Sunday, July 31, 2016

ወደ ጎንደር ፊታችሁን አዙሩ … ኢትዮጵያዊነት በጎንደር ደምቆ ተመልከቱ



ተገፋሁ ያለ ፣ ያመረረ ፣ የጨከነ የኦሮሞ ህዝብ ንቅናቄ ባየን ማግስት አማራ ተገፍቶ ከፍቶት ፣ በደል አማሮት ፣ ንቀት አስቆጥቶት ቁጣውን እየገለጸ ነው ! … አማራው ሲቆጣ እንዲህ በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ደምቆ በሁሉም ወገኑ ላይ ሰለሚደርሰው የመብት ገፈፋ ተቃውሞውን በማሰማት…

የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ህዝቡ አገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ ያስመሰከረበት ሰልፍ ተካሄ

እናቶች በሰልፋ ለደከሙ ወጣቶች ውኃ እያቀረቡ ነው፤ የሃይማኖት አባቶች ተጋድሏችንን እየባረኩ ነው! አማራነት እኮ እንዲህ ነው! እቴጌ ባአድዋ ያደረጉትን አስታውሱ!
የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ኣገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ የመሰከረበት ሰልፍ


Minilik Salsawi – mereja.com ፖለቲከኞችን ያሳፈረው ሕዝብን ያነገሰው ዛሬ በጎንደር የተካሄደው ሰልፍ በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል ሂደት ውስጥ ራሱን የቻለ ጫና እንዳለው ያረጋግጣል።ሕዝብ በራሱ ያሰናዳውና የተሳካ ታላቅ ሰልፍ በጎንደር ደሞቆ ውሏል።ሕዝባዊ ኣንድነት ጎልቶ የታየበት የወያኔ የጎሳ ፖለቲካና የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ የተዋረደበት ኣገዛዙን መጥላቱን ሕዝብ የመሰከረበት ሰልፍ ነበር፤የሕወሓት ኣገዛዝ በቃኽን የተባለበትም ሰልፍ ነው፥ ሚሊዮኖች ኣደባባይ ወጥተው ወያኔን ልክ እንደሚያስገቡት ነግረውታል።
Minilik Salsawi's photo.
ሕዝብን በሃይማኖት ለመከፋፈል ሞከሩ ኣልተሳካም። ሕዝቡ ሃይማኖታችንን እንደያዘን የሌላውን ኣክብረን ቤታችን በታቸው ሆኖ የኣንዱ ደስታና ሃዘን የኣንዳችን ሆኖ በተሳሰረ የኢትዮጵያዊነት ሰንሰለት ላይፈታ ታስሯል ብሎ በተደጋጋሚ እያረጋገጠ ነው። የብሄረሰብ መብት ሽፋን በሚል ኣንዱን ጨቋኝ ሌላውን ተጨቋኝ ኣድርጎ ለማቅረብ ቢሞክርም ሰሚ ጆሮ ኣላገኘም ወያኔከኦሮሞ ሕዝብ ጎን መቆሙን ኣማራው በተግባር በሚሊዮኖች ድምጹ ኣረጋግጧል፤ በሕዝብ ዘንድ ጥላቻና ዘረኝነት እንዳሌለ የጎንደሩ ሰልፍ ለገዢዎች ኣሳይቷል። ችግሩ ወያኔና ፖለቲከኞቹ እንደሆኑ እንጂ በሕዝቦች መካከል ችግር እንደሌለ ኢትዮጵያዊነት እንዳስተሳሰረ በተግባር ከመመስከሩም በላይ የወያኔን ባንድራ ተቀባይነት እንዳሌለው ታይቷል በጎንደሩ ሰልፍ።

...


Saturday, July 30, 2016

ጎንደር በፌደራልና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ተጨናንቃለች :: ዋናው የሰልፉ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› እንዳይዳፈን ስጋት አለ

መፈክሮች ታትመው ተዘጋጅተው ኣልቀዋል። ጎንደር ነገ በነጻነት ጠያቂ ሕዝቦች ትጥለቀለቃለች።Minilik Salsawi – mereja.com – በጎንደር ተሰማርቶ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የልዩ ሐይልና የአካባቢ ሚሊሻ ባጠቃላይ ነገ የሚካሄደዉን የጎንደርን ሰልፍ ተነተርሶ የተሰጣቸዉን ሰላማዊ ሰልፍ የማክሸፍ ሴራ ያለማቀበላቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ደርሰዉናል። ነገ በጎንደር የሚደረገውን ሰላማዊ ሰልፍ ለመቀላቀል ዛሬ ከባህር ዳር ብዙ ወንድምና እህቶቻችን ወደ ጎንደር እየገቡ ነው ። ምንም እንኳ ስንዝር ለሆነች መንገድ ሶስት ጊዜ መፈተሽ ግድ ቢሆንባቸውም እንኳን ይህን ሌላም ፈተና ቢመጣ እንጋፈጠዋለን በማለት ወደ ጎንደር እየተጓዙ ነው
ዋናው የሰልፉ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› እንዳይዳፈን ስጋት አለ
ጎንደር በፌደራልና በልዩ ኃይል ፖሊሶች ተጨናንቃለች
ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ ከግማሽ ሚሊዮን የሚልቁ ዐማሮች ሰላማዊ ሰልፍ ይወጣሉ፡፡ ይህን ተከትሎ ከባሕር ዳር፣ ደብረ ታቦር፣ ደባርቅ፣ ቆላ ድባ፣ ሳንጃና ጭልጋ መተማ የሚመጡ መኪኖች ላይ ታላቅ ፍተሸ እየተካሔደ ነው፡፡ ከጭልጋ ሰራባ አካባቢ እንዲሁም ከባሕር ዳር ብዛት ያላቸው የመከላከያ ኃይል አባላት ወደ ጎንደር መጥተዋል፡፡ በጎንደር የሚታየው ፖሊስ ዛሬ በጽጥታ አካላት ብቻ ሰልፍ የተካሔደ አስመስሎታል፡፡
ዐማሮች ከሁሉም ቦታ ወደ ጎንደር እየጎረፉ ነው፡፡ የሰልፉ ዓላማም አንድ እና አንድ ነው፤ ይኸውም የወልቃይት ዐማሮች የማንነት ጥያቄን ለማዳፈን የሚደረገውን ጥረት መቃወም ነው፡፡ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ መጠየቅ፤ ወልቃይት ዐማራነትን መመስከር ነው፡፡
ይህ ሰልፍ ከዚህ የዘለለ ሌላ ዓላማ የለውም፡፡ ሆኖም ይህን ሰልፍ ዓላማ በሌላ ‹‹የተቀደሰ ዓላማ›› ለመሸፍ የሚደረግ ጥረት አለ፡፡ የኦሮሞ ወንድሞቻችን ግድያና አፈና፣ የሀብታሙ ሕመም ሁላችንም የምናወግዘው ጉዳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያን መበታተን ማንም አይሻም፡፡
እነዚህ ‹‹ቅዱስ ዓላማ›› ያላቸው መፈክሮች ጎልተው የሰፊውን ዐማራ ሕዝብ ጥያቄ በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለማዳፈን የሚደረገው ጥረት ዋጋ ያስከፍላል፡፡ ስለዚህ የዐማራውን ሕዝብ ትግል እንቅስቃሴ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰውን በደል በማጋለጥ ላይ ብቻ ያተኮረ ነው፡፡ ሁሉም የሰልፉ ተሳታፊ የዐማራ ሕዝብ ከወልቃይት ጠገዴ የዐማራ የማንነት ጥያቄን በደንብ አጉልቶ ማውጣት አለበት፡፡

በጎንደር የሚካሄደውን ሰልፍ ለማደናቀፍ ሕወሓት እየተሯሯጠ ነው። ሕወሓት ተሸብሮ ሕዝብን ለማሸበር አየተንደፋደፈ ነው

በጎንደር የሚካሄደውን ሰልፍ ለማደናቀፍ ሕወሓት እየተሯሯጠ ነው። ሕወሓት ተሸብሮ ሕዝብን ለማሸበር አየተንደፋደፈ ነው።
በጎንደር ተሰማርቶ የሚገኘዉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የልዩ ሐይልና የአካባቢ ሚሊሻ ባጠቃላይ ነገ የሚካሄደዉን የጎንደርን ሰልፍ ተነተርሶ የተሰጣቸዉን ሰላማዊ ሰልፍ የማክሸፍ ሴራ ያለማቀበላቸዉን የሚጠቁሙ መረጃዎች ደርሰዉናል።
በወልቃይት የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎች ላይ የሚደርሰውን አፈናና ግድያ እንዲቆም የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ በጎንደር ከተማ እሁድ ሐምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. መላው አማራ ታሪካዊ ሰልፍ ያደርጋል ፡፡ በጎንደር የሚካሄደውን ሰልፍ ለማደናቀፍ ሕወሓት እየተሯሯጠ ነው።ሕወሓት ተሸብሮ ሕዝብን ለማሸበር አየተንደፋደፈ ነው። ነገ እሁድ ሃምሌ 24 2008 በጎንደር ከተማ የሚደረገው ሕዝባዊ ተቃውሞ እንዳይደረግ የሕወሓት ኣገዛዝ በከፍተኛ ደረጃ እየሰራ መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል። ምንጮቹ እንዳሉት በዚህ ሳምንት ሕዝቡን በስብሰባ ለማታለል ቢሞክሩም በፍጹም ሊበገርላቸው ስላልቻለ ያለው እድል የሕወሓት ሰራዊትና የኣማራ ክልል ፖሊስን በጋራ በጎንደር ከተማ ማስፈርና ወደ ከተማዋ የሚያስገቡ መንገዶችን መዝጋት ነው።
Minilik Salsawi's photo.
በዚህም መሰረት በክልሉ የፖሊስ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተመራ ኣንድ የግብረ ሃይል ቡድን በስሩ 8 ቲሞችን በማዋቀር ከባህር ዳር ተነስቶ ጎንደር የገባ ሲሆን ይህ የኣማራ ክልል የፖሊስ ቡድንን ከጀርባው ሆኖ ለመንቀሳቀስ ከኣይከል ሳርባ ወታደራዊ ካምፕ የሕወሓት ሰራዊቶች ጎንደር ከተማ የገቡ ሲሆን በጎንደር ዙሪያ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ ፍተሻ የሚካሄድ ሲሆን ከከሰኣት በኋላ ጀምሮ በተለያየ ምክንያት ወደ ጎንደር የሚገቡ መኪኖች እንዳይገቡ እንዲደረግ ለሕወሓት ሰራዊቶች ትእዛዝ ተሰጥቷል።ይህ የሚያሳየው የሕወሓት ኣገዛዝ ከፍተኛ ሽብር ውስጥ እንደገባና ህዝብን እያሸበረ እንደሆነ ነው። በጎንደር ይካሄዳል የተባለው ሰልፍ ለኣምባገነኖች ታላቅ ሽብር መፍጠሩ በየሚዲያዎቻቸው እየለፈፉ የሚገኙት ፕሮፓጋንዳ በቂ ማረጋገጫ ነው።እሁድ ሐምሌ 24 ቀን 2008 በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ መላው አማራ ታሪካዊ ሰልፍ ያደርጋል::
http://www.mereja.com/amharic/505163
እኔም ጎንደሬ ነኝ !!! እኔም ወልቃይቴ ነኝ !!!!!!!!!

Friday, July 29, 2016

ይድረስ ለጎንደር ሕዝብ ከጎጃም ሕዝብ የተላከ



የወያኔ መንግስት በአንተ በውዱ ወገናችን ላይ ከጥቂት ሳምንታት ወዲህ እየፈፀመ ያለውን የማን አለብኝነትና የእብሪት ተግባር በቁጭትና በእልህ እየተከታተልንና ከአንተ ወገናችን ጎን በመቆም ያለንን አጋርነት እየገለፅን ቢሆንም፣ ይህንን የእናት ጡት ነካሽ የሆነውን የዘረኛና የፋሽስት መንግስት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ጠራርጎ ለማስወገድ ተግባራዊ ስራዎችን ተባብረን መስራት ስለሚጠበቅብንና የመይሳው ካሳና ልጆች ሲጠቁ የበላይ ዘለቀ ልጆች አርፈው አይተኙምና የሚከተሉትን ነጥቦች በማንሳት የትግል አጋርነት መልዕክታችን ይድረሳችሁ እንላለን።
1. የብአዴን አመራር አባላት (እንደ አለምነው መኮንንና ብናልፍ አንዷለም) ሌሎችም ከአማራው ይልቅ ለሆዳቸው አድረው ከወያኔ ጋር በተሰለፉ የአማራው ካድሬዎች ላይ ሁሉ የማያዳግም ርምጃ መውሰድ፤
2. የስርዓቱ ተጠቃሚ በሆኑ በወያኔ/ብሕአዲን የንግድ ተቋማትና ጥቅማ ጥቅሞች ላይ እንዲሁም ከአንዱ አካባቢ ወደሌላው አካባቢ በሚንቀሳቀሱ የስርዓቱ የንግድና የግል ተሽከርካሪዎች ላይ ርምጃ መውሰድ፤
3. ታፍነው የተወሰዱ የወልቃይት ጠገዴ የማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ካልተለቀቁ፣ በምትኩ የወያኔ ገዥ አባላትንና ቤተሰባቸውን አፍኖ በመውሰድ መደራደሪያ ማድረግ፤
4. ከአሁን በኋላ ለሚሰነዘርብን ማንኛውም ጥቃት ሁሉ አፀፋዊ ምላሻችን እጥፍ ድርብ መሆን ይኖርበታል፤ እነሱም የያዙት እንደኛው ነፍስ ነውና ለሚሰነዝሩት ጥቃት ማንኛውም ዜጋ በተጠንቀቅ በመቆም አይቀጡ ቅጣት ልንቀጣችው ይገባል። ጀግንነትን ተወልዶ ያደገው ከእኛው ዘንድ መሆኑን ቢያውቁትም የበለጠ ማንነታችንን ልናስተምራቸው ይገባል።
5. እነሱ ያላከበሩትን ሕግ ሌላው ዜጋ እንዲያከብረው ደጋግመው የሚጠይቁትን፣ ድርድርና ሽምግልና እያሉ ጊዜ ለመውሰድና ትግሉን ለማኮላሸት የሚጠቀሙበት ስልት ስለሆነ ካለፈው ተምረን በዚህ ሳንታለል ጊዜያችንን በስር-ነቀል ለውጥ እንጂ በጥገናዊ ለውጦች እንዳንታለል።
6. የወያኔ መንግስት መሳሪያችንን ለማስፈታት እያሴረ በመሆኑ፣ ይህን ለማስፈፀም የሚንቀሳቀስ ሰራዊት ከመጣ ውረድ እንደውረድ ተባብለን በምናውቀው ተራራ ዋሻና ቀዳዳ መፋለም ይኖርብናል። በቁማችን ከሞትን ቆይተናል፤ የወልቃይት ጠገዴና የጠለምት ሕዝብ 36 ዓመት ተገድሏል፣ ታስሯል፣ ተሰዷል በአካል ያለውም መሬቱን ተነጥቋል፤ የተቀረው ሕዝብም መንገድ ከፍቶ ላሳለፋቸው ውለታ 25 ዓመታት በሙሉ የሰቆቃ በትራቸውን አሳርፈውበታል። ጣሊያንም ከዚህ የበለጠ በወገናችን ላይ አልፈፀመም።
7. ማንነቱን እንዲረሳ ወደ ትግራይ በግዳጅ የተካለሉ አካባቢዎችን ሆን ተብሎ ወደ ትግርኛ ስያሜ እየተቀሩ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ በነዚህ ስሞች በምንም ዓይነት እንዳይጠቀም ተገቢው ቅስቀሳ መካሄድ አለበት።
8. ለወሎ ወገናችን፣ ግዛትህ ተቆርሶ እንደ ጎንደር ተወስዶ፣ ክብርህ ተዋርዶ፣ ማንነትህ ተንቆ እንደ ስልቻ እየታሰርህና እየተፈታህ ባለህበት በዚህ ፈታኝ ወቅት ከጎንህ አለንና ተነስተህ ከጎንደር ወገናችን ተሰልፈህ የተነጠቅኸውን መሬት ለማስመለስ ተነስ። ሁሌም የማታሳፍረን የሸዋ ወገናችን ለጥሪያችን በተንቀቅ ተዘጋጅተህ ጠብቀን።
9. የአማራ የመከላከያ ሰራዊት ሆይ፣ መሳሪያህን በአማራ ሕዝብ ላይ በማንሳት ይቅርታ የማይደረግለት ስህተት እንዳትፈፅም፤ የመሳሪያህን አፈሙዝ በወያኔና በግብረ በላው ብሕአዲን ላይ እንድታዞር ጥሪ አቅርበንልሃል።
10. ዋናው ግባችን የወያኔ/ኢሕአዲግ ፋሺስታዊ መንግስትን መገርሰስ በመሆኑ፣ ለማይቀረው ድል አብረን እንሰለፍ። እስከ መጨረሻው የደም ጠብታ ከጎንህ ነንና ትግላችን በድል ሳይጠናቀቅ አርፈን እንደማንተኛ ልናረጋግጥልህ እንወዳለን።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!

አጋጣሚውን መጠቀም ብልህነትና ማስተዋል ነው ! ከአዲስ አበባ ወጣቶች የተላከ መልእክት

  
አገር ሰላም's photo.
አሁን የደረስንበት ሰዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ያለውን እውነተኛ ስሜት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ከጫፍ ጫፍ በሚባል መልኩ እየተቀጣጠለ ይገኛል። በውስጥም በውጭ ይህንን እንቅስቃሴ ለድል ለማብቃት ትግሉን የጋራ ማድረግና በጥበብ መምራት ግድ ይላል። ከአፋኞቻችን ውልደት ጀምሮ በብሔር በክልል በፖለቲካዊ ቡድን እየተቧደንን በሰላማዊ መንገድም ሆነ በአመጽ በተናጠልና ህዝቡን ባላማከለበት መንገድ ስናካሂደው ቆይተናል ውጤቱ ግን ዋናዎቻችንን መገበርና የአፋኙን ሥርዓት እድሜ ማራዘም ነው።
“የብዙ ኪሎ ሜትር ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀመራል” ጉዞውን ለማስካት ደግሞ የጉዞ አቅጣጫውን መያዝ ግድ ይላል። ነፃነታችንን ለማስመለስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በአስቸኳይ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ምሁራንን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን የሚዲያ ሰዎችን በህብረተሰቡ ተደማጭ የሆኑ ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ቡድን ተመስርቶ ትግሉ ሊመራ ግድ ይላል መከፋፈል ይቁም የአብዛኛው የትግል እንንቅስቃሴ ነፃነታችንን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቻችንን ማስከበርና ተከባብረን በሰላም የምንኖርባት ሉዓላዊነቷ የተከበረ ሀገር እንድትኖረን ነው።
የአባቶቻችንን ክብር እንዉረስ ተዋርደናልና ክብራችንን እናስመልስ ! ሀገር እያለን ባይተዋር ሆነናልና እንተባበር ! ይህንን ከጫፍ ጫፍ ያለ ህዝባዊ እንቢተኝነት ተባብረንና ተከባብረን እንምራው ልዩነቶች ካሉ ከድል በኋላ በሰለጠነ መንገድ በአግባብ በጠረንጴዛ ዙሪያ ተወያይተን እንፍታ እርስ በእርስ ተጋጭተን ሀገራችንን አደጋ ላይ እንዳንጥል በማስተዋል እንራመድ።
ከአዲስ አበባ ወጣቶች የተላከ መልእክት

አጋጣሚውን መጠቀም ብልህነትና ማስተዋል ነው ! ከአዲስ አበባ ወጣቶች የተላከ መልእክት




  
አገር ሰላም's photo.
አሁን የደረስንበት ሰዓት በኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ ያለውን እውነተኛ ስሜት ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው ህዝባዊ እንቢተኝነቱ ከጫፍ ጫፍ በሚባል መልኩ እየተቀጣጠለ ይገኛል። በውስጥም በውጭ ይህንን እንቅስቃሴ ለድል ለማብቃት ትግሉን የጋራ ማድረግና በጥበብ መምራት ግድ ይላል። ከአፋኞቻችን ውልደት ጀምሮ በብሔር በክልል በፖለቲካዊ ቡድን እየተቧደንን በሰላማዊ መንገድም ሆነ በአመጽ በተናጠልና ህዝቡን ባላማከለበት መንገድ ስናካሂደው ቆይተናል ውጤቱ ግን ዋናዎቻችንን መገበርና የአፋኙን ሥርዓት እድሜ ማራዘም ነው።
“የብዙ ኪሎ ሜትር ጉዞ በአንድ እርምጃ ይጀመራል” ጉዞውን ለማስካት ደግሞ የጉዞ አቅጣጫውን መያዝ ግድ ይላል። ነፃነታችንን ለማስመለስና ትግሉን ውጤታማ ለማድረግ በአስቸኳይ ታዋቂ ፖለቲከኞችን ምሁራንን የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን የሚዲያ ሰዎችን በህብረተሰቡ ተደማጭ የሆኑ ታዋቂ ሰዎችን ያካተተ ቡድን ተመስርቶ ትግሉ ሊመራ ግድ ይላል መከፋፈል ይቁም የአብዛኛው የትግል እንንቅስቃሴ ነፃነታችንን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶቻችንን ማስከበርና ተከባብረን በሰላም የምንኖርባት ሉዓላዊነቷ የተከበረ ሀገር እንድትኖረን ነው።
የአባቶቻችንን ክብር እንዉረስ ተዋርደናልና ክብራችንን እናስመልስ ! ሀገር እያለን ባይተዋር ሆነናልና እንተባበር ! ይህንን ከጫፍ ጫፍ ያለ ህዝባዊ እንቢተኝነት ተባብረንና ተከባብረን እንምራው ልዩነቶች ካሉ ከድል በኋላ በሰለጠነ መንገድ በአግባብ በጠረንጴዛ ዙሪያ ተወያይተን እንፍታ እርስ በእርስ ተጋጭተን ሀገራችንን አደጋ ላይ እንዳንጥል በማስተዋል እንራመድ።
ከአዲስ አበባ ወጣቶች የተላከ መልእክት

“ጀግናው ይፈታ፣ ጀግናው ይፈታ” በማለት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ጉዳዩውን በአይነ ቆራኛ ሲከታተል ቆይቶአል


ጀግናው ይፈታ ጀግናው ይፈታ በማለት ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ ጉዳዩውን በአይነ ቆራኛ ሲከታተል ቆይቶአል።
ኮሌነር ደመቀ ፍርድቤት አልቀረቡም ወደ ሰኞ ተራዝሟል የከተማው ሰው በነቂስ ወጥታል በአሁን ስዓት ወደ መስቀል አደባባይ ቅስቀሳ ለማድረግ ከወህን ቤቱ እየተመለሰ ነው ። እውነት እላቹሀለው ወያኔ ፈርቷል!!!
የሰሜን ጎንደር ዞን ከፍ/ፍ/ ቤት ተወካይ ፕሬዝዳንት አቶ ባህሩ አዲስ በዛሬው ዕለት የኮ/ል ደመቀ ዘውዱ የጊዜ ቀጠሮ ቢኖርም በመንግስት ርካሽ ተወዳጅነትን ለማትረፍ ብሎም ፕሬዝዳንት ሆኖ ለመሾም ሲል በዳኞች ላይ ጣልቃ በመግባት ኮሎኔሉ ችሎት ሳይቀርብ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ ለፖሊስ ፍቀዱ በሚል ከዳኞች ጋር ዝግ ስብሰባ ይዟል:: ቀጠሮው ጥዋት ላይ የነበረ ቢሆንም ከሰዓት በኋላ በሚል የተራዘመው በዚሁ የተነሳ ውዝግብ በመፈጠሩና መግባባት ባለመቻሉ ነው!!
ዳኞችም ኮሎኔሉ ችሎት የመቅረብ ህገመንግስታዊ መብት እያለው ሳይቀርብ ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ መፍቀድ አግባብ አለመሆኑን በመግለፅ እስካሁኗ ስዓት ድረስ በአቋማቸው ፀንተው ቀጥለዋል!!
የከፍተኛ ፍ/ቤቱ ተወካይ ፕሬዝዳንት አቶ ባህሩ አዲስ ግን የኮለኔሉን መብት በማፈን ለመሾም ለመንግስት የእጅ መንሻ አድርጎ ማቅረቡንና ዳኞችንም ጭምር ሊያስበላ የተዘጋጀ አድር ባይነት የተጠናወተው ሰው ስለሆነ ጀግናው የጎንደር ህዝብ ጥብቅ ክትትል ሊያደርግበት ይገባል!!










:)

Thursday, July 28, 2016

የረኀብ አድማ ከመቱ 9ኛ ቀናቸውን ያስቆጠሩት 9 የፖለቲካ እስረኞች ራሳቸውን ስተው በግሉኮስ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው ገለጹ።

የረኀብ አድማ ከመቱ 9ኛ ቀናቸውን ያስቆጠሩት 9 የፖለቲካ እስረኞች ራሳቸውን ስተው በግሉኮስ መሆናቸውን ቤተሰቦቻቸው  ገለጹ።
ከኃምሌ 13 ጀምሮ ከቤተሰቦቻቸው የሚሄድላቸውን ምግብ ያልተቀበሉ ሲሆን፣ በትላንትናው ዕለት እና ከትላንት በስቲያ ሰውነታችው ደክሞ በአምቡላንስ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ እንዳሉ ለመረዳት ተችሏል።
1.በቀለ ገርባ 2.ብርሀኑ ተክለያሬድ 3.ዮናታን ተስፋዬ 4.ደጀኔ ጣፋ 5.ፍቅረማርያም አስማማው 6.ማስረሻ ሰጠኝ 7.ጉርሜሳ አያኖ 8.አዲሱ ቡላላ 9.አበበ ኡርጌሳ
ከላይ የተዘረዘሩት የፖለቲካ እስረኞች 5 ነጥብ ያለው መግለጫ አውጥተው የምግብ ማቆም አድማ መጀመራቸው ይታወሳል።
1. በሽብርተኛነት ተከሰው በእስር ቤት ያሉ እስረኞች ላይ የሚፈጸመው አሰቃቂ ምርመራ እንዲቆም
2.ፍርድ ቤቶች ነጻ ካለመሆናቸው የተነሳ ፍርድ ያጓትታሉ፣ በክልል መታየት የሚገባቸውን ጉዳዮች ያለሕግ በመንጠቅ ወደፌደራል ፍርድቤቶች መውሰድ ፌዴሬሽኑን የማፍረስ ተግባር ስለሆነ በአስቸኳይ እንዲቆም።
3.በፖለቲካ አመለካከታቸው ብቻ ለእስር ተዳርገው የሚገኙ ዜዜጎች ላይ የሚፈጸመው ግፍ እና አድልዎ ይቁም
4.በተለያዩ የሀገሪቱ ክልሎች ተሰማርቶ እየገደለ ሰቆቃ እየፈጸመ የሚገኘው የፌደራል ሠራዊት እንዲወጣ እና በዜጎች ላይ የሚፈጸመ አፈና፣ እስራት፣ ግድያ እንዲቆም
5. ሕገወጥ በሚል ሰበብ በዚህ ክረምት የዜጎችን ቤት የማፍረስ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም
ይህን እየጠየቅን በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር የሚገኝ ሕዝባችን ስለሰብአዊ መብት መከበር እና ስለፍትሕ ከጎናችን እንዲቆም ጥሪ እናቀርባለን::
 ኢሳት
Nafkot Eskinder's photo.

በጎንደር ብአዴን እና ሕዝቡ ያደረገው ስብሰባ ተጠናቀቀ

ሐምሌ 14 ቀን 2008 ዓ.ም ከሰሜን ጎንደር ሕዝብ የተወጣጡ ሽማግሌዎች ከብአዴን ባለስልጣናት ጋር ዉይይት ማድርጋቸው ይታወሳል። በዚህ ወይይት ሐምሌ 17 ቀን በጎንደር ሰልፍ እንደሚደረግ ሽማግሌዎች ባሳወቁት መሰረት የብአዴን ባለስልጣናት ሰልፉ ለ10 ቀናት እንዲራዘም መጠየቃቸውም ተዘግቧል።
ሰልፉ ለሐምሌ 24 ቀን እንዲሚደረግ ዘገባዎች በስፋት እየጠቆሙ ሲሆን አቶ በረከት ስምኦንን እና የክልሉ አስተዳዳሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ያካተተ የብአዴን አመራር ከሕዝቡ ጋር በጎንደር ከተማ ላለፉት ሶስት ቀናት መወያየታቸዉንም ለማወቅ ተችሏል።
ከስፍራው የደረሱ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በስብሰባው የሕዝቡን አቋም ያንጸባርቁ የነበሩ ሲሆን፣ አቶ በረከትም ከሕዝቡ የተነሱ ብሶቶችና ጥያቄዎችን በማስታወሻ ደብተራቸው ላይ ማስፈራቸዉን ጠቁመዋል። አቶ በረከት የሕዝቡን ጥያቄ ይዘው እንደሚቀርቡና ተመልሰው መጥተው ለሕዝቡ ሪፖርት እንደሚያደረጉም ቃል ገብተዋል። “አንድ ደብተር ሙሉ ጥያቂያችሁን ፅፌ ይዤያለሁ ፣ ለሚመለከተው አካል ወስጄ አንድም ሳልቀንስ አቀርብና እንወያይበታለን። ከዛ መልሱን ይዤ ወደ እናንተ ተመልሼ እመጣለሁ” ነበር ያሉት።
ሕዝቡ ጌታቸው ረዳ የተባለው ግለሰብ እና ኢቢሲ በአማራው ክልል ህዝብ ላይ ሲያሾፉና ስድብ ሲዘነዝሩ እንዴት ዝም ብላችሁ ታያላችሁ ሲሉም የብአዴን አመራር አባላትን አፋጠዉም ነበር። “ እንዴት ጌታቸው ረዳ የተባለ ጅል የአማራው ክልልን ህዝብ ሲሰድብ ዝም አላችሁ? እንዴት ብትንቁን ነው ይህን ትንሽ ሰው ሚኒስትር አድርጋችሁ የሾማችሁብን? ..” የሚሉት በጌታቸው ረዳ ላይ ከቀረቡት አቤቱታዎች ውስጥ ጥቂቶቹ ነበሩ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በጌታቸው ረዳና በኢቢሲ ሲቀርቡ የነበሩ ዘገባዎች አሳዛኝ እንደሆነ ገልጸው ሕዝቡን በአሰቸኳይ ይቅርታ መጠየቅ እንዳለባቸው የገለጹ ሲሆን ፣ አቶ በረከትም በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ላይ እየቀረበ ያለው ነገር ብዙ እንደማይጥማቸው ለሕዝቡ ገልጿል።
ሌላው የብአዴን አመራር አቶ ብናልፍ አንዷለም የተባሉኢ ግለሰብ ሲናገሩ ላዳመጠ የትግራዩ አባይ ወልዱ የሚናገር ነበር የሚመስለው። የክልሉን ህዝብ እንደሚወክሉ ፖለቲከኛ ሳይሆን በጥቅም የተገዙ፣ የለየለት የህወሃት ካድሬ መሆናቸዉንም ነበር ያረጋገጡት። እንደ ወንበዴ በሌሊት መጥቶ ዜጎችን ለማፈን የተንቀሳቀሰውን አሸባሪ ቡድን በማሞገስ ” የፌድራል ፖሊስ ህጋዊ ነው…” የሚል የመሳሰሉትን ፍሬከርስኪ አስተያየት ለመስጠት ሲሞክሩም በተሰብሳቢው ጩኸት ንግግራቸው በተደጋጋሚ ተቋርጧል። ሰዉዬ በተናገሩ ቁጥር ሕዝብ እያስቆማቸው ምናምንቴ ነበር የሚመስሉት።
ከሕዝቡ ይሰጡ ከነበሩ አስተያየቶች መካከል፡
“ ይሄን ሁሉ ግፍ በሰፊ ትዕግስታችን ችለን ተቀምጧል ።አሁን ግን ትግስታችን ተንጠፍጥፎ አልቋል”
“ ህወሓት አንዳች እርምጃ እወስዳለሁ ብትል የሚመጣው አፀፋ የከፋ እንደሆን የጎንደር ሕዝብ መልክቱን በብአዴን በኩል ልኮላታል”
“ የህወሓት የበላይነት እስከ መቼ? ከአሁን በኋላ ኢህአዴግ አብቅቶለታል ፣ ኢህአዴግ የጎንደር እናቶችን ደም እምባ ያስነባውን የመላኩ ተፈራን ስራ በሕወሓት አማካኝነት በጎንደር ሕዝብ ላይ ደጋግሞ እያደረገው ነው “
“ወንድሞቻችንን ከወልቃይት ገፍታችሁና አባራችሁ፣ ጎንደር መጠው ቢጠጉ፣ ህዝብን ንቃችሁ አፍናችሁ ወስዳችሁ ፣ ህወሓት የጎንደር ሕዝብን በደንብ ታውቀዋለች እንግዲህ ይለይልናል ፣ “
ይገኙበታል።
ለ10 ቀናት ተላልፎ የነበረዉና እሁድ ሐምሌ 24 ቀን በጎንደር ክተማ ይደረጋል ተብሎ የታቀደው የሰላማዊ ሰልፍ ነገር፣ እነ በረከት በተገኙነት ስብሰብ ላይ ሳይነሳ ስብሰባው ተበትኗል። በእርግጥ ሰላማዊ ሰልፉ በታቀደለት ቀን እንደሚካሄድ ሕዝቡ የስማ እንደሆነ ከጎንደር የሚደርሱ መረጃዎች ሲጠቁሙ፣ በሶሻል ሜዲያም ቅስቀሳዎች በስፋት እየተደረጉ ነው።
አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሕዝቡ ወገን መሆናቸዉን አስመስክረዋል። አቶ በረከትም በርጋታና በአክብሮት ነበር ሕዝቡን ሲያዳምጡ የነበሩት። ምን ያህል ሕዝቡ እንዳከረረ በመረዳታቸው አቶ በረከት አዲስ አበባ ያሉ ጓደኞቻቸውን አሳምነው መሰረታዊ የፖለቲክ ለዉጥ እንዲመጣ በመጨረሻው ሰዓት የድርሻቸዉን አዎንታዊ ሚና ይጫወቱ ይሆናል የሚል ግምት ያላቸው ጥቂቶች ቢኖሩ፣ አቶ በረከት የተላኩት ጊዜ ለማራዘም እና ህዝቡን ለማዘናጋት ነው የሚለው አስተያእይት ግን አይሎ የሚሰማ አስተያየት ነው።
በኦሮሚያ የተነሳው ቀዉስ፣ ሰሞኑን የቀድሞ የሕወሃት ጀነራሎች ያቀረቧቸው ጠንካራ ማስጠንቀቂያዎች ተደምረው፣ በኢሕአዴግ ዉስጥ ለዉጥ እንዲመጣ የማይፈለገውን አክራሪ ቡድን ወደ ጎን ተገፍቶ፣ ፔሪስትሮይካ በኢትዮጵያ እንዲመጣ የሚረዳ ሃይል ከኢሕአዴግ ዉስጥ ይወጣ ይሆን ? በቅርብ የምናየው ይሆናል። አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው፤ ጨዉ ለራስህ ስትል ጣፍጥ እንደተባለው አራት ኪሎ ያሉ ባለስልጣናት ለራሳቸው ያስቡበታል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

በጎንደር ወጣቶችና በሕወሓት ወታደሮች መካከል ግጭት ተነሳ

በጎንደር ወጣቶችና በሕወሓት ወታደሮች መካከል ግጭት ተነሳ
በጎንደር እሁድ ሰልፍ ይኖራል ብአዴን ሰልፉን ለማስተጓጎል አድማ በታኝ ፖሊስ መድቧል
በጎንደር ከተማ ከትላንትና ምሽት ጀምሮ ሕወሓት ያሰማራቸውና ጨለማን ተገን ኣድርገው ወጣቶችን ሊያፍኑ ሲሞክሩ የነበሩ የደህንነት ሃይሎች የኣፈና ድርጊታቸውን ዛሬም በቀን በቀጠሉበት ሰኣት ላይ በተፈጠረ ኣለመግባባት በጎንደር ወጣቶችና በሕወሓት ወታደሮች መካከል ግጭት መከሰቱና የተኩስ ድምጾች መሰማታቸውን በኣከባቢው የሚገኙ ምንጮች ተናግረዋል።
የእሁዱን ሰልፍ ያስተባብራሉ ለኮሎኔል ደመቀ የፍርድ ቤት ቀጠሩ በፍርድ ቤት የሚገኙ ደጋፊዎችን እያስተባበሩ ይሰበስባሉ የተባሉ ወጣቶችን ለማፈስ የተሰማራውን ሃይል የጎንደር ወጣቶች እንዳስደነበሩት ቀበሌ 18 ኣከባቢ የሚገኙ ሁኔታውን የሚከታተሉ ወገኖች ተናግረዋል። ወያኔ የፊታን እሁድ ይደረጋል የተባለው ሰልፍ እንዳስፈራውና እንዲራዘም በውስጥ እየተማጸነ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቁመዋል።
በጎንደር እሁድ ሰልፍ ይኖራል
ብአዴን ሰልፉን ለማስተጓጎል አድማ በታኝ ፖሊስ መድቧል
እሁድ ሀምሌ 24 ቀን 2008 ዓ.ም. በጎንደር የሚካሄደውን የተቃውሞ ሰልፍ በተመለከተ በብአዴን አመራሮችና በሕዝብ ሽማግሌዎች መካከል እስካሁን ስምምነት አልተደረሰም። ገዥው ቡድን ችማግሌዎችን ለየብቻ እየወሰደ በማስፈራራት እና በማባበል ሰልፉን እንዲሰርዙ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው። ሆኖም ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በነበረው ስብሰባ ሰልፉ እንደማይቀር ከሕዝብ የተውጣጡ ተሳታፊዎች እንቅጩን ተናግረዋል።
ይህን ተከትሎ ለኣማራ ክልል አድማ በታኝ ፖሊስ ወደ ሰልፉ የሚወጡ ሰዎች ላይ እርምጃ እንዲወስድ ብሎም ወደ መስቀል አደባባይ መሔጃ መንገዶች እንዲዘጉ እንዲያደርግ ከብአዴን ጽ/ቤት ደብዳቤ መላኩን ለማወቅ ተችሏል። የአማራ ልዩ ኃይል ፓሊሶችም ልዩ ዝግጅት እንዲያደርጉ ተነግሯቸዋል።
ይህን ተከትሎ በሰልፉ ለሚሳተፉ አንዳንድ ግለሰቦች “ሰልፉ ቦታ ትሄዳላችሁ?” ስንል ላቀረብንላቸው ጥያቄ “መትረየስ ቢጠመድም አንቀር!” ሲሉ በእርግጠኝነት ተናግረዋል።

#‎ምንሊክሳልሳዊ‬
 
Minilik Salsawi's photo.
 

Wednesday, July 27, 2016

በጎንደር ሕወሓቶች ሰልፍ ሊጠሩ ነው

በጎንደር ሕወሓቶች ሰልፍ ሊጠሩ ነው
አርብ ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ፍርድ ቤት በሚቀርብበት ጊዜ “የሕግ የበላይነት ይከበር” በሚል ጭንብል ኮሎኔል ደመቀን እና የአማራውን ተጋድሎ ተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ በጎንደር ከተማ ለሚኖሩ ትግሬዎች በሚስጥር መልእክት እየተላለፈ መሆኑን ከሥፍራው የተገኘ መረጃ አመልክቷ።
በተጨማሪም በዕለቱ የመንግሥት ሠራተኞች ቢሮ በገቡበት ሰአት ሕወሓትን ደግፈው በድንገት ሰልፍ ውጡ ሊባሉ እንደሚችሉ የወጡ መረጃዎች ጠቁመዋል።

የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ አስቸኳይ ጥሪ እናደርጋለን:: ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ

የዜጎችን ሕይወት ለመታደግ አስቸኳይ ጥሪ እናደርጋለን:: ከኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ የተሰጠ መግለጫ
ከሕገመንግስታዊ አግባብ ዉጭ በዜጎች ላይ የሚወሰዱ የመንግስት እርምጃዎች እንዲቆሙ በፓርቲያችንም ሆነ የትግል ጓዶቻችን በሆኑ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ ሲሰጡ የቆዩ ጋዜጣዊ መግለጫዎችንና ጋዜጣዊ ኮንፌረንሶች እናስታዉሳለን፡፡ በተለይም የዜጎቻችን ከፊንፊኔ ዙሪያ የማፈናቀል ድርጊት እንዲቆም ሲቀርቡ የቆዩ ተማፅኖዎች የመንግስት ባለሥልጣኖች ጆሮ እንዳልገባ አረጋግጠናል፡፡ በሥልጣን ላይ ያለዉ ሥርአት ደጋፊዎች ጥቂት የማይባሉና ከአንድም በላይ ቤት ሲኖራቸዉ በመኖሪያ ቤት እጦት የሚቸገሩ ዜጎች ቁጥር የትየሌለ መሆኑና እነዚህም ዜጎች ከራሳቸዉና ከልጆቻቸዉ ጉሮሮ ቆጥበዉ የሰሩት መጠለያ፤ ለዚያዉም የክረምቱ ጊዜ ከፍተኛ ደረጃ ላይ በደረሰበት ጊዜ ላይ ሲፈርስባቸዉ ማየት ምን ያህል ዘግናኝና አሳዛኝ እንደሆነ መድረክ ከሰጠዉ መግለጫ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ምንም እንኳን መንግስት ሕግና ሕጋዊነትን የማስከበር ግዴታ ቢኖርበትም፤ ሰርቶ ለአገሪቱ ገቢ እያመጣ ጎጆዉን የሚቀልስ ብቻ ሳይሆን በእንፉቅቅ እየተንቀሳቀሰ ጎሮሮዉን ለሚዘጋ ዜጋ ሳይቀር መንግስት ኃላፊነት እንዳለበት ተዘንግቶ ዜጎች በድቅድቅ ጨለማ ክረምት ሜዳ ላይ መጣላቸዉ አሳዝኖናል፡፡
ቀደም ሲልም በልማትና እንቬስትመንት ስም በተለይም በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ስም ሁሉንም ዜጎች ተጠቃሚ የማያደርገዉንና በፊንፊኔ ዙሪያ የሚገኙ የኦሮሞ ሕዝብን ከቀዬያቸዉ የሚያፈናቅል ልማት ተብዬ እንቅስቃሴ እንዲቆም የኦሮሞ ሕዝብና የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ ከ2006 ጀምሮ በመቃወማችን በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግስት በተወሰደዉ የኃይል እርምጃ 74 ዜጎች ተገድለዋል፡፡ በዚህ በ2008፤ በተለይም ከስምንት ወራት ወዲህ መንግስት ከሕዝብ ፍላጎት ዉጭ ጥቂቶች የሥርአቱ ደጋፊዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገዉን፤ ነገር ግን መላዉ የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ በተለይም የኦሮሚያ ክልል ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ የተቃወመዉን የሕዝብን ድምፅ እንደመስማት በማን አለብኝነት በወሰደዉ ያልተገባ እርምጃ እስካሁን ከ400 በላይ የኦሮሞ ዜጎች በመንግስት ኃይሎች ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ታስረዋል፤ ከቀዬያቸዉና ከሥራቸዉ የተፈናቀሉና የተሰደዱ ዜጎች ቁጥር ማወቅ አይቻልም፡፡
በመንግስት ኃይሎች በተወሰደዉ እርምጃ ነፍሰ ጡሮች፣ ዕድሜያቸዉ ከ18 ዓመት በታች የሆኑ ለጋ ወጣቶች፣ ምሁራን፣ እናቶችና አዛዉንቶች ተገድለዋል፡፡ በቅርቡ እንኳን በምዕራብ ሸዋ ዞን በግንጪና በእጃጂ ወረዳዎች እንዲሁም በምስራቅ ሐረርጌ ዞን በጉራዋና ሐረማያ ወረዳዎች ታዳጊ ወጣቶች የሆኑ ተማሪ እሸቱ ወርቁ ሞረዳ፣ ተማሪ ታረቀኝ ላቺሳ፣ ተማሪ ሣብሪና አብደላ እና ተማሪ ሪሐና አህመድ የተባሉት ራሳቸዉን በኦሮሞ ሕዝብ ጠላትነት በፈረጁ የመንግስት ኃይሎች ተገድለዋል፡፡ የእነዚህ ለጋ ወጣቶች ሕይወት መቀጠፍ የሚፈጥረዉን ስሜት ምን ሊመስል እንደሚችል የወላድ አንጀት ይፍረድ ከማለት ባለፈ ምንም ሊባልአይቻልም፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝቦችም ሆኑ የዓለም ሕብረተሰብ እንደሚመሰክረዉ የኦሮሞ ሕዝብ በበቀል ስሜት ተነሳስቶ በአንዳችም የሌላ ብሔር ዜጎች ላይ ግድያ መፈጸም ቀርቶ ያሳየዉ የጥላቻ እርምጃ እስካሁን አልነበረም፡፡ ይህ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብን አርቆ አስተዋይነት ከማሳየቱም በላይ፤ ላቅ ባለ ደረጃ ደግሞ የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ከአፋኝ ሥርአት ጋር እንጂ ከጠባብ ፍላጎት ያልመነጨና ከንፁኃን ዜጎች ጋር አንዳች ቅራኔ እንደሌለዉ ያሳያል፡፡
ዛሬ በመቶዎች የሚቆጠሩ የኦፌኮ አባላትና ደጋፊዎች እንዲሁም የኢህአዴግን አገዛዝ የተቃወሙ የኦሮሞ ዘጎች በየእስር ቤቶች ታጉረዉ መገኘታቸዉ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከነዚህ ዉስጥም አቶ በቀለ ገርባ፣ አቶ ደጀኔ ጣፋ፣ አቶ ጉርሜሳ አያኖ፣ አቶ አዲሱ ቡላላ፣ እነዮናታን ተስፋዬ፣ በረሃብ አድማ ላይ ናቸዉ፡፡ እነዚህ ዜጎች ያለ ወንጀል የታሰሩ መሆኑ እየታወቀም ቢሆንም፤ ነገር ግን በፍርድ ቤት የተያዘ ጉዳይ ስለሆነ ቤተሰቦች፣ የትግል ጓዶችና ወገኖች ዉሳኔዉን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡ ታሳሪዎቹ ወገኖቻችን በታሰሩበት ቦታ ላይ የሚደርስባቸዉን የሰብአዊ መብት ረገጣ በመቃወም ለፍትሕ አካል ያቀረቡት አቤቱታ ሰሚ በማጣቱ በራሳቸዉ ላይ የወሰዱት ቀጣይ የተቃዉሞ እርምጃ እንጂ የቅንጦት አይደለም፡፡
እነዚህም ሆኑ ሌሎች ዜጎች ፍትሕ የማግኘት መብታቸዉ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ አቤቱታቸዉ እንዲሰማላቸዉ በራሳቸዉ ላይ በወሰዱት የምግብ አለመመገብ አድማ መሞት የለባቸዉም፡፡ የሕክምናና የነፍስ ማዳን ዕርዳታ ሊደርግላቸዉ ይገባል፡፡ እነዚህ ዜጎች በእንክብካቤ እጦት ቢሞቱ ዉሎ አድሮ የሚያስከትለዉ ጉዳት ቀላል እንደማይሆን ለማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም የኢትዮጵያ ሕዝቦች፣ የኢፌዲሪ መንግስት፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሰብአዊ መብት ተከታታዮችና የዓለም ሕብረተሰብ በተለይም በአገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ የሚትገኙ ዜጎች ይህንን የይድረሱልን ጥሪያችንን በመቀበል የእነዚህ ንፁኃን ዜጎች ሕይወት ከሞት አፋፍ እንዲያተርፉልን የበኩላችሁን ድጋፍ እንዲታደርጉልን በእግዚአብሔርና በኢትዮጵያ ሕዝብ ስም እንማፀናለን፡፡
በመብት ረገጣና እንግልት የሕዝቦች የመብትና የነፃነት ትግል አይገታም!
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግሬስ
ሐምሌ 20 ቀን 2008
ፊንፊኔ
Minilik Salsawi's photo.

በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ቦኮሉቡማ ከተማ ከባድ ተቃውሞ ተደርጎዋል ። (Photos & Video) Oromo Protests



#Ethiopia #Oromoprotests #Borena በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ቦኮሉቡማ ከተማ ከባድ ተቃውሞ ተደርጎዋል ።የሕወሓት ጁንታ ኣግዓዚ ሰራዊት ሃይሎች እንደልማዳቸው ሰለማዊ ህዝብ ላይ በቀጥታ በመተኮስ 3 ሰዎችን ክፉኛ አቁስለዋል ።
 ይህንን ጸረ ሕዝብ ተግባር VIDEO‬ ኣይቶ መፍረድ የሕዝብ ልጆች ግዴታ ነው።



በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ቦኮሉቡማ ከተማ ከባድ ተቃውሞ ተደርጎዋል ። (Photos & Video) Oromo Protests



#Ethiopia #Oromoprotests #Borena በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ቦኮሉቡማ ከተማ ከባድ ተቃውሞ ተደርጎዋል ።የሕወሓት ጁንታ ኣግዓዚ ሰራዊት ሃይሎች እንደልማዳቸው ሰለማዊ ህዝብ ላይ በቀጥታ በመተኮስ 3 ሰዎችን ክፉኛ አቁስለዋል ። #MinilikSalsawi
 ይህንን ጸረ ሕዝብ ተግባር VIDEO‬ ኣይቶ መፍረድ የሕዝብ ልጆች ግዴታ ነው።



የአተት ወረርሽኝ በቀጣዮቹ ሳምንታት ይባባሳል ተባለ

የአተት ወረርሽኝ በቀጣዮቹ ሳምንታት ይባባሳል ተባለ – በከተማዋ 80 ሆቴሎችና 12 የጤና ተቋማት ታሸጉ – 10 ሺ ኪሎ ምግብና 1200 ኪሎ ሥጋ ተወገደ


በአዲስ አበባ ሰኔ 2 ቀን 2008 ዓ.ም መከሰቱ በይፋ በተገለፀው የአተት በሽታ የሚያዙ ነዋሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ የተገለፀ ሲሆን በሽታው በወረርሽኝ መልክ ሊከሰት እንደሚችልና በቀጣዮቹ ሳምንታት እንደሚባባስ የዩኤን የረድኤት ማስተባበሪያ አስታወቀ፡፡ በሽታው ከጎርፍ መከሰት ጋር ተያይዞ የሚስፋፋ መሆኑን የጠቆመው መረጃው፤ በመጪው ነሀሴ ወር ሊባባስ እንደሚችል አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በከተማዋ ለህብረተሰቡ ንፅህና የጎደለው አገልግሎት ሲሰጡ ተገኝተዋል የተባሉ ከ80 በላይ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶችን ማሸጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የምግብ፣ መድሃኒትና ጤና ክብካቤ ቁጥጥር ባለስልጣን ገልጿል፡፡
ሰሞኑን በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች በሚገኙ ሆቴሎችና ምግብ ቤቶች ላይ ድንገተኛ ፍተሻና ቁጥጥር ሲያካሄድ መሰንበቱን የጠቆመው ባለሥልጣን መ/ቤቱ፤ የመመገቢያና የማብሰያ ዕቃዎቻቸው ንፅህና በአግባቡ ያልተያዘ፣ በቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓታቸው ላይ ጉድለት የተገኘባቸውና ንፅህናውን የጠበቀ የምግብና መጠጥ አገልግሎት አልሰጡም ያላቸውን ከ80 በላይ ምግብ ቤቶች፤ ሆቴሎችና መጠጥ ቤቶች ማሸጉን አስታውቋል። በፍተሻው ወቅት የተገኙና ከአተት በሽታ ጋር ተያይዞ በህብረተሰቡ ጤና እና ህይወት ላይ አደጋ ሊያስከትሉ ይችላሉ የተባሉ ከ10 ሺ ኪ. በላይ ምግቦች፣ 120ኪ. ስጋና በርካታ አትክልቶች እንዲወገዱ መደረጋቸው ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአተት በሽታ ተይዘው ወደ ተቋሞቻቸው ለሄዱ ህሙማን ተገቢውን የህክምና እርዳታ አልሰጡም የተባሉ 10 ክሊኒኮችና ሁለት ሆስፒታሎችም መታሸጋቸው ተገልጿል፡፡
የግል የጤና ተቋማቱ ለአተት ህሙማን ሊደረግ የሚገባውን የቅብብሎሽ ህክምና በአግባቡ አላከናወኑም በሚል ነው እርምጃው የተወሰደባቸው፡፡

በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።



Minilik Salsawi's photo.
በኦሮሚያ ክልል ተቃውሞው ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎OromoProtests‬ ‪#‎Oromo‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬
Minilik Salsawi – mereja.com በኦሮሚያ ክልል አርሲ ፣ሃረርጌ ፣ቦረና እና በኣከባቢው ወረዳዎችና ከተሞች በዛሬው እለት ከፍተኛ ተቃውሞ ሲካሄድ ውሏል።በቦረና ዞን ሚዮ ወረዳ ሂዲ ሎላ ከተማ በኣርሲ ሮቤ ገርጄዳ በሃረርጌ ደደር ከተማ ፣ጉራዋ ወረዳ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን ከሮቤ ወደ በቆጂና ኣሳሳ የሚወስደው መንገድ ተዘግቷል።
በዚህ ተቃውሞ ላይ የኣግዓዚ ሰራዊት ከሕዝብ ጋር መጋጨቱ ታውቋል፤ ከዚሁ ከተያያዘ መረጃ ሪሃና ኣህመድ የተባለች የኮምቦልቻ ኮሌጅ ኣንደኛ ኣመት ተማሪ በኣግዓዚ ወታደሮች በጉራዋ ከተማ ተገድላለች። ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ

ፕርፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ስለ ኦሮሞና አማራ ትክክለኛ የዘር ምንጭ ያብራራሉ!!




• ሁሉም የኢትዮጵያ ብሔር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች ነው
• አዳም የተፈጠረው ጎጃም፤ ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው
• ስለ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ አጥንተዋል
ኑሮአቸውን በአሜሪካ ያደረጉት ታዋቂው የሥነፅሁፍ ምሁር ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ፤ የፃፉት‹‹የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ›› የተሰኘ አዲስ አነጋጋሪ የታሪክ መፅሐፍ ዛሬ ለገበያ ይቀርባል፡፡ የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ ማን እንደሆነ በጥናት ደርሼበታለሁ የሚሉት ፕሮፌሰሩ፤ እስከ ዛሬ የተለያዩ የታሪክ ምሁራን ከተናገሩት ፍፁም የተለየና አዲስ የጥናት ውጤት ማግኘታቸውን ይናገራሉ፡፡ የሁለቱ ቋንቋዎች አመጣጥም በጥናቱ ተካቷል ብለዋል። በሊንከን ዩኒቨርሲቲ በሂዩማኒቲስ የትምህርት ዘርፍ የሚያስተምሩት ፍቅሬ ቶሎሳ ፤ከዚህ ቀደም ‹‹Heaven to Eden›› እና ‹‹The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians›› የሚሉ መጽሐፍትን በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሙ ሲሆን ሁለቱም በኢንተርኔት “አማዞን” በተባለ የመፅሃፍ ሽያጭ ድረገፅ ላይ ከተፈላጊ መፃህፍት ተርታ ተሰልፈዋል፡፡ በሙያቸው ፀሃፌ-ተውኔትና የሥነ ፅሁፍ ምሁር ሲሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ጥልቅ ጥናትና ምርምሮችን በማድረግም ይታወቃሉ፡፡
አንጋፋው ምሁር ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም በቅርቡ ለንባብ ባበቁት “አዳፍኔ” የተሰኘ መፅሃፋቸው ላይ፤“የኦሮሞን ታሪክ ሙሉ አደርጎ ሊፅፍ የሚችለው ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሳ ብቻ ነው” ሲሉ ለብቃታቸው ምስክርነትና ዕውቅና መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡ ፕ/ር ፍቅሬ ቶሎሣ በርካታ ቲያትሮችን ለደረክ ያበቁ ሲሆን ከእነዚህም መካከል “ጓደኛሞቹ”፣ “ፍቅር በአሜሪካ” እና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ በቅርቡም ‹‹ላሟ›› የተሰኘ ባለ ሁለት ገቢር ቲያትር ፅፈው ማጠናቀቃቸውንም ተናግረዋል፡፡ ፕሮፌሠሩ ለአጭር ጊዜ ዕረፍት ወደ ኢትዮጵያ መጥተው የነበረ ሲሆን ወደ አሜሪካ ከመመለሳቸው በፊት ከአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ ጋር በታሪክ ጥናቶቻቸው ዙሪያ ቃለ ምልልስ አድርገዋል፡
በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያሳተሟቸው “Heaven to Eden” እና “The Hidden and untold History of the Jewish People and Ethiopians›› የሚሉት መፃህፍት በአለማቀፍ ደረጃ ሰፊ ተቀባይነት ያገኙበት ሚስጥር ምንድነው? በምን ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው የሚያተኩሩት?
የመፅሐፍቱ ይዘት ነው ወሳኙ፡፡ ተቀባይነት ያገኙት በቋንቋ አጠቃቀም ለአንባቢያን ምቹ ስለሆኑ ይመስለኛል፡፡ በአይሁዶች ታሪክ ላይ የሚያተኩረው መፅሐፍ፤በጉዳዩ ላይ ከተጻፉ ሌሎች መጻህፍትና በተለምዶ ስለ አይሁዶች ከሚታወቀው ምን የተለየ ነገር ይዟል? ብዙ ጊዜ ስለ አይሁዳውያን ሲወራ፣ቀዳማዊ ሚኒልክ የዛሬ 3ሺህ ዓመት፣ 40ሺህ አይሁዳውያንን ይዞ መጣ የሚለውን ነው የምናውቀው፡፡ ከመጡት መካከል 12ሺህ ያህሉ ንፁህ እስራኤላውያን ናቸው። 28ሺህ ያህሉ እነሱን በሥራ ያገለግሉ የነበሩ ኢያቡሳውያን የሚባሉ ነገዶች ናቸው፡፡ ቀዳማዊ ሚኒልክ ለ12 ሺህዎቹ ልዩ ቦታ ሰጥቷቸው፣ በሀገሪቷ ላይ ካህናት አድርጎ ታቦት እያስቀረፀ፣ ኢትዮጵያ ላይ በዚህ መልክ ሾሟቸው ነበር፡፡ ኢያቡሳውያን ደግሞ ንጉሱን በእጅ ስራና በውትድርና ያገለግሉት ነበር፡፡ ይሄ እንግዲህ አይሁዳውያን ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ሁለተኛው ፍልሰት ነው፡፡
የመጀመሪያውና ብዙም የማይነገረው የአይሁዳውያን ፍልሰት፣ የእስራኤላውያኑ መሪ ሙሴ በህይወት እያለ አባ ብሄር የሚባል ልኡል ነበር። የሙሴ አማች ነው፡፡ አባ ብሄር የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሊሆን ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ፣አይሁዳውያን ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡ ምክንያቱም አባ ብሄር ያገባት ልጅ የሙሴ እህት ነበረች፡፡ ሙሴ በወቅቱ ለአባ ብሄር ፅላት ቀርፆ እንዲሁም ቀይ ባህርን የከፈለባትን በትር ሰጥቶት፣ወደ ሳባ ከተማ መጥቶ ነግሷል፡፡ በወቅቱ ብዙ አይሁዳውያንም ተከትለውት መጥተው ነበር፡፡
ሶስተኛው ፍልሰት የምንለው፣የኢራቁ ናቡከደነፆር አሸንፏቸው በሚያሳድዳቸው ጊዜ፤ “ኢትዮጵያ ውስጥ አይሁዳውያን ወገኖች አሉን” ብለው ወደ ኢትዮጵያ መጥተዋል፡፡ አይሁዳውያን በነዚህ መንገዶች ነው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት፡፡ ትክክለኛዎቹ አይሁዳውያን በኢትዮጵያ ያሉት ናቸው የሚሉ ወገኖች አሉ…? የሃይማኖታቸውን ስርአት፣ መፅሃፍትና ህግጋት ከመጠበቃቸው አንፃር ከሌላ ህዝብ ጋር ስላልተደባለቁ ትክክለኛው ያለው እነሱ ጋ ነው፡፡ ሌሎቹ ወደ አውሮፓ፣ እስያ፣ አሜሪካ የተሰደዱት እነዚህን ነገሮች በተለያዩ ጫናዎች የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ጠብቀው አላቆዩትም፡፡ ወደዚህ የመጡት ግን በግድ ባህላችሁን ሃይማኖታችሁን ለውጡ ተብለው በኢትዮጵያውያን አልተረበሹም፤ነፃነት ነበራቸው፡፡ መሬትና ሁሉ ነገር የተመቻቸላቸው ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ ነበር፡፡ ሌላ አገር ላይ ቦታ እንዳይኖራቸው ተደርገው በየጊዜው ይሰደዱ ነበር፡፡
እንደውም በሩሲያ ውስጥ በድንገት አይሁዳውያንን የመግደል ድርጊት ይፈፀም ነበር። ሩሲያውያኑ ተሰባስበው፤“ዛሬ አይሁዳውያንን ገድለን እንምጣ” እያሉ ይዘምቱባቸው ነበር፡፡ ወደ መንደራቸው ሄደው አውድመዋቸው ይመለሳሉ፡፡ ማንም ስለማይበቀልላቸው ደማቸው ደመ ከልብ ሆኖ ነበር የሚቀረው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ግን ከተሰጣቸው ክብር የተነሳ በትንንሽ ንጉስነት ጭምር ይሾሙ ነበር፡፡ በርካቶቹም ካህናትና ሊቀ-ካህናት ተደርገው ለአይሁድ እምነት ተሹመል፡፡ ቀጥሎ ደግሞ የሰለሞን ዘር ነን በሚሉት ውስጥም ገብተው፣ ስርወ መንግስት እስከ መመስረት የደረሱ ነበሩ፡፡ በዓለም ላይ አይሁዳውያን ደልቷቸው የኖሩት ኢትዮጵያ ላይ ብቻ ነው፡፡ በጠቅላላው በኢትዮጵያ ሀገራት ማለትም፡- በግብፅ፣ የመን፣ ኑቢያ—ኢትዮጵያ ባስተዳደረቻቸው አካባቢዎች በሙሉ በክብር ተይዘው ነው የኖሩት፡፡ ትልቁ ማስረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ፣ እናቱ ማርያምና ቅዱስ ዮሴፍ በስደቱ ዘመኑ እኛ ጋ ብቻ ነው ጥገኝነት ያገኙት። በወቅቱ ግብፅ ለሁለት ተከፍሎ ነበር፡፡ አንዱ ክፍል በሮማውያን ቁጥጥር ስር ነበር፡፡ ሁለተኛው የኢትዮጵያ ክፍል ነው፡፡ ኢየሱስ ከመወለዱ ከ880 ዓመት በፊት አማራዎች፤ አማሩላ ደልታ ወደሚባል ቦታ ሄደው፣ አክሱማይት የተባለውን ህፃን ልጅ ዙፋን በመጠበቅ ያገለግሉ ነበር፡፡ በኋላ በ800 ዓመታት ውስጥ አማሩላ ደልታ የሚባል መንደር መስርተው ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ጋርና ከቅዱስ ዮሴፍ ጋር ሲሸሹ፣ እዚያ ነው ማረፊያ ያገኙት፡፡ ይሄ መፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ የለም፤እኛ ግን ከተለያዩ መዛግብት እናገኘዋለን፡፡ በወቅቱ የአካባቢው ንጉስ አማናቱ ተትናይ ይባላሉ፡፡ ከጎጃም ከጣና አካባቢ ነው ወደዚያ የሄደው፡፡ ሌላው አይሁዳውያኑ መፅሐፍ ቅዱሳቸው ሲጠፋባቸው ከኛ ነው የወሰዱት፡፡ አፄ ደንቀዝ የተባለው ንጉሰ ነገስት ነው ከግዕዝ ወደ እብራይስጥ አስተርጉሞ የሰጣቸው፡፡
ትክክለኛውን የአይሁድ ባህልና እምነት በመጠበቅ በኢትዮጵያ ያሉት አይሁዳውያን ብቸኞቹ ናቸው ማለት ይቻላል? አዎ! ኦሪትን ይዘዋል፡፡ ግን በደማቸው ከኛ ተደባልቀዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ነው ሃበሻ የተባሉት። ሃበሻ ማለት የተደባለቀ ነው፡፡ “አበሳ” ያለበት ወይም እንከን ያለበት ማለት ነው፤ ሃበሻ ማለት፡፡ በቀዳማዊ ሚኒልክ ጊዜ የመጡት ከኛ ጋር ተደባልቀው 560 ዓመት ከቆዩ በኋላ በባቢሎን ስደት ጊዜ ሶስተኛዎቹ ሲመጡ፣ነባሮችን ሲያዩአቸው በመልካቸው አይሁዳውያንን አልመስል አሏቸው። ስለዚህ፤“እናንተማ ክልስ ናችሁ፤አበሳ አለባችሁ” ብለው ይሰድቧቸዋል፡፡  ነባሮቹ አይሁዶች ደግሞ፤ “እናንተ ፈላሾች፤እኛ ሀገር አለን” እያሉ ይሰድቧቸው ነበር፡፡ በዚህም “አበሻ” እና “ፈላሻ” የሚለው መጠሪያቸው ሆነ፡፡ “ሀበሻ” የሚለው ቃል እኛን አይወክለንም የምለው ለዚህ ነው፤ሀበሻ አይሁዳውያኑን ነው የሚወክለው፡፡ እኛ የኢትዮጰያ ልጆች ነን፤ ኢትዮጵያውያን ነን፡፡
“በሃበሻነቴ እኮራለሁ” ስንል የከረምነውስ—–ቀለጠ ማለት ነው? አዎ! እኔ ኢትዮጵያዊ እንጂ ሀበሻ አይደለሁም። ሀበሻ የሚለው ቃል የስድብ ቃል ነው፡፡ እኛን አይወክለንም፡፡ አይሁዳዊ ካልሆነ በስተቀር አንድ ሰው ራሱን “ሀበሻ ነኝ” ብሎ ሊጠራ አይገባውም። ስድብ አያኮራም፡፡ ብዙ ሰው ስለማያውቅ ነው በሀበሻነቴ እኮራለሁ የሚለው፡፡ በአረብኛም ብናየው “የተደባለቀ”፤ “ንፁህ ያልሆነ” ማለት ነው። ይሄ መልካም ቃል አይደለም፡፡ ግን ሀበሻ የሚለው “አበሳ” ከሚለው እንጂ ከአረብኛ የመጣ አይደለም። ሁለቱ አይሁዳውያን መሃል ያለ የመሰዳደቢያ ቃል ነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያንን አይመለከተንም፡፡
‹‹ኢትዮጵያ›› የሚለውስ ከየት የመጣ ነው?
ኢትዮጵያ የሚለው ‹‹ኢትዮጵ›› ከተባለው ሰው የመጣ ነው፡፡ ኢትዮጵ ማን ነው ካልን፣ በመፅሐፍ ቅዱስ ላይ የተጠቀሰው መልከፀዴቅ የሚባል የሳሌም ንጉሰ ነገስትና ሊቀካህን ነበር፡፡ ይህ ሰው ሃገር ያስተዳድራልም፤ሃይማኖትም ይመራል፡፡ እሱም የኢየሱስ ክርስቶስ ምሳሌ ነበር፡፡ ይሄ እንዴት ይሆናል ከተባለ፣ኢየሱስ በምፅአት ቀን ሲመጣ፣ የንጉስ ንጉስ፣ የካህን  ካህን ሆኖ ነው፤መልከፀዴቅም የዚህ ምሳሌ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከዚሁ ጋር ምን ያገናኛታል ሊባል ይችላል፡፡ በጣም የሚያኮራ ግንኙነት አለው፡፡ የመልከፀድቅ ልጅ ኢትኤል ይባል ነበር፡፡ እግዚአብሔር ኢትኤልን ካለህበት የሳሌም ምድር ለቀህ ጣና ላይ ስፈር አለው፡፡ ‹‹ከዚያም ያንተ የልጅ ልጆች፣ እኔ ከ2000 አመታት በኋላ በምወለድበት ጊዜ በኢትዮጵያ  ግዛት ላይ ስለ መወለዴ ኮከብ አሳይሃለሁ” ይለዋል (እንደኔ ምርምር፤ይሄ ኮከብ የተባለው መልአኩ ገብርኤል ነው) በዚህ ሁኔታ ኢትኤል አሁን ወዳለችው ኢትዮጵያ ሲደርስ እግዚአብሔር፤‹‹ኢትዮጵ›› ተብለህ ተጠራ አለው፡፡ ‹‹ኢት›› – ስጦታ ማለት ነው፡፡ ‹‹ዮጵ” – ማለት ደግሞ ቢጫ ወርቅ ነው፡፡ ስለዚህ “ቢጫ ወርቅ ስጦታ” ተባለ፡፡ በኋላ ሃገሪቷን ኢትዮጵያ አሠኛት፡፡
በመፅሐፍ ቅዱስ በተደጋጋሚ ኢትዮጵያ ተብሎ የሚጠቀሰው ስም የትኛዋን ኢትዮጵያ ነው የሚወክለው? እሱ አሁን ያለችውን ኢትዮጵያን ነው የሚወክለው፡፡ ግን ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እስከ 13ኛው ክ/ዘመን ድረስ ለመላዋ አፍሪካ መጠሪያ ሆኖ ሲያገለግል ቆይቷል፡፡ በኋላም የመጣው አፍሪካ የሚለው ስም ከዚሁ ከኢትዮጵያ የተገኘ ነው፡፡ ከአፋሮች ነው አፍሪካ መጠሪያዋን ያገኘችው፡፡ በመፅሃፈ እዝራ ምዕራፍ ስድስት ላይ፤‹‹አፍሪካንሳውያን›› ይላል፡፡ ይሄ አፋሮችን ነው የሚወክለው፡፡ በመርከብ ስራ በቀይ ባህር ላይ የተራቀቁ ሰዎች ነበሩ፡፡ የዛሬ 3ሺህ አመት ንጉስ ሰለሞን ቤተመቅደሱን ሲሰራ፤ልዩ እንጨት፣ እጣን፣ ወርቅ (ኦፊር የተባለ ታዋቂ ወርቅ- በነሱ የተሰየመ) ጭምር ይነግዱና ለንጉሡ ያቀርቡ ስለነበር፣ስማቸው የገነነ ሆኖ አፍሪካንሳውያን የተባሉት፡፡ በሳይንሱም አፋር የሰው ዘር መገኛ እያልን ነው፡፡ ኢስያውያንም ስያሜያቸውን ያገኙት ከሣባ ቀድሞ ከነገሰው ‹‹ኢስአኤል›› ከተባለው ንጉስ ነው፡፡ ምድሪቱን ያስተዳድር ስለነበር ኢስያ ተባለች፡፡ ‹‹አፄ” የሚለውም ከዚህ የመጣ ነው፡፡
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል የመጣ ነው የሚለውስ —?
ኢትዮጵያ የሚለው ከግሪክ ቃል  የመጣ ነው የሚለው ውሸት ነው፡፡ ይሄን አጣርቻለሁ፡፡ በነሱ መዝገበ ቃላት ውስጥ ይሄ ቃል የለም፡፡ ‹‹ፊቱ የተቃጠለ›› የሚለው ቃል በግሪክ ቋንቋ ኢትዮጵያ የሚለውን ሳይሆን ሌላ ትርጉም ነው የሚኖረው፡፡ ግሪኮቹ ከኛው ሰምተው ነው መልሠው ኢትዮጵያ ያሉን፡፡ እኛ ከነሱ በፊት ነበርን እንጂ እነሱ ከኛ በፊት አልነበሩም፤ ስማችንን ሊያወጡልን አይችሉም፡፡ በምርምርዎ አዳምና ሄዋን የተፈጠሩበት ቦታ የት ሆኖ አገኙት? ኢትዮጵያ ውስጥ ነው፡፡ ጎጃም፤ ዳሞትና ጣና አካባቢ ያለ ቦታ ነው፡፡
ለዚህ ድምዳሜ ማስረጃዎ ምንድን ነው? አንደኛ ኤደንን ከሚያጠጡ አራት ወንዞች ውስጥ አባይ የምንለው ነው ኤፌሶን የሚባለው። በኦፌር ወርቅ ዙሪያ የሚዞር መሆኑ ተፅፏል፡፡ በኔ ድምዳሜ፣የኤፌሶን ወንዝ የአሁኑ ዋቢ ሸበሌ ነው። ጤግሮስና ኤፈራጥስ ደግሞ ጊዮን ራሱ ጥንት ሜዲትራኒያን ባህር ይገባ ነበር፡፡ ድሮ ሜድትራኒያን “ኪቲ” ይባል ነበር፡፡ ጥንት ጊዮን ወንዝ ሜድትራኒያን ሲደርስ ተራራ ስለነበር ተጋጭቶ ይመለስ ነበር፡፡ ከዚያ ነው መሬት ተነቃንቆ፣ቦታው ተቆራርጦ አሁን ወዳለበት ኢራቅ የሄደው እንጂ አካባቢው እዚሁ ነበር፡፡
አዳም የት ተፈጠረ ለሚለው በመፅሃፈ ሄኖክ ላይ “ኤልዳ” በሚባል ቦታ ተፈጠረ ይላል፡፡ ኤልዳ ደግሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያለው፡፡ ምክንያቱም አስሌዳውያን ወይም ኤልዳውያን የሚባሉ አሁንም ድረስ ጎጃም ውስጥ አሉ፡፡ ሄኖክ በመፅሃፉ ኤልዳ ነው የተፈጠረው ይላል፡፡ ከዚያ ወስዶ ነው እግዚአብሄር በ40 ቀኑ ወደ ኤደን ገነት የከተተው ይላል፡፡ ሄዋንን ደግሞ ከአዳም ጎን አውጥቷት ነው በ80 ቀኗ ወደ ኤደን ገነት የከተታት፡፡ ከዚህ ተነስቶ ነው ወንድ በ40፣ ሴት በ80 ቀን ክርስትና የሚነሱት። ይሄ አይነቱ ስርአት በዓለም ላይ የትም የለም፤እና ይሄ በሄኖክ መፅሃፍ የተፃፈውና አሁን ያለው እውነታ ይገኛል፡፡ ሌላው ኮሬብ የሚባል ዋሻ ውስጥ አዳም ተቀበረ ይላል፡፡ በእርግጥ በሲናይ በረሃ አካባቢ ኮሬብ የሚባል ቦታ አለ፤ ግን በተመሳሳይ ይህ ቦታ ኢትዮጵያ ውስጥም አለ፡፡ ሌላው ኖህ መርከቡን ያሳረፈው አራራት ተራራ ላይ ነው ይላል፡፡ አራራት ተራራን ለመፈለግ ወደ ቦታው ሄጄ ነበር፤ በታንኳ ጣናን አቋርጬ፡፡ አራራት ተራራ የሚባለውን ሳገኘውና አቀማመጡን ሳጠናው፣ ለመርከብ ማሳረፊያነት በአናቱ ላይ ምቹ ሜዳ አለው፡፡ ኖህ ወይን ጠጅ ጠጥቶ ሰክሮ ነበር ይላል፤መፅሃፍ ቅዱስ፡፡ በእርግጥም ቦታው የወይን ጠጅ ፍሬ ለማብቀል ተስማሚ ነው፡፡
አሁንም አትክልቶችና ጌሾ ይበቅልበታል፡፡ ከዚሁ ማስረጃ ሳልወጣ፣አዲስ አመትን አበቦች አብበው አከበረ፤የእንጨት መስዋዕትም አደረገ ይላል፡፡ ይሄ እንግዲህ ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ያለው የአዲስ ዓመት መቀበያ ስርአት፣ ከየት መጣነትን ሊያስረዳ ይችላል። በኋላ ወደ ክርስትናው የመስቀል በዓል ደመራነት ተለወጠ እንጂ በፊት ደመራ የሚነደው በአዲስ ዓመት መጀመሪያ ላይ ነው፡፡ ለዚህ ማስረጃው አሁንም ድረስ ክርስቲያን ያልሆኑ የሀገራችን ሰዎች የደመራ ስርአት አላቸው። ይሄ የአባታቸው የኖህ ትዝታ (ማስታወሻ) ነው ሲወረስ ሲዋረስ የመጣው፡፡ በዚህና በኖህ ጉዳይ ሰፊ ጥናት እያደረግሁ ነው፤ወደፊት ይፋ ይሆናል፡፡ አንድ እዚህ ላይ ልጠቅሰው የምፈልገው፣ሌላ አራራት የሚባል ተራራ አርመን ውስጥ አለ፡፡ ተራራው ግን በረዶ ያለበት፣ ገደላገደል፣ እንኳን መርከብ ሊያሳርፍ ለሰው ልጅ የማይመችና የማያብብ ቦታ ነው፤ ስለዚህ ያ ሊሆን አይችልም፡፡ በሰንደቅ አላማው ላይም የተለየ መከራከሪያ ያቀርባሉ፡፡ ለኢትዮጵያ የተሰጠ ስጦታ ነው ሲሉ ምን ማለትዎ ነው? ሰንደቅ አላማው ለኖህ ከተሰጠው ምልክት የመጣ ነው፡፡ አረንጓዴ፣ ቢጫ፣ ቀይ የጎሉበት ቀለማት ሰማይ ላይ ታይተዋል፡፡ እነዚያ ቀለማት ናቸው ዛሬ ያሉት፡፡ ከንግስት ሳባ በፊት የነገሰው አፄ ኢሲአኤል ነው ሰንደቅ አላማ እንዲውለበለብ ያደረገው፡፡ ሰንደቅ አላማ የሚለው የመጣው የኢስአኤል መንግስት “ሰንደቅ አለማ” ከሚለው ነው፡፡ ከዚያ የመጣ ነው። እሱ በወቅቱ የመረጠው፡- አረንጓዴ ቢጫ፣ቀይና ሰማያዊ ቀለማት ነበር፡፡ ለሰንደቅ አላማው ያልተገዛና ያላውለበለበ ይቀጣል ብሎ ለመጀመሪያ ጊዜ አስገዳጅ ህግ ያወጣውም እሱ ነበር፡፡ በሰንደቋ አናት ላይ ኮከብ ነበር የሚቀመጠው፡፡ ኢየሱስ ሲወለድ የሚጠቁመውን ኮከብ ለማስታወስ ይጠቀም ነበር፡፡ በዓለም ላይ ሰንደቅ አላማን የፈለሰፈ የመጀመሪያው ሰውም ሊሆን ይችላል፡፡
የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነው ኢስአኤል ከፈለሰፈው ሰንደቅ አላማ ነው፣ዛሬ ያሉት የሰንደቅ አላማ ቀለማት የመጡት፡፡ ስለዚህ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በሰንደቅ አላማው ላይ ከዚህ ተነስቶ አንድ አይነት አቋም ቢይዝ መልካም ነው፡፡ ኢስአኤል ለኦሮሞውም፣ ለአማራውም፣ ለትግሬውም፣ለአፋሩም ለሌላውም ብሄረሰብ ሁሉ አባት ነው፡፡ ከአባቶቻችን የወረደ ሰንደቅ አላማ እንጂ ከባዕድ የመጣ አይደለም፡፡ ሰውየው እጅግ ጠቢብ ነበር፤ልእለ ሰብዕ (superman) ነበር፡፡ 150 አንበሳ መግደሉን ለማስታወስ ጭምር አፄ ኢስአኤል የሰብዕ እና የአውሬዎች ንጉሰ ነገስት ብሎ ነበር ራሱን የሚጠራው፡፡ ሰውየው እጅግ ጠቢብ ከመሆኑ የተነሳ የጀነቲክ ኢንጅነሪንግን የፈለሰፈውም እሱ ነው፡፡ እንስሳን ከእንስሳ፣ ዘርን ከዘር እየቀላቀለ የፈለሰፈ የመጀመሪያው የጀነቲክ ኢንጅነር ነበር። በቅሎን የፈጠረውም እሱ ነው፡፡ አህያንና ፈረስን አዳቅሎ፡፡ ይህ ሰው የሁሉም ኢትዮጵያውን አባት ነው፡፡ የኢትዮጵ ልጅ ነው፡፡ የኢትዮጵ 10 ወንዶች ልጆች ናቸው፤ አሁን የምናያቸውን የኢትዮጵያውያን ጎሳዎች ሁሉ የፈጠሩት፡፡
ሰሞኑን ለአንባቢያን የሚቀርብ መፅሃፍ እንዳዘጋጁም ሰምቼአለሁ፡፡ የመፅሐፉን ይዘት በአጭሩ ሊነግሩኝ ይችላሉ? መፅሐፉ፤“የኦሮሞና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ” የሚል ነው፡፡ አሁን ያሉት ኢትዮጵያውያን በሞላ የኢትዮጵ ልጆች መሆናቸውን ከላይ አስረድቻለሁ፡፡ አሁን እንደምናው በሁላችንም ላይ የማንነት ቀውስ አለ፡፡ የማንነት ቀውሱ የመጣውም እኛ ማን እንደሆንን በትክክል ባለማወቃችን ነው፡፡ ስለዚህ ይህ መፅሐፍ እኛ ማን እንደሆንን፣በርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎችና ሰነዶችን አስደግፎ፣ግልጥልጥ አድርጎ  ያስረዳናል፡፡ ይህ የማንነት ቀውሳችን ከተስተካከለና ራሳችንን ካወቅን፣ በመካከላችን ግጭቶች ሊኖሩ አይችሉም፡፡ መፅሐፉ፤ፍቅር፣ ሰላምና ህብር ሊፈጥር ይችላል የሚል እምነት አለኝ፡፡ እኛ የትልቅ ሰው ዘር ነን የሚለውን በማስረጃ የሚያሳየን ነው፡፡ የሰው ዘር ምንጭ ናሙናዎች መሆናችን ይተነትናል፡፡ ማንነታችንን በትክክል ተረድተን፣ አንድ ላይ ለመጓዝ ያስችለናል ብዬ አስባለሁ – ይህ ብዙ የተደከመበት የምርምር ውጤት፡፡
የኦሮሞና የአማራ የዘር ሀረግ አንድ ነው የሚለውን ነው መፅሃፉ የሚያስረዳው? አማራና ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም በኢትዮጵያ ግዛት ያለው ብሄር፣ ጎሳ ከ10ሩ የኢትዮጵ ልጆች ነው የመጣው፡፡ ዝቅ ሲል ደግሞ የኢትዮጵ የልጅ ልጅ የሆነ፣ ጎጃም ላይ አዳምና ሄዋን ተፈጥረዋል ብዬ ባልኩት አካባቢ አንድ ጠቢብ ሰው ነበር፡፡ “ደሴት” ወይም “ደሸት” ይባላል፡፡ እሱ ነው የኦሮሞና የአማራ አባት፡፡ የዛሬ 3600 ዓመት 4 ወንዶች ልጆች ወለደ፡- መንዲ፣ መደባይ፣ ማጂ፣ ጅማ የሚባሉ፡፡ እነዚህ 4ቱም አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሀገር መጠሪያ ሆነዋል። ማጂ ደግሞ ማራ እና ጀማን ይወልዳል። ዛሬ አማራ የምንለው ማራ ነው፡፡ “ማራ” ማለት “እውነተኛ ብርሃን” ማለት ነው፡፡ አማራ ያሉት አጋዚያን ወይም የግዕዝ ቋንቋ ተናጋሪዎች ናቸው፡፡ ማጂ ማራን ወለደ ካልን፤ ጀማ እና ማራ ወንድማማቾ ናቸው፡፡ ሁለቱ ወንድማማቾች በአካባቢው ካሉት ጋፋቶች ጋር መዋጋት ሰልችቷቸው፣ ሃገር ለቀው ወደ ሸዋ ሲመጡ አንድ ወንዝ ያገኛሉ፡፡ ወንዙን ጀማ አሉት። አሁን የጀማ ወይም የ“ዠማ” ወንዝ ማለት ነው። ከአካባቢው እየራቁ ሲሄዱ የጥንት አባቶቻቸውን ቋንቋ “ሱባ”ን ትተዉ አማርኛን መፈልሰፍ ጀመሩ፡፡ መደባይ፣ ጅማና መንዲ ደግሞ ግማሾቹ ጎጃም ላይ ቀሩ፤ ግማሾቹ ወለጋ ሄዱ፤ሌሎቹም እየራቁ በምስራቅ አፍሪካ ተሰራጩ፡፡ ኦሮሚኛ ቋንቋ የሚባለውንም ፈጠሩ፡፡ በዚህ ሁኔታ ነው ዛሬ ያሉት ኦሮሞና አማራ የመጡት፡፡ ዘረ ደሸት ይባላሉ፡፡ የደሸት ልጆች ናቸው። የዘር ሀረጋቸው አንድ ነው፡፡ ቋንቋቸው የተለያየ የሆነው በሂደት ነው፡፡
ኦሮሞው የኩሽቲክ፣ አማራው የሰሜቲክ ዘር ናቸው፤ የመጡትም ከውጭ ነው የሚለው ለዘመናት የዘለቀ ታሪክስ …? እሱ ፈፅሞ ውሸት ነው፡፡ ሁለቱም ከውጭ አልመጡም፡፡ እንዳስረዳሁት እዚሁ የበቀሉ ናቸው። የአማራም የኦሮሞም አባት ደሸትም ሆነ ታላቁ አባት ኢትዮጵ ኩሽ ነው፡፡ መልከፀዴቅም ኩሽ ነው። ኦሮሞና አማራ ሁለቱም ኩሽ ናቸው፡፡ አማራ ሴም አይደለም፤ ኩሽ ነው፡፡ እስከ ዛሬ ሲነገር የነበረው ውሸት ነው። ምናልባት የአማርኛ ቋንቋ ከሌሎች ጋር ሲደበላለቅ ሴሜቲክ ቤተሰብ ውስጥ ተገኝቶ ሊሆን ይችላል። ሁሉም ኢትዮጵያውያን የኩሽ ዘሮች ናቸው። በዚሁ መፅሐፌ ላይ ስለ ቋንቋም አስረድቻለሁ፡፡ በእብራይስጥም ሆነ በአረቢክ የሌሉ እንደ ጨ፣ቀ፣ፀ ያሉ ድምጾች በአማርኛና በኦሮሚኛ ቋንቋ ውስጥ አሉ። ይሄን በዝርዝር በመፅሐፉ አስቀምጫለሁ፡፡ ኦሮሞና አማራ አንድ ነው የሚለው አመለካከት በተለይ በኦሮሞ ምሁራን ዘንድ እምብዛም ተቀባይነት ያገኘ አይመስልም፡፡ በግድ ኦሮሞን አማራ ለማድረግ ነው በሚል ወቀሳ የሚሰነዝሩ አሉ … እንዲህ የሚሉት ሁሉም ከኢትዮጵ ዘር የመጣው የደሸት ልጆች መሆናቸውን ባለማወቃቸው ነው። ይሄ መረጃ ስለሌላቸው ራሳቸውን እንደ ባዕድ አግልለው ስለሚያዩ ነው እንጂ አሁን ይሄ እኔ ያቀረብኩትን ማስረጃ በቅን ልቦና አገናዝበው ለመረዳት ከሞከሩ፣ የትልቁ ሰው የኢትዮጵ፣ የጠቢቡና የሊቀካህናቱ የደሸት ልጅ እንደሆኑ በሚያውቁ ጊዜ፣ እነሱ እንደተሳሳቱ ተገንዝበው ወደ ማንነታቸው ላይ አተኩረው ይኮሩበታል ብዬ አስባለሁ፡፡ የመጣነው ከትልቅ ዘር ነው፡፡ ኦሮሞውም አማራውም የመጣው ከዚህ ትልቅ ሰው ነው፡፡ በዚህ ሁላችንም ልንኮራ ይገባናል፡፡
የአሁኗ እና የቀድሞዋ ኢትዮጵያ ልዩነታቸውና አንድነታቸው ምንድን ነው? በግዛት ከሄድን ጥንት መላው አፍሪካ ኢትዮጵያ ነው የሚባለው፡፡ ከየመን አልፎ ሁሉ ይሄዳል፡፡ ግብፅ ውስጥ ፈርኦኖች የሚባሉት ኢትዮጵያውያን ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያውያን ከአባይ ላይ ከመርከብ ወርደው ሜዳ አግኝተው የሰፈሩበት ቦታ ነው፤ ግብፅ፡፡ የአፍሪካ ሁሉ ነገር ከኛ አይወጣም፡፡ የኢትዮጵያ ታሪክ የ3ሺህ ዘመን ነው ይባላል፡፡ እርሶ የደረሱበት የጥናት ውጤት ምን ይላል?አዎ፤ በተለምዶ 3ሺህ አመት ይባላል እንጂ ከ7ሺ በላይ ነው፤ የኢትዮጵያ ታሪክ፡፡ ኖህ ኢትዮጵያ ላይ ነግሷል፤ ከዚያ ጀምሮ 7ሺህ አመት ነው፡፡
እስካሁን በነገሩን ታሪክ ውስጥ መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ ነው በማስረጃነት የሚጠቅሱት፡፡ መፅሐፍ ቅዱስን ብቻ የታሪክ ምንጭ ማድረግ ይቻላል? መፅሐፍ ቅዱስ ብቻ አይደለም፡፡ 42 ሰነዶችን አሁን በሚወጣው መፅሐፌ ላይ በግልፅ አስቀምጫለሁ። እነዚህ ሰነዶች በተለያዩ ሰዎች በጥንት ጊዜ የተፃፉ ናቸው፡፡ ኑቢያ ውስጥ ጀበል ኑባ በተባለ ቦታ ተቀብረው የቀሩ፣በጥንት ፍርስራሽ የኢትዮጵያ ቤተ-ክርስቲያን (ከእስልምና በፊት የነበረ) ድንጋይ ሳጥን ውስጥ ተቀብረው የነበሩ የብራና ሰነዶች አግኝቻለሁ፡፡  በዚያ ላይም የተመሰረተ ነው። ከመፅሐፍ ቅዱስ ውጪ 42 ተጨማሪ የታሪክ ሰነዶችን ተጠቅሜያለሁ፤ይሄን መፅሐፍ ሳዘጋጅ፡፡ ቀጣይዋ ኢትዮጵያ ምን መምሰል አለባት ይላሉ? አሁን ማንነታችንን አውቀን፣ የማንነት ቀውሳችንን ፈትተን፣ሁላችንም የኢትዮጵያ ዘር፣ የአንድ አባትና እናት ልጆች—–መሆናችንን ተገንዝበን፤ በፍቅር፣ በሰላም፣ በመከባበር፣ በእኩልነት መኖር አለብን ብዬ አስባለሁ፡፡ ሁላችንንም ኢትዮጵ ያገናኘናል፡፡

Tuesday, July 26, 2016

የቃሊት እስርቤት ታሳሪዎችለፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዳይረክተር የላኩት ግልፅ ደብዳቤ


የቃሊት እስርቤት ታሳሪዎችለፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዳይረክተር የላኩት ግልፅ ደብዳቤ
ለፌደራል ማረሚያ ቤቶች ዳይረክተር
በፌደራል ማረሚያ አስተዳደር ካሉ ማረሚያ ቤቶች አንዱ የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሲሆን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ የሚሰሩት መጥፎ ድርጊቶች ወይንም የመልካም አስተዳደር ችግር ለሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እና ለሚመለከታቸው የመንግስት ተወካዬች ተነግሮ ዋና አስተዳደሪ ከተቀየረ በኃላ የተወሰኑ ለውጦችን መመልከታችን የማይካድ ቢሆንም ነገር ግን የቀድሞ አስተዳደር አመለካከት እና ህገወጥ አሰራሮች አንዳንዴ በታራሚው ላይ በመጫን የቀድሞውን አስተዳዳሪ በደሎች ለመድገም እና በዚህ ማሃል በሚፈጠሩት ግር ግር ማጥቃት የሚፈልጉትን ታራሚዎች አጥቅቶ የግል ጥቅማቸውን በማሳደድ መንገድ እየጠረጉ ያሉትን አባላት ለመቆጣጠር የሚቻል የሚመስሉ ምልክቶች እየታዩ ነው፡፡
የዚህ ችግር መሰረት ባለፈው አመታት ለመልካም አስተዳደር እጦት
ዋናው ተዋናይ የነበሩት አባላት አሁንም በሀላፊነት ላይ መሆናቸው ነው። የዋናው አስተዳዳሪው ጥረት ብቻውን መሰረታዊ ለውጥ ሊያመጣ አይችልም፡፡ እነዚህ ሀላፊዎች የሲጋራና የሀሺሺ ነጋዴዎች ተላላኪዎች በመሆናቸው እና ይህን የጥቅም መረባቸውን ዘርግተው የሚነግዱበት ሲሆን በአሁን ሠዐት በማረሚያ ቤቱ ውስጥ አንድ ፍሬ ሲጋራ 25 ብር አንድ ፓኬት 500 ብረ አንድ እሰቴክ 5000 ብር እየተሸጠ በመሆኑ መንግስት እንዲያርሙ የተሰጣቸውን ሃላፊነት ጥለው የግል ጥቅማቸውን እያሳደዱ ይገኛሉ።
በማረሚያ ቤት ውስጥ የግል ጥቅማቸውን ለማስከበር የሚራራጡ ባለስልጣኖች ዛሬም በስብሰባ ያጋለጣቸውን ታራሚዎች ስም በማጥፋት አደገኛ ነው ያመልጣል ወይም ከተቃዋሚዎች ጋር ይገናኛል ይነጋገራል ወዘተ በሚል ማረሚያ ቤቱ በስጋት እንዲያያቸው በማድረግ እነዚህን ታራሚዎች የማሸማቀቅ ዘመቻ ቀጥለዋል።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የጥበቃ እና የደህንነት ሃላፊ ሱፐር እንዲፔንደንት ተስፈሚካኤል እጃቸው እየተጠመዘዙ የቀድሞው የጥበቃ ሃላፊ ኢንድፔንደንት ሀጎስ የሰራቸውን ስህተቶች እየደገመው ነው ።ለምሳሌ የቀድሞ የጥበቃ የደህንነት ሀላፊ የነበሩት ሱፐር ኢንድፔንደት ሀጎስ ወዳጅ ነህ ያዙዋቸው የነበሩት የስራ ሃላፊዎች ታራሚዎችን ዛሬም ዝዋይ ለቅጣት መላክ፣ ጨለማ ቤት ማጎር ፣ማስፈራራትና መዛት ቀጥለዋል።
በ29/ 8 / 2008 ወደ ዝዋይ የተጫኑ እና አሁንም ዝዋይ ጨለማ ቤት የሚገኙ ታራሚዎች የተመረጡት በሱፐር እንዲፔንደት ተስፋ ሚካኤል አሰግድ እና በዞን 4የቀድሞው ዞን አንድ ዞን ተጠሪ ገብረ ማሪያም የተመለመሉ ናቸው፡፡ ገብረማሪያም በዞን አንድ ውስጥ እልቂት ለመፍጠር ተግቶ የሚሰራ ሰው ነው ። ለምሳሌ 11/11/2008 ተስፋ የሚወጡ ማእከል የሚጠጡ ታራሚዎች ወደ ስራ ከሄዱም ቡሃላ ቤት የቀሩትን ታራሚዎች ሰብስበው ውጡ በማለት ሁሉንም ካስወጡ ቡሃላ 1ኛ ቤት 50 የሚደርሱ የፖሊስ አባላት እየመሩ አስገብተው የታራሚው ኮሚቴ ወይም ታራሚው በሌለበት ፍተሻ በማድረግ ከተለያዩ ታራሚዎች ከ15ሺ ብር በላይ አዘርፈዋል፡፡ ከዛም አልፎ ገንዘብ ጠፍቶናል ብለው የጠየቁትን ታራሚዎች ጊቢው ላይ አድማ ወይም ረብሻ ልታስነሱ ነው በማለት አስፈራርተዋል፡፡ ሌላው በዚህ ፍተሻ ታራሚዎች የሚተኙበት ምንጣፎች፣ ፎጣዎች፣ አንሶላዎች፣ መቀመጫ ወንበሮች፣ የውሃ መጠጫ ትናንሽ ጀሪካኖች ሁሉ ተወስደዋል፡፡ በጣም የሚገርመው ነገር ደግሞ የዞን ተጠሪው ገብረማሪያም ሁለት ቤት በማስገንባት አንድ ቤት የእሱ ጠላቶች መሰብሰቢያ አንዱ ቤት ደግሞ የሱ ወዳጆች መስብሰቢያ ማድረግ ከጀመረ የሰነበተ ሲሆን በዚህ ፍተሻ ቀን ፖሊሶች አንደኛ ቤት ፈትሸው ሁለተኛ ቤት እንደጀመሩ እዚኛው ቤት እነታምራት ገለታን የመሳሰሉ ትልልቅ ሰዎች ያሉበት ቦታ ነው በማለት ለፍተሻ የገቡትን ፖሊሶች እንዲወጡ አድርጎዋል።
የዞን ተጠሪው ገብረ ማሪያም አላማው የነበረው በፍተሻው ጊዜ በተወሰደው ንብረት ምክኒያት ታራሚው ረብሻ እንዲያስነሳ እና በዚህ ግርግር ሊያስመታ የፈለገውን ለማስመታት ነበር፡፡ ይህ ያቀደው ሴራ አልሆንለት ሲል ደግሞ በ12 / 11 /08 የአንደኛ ቤት ታራሚዎች አልቆጠርም ብለው ስራ እንደወጡ በማድረግ በማታው ቆጠራ ከ20 በላይ የሚሆኑትን ፖሊሶች ዱላ አስይዘው አስገበቶ ነገር ለመቀስቀስ ሞክሮዋል፡፡ የዞን አንድ ተጠሪ ሻለቃ ገብረማሪያም የተሳሳቱ ኢንፎርሜሽኖች ለሃላፊዎች በመስጠት መስሪያ ቤቱን ለታራሚዎች መልካም ሀሳብ እንዳያደርግ ቀን እና ለሊት የሚሰራ ሰው ነው። ሻለቃ ገብረማሪያም በተለያየ ስብሰባዎች ላይ ታራሚው ሲጋራ ሀሺሽ የሚያስገባ መሆኑን ከ10 ሠዐት ቡሃላ ቢሮው ውስጥ ከነሱ ውጭ ማንንም እንደማያነጋግር እነዚህ ታራሚዎች ለሚሰሩት ማጭበርበር ስራ ቢሮ ውስጥ በስልክ በማገናኘት ከሚያጭበረብሩት ገንዘብ የጥቅም ተካፋይ መሆኑን በተለያዩ መንገዶች ለሀላፊዎች ቢደርስም የተሰጠ ውሳኔ የለም፡፡
ይህ ሳያንሰው ጊቢ ውስጥ ማንኛውም ችግር ቢነሳ ተጠያቂዎች ናቸው የሚል ፊርማ ሆነ ማህተም የሌለው የታራሚዎች የስም ዝርዝር በቦርድ ላይ አውጥቷል። ይህ ሰው እርስ በርሳችን ሳያጨራርሰን ካልተነሳልን ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ ማን ነው? ይንን በጥልቀት ያስቡበት እና ያለብንን ችግር በሃላፊነት በኢትዮጲያዊነት መንፈስ ይፍቱልን፡፡
ከሰላምታ ጋር
ግልባጭ
1 ለኢትዮጲያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን
2 ለቃሊቲ ክፍለ ከተማ ማረሚያ ቤት አስተዳደር
3 ለቃሊቲ ክፍለከተማ ማረሚያ ቤቶች ጥበቃና ደህንነት ሀላፊ
4 ለኢትዮጲያ ህዝብ በሶሻል ሚዲያ

ለብአዴኖች ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር አለኝ – ግርማ ካሳ

ለብአዴኖች ማስጠንቀቂያ አዘል ምክር አለኝ – ግርማ ካሳ
በሕዝቡና ህዝቡ መብቱን ለማስከበር በሚያደርገው እንቅስቅሴ መሃል አትግቡ። ይልቅ የሕዝቡን እንቅስቃሴ ተቀላቀሉ። የእንቅስቃሴው አካል ሁኑ። ሕወሃት የበሰበሰ፣ እንኳን በአማራው ክልል፣ እንኳን በሌሎች ክልሎች፣ በትግራይ ክልል ራሱ የተተፋ ዘረኛ ድርጅት ነው። አታዩም እንዴ በኦሮሚያ የተነሳዉን ተቃዉሞ ? አታዩም እንዴ በድፍን ሰሜን ጎንደር ዞን ምን ያል የህወሃት ነገር ሰውን እንዳንገፈገፈው ? አታዩም እንዴ እንደ ጄነራል ጻድቃን ገብረትንሳኤ፣ እንደ ጀነራል አበበ ተክለ ሃያማኖት ያሉ ቱባ ቱባ የቀድሞ ሕወሃት አመራሮች የሚጽፉትን እና የሚናገሩትን ? ሕወሃት ራሷ እርስ በርስ እየተከፋፈለችና እየተበጣበጠች ነው። ታዲያ ሞኝ ሆናችሁ ስለምን በስብሶና ደርቆ ተቀንጥሶ ሊወድቅ ትንሽ የቀረው ቅርንጫፍ ላይ መንጠልጠሉን መረጣችሁ ?
አብዛኛው የብአዴን መካከለኛው እና ታችኛው አመራር አባል የሆናችሁ ሕወሃት በብአዴን ላይ የጫነዉን ቀንበር አራግፋችሁ ለመጣል የቆረጣችሁ እንደሆነ እንሰማለን። ባለፈው የባህር ዳሩ የብአዴን ጠቅላላ ጉባኤ ላይ፣ ህወሃትን በተመለከተ ምን ትሉ እንደነበረ ይታወቃል። “”እነርሱ ባለ ፎቅ እየሆኑ እኛ ከነርሱ ጋር በመስራታችን የተረፈልን ሎተሪ መሸጥ ነው” ስትሉ እንደነበረ።
እንግዲህ የብአዴን አባላት በየቀበሌው በወረዳና ዞን ደረጃ ብተወያዩና ከታች ወደ ላይ የሆነ ድርጅታዊ እንቅስቃሴዎችን ብታደርጉ ጥሩ ሊሆን ይችላል። ከሕዝቡ ጋር ያላችሁት እናንተ ናችሁ። በሕወሃት ታዘው ከህዝብ ስሜትና ጥይቄ ጋር የሚቃረን መመሪያ የሚልኩ ከፍተኛ የብአዴን አመራር አባላትን ካሉ (ይኖራሉም) እነርሱን አንታዘዘም ማለት መጄምር አለባችሁ። በዚህ ወቅት ለሕዝቡ ያሳያችሁት ታሪካዊ አጋርነት በሕዝብ ልብ ዉስጥ የሚመዘገብ ነው የሚሆነው።
በፓርላማ ወደ 138 የምትሆኑ የብአዴን አባላት በአማራው ክልል የሚኖረዉን ህዝብ እንወክላለን የምትሉ አላችሁ። ምናልባት ሕወሃት በአዲስ አበባ ዘመናዊ ቤት ስለሰጣችሁ ወይንም ደሞዝ ስለምትቀበሉ፣ በፓርላማ በሕወሃት ረቆ የሚቀርቡትን አፋኝ ህጎች ለማጽደቅ ታጎበድዱ ይሆናል። ሆኖም ነገ ሕወሃቶች ከተጠቀሙባችሁ በኋላ እንደ ሸንኮራ አገዳ መጠው እንደሚተፏችሁ መርሳት የለባችሁም። ወክሎናል ከምትሉት ሕዝብ ጎን መቆሙ ይሻላቹሃል። ፓርላማው የሕወሃት መፈንጫ ሳይሆን የሕዝብን ጥያቄ የምታነሱበት ቦታ ይሁን። ፓርላማው ጌታቸው አሰፋ፣ ሶሞራ የነሱን እና ሌሎች በጸረ-ሽብርተኝኘት ስም ሕዝቡን የሚያሸብሩት ጠርቶ ማነጋገር መቻል አለበት ? እነ ሶሞራ የኑስ ምንድን ናቸዉና በፓርላማው ፊት የማይቀርቡት ? ጌታቸው ረዳ የተባለዉ የሕወሃቱ ግለሰብ እና የኢቢሲ ሃላፊዎች በሰሜን ጎንደር ሕዝብ ላይ ለከፈቱት የስም ማጥፋትና ዘረኛ ፕሮፖጋንዳ ለምንድን ነው በፓርላማ ቀርበው ተጠያቂ የማይሆኑት ? በዚህ ረገድ ጡንቻችሁን አፈርጥማችሁ በፓርላማ ዉስጥ መንቀሳቀስ አለባችሁ። ያንን ባታደርጉ ማን እንደሆናችሁ ህዝብ ያውቃል። በዚህ ወቅት ሕዝብን ወክለናል ብላችሁ ዝምታን ከመረጣችሁ ህዝብን እንደ ካዳችሁ ተደረጎ ነው የሚቆጠረው። ለዚህ ለክህደታችሁም ትልቅ ዋጋ እንደምትከፍሉ መረዳት አለባችሁ። ከዚህ በፊት የደነዛችሁና የሞታችሁ ነበራችሁ። ቢያንስ አሁን እንኳን ነቃ በሉ። ያን ካደረጋችሁ ሕዝብ የከዚህ በፊት ድንዛዜያችሁን ይቅር ብሎ በወሳኝ ወቅት ለወሰዳችሁት ወሳኝ አቋም አክብሮቱን ይለግሳቹሃል። ።

እርምጃ ይወሰድባቸዋል (ትረሸናላችሁ) ከተባሉ መካከል የሰባ እስረኞች የስም ዝርዝር ቃሊቲ እስረኞች ቦርድ ላይ ተለጥፏል፡፡

እርምጃ ይወሰድባቸዋል (ትረሸናላችሁ) ከተባሉ መካከል የሰባ እስረኞች የስም ዝርዝር ቃሊቲ እስረኞች ቦርድ ላይ ተለጥፏል፡፡ ==================================================================
የቃሊት መረሚያ ቤት ሊረሽናቸው የፈለገውን ታራሚዎች የስም ዝርዝር በገሃድ ለጥፎታል።
የቃሊት ከፍተኛ ጥበቃ ማረሚያ ቤት አድማ አስነስተዋል ወይም ለማምለጥ ሞክረዋል የሚል ሰበብ በመፍጠር እንደ ልማዱ ለመረሸን ያዘጋጃቸውን የሰባ የህግ ታራሚዎች የስም ዝርዝር በቀድሞ አጠራር ዞን አንድ የታራሚዎች ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ፣የ84 ታራሚዎች የስም ዝርዝር በዞን ሁለት የታራሚዎች ማስታወቂያ ቦርድ ላይ ለጥፏል፡፡ ከነዚህም መካከል የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባል የሆነው የአህመዲን ጀበል ስም ይገኝበታል፡፡
ይህንን ለማረጋገጥ የሚፈልግ የስራ ሃላፊ ወይም ባለ ስልጣን የቀድሞ ዞን አንድ እና ዞን ሁለት ውስጥ ገብቶ በማስታወቂያ ቦርዱ ላይ ማየት እንደሚችል ከማረሚያ ቤት የደረሰን መረጃ ያሳያል።
በማስታወቂያ ቦርዱ ላይ የስም ዝርዝራቸው የወጣው በግፍ የታሰሩ 1 /የአማራ ክልል ተወላጆች 2 /የኦሮሞ ክልል ተወላጆች 3 / የደቡብ ክልል ተወላጆች ናቸው፡፡
በዚህ ዝርዝር ውስጥ ትግርኛ ተናጋሪ ታራሚዎች አልተካተቱም ። በዚሁ ቃሊቲ ማረሚያ በ1998 የተነሳውን ሀገር አቀፍ ተቃውሞ ተከትሎ በዚህ አይነት የዘር ጥላቻ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ ታራሚዎች ረብሻቹሃል በሚል ሰበብ መረሸናቸው የሚታወቅ ነው።
አሁኑም በህዝበ ሙስሊሙ የገቡ ታራሚዎች፣ በኦነግ ስም የታሰሩ፣በግንቦት 7 እና በአርበኞች የታሰሩ ታራሚዎች እና ከነሱ ጋ ይበላሉ ይጠጣሉ ወይም ይጫወታሉ የሚሉዋቸውን ታራሚዎች በመቀላቀል የበቀል ስሜት የወለደውን የጥፋት እርምጃ ለመውሰድ ተዘጋጅተዋል።
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ውስጥ ዋናው አስተዳዳሪው ፣ የጥበቃ እና ደህንነት ሃላፊው የደህንነት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ ሃላፊዎች ፣ የዞን ተጠሪ ፣ የሽፍት መሪ ፣ የህክምና ክፍል ነርሶች ተብለው የተመደቡት ባጠቃላይ ትግሬዎች ናቸው። በቃሊቲ ውስጥ ኦሮሞ አልያም አማራ ኮሎኔል ሻለቃ ወይም መቶ አለቃ በትግሪኛ ተናጋሪ ተራ ወታደር የሚታዘዝ ነው።
የቃሊቲ ማረሚያ ቤት የተደራጀ ፣ህውሃት ከየ ክልሉ የሚፈልጋቸውን ሰዎች የሚያጉሩበት እስር ቤት ነው ። የህወሀት መንግስት አሁን እስረኞችን ለመረሸን የተነሳው በተለይ በአሁኑ ሠዐት በተለያዩ አካባቢዎች የተነሳበትን ተቃውሞ ማስተንፈሻና መበቀያ ነው።
ድምፃችን ይሰማ ‪#‎EthioMuslims‬ ‪#‎EthioMuslimCommitteeMembers‬ ‪#‎EthioMuslimsPeacefulStruggle‬ ‪#‎GovtBrutalityAgainstMuslims‬ ሰበር ዜና!!! መንግስት በእስር የሚገኙ የሰላም አምባሳደሮቻችን ላይ የሚያደርሰውን ጫና እና ጥቃት ቀጥሎበታል!
‹‹እርምጃ ይወሰድባቸዋል›› ከተባሉ እስረኞች መካከል የ4ቱ ወኪሎቻችን ስም እንደሚገኝ የውስጥ መረጃዎች ጠቁመዋል! ማክሰኞ ሐምሌ 19/2008 የህዝበ ሙስሊሙ ድምጽ በመሆናቸው ብቻ ያለአንዳች ወንጀል በሐሰት ክስ ተፈርዶባቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከሚገኙት ጀግኖቻችን መካከል 4ቱ በማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ጫና እና አካላዊ አደጋ ስር መሆናቸውን የሚጠቁሙ መረጃዎች እየወጡ ይገኛል፡፡ ገና ከጅማሮው ከቶርቸር አንስቶ ጠያቂ እስከመከልከል፣ ጨለማ ክፍል እስከመታሰር እና ቤተሰቦቻቸውን እስከማንገላታት የሚደርሱ የተለያዩ ህገወጥ ጫናዎች ሲደርስባቸው የቆዩት ህጋዊ ወኪሎቻችን በእስር ቤት ሆነውም ሰላም እንዳያገኙ ለማድረግ የመንግስት ደህንነቶች ሲያደርጉ የቆዩትን ጥረት አሁንም አጠናክረው የቀጠሉበት መሆናቸው ታውቋል፡፡ የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር ‹‹ረብሻ ለመፍጠር አሲራችኋል›› በሚል በርካታ እስረኞችን በሃሰት የወነጀለ ሲሆን ከጀግኖቻችን መካከል 4ቱም እርምጃ ለመውሰድ ከተዛተባቸው እስረኞች ስም ዝርዝር መሐል ስማቸው መካተቱን እና መለጠፉን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ይህ ዓይነቱ አሰራር መንግስት ቂም በያዘባቸው ታሳሪዎች ላይ በ‹‹ብጥብጥ አስነስተዋል›› ሰበብ እስከ ግድያ የሚደርስ እርምጃ ሲወስድ የቆየበት አሰራር መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከዓመታት በፊት በርካታ የፖለቲካ እስረኞች ‹‹ለማምለጥ በሚል ብጥብጥ አስነስተዋል›› በሚል ውንጀላ በማረሚያ ቤት ጥበቃዎች መገደላቸው የሚታወስ ሲሆን አሁንም መንግስት ተመሳሳይ እርምጃ በሰላም አምባሳደሮቻችን እና በሌሎች ታሳሪዎች ላይ ለመውሰድ እቅድ የያዘ ስለመሆኑ የውስጥ አዋቂ ምንጮች እየጠቆሙ ነው፡፡ ህገ መንግስታችን የእስረኞችን ከህገወጥ ጥቃት እና ጫና የመጠበቅ መብት በግልጽ ያስቀመጠ ሲሆን አገሪቱ ተቀብላ የፈረመቻቸው በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ውሎችም በእስረኞች ላይ የሚደርስን አላግባብ ጥቃት አጥብቀው ይኮንናሉ፡፡ በመሆኑም በሰላም አምባሳደሮቻችን ላይ ዘርፈ ብዙ ጥቃት ሲያደርስ የቆየው መንግስት አሁን ላይ ለማድረስ አቅዷል እየተባለ ካለው ህገ ወጥ ተግባር በአስቸኳይ እንዲቆጠብ እያሳሰብን በእስር በሚገኙ ብርቅዬ መሪዎቻችን ላይ በሐሰት ‹‹የብጥብጥ ድራማ›› ሰበብነት አንዳች ጉዳት ቢደርስ መላው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም መንግስትን ተጠያቂ ከማድረግ ወደኋላ የማይል እና በደለኞችንም እስከመጨረሻው የሚፋረድ መሆኑን በአጽንኦት እናስታውቃለን! እስረኞችን ማዋከብ እና ማጥቃት ህገ መንግስቱን የሚጻረር ወንጀል ነው! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማል! አላሁ አክበር!
 

Friday, July 22, 2016

የትግራይ ግዛት ክፍሎች እነማን ነበሩ (ከታሪክ መዝገብ በዶ/ር ኀይሌ ላሬቦ)

አንዳንድ የምዕራብ መንግሥታት በአፍሪቃ ቀንድ ላይ ባላቸው ጥቅምና ቀዝቃዛ ጦርነት በወለደው ፉክክር ተገፋፍተው፣ በወያኔ ስም የሚጠራውን የድሮውን የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር በአፄ ምኒልክ ዙፋን ካስቀመጧቸው ጊዜ ጀምረው፣ መሪዎቹ በስመ የብሔር ብሔረ-ሰቦች ነፃነትና እኩልነት ከፍተኛ ያስተዳደር ክልል ለውጥ አድርገዋል። ከነዚህ ለውጦች መካክል
ቀንደኛ ቦታ ይዞ የሚገኘው የኢትዮጵያን መሬት እነሱ ላመኑበት ዓላማና ዕቅድ በሚመቻቸው መንገድ፣ ዘርማንዘርን መሠረትና መስፈርት ባደረገ መልኩ ሸንሽኖ በመከለል፣ በዚህ መንገድ የተፈጠረው እያንዳንዱ ጐሣ ራሱን በራሱ እንዲያስተዳድር ማድረግ ነው። ኢትዮጵያ የሚትባል አገር ከተፈጠረች ጀምሮ በልዩ ልዩ መልክና መንገድ በመወላለድና በመቀላቀል የተዋሐደውንና የተሳሰረውን ሕዝብ፣ በዚህ ወያኔ በፈጠረው የምናብና የልበወለድ ምሥል ያገሪቷን ሕዝብ መከፋፈሉ አነጋጋሪ ብቻ ሳይሆን አጨቃጫቂም ሁኗል ማለት ነገሩን በጣም አቅልሎ ማየት ነው። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን በተወሰኑት አካባቢዎች ወደ ታላቅ ሽብርና ጦርነትም መርቷል።
Tigray Region after 1991
ወያኔ እንደ አውሮጳ አቈጣጠር (አ. አ.) በሺ ዘጠኝ መቶ ስድሳዎቹና ሰባዎቹ መኻል አብዛኛውን ዓለምንም ሆነ፣ ኢትዮጵያን ያናውጥ የነበረ የወጣቱ ተማሪ እንቅስቃሴ ርዝራዥ መሆኑ መረሳት የለበትም። ይሁንና ወጣትነት በዐዋቂነት፣ ከዚያም በሽማግሌነት ሲተካ ገጠመኛቸው እየሰፋ፣ ያስተሳሰብ ችሎታቸውም እየረቀቀና እየተሻሻለ ሄዶ፣ ከነዚህ ወጣቶች አብዛኞቹ አሁን አድገውና በስለው ወደኋላ ተመልሰው ያኔ ይሠሩት የነበሩትን ድርጊቶች ሲመለከቱ፣ አንዳንዶቻቸው ሲስቁበት፣ ሌሎቹ ሲጸጸቱበት ይታያል። ወያኔዎች ግን ለዚህ የታደሉ አይመስሉም። ከልጅነት እምነታቸውና ግትርነታቸው ፈቀቅም አላሉም። በቅዱስ መጽሐፍ አነጋገር፣ እንደግብጻዊው ፈርዖን ልባቸው እንደነደነ፣ አንገታቸው እንደገዘፈ፣ ርእዮታቸው በቅዠትና በምናብ ዓለም እንደተሰቀለ ቀርቷል። ከዕድሜና ከትዝብት ማለትም ከገጠመኝ የሚመጣው የአእምሮና የአስተሳሰብ ብስለት ሳይጐበኛቸው ወደሕይወታቸው መጨረሻ እየቀረቡ ናችው። ሥልጣናቸውን ያገኙት እንደአብዛኞቹ አላንዳች ዕፍረት እንደሚወቅሷቸው የድሮዎቹ አጤዎች በጒልበትና በጦር ኀይል ሲሆን፣ ግን እንደነሱ ሕዝቡን በማስደሰትና ጥቅሙን በመጠበቅ የማስተዳደር ችሎታም ብቃትም ከቶ አላሳዩም ብቻ ሳይሆን አገሩን የብዝበዛና የወረራ ምድር እንጂ እንደእናትና እንደትውልድ አገራቸው አድርገው አላዩትም ማለቱ ስሕተት አይመስለኝም። ይኸ ሁናቴ ግን ከፍተኛና ሰፋ ያለ የታሪክ፣ የኅብረተሰባዊና የሥነልቡና ትንተናና ጥናት የሚፈልግ ራሱን የቻለ ርእስ ስለሚፈልግ ለጊዜው አልፈዋአለሁ።
የዛሬ ጽሑፌ የሚያተኩረው ለብዙ ጊዜ አነታራኪ ሁኖ ቈይቶ፣ አሁን ግን እየከፋ መጥቶ፣ ወደጥኑ ጦርና ደም መፋሰስ ደረጃ ሊያደርስ የቀረበውን፣ በትግራይና በኩታገጠም አገሮች፣ በተለይም ጥንት በጌምድር፣ አሁን ደግሞ ጐንደር ተብሎ በሚጠራው ግዛት መካከል በተፈጠረው ውዝግብ ላይ ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው፣ ነገሩ የተነሣው በወያኔዎች የሚመራው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደሞክራሲያዊ ግንባር መንግሥት የዘረጋው በዘርማንዘር ላይ የተመሠረተው የክልል መንግሥት ሥርዐት፣ ከማንኛውም ክልል ይበልጥ ትግራይን የሚበድል ሁኖ ስለተገኘ ይመስላል። ይኸንን ለመረዳት ብዙም መመራመር አይጠይቅም። ገና ወጣት ልጅ ሳለሁ ዕድል ገጥሞኝ ወደኤርትራ ለትምህርት ስሄድ፣ በጣም የገረመኝና በጭንቅላቴ ውስጥ እስካሁን ተቀርጾ የቀረ ነገር ቢኖር፣ እግሬ ትግራይን እንደነካ መሬቱ ከልክ በላይ ከመበላቱ የተነሣ ከድንጋይ ውጭ አፈር ማየት ብርቅ ነበር። ሕዝቡ በጣም የሚደነቅ፣ ጨዋና እጅግ በጣም በኢትዮጵያዊነቱ የሚኰራ ሁኖ ሳለ፣ መሬቱ ግን አሳዛኝ ነበር። እርሻው የጠጠርና ያፈር ድብልቅ፣ ጭንጫ መሬት ነው። ገና በልጅ እግርነቴም ቢሆን፣ ይኸ ምንድር ነው ብዬ ስጠይቅ እየተዘራ ያለ ማሳ ነው ሲሉኝ እጅግ ደነገጥሁኝ፤ እንዴት አባቱን እህል እዚህ መሬት ላይ ሊበቅል ይችላል ብዬ ላምን አልቻልኩም ነበር።
በተደጋጋሚ በተለያየ ቦታ እንደተጻፈውና እንደተገለጠው ወያኔ ገና የሽምቅ ጦርነቱን ሲያካሂድ ያለመውና የፀነሰው ዓላማ፣ ከኢትዮጵያ ነፃነቷን አግኝታ፣ ሀብታምና ኀያል የሆነች የትግራይን መንግሥት መፍጠር ነው። ይኸ ነገር እስካሁን ግቡን ባይመታም የወያኔ መሪዎች አሳቡ ስሕተት መሆኑንና፣ አሁን ግን እንደማይቀበሉት የገለጹትና የተናገሩት ነገር የለም። የረጅም ጊዜ ዓላማችን አይደለም ብለውም አልተናዘዙም። ይልቅስ የተያያዙት በጦር ሜዳ ላይ የጠነሰሱትን ዕቅድ በተግባር በማዋል ላይ መስሎ ይታያል። ዕቅዱም የሚከተለውን ይመስላል።
በነሱ አስተሳሰብ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የትግራይ መልክዐ ምድር፣ የተወሰነ ቅርጽና ይዘት ኑሮት አያውቅም። በየጊዜው ይቀያየር ነበር። ከመላ ጐደል ግን፣ በምዕራብ ከሱዳን፣ በምሥራቅ ከቀይ ባሕር ሲካለል፣ በሰሜን በአሁኑ የኤርትራ መንግሥት ውስጥ የተጠቃለሉትን አብዛኞቹን አገሮች፣ በደቡብ ደግሞ አያሌውን የወሎን ክፍሎች ያካትት ነበር ባዮች ናቸው። ከዚህም የተነሣ የትግራይን የተፈጥሮ ሀብትና የአፈር ድኽነት፣ ከወሎና ከበጌምድር መሬቶች በመውሰድ ሊክሡ ፈለጉ። መንግሥት እንደመሆናቸው ሥልጣናቸውን በመጠቀም እንዳሉት መተገበር ጀመሩ። አንዳንድ የተማርን ዐዋቂዎች ነን ባዮች የአካባቢያቸው ምሁራንም የፈበረኩትን የታሪክ ማስረጃ በማቅረብ ድጋፋቸውን አበረከቱላቸው። እንደነዚህ እኔ ጥራዝ-ነጠቅ በምላቸው የታሪክ ምሁራን አባባል በሰሜን በጌምድር (በአሁኑ ቋንቋ ጐንደር) የሚገኙ ወልቃይት፤ ጸገዴ፣ ጸለምትና ሌሎችም እነሱን የመሳሰሉ አገሮች በተለያየ ጊዜ በትግራይ ገዢዎች አስተዳደር ሥር ነበሩ በማለት ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል[1]
ሐቁ ግን እጅግ ከዚህ የራቀ ነው። በእጃችን ያሉት የታሪክ ሰነዶች የሚነግሩንም ሆነ አገሩን ያስተዳድሩት የነበሩት ገዢዎች የሚሰጡን ማስረጃዎች በፍጹም ይኸንን አቋም አይደግፉም። ከውጭ አገር ጸሓፊዎች መካከል እንደ አ. አ. በሺ ስድስት መቶ ኻያ ዐራት ዓ. ም. ገደማ ወደኢትዮጵያ መጥቶ አገሩን ለረጅም ዓመታት ያህል ዙሮ የጐበኘው የጶርትጓሉ የማኅበረ ኢየሱሳውያን ቄስ አባ ማኑኤል ዳልሜይዳ፣ የደጋው ኢትዮጵያ ወይንም የሐበሻ ታሪክ (Historia de Ethiopia a alta ou Abassia[2])” በተባለው መጽሐፉ የትግራይን ግዛት ርዝመትና ስፋት በመጠኑ ይገልጥልናል። እንዲሁም እንደ አ. አ. በሺ ስድስት መቶ ኻያ ዐራት ዓ. ም. ኢትዮጵያ ሄዶ መቀመጫውን ትግራይ ውስጥ አድርጎ ላሥር ዓመት ያኽል ባገሩ የኖረው አባ ማኖኤል ባራዳስ (Manoel Barradas) የተባለው ሌላ ኢየሱሳዊ፣ “በኢትዮጵያ ስለትግራይና አስተዳደሯ ዳግማዊ ሐተታ (Tratado secondo do regno de Tegre’ e seus mandos em Ethiopia[3])” በሚለው መጽሐፉ፣ የትግራይን ግዛት ክልልና ስፋት በደምብ አድርጎ ይተነትናል። ለናሙና ያህል የጠቀስኳቸውን የውጩን አገር ማስረጃዎች እዚሁ አቁሜ፣ ወዳገር ቤት ብገሠግሥ የነገሥታቱ ታሪኮች አሉ። እነሱም ደጋግመው የሚነግሩን ከጶርትጓሎቹ ማስረጃ የተለየ አይደለም።
በእነዚህ መረጃዎች መሠረት የትግራይ የሹመት ወይንም የግዛት ክፍሎች በተናጠል ሲዘረዘሩ፣  አክሱም ካለበት ትግሬ ከተባለው አውራጃ ራሱ፣ ቦራ፣ ሐዋዜን፣ መንበርታ፣ ሰለዋ፣ ሰሐርት፣ ሠራዬ (ሠራዌ)፣ ሺሬ፣ ተምቤን፣ ናግና፣ አበርጌሌ፣ አጋሜ፣ እንደርታ፣ ዐረብ፣ ዋጅራትና ገራልታ ናቸው። በጥንት እነዚህ ክፍለ-ግዛቶች በየራሳቸው ሹም ሲተዳደሩ፣ የመላው አገሩ የበላይ አስተዳደሪ ሁኖ የሚታወቀው “ትግሬ መኰንን” በሚል ማዕርግ የሚጠራው ሹም ነው። በቀረው ከትግራይ ማዶ ባለው አሁን ኤርትራ በመባል በሚታወቀው አገር ውስጥ ያሉት ክፍለ አገሮች የበላይ አስተዳዳሪ ባሕርነጋሽ ነበር። ግን በሺ ዐምስት መቶ ሰማንያ ዓ. ም.  ላይ ባሕርነጋሽ ይስሐቅ ምፅዋን ይቈጣጠር ከነበረው ከቱርክ መንግሥት ጋር ጐን ሁኖ በመሰለፍ ቢሽፍትና፣ እናት አገሩን አብሮ ወግቶ ቢሸነፍ፣ ግዛቱ ለትግሬ መኰንን ተሰጥቶ ቀረ። ይኸም ሁናቴ ኢጣሊያን የድሮውን የባሕርነጋሽ ግዛት በጉልበት ወስዳ ኤርትራ ብላ አዲስ ስም አወጥታ በቅኝ ግዛት እስከያዘችበት ጊዜ ድረስ አልተለወጠም።
በኢትዮጵያ፣ ማእከላዊ መንግሥቱ በዘመነ-መሳፍንት ወድቆ ከነበረበት፣ መልሶ በሦስቱ ነገሥታት (አፄዎቹ ቴዎድሮስ፣ ዮሐንስ፣ ምኒልክ) ጥረት በዘመናዊ መልኩ ከተቋቋመ በኋላም ቢሆን፣ ይኸ ያስተዳደር ክልል አልተቀየረም። በአፄ ኀይሌሥላሴም ዘመን የትግራይ ክልል በምዕራብ ከተከዜ ወንዝ፣ በደቡብ ከአላማጣ የማይሻገር እንደነበር፣ በጊዜው ጠቅላይ ግዛቱን የበላይ ሹም ሁነው ያስተዳድሩ የነበሩት ልዑል ራስ መንገሻ ሥዩም ለአሜሪቃ የሬድዮ ድምፅ [Voice of America] በሰጡት መጠይቅ በይፋ በማያወላውል መንገድ ገልጠውታል[4]
እንግዴህ የሰሜን ጐንደርም ሆነ የወሎ ክፍለ አገሮች የትግራይ ግዛት ክፍል ሁነው የሚገኙት በወያኔ መሪዎች ጭንቅላትና እነሱ በተጠናወታቸው ልማዳቸው መሠረት በቅርቡ በፈበረኩት ልበወለድ ታሪክ ብቻ ነው ማለት ይቻላል። አፈታሪክም ሆነ የጽሑፍ ማስረጃዎች ግን በምንም መልክ አይደግፉም።
=================
[1] . ከነዚህ መካከል ብዙ ንትርክ የፈጠረው ዶ/ር ገላውዴውስ አርአያ በአ. አ. 16 የካቲት 2016 (March 16, 2016) ለVoice of America Tigrigna Program ላይ ወያኔ በሰሜን ጐንደር የሚያደርገውን ያስተዳደር ክልል የማኖኤል ባራዳስን ጽሑፍ አሳስቶ በመተርጐም  የሰጠው የቃለመጠይቅ ድጋፍ ነው። ስለንትርኩ http://www.ipetitions.com/petition/complaint-against-dr-ghelawdewos-araias ይመልከቱ።
[2] . የዚህ ጽሑፍ መጠነኛው ክፍል በC. F. Beckingham and G. W. Huntingford,  Some Records of Ethiopia, 1593-1646 (London: Hakluyt Society, 1954) በእንግሊዝኛ ተተርጉሟል። ከገጽ 14-15 ያለው የትግራይን ወሰንና ስፋት ይገልጣል።
[3] . ይኸ ጽሑፍ በElizabeth Filleul ተርጓሚነት በRichard Pankhurst አርታኢነት እንደ አ. አ. በሺ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስድስት በእንግሊዝኛ ታትሟል። ሙሉ አርእስቱ Manoel Barradas, Tractatus Tres Historico-Geographici (1634): A Seventeenth Century Historical and Geographical Account of Tigray, Ethiopia (Wiesbaden: Harrassowitz, 1996). መጀመርያው ምዕራፍ ስለትግራይ ግዛት ስፋትና ወሰን [ገጽ 1-2]፣ ገቢና አስተዳደር ይገልጣል።

Tuesday, July 19, 2016

ሰው በመግደል ወንጀል ጥርጣሬ በሚል በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ሕወሓት ክስ መሰረተች


ሰው በመግደል ወንጀል ጥርጣሬ በሚል በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ሕወሓት ክስ መሰረተች::

======== የዐማራ ተጋድሎ የዛሬ (ሀምሌ 12 ቀን 2008 ዓ.ም.) ውሎ ==========
1. በኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ላይ ክስ ተመስርቷል፤ ሐምሌ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ሰሜን ጎንደር ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡ የቀረበው ክስ ‹‹ሰው በመግደል የተጠረጠሩ›› የሚል ሲሆን ከሐምሌ 5 ቀን በፊት ባለ ጉዳይ ይሁን ወይም ሐምሌ 5 ቀን ራሱን ለመከላከል ባደረገው ጥረት የታወቀ ነገር የለም፡፡ ሐምሌ 22 ቀን ከሳሽ ማን እንደሆነም ይለያል ተብሏል፡፡
2. ኮሎኔል ደመቀን በየቀኑ የሚጠይቀው የዐማራ ሕዝብ ብዛት እስከ 1000 (አንድ ሺህ) ይደርሳል፤ በወያኔ አዋጅ አሸባሪን የጠየቀ አይደለም በቅርብ ርቀት አብሮ ሻይ የጠጣ አሸባሪ ነው፤ ምን እንደሚሉ አይታወቅም፡፡ በነገራችን ላይ ኮሎኔል ደመቀን ከጎጃም፣ ከሸዋም፣ ከወሎም እየመጡ የሚጠይቁት (ጀግናውን የሚያዩት) ሰዎች ብዛት አላቸው፡፡
3. ዐማሮችን በመወከል 22 ሽማግሌዎች ድርድራቸውን ቀጥለዋል፡፡ እስካሁን አሸናፊ ናቸው፡፡ ሐምሌ 5 ቀን ራሱን ለማዳን ባደረገው ተኩስ በሞቱት የወያኔ ፖሊሶች ኮሎኔል እንደማይጠየቅ ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡ ኮሎኔል ደመቀ በምንም መልኩ ወደ ፌደራል (የትግራይ መንግሥት) ተላልፎ አይሰጥም፡፡ የታሰሩ የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሚቴዎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጥረት ላይ ናቸው፡፡
4. የትገሬ ቤቶችንና ዜጎችን ለመጠበቅ ጎንደር ገብተው የነበሩ የመከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከከተማው እንዲወጡ ተደርጓል፤ በቅርብ እርቀት ላይ ሰፍረዋል፡፡ ጸጥታውን የዐማራ ልዩ ኃይልና ሲቪል ፖሊስ ተረክቧል፡፡ የጎንደር ዐማሮች እናንተ ጠብቃችሁ አታድኗቸውም፤ እኛ ጋር ካልተጣሉ ችግር የለብንም የሚል መልስ በተመረጡ ሽማግሌዎች ተላልፏል፡፡
5. ነገ በጎንደር የአጼ ፋሲል ስታዲዮም የፋሲል ከነማና ኢትዮጵያ መድን ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፤ የከተማው ሕዝብ እኛ ከተጫዋቾች ሳይሆን ችግራችን ከወያኔ ቅጣ ያጣ አገዛዝ ጋር ነው በማለታቸው ጨዋታው በተያዘለት መርሀ ግብር መሠረት ይሔዳል፡፡ የፋሲል ከነማ ነገ ካሸነፈ የኢትዮጵያን ፕሪሜር ሊግ ይቀላቀላል፡፡
6. ዐማሮችን የሚያወግዙ ሰልፎች በየከተሞቹ እንዲደረጉ ወያኔ ያመጣው ሐሳብ ለሁለት ተከፍሏል፡፡ እንዲያወግዙ ታስበው የተዘጋጁት ሰልፎች በዐማራና በአዲስ አበባ ወደ ተቃውሞ ይዞራሉ የሚል ስጋት በመምጣቱ ሰልፉ መቅረት አለበት ወደሚል ተደርሷል፡፡ እብሪተኛው ሕወሓት ግን ከሰልፈኞች እኩል ብዛት ያለው የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ ጋር መውጣት አለባቸው የሚል ግትር አቋም ይዟል፡፡ ወያኔ በዚህ አቋሙ ገፍቶ ከቀጠለ የሚፈጠረውን መገመት አይከብድም፡፡
7. የዐማራ ብሔር በሆኑ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባላት ላይ ከፍተኛ ክትትል መኖሩም ታውቋል፡፡ የመከላከያና የፌደራል ፖሊስ አባል የሆኑ ዐማሮች በምንም መልኩ ወገኖቻቸው ላይ አይተኩሱም፡፡ ወያኔም ይህን ስለሚያውቅ አቋሙን እያለሰለሰ እንደሆነ ተገምቷል፡፡
ሌሎች መረጃዎች ሲኖሩ በየሰአቱ እናደርሳለን፡፡
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!! Muluken Tesfaw
Minilik Salsawi's photo.

ሰበር ዜና፤በጎንደር ክፍለ ሐገር በሥርዓቱና በአገልጋዮቻቸው ላይ ዛሬ ተጋድሎው እንደተጀመረ ዛሬ አመሻሽ ላይ የደረሱን መረጃዎች አመልክተዋል

የጎንደር ዐማሮች የዛሬ ውሎ በአጭሩ፤
1. የሥርዓቱ ደጋፊ ትግሬዎች ከሽንፋና ገንዳ ውኃ አንድ ባንድ ውልቅ ብለው እየወጡ ነው፤ ያለሁልጊዜው በመተማ ትግርኛ የሚናገር ሰው መስማት ብርቅ ሆኖ ውሏል፤
2. በየዳ ኢየሱስ ዐማሮች ዛሬም ከወያኔዎች ነጻ ቀጠና ይዘው ውለዋል፤
3. የሕወሓት ልዩ ኮማንዶ ቡድን ማክሰኝት (ከጎንደር 40 ኪሜ) ላይ መሸጓል፤ ከፍተኛ የታጠቀ ኃይል ይመጣበታል የሚባለው የአርማጭሆ በር ከብልኮ እስከ ሸንበቂት ድረስ ለቆረጣ ውጊያ በሚመች መልኩ አልፎ አልፎ ብዙ ወታደሮች ጉድብ (ጥግ) ይዘው መሽገዋል። ድርቡሽ የገባ አስመስለውታል፤
4. አጠቃላይ የጎንደር ዐማሮች ከኢንተርኔት አገልግሎች ውጭ ሆነዋል፤ ከተለያዩ የዐማራ አካባቢዎች ለወገኖቻቻው የሚዘምቱ ሰዎች ቀጥር ጨምሮ ውሏል፤
የዐማራ ሕዝብ ትግል ያሸንፋል!!