Friday, September 23, 2016

የትግራይ ወያኔ ሌባ ነው የሚለው የኢቶዮጵያ ህዝብ እዉነታነቱን እራሱ ወያኔ በድጋሜ መሰከረ

  


የትግራይ ወያኔ ሌባ ነው የሚለው የኢቶዮጵያ ህዝብ እዉነታነቱን እራሱ ወያኔ በድጋሜ መሰከረ
——————————————————————-
ባለፈው ወር አካባቢ ወያኔ ባወጣው የልሳኑ መግለጫ በስልጣን ላይ ያሉ አባላት ስልጣናቸዉን መከታ በማድረግ ህዝብን ከማገልገል ይልቅ የግል ጥቅማቸዉን በማሳደድ ሃገርን መዝረፍ ስራየ ብለው ይዘዋል ብሎ በግልጽ ወያኔ የሌባ ድርጅት መሆኑን ለኢትዮጵያ ህዝብ ተናገረ። አሁንም እንደገና በ ፩፱፱፰ (1998) አመተ ምህረት አሳትሞ ትምህርት ሲያስተምርበት የነበሩት መጽሃፎች የሃገሪቱን የተለያዩ ክልሎችን በተለይ የአማራዉን ክልል ዙሪያዉን ተቀራምተው አሳንሰው በመሳል በትክክል ያላስቀመጠና ትልቁን የኢትዮጵያን ራስ ደጀን ተራራርን ከጎንደር አዉጥተው ትግራይ ዉስጥ ነው ብለው ለአመታት ሲያስተምር እንደነበርና ይህ በስተት መሆኑን ይቅርታ እንጠይቃለን መጽሃፎቹንም አስተካክለን ልከናል አሉ። ይህ አይደለም ሌባ ማለት? ይሀን ያህል አመታት እንዴትስ ሆኖ ነው መምህራኖች ይሀን ሲያስተምሩት የነበሩት፤ ራስ ደጀን ትግራይ ዉስጥ ነው ብሎ ማስተማር? በመምህርነት የሰለጠነ ሰው ዉሸትን እንደ እዉነት አምኖ እንዴት ይሀን ያህል አመታት ያስተምራል? ምንስ አይነት መምህር ነው? የትግራይ ዋና ከተማ ደደቢት ነው ብሎ የተጻፈዉን መጽሃፍ እንዴት ነው አስተማሪው ይሀን ከማስተማሩ በፊት ይህ ነግር እዉነት አይደለም ብሎ መጠየቅ የማይችለው? ነው ወይስ ደደቢት የትግራይ ዋና ከተማ መሆኑን ወይም አለመሆኑን አያዉቅም ወይም እንዲሆን ስለሚመን ዝም ብሎ የተጻፈዉን ዉሸት ያስተምራል? እኔ የሂሳብ አስተማሪ ነኝ፤ እንዴት ሆኖ ነው መጽሃፍ ላይ ፩+፪ = ፩፪ ባገኘው ይህ ትክክል ነው ብየ ዉሸትን እያስተማርኩ ሂሳብ አስተማሪ ነኝ የምለው? ትምህርቱስ እንዴት ነው የሂሳብ ትምህርት የሚባለው ተማሪዉስ ምን አይነት ነው ይችን ትንሽ ነገር እንኳን ስህተት መሆኑን ማየት የማይችለውና ስህተት መሆኑን ለመናገር የማይሞክረው? ሂሳብ እዉነትን የምናረጋግጥበት የጥናት መስክ እንጅ ዉሸትን የምንማርበት አይደለም ። ማነው ነው ተጠያቂዉ ይሀን ዉሽት ተምሬአለሁ ብሎ ይዞ ወጥቶ ሃገርን በዉሸት የሚያምስና የሚያበጣብጥ እንደነ መለስ ዜናዊና የወያኔ ቁጭበሉወች? ለዚህ ነው ወያኔ ሌባ እያለ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚናገረዉና የወያኔን ትክክለኛ ባህሪ የሚገልጸው ። የትግራይ ወያኔ የራሱ ያልሆነን ነገር በመዝረፍ የራሱ በማድረግ ሃብትና ንብረት ማግበስበ ሞያው ነው አሁን እንደታየው የንብረቱ ባለቤቶቹ አምርረው ከጠየቁ በስተት ነው ብሎ መመለስ ነው። አሁንም ወልቃይት ጠገዴ፤ራያ፤መተከል ሁሉም ወደ አማራው መልሰናል ይቅርታ በስህተት ነው ይህ ሁሉ ወንጀል በደልና ግፍ የፈጸምነው ብለው ብቅ ይሉ ይሆናል፤ ግን አሁን ያን ማድረጉ ጅብ ከሄደ ዉሻ ጮሀ ነው፤ ከብዙ ወንጀል በኋላ ዘግይቶ የመጣ መፍትሄ መፍትሄ ሳይሆን ራስን ለማዳን የሚደረግ ጥረት ነው፤ በዚህም ምክንያት እርምጃው ተገዶ የሰዉን ንብረት መመለሰ ብቻ ሳይሆን ለዘረፋ ለአድሎ ለግድያና ግፍ መፈጸሚያ መሳሪያ ያደረገውን ስልጣኑን እንዲለቅና ፍትሃዊ እርምጃን ለመቀበል ዝግጁ መሆን ብቻ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ በሌባ መታሰር፤ መገደል፤ መዘረፍና ሌቦች በቅንጦት እየኖሩ የንበርቱ ባለቤት የሆነው ህዝብ ግን በድህነት ብግፍ በስራትና ብግድያ የሚኖርበት ዘመን ማቆም አለበት፤ የህዝቡም ጥያቄና ተጋድሎ ይሀንን እዉን ለማድረግ ብቻ ነው።

No comments:

Post a Comment