Monday, September 26, 2016

በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም አደራሽ በነበረው ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለቀሰ፤

   Bilderesultat for ato gedu andargachew


በአብቁተ አደራሽ በነበረው ስብሰባ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው አለቀሰ፤
የባህር ዳር ከተማ ወጣት ተወካዩችን በአማራ ብድር እና ቁጠባ ተቋም (አብቁተ) የመሰብሰቢያ አዳራሽ በወቅታዊ አገራዊ ጉዳይ ባወያየበት ሰዐት ከወጣቶች የተሰነዘረው አሰተያየት የክልሉን ፕሬዝዳንት አስለቀሰ፡፡

ከተሰበሰቡ ወጣቶች መካከል ‹‹እኛ ስለአማራ ሕዝብ ቆሰልን፤ ሞትን፤ ተገደልን፤ ደማችን አፈሰስን አንተስ ለእኛ ለአማሮች ምን አደረክልን? እኛ ጓደኞቻችንን ቀብረናል፡፡ የሞተው ግን ያንተም ወንድም ነው፡፡ በዚህ ስዓት ብር ሸለቆና ሰባታሚት በቶርቸር ስነ ልቦናቸው የሚሰለቡት የእኛ ወንድሞች ናቸው፤ አንተ መቼ ነው የምትደርስልን?›› በማለት በስሜት ሲናገር ገዱ አለቀሰ፡፡ እንባውን አዝረከረከ፡፡ ከማይግራፎኑ ድመፁ ጎልቶ ተሰማ፡፡


ሌላኛው ተወያይ ወጣት መነጋገሪያውን ተቀበለ ‹‹አዎ ገዱ ለሞቱት አንተም ብታነባ የተሻለ ነው፡፡ እኔ እልሃለሁ፡፡ አማራን እየኖርክበት አላወከውም፡፡ አማራ መቸም ቢሆን ሀብቱን ብትዘርፈው ይቅር ይልሃል፡፡ ወንድሙን ልጁን ገለህ፤ ደሙን አፍሰህ ግን ይቅርታ አያደርግም አማራ ደምን በደም እንጅ መቸም ቢሆን የደመ ቂሙን አታደርቀውም፡፡ ልጁንም ደም መላሽ እያላ ያሳደገ ሕዝብ ነው፡፡ አንተስ ስታስበው ደማቸው የፈሰሰው ወንድሞቻችን ባክኖ የሚቀር ይመስልሃል? እኛ ዝም ብንል የእነሱ ቤተሰብ እንደትስ ዝም ሊሉ ይችላሉ? ከሞተው ደም ይልቅ፤ ካሳ የተከፈለው እኮ ለፈረሰው የአበባ ልማት ነው፡፡ አትሉንም እንጅ ብትሉንም ነፍስን በገንዘብ አንቀይርም፡፡ የአንድ ሰው ህይዎት ዋጋውስ ስንት ነው? ለማንኛውም ስሙን ለመጥራት አንፈልግም አንተ እና ያ ተላላኪ አንዴ በአማራ ህዝብ ላይ ሞት በቃላችሁ አውጃችኃል፡፡ የወንድሞቻችን ደም በእናንተ እና በሥርዓቱ ላይ ነው፡፡ ይቅርታ ለማድረግ እና አብሮ ለመሆን እንዴት ይቻለናል?››


ወይይቱ ወደ ባሰ ጭቅጭቅ በማምራቱ ያለመፍትሄ የባህር ዳር ወጣቶች ስብሰባው ጥለውት በመውጣታቸው ተበትኗል፡፡

No comments:

Post a Comment