Sunday, September 25, 2016

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በስብሰባ ወቅት ምሁራኑን ሳቅ በሳቅ ያደረገና እንባ በእንባ ያራጩ ጥቂት ነገሮች



ሳቅ እና ለቅሶ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ
በስብሰባ ወቅት ምሁራኑን ሳቅ በሳቅ ያደረገና እንባ በእንባ ያራጩ ጥቂት ነገሮች እኒህ ነበሩ።
1 – አንዲት ሴት መምህርት ነች እጇን አወጣች እድሉን ስታገኝ “አሁን ወደ ስልጠናው ልገባ ስል ባለቤቴ ደውሎልኝ ነበር ‘ አደራሽን እናገራለሁ እንዳትይ እኔና ልጃችንን አስቢ አለኝ”….ሳቅ.. .በሳቅ…”ይሄዋ እርግጠኛ ነኝ ብዙዎቻችሁ እንደኔ ተብላችኋል”…ሌላ ሳቅ.. ይህኔ ክቡር ሰብሳቢው አቋርጠው “እረ ይሄ ፍርሃት ተደጋገመ ምንጬ ምን እንደሆን አልገባኝም? “ሴትዮዋ ተቀብላ” እንዴ አቶ ካሳ የምርዎን ነው? ምን እንደሚያስፈራን አያውቁም? ለነገሩ ህዝቡን አታውቁትም! ምን እንደሚያስደስተው እና እንደሚያስፈራው አታውቁም። ረጅም ጭብጨባ…!

2 – ሰብሳቢ ለተነሱት ጥያቄዎች ሲመልሱ ነገር ሲያረዝሙ ጊዜ መምህራኑ በጭብጨባ አቋረጡ ይህኔ “ባካችሁ 1 ደቂቃ ብቻ” አሁንም በጭብጨባ ተቋረጠ ሲጨንቃቸው ምን ቢሉ ጥሩ ነው? “እሽ በቃ የአይጥ መንገድ ብቻ ስጡኝና ልውጣ! “በልመና በአይጥ መንገድ ወጡ።

3 – ተናጋሪው የኩላሊት ህክምና ስፔሻሊስት ነው “እኔ ሀኪም እንጅ ፖለቲከኛ አይደለሁም። ግን አሁን አቶ ካሳ ሲናገሩ ‘እናየዋለን፣እናጠናዋለን ‘ብለዋል። የዛሬ 14 ዓመትም ነፍሳቸውን ይማርና የቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር አቶ መለስ እኔ ራሴ በተገኘሁበት ስብሰባ ላይ እንዲሁ ብሎ ነበር እና ዛሬም ከ14 ዓመት በኋላ እንደገና እናየዋለን፤ እንደገና እናጠናዋለን?” ስብሰባ ማዕከሉ በሳቅ ተወዛወዘ።

4 – ሰብሳቢው አቶ ካሳ ናቸው። ለተነሱት በርካታ ጥያቄዎች ሲመልሱ…ሰው ሲታገስ… ሲመልሱ..ሰው…ሲታገስ.መካከል ላይ ቦሌ አካባቢ ፎቆቹና ቪላዎቹ በአንድ ብሄር ጋንግስተሮች ተወሯል። ለሚለው ጥያቄ መልሱን ሲያብራሩ ..”ይሄን ነገር በደንብ ልንመረምረው ይገባል ፤ Rlly እንደተባለው ባንድ ብሄር ነው የሚለውን ልንፈትሸውና ልናጠናው…..” ..የሙህራኑ ሳቅ….እንጦጦ ድረስ ጮኸ።

5 – በጣም ወጣት ልጅ ነው እድሉን ሲያገኝ “ሌላ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ጓደኞቼ በመናገራቸው ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው አውቃለሁ። ዝም ማለት ስላስላስቻለኝ እኔ ግን እናገራለሁ። ተናግሬ እንግዲህ የመጣውን ያው…..(ሰው በሳቅ)…እሽ ! ሰልፍ ይቻላል ተብሏል አዎ ለድጋፍ ሲሆን መኪና ተመድቦ፣ ክላሽ ተይዞ በፌዴራል ታጅቦ ይደረጋል። ችግሩ ህዝቡ ለመብቱ መሰለፍ ሲፈልግ ግን……” ምስኪን ይሄው ጥያቄው ማታ በኢቢሲ ተለቀቀለታ። እግዚኦ ነው ለቤተሰቡ
በመጨረሻም በቡድን ውይይት ወቅት(ስለ ትምህርት ጥራት ነበር ርዕሱ) አንድ ነፍሰ ጡር ሴት ተነስታ በሲቃ “ዛሬ ህዝብ እየሞተ የምን የትምህርት ጥራት ነው? ሁሉም የሚኖረው አገር ሰላም ሲሆን ነው። እኔ ለምሳሌ በዚህ ተቃውሞ ቤተሰቤን አጥቻለሁ (ሳግ እየተናነቃት) ዛሬ የስድስት ልጆች እናት የምትገደልበት፣ ልጇን ገድለው እላዩ ላይ ተቀመጭ የሚባልበት ጊዜ ላይ ተገኘን። ምነው ይሄ ታሪክ የሌላ በሆነልን፤ ምነው በሃገሬ ባይሆን ብየ ተመኘሁ ግን ሆኗል (ረጅም የሳግ ድምጽ) ሁሉም አንገቱን ደፋ፣ ግማሾቹ ዓይናቸውን በሶፍት ይጠርጉም ነበር።
ከዚህ በኋላ ነው የምሩ ሳታየር የተመለሰው መምህራኑ ስለ ሌላ አናወራም አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ብቻ ነው በማለት።

፩ኛ – ጠ/ሚኒስትሩ ያወጁትን አዋጅ ባስቸኳይ ይመልሱ፤ ወታደሩም ወደ ቦታው ይመለስ!

፪ኛ – በየቦታው የሚፈጸሙት እስራት ፣ ቶርቸር እና አፈና ባስቸኳይ ይቁም!

፫ኛ – ለሁሉም መፍትሔው የስርዓት ለውጥ ነውና የስርዓት ለውጥ እንፈልጋለን። ይሄን ብቻ በዋናው መድረክ እንድታሰሙልን እንፈልጋለን።

ዋናው መድረክ ላይ ከሰዓት ሲቀርብ አወያይ ሆየ “በኛ ግሩፕ ከተነሱት የትምህርት ጥራት ችግሮች አንዱ ……..(divert እንዲህ ነዋ!)
 ኢዮብ ብርሃነ

No comments:

Post a Comment