Friday, September 23, 2016

የመምህራን ተቃውሞ በማስጠንቀቂያ በከባድ ትችትና በእንቅልፍ ታጅቦ ቀጥሏል።  


Minilik Salsawi's photo.
የመምህራን ተቃውሞ በማስጠንቀቂያ በከባድ ትችትና በእንቅልፍ ታጅቦ ቀጥሏል።
#Ethiopia #EthiopiaTeachers #EthiopiaProtests #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በኣዲስ ኣበባና በኣንዳንድ ክልሎች የሚካሄዱ የወያኔ መጭው ያስፈራኛል ለመምህራን የሚሰጥ ስልጠና ቀመስ የሆነ ስብሰባ በተቃውሞ እየታሸ መምሕራን ለወያኔ ኣገዛዝ በሚሰጡት ማስጠንቀቂያና የሰላ ትችት ታቦ መዋሉ ሲታወቅ በተወሰኑ ኣደራሾች የመድረክ መሪዎችን ያስደነገጡ ቡድናዊ ተቃውሞዎች ተነስተው እንደነበር ተጠቁሟል።
ከኣዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስንጀምር በዛሬው እለት የዩንቨርስቲው መምህራን መስከረም 12 2009 ዓ።ም በዋነኝነት ያነሷቸው ሦሰት ጉዳዬች፥፡
* ኦሮምኛ እንደ አንድ የቋንቋ ትምህርት በአዲስ አበባ ከተማ እና በአማራ ክልል በሚገኙ ትምህርት ቤቶች መስጠት እንዲጀመር ጠይቀዋል፥፥
* 1 ለ 5 የተባለው አደረጃጀት የዩኒቨርስቲውን የመማር ማስተማር ሂደት ወደ ሗላ እየጎተተ መሆኑን አስረድተዋል፥፥
* የዩኒቨርስቲው ከማንኛውም ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ የመሆን መሠረታዊ መርህ እንዲከበር ጠይቀዋል።
Minilik Salsawi's photo.
በደብረ ብርሃን ከተደረጉ የመምህራን ስልጣናዊ ስብሰባዎች ኣብዛኛዎቹ እየተበተኑ ሲሆን በኣንዱ ኣደራሽ ግን ኣንዲት እንስት መምህር በሰጠችው ኣስተያየት የተነሳ የመድረኩ መሪዎች በእምባ ታጅበው ስብሰባውን መበተናቸውን ከተሳታፊዎች የተላከ መረጃ ጠቁሟል፤ ዝርዝሩ ከዚህ ሊንክ ይገኛል። http://www.mereja.com/amharic/514976
Minilik Salsawi's photo.
በኣዲስ አበባ ኣንሰበሰብም ያሉ በገርጂ በኣዲሱ ገበያ በመካኒሳ በኣራዳ ኣከባቢ ያሉ መምህራን ከሰዓት በኋላ ያለው የኣበል ክፍያ እንደሚቆረጥ ቢነገራቸውም የሙሉ ቀኑንም ውሰዱት ኣንፈልግም በማለት ኣተካራ ገጥመው ሳይስማሙ የከሰዓት በኃላው ስብሰባ መበተኑ ታውቋል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቡድን እንዲወያዩ የተደረጉ መምህራን የጋራ ኣቋም በመያዝ የመድረኩን መሪዎች ግራ ኣጋብተው ኣሳፍረው ዝም ኣሰኝነዋል። ሁለት ሺህ መምህራን ኣበል ኣልተከፈላቸውም። የሚለው መረጃ መውጣቱን ተከትለው ድሮም ኣገዛዙ ኣጭበርባሪ ነው የከፈሉንም በተዘዋዋሪ ይወስዱታል በማለት መምህራኑ ተናግረዋል።ከኣበል ጋር በተያያዘ ከባድ ፍጥጫ መጀመሩ ሲታወቅ መምህራኑ ለወያኔ የሚሆን መልስ ኣናጣም
በማለት በግልጽ ዝተዋል።
Minilik Salsawi's photo.
በቦሌ ኮሚኒቲ ስኩል በተካሄደው ስብሰባ ስብሰባው ኣሰልቺ ከመሆኑ የመጣ ኣብዛኛው መምህራን በተለይ ሴቶቹ ከመተኛት ኣልፈው ሲያንኮራፉ እንደነበር የሚናገሩት ተሳታፊዎች በኣብዛናው መድረክ ወያኔ ሙድ መያዣ መሆኑንና ከልቡ ስብሰባውን የሚከታተል እንደሌለ ታውቋል፤ የመድረኩ መሪዎች በድካም ሲንገላጀጁ የተከፈተው የኣዲስ ኣበባ መስተዳደር የትምህርት ቢሮ የፕላዝማ ቲቪ ስርጭት ላይ እንደተለመደው የቀድሞ መንግስታትን በማጣጣል ስለ ወያኔ ጻድቅነት ሊሰብኩ ማንም ኣዳማጭ ባለመኖሩ እንዲዘጋ መደረጉ ታውቋል። እንዲሁም መምህራኑ ለምሳ ከወጡ በኋላ ኣንገባም በማለት መሰላቸታቸውን ኣሳይተዋል።
=============================
ይቀጥላል።

No comments:

Post a Comment