Tuesday, September 13, 2016

20 የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው ከሕዝብ ጋር ተቀላቀሉ



ከአዲስ አበባ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ቦሌ አየር መንገድ ሕገ ወጥ የእጽ ዝውውር ላይ አንድ ሻለቃ ውስጥ ይሠሩ የነበሩ ሃያ የዐማራ ተወላጅ የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ክደው ባለፈው ሳምንት ከሕዝብ ጋር መቀላቀላቸው ታውቋል፡፡ የፌደራል ፖሊስ አባላቱን ለዚህ ውሳኔ ያበቃቸው በሕዝባቸው ላይ እየደረሰ ያለው መቆሚያ ያጣ ፍጅት ነው ተብሏል፡፡

በፌደራል ፖሊስና በመከላከያ ሠራዊት የዐማራ ተወላጆች ተለይተው መሣሪያ እንዳይዙ እንዲደረግ ሀሳብ የቀረበ ቢሆንም ስምምነት ባለመኖሩ እስካሁን ተግባራዊ አልተደረገም፡፡ ሆኖም የዐማራ ተወላጆችን መሣሪያ ከሰጡ በኋላ ልዩ ክትትል እንደሚደረግባቸው የዐማራ ተወላጅ የሆኑ የፌደራል ፖሊስ አባላት ገልጸዋል፡፡ በተያያዘ ዜና ደግሞ የአዋሽ አካባቢ የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ሌሎች ሁለት የፌደራል ፖሊስ አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው አገዛዙን ከድተው መሄዳቸው ታውቋል፡፡


No comments:

Post a Comment