Thursday, September 15, 2016

አንድ ነገር ይገርመኛል – ኢህአዴግ ዘንድ ቀላል እና ከባድ ነገር እንኳን የሚለይ ሰው መጥፋቱ!



By Meski Ab Fits : የኮንሶ ህዝብ ጥያቄ በጣም ቀላል ነው :: እነዚህ ወገኖች የጠየቁት ‘ጉዳያችንን ለማስፈፀም የዞን ከተማ ፍለጋ እንደ ማጅላን ከምንዞር በአቅራቢያችን ማዕከሉን ያደረገ የዞን መዋቅር ኖሮን ፖለቲካዊ ጉዳያችንን በቅርብ እያስጨረስን እንኑር’ ነበር ። ገታራው መንግስት በዚህ መስማማቱን በጄ ስላላለ ደግሞ ‘እሽ የልዩ ወረዳ መዋቅራችንን እንኳን ይዘን እንቀጥል’ ሲሉ ለድርድር የተመቸ ሃሳብ ይዘው መጡ :: ይህም አይሆንም ባይ ነው ጀግናው ኢህአዴግ ! ይህ ነው ከሃያ ዘለግ ያሉ ኮንሶዎች እንዲሞቱ በቂ ሰበብ የሆነው ::

አንድ ነገር ይገርመኛል – ኢህአዴግ ዘንድ ቀላል እና ከባድ ነገር እንኳን የሚለይ ሰው መጥፋቱ!
ከወልቃይት እና የአዲስ አበባ ዙሪያ (የኦሮሚያ ) ጥያቄ አንፃር የኮንሶ ጥያቄ እጅግ ቀላል ነው :: ለምን ቢባል የኮንሶ ጥያቄ የሚያደናቅፈው ነገስታት እና ቤተ ዘመዶቻቸው የገተሩት ፎቅ የለም ፤ በኮንሶ “ዲሞቢላይዝድ” የሆነ ወታደር የሚንፈላሰስበት “ፕላንቴሽን” የለም ፣ በኮንሶ በደባልነት ገብቶ ባለቤት ሊያስወጣ የሚያምረው የመንግስት ቤተዘመድ ብዙ የለም ::
ነገሩን በአንፃራዊነት ለማሳየት እንጅ የእነ አጅሬ እግር ያልረገጠው ለምለም መሬት የለምና በኮንሶ የሉም ለማለት እንዳልሆነ ይሰመርበት ::  ኢህአዴግ ለቤተ ዘመዶቹ እግራቸው የረገጠውን ሁሉ የሚያወርስ የዘመድ አዝማድ መንግስት መሆኑ ሳይረሳ ኮንሶዎች የጠየቁት ጥያቄ ቢያንስ ዛሬ ለቤተዘመዳዊው መንግስት የቅርምት ስስ ብልቱንየሚመታ አይደለም:: በቅርምት ቀልድ ለማያውቁ ገዥዎችም የኮንሶ ጥያቄ እንደ ኦሮምያና ወልቃይት እጅግም አስበርጋጊ አይደለም ::
ኮንሶዎች የጠየቁት ለስልጤ ህዝብ ከተደረገው ቢያንስ እንጅ አይበዛም ፤ ለቅማንት እና ለአርጎባ ህዝብ ከተደረገው ልዩ ነገር ኮንሶ አላነሳም። ምን ቆርጧችሁ ትንፋሻችሁ ተሰማ ካልተባለ በቀር ! ‘ያለ አግባብ የትራንስፖርት አናውጣ ጉዳይ ይዘን የዞን ከተማ ፍለጋ አንንከራተት’ ማለት የአዲስ አበባውን ዙፋናችሁን አስረክቡን ማለት አይደለም ::እንደምንም አድርጌ ባስበው የኮንሶ ህዝብ ዞኑ ቢቀር የልዩ ወረዳ መዋቅር ይኑረን የሚል ጥያቄ የሚያስገድል ሆኖ አልታይሽ አለኝ :: ነገሩ የኢህአዴግ መንግስት ከአረጁ አይበጁነት ያመጣው ካልሆነ ሌላ አይደለም ::

No comments:

Post a Comment