጊዜ የዘ-ህወሀት ክልል (የጎሳ ፌዴራሊዝም) ስርዓት የአፓርታይድ ባንቱስታን ወይም ደግሞ መኖሪያ ሀገር ስርዓትን በሚመለከት ከደብረጽዮን አፍ ማጠቃለያ ማስረጃ አለ፡፡
አሁን ባለፈው ሚያዝያ “ባንቱስታናይዜሽን (ክልላዊነት) በኢትዮጵያ“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችት በዘ-ህወሀት በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረው እና እየተጠበቀ ያለው ስርዓት ከደቡብ አፍሪካ ጥቂት ነጮች ዘረኛ አገዛዝ ጋር እንደሚመሳሰል እና እ.ኤ.አ በ1994 የብዙሀኑን ጥቁር አገዛዝ ከመመስረቱ በፊት ከነበረው ጋር አንድ ዓይነት እንደሆነ ከምንም ጥርጣሬ በላይ አሳይቻለሁ፡፡
መማቆ ደብረጽዮን በቃለ ምልልሱ እንዲህ ብሎ ነበር፡
“በአማራ ክልል ትግራውያን አስተዳዳሪዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡ በጋምቤላ ውስጥ አስተዳዳሪው ትግራውያን ሊሆን አይችልም፡፡ ይህ (የጎሳ ፌዴራሊዝም ስምምነት) ለሌሎች የበላይነት ዕድል አይሰጥም፡፡ አንድ ዓይነት ጎሳ ያላቸው እራሳቸውን በእራሳቸው ያስተዳድራሉ፡፡ ትግራውያን እዚህም እዚያም የበላይ (አለቆች) ናቸው የምትል ከሆነ መሰረተቢስ ነው“ ነበር ያለው፡፡ 
ይኸ ነበር እንግዲህ በአፓርታይድ ባንቱስታን ሀገር በግልጽ የተፈጸመው!
በክዋዙሉ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው ዙሉስ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በሲስኬይ እና በትራንስኬይ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የኮሳ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በቦትስዋና ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የትስዋና ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በሌቦዋ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የፔዲ እና የሰሜን ድበሌ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በቬንዳ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የቬንዳ ሕዝብ ብቻ ነበር፡፡
በጋዛንኩሉ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የሻንጋን እና የሶንጋ ሕዝቦች ብቻ ነበሩ፡፡
በክዋ ክዋ ሀገር ስልጣን የሚይዝ እና የመንግስቱን ስራ ሊያንቀሳቅስ የሚችለው የባሶቶስ ሕዝብ ብቻ ነው፡፡
ሆኖም ግን በደቡብ አፍሪካ የመጨረሻውን ስልጣን የያዘው ማን ነው? የጥቂት ነጮች የአፓርታይድ አገዛዝ ነው፡፡
በደቡብ አፍሪካ ያሉ ሕዝቦች ነጻነት ምን ያህል ነጻ ነው?
እንዲያው ለነገሩ ያህል ዘ-ህወሀት ነጻ ናቸው ይላል፡፡
የኢትዮጵያ 9ኙ ባንቱስታንስ ምን ያህል ነጻ ናቸው? ዘ-ህወሀት እንዲያው ለነገሩ ያህል ነጻ ናቸው ይላል፡፡
በእውነተኛ የፌዴራሊዝም ስርዓት ዘር፣ ጎሳ፣ ጾታ፣ ኃይማኖት፣ ርዕዮተ ዓለም፣ ወዘተ የፖለቲካ መብቶችን ከመተግበር ጋር በተያያዘ መልኩ ምንም ዓይነት ጠቀሜታ የላቸውም፡፡
ለምሳሌም ያህል ሂላሪ ክሊንተን ከኒዮርክ የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት አባል ከመሆኗ በፊት የሞያ ህይወቷን ያሳለፈችው በአርካንሳስ ግዛት ነበር፡፡ ሚት ሮምነይ የተወለደው በሚችጋን ሲሆን የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው በኡታህ ሆኖ የማሳቹሴትስ አስተዳዳሪ ሆኗል፡፡ ባራክ ኦባማ የተወለደው በሀዋይ ሲሆን የኮሌጅ ትምህርቱን የተከታተለው ደግሞ በካሊፎርኒያ፣ በኒዮርክ እና በማሳቹሴትስ ሆኖ ከኢሊኖይስ የዩኤስ አሜሪካ የምክር ቤት አባል ለመሆን በቅቷል፡፡
የዘ-ህወሀት የጎሳ ፌዴራሊዝም ስርዓት የቅርብ እና ታላቅ የደቡብ አፍሪካ አፓርታይድ አገዛዝ ተቀጽላ መሆኑን መማቆ ደብረጽዮን ማስተባበል የማይቻል ማስረጃ ያቀረበልኝ ስለሆነ አመሰግነዋለሁ፡፡
ኃይል ያለው ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ነው፡ የዘ-ህወሀት መገዳደር እርባናቢስ ነገር ነው፣
በዘ-ህወሀት አገዛዝ ላይ መጠነ ሰፊ እየሆነ እና እየተስፋፋ የመጣው ሕዝባዊ እምቢተኝነት እና መገዳደር እልቂትን በመፈጸም፣ የተዛባ የማወናበጃ መረጃ በማቅረብ ወይም ደግሞ በሌላ በማንኛውም መንገድ የሚቆም አይደለም፡፡
በአንዲ ዊሊያም የግጥም ስንኞች ጸሀይ ሰማይን ትለቃለች ብሎ መናገር አይቻልም/ህጻንን እንዳያለቅስ መጠየቅ አይቻልም/የውቅያኖስን ማዕበል ወደ ዳርቻው እየገፋ እንዳይመጣ ለማስቆም አይቻልም/
እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ሕዝቦች የሰብአዊ መብቶቻቸውን እንዳይቀዳጁ እና የሕግ የበላይነት የተረጋገጠባት፣ የማትከፋፈል፣ ነጻነት እና ለሁሉም ፍትህ የሰፈነባት ዴሞክራሲያዊ የሆነች ሀገርን እንዳይመሰርቱ ማስቆም አይቻልም፡፡
የኢትዮጵያን ሕዝብ ማስቆም በፍጹም አይቻልም!!!
ምክንያቱ ደግሞ ግልጽ እና ቀላል ነው፡፡
እ.ኤ.አ በ2008 ዓለም አቀፍ ንቃት የተፈጠረ መሆኑን ዥብግኒው ብርዜንስኪ እንደተናገሩት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ በአሁኑ ጊዜም በኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ መነቃቃት ተፈጥሯል፡፡
ብርዜንስኪ እንዲህ የሚል የመከራከሪያ ጭብጥ አቅርበዋል፡
በሰው ልጆች ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሁሉም የሰው ልጆች ሁሉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ናቸው፣ የፖለቲካ ንቃታቸው ከፍ ብሏል እናም የፖለቲካ ተሳትፏቸው እየጨመረ የመጣበት ሁኔታ ተከስቷል…የዓለም አቀፉ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውጤት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለበርካታ ዘመናት በቅኝ ግዛት ትዝታ እና በአገዛዝ የበላይነት ተቀፍድዶ የኖረው ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ለግል ክብር መጨመር፣ ለባህል መከበር እና ለኢኮኖሚ ዕድሎች ጥያቄዎችን በማቅረብ ላይ በመገኘቱ ምክንያት ነው…ለክብር የሚጠየቀው ዓለም አቀፍ ጥያቄ ለዓለም አቀፉ የፖለቲካ መነቃቃት ዋና መሰረታዊ ክስተት ነው…ያ መነቃቃት ማህበራዊ መጠኑ ግዙፍ እና ስር ነቀቀል የፖለታካ ጥያቄ ነው… ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ዓለም አቀፍ የሬዲዮ፣ ቴሌቪዥን ስርጭት እና እየጨመረ የመጣው የኢንተርኔት አገልግሎት የፖለቲካ ወይም የኃይማኖት ጉዳዮችን መስመር እያስያዘ ለመብቱ እና ለወደፊቱ ብሩህ ተስፋ ሲል የጋራ ግንዛቤ ያለው ማህበረሰብን በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ እነዚህ ኃይሎች ዓለም አቀፍ ወሰንን በመሻገር በአሁኑ ጊዜ ባሉት መንግስታት እንደዚሁም ባለው ዓለም አቀፍ ተዋረድ ላይ መገዳደሮችን በመፍጠር ላይ ይገኛል… 
የሶስተኛው ዓለም ወጣቶች በተለይ እረፍትየለሽ እና በቀልተኞች ናቸው፡፡ እንደዚሁም ሁሉ አሁን ያሉበት የሕዝብ የመጨመር አብዮትም የፖለቲካ የጊዜ ፈንጂ ቦምብ ነው…የወጣቶቹ የወደፊት አብዮተኞች የመሆንም ሁኔታ በርካታ ተማሪዎች የሶስተኛ ደረጃ የከፍተኛ ትምህርት በታዳጊ ሀገሮች ተከታታይ እና በምሁራን ካምፕ ውስጥም የሚገኙ በመሆናቸው የሁኔታው መከሰት ጎልቶ በመውጣት ላይ ይገኛል… 
የዓለም ዋና ዋና ኃይሎች፣ አዲሶቹ እና የቀድሞዎቹ አስደናቂ ከሆነ እውነታ ጋር ተጋፍጠዋል፡ የጦር ኃይላቸው አደገኛነት ከምንጊዜውም በላይ የበለጠ ሆኖ የሚገኝ ቢሆንም የፖለቲካ መነቃቃት በተፈጠረበት ማህበረሰብ ላይ በመግባት ሁኔታውን ለመቆጣጠር መሞከር በጣም ዝቅተኛ የሆነ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ አቅምን የሚገድብ ስለሆነ ማለት ነው፡፡ ጉዳዩን በግልጽ ለማስቀመጥ በዱሮ ጊዜ አንድ ሚሊዮን ሕዝብ በአካል ከመግደል ይልቅ አንድ ሚሊዮን ሕዝብን መቆጣጠር ይቀል ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን አንድ ሚሊዮን ሕዝብን ከመቆጣጠር ይልቅ አንድ ሚሊዮን ሕዝብን መግደል መቁጠር ከሚያስችል በላይ ቀላል ነገር ነው፡፡   
ለዘ-ህወሀት የተገኙት ትምህርቶች ቀላል እና እንዲህ የሚሉ ናቸው፡
70 በመቶ ያህሉን የሕዝብ ብዛት የሚይዙት የኢትዮጵያ ወጣቶች ሕዝባዊ የእምቢተኝነት አመጹን እና አብዮቱን የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ መሪዎች እና ሌሎች ቀሪዎች ሳይሆኑ ወጣቶቹ በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች የሰብአዊ ክብር እና ሰብአዊ መብቶች እንዲከበሩ በመጠየቅ ላይ ናቸው፡፡ ይኸ ነገር ምንም ዓይነት ድርድር ሊቀርብበት የሚችል ጉዳይ አይደለም፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች እረፍትየለሾች እና በቀልተኞች ናቸው፡፡ ምንም ዓይነት ትዕግስት የላቸውም፡፡ እንደ እቃ ሊገዙ ወይም ሊሸጡ አይችሉም፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች በዘ-ህወሀት የጭቆና አገዛዝ የሁለተኛ ዜግነት ባርነት ተጭኖባቸው የሚገኙ ስለሆነ በዚህ መቅነቢስ ዘረኛ ስርዓት ታመዋል፣ ደክመዋል፡፡
የኢትዮጵያ ወጣት ሕዝቦች የዘ-ህወሀት መሪዎች ባልሰለጠነው አውሪያዊ ምዕናባቸው ከሚስሉት በእጅጉ የበለጠ ስረነቀል ለውጥን ናፋቂ እና ለተግባራዊነቱም ሌት ከቀን የሚታገሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ናቸው፡፡
ዘ-ህወሀት አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን ከመቆጣጠር ይልቅ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን መግደል በእጅጉ ይቀለዋል፡፡
የዘ-ህወሀት ወታደራዊ ኃይል አደጋ ጣይነት ከምንጊዜውም በላይ ከፍተኛ ነው፣ ሆኖም ግን ከኢትዮጵያ ወጣቶች ኃይል ጋር ስናነጻጽረው በአውሎ ነፋስ ዉስጥ አንዳለ የላባ ያህል ነው፡፡
እንግዲህ የዘ-ህወሀት ዕድል እንደዚህ ነው፡፡
ዘ-ህወሀት ባዶ ይሆናል እናም ወደታሪክ ቆሻሻ መጣያ ቅርጫት ይጣላል፡፡
ዘ-ህወሀት ማወቅ ያለበት አንድ የማይሞት እና የማይበገር ሕግ አለ፡፡
ያንን ሕግ ያቀናበሩት ማህተመ ጋንዲ ሲሆኑ ሕጉ እንዲህ የሚል ነው፡
“ጨቋኞች እና ገዳዮች ለጊዜው የማይበገሩ መስለው ይታያሉ፣ ሆኖም ግን በመጨረሻ ሁልጊዜም ቢሆን ይወድቃሉ፣ አስቡት ሁልጊዜ፡፡“
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  
መስከረም 17 ቀን 2009 ዓ.ም

Monday, September 26, 2016

በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አደራሽ በነበረው ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለቀሰ፤

   Bilderesultat for ato gedu andargachew


በአብቁተ አደራሽ በነበረው ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለቀሰ፤
የባህር ዳር ከተማ ወጣት ተወካዩችን በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የመሰብሰቢያ አዳራሽ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ባወያየበት ሰዐት ከወጣቶች የተሰነዘረው አሰተያየት የክልሉን ፕሬዝዳንት አስለቀሰ፡፡

ከተሰበሰቡ ወጣቶች መካከል ‹‹እኛ ስለአማራ ሕዝብ ቆሰልን፤ ሞትን፤ ተገደልን፤ ደማችን አፈሰስን አንተስ ለእኛ ለአማሮች ምን አደረክልን? እኛ ጓደኞቻችንን ቀብረናል፡፡ የሞተው ግን ያንተም ወንድም ነው፡፡ በዚህ ስዓት ብር ሸለቆና ሰባታሚት በቶርቸር ስነ ልቦናቸው የሚሰለቡት የእኛ ወንድሞች ናቸው፤ አንተ መቼ ነው የምትደርስልን?›› በማለት በስሜት ሲናገር ገዱ አለቀሰ፡፡ እንባውን አዝረከረከ፡፡ ከማይግራፎኑ ድመፁ ጎልቶ ተሰማ፡፡


ሌላኛው ተወያይ ወጣት መነጋገሪያውን ተቀበለ ‹‹አዎ ገዱ ለሞቱት አንተም ብታነባ የተሻለ ነው፡፡ እኔ እልሃለሁ፡፡ አማራን እየኖርክበት አላወከውም፡፡ አማራ መቸም ቢሆን ሀብቱን ብትዘርፈው ይቅር ይልሃል፡፡ ወንድሙን ልጁን ገለህ፤ ደሙን አፍሰህ ግን ይቅርታ አያደርግም አማራ ደምን በደም እንጅ መቸም ቢሆን የደመ ቂሙን አታደርቀውም፡፡ ልጁንም ደም መላሽ እያላ ያሳደገ ሕዝብ ነው፡፡ አንተስ ስታስበው ደማቸው የፈሰሰው ወንድሞቻችን ባክኖ የሚቀር ይመስልሃል? እኛ ዝም ብንል የእነሱ ቤተሰብ እንደትስ ዝም ሊሉ ይችላሉ? ከሞተው ደም ይልቅ፤ ካሳ የተከፈለው እኮ ለፈረሰው የአበባ ልማት ነው፡፡ አትሉንም እንጅ ብትሉንም ነፍስን በገንዘብ አንቀይርም፡፡ የአንድ ሰው ህይዎት ዋጋውስ ስንት ነው? ለማንኛውም ስሙን ለመጥራት አንፈልግም አንተ እና ያ ተላላኪ አንዴ በአማራ ህዝብ ላይ ሞት በቃላችሁ አውጃችኃል፡፡ የወንድሞቻችን ደም በእናንተ እና በሥርዓቱ ላይ ነው፡፡ ይቅርታ ለማድረግ እና አብሮ ለመሆን እንዴት ይቻለናል?››


ወይይቱ ወደ ባሰ ጭቅጭቅ በማምራቱ ያለመፍትሄ የባህር ዳር ወጣቶች ስብሰባው ጥለውት በመውጣታቸው ተበትኗል፡፡

በወለጋ በነቀምት ከተማ በቀበሌ 04 ከተገደሉት የኦሮሞ ወጣቶች መሀል ኣንዱ

በወለጋ በነቀምት ከተማ በቀበሌ 04 ከተገደሉት የኦሮሞ ወጣቶች መሀል ኣንዱ


በወለጋ በነቀምት ከተማ በቀበሌ 04 ከተገደሉት የኦሮሞ ወጣቶች መሀል ኣንዱ Oromo Protests
welega
neqemt
nek welega

አቡነ አብርሀም ታሪክ ሰሩ! ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል።



Image may contain: 1 person , beard
አቡነ አብርሀም ታሪክ ሰሩ! ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። #Ethiopia #Meskel #BahrDar #AmharaResistance #MinilikSalsawi
የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም ታሪክ ሰሩ። ከፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላዎች ፊት ለፊት እውነትን ተጋፍጠዋል። ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። እንዲህም አሉ…
«ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም ፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን?፤ መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልዩ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ» ብለዋል። ህዝብ ክርስቲያኑ አቡነ አብርሀም ይንን ንግግር ሲያደርጉ በእልልታና በጭብጨባ ድጋፉን ገልጧል።
ባህር ዳር ላይ «የተከበረው» የደመራ በዓል ጸሎትና ሀዘን ታስቦ ውሏል። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቱ ወረብ፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ደግሞ ወቅቱን የተመለከተ መዝሙሮችን አቅርበዋል። የበገና ደርዳሪው እንዲህ ብሏል፦
«ማዕበሉን አይቶ ልባችን አይፍራ፣
“ሁሉን ቻዩ አምላክ አለ ከኛ ጋራ፤ የሚል ነበር።
በመጨረሻም በየቤተክርስቲያኑ ይደረግ የነበረው የምህላና ጸሎት በጋራ መሀል ባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ተስተጋብቷል። አባታችንን አቡነ አብርሀምን፣
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቶቻችንን፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ቃለ ህይወት ያሰማልን። ረጅም እድሜ ይስጥልን።
ሁሉም መርሀ ግብር ካለቀ በኋላ አቡነ አብርሐም መጀመሪያ «ሕዝቡ ወደቤቱ ሳይገባ እኔ አልንቀሳቀስም» በማለታቸው እዚያው መስቀል አደባባይ ከቀሩ በኋላ፤ በመጨረሻ ላይ የአማራ ፖሊስ ዩኒፎርም በለበሱ የትግራይ ወታደሮች ከታት በሚታየው መልኩ በፖሊስ መኪኖች ታጅበው እሳቸው ግን በእግራቸው ወደ ባዕታቸው ተመልሰዋል።

በኦስሎ በአገራችን ወቅታዊ ጉዳይ ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ


በሁለት ተቋማ በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ እና በጋራ የምክክር መድረክ አዘጋጅነት በወቅታዊ የአገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊ ህዝባዊ ውይይት ተካሄደ። ውይይቱ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ከመጨረሻው ግብ ለማድረስ የተያዘው የነጻነት ትግል ለውጤት እንዲበቃ ምን መደረግ አለበት የሚለውን ትልቅ አጀንዳ በመያዝ ሁሉም ለኢትዮጵያ ፍትህና ዲሞክራሲ መስፈን፣ ዲሞክራሲያዊና ሰባዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ የሚሰሩ የፖለቲካ ድርጅቶችና ህዝባዊ ተቋማትና የእያንዳንዳችን እንደግለሰብ ልናበረክት የሚገባን አስተዋጾ ላይ በሰፊው መክሯል። \
በተጋባዥ እንግዶችም እጅግ ጠቃሚ ነጥቦችንና ሃሳቦችን አቅርበዋል። የመጀመርያ ተናጋሪ የነበረው ዶ/ር ሙሉዓለም አ...ዳም አጠቃላይ ህዝባዊ እምቢተኝነቱ እዚህ ደረጃ እንዴት እንደደረሰ፣ ያሁን ላይ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ እና ወደፊት ሊደረግ የሚገባውን የትግል አቅጣጫ በሰፊው አሳይተዋል፤ በመቀጠልም ወጣት ኤልሳቤጥ ግርማ በነጻነት ትግሉ የወጣቶች ተሳ ትፎ በሚል ርዕስ ሰፊ ገለጻ አድርጋለች፤ ወጣቷ በገለጻዋም የወጣቱን የፖለቲካ እንቅስቃሴ በአጼ ኃይለስላሴና ደርግ ዘምን ፣ በወያኔ ዘመንና የወቅቱን አጠቃላይ የወጣቶች እንቅስቃሴ በማሳየት እንዲሁም ተግዳሮቶቹን በመጠቆም በተቀጣጠለው የለውጥ እንቅስቃሴ ወጣቱን ለበለጠ ትግል እንዴት ማነሳሳት እንደሚቻል በሰፊው አብራርታለች። ሦስተኛው ተጋባዥ ዶ/ር ተክሉ አባተ የፖለቲካ ድርጅቶች እና ህዝባዊ ተቋማት በተጀመረው የነጻነት ትግል ላይ ሊያበረክቱት የሚገባቸውን ከፍተኛ ሚና በዝርዝር አስረድተዋል፤ በግለሰብ ከእያንዳንዳችንም የሚጠበቅብንን ኃላፊነት በግልፅ አሳይተዋል።
በአጠቃላይ ህዝባዊ ውይይቱ እጅግ ጠቃሚ ወቅታዊ ጉዳዮችና የመፍትሄ ሃሳቦች የተነሱበት፣ ከፍተኛ የትግል መነቃቃትና አብሮነት የተንጸባረቀበት ነበረ። የተጀመረው ህዝባዊ እምቢተኝነት ከጫፍ ደርሶ አረመኔያዊ አገዛዝ ከህዝባችን ጫንቃ አውርደን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመቅበር ሁለገብ እንቅስቃሴ አስፈላጊ እንደሆነ በመድረኩ ከቀረቡ የውይይት ርዕሶች፣ ነጥቦችና በተሳታፊዎች ከተሰጡ አስተያየቶችና የሃሳብ ልውውጦች በቂ ግንዛቤ ላይ ተደርሷል።
በመጨረሻም ኢትዮጵያውያ አገራችን ከገባችበት አስቸጋሪ አጣብቂኝ ውስጥ በማውጣት እውነተኛ ሰላም፣ ፍትህና ዲሞክራሲ የሰፈነባት፣ የህግ የበላይነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን ለመገንባት የበኩላችንን ጥረት ማድረግ እንደሚገባ እና በውይይቱ የተሰጡትን የመፍትሄ ሃሳቦች፣ አቅጣጫዎችና የትግል ስልቶች በሚገባ ተረድቶ ለተግባራዊነቱ መንቀሳቀስ እንዳለብን አጽንኦት ተሰጦ የአቋም መግለጫ በማውጣት ስብሰባው ተጠናቋል።

See More

ሴት አትሌቶች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል



ሴት አትሌቶች ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል
Ethiopian Hirut Guangul, the first woman runner to show gesture of protest (the × sign) against her gov’t after finishing first @ Quad cities Marathon in US.
Abdurehim Ahmed's photo.
በአሜሪካ ኩዋዲ ሲቲ ማራቶን ውድድር አሸናፊ የሆነችው ኢትዮጵያዊቷ ጀግናዋ አትሌት ሂሩት ጓንጉል ውድድሯን ስታጠናቅቅ ልክ እንደ ሌሊሳ እጆቿን ወደ ላይ በማጣመር የኢትዮጵያ መንግስት በሕዝብ እየፈጸመ ያለውን አፈናና የመብት ረገጣ ለዓለማቀፉ ህብረተሰብ አጋልጣለች።

ስለ “ደህንነቱ” መሥሪያ ቤት ከማውቀው በጥቂቱ – Tadesse Biru Kersmo



ስለ “ደህንነቱ” መሥሪያ ቤት ከማውቀው በጥቂቱ – Tadesse Biru Kersmo
በርዕሴ ላይ “ደህንነትን” በጥቅስ ያስገባሁት ለተቋሙ የሚገባ ስያሜ ባለመሆኑ ነው ። ሙሉ ስሙ “የአገርና የሕዝብ ደህነት ጽ/ቤት” የሚባል ይመስለኛል፤ እርግጠኛ አይደለሁም፤ ኦፊሳላዊ ስሙን የማወቅ ፍላጎትም የለኝም። የጽ/ቤቱ ሥራ ከአገርም ከሕዝብም በተቃራኒ የቆመ፤ የህወሓት አገዛዝን ለማስቀጠል ማናቸውንም ዓይነት ክፋቶች የመፈጸም ስልጣንም ፍላጎትም ያለው፤ ሰዎችን በማሰቃየት የሚደሰቱ ሳዲስቶች የተሰባሰቡበት ነው። እኔ የአገዛዙ የስለላ ተቋም ወይም የአገዛዙ ጆሮ ጠቢዎች በሚል ስያሜ ነው ልጠራቸው የምፈልገው።
ስለዚህ መሥሪያ ቤት የተቻለኝን ያህል ማወቅ የሚያዝናናኝ ሥራዬ (hobby) ነው። ስለዚህ አሳፋሪ መሥሪያ ቤት ከማውቀው ጥቂቱን ከማካፈሌ በፊት ከቆዩ ግጥሞቼ አንዱን ልጋብዛችሁ።
የአምባገነኖች “ደህንነት”
“መልከ ጥፉ
በስም ይደግፉ”
ሆነና ….
አንተን ፀረ-መብት ወአርነት
የነፃነት ተጋድሎ እንቅፋት
ስምህ ነው አሉን “ደህነት”
አንት ጆሮ ጠቢ አሳባቂ
የግል ምስጢርን አውላቂ
መብት ነጣቂ
የከንፈር ዚፕ
የብዕር ክዳን
መች አጣነው
መቆምህን ለአምባገነን ሥልጣን
ሕዝብ ርቦት “ራበኝ” ‘ዳይል
ጠምቶት “ጠማኝ” ‘ዳይል
መከፋቱ፣
መጎዳቱ፣
“እዩልኝ፣ ተመልከቱ
አይታችሁም ፍረዱኝ”
እንዳይል ….
በልሳኑ የተወተፍክ ውታፍ
በመንገዱ የተቸከልክ ችካል
እንቅፋት!!!
የአምባገነኖች “ደህነት” – የብዙሃን ሰቆቃ በር
የሰብዓዊ መብቶች ፀር።
______________
የካቲት 12 ቀን 2006 ተሻሽሎ እንደተፃፈ
Feb 19, 2014
የህወሓት አገዛዝ የስለላ ተቋም ምን ይመስላል?
ከሰው አመዳደብ ልጀመር። በከፍተኛ አመራር ላይ ከሚገኙት አድራጊና ፈጣሪዎች ከ90 በመቶ በላይ የሆኑት የትግራይ ተወላጆች ናቸው፤ ሁሉም የህወሓት አባላት ናቸው። ለህወሓት የሚከፍሉት መዋጮ ከየወሩ ደመወዛቸው ይቆረጣል። ከእነዚህ ውስጥ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆኑት የህወሓት “ነባር” ታጋዮች የነበሩ ናቸው። እድሜያቸው በርከት ያሉት ከ 60ዎቹ የዘለሉ አዛውንት ሊባሉ የሚችሉ ናቸው። የእነዚህ ሰዎች የስለላ እውቀት “ከባዶ ስድስት” ልምዶቻቸው የዘለለ አይደል። ህወሓት ያስተማራቸው ጭካኔና በሰው ስቃይ መደሰትን ነው። ለእነሱ ስለላ ማለት ሰውን በመደብደብ መረጃ ማግኘት፤ በጨለማ አድፍጦ መምታት፤ ቤትና ቢሮ ሰብሮ ሰነድ መዝረፍ፤ በተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ውስጥ አንጃዎች እንዲፈጠሩ በማድረግ እርስ በርስ ማባላት ነው።
የድድብናቸው ጥልቀት ይገርማል። አንዱ የዚሁ መሥሪያ ቤት ከፍተኛ ባለሥልጣን “ብፈልግ የአሜሪካን ዲሞክራቲክ ፓርቲ ማዳከም እችላለሁ፤ ተለጣፊ መፍጠር ምን ይከብዳል” ብሏል። እነዚህ ሰዎች ለሚሠሯቸው የተንኮልና የሸር ሥራዎች ተቀባይነት ያለው ሽፋን ለመፍጠር እንኳን አይሞክሩም። Plausible deniability የሚባል ነገር የለም። መሥሪያ ቤቶችን ከእዝ ሰንሰለት ውጭ በድፍረት በቀጥታ ያዛሉ። የስለላ መሥሪያ ቤት መሥራታቸው የሁሉም መሥሪያ ቤቶች አለቃ አድርጓቸዋል፤ ይህ የህወሓት አገዛዝ በአፍጢሙ የተደፋ የመንግሥት አደረጃጀት አቢይ መገለጫ ነው። ለምሳሌ፤ አንድ ፓርቲ አዲስ አበባ ሰልፍ ቢጠራ እና የስለላው ቢሮ አዛውንት ሰልፉ መፈቀድ የለበት ብለው ካሰቡ ለአዲስ አበባ መስተዳደር የሰልፎች እውቅና ክፍል ኃላፊ በግል ሞባይሉ ይደውሉና እውቅና እንዳይሰጥ፤ ይህንን ትዕዛዝ የሰጠውን አካል ግን እንዳይናገር ያዛሉ። ይህ የክፍል ኃላፊ በምን የህግ አግባብ ፈቃዱን እንደሚከልክል አይነግሩትም፤ የደህንነት መሥሪያ ቤት ከልክሏል ማለት ደግሞ አይችልም። እንዲህ ዓይነት አጣብቂኝ ውስጥ የገቡ ኃፊዎች በጭንቀት ቢሮ ዘግተው የሚጠፉበት አጋጣሚ ይፈጠራል። ሌላ ቀላል ምሳሌ፤ አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ለስብሰባ የሆቴል አዳራሽ ተከራይቷል። ስብሰባው ሊጀመር 1 ሰዓት ሲቀር አዳራሽ እንዳታከራይ ተብሎ ይነገረዋል፤ ይህ ውሳኔ “የደህንነቱ” መሥሪያ ቤት ውሳኔ ነው እንዳይል ማስጠንቀቂያ ይሰጠዋል። አሁን ደንበኞችን የማስቀየም ሸክም የሚወድቀው በሆቴሉ ኃላፊ ነው። እንዲህ ዓይነት ተግባር በሰለጠነ የስለላ አሰራር አሳፋሪ ነው፤ በህግም ያስጠይቃል። ተንኮል እንኳን ቢሠራ ህጋዊ አሳማኝ ምክንያት የመፍጠር ሸክም መውደቅ የነበረበት በስላላው መሥሪያ ቤት ነው።
በእድሜ የገፉት ከፍተኛዎቹ ባለሥልጣኖች ይህ ዓይነቱ አሠራር ህገወጥና ጊዜ ያለፈበት መሆኑ አይረዱም። እንዲያም በእኔ እበልጥ እኔ እበልጥ ፉክክር ውስጥ ገብተዋል። በመካከላቸው ከፍተኛ መናናቅ አለ። በአራቱ ምክትል ዳይሬክተሮች መካከል መካከል መናናቅ አለ እያንዳንዱን ፓርቲ የሚከታተል ቢሮ ከፈተዋል፤ ይህ በህጋሚ መንግድ የተመዘገቡትም ይጨራል። ፒያሳ-ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ እና እንቁላል ፋብርካ -የስደተኞች እና ከሰደት ተመላሾች ግቢ ዉስጥ ካሉት ቢሮዎቻቸው በተጨማሪ አዲስ አበባ ውስጥ safe house እያሉ የሚያቆላምጧቸው ሰዎችን አፍኖ በመውሰድ ማሰቃያ ቦታዎች አሏቸው። በ safe houses የሚሠራው ማፍያ እንጂ ሌላ ድርጅት ይሠራዋል ተብሎ የሚታሰብ አይደለም። በህግ የሚመራ፣ የሰለጠነ፣ ኃላፊነት የሚሰማው የስለላ ተቋም የሚያስመስሉት አንዳችም ነገር አታገኙም። አዛውንቶቹ በመሥሪያ ቤቱ ሥራ ላይ ከሚያውሉት ጊዜ ይበልጥ ሀብት ለማጋበስ የሚያውሉት ይበልጣል፤ ሁሉም ቱጃሮች ናቸው። የመሥሪያ ቤታቸውን መታወቂያ በቢስነስም ውስጥ ይጠቀሙበታል። መጠጥ ቤትም ውስጥም ይመዙታል። በአጋጣሚም ይሁን በቢስነስ ጉዳይ የተከራከራቸው ሰው ጠላት ነው። ከእነሱ ጋር በማናቸውም ምክንያት መጣላት ከፓለቲካ ልዪነት እኩል ነው።
ከእነዚህ ሰዎች በታች ያሉት ቆሻሻው ሥራ የሚሠሩ “ኦፊሰሮች” የሚል የመሸንገያ ስያሜ የተሰጣቸው በእድሜ ወጣቶች፣ በትምህርትም ሻል ያሉ የሚበዙበት ስብስብ ነው። እዚህ የብሄር ስብጥሩ የተሻለ ነው። ከሕዝብ ብዛት አንፃር ከታየ የትግራይ ድርሻ ከፍ ያለ ቢሆንም እንኳን የኦሮሞና የአማራ ተወላጆች በብዛት አሉበት፤ ከሌሎችም እንደዚሁ። ከእነዚህ ኦፊሰሮች አንዳንዶቹ በስልጠናም በግል ንባብም የዘመናዊ የስለላ ድርጅቶችን አሠራር የማወቅ እድል አግኝተዋል፤ እናም “አሠራራችን እናዘምን፤ ከ CIA, FBI, MI5, MI6, ከሞሳድ … ልምድ እንቅሰም፤ የመንደር ጉልበተኛ ቦዘኔ አንምሰል” እያሉ ይጨቃጨቃሉ፤ የሚሰማቸው ግን የለም።
ኦፊሰሮቹ ሰፈር የሚሰማው ምሬት ነው። ቁጥር አንድ የምሬት ምክንያት ደግሞ ገንዘብ ነው። ኦፊሰሮች ብዙ ሰው የሚገምተውን ያህል አይከፈላቸውም፤ ከሚዘረፈውም ገንዘብ አይደርሳቸውም። በትርፍ ጊዜዓቸው ሌላ ሥራ ለመሥራት ቢፈልጉም አይችሉም። በግል መማርም አይፈቀድላቸውም። የመንግሥት ሠራተኖች ይሁኑ ባሮች ግልጽ አይደለም።
ኦፎሰሮች በሥራቸው ምክንያት ከማኅበረሰቡ የተገለሉ ናቸው። ቅን ህሊናቸው አንዳንዴ በመጠጥ አንዳንዴ ደግሞ በህልማቸው ተሸፍኖ ይመጣና እረፍት ይነሳቸዋል። ሥራው ለቆ ለመውጣት ያስባሉ ግን ይፈራሉ። የአብዛኛዎቹ ኦፊሰሮች ስነልቦናዊ ሕይወት የሚገለፀው በፍርሃት ነው፤ ሁሌ እንደፈሩ ናቸው። የሚተማመኑ ሁለት ጓደኛሞች እዚያ መሥሪያ ቤት ውስጥ ማግኘት አይቻልም። ፍርሀት እጃቸው ውስጥ የገቡ ምስኪኖች ላይ ጨካኞች ያደርጋቸዋል፤ በዚህም ምክንያት ብዙ የጭካኔ ተግባር ይፈጽማሉ። በታሳሪዎች ላይ ሽንታቸውን መሽናት የመሰለ ተግባር የሚፈፅሙት እነዚህ በፍርሃት የሚባንኑት ኦፊሰሮች ናቸው። በተለይ በአሁኑ ሰዓት የኦፊሰሮች ሕይወት እየተመሰቃቀለ ነው። የኑሮ መወደድ እነሱንም አደህቷቸዋል፤ የአለቆቻቸው በሀብት መንበሽበሽ ያውቃሉ፤ ያያሉ። NGO ውስጥ ስለመቀጠር ወይም ትንሽም ብትሆን የራስ ቢዝነስ ስለመጀመር ያልማሉ፤ ከማለም አልፈው የተሳካላቸው አሉ ግን ጥቂቶች ናቸው።
ያለምንም ማጋነን የደህንነቱ መሥሪያ ቤት መረጃ ሰብሳቢዎች ከኢቲቪ/EBC ዜና አጠናቃሪዎች የተሻለ መረጃ አያመጡም። መረጃ ብለው የሚያመጧቸው ነገሮች የተሳሳቱ ወይም የተጋነኑ ናቸው። ሁሉም ኦፊሰሮችም የፓርቲ አባላት ናቸው፤ በየብሔራቸው። አብዛኛዎቹ በየመጡበት ድርጅት ሰላይነታቸው ስለሚታወቅ እዚያም መረጃ ስጡን ይሏቸዋል። አለቃቸው ፓርቲያቸው ይሁን የስለላው መሥሪያ ቤት አይታወቅም። ለሁለት አለቆች ማደር አለባቸው። ከህወሓት የመጡት ኦፊሰሮች ህወሓትን የመጠበቅ ተጨማሪ ሥራ አለባቸው፤ ሥርዓቱን የመጠበቅ የተለየ ኃላፊነት እንዳለባቸው ይነገራቸዋል። የህወሓት ደጋፊ ያልሆነ ሁሉ ጠላት እንደሆነ ነው የሚያውቁት። ከህወሓት በመጡት እና ከኦህዴድ፣ ብአዴን፣ ደህዴድ … በመጡት መካከል ከፍተኛ አለመተማመን አለ።
ከኦፊሰሮች ውስጥ የህሊናቸውን ወቀሳ እያዳመጡ ያሉ ወገኖች አሉ። መወላወሉን ትተው በቶሎ ቢወስኑ ይሻላቸዋል። የህወሓት አገዛዝ መወደቁ አይቀርም። የሥርዓቱ መበስበስ ከሚታይባቸው ቦታዎች ቁጥር 1 የገዛ ጥላውን መፍራት የጀመረው የስለላው መሥሪያ ቤት ነው። መሥሪያ ቤቱ ራሱ እንደተቋም ፍርሀት ውስጥ ገብቷል። ወደ መሥሪያ ቤቱ ጎራ የሚል እያንዳንዱ ተሽከርካሪ ታርጋው ይመዘገባል። እያንዳንዱ ኦፊሰር በሌላ ኦፊሰር ይሰለላል። ከላይ ያሉት ሽማግሌዎች የጦር ሜዳ ተረታቸውን እያወሩ የተዋጉበት ካሳ ይመስል በሀብት ላይ ሀብት ይከምራሉ። ይህ የወጣት ኦፊሰሮችን ልብ እያሸፈተ ነው።
ለእነዚህ ወጣት ኦፊሰሮች የግል መልዕክት አለኝ።
እኔ ስለላ በተለይም ኢንተለጀንስ የተከበረ ሙያ መሆኑን አውቃለሁ፤ ትምህርትና ስልጠና እንደሚፈልግም እረዳለሁ፤ አውቃለሁ። ኢንተለጀንስ ከፍተኛ የስነምግባርና የህግ ልጓም እንዳለበትም አውቃለሁ። እናንተ የምትሠሩት ግን እሱን አይደለም። እናንተ ባለሙያ የሆናችሁ ይመስላችኋል እንጂ አይደላችሁም። የምትሠሩት ሥራ እጅግ አሳፋሪ ነው። ህግም ስነምግባርም አይገዛችሁም። በግጥሜ ላይ እንደገለጽኩት እናንተ የከንፈር ዚፕ እና የብዕር ክዳን ነው የሆናችሁት፤ ይህ ሙያ አይባልም። በነፃነት መንገድ ላይ የተቸከላችሁ እንቅፋቶች መሆናችሁ መብቃት አለበት። ወገኞቼ፣ የዚህ ሥርዓት መለወጥ ጥቅሙ ለእናንተም ነው። የሙያው ፍቅርና እውቀት ያላችሁ ወገኖች የሙያውን ስነምግባር ጠብቆ ህግን አክብሮ በሚሠራ መንግሥት ሥር አገልግሎታችሁን ትቀጥላላችሁ። የነፃነት እንቅፋቶች ሳይሆን የነፃነት ዘብ ጠባቂዎች መሆን ትችላላችሁ። የፍትህ ፀሮች ሳይሆን የፍትህ ጠበቆች መሆን ትችላላችሁ። ውሳኔ መወሰን ያለባችሁ ግን ዛሬ ነው። ከቻላችሁ ለቃችሁ ውጡ፤ ካልሆነ እውስጡ ሆናችሁ አሳፋሪውን መሥሪያ ቤታችሁን ግደሉት።

በቀልድ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም። ትውልዱን እንዴት እየመረዙት እንደሆነ ልናስተውል ይገባል።



Image may contain: text
ይህ የ8ኛ ክፍል አማርኛ መማሪያ መፅሀፍ ገፅ 26 ነው ተብሎ የተለቀቀ ምስል ነው። ላሊበላን እና ፋሲል ግምብን ያነፁት አክሱማውያን ናቸው ይላል።
ጎበዝ ይህ ነገር በቀልድ ሊታለፍ የሚገባው አይደለም። ትውልዱን እንዴት እየመረዙት እንደሆነ ልናስተውል ይገባል። የሰዎቹ ተንኮል ከአይሁዳውያኑም ይልቅ የረቀቀ ሆኗል።


Sunday, September 25, 2016

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስብሰባ ወቅት ምሁራኑን ሳቅ በሳቅ ያደረገና እንባ በእንባ ያራጩ ጥቂት ነገሮች



ሳቅ እና ለቅሶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በስብሰባ ወቅት ምሁራኑን ሳቅ በሳቅ ያደረገና እንባ በእንባ ያራጩ ጥቂት ነገሮች እኒህ ነበሩ።
1 – አንዲት ሴት መምህርት ነች እጇን አወጣች እድሉን ስታገኝ “አሁን ወደ ስልጠናው ልገባ ስል ባለቤቴ ደውሎልኝ ነበር ‘ አደራሽን እናገራለሁ እንዳትይ እኔና ልጃችንን አስቢ አለኝ”….ሳቅ.. .በሳቅ…”ይሄዋ እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችሁ እንደኔ ተብላችኋል”…ሌላ ሳቅ.. ይህኔ ክቡር ሰብሳቢው አቋርጠው “እረ ይሄ ፍርሃት ተደጋገመ ምንጬ ምን እንደሆን አልገባኝም? “ሴትዮዋ ተቀብላ” እንዴ አቶ ካሳ የምርዎን ነው? ምን እንደሚያስፈራን አያውቁም? ለነገሩ ህዝቡን አታውቁትም! ምን እንደሚያስደስተው እና እንደሚያስፈራው አታውቁም። ረጅም ጭብጨባ…!

2 – ሰብሳቢ ለተነሱት ጥያቄዎች ሲመልሱ ነገር ሲያረዝሙ ጊዜ መምህራኑ በጭብጨባ አቋረጡ ይህኔ “ባካችሁ 1 ደቂቃ ብቻ” አሁንም በጭብጨባ ተቋረጠ ሲጨንቃቸው ምን ቢሉ ጥሩ ነው? “እሽ በቃ የአይጥ መንገድ ብቻ ስጡኝና ልውጣ! “በልመና በአይጥ መንገድ ወጡ።

3 – ተናጋሪው የኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስት ነው “እኔ ሀኪም እንጅ ፖለቲከኛ አይደለሁም። ግን አሁን አቶ ካሳ ሲናገሩ ‘እናየዋለን፣እናጠናዋለን ‘ብለዋል። የዛሬ 14 ዓመትም ነፍሳቸውን ይማርና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ መለስ እኔ ራሴ በተገኘሁበት ስብሰባ ላይ እንዲሁ ብሎ ነበር እና ዛሬም ከ14 ዓመት በኋላ እንደገና እናየዋለን፤ እንደገና እናጠናዋለን?” ስብሰባ ማዕከሉ በሳቅ ተወዛወዘ።

4 – ሰብሳቢው አቶ ካሳ ናቸው። ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች ሲመልሱ…ሰው ሲታገስ… ሲመልሱ..ሰው…ሲታገስ.መካከል ላይ ቦሌ አካባቢ ፎቆቹና ቪላዎቹ በአንድ ብሄር ጋንግስተሮች ተወሯል። ለሚለው ጥያቄ መልሱን ሲያብራሩ ..”ይሄን ነገር በደንብ ልንመረምረው ይገባል ፤ Rlly እንደተባለው ባንድ ብሄር ነው የሚለውን ልንፈትሸውና ልናጠናው…..” ..የሙህራኑ ሳቅ….እንጦጦ ድረስ ጮኸ።

5 – በጣም ወጣት ልጅ ነው እድሉን ሲያገኝ “ሌላ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ጓደኞቼ በመናገራቸው ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አውቃለሁ። ዝም ማለት ስላስላስቻለኝ እኔ ግን እናገራለሁ። ተናግሬ እንግዲህ የመጣውን ያው…..(ሰው በሳቅ)…እሽ ! ሰልፍ ይቻላል ተብሏል አዎ ለድጋፍ ሲሆን መኪና ተመድቦ፣ ክላሽ ተይዞ በፌዴራል ታጅቦ ይደረጋል። ችግሩ ህዝቡ ለመብቱ መሰለፍ ሲፈልግ ግን……” ምስኪን ይሄው ጥያቄው ማታ በኢቢሲ ተለቀቀለታ። እግዚኦ ነው ለቤተሰቡ
በመጨረሻም በቡድን ውይይት ወቅት(ስለ ትምህርት ጥራት ነበር ርዕሱ) አንድ ነፍሰ ጡር ሴት ተነስታ በሲቃ “ዛሬ ህዝብ እየሞተ የምን የትምህርት ጥራት ነው? ሁሉም የሚኖረው አገር ሰላም ሲሆን ነው። እኔ ለምሳሌ በዚህ ተቃውሞ ቤተሰቤን አጥቻለሁ (ሳግ እየተናነቃት) ዛሬ የስድስት ልጆች እናት የምትገደልበት፣ ልጇን ገድለው እላዩ ላይ ተቀመጭ የሚባልበት ጊዜ ላይ ተገኘን። ምነው ይሄ ታሪክ የሌላ በሆነልን፤ ምነው በሃገሬ ባይሆን ብየ ተመኘሁ ግን ሆኗል (ረጅም የሳግ ድምጽ) ሁሉም አንገቱን ደፋ፣ ግማሾቹ ዓይናቸውን በሶፍት ይጠርጉም ነበር።
ከዚህ በኋላ ነው የምሩ ሳታየር የተመለሰው መምህራኑ ስለ ሌላ አናወራም አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ብቻ ነው በማለት።

፩ኛ – ጠ/ሚኒስትሩ ያወጁትን አዋጅ ባስቸኳይ ይመልሱ፤ ወታደሩም ወደ ቦታው ይመለስ!

፪ኛ – በየቦታው የሚፈጸሙት እስራት ፣ ቶርቸር እና አፈና ባስቸኳይ ይቁም!

፫ኛ – ለሁሉም መፍትሔው የስርዓት ለውጥ ነውና የስርዓት ለውጥ እንፈልጋለን። ይሄን ብቻ በዋናው መድረክ እንድታሰሙልን እንፈልጋለን።

ዋናው መድረክ ላይ ከሰዓት ሲቀርብ አወያይ ሆየ “በኛ ግሩፕ ከተነሱት የትምህርት ጥራት ችግሮች አንዱ ……..(divert እንዲህ ነዋ!)
 ኢዮብ ብርሃነ

የውሸትና የማስመሰል ጸብ በመቀሌ ተጀምሯል።የነ ኣባይ ወልዱ ኣንጃ ከተሸነፈ ሳሞራ ዮኑስ ሊባረሩ ወይም በጡረታ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ኣለ



Amdom Gebreslasie's photo.
የነ ኣባይ ወልዱ ኣንጃ ከተሸነፈ ሳሞራ ዮኑስ ሊባረሩ ወይም በጡረታ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ኣለ
የህወሓት “ጥልቅ ተሃድሶ”(ጥሎማለፍ) !
===========
የህወሓት ሁለቱ ኣንጃዎች ” በጥልቀት ለመታደስ” ተሰብስበዋል።
ለኣዲስ ኣበባው ኣንጃ “ኣቶ ኣባይ ወልዱ ከትግራይ ክልል ኣስተዳዳሪነታቸውና ከህወሓት ሊቀ መንበርነታቸው ማውረድ የሚል ኣላማ ኣንግበው መጥተዋል።

Amdom Gebreslasie's photo.
ይህ ማሳካት ማለት “በጥልቀት መታደስ” የሚል ትርጉም ይሰጡታል ይህ እውን ለማድረግ እንደመጡም እያስወሩ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ የመቐለው ኣንጃ የተፎካካሪው ኔትወርክ ኣፈራርሶ ስልጣኑ የበለጠ ሊያሰፋና ልእልናው ሊያስጠብቅ እየተጣጣረ ነው።
የመቐለው ኣንጃ ኣቶ ኣባይ በስልጣን ማቆየት፣ የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ስልጣን ማዳከም ማሳካት ማለት በጥልቅ መታደስ ነው።
የመቐለው ኣንጃ ዋነጃ ደጋፊ ጀነራል ሳሞራ ከመባረር(የነ ኣባይ ወልዱ ኣንጃ ከተሸነፈ ሳሞራ ዮኑስ ሊባረሩ ወይም በጡረታ ሊሰናበቱ ይችላሉ የሚል ስጋት ኣለ) ማዳን የሚል ግብም ለማሳካት እየታገለ ይገኛል።
Amdom Gebreslasie's photo.
የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ኣባይ ሲያወርድ ሊፈጠር የሚችል ግርግርና ኣለመግባባት ለማረጋጋት የሚለምኑና የሚሸመግሉ የድሮ የማእከላይ ኮሚቴ ኣባላት ከያሉበት ኣሰባስበው ኣሳትፈዋል።
የኣዲስ ኣበባው ኣንጃ ወቅታዊ ፕሮፖጋንዳ “ኣዲስ ኣበባው የኢህኣዴግ ግምገማ ኣባይ ወልዱና ገዱ ኣንዳርጋቸው ከስልጣን እንዲወርዱ ተወስነዋል በውሳኔው መሰረት ኣባይ በሌላ ኣመራር መተካት ብቻ ነው” የሚል ወሬ በመንዛት የኣባይ ወልዱ ከስልጣን መውረድ የማይቀር መሆኑ እየገለፁ ይገኛሉ።
Amdom Gebreslasie's photo.
የህወሓት በጥልቅ መታደስ ዓላማ ኣቦይ ስብሓት የተነጠቁት የበላይነት ማስመለስ፤ ኣቶ ኣባይ ወልዱ በኣጋጣሚ በእጃቸው የገባው ልዕልና ኣስጠብቆ መውጣት ከሚል ትርጉም የዘለለ ኣይደለም።
በህዝባችን ዓይን የዚህ ጥሎማለፍ (ጥልቅ ተሃድሶ) ውጤቱ “ጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ ኣይጣፍጥም” እንደሚባለው ፋይዳ ቢስ ነው።

«ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይንም «የእባብ ልጅ እባብ» ያለው ጁኔይድ ሳዶ ሙሉ ታሪኩ እነሆ፤



«ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይንም «የእባብ ልጅ እባብ» ያለው ጁኔይድ ሳዶ ሙሉ ታሪኩ እነሆ፤ Achamyeleh Tamiru
«ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይንም «የእባብ ልጅ እባብ» ያለው የቀድሞው የኦሮምያ ክልል ፕሬዝደንት የነበረው ጁኔይድ ሳዶ ነው። ጁኔይድ ሳዶ «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይንም «የእባብ ልጅ እባብ» ያለው ያሁኑን የአማራ ትውልድ ነው። ሙሉ ታሪኩ እንደወረደ እነሆ፤
__________
<< «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ/የእባብ ልጅ እባብ» የሚለውን አቶ ጁነዲን ሳዶ ነበር ያሉት!!! ሰውየው ከኢህአዴግ ጋር በትልቅ የስልጣን ኮርቻ የነበሩና ዛሬ እራሳቸውን ከፓርቲው ያራቁ ወደተቃውሞም የገቡ ሊደነቁ የሚገባቸወ ናቸው። ቢሆንም ቅሉ ከመንግስት ጋር ተጣልቶ የሸሸ የድሮ ባለስልጣን ሁሉ እንደ ሀቀኛ መቁጠርና ማጀገን ግን ጅልነት ነው። የአቶ ጁነዲን ሳዶን ለአብነት እንይ ከዚህ ቀጥሎ የማወራላችሁ በጊዜው እዚያው ሰብሰባ ላይ በአካል ከነበረና የአቶ ጁነዲን ሳዶ ስም ሲነሳ እጅጉን የሚያመው አንድ ጓደኛየ ነው።
ጊዜው በ1997 ዓ.ም. የምርጫ ወቅት ነበር። አቶ ጁነዲን ሳዶ የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የሆኑትን የአዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ሰብስቦ ፖለቲካዊ ስብከት እያደረገ ነው። በሰብሰባው የነፍጠኛው ስርዓት በኦሮሞ ህዝብ ላይ ያደረሰው በደል፣ የነፍጠኛ ስርዓቱ የኦሮሞ ህዝብ ጠላትነት ብዙ ተሰበከ ከዚያም ለጥቆ አሁን ያሉት የነፍጠኛ ልጆችም ከአባቶቻቸው እንደማይለዩ እንደውም ተደራጅተው የነፍጠኛውን ሰርዓት ለመመለስ እየጣሩ እንዳሉና ይሀንን መፍቀድ አንደሌለባችው ብዙ ተባለ። በዚሁ ብዙ ሰው በስሜት ተናጠ። በመሀል አንድ ተማሪ ተነስቶ «ታድያ የዛሬ መቶ ዓመት የነበረን ነገር ካሁኑ ጋር እንዴት በቀጥታ ማገናኘት ይቻላል? እንዴት ያሁኑ የአማራ ተወላጆች ከዚያኛው ጋር በቀጥታ መገናኘት ተጠያቂም ማድረግ ይቻላል?” ብሎ ጠየቀ።
አቶ ጁነዲን ሳዶ የሰጡት መልስ እጅግ አሸማቃቂ ነበር። ቃል በቃል «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ/ የእባብ ልጅ እባብ» ነበር ያሉት። እጅግ አደገኛና መሰሪ አገላለፅ ነበር ያስፈራል! እንደነጁነዲን ሳዶ ዐይነቶች ጥላቻን የሚዘሩና ሌላ በርካታ በደል በህዝብ ላይ ያደረሱ ሰዎች ከመንግስት ጋር ተጣልተው መፅሐፍ ፅፈው ወይም በሌላ መልክ ተከስተው ይቅርታ ቢጠይቁ እንደኔ ተቀባይነት ያለው አይመስለኝም።>>
––––––––––
አቶ አሰፋን እጅግ እናመሰግናለን። ምንም እንኳ ሰውየውን የምናውቀው ብናውቀውም እሳቸው ደፍረው ይህንን የጁኔይድ ጉድ ባይነግሩን ኖሮ «የእባብ ልጅ እባብ» ብሎ እባብ ያደረገን ጁኔይድ ትናንት ወያኔ አላምጦ ስለተፋው ዛሬ እንደ እስስት መልኩን በመቀየር ህዝባዊ መስሎ የአዞ እንባ እያነባ የዋህ መስሎ ሊታይ «ቢሞክር ጅብ በማያውቀው አገር ሂዶ ቆርበት አንጥፉልኝ አለ» እንለዋለን።
የጋሽ አሰፋን ጽፉፍ ካነበብሁ በኋላ ጁኔይድ ትናንትና በአሜሪካ ድምጽ የአማርኛው ክፍል ያደረገውን ቃለ ምልልስ ካደመጥሁ በኋላ ዛሬ በሶስት ነገሮች ብቻ «ይቅርታ!» የጠየቀው ሰውዬ ትናንትና ያን ሁሉ አጥፍቶ ይቅርታው አልከበደውም ወይ ብዬ ትናንትና የተናገራቸውን ንግግሮች ፍለጋ ገባሁ። አንዱን ከታች ለጥፌዋለሁ። በዚህ ንግግሩ ውስጥ «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ/ የእባብ ልጅ እባብ» የሚለው ንግግሩ በኮድ ስም አለ። ወደ ድሮው ስርዓት ሊመልሱን ምናም የሚለው የኮድ ንግግር ነው። በዚህ የኮድ ንግግር ጁኔይድ እነ ልደቱን እያለ ያለው «ኢልሜን ቦፋ ቦፋደቴ» ወይም «የእባብ ልጅ እባብ» ነው።
ጁኔይድ ሳዶ ትናንትና በአሜሪካ ድምጽና በኦ.ኤም.ኤን የሰጠውን ላዳመጠ አሁን ይህንን ከታች ያተምሁትን ንግግር ከስድስት አመታት በፊት የተናገረው ነው ቢሉት ማን ያምናል? ይህንን ንግግር ይቅርታስ ያነጻዋል?



Saturday, September 24, 2016

አባሎቻችንና ሌሎች ዜጎች ከሕግ ውጭ እየታሰሩ ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ



አባሎቻችንና ሌሎች ዜጎች ከሕግ ውጭ እየታሰሩ ነው ሲል ሰማያዊ ፓርቲ ከሰሰ
በመላው ሀገሪቱ የሰማያዊ ፓርቲ አባሎችና ሌሎችም ዜጎች ከሕግ ውጭ በሆነ አያያዝ በገፍ እየታሰሩ መሆናቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ፕሬዝዳንት ተናገሩ።
በተመሳሳይ ሁኔታ ከ20 የማያንሱ ዜጎች ከሕግ ውጭ በምዕራብ ኦሮምያ በጅማ ገነት ወረዳ መታሰራቸውን አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ ወኪል ገለጹ።
ከመንግሥት በጉዳዩ ላይ ለጊዜው ማብራርያ ለማግኘት አልተቻለም።
በኦሮምያና በአማራ ክልሎች የተቃውሞ ሰልፎች መካየድ ከጀመሩ በኃላ በአጠቃላይ በሀገሪቱ ውስጥ በዜጎች ላይ እየተካሄዱ ነው ያሉት የአፈና እርምጃዎች እየተባባሰ መሆኑን በመግለጽ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት መንግሥትን ከሰዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/09/23/7d0edaac-75aa-4c66-9b40-d0e20479a612.mp3
Vm
P

ፋይል- የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ-መንበር አቶ ይልቃል ጌትነት

የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሉ ኣምባገነንና ኣሮጌ ስርዓቶችን ለማስወገድ ኣዲስ ኣይደለም። ሕወሓት መራሹን ኣገዛዝ እስካልጣልን ዘንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሰላምና ነጻነት አናገኝም።



ሕዝቤ ሆይ :- ሕወሓት መራሹን ኣገዛዝ እስካልጣልን ዘንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሰላምና ነጻነት አናገኝም። የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሉ ኣምባገነንና ኣሮጌ ስርዓቶችን ለማስወገድ ኣዲስ ኣይደለም።
Image may contain: 3 people , text
ሕዝቤ ሆይ :- ሕወሓት መራሹን ኣገዛዝ እስካልጣልን ዘንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ሰላምና ነጻነት አናገኝም።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕወሓት ወንጀለኛ ነው። ነጋሪ ኣንፈልግም። አሁን የሚያስፈልገው ሕዝቡን በጋራ ኣያይዞ ሕወሓት የሚባለውን ማፊያ መሰሪ በቀለኛ ጸረ ሰላምና ጸ ሕዝብ ሰው በላ ኣገዛዝ ማስወገድ ብቻና ብቻ ነው። ለዚህም ነው የስርዓት ለውጥ ያስፈልጋል ብለን እየጮኽን ያለው።ለዚህም ነው ሕዝባዊ መንግስት ያስፈልጋል ብለን እየጮኽን ያለነው።ለዚህም ነው በዘርና በመንደር መቧደን ቆሞ በጋራ የሕዝቦች እኩልነት የተረጋገጠባት ኢትዮጵያ ትመስረት እያልን የምንጮኸው።ለዚህም ነው በኣንድነት በባንድራ በሃገር ወዳድነት ሽፋን ሕዝብ እንዳይረገጥ በጩኸት በማስፈራራት ከኛ በላይ ላሳር የሚል ስሜታዊ የጡዘት ፖለቲካ ይቁም እያልን ኣምባገነነኦችን ለሜጣል ላሌመፍጠርም እየታገልን ያለነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያውያን በመላው ሃገሪቱ ተዘዋውረው የመስራት መብታቸው ይከበት ብሌን የምንታገለው።ለዚህም ነው ግድያና እስር ቆሞ በመከባበርና በመቻቻል ፖለቲካ ኣገር ትመራ ብለን የምንጮኸው በኣጠቃላይ ለሕዝብ ነጻነትና መብት መከበር ስኬት ለፖለቲካና ኢኮኖሚ ሰላም መረጋገጥ ሕወሓት መወገድ ኣለበት።
የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግሉ ኣምባገነንና ኣሮጌ ስርዓቶችን ለማስወገድ ኣዲስ ኣይደለም። በደሃው ገበሬ ላብ ሲኖር የነበረውን የጥቂት መሳፍንቶችና የራስ ተፈሪ መኮንንን ፊውዳላዊ ጨካኝ የሆነ ኣገዛዝ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዳር እስከዳር በመንቀሳቀስ ራሱን ንጉስ ኣድርጎ የሾመውን ኣገዛዝ ያስወገደ ቢሆንም በጣልቃ ገብነት የመጡት ወታደራዊ መኮንኖችም ለሃገርና ለወገን ይጠቅማሉ የተባሉ ዜጎችን ደም በመጠጣት በማሰር በማሳደድ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በመስራት በሃገር ኣንድነትና በባንድራ ሽፋን በግዳጅ ወጣቱን ለስልጣናቸው ማቆያ በመማገድ ሲተጉ የኢትዮጵያ ሕዝብ ዝም ብሎ ኣላየም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች በተከፈሉ መስዋትነቶች ደርግ ላይነሳ የተንኮታኮተ ሲሆን ይህን ተከትሎ ስልጣን ላይ የወጡት ዘረኛ ዘራፊ መንደርተኛ ተሳዳቢ ገዳይ እጅግ ጨካኝና በመሳሪያ ብቻ የሚተማመኑ የሕወሓት ኣምባገነን ኣመራሮች ስልጣኑን ተቆጣጥረው በዲሞክራሲና በልማት ሽፋን ሕዝቦችን ለከፍተኛ ሰቆቃ ከመዳረጋቸውም በላይ ኢትዮጵያ በዘመኗ ተፈራርቀው የነበሩ መንግስታት ያልሰሩትን ወንጀሎች በሕወሓት እየተሰሩ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ በዘረኞች እየተፈጸመ ነው።
ስለዚህ እነዚህም ጨካኖች በሰለጠነ ዘመን ያልሰለጠኑ ዘረኞችን ተባብረን ማስወገድና ለመጭው ትውልድ መብት ነጻነት እና እኩልነት የተረጋገጠባትን ኢትዮጵያ ለማስረከብ የዜግነት ድርሻችንን እንወጣ። #ምንሊክሳልሳዊ

Friday, September 23, 2016

የትግራይ ወያኔ ሌባ ነው የሚለው የኢቶዮጵያ ህዝብ እዉነታነቱን እራሱ ወያኔ በድጋሜ መሰከረ

  


የትግራይ ወያኔ ሌባ ነው የሚለው የኢቶዮጵያ ህዝብ እዉነታነቱን እራሱ ወያኔ በድጋሜ መሰከረ
——————————————————————-
ባለፈው ወር አካባቢ ወያኔ ባወጣው የልሳኑ መግለጫ በስልጣን ላይ ያሉ አባላት ስልጣናቸዉን መከታ በማድረግ ህዝብን ከማገልገል ይልቅ የግል ጥቅማቸዉን በማሳደድ ሃገርን መዝረፍ ስራየ ብለው ይዘዋል ብሎ በግልጽ ወያኔ የሌባ ድርጅት መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናገረ። አሁንም እንደገና በ ፩፱፱፰ (1998) አመተ ምህረት አሳትሞ ትምህርት ሲያስተምርበት የነበሩት መጽሃፎች የሃገሪቱን የተለያዩ ክልሎችን በተለይ የአማራዉን ክልል ዙሪያዉን ተቀራምተው አሳንሰው በመሳል በትክክል ያላስቀመጠና ትልቁን የኢትዮጵያን ራስ ደጀን ተራራርን ከጎንደር አዉጥተው ትግራይ ዉስጥ ነው ብለው ለአመታት ሲያስተምር እንደነበርና ይህ በስተት መሆኑን ይቅርታ እንጠይቃለን መጽሃፎቹንም አስተካክለን ልከናል አሉ። ይህ አይደለም ሌባ ማለት? ይሀን ያህል አመታት እንዴትስ ሆኖ ነው መምህራኖች ይሀን ሲያስተምሩት የነበሩት፤ ራስ ደጀን ትግራይ ዉስጥ ነው ብሎ ማስተማር? በመምህርነት የሰለጠነ ሰው ዉሸትን እንደ እዉነት አምኖ እንዴት ይሀን ያህል አመታት ያስተምራል? ምንስ አይነት መምህር ነው? የትግራይ ዋና ከተማ ደደቢት ነው ብሎ የተጻፈዉን መጽሃፍ እንዴት ነው አስተማሪው ይሀን ከማስተማሩ በፊት ይህ ነግር እዉነት አይደለም ብሎ መጠየቅ የማይችለው? ነው ወይስ ደደቢት የትግራይ ዋና ከተማ መሆኑን ወይም አለመሆኑን አያዉቅም ወይም እንዲሆን ስለሚመን ዝም ብሎ የተጻፈዉን ዉሸት ያስተምራል? እኔ የሂሳብ አስተማሪ ነኝ፤ እንዴት ሆኖ ነው መጽሃፍ ላይ ፩+፪ = ፩፪ ባገኘው ይህ ትክክል ነው ብየ ዉሸትን እያስተማርኩ ሂሳብ አስተማሪ ነኝ የምለው? ትምህርቱስ እንዴት ነው የሂሳብ ትምህርት የሚባለው ተማሪዉስ ምን አይነት ነው ይችን ትንሽ ነገር እንኳን ስህተት መሆኑን ማየት የማይችለውና ስህተት መሆኑን ለመናገር የማይሞክረው? ሂሳብ እዉነትን የምናረጋግጥበት የጥናት መስክ እንጅ ዉሸትን የምንማርበት አይደለም ። ማነው ነው ተጠያቂዉ ይሀን ዉሽት ተምሬአለሁ ብሎ ይዞ ወጥቶ ሃገርን በዉሸት የሚያምስና የሚያበጣብጥ እንደነ መለስ ዜናዊና የወያኔ ቁጭበሉወች? ለዚህ ነው ወያኔ ሌባ እያለ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናገረዉና የወያኔን ትክክለኛ ባህሪ የሚገልጸው ። የትግራይ ወያኔ የራሱ ያልሆነን ነገር በመዝረፍ የራሱ በማድረግ ሃብትና ንብረት ማግበስበ ሞያው ነው አሁን እንደታየው የንብረቱ ባለቤቶቹ አምርረው ከጠየቁ በስተት ነው ብሎ መመለስ ነው። አሁንም ወልቃይት ጠገዴ፤ራያ፤መተከል ሁሉም ወደ አማራው መልሰናል ይቅርታ በስህተት ነው ይህ ሁሉ ወንጀል በደልና ግፍ የፈጸምነው ብለው ብቅ ይሉ ይሆናል፤ ግን አሁን ያን ማድረጉ ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮሀ ነው፤ ከብዙ ወንጀል በኋላ ዘግይቶ የመጣ መፍትሄ መፍትሄ ሳይሆን ራስን ለማዳን የሚደረግ ጥረት ነው፤ በዚህም ምክንያት እርምጃው ተገዶ የሰዉን ንብረት መመለሰ ብቻ ሳይሆን ለዘረፋ ለአድሎ ለግድያና ግፍ መፈጸሚያ መሳሪያ ያደረገውን ስልጣኑን እንዲለቅና ፍትሃዊ እርምጃን ለመቀበል ዝግጁ መሆን ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በሌባ መታሰር፤ መገደል፤ መዘረፍና ሌቦች በቅንጦት እየኖሩ የንበርቱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ግን በድህነት ብግፍ በስራትና ብግድያ የሚኖርበት ዘመን ማቆም አለበት፤ የህዝቡም ጥያቄና ተጋድሎ ይሀንን እዉን ለማድረግ ብቻ ነው።

መስከረም 11—2009 ዓ/ም— በደ/ብርሃን ዩኒቨርስቲ የአድሀሪው ወያኔ መድረክ መሪዎች በእምባ ሲራጩ የዋሉበት ቀን




Bilderesultat for debre berhan university






መስከረም 11—2009 ዓ/ም— በደ/ብርሃን ዩኒቨርስቲ የአድሀሪው ወያኔ መድረክ መሪዎች በእምባ ሲራጩ የዋሉበት ቀን 3ኛ ቀኑን ያስቆጠረው የወያኔ የከፍተኛ ት/ት ተቋማት ምሁራንና ሰራተኞችን አትኩሮት የማስቀየስ የውይይት መድረክ ዛሬ ብዙዎችን በእምባ ሲያራጭ ውሏል።
በተለይም በደ/ብርሃን ዪኒቨርስቲ በወያኔ ካድሪዎችና አጎብጓቢዎች የተመራው መድረክ ሳያምኑበትና ውስጣቸው ሳይቀበለው በአረመኔዎቹ የድርጅቱ ከኛ በላይ ላሳር ባዮች የተሰጣቸውን ተልዕኮ በዪኒቨርስቲው ማህበረሰብ ላይ ለመጫን የሚሞክሩትን የመድረኩመሪዎቹን ሳይቀር አስለቅሷል።
ነገሩ እንዲህ ነው በዪኒቨርስቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ስር በተማሪዎች መኝታ ቤት ኦፊሰርነት የምትሰራው ወጣት መልካም በአማራነቷ የምትኮራ በትውልዷ ጎጃሜ ናት።ሆኖም ይህን እንዝህላል መንግስት/መንግስት ስለው ይከብደኛል ይህን የደደብ ራስ ወዳዶች የዘራፊ ባንዳዎች ጥርቅም/ተቃውመው የህብረተሰቡን ጥያቄ አንግበው ወደ አደባባዮች የወጡ 4 ወንድሞቿ 4 የአጎቶቿ ልጆች በድምሩ 8 የቤተሰቧ አባላት የደረሱበት አልታወቀም።
ይህንንናሌሎች መብታቸውን ለመጠየቅ በሚል ወደ አደባባይ ወጥተው የነበሩ የህዝብ ልጆች በህዝብ ደም በደነደነው ወያኔ ሰለባ መሆናቸውን ጠቅሳ ፍረዱኝ ቤተሰቦቼን መልሱልኝ ፍትህ ለኢትዮጵያ ህዝብ ማለቷ ነበር መላውን ተሰብሳቢ በእንባ ያራጨው። መድረኩን ሲመሩ የነበሩት የዩኒቨርስቲው ፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ባዪ ጌታሁን እና የጤና ኢንስቲቲዪት ዳይሬክተርና መምህሯ ወይዘሮ ሶደሬም ሲቃ እየተነነቃቸው የእንባ ዘለላ ከፊታቸው ዱብ ዱብ ሲል ታይተዋል።
ከ110 በላይ ተሰብሳቢዎችን ሲመሩ የነበሩት እነዚሁ ሰዎችም መሪ ተብዬው ደንባራው ኃ/ማሪያም/ስሙን ሞት ይጥራውና/በግብታዊነት የተናገረውን የእርምጃ ይወሰድ ትዕዛዝ ከማውገዝም በሻገር አንቀበለውም እኛም አናምንበትም ሲሉ አቋማቸውን አሳውቀዋል።
የኢትዮጵያውያን ደም መቼም ደመ ከልብ ሆኖ አይቀርም!!! እንዋጋለን በዳዮቻችንን እንፋረዳለን!!! ትግሉ ተጠናክሮ ይቀጥላል!!! ድል ለሰፊው የሃገሬ ህዝብ!!!