Wednesday, September 28, 2016

የህወሃትን የ minority ቁማር ጫወታ ይጠንቀቁ!! ጀዋር መሀመድ

  


የህወሃትን የ minority  ቁማር ጫወታ ይጠንቀቁ!! ጀዋር መሀመድ
*********
በቅርቡ ብዙዎቻቹ እንደተመለከታቹት፣ ህወሃት ሶማሊዎች ኦነግን ወይም ግንቦት ሰባትን በመቃወም ወጡ የሚል ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ነው። መታወቅ ያለበት እውነት እንዲህ ዓይነቱን የህወሃት ድራማ እየተጫወቱ ያሉት ክልሉን አስተዳድራለው የሚለው አሻንጉሊት ፓርቲ አባላት ብቻም ሳይሆኑ፣ ከጅቡቲ፣ ከሶማሊያ፣ ከሶማሊ ላንድ እንዲሁም ከኬኒያ የመጡ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች መሆናቸውን ነው። እብደት፣ እንዝላልነትና ስርዓት አልበኝነት የተጠናወተው የክልሉ የህወሃት ቅጥረኛ ፕሬዚደንት አብሲ ኢሌ፣ የቡና ቤት ሰራተኞች ሳይቀር በማስገደድ ሰልፍ አስወጥቷል ዛሬ። የህወሃት መንግስት ይሄን ለምን አደረገ? በመጀመሪያ ይሄ የሚያሳየው ህወሃት በኦሮሚያና በኣማራ ክልሎች ባበጃቸው ታዛዥና አሻንጉሊት የነበሩ ፓርቲዎችም ጭምር ሳይቀር መተፋቱንና ተስፋ መቁረጡን ነው። በነዚህ ሁለት ትልልቅ ክልሎች (ኦሮሚያና አማራ) ስርዓቱ የድጋፍ ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠራም አንድም ወደ ተቃውሞ ይቀየራሉ በሚል ስጋት ሰርዟቸዋል ወይም ደግሞ ማንም ሰው ባለመገኘቱ የድጋፍ ሰልፎቹ ከሽፈዋል።
ጉዳዩ ግን ከዚህም በላይ ክፉ (sinister) እሳቤ ያለበት ነው። ጉዳዩ ህወሃቶች የሞት ሽረት ትግል (existential fight) የሚያደርጉበት የኣናሳዎች ፖለቲካዊ ቁማር ጫወታ አካል ነው። የዚህ ዓይነቱን ቆሻሻ ቁማር ካርድ ከሁለት ሳምንታት በፊት ስዩም መስፍንና አባይ ጸሃዬ በሰጡት ቃለ ምልልስ ላይ መዘውት ነበር። ይሄን ለማድረግ ሁለት ተልዕኮ ነበራቸው፥
የመጀመሪያው፣ ካለምዓቀፉ ዳተኛ ማህበረሰብ (liberal international community) ‘ትግሬዎች ላይ በሁለቱ ትልልቅ የኢትዮጵያ ብሄረሰቦች (ኦሮሞና አማራ) አጋርነት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው’ በሚል የድረሱልን ጥሪ ለማስተላለፍ ነው የተፈለገው። ወያኔዎች ላለምዓቀፍ ዲፕሎማቶች ‘ትግሬ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የሃገሪቱ አናሳ ቡድኖችም ጭምር ለጥቃት እየጠጋለጡ ነው’ በሚል ከፍተኛ አቤቶታና ውትወታ እያቀረቡ እንደሆነ ማወቅ ተችሏል።
ሁለተኛው ምክኒያት ግን ህወሃት ከትግሉ ዘመንም አንስቶ ሲሰራበት የነበረውና የኦሮሞንና የኣማራን የተባበረ ጫና (concerted impact) ለመቋቋም ሌሎች የሃገሪቱን አናሳ ቡድኖች አደርጅቶና ዶሚኔት አድርጎ ማንቀሳቀስ የሚለው ሸፍጠኛ ፖሊሲው ነው። ይሄ ከትግሉ ዘመን ጀምሮ ሲያራምዱት የነበረ ስትራቴጂ ነው። ትግራይን ከቤኒሻንጉልና በምዕራብ ታች ጋምቤላ ድረስ ወርዶ እንዲሁም በምስራቅ በኩል በኣፋርና ሶማሌ ላይ የሚያገናኘው ካርታ ተራ ስ ህተት ሳይሆነ ካ1970ቹ ጀምሮ ታቅዶ የተሰራበት ፕሮጀክት ነው። በትግራይ ልህቃን የኢኮኖሚ ስግብግብነት የተነሳ ባይሳካላቸውም፣ በከተሞች ውስጥ የሚኖሩ የተለያዩ አናሳ ቡድኖችንም ከጎናቸው ለማሰለፍ ጥረው ነበር ህወሃቶች።
በእርግጥ ግን ህወሃት በኢትዮጵያ የአናሳ ቡድኖች አጋር ነውን? ስራው የሚያሳየው ግን እንዳልሆነ ነው። ምሳሌዎችን እንጥቀስ፥
-የህወሃት ሰራዊት በሶማሊ ክልል ዘር ማጥፋትን ጨምሮ ዘግናኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ፈጽሟል። ይሄንን አሰቃቂ ወንጀል ደግሞ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በሰፊው የዘገቡት ሲሆን ያሁኑ የክልሉ ፕሬዚደንት አብዲ ኢሌ በቅጥረኛ ነፍሰገዳይነት እንደተባበረ እልፍ አእላፍ መረጃዎች አሉ።
-በ2003 በጋምቤላ ክልል በኣኙዋኮች ላይ የዘር ማጥፋት ጭፍጨፋ ያካሄደ ሲሆን፣ ይሄንኑ ዓይነት ጭፍጨፋ እስካሁንም ቀጥሎበታል።
-በ2002 ሎቄ ላይ ለሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ሲዳማዎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ አካሂዷል።
-አሁን በዚህ ወቅት እንኳን የኮንሶ ህዝብ ራስን በራስ ለማስተዳደር ስለጠየቀ ብቻ መንደሮቹን በእሳት እያጋየ ነው የህወሃት ሰራዊት።
-ሙርሲዎችን በገፍ ገድሏል፣ የተቀሩትን ደግሞ እንደ ጥንት ዘመን ባሮች አጠላልፎ በማሰር የሰው ልጅ በዚህ ዘመን ሊያየው በማይገባ ሁናቴ አስሮ እያሰቃያቸው ነው።
-የስልጤና ጉራጌ ነጋዴዎችን ከንግድ ስርዓቱ በማስወጣት በትግሬዎች ተክቷል።
-የኣፋርን መሬት ትግሬዎች መቀራመት ብቻም ሳይሆን ሲፈልጉም የሱማሌ ኢሳዎችና ሌሎች እንዲቀራመቱት አድርገዋል።
-ወዘተርፈ……
በምቀጥሉት ሳምንታትና ወራት የኦሮሞና የኣማራ አክቲቪስቶችና የነጻነት ቀንዲሎች የተባበረ ክንዶቻቸውን ማሰረፍ ሲቀጥሉ፣ ህወሃት የኣናሳዎችን ቁማር ካርድ ይበልጥ እንደምትመዝ ይጠበቃል። የዚህ ዓይነቱ አስነዋሪ ቁማር ደግሞ በኢትዮጵያ ባሉት ሌሎች አናሳ በሄረሰቦች እንዲሁም በኦሮሞና በኣማራ መካከል ቅራኔና ቁርሾ ለመፍጠር ያለም ነው የሚሆነው። በዚሁ መሰረት ወያኔ ከዚህ ቀጥሎ የተጠቀሱትን እኩይ ተግባራት ለመፈጸም ይችላልና እንንጠቀቅ፥
-በዳያስፖራም ሆነ በተወሰኑ ያገር ውስጥ አካባቢዎች ተመሳሳይ የሆኑ ኦሮሞንና አማራን ለማናደድ (offend) ያለሙ ሰልፎችን ሊያዘጋጅ ይችላል፤
-ተንኳሽና ቆስቋሽ ቃላትን በመጠቀም ፕሮፓጋንዳ የመንዛት ዘመቻው ሊጧጧፍ ይችላል፤
-በሶማሊዎችና በኣማራ እንዲሁም በኦሮሞ መካከል ግጭት ለመፍጠር፣ ግለሰባዊ ትንኮሳዎች እንዲሁም በተቋማት ላይ ሊደረግ የሚችል ጥቃት ሊኖር ይችላል፤
-በክልሎች የድንበር አካባቢዎች መፍጠር የጀመሩትን ግጭት ይቀጥላሉበታል። በኣማራና በቤኒሻንጉል እንዲሁም በኦሮሚያና በሶማሊ ክልሎች መካከል ህወሃት በቅርቡ የፈጠረችውን ግጭት ይበልጥ እንዲባባስ ልታደገው ትችላለች፤
እነዚ የህወሃት ሸፍጦች እንዲከሽፉ ተባብረን ካልሰራን፣ ኢትዮፕጵያ ውስጥ በሚገኙ ብሄሮች መካከል የማይሽር ጠባሳ ሊያሳርፉ ይችላሉ። ስለሆነም ይሄን ለመመከት የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ይኖርብናል፥
-የኦሮሞና የኣማራ ተወላጆች በዚህ ዓይነቱ የህወሃት ወጥመድ ውስጥ ላለመውደቅ፣ ከሶማሊ ክልል ካድሬዎችና የኣብዲ ኢሌ ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች ጋር ውይይትም ሆነ ክርክር ወይም ማናቸውንም ዓይነት መሳፈጥ ማድረግ እንደማያስፈልግ መረዳት ያስፈልጋል፤
-ይሄንን ዓይነቱን ጉዳይ ለኣክቲቪስቶችና ለፖለቲካ መሪዎች ተውላቸው። እነሱ እንዳስፈላጊነቱ ያሳጧቸዋል (debunk)፤
-የስርዓቱ ቅጥረኞች እንደ ኦሮሞ፣ አማራ ወይም ሶማሊ በመምሰል ግጭት ለመጫር እንደሚተጉም ማስተዋል ያስፈልጋል።
-ወያኔ ነፍሰ ገዳይ ቅጥረኞችን ልታሰማራ ስለምትችል የታወቁ አክቲቪስቶች እንዲሁም የፖለቲካ መሪዎች በያሉበት መጠንቀቅ አለባቸው። በኦሮሞም ሆነ በኣማራ ኮሞኒቲዎች ውስጥ ያሉ የስርዓቱ ቅጥረኞች ሶማሊዎችን እንዲያጠቁና ግጭት እንዲፈጥሩ ሙከራዎች ሊደረጉ ይችላሉ። የኦሮምና የኣማራ ሰዎች ላይም ጥቃት ሊቃጣ ይቻላል። ምንም ሆነ ምን ግን ምላሹ የጋርዮሽ (communal) ሆኖ በሶማሊ ወይም በሌላው የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ላይ ያነጣጠረ መሆን አይገባውም። አካሄዳችን የዚህ ዓይነቱን የወንጀል ጥቃት የሚፈጽሙትን ግለሰቦች ነጥሎ በማውጣት ለህግና ፍትህ ማቅረብ መሆን ይኖርበታል።
የዚህ ዓይነቱ ያረጀና ያፈጀ የወያኔ ክፉ የከፋፍለህ ግዛ አባዜ የስርዓቱን እድሜ ሊያራዝመው አይችላም።

No comments:

Post a Comment