Wednesday, December 28, 2016

በአገሪቱ ለሚታየው ፖለቲካዊ ቀውስና ህዝባዊ እምቢተኝነት ዛሬም የፕሮፖጋንዳ መፍትሄ ?ቆንጅት ስጦታው



በአገሪቱ ለሚታየው ፖለቲካዊ ቀውስና ህዝባዊ እምቢተኝነት ዛሬም የፕሮፖጋንዳ መፍትሄ ?
የህወኃት/ኢህአዴግ የ25 ዓመታት ጭቆና የወለደው ብሶት በአገራችን አራቱም አቅጣጫዎች ከህዝብ የወጣ በህዝብ የተከወነና የተመራ የህዝባዊ እምቢተኝነት ተቃውሞ እንቅስቃሴ ለኣመታት መደረጉ አይካድም ፡፡ ከህገመንግስት ዝግጅት አንስቶ ከጅምሩ ህዝብ ያሰማውን ተቃውሞና የመገለል ስሜት አቆይተን ከምርጫ 2002 ወዲህ የተከሰሰቱትን የቅርቦቹን በጥቅል ብንመለከት እንኳ–
1. የሙስሊም የእምነት መብት መከበር ጥያቄና ለዓመታት የዘለቀ ጠጠር ያልተወረወረበት ሰላማዊ ህዝባዊ እንቅስቃሴ፤
2. በኦሮሚያ ፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን የመሬት ወረራና የነባር ባለይዞታ ገበሬዎችን የማፈናቀል ተቃውሞ፤
3. የደቡብ ኦሞ የሃመር ወጣቶች ዓመታት ያስቆጠረው የሰብዐዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ጥያቄ፤
4. የኦሮሚያ ከላይ የህዝብ ተቃውሞ እንደገና ማገርሸትና የህዝባዊ የተቃውሞ እንቅስቃሴው ያለመገታት ፣
5. የቁጫ፣ የኮንሶና የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ የማንነትና አከላለል ጥያቄ ፣….. እናገኛለን ፡፡
ለእነዚህ ሰላማዊና ህገመንግስታዊ የመብት ጥያቄዎችና የህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች መንግስት ምን እና እንዴት ምላሽ ሰጠ ? በውጤቱስ ምን ተከተለ ? ችግሩ ተፈታ ወይስ ችግሩን ‹ለሚያዳፍን › ለአስቸኳይ አዋጅ ዳረገን ? …እያልን በርካታ ጥያቄዎች ማዥጎድጎድ ይቻላል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎችና ህዝባዊ ተቃውሞዎች ዘላቂና አካታች መፍትሄ በሚፈልጉበት ወቅት ላይ የመገናኘታችን እውነት የጋራ ሥምምነት የተደረሰበት ቢመስልም በመፍትሄው ላይ ግን ለዋናው የችግሮች ምንጭና መንስኤ /ህወኃት/ኢህአዴግ/ ሽፋን/ከለላ ለመስጠት ‹ ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ › እንዲሉ በተቃዋሚዎች የውስጥ ችግሮችና ድክመቶች ላይ ‹ትኩረት › ማድረግ ተይዟል፡፡ ለዚህም እንዲህ እንጠይቃለን፡፡
ተቃዋሚ ፓርቲዎች ድክመት፣ የውስጠ- ዲሞክራሲ ፣የአቅም ፣አደረጃጀት፣ … ውስንነትና ችግሮች እንደተጠበቁ ሆነው-
1. በተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹ ሰርጎ በመግባት፣ በህግ/አዋጅ በማፈን ፣ በእስራት፣ ማስፈራራትና ግድያ ፣….. ዕድገታቸውን ያቀጨጨው ፣ እንቅስቃሴኣቸውን የቀየደው ማነው?
2. የዲሞክራሲ ተቋማት ለዲሞክራሲ ሥርዓት ያላቸውን አበርክቶ በአዋጅ የገደለው፣… የዲሞክራሲ ዕድገት ሂደት ነው እያለ ‹ የዲሞክራሲ አቀንጭራ › የሆነው ማነው ? የህዝብ መገናኛ ብዙሃንን በቁጥጥሩ ሥር አውሎ፣ መያዶችንና ነጻውን ፕሬስ በአዋጅ ቀይዶ የኃሳብ ልዩነቶችን ፣ፍጭቶችን ያፈነው ማነው?
3. ከውይይትና የኃሳብ ፍጭት ይልቅ ‹‹ ከፈለጋችሁ ‹መንገዱን ጨርቅ › ያርግላችሁ›› እያለ ጦርነት ሲጣራ የኖረው ማነው? የውይይትና ብሄራዊ መግባባትና ዕርቅ ጥሪ ሲቀርብለት ‹ማን ከማን ተጣላ› በማለት ሲያሾፍ የከረመው ማን ነው ?
4. በህገ መንግስት የተደነገጉ የዲሞክራሲ ተቋማትን /ምርጫ ቦርድ፣ ሰብዐዊ መብት ኮሚሽን ፣ እንባ ጠባቂ ፣ ጸረ-ሙስና …/ የራሱ ንብረት አድርጎ የህዝብ አሜነታ ያሳጣው ማነው?
5. ‹የመንግስት ሥልጣን ከኢኮኖሚ የበላይነት አይነጣጠልም› በሚል ፖሊሲ እየተመራ የኢኮኖሚ ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የማይቻል ያደረገውና በኢኮኖሚ ልማት አውታሮች ላይ ጥፋት የጋበዘው ማነው ?
6. ፖለቲካ ማጭበርበር ፣ማታለል፣ በቃል አለመገኘት ፣ክህደትና ውሸት … እንደሆነ በተደጋጋሚ የገባውን ቃል እያጠፈ፣ በአደባባይ ህዝብን እየዋሸ ፣ የማይተገበር ዕቅድ እየነደፈ ( ባድሜ……፣ከሰማይ በታች ….. ተሃድሶ… ጥልቅ ተሃድሶ…) ለህዝብ ያስተማረው ማነው ?… ህዝብን በምርጫ ፖለቲካ ተስፋ ያስቆረጠው ማነው?
7. የወጣቱን ችግር እፈታለሁ እያለ…ነገር ግን እየሰደበ ያለው ማነው ? ለመሆኑ በድንገት ተነስቶ 10 ቢሊዮን ብር መደብኩ ያለው መንግስት በኦሮሚያ ብቻ ሥራ ይፈጠርለታል ለተባለው (ኢቢሲ/ኢቲቪ ታህሳስ 13/09 ዓም) 4.3 ሚሊየን ወጣት ብቻ ቢውል ለአንድ ወጣት የሚደርሰው 2 325 ብር መሆኑን ስናስብ ማታለል/ የህዝብ ንቀት ባለቤት ማነው ?
8. ህገመንግስቱን እየረገጠ፣ እየሸራረፈና እየደፈጠጠ ያለውና ህገመንግስታዊነትን ‹የተስፋ ዳቦ› አድርጎ ለአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ያበቃን፣ ጥላቻንና አድሎኣዊነትን በመዝራት ለዘረኝነትና ጠባብነት በሩን የከፈተው ማነው ? ሲጠቃለል፡- የሁሉም መልስ ህወኃት/ኢህአዴግ ህገመንግስቱን በመጨፍለቅ የፈጸመው ነው፡፡ ይህ በሆነበት፡-
በአገራችን ለሚታየው ፖለቲካዊ ቀውስ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን ድክመቶችና ችግሮች በሽፋንነት ሣያነሱ፣ህገመንግስቱን አክብሩ ሳይሉ ገዢው ፓርቲ/መንግስት በብቻውና በራሱ የፈጸማቸውን ስህተቶችና በዲሞክራሲ ሂደት ላይ ያበጃቸውን ጋሬጣዎች በማንሳትና እነዚህን በማስተካከል ብቻ ሊገኝ የሚችለውን ለውጥ ማሳየት አይቻልምን? እንዲያው የተቃዋሚዎች ድክመት ህዝብ ለሚጠብቀው ዘላቂ መፍትሄ ያላቸውን ብቃት፣ ዝግጅትና ቁርጠኝነት እንዲሁም የጠራ ሃሳብና የአቋምና የፖለቲካ መፍትሄ ወጥነት አጠያያቂ ያደርግ ከሆነ እንጂ እስካሁን በአገራችን ለታዩት ችግሮች እንደምን በምክንያትነት መቅረብ እንደሚችልና ለዘላቂ መፍትሄው ያለውን ፋይዳ በግልጽ ብንወያይበት መልካም ነው፡፡
በ1986 በግዮን ኮንፍረንስ ያነሳውንና እስከዛሬ የቀጠለውን የሠላምና ዕርቅ ተቀራርቦ የመነጋገር አጀንዳ እንደአዲስ ግኝት አንስቶ ባለቤቱን የተቃውሞ ጎራ ህገመንግስት እንዲያከብር መወትወት ወደ መፍትሄው ያደርሰናል? እንነጋገርበት፡፡

Egypt warns Ethiopia . ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች።ቆንጅት ስጦታው

  


#Egypt warns #Ethiopia . ግብጽ ኢትዮጵያን አስጠነቀቀች።
የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በሀገር ውስጥ የተነሳውን ህዝባቂ አመጽን ተከትሎ በተደጋጋሚ የግብጽ መንግስት እጅ አለበት ሲሉ መደመጣቸው ይታወቃል። ለዚህም የግብጽ መንግስት ምላሽ ይስጠን ሲሉ የሰነበቱ ሲሆን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ ኢትዮጵያ ምንም መረጃ ሳትይዝ የግብጽን ስም ማጥፋቱና ታቁም ብሏል።
በካይሮ የሚኖሩ ስደተኞችን ፎቶ እያቀረቡ ግብጽ የምትረዳቸው ብሎ መናገር የአለማቀፍ ህጎችን አለማክበር ነው ሲል ያተተው መግለጫው ስደተኞች በሚኖሩበት ሀገር የራሳቸውን ፖለቲካ የማንጸባረቅ ሙሉ መብታቸው ነው ብሏል።
ዝርዝሩን ይመልከቱ። http://mereja.com/network/post/648/egyptian-official-calls-on-addis-ababa-to-stop-accusing-cairo-of

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጅግ ታሟል ( Tariku Desalegn)



ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እጅግ ታሟል
በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁል ዛሬ ታህሳስ 18/09ዓ.ም ተመስገን ታሞ በአንፖላንስ ወደ ሆስፒታሉ እንደመጣ ነው፡፡ የእስር ቤቱ ወታደሮች ወደ ሆስፒታል ይዘውት ሲገቡ ቀደመው በአቅራቢያው የነበረውን ሰው ከቦታው ዙር እንዲሉ ስላደረጉ የተመስገንን የህምም ደረጅ ቀረብ ብሎ ማየት አልተቻለም፡፡ተመሰገን በእስትሬቸር እየገፉ ወደ ሆስፒታል ውስጥ አንደስገቡት ለማወቅ ችለናል፡፡አሁን ከቀኑ 8፡10 ሆናል እስካሁን ተመስገን በዝዋይ ባቱ ሆስፒታል ይገኛል::
የዛሬን ቀን በተመለከተ የዝዋይ እስር ቤት አስተዳዳሬዎችና የዛሬው የሽፍት መሪ ሻለቃ ንጉሴ እንዲሁም እስከ ዛሬ በተመሰገን ላይ ለደረሰው እና ለሚደርሰው ነገር ሁሉ መንግስት ሀላፊነቱን ይወስዳል፡፡
ታህሳስ 18/09 ዓ.ም (Tariku Desalegn)

Tuesday, December 20, 2016

የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ከባድ ተልዕኮ ይዘዉ ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን የዋና አስተዳዳሪነት ቦታ ተላኩ፡፡ቆንጅት ስጦታው



አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ለአመታት የአማራ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ የነበሩት ከባድ ተልዕኮ ይዘዉ ወደ ሰሜን ጎንደር ዞን የዋና አስተዳዳሪነት ቦታ ተላኩ፡፡
ሙሉዓለምከ100 ዓመት በፊት ፋሺስቶች ለቅኝ ግዛት እና ባሪያ ንግድ ሲጠቀሙበት የነበረዉ የከፋፍለህ ግዛዉን መርህ ዛሬም የትግሬዉ ህዉሃት ስትራቴጂ አድርጎ እያጫረሰን ይገኛል፡፡
አቶ አየልኝ ሙሉዓለም ትዉልዱ ከጀግናዉ አገር ከዳባት ቢሆንም ተልዕኮዉ እና ሃሳቡ ግን ፀረ-ዳባት እና ፀረ-ህዝብ ከሆነዉ የትግሬ ቡድን ጋር በመሰለፍ ዳባትን እና መሰል የጎንደር እና የአማራ ህዝቦቹን መጨረስ ነዉ፡፡
ሰሞኑን ትግሬ ወያኔ እና ወታደሮቹ የዳባት እና ወገራ ጀግኖቹን መዋጋት ሲያቅታቸዉ እና በየስርቻዉ ተደፍተዉ ሲወድቁላቸዉ ወያኔ አንድ ሴራ ጠነሰ፤ የዳባት እና ወገራ ጀግኖቹን ተዋግቶ ማሸነፍ ሲያቅተዉ ቤታቸዉን ከተራራዉ ላይ በመሆን በአብሪ ጥይት በመምታት መቱን ተያይዘዉ ያሉትን የሳር ቤቶች በሙሉ አጋያቸዉ፡፡ ከዉስጥ የሚገኙትን ሴት እና ህፃነት አዛዉንት እና ሩጠዉ ማምለጥ የማይችሉ አቅመደካሞች ሳይቀሩ በእሳት ለበለባቸዉ፡፡
የዚህ ግፈኛ መንግስት ክፉ ስራ በዚህ አይመለስም ይልቁንስ ስራዉ አማራን ከዚህ ምድር ማጥፋት ነዉና አመቱን ሙሉ ሲለፋበት የከረመዉን እና ለቀጣይ የአመት ቀለብ ይሆነኛል፣ልጆቼን አሳድግበታለሁ፣ዝክር እዘክርበታለሁ፣እንግዳም እሸኝበታለሁ ያለዉን አዝመራዉን በየአዉድማዉ ከርቀት በአብሪ ጥይትና በመትረየስ እያነደደ የዚህን ምስኪን አርሶ አደር የእህል ክምር ወደ አመድነት ቀየረዉ፡፡
እግዚአብሄር ያሳያችሁ ድሮ እኛ የምናዉቀዉ ወታደር አገርን፣ ዳር ድንበርን፣ሉዓላዊነትን ሲጠብቅ ነበር፣ እኛ የምናዉቀዉ በታሪክም የሰማነዉ እንደ ትግሬ ወያኔ በቴሌቪዥን እና ራዲዮ ልማታዊ ነኝ አርሶ አደሩን ዋስትና እሆነዋለሁ እያለ አ/አደሩን የሚያሳድድ እና አዝመራዉን እና ቤቱን ዶግ አመድ የሚያደረግ ሳይሆን ሁላችንም ከታሪክ የተማርነዉ፣ካለፉት መንግስታትም ያየነዉ የጣሊያንን፣የግብፅን፣የሱዳንን፣የሱማሌን ወራሪ ዶግ አመድ ሲያደርጉ ነበር፣አ/አደሩንም በጥይት ሳይሆን በፍቅር ሲመሩት ነበር እርስ በርስ በመከፋፈል ሳይሆን በመፈቃቀር እና እኩል በመጥቀም ነበር፡፡ ግን ምን ያደርጋል ጊዜ የሰጠዉ ቅል ሆነነና ከትግሬ አብራክ የወጣ ሳይጣን አገሪቱን በጥብጦ መኖሩ ሳያንሰዉ አሁንም በጅምላ ይጨርሳል፣ . . . የአማራ ልዩ ኃይል፣መከላከያ፣ፖሊስና ደህንነት፣አንተ አማራን ዘሩን የምታስጨርስ፣ደሙን የምታፈስ ካድሬ እና ካቢኔ ከቀበሌ እስከ ፌደራል ተዉ ወገንህን አታስጨርስ፣ተዉ የመረረዉ ህዝብ ነገ አንተን ከነቤተሰብህ ይዉጥሃል፣ተዉ እንደ ንብ ገንፍሎ ሊወጣ ነዉ፣ተዉ መተላለቅ ሊመጣ ነዉ፣ተዉ ፊትህን መልስ፣ተዉ ጠብመንጃህን አሁን አዙር፣ተዉ ወያኔ በየተራ ይጎበኝሃል፣ተዉ ይሄ ባንዳ መንግስት 25 አመት ለታገሉት ለነ ኮ/ል ደመቀ፣ ለነ 100 አለቃ ደጀኔ፣ ለነ ኮማንደር ዋኘዉ፣ ለነ ሜጀር ጄኔራል ሃየሎም አርያ ያልሆነ እንኳንስ ለአንተ፡፡ እንግዲህ ቀኗ ደርሳለች፣ አስተዋይ የሆነ ወደ ህዝቡ ወደወገኑ ይጠጋ፣ማዕበሉን የሚችል አይኖርም፡፡ በጣም የሚያሳዝነዉ የአማራን ልዩ ሃይል፣ወታደር እና አመራር በአማራ ህዝብ ለማስጨረስ፣እርስ በርሱ ለማስተላለቅ ትግሬ ወያኔ ከጫፉ ላይ ደርሷል፡፡ ዛሬ የምትገድለዉ፣የምታስረዉ እና የምታሳድደዉ ህዝብ ነገም አንተን ይበላሃል፡፡ ያኔ ትግሬ ከሀገሪቱ የዘረፈዉን እና ያካበተዉን ሃብት ይህን ፊልም እያየ ይበላል፡፡ ወዮልን የአንተን እና የእኔን መጠጊያ፡፡
እንግዲህ በስሜት እና በቁጭት ይህንን ሁሉ ፃፍኩ እንጅ በመነሻየ የጀመርኩትን ጉድ ልቋጨዉ፡፡የከፋፍለህ ጨርስ የትግሬ ወያኔ ስትራቴጂ አማራን አሁንም ለማስጨረስ እየተጋ ነዉ፡፡ አቶ አይልኝን ከክልል ጤና ቢሮ ባንዳዉን እዘዝን ከደ/ታቦር አስተዳዳሪነት በማምጣት 20 የገጠር ወረዳ እና 6 የከተማ መስተዳድር ወረዳ ያለዉን ትልቅ የአንድነት እና የፍቅር የጎንደሬነት ስሜት ያለዉን ህዝብ እምቢ ለትግሬ ወያኔ አንገዛም ያለዉን ህዝብ አከፋፍሎ እርስ በርሱ ለማባላት ከትግሬ ወያኔ የተጠነሰሰዉን ሴራ ለማስፈፀም ከላይ የጠቀስኳቸዉ 2ቱ ባንዳዎች ተልዕኮ ተሰጥቷቸዋል፡፡
ከዚህ በፊት ቅማንትን ከአማራ በመገንጠል ከአማራዉ ጋር በፍቅር ሳይሆን በጥርጣሬ እንዲተያዩ እና አንድ ላይ እንዳይቆሙ፣አማራዉ ወያኔን ለመዋጋት ሲነሳ ቅማንትን ትግሬዉ ከጎኑ በማሰለፍ የአማራን ኃይል ለማድከም የታሰበዉ ስትራቴጂ እንዳዋጣዉ እና ዛሬወም ቅማንቱ ከአማራ ጋር ሆድና ጀርባ እንዲሆን ብዙ ደክሞ፣ብዙ ለፍቶ እንደተዋጣላት ሁሉ (ከዚህ ላይ ለቅማንት ነባር ወገኖቻችን ብዙ ማለት የሚቻል ቢሆንም ለጊዜዉ በአጭሩ ማለት የምፈልገዉ ከትግሬ አማራ መቼም ቢሆን እንደሚሻልህ እና ነገ ትግሬ ወያኔ እንደሸንኮር አገዳ መጦ እንደሚታፍህ ይችን ቃልም እንዳትረሳት ለአማራ እንደነ ደመቀ መኮነን እና ካሳ ተክለ ብራሃን፣በረከት ስሞን . . . የመሰሉትን የእግር እሳት እንዳስቀመጠለት ለአንትም ስራዉን ሲጨርስ 3 ሆዳም ቅማንት ያስቀምጥና እርስ በርስህ እንደሚያባላህ አትርሳ ፡፡ እንግዲህ ወያኔ ለሰሜኑ ጀግናዉ አማራ ሰሞኑን ይዞት የመጣዉ ተልዕኮ ጎንደርን ከ3 ዞን በመከፋፈል አንደኛዉን መተማ፣2ኛዉን ደባርቅ፣3ኛዉን ጎንደር ከተማ በማድረግ እርስ በርስ እንዲጣሉ እንዲከፋፈሉ እና እንዲጨራረሱ አጀንዳቸዉን ከትግሬ ወያኔ ጋር ሳይሆን እርስ በርስ ደባርቅ ከዳባት፣መተማ ከቋራ፣አርማጭሆ ከቅማንት . . . እንዲፋጅ እና ሃሳቡን በማስቀልበስ ቅማንትን ከትግሬ ጎን በማሰለፍ የአማራን አከርካሪ ለመስበር ዝግጅቱ አልቋል፡፡
ይህንን ጨዋታ እንዲጫወቱ እና ተመልሰዉ ሌላ ኃላፊነት ለመስጠት የታሰቡት 2 ዋና ዋና ሆዳሞች ሲሆኑ የተሸለ ተቆቋሪነት ያላቸዉን አማራዎች በጥልቅ ተሃድሶ በሚል መንፈስ አሸቀንጥሮ ጥሏቸዋል፡፡
እንግዲህ ይህ ጉድ የት እንደሚያደርሰን ለሁላችንም ግልፅ ነዉ፡፡
ከዚህ እልቂት ለመዳን ሁላችንም ኃላፊነት አለብን፡፡
ነገ ዛሬ ሳንል ልባቸዉ የደነደነ በአማራ ህዝብ ስም የሚነግዱ ደም አፍሳሾችን በጋራ፣ በአንድነት እንታገል፣ከነ ጎቤ፣ከነ መሳፍንት፣ከነ 100 አለቃ ደጀኔ፣ከነ ኮሎኔል ደመቀ ዘዉዴ፣ከነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ፣ ተመስገን ደሳለኝ፣ . . .በ20 ሺ ከሚቆጠሩ በእስር ላይ እና እና በሺ ከሚቆጠሩ በርሃ ከገቡ ቆራጥ የአማራ ጀግኖች ጋር እንሰለፍ . . .ጊዜዉ አሁን ነዉ፡፡
እግዚዓብሄር የዚህን ጭራቅ መንግስት እና ምስለኔዎቹን ሞት በቅርቡ ያሳየን፡፡
ድል ለጭቁኖች እና ለተገፋዉ ህዝብ፡፡

Monday, December 19, 2016

ሕወሓት በወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ላይ አስከ ሞት የሚያስቀጣ ክስ መሰረተባቸው።ቆንጅት ስጦታው



ሕወሓት በወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ ላይ አስከ ሞት የሚያስቀጣ ክስ መሰረተባቸው።
–  ከ202 ሚሊዮን ብር በላይ ግምት ያላቸው ንብረቶች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ተብሏል
Reporter  የወልቃይት ሕዝብ የማንነት ጥያቄ በሚባል ሽፋን በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ መሪነት በአማራ ክልል በተለይ በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች፣ ታኅሳስ 5 ቀን 2009 ዓ.ም. ክስ ተመሠረተባቸው፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት ክስ የመሠረተባቸው የሰሜን ጎንደር ከተማ ነዋሪዎች አቶ መብራህቱ ጌታሁን፣ ጌታቸው አደመ፣ አታላይ ዛፌና አለነ ሻማ ናቸው፡፡ ከትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን የሰቲት ሁመራ ነዋሪ አቶ ነጋ ባንተይሁንም በክሱ ተካተዋል፡፡
ተከሳሾቹ የአርበኞች ግንቦት ሰባትን የሽብር ተልዕኮ ለማስፈጸም ‹‹የወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ኮሚቴ›› በማለት ራሳቸውን አባልና አመራር ብለው ከሰየሙ በኋላ፣ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን የፕሮፓጋንዳ ኃላፊ አድርገው መሾማቸውን ክሱ ይገልጻል፡፡
ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው ተከሳሾቹ የማንነት ጥያቄውን ሽፋን በማድረግ፣ ከአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በተለያዩ ተንቀሳቃሽ ስልኮች በቀጥታ ተገናኝተዋል፡፡ በትግራይ ክልላዊ መንግሥትና በወልቃይት አስተዳደሮች ላይ የግድያና የአፈና ዕርምጃ እንዲወሰድባቸው ለወጣቶች የጦር መሣሪያ አስታጥቀዋል፡፡ የታጠቁት ወጣቶች በዳንሻ ከተማ ግለሰቦችን እንዲገድሉ፣ አፍነው እንዲወስዱና በቃፍታ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ላይ የግድያ ሙከራ በማድረግ፣ የዳንሻና ሶሮቃ መንገድ እንዲዘጋ ማድረጋቸውን ክሱ ይዘረዝራል፡፡
በክልሉ በሰሜን ጎንደር ዙሪያ በፀገዴ ወረዳዎች በደባርቅ፣ እንጂባራ፣ ወረታ፣ ደምቢያ፣ መገራ፣ በምዕራብ አርማጭሆ በመተማ ዮሐንስና ዙሪያው ተከሳሾቹ ከመጋቢት 11 ቀን 2008 ዓ.ም. እስከ ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም. ድረስ ባስነሱት አመፅ በመንግሥትና ሕዝብ ተቋማት፣ በግለሰብ መኖሪያ ቤቶች፣ ድርጅቶችና ተሽከርካሪዎች ላይ ከ95.9 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ማድረሳቸውን በክሱ ተጠቅሷል፡፡ በጎንደር ከተማ በሚገኙ ቀበሌዎችም በመንግሥትና በሕዝብ ተቋማትና በተሽከርካሪዎች ላይ ከ10.6 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንም አክሏል፡፡
ከነሐሴ 18 ቀን እስከ ነሐሴ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. ደግሞ በምዕራብ ጎጃም በሚገኙ በባህር ዳር ዙሪያ መርዓዊ ከተማ፣ በሜጫ ወረዳ፣ በቡሬ፣ በደጋ ዳሞት አዴት ከተማ፣ በፍኖተ ሰላምና ባህር ዳር ከተማ ከ95.3 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስ ማድረጋቸውንና በድምሩ ከ202 ሚሊዮን ብር በላይ በሚገመት ንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱን የዓቃቤ ሕግ ክስ ያብራራል፡፡
ተከሳሾቹና ኮሎኔል ደመቀ ሰብሳቢ በመሆን ሰኔ 5 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ቀበሌ 18 ውስጥ በሚገኝ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ ግለሰቦችን በመሰብሰብ፣ ‹‹የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ ሊሰጠን አልቻለም፡፡ የወልቃይት ፀገዴ የማንነት ጥያቄውን ምክር ቤቱ ወርዶ ሊያየው የሚችለው ደም ሲፈስና ግጭት ሲከሰት ብቻ ነው፡፡ ስለዚህ እዚህ ተወክላችሁ የተገኛችሁ በሙሉ ወደ መጣችሁበት ቦታ በመሄድ፣ አመፅ በመፍጠርና መንገዶችን በመዝጋት የሽብር ተግባር መፈጸም አለባችሁ፡፡ ይህንን ስታደርጉ ከእናንተም ሆነ ከመንግሥት አካላት ሰው ሊሞት ይችላል፡፡ በዚህ ጊዜ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለወልቃይት ሕዝብ የአማራ ብሔርተኝነት የማንነት ጥያቄያችንን ይፈታልናል፤›› በማለት ቅስቀሳ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ መስጠታቸውን ክሱ ያብራራል፡፡
በወረቀትና በብዕር የሚመጣ ፍትሕ እንደሌለና በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ አመፅ እንዲነሳ የሚያደርጉና የሚያስተባብሩ ሰዎችን በመምረጥና በመመልመል፣ የሽብር ተግባሩን እንዲያፋፍሙ ተልዕኮ መስጠታቸውንም ክሱ ይገልጻል፡፡
ተከሳሾቹ በተለያዩ አካባቢዎች ለመለመሏቸው ወጣቶች ገንዘብ በመላክ ከአዲ ረመጽ አካባቢ ጥይት ገዝተው እንዲዘጋጁ ማድረጋቸውን፣ ወጣቶችን እያፈኑ መውሰዳቸውን፣ በተለያዩ ሰዎች ላይ ግድያ መፈጸማቸውንና የግድያ ሙከራ ማድረጋቸውንም ክሱ ያብራራል፡፡
በአጠቃላይ ተከሳሾቹ የማንነት ጥያቄውን እንደ ሽፋን በመጠቀም፣ በውጭ አገር ከሚገኙት ስረበ ጥሩነህ፣ መዓዛው ጌጡና አስማረ ከተባሉት የአርበኞች ግንቦት ሰባት አመራሮች ጋር በስልክ ግንኙነት በማድረግ የገንዘብ ድጋፍ ሲያገኙ እንደነበር በክሱ ተጠቅሷል፡፡
የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች በኤርትራ በኩል ወደ ኢትዮጵያ እንዲገቡ በማድረግ፣ የጦር መሣሪያ እንዲገዙና በትግራይ ክልል ምዕራባዊ ዞን ፀገዴ ወረዳዎች በተለያዩ አካባቢዎች መንገድ በመዝጋት እንዲፈጸም ትዕዛዝ መስጠታቸውን ፍርድ ቤቱ ለተከሳሾቹ ክሱን በንባብ አሰምቷቸዋል፡፡ ተከሳሾቹ የተገለጸውን የሽብር ወንጀል ፈጽመዋል የተባለው የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1ሀእናለን)፣ 38 እና የፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001ን ተላልፈው በመሆኑ፣ የሽብርተኝነት ክስ እንደተመሠረተባቸው የጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ክስ ያስረዳል፡፡
ተከሳሾቹ የተጠቀሱባቸው የሕግ አንቀጾች ዋስትና ስለሚከለክሉ በማረሚያ ቤት ሆነው ክሳቸውን እንዲከታተሉ ፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ የቅድመ ክስ መቃወሚያ ካላቸው እንዲያቀርቡና ከጠበቃ ጋር ተመካክረው ታኅሳስ 18 ቀን 2009 ዓ.ም. እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡

Friday, December 16, 2016

ጎንደር – ወያኔ የተዳከመውን ሰራዊት በአዲስ ልትቀይር ነው!ሙሉነህ ዮሃንስ



የጎንደር ሕዝብ ትግል ከቋራ እስከ ጃናሞራ!
ወያኔ የተዳከመውን ሰራዊት በአዲስ ልትቀይር ነው!
ሃሙስ ታህሳስ 6 ቀን 2009

እንደሰደድ እሳት እየተቀጣጠለ የመጣው የጎንደር ሕዝብ ትግል ከሱዳን ጠረፍ ከቋራ እስከ ታላቁ ራስ ዳሸን ተራራ ጥግ ጃናሞራ ተዛምቷል። በአርማጭሆ፣ በቆላማው ወገራ፣ በወልቃይት ጠገዴ፣ በመተማና ቋራ በገበሬወች ላይ ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ሰሞኑን ወደ ስሜን በኩል ስማቸውን መጥቀስ የማልፈልጋቸው አዳዲስ ሶስት ግንባሮች ላይ ጦርነት ተከፍቶ ፍልሚያ አለ። የተገፋው ገበሬ እራሱን ለመከላከል እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ እያደረገ ነው።
ግራ የገባው ወያኔ የወረዳ መንገዶችን በኬላ በመዝጋት ፍተሻ እያደረገ ነው። ከጎንደር ሾልኮ የወጣ መረጃ እንደሚያሳየው ወያኔ ከፍተኛ የአካልና የሞራል ጉዳት የደረሰበትን ጦር አንስቶ በአዲስ ለመተካት እንቅስቃሴ እያደረገ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።
ጭንቅ ውስጥ የገባው ወያኔ ህፃናትን፣ እናቶችንና አረጋዊያንን በመያዣነት አስሮ በግፍ እያንገላታ ነው። ለጊዜው ስማቸውን የማንጠቅሰው የገበሬ ሴት ቤተሰቦች ከ6 አመት ህፃን ጋር ጎንደር ውስጥ በ1ኛ ፖሊስ ጣብያ ታስረው ይገኛሉ። ይህ እጅግ አሳፋሪ ድርጊት የህዝቡን እልህና ቁጣ እየጨመረው እንደሚገኝ ከቦታው ካናገርናቸው ተረድተናል።
ሙሉነህ ዮሃንስ

የኣውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት የዶክተር መረራ ጉዲና ጉዳይን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ።ቆንጅት ስጦታው

  


የኣውሮፓ ፓርላማ ፕሬዚዳንት የዶክተር መረራ ጉዲና ጉዳይን በተመለከተ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው ጠየቁ። ፕረዚደንቱ በይፋ በላኩት ደብዳቤ ሕወሓት ዶክተር መረራን ያሰረበትን ሕጋዊ መሰረት በግልጽ እንዲያስቀምጥ የጠየቁ ሲሆን የ አውሮፓ ሕብረት የዲሞክራሲ ቤት ነው ያሉት ማርቲን ማንኛውም የመንግስት የተቃዋሚ ፓርቲ ይሁን ሌላም ድርጅትና ግለስብ ወደ ፓርላማው መጥቶ ድምጹን የማሰማት መብት አለው ብለዋል።    http://mereja.com/network/post/556/eu-parliament-writes-to-ethiopian-president-over-detained-oromo
https://i1.wp.com/pbs.twimg.com/media/CzvQRBxWQAAnSo_.jpg?resize=526%2C593&ssl=1

በ 7 ወታደሮች ተከቦ ተመሰገንን በዝዋይ እስር ቤት አግኝተነዋል።Tariku Desalegn



ተመስገንን አግኝተነዋል – Tariku Desalegn
ከ 10 ቀናት በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ለ 3 ደቂቃ በዝዋይ እስር ቤት በልዩ ጥበቃ ለብቻው በ 7 ወታደሮች ተከቦ ተመሰገንን አግኝተነዋል። ተመስገንን ሰናገኝው ምን ማውራት ባንችልም ሲራመድ እንደሚያሰቸግረው አይተናል። እሱም ከሌሎቹ ህመሙ ውጪ ጨጓራው እጅጉን መታመሙን ነግሮናል።

እስካሁን የት እንደነበረ ምን እንዳረጉት በንጠይቅም ወታደሮቹ መመለስም መጠየቅም ከልክለውናል። ተመሰገንን ከበው ካመጡት ወታደሮች መካከል ሀላፊያቸውን እስካሁን ለምን እዚህ እንዳለ አልነገራቹህንም ስንለው ተመስገን እዚህ ያገኘነው ዛሬ ነው ብሎናል። የሆነው ሆኖ ተመሰገንን አግኝተነዋል። ተመስገንን አጣነው ካልንበት ግዜ አንስቶ ከጎናችን መሆናቹህን ላሳያቹሁን ሁሉ እጅግ በጣም እናመሰግናለን። Tariku Desalegn

Thursday, December 15, 2016

የብሪታኒያ ፓርላማ አባላት በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ላይ ስለሚወሰደው ዕርምጃ ክርክር ሊያካሄዱ ነው ቆንጅት ስጦታው

Image result for andargachew tsige


የብሪታኒያ ፓርላማ አባላት በአንዳርጋቸው ጽጌ ጉዳይ ላይ ስለሚወሰደው ዕርምጃ ክርክር ሊያካሄዱ ነው
ኢሳት (ታህሳስ 6 ፥ 2009)
የብሪታኒያ መንግስት በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳይ ዙሪያ መውሰድ በሚገባው ዕርምጃ ላይ ለመምከር የሃገሪቱ የፓርላማ አባላት በቀጣዩ ሳምንት የክርክር መድረክ ሊያካሄዱ መሆኑ ተገለጸ።
ካለፉት ጥቂት ወራት ጀምሮ አቶ አንዳርጋቸው በብሪታኒያ መንግስት ተወካዮች ዘንድ እንዲጎበኝ መደረጉ በፓርላማ አባላትና በሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ስጋትን ማሳደሩን የተለያዩ አካላት በመግለጽ ላይ ናቸው።
የጉዳዩ አሳሳቢነትን ተከትሎ የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት የሃገሪቱ መንግስት መውሰድ በሚገባቸው እርምጃዎችና የዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች ዙሪያ ለመምከር የፊታችን ማክሰኞ ልዩ የክርክር መድረግ ማዘጋጀቱን ሪፖሪቭ የተሰኘ የብሪታኒያ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋም ሃሙስ አስታውቋል።
የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጉዳዩን በመከታተል ላይ የሚገኘው ይኸው ድርጅት የአቶ አንዳርጋቸው ወቅታዊ ሁኔታ እጅጉን አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱን ገልጿል።
ከወራት በፊት አቶ አንዳርጋቸውን የጎበኙ የብሪታኒያ መንግስት ተወካዮች አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ለደህንነቴ ስጋት አድሮብኛል ሲሉ ያሉበትን አሳሳቢ ሁኔታ እንዲጋሯቸው ይፋ ማድረጋቸው ይታወሳል።
ይሁንና የሃገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጉዳዩን አስመልክቶ ማብራሪያን ቢጠይቅም ለወራት ያህል ምላሽ ሳያገኝ መቅረቱን ለመረዳት ተችሏል። ይህንንም ተከትሎ የብሪታኒያ የፓርላማ አባላት በቀጣይ መውሰድ በሚገባቸው ዕርምጃዎች ዙሪያ በተያዘው የክርክር መድረክ ቀን ሰፊ ውይይትን ያካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በብሪታኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፓርላማ ተወካይ የሆኑት ቶቢያስ ኤልሙድ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከቤተሰቦቻቸው ጋር የስልክ ግንኙነት እንዲያደርጉ በሃገራቸው መንግስት በኩል ጥያቄ መቅረቡን አስታውቀዋል።
እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በታህሳስ ወር 2014 አም አቶ አንዳርጋቸው ለተወሰነ ደቂቃ ቤተሰቦቻቸውን አግኝተው እንደነበር የሚታወስ ሲሆን፣ የብሪታኒያ ባለስልጣናት በዚሁ ጉዳይ ዙሪያ በመምከር ላይ መሆናቸውም ተገልጿል።
የብሪታኒያ ባለስልጣናት በአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የደህንነት ጉዳይ ስጋታቸውን በመግለጽ ላይ ቢሆኑም የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እስካሁን ድረስ ምላሽን ከመስጠት ተቆጥበዋል።
ሪፕሪቭ የተሰኘው የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት በኢትዮጵያ ተግባራዊ ተደርጎ የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ለአቶ አንዳርጋቸው ስጋትን አሳድሮ እንደሚገኝ በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከነበረበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት የት እንደተወሰደ አየታወቅም።ቆንጅት ስጦታው



ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከነበረበት ዝዋይ ማረሚያ ቤት የት እንደተወሰደ አየታወቅም።
የተለያዬ ሚድያዎች ባለቤት የነበረውና በተደጋጋሚ የሚድያ ተቋሙ የተዘጋበት እንዲሁም በፃፋቸው ፅሁፎች ህዝብን ለአመፅ አነሳስተሃል ተብሎ በ2007ዓ.ም ጥቅምት ወር የ3 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት ታዋቂው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ታስሮበት ከነበረው ዘዋይ ከተማ በሚገኘው የፌደራል ማረሚያ ቤት ሊያገኙት እንዳልቻሉ ቤተሰቦቹ ገልፀዋል።
የጋዜጠኛው ቤተሰቦች በዝዋይ፣ ቃሊቲ፣ ሸዋ ሮቢት፣ በቅሊንጦ በሚገኙ የፌደራል እስር ቤቶች ውስጥ እንዲሁም በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ ተዘዋውረው ቢገልጉትም ከእስር ቤቱ ሰዎች “ተመስገን ደሳለኝ የሚባል እስረኛ አናውቅም” የሚል መልስ ተሰትቷቸዋል።

የዶክተር መራራ ጉዲና እስር እያነጋገረ ነው።ቆንጅት ስጦታው

  


የዶክተር መራራ ጉዲና እስር እያነጋገረ ነው።
ከአማፂ መሪው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአንድ አዳራሽ መታየታቸው ለእስር ዳርጓቸዋል።
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ዶር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን መመሪያ አንድ ጥሰዋል ተብለው ለእስር መዳረግ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው። ዶር መረራ ጉዲና ወቅታዊ የኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በአውሮፓ ህብረት ግብዣ መሰረት ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን በስብሰባ አዳራሹ ከተገኙት መካከል የግንቦት 7 መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ እንዲሁም በሪዮ ኦሎምፒክ የብር ሜዳለያ አሸነፊ የሆነውና እጁን ግንባሩ ላይ በማጣመር የኢትዮጵያ መንግስት በዜጎቹ ላይ እየወሰደ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በአለም መደረክ የተቃወመው አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ የተገኙ ሲሆን ዶክተር መራራ ጉዲናን ለእስር የዳረጋቸው የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በአዳራሽ መገኘት ነው።
የዶክተር መረራን እስር ተከትሎ መንግስት በሰጠው መግለጫ ዶክተር መረራ የታሰሩት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈፀም የወጣውን መመሪያ ቁጥር አንድ በመታሳቸው ነው ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ ፌደራላዊ አንድነት መድረክ በበኩሉ ዶክተር መራረ የጋበዘው የአውሮፓ ህብረት ነው ስለሲህ ሊቀመጥበት የሚችለውን ቦታ ስብሰባውን ያዘጋጀው አካል ነው እንጂ ዶክተር መረራ እይደሉም የሚመርጡት እስራታቸው ምክንያታዊ አይደለም ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት ዶር መረራ ጉዲና በማእከላዊ ወንጀል ምርመራ የሚገኙ ሲሆን አራዳ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርበው የጸረ ሽብር አዋጁ በሚፈቅደው መሰረት የ28 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተሰጥቷቸዋል። ዶክተር መራራ እስከአሁን ድረስ አንድ ጌዜ ብቻ ጠበቃ ያገኙ ሲሆን ፖሊስ ከጎናቸው ቆሞ የሚያወሩትን ሲሰማ ስለነበረ ለማውራት እንደተቸገሩ የዶክተር መራራ ጉዲና ጠበቃ ለቪኦኤ ተናግረዋል።

Tuesday, December 13, 2016

በኮማንድ ፖስቱ ታፍነው የታሰሩ እስረኞች ቤተሰቦች እየተጉላሉ ነው። ቆንጅት ስጦታው



በኮማንድ ፖስቱ ታፍነው የታሰሩ እስረኞች ቤተሰቦች እየተጉላሉ ነው።………….
በኮመንድ ፓስቱ ቁጥጥር ስር ከዋሉ በኃላ፤ 24 ቀበሌ በሚገኘው ፓሊስ ጣቢያ በእስር የሚገኙት ወጣት ወይንሸት ሞላ ፣ ጋዜጠኛ አናንያ ሶሪ ፣ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ እና አቶ ዳንኤል ሽበሺን ጨምሮ አጠቃላይ በኮማንድ ፓስቱ ቀጥጥር ስር የሚገኙት እስረኞች፤ ” በቤተሰብ እንዳይጠየቁ ከሰዓት በኃላ ትዕዛዝ ተላልፏል” በሚል የእስረኞች ቤተሠቦችና ጓደኞች በሃሩር ፀሀይ ላላስፈላጊ እንግልት እየተዳረጉ ይገኛል። የፓሊስ ጣቢያው መዘጊያ ሰዓት ቢደርስም የእስረኞች ቤተሰብ እና ጓደኞች ተስፋ ሳንቆርጥ እንዲህ እየተጠባበቅን እንገኛለን።
Image may contain: 2 people , people standing, child and outdoor
Image may contain: 5 people , people standing, tree and outdoor
Image may contain: 1 person , people sitting and outdoor

ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አንድ ጥናት አመለከተ።ጌቱ በቀለ በዳዳ



ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አንድ ጥናት አመለከተ።
በኢትዮጵያውያን ዙሪያ በፈረንጆቹ 2017 መባቻ ላይ ቁጥራቸው መቶሰባ በሚደርሱ ኬኒያውያን የማህበራዊ ሳይንስ ፕሮፌሰሮች የተካሄደ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ፣ ዜጎችዋ የርስበርስ ትምምናቸው ከመጡበት የዘመናት የመተጋገዝ ያኗኗር እሴታቸው ክፉኛ እየተንሸራተቱ እንደመጡ ከሀያ ሺህ ባላነሱ ከአራቱም ማዕዘን ከተውጣጡ ዜጎችዋ በርካታ ጥያቄዎችን በመጠየቅ የተገኘው የጥናት ናሙና አመላክቷል።
·
የጥናቱ ዋነኛ ማጠንጠኛ፣ እጅግ ቀላል የሆኑ ጥያቄዎችን በሰንጠረዥ ተከፋፍሎ የተዘጋጀ ቅፅ በመበተን የተገኘ ሲሆን ፣ ከጥያቄዎቹ ውስጥ እንዲህ የሚሉ እንደሚገኙበት በቅርበት ጥናቱ ላይ በማስተርጎም ስራ ሲያግዛቸው የነበረ ስሙ እንዳይገለፅ የፈለገ ኢትዮጵያዊ ጥናቱ ስፖንሰር በተደረገው፣ ጊዚያዊ መቀመጫውን ጅቡቲ ባደረገው አለም አቀፍ የማህበረሰብ ጥናት መድረክ ለአለም ይፋ ከመሆኑ በፊት አፈትልኮ እንዲወጣ አድርጎታል።
·
√ የጉርብትና መስተጋብራችሁን ግለፁ፣
√ የበዓል ጊዜ ቅርርባችሁን አስፍሩ፣
√ ጋብቻን መፈፀም የምትፈልጉት ዘርን መሰረት አድርጋችሁ ወይስ ፍቅርን?
√ የስራ አቀጣጠራችሁ በሀገር ልጅነት ወይስ በሞያ ብቃት?
√ ዘር ምንድነው ላንተ(ቺ)
√ ትምክታችሁ በዘር በሚማሰላችሁ የፖለቲካ መሪያችሁ ላይ ምን ያህል ርቀት ይሄዳል?
√ በየእምነት ተቋምህ ተገኝተህ ትፀልያለህ?
√ ለመንግስትህ ያለህ ፍቅርና አክብሮት ምን ያህል ነው?
√ ተቃዋሚዎች ላንተ ምንድን ናቸው?
√ በመንግስትህ ላይ እምነትህ ምን ያህል ነው?
√ ዘርን መሰረት አድርገው ከሚመሰረቱ ቡድኖች በስንቱ ውስጥ ያለማቋረጥ ትሳተፋለህ?
√ በታሪክ ከሚጠቀሱልህ በመሪዎች የተሰሩ ስህተቶች፣ የአሁኑ ትውልድ የመጠየቅ ግዴታ አለበት ትላለህ?
ወዘተ… እና መሰል መጠይቆችን በትነው ያገኙት ምላሾች እጅግ የበረከቱት ፍፁም አስደንጋጭና ተስፋን የሚያሳሱ ሆነው አግተዋቸዋል።
·
የጥናቱ ዙረት እና መልሶች የተሰበሰቡት ከ80% ያላነሱት ያተኮረው ዕድሜያቸው ከ20—30 በሚደርሱ ወጣቶች ላይ ሲሆን አብዛኞቹ ወንዶች ናቸው፣
15% ደግሞ በ40 ዎቹ መጀመሪያ ላይ የሚገኙ ጎልማሶች ላይ ነበር 5%ቱን የሚይዙት በተማሩና ዕድሜያቸው ወደ 50 ገፋ ባደረገ አዋቂ ወንዶች ዙሪያ የተጠየቀ ነው።
·
60% ቱ የመጠይቆቹ መልሶች አሉታዊና የአብሮ መኖር እሴትን የናቁ በራስ ወዳድነት ስሜት የተሸበቡ፣ ለመጡበት ዘር ፍፁም ያደሉ፣ እጅግ አስደንጋጭና በርካታ የቤት ስራን ለትውልዱ የተወ መልስን ከሶስቱም ዕድሜ ጣሪያ ከተውጣጡት የተገኘው የአብዛኛው መልስ አመላክቷል።
·
5% ቱ ብቻ አዎንታዊ መልሶችን የሰጡና፣ የቀድሞውን እሴት በጠበቀ መልኩ መኖርን የሚመርጡና በዚያው መንገድ ላይ እየኖሩ መሆኑን የገለፁ ሲሆን የቀሪው 35% መልሶች በኤክስ ምልክት የተሞሉ፣ ስርዝ ድልዝ የበዛባቸው፣ መልስ መስጫ ወረቀቶቹ የተበሳሱ፣ 95%ቱ ደግሞ አላውቅም እና እኔጃ በሚሉ ቃላቶች ተሞልቶ የተመለሱ ናቸው።
·
ፕሮፌሰሮቹ እንዳጠኑት ከሆነ ኢትዮጵያ በመጪው ጊዜዎችዋ ከባድ ደመናን ያዘለ የርስ በርስ መጠፋፋት ዝናብ እንዳጃበባት አመላካች ፍንጭ ከጥናቱ አግኝተናል ብለዋል።
·
ይሁንና አሁንም በህዝቡ ህዝነ ህሊና ውስጥ ለዘመናት የነበረው ይሉኝታ በአሁኑም ትውልድ ውስጥ መኖሩ በብዙ መልኩ እንደጠቀማት በዳሰሳ ጥናታቸው ደርሰውበታል።
·
ይህ ሳይታወቅ አብሮአቸው የሚኖረው ጨክኖ ያለመጨካከን የይሉኝታ መንፈስ ከአሁን በኋላም አብሮ የመኖር እሴታቸውን እንዲቀጥል በርካታ የቤት ስራን ፣ በአዋቂ ሽማግሌዎች፣ በአዋቂ የሃይማኖት አባቶች፣ በአዋቂ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ በአዋቂ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፖርቲዎች የሚሰሩ ክፍተቶችን ከሞሏቸው አስፈሪው ደመና መግፈፉ አይቀርም ብለዋል።
·
ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ጥራዝ ነጠቅ ምሁራን ደግሞ ለአመታት ብሄራዊ እርቅ እየተባባሉ ከገዢው ፖርቲ ጋር ያልተግባቡበትንና የሚላዘነውን ቀረርቶም ተወት አድርገው፣ መንደር ተወርዶ ከቤተሰብ ጀምሮ ጉርብትና ላይ እርቅና ቅርርብን እንደቀድሞው እንዲጀምር በየአካባቢው ባሉ የየእምነት ተቋማት የቤት ስራው እንዲጀምር ማበረታታት ከቻሉ ፣ ድምር ውጤቱ ወደ ብሄራዊ እርቅ ማደጉ አይቀርም ብለዋል በመፍትሄው የጥናት ክፍላቸው ላይ።
·
ከዚያ ባሻገር ትውልዱ በተመሳሳይ የታሪክ ሁነት ላይ የተለያየ ድምዳሜ መያዛቸውም እጅግ አሳሳቢ ከሆኑ ጉዳዮች ውስጥ ጠቀስ አድርገው አልፈዋል። እንደውም ፈጣን ዕልባት ካልተበጀለት በዘር ጉዳ በሚነሱ የጥላቻ ልዩነት አንቦርቃቂና ብጥብጥ ፣እንደ ቁርቁስ መነሻ አንኳር መንስኤ ሆኖም ሊያገለግ ይችላልን ስጋታችን ነው ብለዋል።
·
ጥፋቶችን አጥፍተዋል በሚባሉ የቀድሞ እና በስልጣን ላይ ያለን መሪዎችን ዘር የያዘ ጎሬቤታቸው ላይ ጥርስ መናከሱ የበዛ መሆኑን ፍንጮችን ከምላሾቹ አግኝተናል እያሉ ነው።
·
ዘርን መሰረት ባደረገው መቧደን ዙሪያ ለተጠየቀው ጥያቄ ባብዛኞቹ የተሰጠው መልስ ፣ የጊዜው ብቸኛ ምርጫችን ነው የሚል ተስፋን የሚያዳፍን ድምዳሜያቸው ፣ ትውልዱ ምን ያህል ወደተገፋው እንደሚገፋና ቻሌንጅ በማድረግ ሌላ መንገድን ለመሞከር ስንፍና እንዳለበት ከምላሾቹ አውቀውበታል።
·
እየተበላሸ የመጣውን የአኗኗር ነባር እሴት ወደቀደመው የክብብርና አብሮ የመተባበር ኑሮ መመለስ ሀላፊነት አለባቸው ከተባሉት ወገኖች ባሻገር የእኛ ድርሻ ምን ድረስ ነው የሚል መልስን ከያንዳንዳችን ጥናቱ ይፈልጋል።
·
የጥናቱ ከፊል መረጃ በሚመጣው እሁድ ሳምንት ከታተመው የኬኒያ ሰንደይ ታይምስ ጋዜጣ የተገኘ ነው።
ጌቱ በቀለ በዳዳ

Friday, December 9, 2016

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በኢትዮጲያ የፌደራል እስር ቤቶች ሁሉ የለምTariku Desalegn



ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በኢትዮጲያ የፌደራል እስር ቤቶች ሁሉ የለም…
ከህዳር 28/09ዓም ጀምሮ ዝዋይ እስር ቤት ብንገኝም የእስር ቤቱ ሹሞች ተመስገን እዚህ የለም ግቢውን ለቃችሁ ውጡ ብለውናል።
አዲስ አበባ የሚገኙት ቃሊቲና ቂሊንጦ እስር ቤቶች ብንሄደም ተመስገን እንደሌለ ነገረውናል። እንግዲህ ተመስገንን ካጣነው ዛሬ 2 ቀናችን ነው። መንግስት ጋዜጠኛ ተመሰገን ደሳለኝን ያደረገበትን ቦታ ወይም ያደረገውን እንዲያሳውቀን እንጠይቃለን።
Tariku Desalegn

በአማራ ክልል ከፋብሪካ የሚወጣ ዝቃጭ የ አማራውን ሕዝብ ለካንሰር በሽታ እየዳረገው መሆኑን ከዚህ ቪድዮ እንመለከታለን።



በአማራ ክልል ከፋብሪካ የሚወጣ ዝቃጭ የ አማራውን ሕዝብ ለካንሰር በሽታ እየዳረገው መሆኑን ከዚህ ቪድዮ እንመለከታለን።



Thursday, December 8, 2016

የአውሮፓ ህብረት በዶክተር መረራ መታሰር በእጅጉ እንዳሳሰበው ገለጸ።ቆንጅት ስጦታው



የአውሮፓ ህብረት በዶክተር መረራ መታሰር በእጅጉ እንዳሳሰበው ገለጸ።
በሀገር ቤት ውስ በሰላማዊ መንገድ ከሚታገሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ የሆነው የኤፌኮ ሊቀመንበር የሆኑት መረራ ጉዲና ለእስር የተዳረጉት በአውሮፓ ፓርላማ ሀገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ማብራርያ ሰጥተው በመመለሳቸው ነው። ህብረቱ እስራቱን አውግዞ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠይቋል። ዝርዝር አለው። http://mereja.com/…/chair-of-the-european-parliament-s-subc…

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ!Muluneh Yohannes



የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አድማ!
በዛሬ ቀን ወያኔ የብሄረሰቦች ባሕል ብሎ ያመጣውን ማወናበጃ በጎንደር ዬኒብርሲቲ አልተከበረም። ምክኒያቱም ወልዲያ ላይ የታሰሩ ተማሪዎች አሉ። ከጥቂት ቀናት በፊት በግፍ የታሰሩ ከ120 በላይ የጎንደር የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብር ሸለቆ ውስጥ ታስረው እየተሰቃዩ ስለሆነ ተማሪው አድማ ላይ ነው።
በተጨማሪም በሃገራችን ገበሬ ላይ የተከፈተው የግፍ ጦርነት በህዝባችን ላይ ወያኔ የዘር ፍጅት እየፈፀመ ነው የሚል እልህና ቁጭት በተማሪው ሁሉ ላይ ፈጥሯል። ተማሪዎች እንደገለፁት ብዙወችም ወገን እያለቀ ቁጭ ብለን አናይም በማለት እየሸፈቱ በርሃ እየገቡ ነው። ሁኔታው እጅግ እየተካረረ የመጣበት የጎንደር ሁኔታ ወያኔን ጭንቅ ውስጥ ከቶታል። ሰፋ ያለ ከተማዎችን ያቀፈ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንደሚጀመር ይጠበቃል። ተማሪዎች እንደገለፁት እነሱም ትምህርት አቁመው ህዝባቸውን ወደመታደግ እንደሚገቡ በቁርጠኝነት ገልፀዋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ወያኔ በጎንደሬው ገበሬ ላይ ያወጀው ጦርነት እራሱን መልሶ እየለበለበው ነው። ጦርነቱም በርትቶ ቀጥሏል። በየቀኑ ብዛት ያለው የወያኔ ሙትና ቁስለኛ ወደ ጎንደርና ሌሎች የወረዳ ከተማ ጤና ማእከላት እየተከማቸ ስለመሆኑ ዛሬም የአይን እማኞች ገልፀዋል።
ሙሉነህ ዮሃንስ
Muluneh Yohannes

Tuesday, December 6, 2016

በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተቃጥሏልMuluken Tesfaw



በወገራ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ቤተሰቦች ቤታቸውና ንብረታቸው በመንግሥት ወታደሮች ተቃጥሏል፤
o በዐማራ ገበሬዎች ላይ እየደረሰ ያለውን ሰቆቃ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በቸልታ እያየው ነው፤
Muluken Tesfaw – የትግሬ ወያኔ አገዛዝ በዐማራው ሕዝብ ላይ እያደረሰው ያለው በደል ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ ሒዷል፤ በዐማራ ሕዝብ ላይ ይፋ የእልቂት አዋጅ ታውጇል፡፡ ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል እየተጋደሉ ያሉ ዐማሮች በሕይወታቸውና በንብረታቸው ላይ ይህ ነው የማይባል ጉዳት ደርሷል፡፡ በተለይ በሰሜን ጎንደር በአርማጭሆና በወገራ ወረዳዎች የዐማራ ገበሬዎች ቤት እየተቃጠለ፣ ንብረታቸው እየተወረሰና እወደመ ሕፃናት፣ ነፍሰ ጡር ሴቶችና አዛውንቶች በሜዳ ላይ ተበትነዋል፡፡
ሰሞኑን ከኅዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. ጀምሮ በወገራ ወረዳ በእንቃሽና ጃኖራ ቀበሌዎች ይኖሩ የነበሩ ከ500 በላይ ቤተሰቦች ተበትነዋል፡፡ በጎተራና በአውድማ ያለ ሰብል ከከባድ መሣሪያ በሚወጣ እሳት ዶጋ አመድ ሆኗል፡፡ በ2007/8 ዓ.ም. በነበረው ድርቅ ያላገገሙ ቤተሰቦች ዘንድሮ ያመረቱት ምርት በወያኔ መንግሥት ያለምንም ምሕረት ወድሟል፡፡ ይህ የለየለት አረመኔያዊ ተግባር ሲሆን የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሁሉ ሊያወግዘው የሚገባ ጉዳይ ቢሆንም በቸልታ እየታየ ነው፡፡
ዛሬ ከተጎጅ ቤተሰቦች ጋር ባደረግነው ውይይት በእንቃሽ ቀበሌ ከ50 በላይ ቤቶች ወድመው ወደ 200 የሚሆኑ ቤተሰቦች ተበትነዋል፤ በጃኖራ ቀበሌም ተመሳሳይ ውድመት ደርሷል፡፡ ትናንት እና ዛሬ ተበትነው የሚገኙ ቤተሰቦች ወደ 500 እንደሚደርስ ተጎጅዎች ተናግረዋል፡፡ የሚከተሉት አባውራ ቤቶችና ቤተሰቦች ስም ዝርዝራቸውን ያገኘናቸው ነው፤
ስም የቤተሰብ ብዛት ቀበሌ
1) ምስጋነው አጠኔ 12 እንቃሽ
2) መለሠ ተሾመ 7 እንቃሽ
3) ተሾመ ደሴ 5 እንቃሽ
4) ታደለ መልሰው 4 እንቃሽ
5) ደመወዝ ነጋሽ 10 እንቃሽ
6) ለከው ይለፉ 10 እንቃሽ
7) ካሣው ታየ 5 እንቃሽ
8) ዘሪሁን ተዘራ 4 እንቃሽ
9) ንጉሥ ዘሬ 3 እንቃሽ
10) ታከለ ማረው 4 እንቃሽ
11) ቀኑ ገሠሠ 2 እንቃሽ
12) ያለው አበበ 9 እንቃሽ
13) ደጉ በዜ 5 እንቃሽ
14) መሳፍንት ተስፋ ጃኖራ
የችግሩ አሳሳቢነት ከዚህ ላይ የተገለጸውን ያክል ብቻ አይደለም፡፡ በጎዳና የተበተኑ ሕጻናትንና አቅመ ደካማ ሰዎችን ልቅሶ መስማትም የበለጠ የሚያም ነው፡፡ ማንኛውም በዐማራ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን እልቂት የሚያሳስበው ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ይህን አረመኒያዊ ድርጊት እያወገዘ በሚቻለው ሁሉ እንዲያግዝም ጥሪ ቀርቧል፡፡

በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ያስመዘገቡት ዝርዝር መረጃ Muluken Tesfaw

  


በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬዎች ተጋድሎ ያስመዘገቡት ዝርዝር መረጃ – Muluken Tesfaw
በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬዎች በትግሬ ወያኔ ፋሽስታዊ ድርጅት የተቃጣባቸውን ጀምላ ዕልቂት በሚገባ ለመመከት ችለዋል፡፡ በጎበዝ አለቆች የተደራጁት የቆላ ወገራ ገበሬዎች በተደጋጋሚ ከሦስት ጊዜ በላይ የመጣውን የወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቡድን እንዳለ ሲያረግፉት በቤታቸውና ንብረታቸው ላይ በከባድ መሣሪያ ማቃጠልን መርጧል፡፡ ይህንንም በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡
በሦስት ጊዜ ውጊያው የሚከተሉት ድሎች ተመዝግበዋል፤
ኅዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. በነበረው ውጊያ 22 የወያኔ ወታደሮች ሲገደሉ 14ቱ ደግሞ በከባድ ቆስለው የመጣው ወታደር ሙትና አስከሬን ሆኖ ተመልሷል፡፡
ኅዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. በቀጣዩ ቀን ተጨማሪ ጦር ወደ አካባቢው መጥቶ ጦርነቱ ቀጥሎ ነበር፡፡ በዚህ ቀን ደግሞ 10 ወያኔዎች ተገድለው 7 ቆስለው ተመለሱ፡፡
ኅዳር 24 ቀን 2009 ዓ.ም. በባንዳዎች የሚመራ የወያኔ ጦር ድንገተኛ ጦርነት ከፍቶ ነበር፡፡ በዚህ ዕለት ደግሞ ከፍ ያለ ድል በወገራ ገበሬ ታጋዮች ተመዘገበ፡፡ 24 የነፍሰ በላ አስከሬኖችና 14 የቆሰሉ ወታደሮች ተጭነው አካባቢውን በግዴታ ለቀዋል፡፡
የተማረከ የጦር መሣሪያ፤
አንድ መትረየስ ከ260 ጥይት ጋር እንዲሁም 56 አውቶማቲክ ክላሽንኮቭ ጠመንጃዎች ከነሙሉ ትጥቃቸው በቆላ ወገራ የዐማራ ገበሬ ተጋድሎ እጅ ገብቷል፡፡
ከተገደሉ የወያኔ ወታደሮችና ባለሥልጣናት ጥቂቶቹ
ኮሎኔል ይመር መሰለ አቡሃይ (የጸረ ሽምቅ ወታራዊ ግብረ ኃይል አዛዥ)፣ ምክትል ሳጅን ዋጋዬ ጫቅሉ (የፀረ ሽምቅ ግበረ ኃይል አመራር) እንዲሁም ስሙ ለጊዜው ያልታወቀ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮነን ይገኙበታል፡፡
በዐማራ ገበሬዎች ላይ የደረሰ ጥፋት፤
ሴት ምላስና ሰበንተራ በተባሉ አካባቢዎች በቤታቸው ውስጥ የነበሩ አንድ አቅመ ደካማ ሽማግሌ አዛውንት እንዲሁም አንድ ልጅ ተገድለዋል፡፡ በተጨማሪም ብዙ የዐማራ ገበሬዎች ቤት በጅምላ እንዲነድ ሆኗል፡፡
(ይህ ሪፖርት የተሠራው በተጋድሎው በሰነበቱ የዐማራ ገበሬዎች መረጃና ብሎም በፍላገታቸው መሠረት መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን)

Monday, December 5, 2016

በዶ/ር መረራ እስርና በመብት ረገጣው ዙሪያ አሜሪካ አዲስ ጥረት ጀመረች ; ዋዜማ ራዲዮ



ዋዜማ ራዲዮ-የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና መታሰር በኢትዮጵያና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ባለው ግንኙነት ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ሊያሳድር እንደሚችል አንድ የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት አማካሪ ገለፁ።
በመጪዎቹ ቀናት የአሜሪካ ዲፕሎማቶች ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚንስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ቅሬታና ጥያቄ ለማቅረብ እየተሰናዱ መሆኑን ያመለከቱት አማካሪው አርብ ዕለት በተደረገ ውይይት የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ተከታታይ እርምጃዎች ለመውሰድ ማቀዱን አመልክተዋል።
“የዋሽንግተን አስተዳደር የኢትዮጵያን መንግስት ላለማስቆጣት በብዙ ጉዳዮች ላይ ለዘብተኛ አቋም ነበረው፣ ይህ ግን የሚቀጥል አይመስለኝም” ብለዋል ላለፉት አስራ ስድስት አመታት በአፍሪቃ ጉዳይ የውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱን ያማከሩት ዲፕሎማት።
በአሜሪካ የስልጣን ሽግግር የሚደረግበት ወቅት ቢሆንም አዲሱ አስተዳደር ጉዳዩን በበለጠ ትኩረት ይመለከተዋል ብለው እንደሚገምቱ እኝሁ አማካሪ ለዋዜማ ተናግረዋል።
“የዶ/ር መረራ መታሰር ብቻ ሳይሆን በሀገሪቱ የተከሰተውን ህዝባዊ አመፅ ለመፍታት የኢትዮጵያ መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ ‘አስመሳይነት’ እንጂ ፈፅሞ ችግሩን የሚፈታ እንዳልሆነና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተገን በማድረግ በዜጎች ላይ የሚፈፀመው አፈና ሀገሪቱንም ሆነ በስልጣን ላይ ያለውን መንግስት ወደተሻለ መንገድ የሚያደርሱ አይደሉም” ይላሉ ዲፕሎማቱ።
“ከመጪዎቹ ቀናት ጀምሮ የኢትዮጵያ መንግስት የማሻሻያ እርምጃ እንዲወስድ ዲፕሎማሲያዊ ጥረት ይደረጋል። ማሻሻያ ለማድረግ ፈቃደኛ ካልሆነ ግን ጠንከር ያለ እርምጃ መውስድ አስፈላጊ መሆኑን ከመግባባት ተደርሷል” ይላሉ አማካሪው።
“የፀጥታ ትብብራችንን እንደመደራደሪያ ማቅረብ የሚያዋጣ አይደለም ……. ለተሻለች ኢትዮጵያ- ህዝብን ማዳመጥና ጥያቄውን የሚመጥን ምላሽ መስጠት ያስፈልጋል” ሲሉ ያክሉበታል።
“ከወራት በፊት ዶ/ር መረራን እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ አግኝቼው ነበር፣ ለኦሮሞ ህዝብ ጥያቄና ለኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሂደት መወሰድ ባለበት እርምጃ ላይ ምኞቱን አጋርቶኛል። መንግስት ይህን አይነት አስተያየቶችን ለመስማት ካልፈቀደ ሀገሪቱን ወደባሰ ቀውስ ይገፋታል” ብለዋል።
ዶ/ር መረራ በአውሮፓ ህብረት በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ከዶ/ር ብርሀኑ ነጋ በአንድ አዳራሽ ተገኝተዋል ተብለው ወደሀገር ቤት ሲመለሱ መታሰራቸው ይታወሳል።
የአውሮፓ ህብረት የዶ/ር መረራን መታሰር በማውገዝ መግለጫ ያወጣ ሲሆን የኢትዮጵያን መንግስት በዝግ ዲፕሎማሲ ለመጫን ሙከራ እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል።
በርካታ የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎችም በኢትዮጵያ የተባባሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት መላ እንዲበጅለት እየወተወቱ ነው።

ከሚኒስትሮች ጀምሮ እስከ ታችኛው ዕርከን ድረስ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት የህወሃት አገልጋዮች መሆናቸውን አንድ የኤምባሲ ባልደርባ ተናገሩ



ከሚኒስትሮች ጀምሮ እስከ ታችኛው ዕርከን ድረስ በስልጣን ላይ የሚገኙ ባለስልጣናት የህወሃት አገልጋዮች መሆናቸውን አንድ የኤምባሲ ባልደርባ ተናገሩ
ኢሳት
አሁን በስልጣን ላይ ባለው ስርዓት ውስጥ ከሚኒስትር ጀምሮ እስከታችኛው ዕርከን የሚሰሩ በሙሉ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አገልጋዮች መሆናቸውን በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባልደርባ የነበሩ ገለጹ። ከስርዓቱ ጋር በመቆየታቸው መጸጸታቸውንም የኢትዮጵያን ህዝብ ይቅርታ ጠይቀው ከህዝብ ጎን በመሰለፍ ለለውጥ እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።
በጀርመን ፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ቆንስላ ማዕረግ የዳያስፖራ ዘርፍ ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩትና በቅርቡ ከስርዓቱ የተለዩት አቶ ግርማ መንገሻ ይህንን የገለጹት ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። በኦህዴድ አባልነት ስርዓቱ ተቀላቅለው ለደረሱበት ሃላፊነት መብቃታቸውንም አስረድተዋል።
በቆንስላው ውስጥ ከሚሰሩት የኢምባሲው ሰራተኞች አብዛኞቹ የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውን የገለጹት አቶ ግርማ መንገሻ፣ በፍራንክፈርት ከተማ ከሚገኙ የስርዓቱ ደጋፊዎች 90% የትግራይ ተወላጆች መሆናቸውም አስረድተዋል። የቀሩትም 10 በመቶ የሚሆኑት ከተለያዩ ብሄረሰብ ቢሆኑም፣ እነዚህ በሃገር ቤት ንብረትና ንግድ ያላቸው መሆናቸውን አስረድተዋል። ከመካከላቸው 1 በመቶ የሚሆኑት በቅንነት ሃገራቸውን እያሰቡ ከኢምባሲው ጋር ግንኙነት የሚያደርጉ መሆናቸው ገልጸዋል።
በዲያስፖራው ክፍል ሃላፊነታቸው ቁጥሮችን በማጋነንና በማዛባት ሪፖርት ሲያቀርቡ መቆየታቸውን፣ ይህም የተለመደና በሃላፊዎች የሚደገፍ አሰራር እንደነበርም አብራርተዋል። በዲያስፖራ የብሄረሰብ ልማት ድርጅቶችን ለማቋቋም የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን፣ በደቡብ በኩል የልማት ማህበር ተብሎ የተቋቋመ ቢኖርም፣ አባላቱ ራሳቸው አመራሮቹ ብቻ መሆናቸውን አስረድተዋል። የትግራይ ልማት ማህበር ግን ቀደም ሲልም የነበረ መሆኑን አብራርተዋል።
በኦሮሚያ ክልል ዓመጽ በተቀጣጠለው ወቅት ዓመጹን ተቆጣጥረዋል የሚል መግለጫ እንዲሰጥ ተዘጋጅቶ ነበር ያሉት አቶ ግርማ መንገሻ፣ የሟቾቹን ቁጥር እንዳንናገር እንከለከል ነበር ሲሉም አስታውሰዋል። በኢትዮጵያ ሰብዓዊ ይዞታ ላይ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች የሚሰጡት መግለጫ እንዲለዝብ ስራ ይሰጠን ነበር ያሉት አቶ ግርማ መንገሻ፣ ሰብዓዊ መብት አለመርገጥ እየተቻለ፣ ሪፖርቱ መደበቁ እንዳማይገባቸው ለኢሳት ገልጸዋል።
በአጠቃላይ በስርዓቱ ውስጥ ከትግራይ ተወላጆች ውጭ ያሉ ከሚኒስትር እስከ ተራ ሰራተኛ ሚናቸው አገልጋይነት መሆኑንም በመዘርዘር ስልጣን በህወሃት ሰዎች እጅ መሆኑን አስረድተዋል

” ዶ/ር መረራ ጉዲናን ማሰር የአምባገነንነት ማሳያ ነው” ዶ/ር አረጋዊ በርሄ



VOA -ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
ዋሽንግተን ዲሲ — “የኢትዮጵያ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ መብት እንዲጎናፀፍ በሰላማዊ መንገድ ያላሰለሰ ትግል የሚያደርጉትን ዶ/ር መረራ ጉዲናን ማሰር የአምባገነንነት ማሳያ ነው” ሲሉ የቀድሞ የሕወሓት ታጋይና የትግራይ ዴሞክራሲያዊ ትብብር ሸንጎ ሊቀመንበር ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ተናገሩ።ዓለም አቀፉ የመብት ተሟጋች ድርጅት በበኩሉ ኢትዮጵያዊው የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ዶር መረራ ጉዲና መታሰራቸው “በመናገር ነጻነት ላይ የተወሰደ ቅጥ ያጣና አናዳጅ እርምጃ ነው” ብሎታል
የአምነስቲ የምስራቅ አፍሪካ፣ የአፍሪካ ቀንድና የታላላቅ ሃይቅ ሀገሮች ምክትል ስራአስኪያጅ ሚሸል ካጋሪ የዶር መረራ እስራት “ለወራት የዘለቁ የበርካታ ሰዎች ሕይወት የጠፋባቸውን ሰልፎች ከመቆስቆስ ባለፈ መፍትሄ አይሆንም” ብለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት የህዝቡን የሰብዓዊ መብት ሮሮዎችና የአስተዳድር መከፋቶችን ተጨማሪ የመብት ጥሰቶችና እስራትን በማከል መፍታት እንደማይችል አምነስቲ አሳስቧል።

Friday, December 2, 2016

የአውሮፓ ኅብረት የማይታጠፍ ጫና ኢትዮጵያ ላይ እንዲያሳድር ተጠየቀ ቆንጅት ስጦታው  



የአውሮፓ ኅብረት የማይታጠፍ ጫና ኢትዮጵያ ላይ እንዲያሳድር ተጠየቀ
አና ጎሜዥ
በኢትዮጵያ መንግሥት ትናንት የታሠሩት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድነት መድረክና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ መሪ ዶ/ር መረራ ጉዲና የተገኙበትን የአውሮፓ ፓርላማ የእማኝነት መስሚያ መርኃ ግብር ያዘጋጁትና ግብዣውንም ያደረጉት የፓርላማው አባል አና ጎምሽ የአውሮፓ ፓርላማ የዶ/ር መረራን እሥራት በብርቱ እንዲያወግዝ ጠይቀዋል፡፡
ዶ/ር መረራ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ያለማወላወል ጫና እንዳያሳድሩና መታሠራቸው በራሱ ኢትዮጵያ ግዴታ የገባችባቸውን የኮቶኑ ስምምነት የሰብዓዊ መብቶች ድንጋጌዎች የጣሰ መሆኑን የኅብረቱ ኮሚሽን ምክትል ፕሬዚዳንት ሞጌሪኒ አጢነው በብርቱ እንዲያወግዙት አና ጎምሽ አሳስበዋል፡፡
ዶ/ር መረራ ጉዲና /ፎቶ ፋይል/
ዶ/ር መረራ ጉዲና /ፎቶ ፋይል/
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የሪዮ ኦሊምፒክ የማራቶን የብር ሜዳልያ አሸናፊው ፈይሣ ሌሊሣ የአውሮፓ ፓርለማ መቀመጫ ወደሆነችው የቤልጅግ ዋና ከተማ ብራስልስ ሄደው በኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ እማኝነታቸውን እንዲሰጡ የጋበዙ፣ መድረኩንም ያዘጋጁት አና ጎምሽ የዶ/ር መረራ መታሠር “ቢያስደነግጠኝም አልገረመኝም” ብለዋል፡፡
Audio Player
Vm
P
ለተጨማሪ ዘገባውንና ከአና ጎምሽ ጋር የተደረገውን ቃለ ምልልስ ሙሉ ቃል የያዘውን ፋይሎች ያዳምጡ

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ዶ/ር መረራ መታሠር ቆንጅት ስጦታው

  


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ስለ ዶ/ር መረራ መታሠር
“የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበር የሆኑት ዶክተር መረራ ጉዲና በኢትዮጵያ መንግሥት መታሠራቸውን ሰምተናል፡፡ ዘገባው አሳስቦናል፡፡ መንግሥቱ በዶክተር መረራ ላይ ያለውን ማንኛውንም ክሥ ለሕዝብ እንዲያሳውቅ በፅኑ እናበረታታለን፡፡ የመታሠራቸው ነገር እውነት ከሆነ አድራጎቱ ኢትዮጵያ ውስጥ ነፃ ድምፆችን ለማፈን የሚጣሉት ገደቦች እየተጠናከሩ ለመምጣታቸው አንድ ተጨማሪ ማሳያ ነው የሚሆነው፤ በግልፅ ለመናገር ደግሞ ኢትዮጵያ ያወጀችው የአስቸኳይ ጊዜ ሁኔታ ምናልባት …

አዎን ፈሪዎች ነን፤ ግርማ በቀለ ወ/ዮኃንስ



አዎን ፈሪዎች ነን፤ ግርማ በቀለ ወ/ዮኃንስ
ፈሪዎች ስለሆንን ከአገርና ከወገን መለየትን አንደፍርም፤
ፈሪዎች ስለሆንን ከአገርና ከወገን መለየትን አንደፍርም፤
ፈሪዎች ስለሆንን ከስደት ይልቅ ማሰቃያና ማጎሪያ  ቤቶችን፣ሲያልፍም የህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል  እንደፍራለን፤
ፈሪዎች ስለሆንን ውርደትና ጭቆናን ለመሸከም ድፍረት የለንም፤
ፈሪዎች ስለሆንን የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲን ለመሸከም አቅም አጥተናል፤ …….
በመሆኑም ፡-
ለህዝባችን ጭቆና አይመጥነውም ብለን ስለምናምን  ኑሮኣችንም ሞታችንም በአገራችን ከህዝባችን ጋር ይሆን ዘንድ መርጠናል፡፡ ዋጋው ጠፍቶን አይደለም፡፡ ሰላማዊ ዜጎች መብታቸውንና ክብራቸውን በመጠየቃቸው፣ አገሬን በማለታቸው የደረሰባቸውን ሳናውቅና ስላልደረሰብን አይደለም፤ የተገደሉትን፣ አካላቸው የጎደለውን፣ የተሰደዱትን የአገርና ወገን ብርቅዬ ልጆችና ለሌላውም የሚተርፉ ምሁራን ፣ በእስር ቤት የሚሰቃዩትን፣ … ከርቀት ሳይሆን ከድርጅታችን ጭምር  በቅርብ እናውቃለን፡፡ ይህን እየጻፍኩ ባለሁበት የድርጅታችን የኦሞ ህዝቦች ዲሞክራሲያዊ ኅብረት/ኦህዲኅ/ ም/ሊቀመንበርና የዞኑ ሰብሳቢና ጽ/ቤት ተጠሪ መምህር ዓለማዬሁ መኮንን ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የዞን ሥራ አስፈጻሚ አባላችን ወጣት ዳዊት ታመነ ፣የዞን ምክትል ሰብሳቢ መምህር ኢንድሪስ መናን ፣ የዞኑ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላችን ወጣት መሃመድ ጀማል  በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሥም በእስር ቤት ናቸው፡፡ ከዞኑ ሥራ አስፈጻሚዎች የቀሩት ሦስት ብቻ ናቸው፡፡ ወጣት ዳዊት ታመነ አምና አቶ ዓለማዬሁና ሌላው የዞን ሥራ አስፈጻሚ አባላችን አቶ አብረሃም ብዙነህ፣እንዲሁም ወዳጃችን አቶ ስለሺ ጌታቸው በፀረ- ሽብር ህጉ ከጂንካ ከ500 ኪ/ሜትር በላይ ርቀት ተወስደው አዋሳ በታሰሩ ጊዜ እስከሚፈቱ ተመላልሶ ይጠይቅና ጉዳያቸውን ይከታተል የነበረ ቆራጥ ታጋይ ነው፡፡ድርጅታችንና  ዳዊት በየትም የሚደረግ  ሰላማዊ ትግል አጋር ናቸው፡፡ ዳዊት አሁን የታሰረው  የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነውን የጎጃሙን  ሰማዕት የ ‹‹ሣሙኤል አወቀ›› የዝክር ቲ-ሸርት ከቤቱ መገኘቱ ከ‹ወንጀል› ተቆጥሮበት  ነው፡፡  አዎን ዛሬም ነገም በየትም የአገራችን ክፍል የሚደረገው የነጻነት፣ የመብት ህዝባዊ ትግል አጋር ነን፡፡ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎችን ሰላማዊ ትግል፣ በኦሮሚያ፣ በአማራ ክልል፣ በኮንሶ ህዝብ … የተደረጉት ህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች አጋርነታችን በአደባባይ ገልጸናል፡፡አማራ በራሱ ተወካይና አስተዳዳሪ ሲሰደብ እስከ ባህርዳር ተጉዘን አውግዘናል፡፡
እስራትን እኛም ታስረን- ለዚያውም ከመኖሪያችንና ከሥራችን ቦታ በ750 ኪ/ሜትር ርቀት፣ ለዓመት ያህል ታስረን አይተነዋል፡፡ እስራትን አንድ ጊዜ ሳይሆን ደጋግመን አጣጥመነዋል፡፡ ለብቻችን ሳይሆን ባለቤታችንና ወዳጆቻችን ጋርም እስራትን ቀምሰናል፤ ሩቅ ሳይሆን ካቻምና፡፡  በዚህ ሁሉ ውስጥ  እየወደቅን እየተነሳን ላለፉት 25 ዓመታት በሰላማዊ ትግል  የገፋነው፣ዛሬም  ‹‹ሣይቃጠል በቅጠል ›› እያልን የምንጮሄው  መከፈል ያለበትን ለመክፈል ስለወሰንን ፤ ስለሁላችን መብት፣ክብርና ጥቅም፣ ‹የአገራችን ታላቅነት› መመለስ  ነው፡፡
ሰላማዊ ትግል የሚጠይቀንን መክፈል የወሰነው ደግሞ የትግሉም የለውጡም ቀዳሚና ዋነኛ (ብቸኛ አይደለም)  ባለቤት አገር ቤት ያለው  ህዝብ በመሆኑና ፣ለዘላቂ መፍትሄው ለውጡ በሠላማዊና ሠላማዊ  መንገድ ብቻ መሆን አለበት በሚለው ላይ የጸና አቋም ስላለን ነው፡፡ ከተለመደው  በኃይል የሚደረግ  የአሸናፊዎች የሥልጣን  ሽግግር በዘላቂ ሰላማዊ ሁላችን አሸናፊ የሚያደርግ የሥርዓት ለውጥ  መሆን አለበት በሚለው ላይ ግልጽና የማይናወጥ ጠንካራ እምነት ስላለን ነው፡፡ ለዚህም ነው ለዘላቂ መፍትሄ  በአገራችን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ ወገኖችን ሁሉ አካታች የሽግግር መንግስት በማለት ደጋግመን የምንጮሄው ፣ ለተግባራዊነቱ ያለማሰለስ የምንታገለው – ስለሁላችንና አገራችን ስንል ፡፡
ግን ፣
የምንፈራው ዘረኝነት ነግሶ – መከባበር፣ መተማመንና የወንድማማችነት መንፈስ ረክሶ፣ የወንድም ደም በወንድሙ ፈሶ….የትናንት አብሮነታችን ተዘንግቶ፣ የጋራ ተጋድሎኣችንና የሁላችን ድሎች ተረስተው ብቻ ሣይሆን ለ‹‹ከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ›› ማዳበሪያ፣ ‹ምርጥ ዘር› እና  የመስኖ ውሃ ሆኖ እንዲያገለግል የተሸረበብን ሴራ ስር እንዳይሰድ እንጂ በአገራችን ፣በህዝባችን መሃል ሆነን ይህ ሴራ እውን እንዳይሆን ለመቀልበስ በሚደረገው ሰላማዊ ትግል የሚጠይቀውን ዋጋ ለመክፈል አይደለም ፡፡የፈራነው የክብራችንን መደፈር እንጂ ማስከበርን አይደለም፣ ለዚህማ ዋጋ እየከፈልን አስርተ ዓመታትን አስቆጥረናል፡፡
ነጻነታችንን ማስነጠቅን ክብራችንን ማስደፈርን ፈራን እንጂ በአገራችን በጭቆና ውስጥም ቢሆን ስለክብራችንና ነጻነታችን መጠየቅን አይደለም የፈራነው፡፡ የፈራነው እነርሱ ገዢዎችና ጨቋኞች እንድንፈራ የፈለጉትን- ነጻነታችንን መጠየቅ፣ ክብርና መብታችንን ማስከበር ሳይሆን  በተቃራኒው እንዳንደፍር የፈለጉትን ያለፍርሃት ተጋፈጥን ፤ በፍላጎታቸው ቦይ አልፈሰስንም፤ አንፈስም፡፡ አዎን በኦሮሚያ ‹‹ የአማራው ደም ደሜ ነው›› ፣በአማራ ‹‹የኦሮሞው ደም ደሜ ነው›› የሚል መፈክር መስማት፣ ኢትዮጵያዊያን በሚገኙበት የዓለም መዳረሻ በሙሉ የአማራው፣ የኦሮሞው ፣ የኮንሶው ፣ የጋምቤላው፣ የሱማሌው፣ .. ጉዳይ ጉዳዬ ነው የሚል የጋራ ድምጽ በአንድነት ሲሰማ ፍርሃታችን ይገፈፋል፣በተቃራኒው እነርሱ የዘረኝነት ድልድያቸው በመሰበሩ  ፣ የመከፋፈል መርዛቸው በመርከሱ  ፍርሃት ያርዳቸዋል፡፡ በቅድሚያ የተከተልነው አቅጣጫ ትክክለኛ፣ የተያዝነው ትግል ሰላማዊና የዘላቂ መፍትሄ አዋላጅ፣ ዓላማችን የሁላችን በሁላችን የምትገነባ የዜጎች እኩልነትና መብት፣ ዲሞክራሲና የህግ የበላይነት የተከበረባት ፣የሁላችን  ፍትሃዊ ጥቅምና ፍላጎታችን የምናረካባት በልማትና ታሪክ የቀደመች፣ ስመጥር ሉዓላዊት አዲስቱን ኢትዮጵያ መመስረት ነውና የምንፈራው እነዚህን እንዳንጠይቅ ለእነዚህ እንዳንታገል ቀፍድዶ የሚያስረውን መከፋፈልና አንድነት ማጣት  እንጂ ስለነዚህ የሚከፈለው ዋጋ አይደለም፡፡ የምንፈራው ከሰው በታች የሚያውለንን ጭቆና አሽቀንጥሮ ለመጣል ከሚደረገው ትግል የሚያግተን  ለአብሮነታችንና ለተባበረ ትግላችን እንቅፋት የሚሆኑ ሁኔታዎችን ነው፡፡
የስደት መንገድ ባይጠፋንና ፤ ገና በወጣትነታችን- በላጤነታችን ከዓመት እስራት ከወጣን  በኋላ  አውሮፓና አሜሪካ ብንሄድም፤
ከዚያ በኋላም በተለያዩ  የሥራ አጋጣሚዎች ደጋግመን ከአገር ወጥተን ብናውቅም ፤……ስደትን በእጅጉ እንፈራለን፡፡
ብርቅየዋ የአገር ልጅ ዓለም ጸሃይ ወዳጆ በግጥሟ እንደገለጸቺው ስደት መነቀልና ባዶነት ነው፤ የፈለግነው ቁሳዊ ፍላጎት ሁሉ ቢሟላ ያለመርካት፣ ምግብ በሞላበት መራብ፣ የሚጠጣው በሞላበት መጠማት… ፣ሁሌ  ‹‹ ማን እንደሃገር ፣ማን እንደ ወገን›› እያሉ በትዝታ መቆዘም፣ ከአገርና ወገን ናፍቆትና ሰቀቀን የጸዳ የተሟላ ሥነልቡናዊ መደላደል ማጣት፡፡ ስደት ክብርን ይነጥቃል፣ ለውርደት ይዳርጋል፡፡ ‹‹ ከአገሩ የወጣ አገሩ እስኪመለስ- ቢጭኑት አህያ ቢለጉሙት ፈረስ ›› እንዲል የአገሬ ሰው፡፡ ይህ አገሩን ይዞ ይዞራል ለሚባለው ኢትዮጵያዊ ምቾትን ሙሉ አያደርግም ሳይሆን ምቾት ይነሳል፡፡ ይህም በአገር ከህዝባችን ጋር አብረን ኖረን፣ አብረን ለመሞት ያለንን  የጸና አቋማችን  የሚያጠናክር ነው፡፡ ይህን ደግሞ ዕድሜ ለመረጃ ቴክኖሎጂ ዘመን- ዓለም መንደር ሆናለችና ሄደን ‹በባዶነት› ተሰቃይተን ማረጋገጥ የለብንም፡፡ በተለያየ ምክንያት በተለይም ያለንበት የመረረ ጭቆናን በአገራቸውና ህዝባቸው መሃል ሆነው ማየትና መቋቋም ፣… ያልቻሉ (የጭቆናው  ቀንበር ለኅሊናቸው ሸክም አቅም በላይ የሆነባቸው)፣ በአገራቸው እንዳይኖሩ በወጡበት እንዲቀሩ የተገፉ፣  በአገራቸው ጥረው ግረው የመኖር ዕድል ያጡ፣ የዕድሉ በር የተዘጋባቸውና ተስፋቸው የተሟጠጠ፣ የኑሮውን ጫና መሸከም ያልቻሉ ግን ከእኛ በማያንስ ሁኔታ ስለአገራቸውና ወገናቸው የሚንገበገቡ ስደተኛ ወገኖቻችን የሚያከፍሉን የስደት ኑሮ ተሞክሮና መረጃ ከበቂ በላይ ነው፤ ትግሉንና መስዋዕትነትን ሳይሆን ስደትን የሚያስፈራ ነው፡፡ የሰላማዊ ትግል አርበኛው እስክንድር ነጋ አስተምህሮም ይሄው ነው፡፡ ስለሆነም ስደተኛ ወገኖቻችን በአገራችን ከህዝባችን ጋር አብረን ኖረን፣ አብረን ለመሞት አደፋፈሩን እንጂ አላስፈራሩንም፡፡ የስደትን ክብደት አስተማሩን እንጂ ለቁሳዊ ፍላጎት እንድንገዛ አልቀሰቀሱንም ፡፡ ከእነርሱም የተማርነው  ‹‹ ነቢይ በአገሩ አይከበርም››  የሚለውን ነውና በእነርሱ ውስት ያለው ለሌላው የሚተርፍ እምቅ አቅም የወሰድነውን አቋም አጠነከረልን እንጂ፣ ቀበቶኣችንን እንድናላላ አላደረገንም፡፡ ስለዚህም ስደትን ፈራን፤ አዎን ለዚህ ፈሪዎች ነን፡፡ ሰው እንኳን  በቀዬውና በአገሩ  ቀርቶ በተሰደደበትም ያለውን የሰው ልጅ ክብርና ነጻነት ነገሩንና በአገራችን ያለው ጭቆና እስከአጥንታችን ዘልቆ ገብቶ እንዲሰማን ፣ የተያዝነውን የነጻነት ትግል እንዲናጠናክር የሞራል  ስንቅ አቀበሉን እንጂ ስለመብትና ክብራችን መሞትን እንድንፈራ አላስተማሩንምና ፣ ስለነጻነታችንና ክብራችን ደፈርን፡፡
የዓለም ህዝብ ወደፊት እየገሰገሰ ባለበት ወደኋላ የመመለሳችን ጉዳይ ያስፈራናል ፣ለዚህ በጣም ፈሪዎች ነን፡፡ ይሁን እንጂ ወደነበርንበት የሥልጣኔ፣ የመከባበርና አብሮነት፣ የጀግንነትና ተጋድሎ የጋራ ታሪክ ከፍታ ለመመለስ የምናደርገው ትግል የሚጠይቀው ዋጋ  ከቶውንም አያስፈራንም ፡፡
ትናንት – የ‹ፈርስት ሂጂራ› መሪ እንዳሉት በዓለማችን የመጀመሪያዋ ስደተኛ ተቀባይ አገር ነበርን፤ በታሪካችን ከተራቡ  አፍሪካዊያን ወንድሞች አልፈን እስከ አውሮፓ ድረስ ለተራቡ መጋቢ ነበርን ፣በጥንታዊ ሥልጣኔ ተምሳሌት አገሮች ተርታ እንጠቀሳለን፣ ( የጥንታዊ ሥልጣኔ ትውፊቶችና አሻራዎች ዛሬም ድረስ አሉን፣ በቱሪስቶች እየተጎበኙ ነው)፣  የቅኝ አገዛዝ አስነዋሪዎችና የጥቁር ህዝብ የነጻነት አርኣያዎች ….. ነበርን፤ ‹ነበርን› ፡፡ ነገር ግን ከእነዚህ አንጻር  ዛሬ ዓለም ከደረሰበት ደረጃ ስንታይ የዓለም ጭራ ሆነናል፡፡ ስደተኛ ተቀባዮች -ስደተኛ፣ የተራበ መጋቢዎች – የረሃብ ምሳሌዎችና ምግብ ተመጽዋቾች፣ የሥልጣኔ ቁንጮዎች – የኋላቀርነት ተምሳሌቶችና ያልተጣራና ያልተመዘነ የውጪ ሸቀጥና ቴክኖሎጂ ማራገፊያዎች፣ ከቅኝ አገዛዝ ተጠያፊነት ማማ ወርደን ‹ወዶ ገቦች› እና የነጻነት አፋኞች ተላላኪ ተዋጊዎች …. ሆነናል፡፡ በዓለም ፊት ረክሰናል፤ ተዋርደናል ማለት ይቻላል፡፡ ያስቆጫል፣ ያንገበግባል፡፡ በጨቋኝ አገዛዝ መንግስታት ተደጋጋሚ በትርና ሥር የሰደደ ጭቆና የትናንቱን አብነትና ትውፊት ከበጎ ጎኑ በተቃራኒ በማተኮራችን የኋሊዮሽ መጓዝ ተገደናል፡፡ ከአንድነታችንና አብሮነታችን ፣ ከጋራ ተጋድሎኣችንና ድሎቻችን በልዩነታችንና በገዢ አመራሮች በደል ላይ እንድናተኩር በመሆኑ ለገዢዎቻችን ተመችተናል፡፡  በተለይ በዚህ በዛሬው የጥቂት ዘረኛ  ቡድኖች   በተሰመረልን አቅጣጫ በተያያዝነው መንገድ  የ‹ሴራው› ሰለባ ሆነን ከቀጠልን  ከዚህ ወደከፋ አዘቅት፣ መቀመቅ መውረዳችን ፣ ለበለጠና የከፋ ውርደት መዳረጋችን አሌ አይባልም፡፡ የሚያስፈራን ይህ ‹ሴራ› የሚያመጣብን ጣጣ እንጂ ይህን ‹ሴራ › ለመቀልበስ የሚደረገው ትግልና የሚጠይቀው መስዋእትነት አይደለም፡፡ በኋሊዮሽ ጉዞኣችን ፣በመለያየታችንና መከፋፈላችን  የደረሰብን እንዳይደገም በተሻለና ወቅቱን በሚመጥን ፣ከዘመኑ በማይጣላ ፣….ከዓለም ጎን  የሚያቆመን፣ በሂደትም ከነበርንበት ከፍታ የሚመልሰን ሥርዓት እውን እንዲሆን አዲስቱን ኢትዮጵያ የመገንባት ተግባር የሁላችን መሆኑን ለመስበክ፣ ለዚህ ተግባራዊነት መስዋዕትነት መክፈል ለነጻነት፣ ለራስ ክብርና ማንነት፣ለሰብዐዊነት  የምንሰጠውን ቦታና ዋጋ የሚያሳይና ክብርን የሚያጎናጽፍ አኩሪ ተጋድሎ መሆኑን በመረዳታችን የምንፈራው ከዚህ ተጋድሎ ወደኋላ የሚጎትተንን ሁኔታ እንጂ  ትግሉ የሚጠይቀውን መስዋዕትነት አይደለም፡፡
አብረሃ ደስታ ‹‹የሰላማዊ ትግል በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ›› እንዳለው እየሆነ ያለው በጊዜ የአመጽ በሩ እንዲዘጋ ገዢው ህወኃት/ኢህአዴግ  ከተያያዘው የተለመደ የትዕቢት፣ እብሪትና ሴራ ፖለቲካ ወጥቶ ሁላችንን አሸናፊ ለሚያደርግ  ሁሉም የአገር ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ኢትዮጵያዊያን ተቀራርበው ብሄራዊ መግባባት የሚፈጥሩበት  ዕርቅ የሚወርድበት የውይይትና ድርድር መድረክ ተዘጋጅቶ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ካልተዘጋጀ በአገርና ወገን የሚያስከትለው ጥፋት በእጅጉ  ያስፈራናል እንጂ፤ ይህን አስፈሪና አሳሳቢ ሁኔታ ለመቀልበስ የሚጠይቀው መስዋዕትነትና ዋጋ አያስፈራንም፡፡
ህወኃት/ኢህአዴግ  እንደለመደው በተያያዘው መንገድ መቀጠልና ‹በጥልቅ ተሃድሶ› ታድሼ፣ ተጠናክሬ ወጥቼ የጭቆና ቀንበሩን አክብጄ እቀጥላለሁ በሚል ‹በአስቸኳይ አዋጅ›  ህዝብንና የሰላማዊ ትግል ሃይሎችን አትስሙ፣ አትናገሩ፣ አትነጋገሩ፣ አትመልከቱ ፣ አትገናኙ/አትሰብሰቡ  … በሚል መተንፈሻ አሳጥቶ፣ በእስራትና ወከባ አጅቦ የሰላማዊ ትግል ምህዳሩን መዝጋቱ፣ የህዝቡን  እምቢተኝነት ማፈኑ … ጊዚያዊ እፎይታ ይሰጠው እንደሆን እንጂ ህዝባዊ ትግሉን አይቀለብሰውም፣ አያስቀረውም፤ይልቁንም የአመጹን በር አስፍቶ ይከፍተዋል፣ በሰላማዊ ትግል ላይ ያለውን የተሟጠጠ የህዝብ ተስፋ ጨርሶ ያጠፋዋል፡፡ በኦሮሚያ ፣አማራ፣ ኮንሶ፣ የ‹በቃኝ› ህዝባዊ እምቢተኝነት እንቅስቃሴዎች ወደ ከፍተኛ ደረጅ ይገፋቸዋል፣ ሌሎችን ዜጎች የእምቢተኝነት ትግሉን እንዲቀላቀሉ ያነሳሳቸዋል ፤ የሰላማዊ ትግል ሰባኪዎችንና ታጋዮችን ወደ በረሃ ይገፋቸዋል ( የትናንት ሰላማዊ ታጋዮች እነ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ፣ የሰማያዊ ወጣቶች፣ የመኢአድ አባላት… ዛሬ የት እንዳሉ ያጤኑኣል ) ፣የሌላውን አማራጭ  ተከታዮችን አብዝቶና አጠናክሮ (ከአገር ቤት ከአርባምንጭ ድረስ ፣ ከውጪ ከአውሮፓ አገራት ጭምር የትጥቅ ትግሉን የተቀላቀሉትን ያስታውሷል) ….. ወደተለመደው በመሳሪያ ኃይል የመተማመንና የኃይል/ትጥቅ ትግልና የአሸናፊ ጠቅላይ ወይም /እና አግላይ (ህወኃትን) የመንግስት ሽግግር አዙሪት ይከተናል፡፡ ይህን እንፈራለን ብቻ ሳይሆን በእጅጉ እንፈራለን፡፡  በወንድማማቾች መካከል በሚደረግ የትጥቅ ትግል/ጦርነት በዜጎች ህይወትና አካል፣ በአገር ሃብትና መሰረተ ልማት የሚያደርሰውን ጥፋትና ውድመት እንዲሁም  የቱንም ያህል የታጠቀና በወታደራዊ ኃይል የተደራጀና የተጠናከረ ጨቋኝ አገዛዝ  ህዝብን አሸንፎ  እንደማያውቅ … ለህወኃት/ኢህአዴግ መካሪ የሚያሻው ጉዳይ አይደለም፡፡ ህወኃት ደርግን ብቻዬን አሸነፍኩ በሚል ግብዝነት ታስሮ በሌሎች የኢህአዴግ አባል ድርጅቶችና በህዝብ ላይ ከሚያሳየው እብሪት ራሱን ነጻ ማውጣት እንዳለበት፣ ለራሱም ለአገሪቱም የሚበጀውን መንገድ ሊመለከት ግድ እንደሚለው፣ ለውጡ አይቀሬ የመሆኑ ሃቅ በህዝባዊ የእምቢተኝነት ትግልና በዲፕሎማሲ መድረኮች በግልጽ ሊነገረው ይገባል ፡፡ ትናንት ህወኃት በአሸናፊነት ሥነ ልቡና ያገለላቸውና  ‹‹ እንዳያማህ ጥራው፣ እንዳይበላ ግፋው ›› በሚል ለይስሙላ አሳትፎ ከሽግግሩ ወቅት ‹ያባረራቸው› ዛሬ ድረስ ህወኃት/ኢህአዴግን ብቻ ሳይሆን አገሪቱንና ህዝቡን እያስከፈለ ያለው ዋጋ መረሳት ያስፈራናል፡፡ ይህ እንዳይደገም የምናደርገው ሰላማዊ ትግል ግን አያስፈራንም፤ ቅንጣት ያህል ፡፡
ህወኃት/ኢህአዴግ የትግራይን ህዝብ ከሌሎች ወንድሞቹ ለመነጠል የሚያሰራጨው ፕሮፖጋንዳና የሚፈጽመው ተግባር በህዝብ ላይ የፈጠረው ስሜት በእጅጉ ያስፈራናል  እንጂ ፣ይህን አደገኛ አዝማሚያና አፍራሽ አስተሳሰብ ለመቀልበስ የሚጠይቀው መስዋዕትነትና  ዋጋ አያስፈራንም፡፡ የትግራይ ህዝብ ላይ የተጫነውን ጭቆና ድርብ ድርብርብ መሆኑን መረዳት ፣ህዝቡ  ቀርቶ ህወኃትም የመፍትሄው አካል የመሆኑ አስፈላጊነት ላይ ጠንክረን መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ አካታች መድረክ የምንለውም ይህንኑ ነው፡፡ ይህን ስናደርግ ህወኃት ‹‹የትግራይ ህዝብና ህወኃት፣ የኢትዮጵያ ህዝብና ኢህአዴግ አንድ ናቸው፤ ዕጣ ፈንታቸውም የተያያዘ/የተሳሰረ  ነው፡፡ እኛ ህወኃት/ኢህአዴግ ከሥልጣን ከወረድን አገር ትፈራርሳለች …›› የሚለው ማስፈራሪያ ይንኮታኮታል ፡፡
ሌላው የአገራችን ህዝብ የህወኃት ፕሮፖጋንዳ ሰለባ ሆኖ ከትግራይ ህዝብ ጋር ያለው ግንኙነት ከጥያቄ የመግባቱ አዝማሚያ ፣ የመተማመንና ወንድማማችነተ መንፈስ መሸርሸሩ ጉዳይ ያስፈራናል እንጂ፣ ይህን ለመቀልበስ …. የምንከፍለው ዋጋ  አያስፈራንም፤ ለዘላቂ ለውጥ ለጤናማ የህዝብ ግንኙነት…. አብሮነትና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ አንድነት መከፈል ያለበት ዋጋ ነውና- አያስፈራንም፡፡
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች  የጥቂት ዘረኛና ጠባብ ጥቅመኛ ቡድን አባላት ጥቅም ለማስጠበቅ ፣ ሥልጣን ለማስቀጠል ጋሻ መከታ ሆኖ የማገልገል የተላላኪነት ሚና ያሳስበናል እንጂ፣ ይህን ለመመከት ጥቅመኞችንና ተላላኪዎችን ከህዝብ ለመለየት የሚጠይቀው መስዋዕትነት አያስፈራንም፡፡ …. የምንፈራው ስለአገር ስለወገን ከምንከፍለው መስዋዕትነት የሚጎትተንን፣ የመስዋዕትነታችን ውጤታማነት የሚያኮላሽ፣ ….የህዝባችን ሥቃይና መከራ ዘመን የሚያራዝም ሁኔታ እንጂ ፣ወደ ትግሉ ስንገባ ያለመስዋዕትነት ድል ያለመኖሩን ተቀብለን ነውና  ይህ አያሳስበንም፣ አያስፈራንም ፡፡
ግን የኢትዮጵያ ህዝብ እንደማይከፋፈል፣ አገሪቱም በማንም መቼውንም እንማትጠፋ፣ የዚህ ጠባብ ዘረኛ አገዛዝ ዘመንም የህዝባችን  አንድነት ሊያጠናክር ፣ የአገራችንን ቀጣይነትና ዘላቂ ሰላምና ክብር በጠንካራ መሰረት ላይ እንድታነጽ በጥልቅ እንድንፈተንበት የመጣ ነው ብለን ስለምናምን በጥቂት ዘረኞችና ጥቅመኛ ቡድኖች የተሸረበው ሴራ እንደሚከሽፍ፣ ለውጡ አይቀሬ ስለመሆኑ  አንጠራጠርም፡፡  ስለዚህም አንፈራም፡፡
በሰላማዊ ትግል  ከተሰለፉ የአገር ቤት ሰላማዊ ታጋዮች አልፎ በውጪ አገር ባሉ ድርጅቶች መካከል  መከባበርና መወያየት፣ …. መጥፋቱ  የተናጠል ሩጫው፣ መከፋፈልና አንጃው፣ አለመተማመን፣  ተባብሮ በአገራዊ ጉዳይ ላይ አብሮ በመስራት ደጋግሞ መክሸፍ፣ ….. ህዝብ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ያለው እምነት ላይ ያሳደረው አሉታዊ ተጽዕኖ  በእጅጉ ያሳስበናል፣ ያስፈራናል፡፡  ይሁን እንጂ ይህ የተቃውሞ ጎራው  ያለመተማመንና አብሮ የመስራት ችግር እንዳይቀጥል ‹ማዶ ለማዶ› ከሚተያዩበት፣ ሲያልፍም ከሚጠላለፉበት ሁኔታ ወጥተው አብረው እንዲሰሩ ለሚደረገው ጥረት የምናደርገው አስተዋጽኦ  አያስፈራንም፣ ይቀጥላል፡፡
ለትግሉ የምንከፍለው መስዋዕትነት አያስፈራንም ስንል የእኛ ትግል የሚፈራው ጭቆናና ጨቋኞችን እንጂ አንዱን ወይም ሌላውን  ህዝብ ባለመሆኑ፣ የትግላችን ግብም አንድን ጨቋኝ በሌላ ለመቀየር፣ ወይም በጥላቻ ላይ ቆሞ  ህወኃት/ኢህአዴግን በማስወገድ ብቻ ያልተወሰነ፤ በአገርና ህዝብ ዘላቂ ጥቅምና ሰላም፣ በእኩልነትና ፍትሃዊነት በምንገነባው አንድነት ላይ ያነጣጠረ፤ መሰረታችን፣ የጥንካሬና ጽናት ምንጫችን እውነትና እውነት ብቻ  በመሆኑ ነው፡፡  ስለዚህም ፍርሃታችን ትግላችን በዝና፣ በሥልጣን ጥማት፣ ሃብትና ጥቅም  ዓላማውን  እንዳይስትና የሥቃይ ዘመናችን እንዳያራዝም፤ በጥላቻ፣ እብሪት፣ ማንአለብኝነትና  የኃይል አምልኮ እንዳይጠለፍ፤ ከዘላቂ፣ሰላማዊ…. ሥር ነቀል የሥርዓት ለውጥ በተቃራኒ አቅጣጫውን ወደ አግላይና ጠቅላይ የሥልጣን ሽግግር እንዳያዞር  ነው፡፡
በውጪ አገር አሁን የተጀመረው የ‹ ቪዥን -ኢትዮጵያ/ ኢሳት› ስለመጪዋ ኢትዮጵያ ፣ የሎንዶንና አትላንታ የኦሮሚያ ተወላጆች ‹ በትብብር ስለመስራት› በተደረጉት የውይይት መድረኮች የተንጸባረቁት ሃሳቦች፣  ….ትምህርታዊነቱ ለመማር ለሚፈልግ ጅምሩ ጥልቅ መልዕክት አለው፡፡ ይህ እንደተለመደው  አንዳይከሽፍ ሥጋት ቢኖረንም በጅምሩ ያለን ተስፋ የቀጣዩን ጊዜ ብሩህነት ያመላክታል፡፡ እንዲህ ዓይነቱን  ጥረት ለማበረታታትና ለማገዝ የምንቆጥበው የለም፡፡ በተመሳሳይ በአገር ቤት እንዲህ ዓይነቱ ትርጉም ያለው ውጤት ሊያመጣ የሚያስችል  የተቃውሞ ጎራው ግንኙነት እንዲጀመር የነቃ ተሳትፎ ለማድረግና የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማበርከት ያለንን ቁርጠኝነት ስናረጋግጥ የፈራናቸው ጉዳዮች  እውን እንዳይሆኑና በአገርና ህዝብ ላይ ጥፋት እንዳያመጡ እያንዳንዱ ዜጋ ያለማሰለስ በንቃት መሳተፍ ጊዜ የሚሰጠው ተግባር አይደለም እላለሁ፣ እናንተስ ???
በመጨረሻም በእኛ በኩል ከላይ ባቀረብነው ሁኔታ በአገራችን ከህዝባችን ጋር እየኖርን፣ እየታገልን – የቱንም መስዋዕትነት ለመክፈል ያለንን ውሳኔና ቁርጠኝነት ደግመን  እንገልጻለን፡፡
  1. በፌስ ቡክ ለመገናኘት ባለብን ችግር  ምክንያት በዚህ መልክ በድረ- ገጾች  ለመወያየት  አስበናል፡፡ ከዚህ በፊት በፌስ ቡክ ‹ጨዋታ› በሚል አቀርብ የነበረው ዓይነት በዚህ ደግሞ ‹እኔ የምለው› በሚል በተከታታይ ለማቅረብ ሙከራው ተጀምሯልና ወዳጆቼበ- Ethiomedia .com   እና Mereja.com  ላይ እንድነገናኝ ጥሪዮ ይድረሳችሁ፡፡
  2. አስተያየታችሁን በኢሜይል አድራሻዬ — girmabkbk62@yahoo.com  ላኩልኝ፡፡
ህዳር ሥላሴ/ 07/03/09.   በቸር  ያገናኘን፡፡

Thursday, December 1, 2016

ኮማንድ ፖስት ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ስብሰባ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም ሲል አቶ የሺዋስ አሰፋ ለአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ገለጸ።

  


ኮማንድ ፖስት ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር ስብሰባ ፋይዳ ያለው ነገር አይደለም ሲል አቶ የሺዋስ አሰፋ ለአሜሪካን ድምጽ ራዲዮ ገለጸ። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ የተቋቋመውና በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ሰብሳቢነት የሚመራው ኮማንድ ፖስት በዛሬው ዕለት ከኢትዮጵያ ተቃዋሚ ድርጅቶች ጋር መወያየቱ ተዘግቧል።ሰሎሞን ክፍሌ ከተሳታፊዎቹ የአንዱን የሠማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር አቶ የሺዋስ አሰፋን አነጋግሯል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

በታሪክ ዓላማውን ሳያውቅ ታግሎ ያሸነፈ ድርጅትም ግለሰብም የለም! – Muluken Tesfaw



በታሪክ ዓላማውን ሳያውቅ ታግሎ ያሸነፈ ድርጅትም ግለሰብም የለም!Muluken Tesfaw
የዐማራ ወጣቶች በወያኔ ፋሽስታዊ ሥርዓት በሰላም እንዲኖሩ ባለመፈቀዱ ምክንያት ለነጻነት ሕይወታቸውን እየገበሩ ይገኛል፤ በደማቸው ሊያኖሩን ለሚተጉ የእኛ ወንድሞች በዕውነት ምስጋና ይገባቸዋል፡፡ ለነጻነት የምናደርገው መንገድ ፈታኝ ቢሆንም በድል እንደምንወጣው ምንም ጥርጥር የለንም፡፡ የምታደርጉት ፍልሚያ የዓለም ሕዝብ በሚገባ እያወቀው እንዳልሆነ ግልጽ ነው፤ ይህን ሊያደርግ የሚችል መገናኛ ብዙሃንም ገና አልመሠረትንም፤ ለዚህም እንታገላለን፡፡
ወደ ጽሑፌ ዋናው ዓላማ ልግባ፡፡ የዐማራ ወጣቶች በኢትዮጵያ ውስጥ የሥርዓት ለውጥ እናመጣለን ብለው ለሚታገሉ ድርጅቶች ሁሉ የዐማራን ሕዝብ በተመለከተ ያላቸውን አቋም በግልጽ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ የምንሰዋበት ዓላማ ግልጽ ነው፡፡ እነ ንግሥት ይርጋ፣ ቀለብ ስዩም፣ አዲሱ ሰረበ፣ ኮ/ል ደመቀ፣ ጄ/ል ተፈራና እልፍ ዐማሮች የታሠሩበትን ዓላማ መዘንጋት የለብንም፡፡ ሁልጊዜም አንድን ድርጅት ስንደግፍ ወይም ስንቃወም፤
1. የወልቃይት ጠገዴ፣ የራያ አላማጣ፣ የመተከል ብሎም አጠቃላይ የዐማራውን ሕዝብ ጉዳይ በድርጅታችሁ የሰጣችሁት ቦታ ምንድን ነው? ነው ወይስ ወልቃይት የትስ ብትሆን ነው የምትሉን እንደ አረናዎችና ዴሕምት?
2. ምን ዓይነት ፌደራሊዝም ትከተላላችሁ? በቋንቋ ወይስ በጂኦግራፊ መቀራረብ? በቋንቋ ከሆነ አሁን ያለው የዐማራ ሕዝብ ሳይወከልበት የጸደቀው ፌደራሊዝም ይጸናል?
3. ቋንቋን መሠረት ያደረገ ፌደራሊዝም ከሆነ በመጀመሪያው የሕዝብ ቆጠራ ወቅት አብዛኛው ዐማራ የሆነባቸው ግን ደግሞ ከዐማራ ክልል ውጭ የተካለሉ አካባቢዎችን ምን ታደርጓዋላችሁ?
4. ላለፈው ሩብ ክፍለ ዘመን በዐማራው ላይ የደረሰውን የዘር ማጽዳትና ማጥፋት ወንጀል እውቅና ትሰጣላችሁ? በዚህ ላይ ያላችሁ አቋም ምንድን ነው? በሌሎች የኢትዮጵያ አካባቢዎች ባሉ የዐማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰውን በደል በተመለከተ ይህን ለማስቀረት ምን እየሠራችሁ ነው?
በትንሹ ለእነዚህን ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባችሁ፡፡ ለእነዚህ ጥያቄዎች መልስ የማይሰጥ ድርጅት በዐማራን ሕዝብ ሕይወት እየቆመረ እንጅ እየታገለ አይደለም፡፡ የዐማራ ሕዝብ ጥያቄ ግልጽ ነው፡፡ ወደ ኋላ ወደፊት የለም፡፡
ዓላማውን ሳያውቅ ታግሎ ያሸነፈ ድርጅትም ግለሰብም የለም፡፡ ከላይ የቀረቡት ጥያቄዎች የዐማራ ሕዝብ ከሚያነሳቸው ጥያቄዎች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡ የዐማራ ሕዝብ ተገቢውን ምላሽ የሚፈልግላቸው ናቸው፡፡ ማንም አሊ ሊል አይችልም፡፡ ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ፣ አታላይ ዛፌ፣ ጌታቸው አደመ፣ አዲሱ ሰረበ፣ ንግስት ይርጋ….. ለምን ታሠሩ? በጎጃምና በጎንደር በሁለት ወራት ብቻ ከ300 በላይ ዐማሮች ለምን ተጨፈጨፉ? እነ ሞላ አጃው፣ ቃቁ .. ለምን ተሰው? እነ ጎቤ ለምን በርሃ ገቡ? 20 ሺህ ዐማሮች ለምን በብር ሸለቆና በተለያዩ እስር ቤቶች ታጎሩ?
መልሱ ግልጽ ነው፡፡ ከላይ ለቀረቡት ጥያቄዎች መፍትሔ ፈልገው ነው፤ ለጥያቄዎቻችን መልስ እነርሱ ተሰው፡፡ በእርሱ ደም መጨዎት ታሪክ ይቅር የማይለው ክሕደት ነው፡፡ አፈ ጮሌዎች ትግላችሁን በሌላ ዓላማቸው ሊያዳፍኑት ይሞክሩ ይሆናል፤ ግን እመኑኝ እናሸንፋለን!!

ወያኔ በአንድ እጁ እየጨበጠ በኣንድ እጁ ቡጢ እያቀመሰ ይገኛል።ምኒሊክ ሳልሳዊ

  


እፍረተ ቢሱ ወያኔ የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተቃዋሚዎችን ሕልውና ኣስጠብቋል እያለ የተቃዋሚ ኣመራሮችን እያፈሰ ማሰሩን ቀጥሏል። የዶክተር መረራ መታሰር ተከትሎ ወያኔን እንደ አዲስ አሳሪ አካል ለማየት የሚሞክሩ ሰዎች ይገርማሉ።የዶክተር መረራ መታሰር የትግሉ አንድ ቅጠል ነው። ወያኔ ከዶክተር መረራ በፊት በርካታ ምሁራንን እና ለሀገር ጠቃሚ የሆኑ ሰዎችን በየማጎሪያ ካምፑ ቆልፎባቸዋል።
ወያኔ በ አንድ እጁ እየጨበጠ በኣንድ እጁ ቡጢ እያቀመሰ ይገኛል። ዶክተር መረራን ብቻ ሳይሆን በኮማንድ ፖስቱ ስም የታሰሩት ሁሉ እንዲፈታ ጫናው ቀጥሏል።ትግላችንን ማሳደግ እንጂ መዘናጋትና መደናገጥ የለብንም፤ ብርታት ይጠበቅብናል።በመረራ ጉዲና ከሚመራው መድረክ ጋር ስብሰባ የተቀመጠው የኮማንድ ፖስቱ ለተቃዋሚዎች ደህንነት ሕልውና ቆመናል ብሎ እየተናገራቸው ስብሰባው ሲበተን የተቃዋሚ አመራሩን አፍኖ ማሰር ስርዓቱ ምን ያህል አጭበርባሪ እንደሆነ ያጋለጠ ነው።
ወያኔ እስካልተወገደ በቀር ይህ የጭቆና ኣገዛዝ መቀጠሉ አይቀርም። ወያኔ የሚያስረው ለመግደል የትግል መንፈስን ለማንኮታኮት እንዲሁም በቁምህ ስቃይ ሊያሸክም ስለሆነ ይህንን ማስቆም የምንችለው ትግላችንን አጠናክረን ስንቀጥል እንጂ ታጋዮቻችን እየታፈኑ ሲታሰሩ በመደነቅ እና በመበሳጨት አሊያም ወሬ በማውራት አይደለም።

ዶ/ር መራራን ማሰሩ ኢህአዲግ እንደልማዱ ተዳፍኖ በነበረው እሳት ላይ ቤንዚን ጠብ አደረገ !!Dereje Gerefa Tullu



ኢህአዲግ እንደልማዱ ተዳፍኖ በነበረው እሳት ላይ ቤንዚን ጠብ አደረገ !! Dereje Gerefa Tullu
ዶር መራራ ኢህአዲጎችን ብዙ ጊዜ በሁለት ነገር አንጀታቸውን እንደሚያቆስላቸው ይታወቃል።
አንዱ ከሰው ጭንቅላት የማይጠፉ አጫጭር አረፍተነገሮችን በመጠቀም እና ብዙ ረጃጅም የኢህአዲግ አረፍተ ነገሮችን በመደረማመስ ነው።
ለምሳሌ የሚበላውን ያጣ ህዝብ መሪውን ይበላል።
ኢህአዲግ አፍ እንጅ ጆሮ የለውም።
አቅም ያጣውን አቅም ግንባታ ትምህርት ያሌለውን ትምህርት ሚንሥቴር ወዘተ
ሌላም መጥቀሥ ይቻላል።
ሌላው የዶር መራራ ኢህአዲጎችን አቁሳይ ሥልት ስሞቅ እየቀጠቀጣቸው ኢህአዲጎች ሰው ለማሰር በንዴት ሥቅዘፈዘፉ ሃይበርኔት ያደርጋል።በዚህ መልኩ ዶር መረራ ኢህአዲጎችን ብዙ ጊዜ አምልጦአቸው አብሽቆአቸዋል።ይህንን ደግሞ በ1998 የቅንጅት መሪዎች ከታሰሩ በኃላ ጠቅላይ ሚንስትር መለስ ዜናው ሳይቀሩ በፓርላማ ቀርበው ተናግረውታል።ጠቅላይ ሚንስትሩ ዶር መራራ በነገር ስጎነትሉአቸው በንዴት “ከDC እስከ አምቦ መንግሥትን ለመጣል ሰንሰለት እየዘረጉ ስከሽፍ ምንም እንዳልተፈጠረ ፓርላማ መግባት እና ማምለጥ ከዚህ በኃላ አንፈቅድም ነበር ያለወቸው።” ዶር መራራ በወቅቱ በለዘብተኛ ፈገግታ አልፈውታል።
የአሁኑን ግን ዶር መራራ በተለመደው እሥትራቴጅው (እሳቸው push and pull ይሉታል ይባላል) ከእሥር ማመለጥ የፈለገ አይመሥለኝም።ዶር መራራ ለተዳፈነው እሳት እራሱን መስዋአት በማድረግ ለማቀጣጠል የወሰነ ይመሥለኛል።እኔ በለኝ መረጃ ዶር መረራ ኢህአዲጎች ነገሮችን ሰከን ብለው እንዲያስቡ እና ነገሮችን በሚመስል መልኩ እንድፈቱ ከፍተኛ ፍላጎት እና መጠነኛ ተስፋ ነበረው።አሁን ግን ያንን መጠነኛ ተስፋውን ኢህአዲጎች በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንደጉም በኖ እንድቀር ያደረጉት ይመስለኛል።ይህንን ደግሞ ከአዋጁ ማግስት በVOA ቀርቦ ተናግሮታል።
ስለዚህ የረጋ የመሰለው ማዕበል እንድናጥ ዶር መረራ አንድ ስልት መቀየስ አለበት ።ለዚህ ደግሞ እራሱን ለመሰዋዓትነት ማዘጋጀት ብቸኛ አማራጩ ነው።መቼም ከዚህ በኃላ እንደ አንዳንድ የፖለቲካ መሪዎች ጫካ ገባለሁ ብሎ አስመራ አይገባም።
ነገሮችን በኢህአዲግ በኩል ካየነው ዶር መራራን በዚህ ጊዜ ማሰሩ ቅንጣት ያክል የፖለቲካ ጥቅም የለውም።ምክንያቱም ሰውዬው አብሮ የሚሰራቸውን ሰው ሰብስበው በማስገባት ምንም ተፅዕኖ እንዳይኖረው ማድረግ ችለውበታል።ስለዚህ እሱን በማሰራቸው በሱ በኩል ልመጣ የሚችል እና ልቀንሱት የሚችሉት ምንም ዓይነት የፖለቲካ ጫና የለባቸውም።
በማሰራቸው ግን የፖለታካ ጫና ውሥጥ እንደሚገቡ ለማወቅ ፖለቲከኛ መሆን አያስፈልግም።
ሰውዬውን ያሰሩት ከአውሮፓ ህብረት ሰዎች ጋር ተማካክሮ ስመለስ ነው።ሀገር ቤት የሚናጠውን እና ለጊዜው የረጋ የመሰለውን ማዕበል እንኳን ብንተው ከነሱ ጋ በመመካከሩ እና በመታሰሩ ለክብራቸውም ጥሩ ስለማይሆን የአውሮፓ ህብረት ሰዎች የሚችሉትን ማድረጋቸው አይቀርም።
ለማጠቃለል ዶር መራራ በወሳኝ ሰዓት ላይ እራሱን መሥዋዓት በማድረግ የረጋ የመሰለውን ማዕበል መናጥ የፈለገ ይመሥለኛል።ይህ እንኳን ባይሆን አጀንዳ አጥቶ እርስ በራሱ የሚባላውን የዲያስፖራ ደጋፍያቸውን አጀንዳ በመሆን ያሰባሰብላቸዋል።።ይህም ባይሆን ከሂሊና ሸክም ይገላግለዋል።
ኢህአዲግ ደግሞ እንደበሬው ሳሩን እንጅ ገደሉን ሳያይ የረገጠው ፈንጅ አለ ቢዬ አስባለሁ።
በኔ ዕይታ የፈንጅው መፈንዳት የረጋ የመሰለውን ማዕበል መናጡ አይቀርም።
በሌላ አነጋገር ኢህአዲግ ዓመቱን ሙሉ ስያደርግ እንደነበረው ረግቶ የነበረውን የህዝብ ማዕበል ዶር መራራን በማሰር ለመቀስቀስ እየሰራ ነው።በተዳፈነው እሳት ላይ ቤንዚን ጠብ አድርጓል።አቅም ላነሳቸው ሃይሎችም ዳገት ላይ ውሃ አቀብሎአቸዋል።የቀረው የጊዜ ጉዳይ ነው