Saturday, September 17, 2016

የሕወሓት የበላይነት አብቅቶ የሕዝብ ልጆች የበላይነት የሚነግስበት ጊዜ ቀርቧል።



የሕወሓት የበላይነት አብቅቶ የሕዝብ ልጆች የበላይነት የሚነግስበት ጊዜ ቀርቧል።
Image may contain: text and one or more people
ሰሞኑን የወያኔ ባለስልጣናትና ጥገኞቻቸው ኣደባባይ ላይ ተሰይመው የባጥ የቆጡን እየዘላበዱ ነው።ማሃይማን ሚኒስቴሮች የሚሉት እስኪጠፋቸው ሕወሓት ሕወሓት እያሉ ቀፎ ከሆነ ኣንደበታቸው ነጠላ ዜማ ሊተፉ ይፈልጋሉ። የሕወሓት የበላይነት የለም ብሎ የሚያምን ኣሊያም በመደለል ራሱ ተሞኝቶ ሌላውን ለማሞኘት የሚዳዳው ኣንድም ኣእምሮው ልክ የማይሰራ ኣሊያም ሞራሉን ለሆዱ የደፈነ ሕሊና ቢስ ነው፤ ሕዝቦች በኣደባባይ ቆመው በመፈክር የሕወሓት የበላይነት ይቁም ብለው ያረጋገጡትን ለመካድ መሞከር እጅግ የወረደ ሰብእና ነው።
ደንብረው የጻፉት እስከመሰረዝ ለደለዙት ይቅርታ እስከማለት ደርሰዋል።በሕወሓት የበላይነት የተጻፉት እነ ራስዳሽን ተራራ ይሁኑ የረዘሙት ትግራይ ካርታዎች ሁሉ በይቅርታ እያነሱ መጥተዋል በሕዝብ ትግል ወልቃይትም ትቀጥላለች ሕወሓትን ማመን ግን ቀብሮ ነው፥ ሕወሓት እስካልወደመች ድረስ የሕዝቦች መብትና ነጻነት ኣይረጋገጥም።ሕወሓት ባለፉት 23 ኣመታት በበላይነት ስልጣኑን ተቆጣጥራ በከፍተኛ ደረጃ ሕዝብን ስትገድል ስታስር ስታስጨንቅ ስታሳዽድ ኖራለች የተለያዩ ቁልፍ የሆኑ ስልጣኖች በሕወሓት ሰዎች እጅ ተቀምጠው ሌላው ሕዝብ የበይ ተመልካች የደሃ ደሃ የለጋሾች እርዳታ ጠባቂ እንዲሆን ተደርጎ የሕወሓት ኣመራሮች ከነቤተሰቦቻቸው ከነካድሬዎቻቸው ሃገሪቷን ዘርፈው ሕዝቡንም ኣጉላልተው እርቃን ኣድርገውታል። ሕወሓቶች በተለያዩ መንገዶች ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ የኢኮኖሚ ኢምፓየር ገንብተው የፖለቲካ የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ ሌትተቀን ሲሰሩ ዛሬ ላይ ደርሰዋል።ይህንን በት ዝብት ሲመለከት የነበረ ሕዝብ እያወቀ እንዳላወቄ እያየ እንዳላየ ሲሆን ሕወሓቶች ግን የሕዝቡን ዝምታ እንደጅልነት ቆጥረው ዘረፋቸውን ሲያካሂዱ ሕዝቡ ድንገት ተነስቶ የሕወሓት የበላይነት ይብቃ በማለት ትግሉን ኣቀጣጥሎታል።
ውሸት ሲበዛ እውነት ይሆናል የሚለውን ብሂል ይዞ ስልጣኑን ለማስረዘም በግፍ ስራ ላይ የተሰማራው ሕወሓት ወደ ደህንነት ቢሮ ሲሄዱ የሚመለከቱት በኣንድ ቋንቋ ተናጋሪ ተወጥሮ የተሰራ የሕወሓት የደህንነት ተቋም እንጂ ኢትዮጵያዊ ተቋም የለም።እስከ ሶስተኛው እርከን የደህንነት ቢሮ በተዋረድ በሕወሓት ሰዎች ቢቻ የተሞላው የደህንነት ተቋም የማፊያ ቡድኖች ቅንጅት እንጂ ለኣንድ ሃገር ሕዝብ የቆመ የደህንነት ድርጅት በፍጹም ኣልመሆኑ በተግባር የታየ ጉዳይ ነው፤ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲሄዱ በየውጭ ኣገራት በሚገኙ ኢትዮጵያን ይወክላሉ በተባሉ ኤምባሲዎች ውስጥ የሕወሓት ካድሬዎች በበላይነት ተቆጣጥረውት ከተወሰኑ የፓርቲ ኣባላት እና ደጋፊዎች ውጪ ማንም ኢትዮጵያዊ በየኤምባሲው ለማስተናገድ ፍላጎት የለም፤ ኣምባሳደሩን የሌላ ብሄር ተወላጅ በማድረግ ለናሙና የሚያስቀምጠው ሕወሓት በተዋረድ እስከ ኤምባሲ ዘበኛ ድረስ በኣንድ ቋንቋ ተጠቃሚ የሆኑ የሕወሓት ሰዎችን በማስቀመጥ ኣለማቀፍ ኣገልግሎት ይሰጣሉ የተባሉ ኤምባሲዎችን የፓርቲ ኣባላት መፈንጫ ከዲፕሎማት ስራ ይልቅ ሕገወጥ ስራዎች ማከናዎኛ በማድረግ ኣገራዊነትን ኣዳክሟል፤የህዝብን ሃብትና ንበርት ለሕወሓት የበላይነት ተጠቅሞበታል፤በወታደሩም ክፍል በኣየር መንገዱም በከተማ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በውጪ ነጻ የትምህርት እድል ወዘተ በከፍተኘ ደረጃ የሕወሓት የበላይነት በግልጽ ይታያል።
የሕወሓት የበላይነት የለም ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ዽብና ኣይናጩ ስራ የምታዩትን ነገር እንስክዳቹ እናሞኛቹ መሆኑን ሊረዱት ይገባል ሕዝቡ ነቅቷል ኣሉ ከሚባሉ ፖለኢከኞች እጥፍ እጥፍ ቀድሞ ሄዷል።ይህን ሕዝብ ማታላል ኣይቻልም ድፍን ኣዲስ ኣበባ ባለሕንጻና ኮንትሮባንድ ነጋዴ የሆኔው የሕወሓት ኣባላቶች ናቸው በኢኮኖሚ ኢምፓየርነት ካለግብር ካለቀረጥ ካለ ምንግስታዊ ክፍያዎች እየተንቀሳቀሱ የሚገኙት የሕወሓት ድርጅቶችና በትግራይ ሕዝብ ስም የሚነገድባቸው እንደ ኢፈርት ያሉ የፓርቲ የንግድ ተቋማት ናቸው፤ ሃገሪቷን ኦና ያስቀሩት ቅጥረኞቻቸውን ከፊት ለፊት ኣስቀድመው በፖለቲካው በኢኮኖሚው እያቦኩ ያሉት ሕወሓቶች ናቸው።ሕዝቡ ይህን ስላወቀ ድምጹን ማሰማት ጀምሯል።ሕዝቡ ይህን ስላወቀ ሕወሓት ከስልጣን እንዲወገድ ትግሉን ቀጥሏል።ሕዝቡ በቃጩን ብሎ ውረዱልን እያለ ነው።ወያነና ቅጥረኞቹ በወያኔ ሚዲያዎች የሚመጡ ሁሉ ውሸታሞች መሆናቸውን ሕዝቡ ሁሉ ኣውቋል ሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ፈርተው የበሉት እያነቃቸው እንጂ የኢሕ ኣዴግ ካድሬዎችም ነቅተዋል። የሕወሓት የበላይነት አብቅቶ የሕዝብ ልጆች የበላይነት የሚነግስበት ጊዜ ቀርቧል። ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment