Friday, September 16, 2016

የሁላችንም አባት ናቸው – #ግርማ_ካሳ


14344129_305466253143839_7518640932821591610_n






ሻለቃ ይላቅ አቸነፍን ይባሉ ነበር። የአርማጭሆ ሰው ነበሩ። በአካባቢያቸው በጣም የተከበሩና የተወደዱ። በወልቃይት ጉዳይ፣ በሚሊዮን እንደሚቆጠረው የጎንደር ነዋሪ አቋማቸዉን ገለጹ። ሰላማዊ በሆነ መንገድ ።
ሆኖም ሕወሃቶች እኝህን የተከበሩ አባት “ወጣቶችን አንተ ነህ የምትቀሰቅሰው” በሚል አፍነው ወሰዷቸው። እንደ ወንበዴ። የፍርድ ቤት ማዘዣ ሳይዙ፣ የክልሉ መንግስት ሳያውቅ።
በጎንደር ስንት እሥር ቤት እያለ፣ ወያኔዎች እኝህን ሰው ወደ ቂሊንጦ ፣ ኪሎሜትሮች አቆራርጠው ነው ወስደዋቸው የነበሩት።በዚያም ቶርቸር ያደርጓቸውም ጀመር።
ብዙዎች፣ ራሳቸው ወያኔዎች የለኮሱት ነው ይላሉ። በቂሊንጦ እጅግ በጣም ሃይለኛ እሳት ይነሳል። ቁጥራቸው እጅግ በጣም በርካታ የሆኑ ዜጎች በእሳት ተለብልበው፣ የተወሰኑቱም በጥይት ተመተው ሕይወታቸው ያልፋል። ሕወሃቶች የሰሩት ወንጀል እንዳይታወቅባቸው ሁሉንም ነገር ከሕዝብ ደበቁ።
በቂሊንጦ በግፍና በጭካኔ በ እሳት ተለብልበው እንዲሞቱ ከተደረጉት ወገኖች መካከል አንዱ የአርማጭሆ አባት ሻለቃ ይሳቅ ነበሩ።
በሰላም ከሚኖሩበት አገር ፣ ወሮበሎች አፈነው ወስደዋቸው፣ አሰቃይተዋቸው፣ በእሳት አቃጥለዉና ለብለበዋቸው፣ አስክሬናቸውን መልሰው ወደ አርማጭሆ ላኩ። ሕወሃቶች የሄዱበት ቦታ በሙሉ ረብሻ፣ ደም መፋሰስ፣ ለቅሶና ሰቆቃ ነው የሚሆነው። ሻለቃ ይሳቅ ወያኔዎች ላይ አልደረሰቡባቸውም ነበር። በሰላም ኑሯቸውን ነበር የሚኖሩት። ወያኔዎች ግን አዎን ገደሏቸው፣ አስገደሏቸው።
እነርሱ ምን አለባቸው ? የሚሞቱት የነርሱ ጓደኞችና ዘመዶች አይደሉም ? የሚታሰሩት የነርሱ ልጆች አይደሉም። ሌላው ድሃ ኢትዮጵያዊ ቢሞት፣ ቢያለቅስ፣ ቢፈናቀል፣ ቢሰደድ ምንም አይመስላቸዋል። አዲስ አበባ ከሕዝብ ተለይተው የሚኖሮባቾች ሰፈሮች፣ ዊስኪ የሚራጩባቸው ቡና ቤቶች ደህን ይሁኑ እንጅ፣ ጎንደር ተቃጠለ፣ ኮንሶ ወደመ፣ ነቀምቴ ተደረመ ..ለነርሱ ምናቸውም አይደለም። የሌላው ኢትዮጵያዊ ሕይወት ለአረመኔዎቹ ወያኔዎች ካርታ እንደመቁጠር ነው።
አቶ ኢሳቅ ለነ ስብሃት ነጋ “ምንም” ቢሆኑም፣ ለአርማጭሆ ህዝብ፣ ለጎንደር ህዝብ ግን፣ ዴሞክራሲና ነጻነት ለተጠማው ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አባት ናቸው። ለመብት፣ ለነጻነት፣ ለፍትህ ሲሉ፣ አገራቸዉን እና ህዝባቸዉን በመዉደዳቸው የተሰው።
የአባታችን ሻለቃ ይላቅ አቸነፍን ነፍስ እግዚአብሄር ይማርልን !



No comments:

Post a Comment