Saturday, September 3, 2016

የህዉሃት ልኡካን በጎንደር ዳግም ተሸነፈ

 14012564_10205198112430990_355381106_o

ከመጀመሪያ ጀምሮ የጦር ሀይል አማራጭን በመጠቀም ሽንፈትን ያስተናገደዉ ሕዉሃት በዲፕሎማሲም ዳግም ተመልሶ ሊያገግም በማይችል ሁኔታ ዛሬ 27/12/2008 ጎንደር ከተማ ላይ ልኩ ተነግሮት በኪሳራ ተሸኘ፡፡ሁሌም ቢሆን “የእኔ መንገድ ብቻ ትክክል ነው” በሚል ተእቢቱ የምናዉቀዉ ህዉሃት አማራ ምድር ላይ የሚሄድበት እግሩ ከተቆረጠ ሰነባበተ፡፡ፌደራል ፖሊስ ከአቅሜ በላይ ነዉ ብሎ ሪፖርት ካቀረበ ማግስት ጀምሮ በስርአቱ የጦር ጠንሳሾች(አግአዚ) ተመርቶ ደም ማፍስስ ከጀመረ ሰነባበተ፡፡
ትእቢተኛ በቆሎ ከጤፍ ሆድ ዱቄት እንዲወጣ አያዉቅምና …..ፍሊሚያዉ የአገዛዙን እድሜ እያሳጠረ መጥቶ የትግሉ የመጨረሻ ምእራፍ ደርሶል፡፡አማራነትም ፈጽሞ ላይከስም እየጎመራ እየተንዠረገገ እየሰፋ እየገዘፈ መጥቶል፡፡ከመከላከል ወደ ማጥቃት ተሸጋግሮል፡፡ ዛሬ በእለተ አርብ ነሃሴ 27 ጎንደር ከተማ ውስጥ ባሉ ሶስት ሰፋፊ የመሰብሰቢያ አዳራሾች ላይ የህዋሃት ልኡካን ባለ ስልጣናት በጎንደር አማራ አማካኝነት መራር ዲፕሎማሲያዊ ሽንፈትን ተጎንጭተዋል።
ከኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ተመርጠዉ የተላኩ የህወሓት መልክተኞች በሶስት ጎራ በኩል ተመዳድበዉ ብሶተኛዉን ህዝብ ለማናገር በአዳራሾቹ ታድመዋል ።
ምድብ 1- ከንቲባ ጽ/ቤት በሚገኘዉ አዳራሽ ዉሥጥ የኮሚኒኬሽን ጉዳይ ሃላፊ ተብየው ወፈፌው ጌታቸዉ ረዳ እንዲሁም የጎንደር ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ጥላሁን ተሰይመዋል፡፡
ምድብ 2- ሳይንስ አምባ በሚገኘዉ አዳራሽ ዉሥጥ የክልሉ ፕሬዝደንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉ እንዲሁም የግብርና ሚኒስተሩ አቶ ተፈራ ደርበዉ ተገኝተዋል፡፡
ምድብ -3 ፒያሳ በሚገኘዉ ሲንማ አዳራሽ ዉሥጥ የክልሉ የብአዴን የፖለቲካ ሀላፊዎች በብሶተኛዉ ተሰብሳቢ ፊት ተደቅነዋል፡፡
ስብሰባዉ አረፋፍዶ ተጀመረ፡፡በእለቱ የሀይማኖት አባቶች ደምቀዉ ዋለዋል፡፡ከወትሮዉ በተለየ መልኩ ኮከብ ሆነዉ ለምሳ አጋማሽ ወጡ፡፡እንዲህም ሲሉ ሞገቷቸዉ :-
“ከዚህ በሆላ መስቀል ጥላ እና ታቦት ይዘን ምንወጣዉ ወጣቱን እኛ ከፊት ሆነን ለማዋጋት እንጂ ለመሸምገል አይደለም ፡፡ከዛሬ በሆላ ድምጽ ማጉያችን ይዘን ምንናገራዉ የእናንተን ዲስኩር ሳይሆን የልጆቻች ስሞታ ነዉ ።ከእነሱ በፊት እኛን ያድርገን” ሲሉ የታወቁ የኦርቶዶክስ አባት ተናገሩ፡፡
ቀጠሉ እና ሌላኛዉ ወንጌላዊ አባትም ከሙሴ የኦሪት መጽሀፍ ጠቅሰዉ ርስትን የሚያፈልስ የተረገመ ነዉ በማለት ህወሃቶች የተረገሙ መሆናቸውን ነገሩአቸዉ፡፡በመሆኑም እግዚሃብሄር ስልጣናቸዉን ነጥቆ ለተተኪዉ ዳዊትን እንዳዘጋጀ ነገሩአቸዉ፡፡አንድ የታወቁ ሸህም “አሏህ ሁሌም ከተበዳዬች ጎን ነው የሚቆመው፣አማራ እጅግ ተበድሏል እናም አሏህ ከእኛ ጋር ነው” ሲሉ በሃይል ተናገሩ ። ጌታቸዉ ረዳ አፉ ተሳስቶ የሚናገረው ጠፍቶት ሲቁለጨለጩ እና ሲደናበር ዉሏል፡፡
የሌላው ምድብ የስብሰባሰው ተሳታፊዎች አቶ ገዱ አንዳርጋቸዉን “ከ 35 ሚሊዩን በላይ ጀግና የአማራ ህዝብ ጋር ሆኖ የሚስፈራህ ምንድን ነዉ? ከጀግናዉ ኮሎኔል ደመቀ ታሪክ ጋር ሊያስደምር የሚችል እድል በእጁ ላይ ነው ተጠቀምበት ፣ የሕወሓት ሎሌነት ታሪክ አይሆንም ፣ ለህዝብ ከወገንክ ህዝብ መከታ ይሆንሃል ።…” ብለውታል። አቶ ገዱ በሚሰሙት ነገር ስሜታዊ እንደነበሩ ለመገንዘብ ተችሏል። ከዚህ በኋላ ለታሪክ እንዲኖር አበክረዉ ነግረውታል፡፡ከአቶ ገዱ ቀጥሎ ተራው የደረሰው ግብርና ሚኒስቴሩ የጎርጎራዉ ልጅ ተፈራ ነበር…25 አመት ሚኒስቴር ነበርክ እኛ በኩራዝ እና በሻማ ያስተማርነህ ለዚህ አልነበረም ፡፡ምነዉ ጄኔሬተሩ ወደ ትግራይ ሲሄድ እናንተዉ ባልመከታቸሁ ኑሮ ? ታዲያ ዛሬ ምን ይዘህልን ነዉ የመጣህዉ የቱሪስት መስህቧ የትዉልድ ከተማህ ጎርጎራ አንኳን ይኸዉ 25 አመት ከጎንደር የሚያገናኛት የ60 ኪሎ ሜትር አስፓልት አልተነጠፈላትም ። ዛሬ ጦር ፍጅት ባወጀብን አለቃህ ትእዛዝ ልትፈጥም መምጣትህ አይበጅህም! ተመከር!ሲሉ በጥብቅ አስጠንቅቀውታል።
ብሶት የወለደዉ የአማራ ድምጽ በመጨረሻም ባለ 4 ነጥብ የአቋም መግለጫ አዉጥቷል፡፡
1ኛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ አማራ ጨፍጨፊው የህዉሀት የመከላከያ ሰራዊት አማራ ምድር በአስቸኳይጨ ለቆ እንዲወጣ
2ኛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ኮ/ል ደመቀ በአስቸኳይ እንዲፈቱ
3ኛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ የታሰሩ የወልቃይት እና የጠገዴ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ
4ኛ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ወራሪዉ የትግሬ መንግሰት በአስቸኳይ ተከዜ ማዶ እንዲሻገር እና የራሱን ምድር እንዲያስተዳድር
ይህ ካልሆነ ግን ከቄስ እስከ ሸህ ከወጣት እስከ ሽማግሌ ፣ሴት ወንድ ሳይል የአማራ ህዝብ በአንድ ላይ በአንድ ልብ ደንበሩን በደም መስዋዕትነት ያፀናል ። ከዚህ በኋላ በሰላማዊ ሰልፍ የሚሞት አንድም የአማራ ነብስ አይኖርም ብለዋል።
ድል ለአማራ ህዝብ!!

No comments:

Post a Comment