Wednesday, November 30, 2016

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ መታሰራቸው ታወቀ

  


merera-1
ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፕሬዚደንት ዶ/ር መረራ ጉዲና
የአይን ምስክሮች እንደገለጹት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቁጥጥር ስር የዋሉት በምን እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን ዶር መረራ እንዲታሰሩ ሰሞኑን በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ ታውቋል። በአውሮፓ ህብረት ግብዣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከአትሌት ፈይሳ ለሊሳ ጋር ብራሰልስ የተገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጥሰዋል የሚል ቅስቀሳ ሲደረግባቸው ቆይቷል። ለዚህም ይቀርብ የነበረው ምክንያት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአንድ መድረክ መገናኘታቸውና ጎን ለጎን መቀመጣቸው መሆኑን መረዳት ተችሏል። ዶ/ር መረራ ጉዲና አውሮፓ የተጋበዙትም በአንድ መድረክ የተገኙትም በአውሮፓ ፓርላማ ግብዣ ሆኖ ሳለ፣ በጉዳዩ ተጠያቂ መደረጋቸውና በዚህም መወንጀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ዶ/ር መረራ ጉዲናን የያዟቸው ወገኖች ወዴት እንደወሰዷቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት ምስክርነት መንግስትን አለማስደሰቱን ለማወቅ ተችሏል። ምንጭ፦ ኢሳት

ፌዴራል ፖሊሶች በየቦታው በገፍ እየታሰሩ ነው።ቆንጅት ስጦታው



~ከኮማንድ ፖስቱ በኋላ ፌዴራል ፖሊሶች በየቦታው በገፍ እየታሰሩ ነው። በተለይ በህዝባዊ አመጹ ጊዜ ያልተኮሱ-ለመተኮስ አስበው መሳሪያቸው እምቢ ያላቸው ሁሉ፣ ፌስቡክ ላይ ጸረ ወያኔ ጽሁፎችን ሸር እና ላይክ አድርገዋል የተባሉት ሁሉ ወደ ወህኒ ወርደዋል።
~ ባሁኑ ሰዓት የትም ለመሄድ ፈቃድ ተከልክሏል። ሌላው ቢቀር ከካም ውጭ ካደሩ ከአሸባሪዎች ጋር ስትመክር ነው ያደርከው ተብሎ ወህኒ እየተወረወረ ነው።
~ከኮማንድ ፖስቱ በኋላ በአዲስ አበባ በየጊዜው ሲደረግ የነበረው የፖሊሶች ስብሰባ ቀንሷል።ምክንያቱ ደግሞ ከ50% በላይ ፌዴራል ፖሊሶች ከአዲስ አበባ ስለወጡ ነው።
~ዛሬ ቦሌ ኤርፖርት ዙሪያ ለየት ያለ ጥበቃ ነበር።



የሎጂስቲክስ ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወደ ኦሮሚያ ክልል ተዛወሩ EthiopianReporter.com



የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ኢንተርፕራይዝ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አህመድ ቱሳ፣ የኦሮሚያ ክልል ገቢዎች ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሾሙ፡፡
በኦሮሚያ ክልል አዲሱ ፕሬዚዳንት አቶ ለማ መገርሳ ፊርማ ሰኞ ኅዳር 19 ቀን 2009 ዓ.ም. በወጣ ደብዳቤ፣ አቶ አህመድ ቱሳ ለአምስት

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሦስት ዘርፎችን በማደራጀት ሹመት ሰጡEthiopianReporter.com

    


– አቶ ሱፊያን አህመድ – የማክሮ ኢኮኖሚ ዘርፍ አስተባባሪ
– ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ – የኢንዲስትሪ ዘርፍ አስተባባሪ
– አቶ ሙክታር ከድር – የመልካም አስተዳደር ዘርፍ አስተባባሪ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጽሕፈት ቤታቸውን በማደራጀት አዳዲስ ሹመቶችን መስጠታቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገለጹ፡፡

Tuesday, November 29, 2016

የደፈረሰው ፖለቲካችን የወያኔና የተቃዋሚዎች ስርስር የግብጽና ኤርትራ የኮማንድ ፖስት ምስረታ እቅድ በጆሮ የሰማናቸው ናቸው::Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)



የደፈረሰው ፖለቲካችን የወያኔና የተቃዋሚዎች ስርስር የግብጽና ኤርትራ የኮማንድ ፖስት ምስረታ እቅድ በጆሮ የሰማናቸው ናቸው::
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ተልባ በጥባጯ እያለች ጎበን በጣሿ ምች የተመታችበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኣሁንም ምኑንም ሳይመልስ ምናምኑን እንዳግበሰበሰ ቀጥሏል። ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እንዲፈቱም ግፊቱ ቀጥሏል።የሚገርመው እያሰረ እየገደለ እያፈነ እያሳደደ ያለው አካል ከተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር ስለ ሰብዓዊ መብት ለመነጋገር ሶስት ቀን ስብሰባ የሚቀመጥበት ግርግር ምን ያህል በሕዝብ ላይ እየተቀለደ እንዳለ እያየን ሲሆን ኮማንድ ፖስቱ እየሰራ ያለው ግፍ እና በሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን አደጋ ለመደገፍ ካልሆነ በቀር በፍጹ ስለ ሰብዓዊ መብት የሚቆረቆር ይገኛል ማለት ሞኝነት የተቃዋሚ ፓርቲዎችም ስልጣን ኣካፍሉን ለማለት ካልሆነ በቀ ስብሰባው ከጭብጨባ የሚዘር ፋይዳ ኣይሰራም ወያኔ ተቃዋሚዎችን ተርታ የምጸበስበው አንድም ለማዘናጋት ኣሊያም አዲስ የፖለቲካ ፍጆታና ሴራ ከማለም የዘለለ ስራ የለውም። የሚገርመው ግብጽና ኤርትራ በካይሮ አሸባሪነትን የሚቆጣጠር በቀይ ባህርና ለምስራቅ ኣፍሪካ የሚያገለግል ኮማንድ ፖስት ሊመሰርቱ ነው።ይህ ኮማንድ ፖስታችው እኮ ስንቱን አስቀና ሆሆሆ…ወያኔ ጠላቶቼ የሚላቸው ሁለት ሃገራት እንኳን እንዲህ ብለው ይቅርና እንዲሁም በነጻ ወንጀል ለማሸከም ኣይቦዝንም ቢሆንም ከጀርባ ያለውንም የፖለቲካ መነባነብ ሰከን ብሎ ማዳመጥ ይበጃል ወዳጆቼ። በአንድ ጉዳይ የፈዘዘ ደንዝዞ ይቀራል። ነቃ እንበል !! እንብሰል !! አንዘናጋ !! ይህን ስል ደግሞ ወዲ ሳልሳዊ ሻእቢያና ወያኔ የተጠና ፖለቲካ ያሴራሉ ብሏል ብለህ መርዝ ምላስህን ዘርጋው አሉ:: #ምንሊክሳልሳዊ

የአማራ ህዝብ የተጋረጡበት አደጋዎች ባለ ፈርጀ ብዙ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ – ኄኖክ የሺጥ



የአማራ ህዝብ የተጋረጡበት አደጋዎች ባለ ፈርጀ ብዙ ናቸው ። ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹ
1) የአማራ ህዝብን በአንድነት ለማደራጀት እና በህብረት እንዲቆም እየተደረገ ላለው ጥረት ከዚህ በፊት አማራ አይደለንም ሲሉ ያልተሰሙትን የአማራ ህዝብ ክፋይ የሆኑትን አካሎች ፥ እንደ አገው እና ቅማንት ያሉ ማህበረሰቦችን ( ህዝብ ባልወከላቸው ተወካዮቻቸው አማካኝነት ) አማራ አይደለንም የሚል ወያኔያዊ አጀንዳ እንዲያነሱ በማድረግ እና የአማራ ህዝብ ህብረት የነርሱ ህልውና ላይ አደጋ ሊጥል የሚችል ጠንቅ እንደሆነ በመስበክ አማራውን እንደ ቁጠባ ቤት በተርታ በመከፋፈል በአንድነት እንዳይቆም የማድረግ ስራ እና ሴራ
2) አማራን በአረንጓዴ ፥ ቢጫ እና ቀይ ሰንደቅ አላማችን እያታለሉ ፥ አማራ የሚያምርበት ኢትዮጵያዊነት ነው በማለት ፥ በኢትዮጵያዊነቱ የማይታማውን የአማራ ህዝብ ፥ ለተራ የፖለቲካ ጥቅም ሲባል ብቻ ፥ የአማራ ህዝብ ስቃይ በገሃድ እየታየ « ኢትዮጵያዊነትህን እንዳትለቅ ብቻ ሳይሆን ፥ ኢትዮጵያዊነትህን ይዘህ ጥፋ» በሚል ሰበካ የአማራን ህዝብ ተክለ ሰውነት ማቀጨጭ እና ጥሪቱን መሞለጭ!
3) በኖርንበት እና ባየነው ፥ ምስክርም በምንሆንበት 25 አመት የወየኔ ዘመናት ፥ አንድም ኢትዮጵያዊ ( ከአማራ በስተቀር ) ከየትኛውም ክልል ሳይባረር ፥ አመራ ግን በዘሩ ሲባረር ፥ ስለዘሩ ሲሳደድ እና በዘሩ ምክንያት ሲገደል እያየነው ፥ ይህንን ህዝብ ለመታደግ የሚደረገውን ርብርብ በዘረኝነት በመፈረጅ ፥ ታሪክን ተገን አድርጎ ፥ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ በማይወክል መልኩ አማራ ራሱን ጨፍልቆ ፥ ከሱ በቁጥርም ይሁን በእውቀት እጅግ ባነሱ አካሎች ተወክሎ ፥ ከስራቸው እንዲንደፋደፍ ፥ ስለት እና ምልጃ እንዲያቀርብ ፥ ራሱን ክዶ ፥ በራሱ በአማራ አጋፋሪዎች በተደረገ የኤሌሎች በአለ ሲመት ላይ አክሊል አቅራቢ ፥ ምንጣፍ አንጣፊ ፥ የዙፋን እግር ወልዋይ እና ሰረገላ ገፊ እንዲሆን እየቴሰረ መሆኑ
4) የአማራ ህዝብ ከብቱን ሽጦ ፥ ደሙን ገብሮ ፥ ልጆቹን ሰውቶ የሚያደርገውን ትግል በጠራራ ፀሃይ ፥ ባልተወከሉ ታጋዮች ትግሉን ተቀምቶ ፥ ለሞቱ ስም ተሰጥቶት ፥ ለትግሉ የሃሰት ዜና ተሰርቶለት ፥ ባልዋለበት ውሎ እና ላልቆመለት አካል ቆሞ ፥ የክብር ሞቱ መነገጃ እና መወስለቻ ሆኖ እያየም ፥ ስድብ እና ክብረ ነክ የሆኑ ትችቶችን ፈርቶ ፥ ከጥቂቶች እውነት ይልቅ ለብዙሃን ነውር ገብሮ ፥ እውነቱን እያወቀ ፥ የሆነውን እያየ ፥ ሞቱን አማራ ለነፃነቱ ሲል ያደረገው እንደሆነ ያልመሰከረ እና ያልተናገረ አማራ ባለበት ዘመን መፈጠራችን እና መኖራችን
5) ከትግሉ ባሻገር ትግሁ አማራ ማንነቱን ጥያቄ አድርጎ ሲነሳ ፥ ወልቃይት አማራ እንጂ ትግሬ አይደለም በሚል የፋኖ መለከት የተቀጣጠለው ትግል ፥ በውጭ ሃገር አርባ ስም ተሰጥቶት ፥ የትግሉ አብሪ ጥይት አማራነት እንደሆነ እየታወቀ ፥ የጎጃም ገበሬ ለጎንደሩ ገበሬ መገደል ባህር ዳር ላይ ሲሞት የሞተው ጎጃሙን እና ጎንደሩን አንድ ያደረጋቸው አማራ መሆናቸው ፥ ባንድነትም ያቆማቸው ይኸው አማራነታቸው እንደሆነ ለሳር ለቅጠሉ ሳይቀር ግልፅ በሆነበት ሰዓት ፥ ይህ የአማራ ትግል ሰላም የነሳቸው ፥ ሲቻል የአማራ ህብረትን ኒዩክሊየር ቦምቦ አስመስሎ በመሳል ሳይቻል ደሞ አማራን በምክንያት በመሰነጣጠቅ ፥ ጎንደር ህብረት ፥ ጎጃም ህብረት ፥ ወሎ ህብረት ፥ ሸዋ ጅብረት እያሉ ሃይሉን ለመበታተን ፥ ገባሪነቱን ዘመን ተሽጋሪ ለማድረግ ፥ ሃይሉን ለመፈረካከስ ፥ የህብረት ክሩን ለመበጠስ ፥ የአንድነት ዋልታውን ለመከስከስ እየሄዱበት ያለው መንገድ በራሱ በአማራው ተወላጅ ሳይቀር በከፊልም ቢሆን ተቀባይነት ማግኘቱ ይመስለኛል ።
ጥያቄ አለኝ ፥ የጎንደርን አማራ በጎንደር ህብረት ፥ የጎጃሙን በጎጃም ፥ የወሎውን በወሎ ፥ የሸዋውን በሸዋ ጠቅልለን ፥ ሰብረን እና ሰንጥቀን ከጨረስን ወዲያ ፥ በሃረርጌ የሚኖሩን የወሎ አማሮችን የሃገረርጌ ወሎዬውች ፥ በጅማ የሚኖሩ የጎንደር አማሮችን የጅማ ጎንደሮች ፥ የ ወለጋ ጎጃሞች ፥ የአዲስ አበባ ሸዋዎች ብለን ሌላ የአማራ ህብረት ልንፈጥር ነው ?
አማራ እንዲበረታ አማራ በህብረት ይቁም! የአማራ ድል በአማራ ህብረት ብቻ የሚገኝ ነው! የብሄር ፖለቲካ የነገሮች ሁሉ መለኪያ በሆነበት ዘመን ፥አማራ አይደራጅ ማለት አማራን በጀርባው በኩል እንደ ማረድ ነው !
አማራ ንቃ!
ኄኖክ የሺጥላ

ልዩ ልዩ ዜናዎች – Finote Democracy- EPRP Radio – ፍካሬ ዜና ምኒሊክ ሳልሳዊ



ልዩ ልዩ ዜናዎች – – Finote Democracy- EPRP Radio – ፍካሬ ዜና
 ኢትዮጵያ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት በተለያዩ በሽታዎች ከሚቀጠፉባቸው ሀገራት ግንባር ቀደምትነቱን መያዟ ታወቀ፡፡ ከሰላሳ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ህፃናት የሚሞቱት በተቅማጥና በሳምባ ምች መሆኑም ተነግሯል፡፡ ወያኔ በየጊዜው የህፃናትና የእናቶች ሞትን መቀነስ መቻሉን ቢያቀርብም ሐቁ ግን በወሊድ የሚሞቱ ህፃናት ቁጥር በእጅጉ የጨመረ መሆኑንና ስድስተኛ ልደተቻውን ሳያከብሩ በሞት የሚነጠቁ ሕፃናትም ቁጥር እየናረ በመሄድ ላይ
እንደሆነ ታውቋል፡፡
 የተለያዩ የነዳጅ ምርቶች ማለትም ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ጋዝ በማቅረብ በኩል ግዙፍ መሆኑ የሚነገርለት የቻይናው ፔትሮቻይና የተባለ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ ማሸነፉ በይፋ ተነገረ፡፡ ይህ በዓለም ግዙፍ ከሆኑት አስሩ ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ድርጅት ከአመታት በፊት ይህንን እድል ለማግኘት ከወያኔ ቁንጮዎች ጋር ውስጥ ውስጡን ይሠራ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ኩባንያ እስካሁን ነዳጅ ያቀርብ የነበረውን ቪቶል ኦይል የተባለን የባህሬን ኩባንያ ገፍተሮ መግባቱ ቻይናና ወያኔ እጅና ጓንት መሆናቸውን የሚያሳይ እንደሆነ የፖለቲካ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡
 በአማራ ህዝብ ላይ የተጫነው ብአዴን የተባለው የ ወያኔ ቡድን፣ ተከስቶ የነበረውን ሕዝባዊ አመጽ በማጣጣል ለወልቃይት ጥያቄ የተድበሰበሰ ምላሽ በመስጠት በመጠናቀቁ ሕዝቡን ክፉኛ ያበሳጨና ጥርሱን ያስነከሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው በማንም ወገን ሳይሆን በወልቃይትና በጎንደር ሕዝብ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሆኖ ሳለ የአማራ ፕሬዚደንት ተብየው ገዱ አንዳርጋቸው ይህ ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው በትግራይ ገዥዎች ብቻ እንደሆነ መናገሩ ሕዝቡ እያካሄደ ላለው ሕዝባዊ አመጽ ነዳጅ ሆኖ እንሚያቀጣጥለው ለማወቅ ችለናል፡፡ በጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ በጎበዝ አለቆች እየተመራ ከወያኔ ነፍሰ-ገዳዮች ጋር ፍልሚውን እያደረገ እንደሚገኝ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚደርሱን ዜናዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡
 በቅሊንጦ እስር ቤት እሳት አያይዛችኋል የተባሉ 38 እስረኞች ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ተነግሯል። በክሳቸው ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከል አመጽ ማስነሳት፤ የአሸባሪ ድርጅቶች አባሎች በመሆን ሌሎች ሰዎችን መመልመል የሚሉት የተጠቀሱ ሲሆን እሳቱ ከመነሳቱ በፊትም ያልተግባቧቸውን ሰዎች ይደበድቡ እንደነበር ተጠቅሷል። በቅሊንጦ የተካሄደው የእሳት ቃጠሎ በወያኔ አገዛዝ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ አመጽ መልኩን እንዲቀይር ያደረገው እኩይ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከእሳቱ በፊት የተኩስ ድምጽ እንደተሰማ የአይን እማኞች ከመመስከራቸውም በላይ በእሳት ቃጥሎ ምክንያት ከሞቱት ዜጎች መካከል
የተወሰኑት በጥይት ተመተው እንደሞቱ የአስከሬናቸው ምርመራ አረጋግጧል።
 በጋምቤላ ታግተው የነበሩና ቪንቴጅ ኤር ራለይ በሚል ስም የሚታወቁ የትናንሽ ሲቪል አውሮፕላኖች አብራሪዎች ተለቀው ጉዟቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ የቀጠሉ መሆናቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። የወያኔ አገዛዝ ሰዎችን ያገተበት ምክንያት የአየር ወሰንን አለፈቃድ በመጣሳቸው መሆኑን ጠቅሶ ከማክሰኞ ኅዳር 13 ቀን ጀምሮ ከጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳይወጡ ያደረገ መሆኑን ገልጿል። ሰዎችን ለማስፈታት በርካታ የምዕራብ አገሮች
ዲፕሎማቶች ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ይታወሳል።
 ባለፈው ሳምንት አንዲት ኢትዮጵያዊት 3.1 ኪሎግራም የሚመዝን ወርቅና $10, 000 ዶላር ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የሌሎች አገሮች ገንዝብ ኖቶች ይዛ ወደ ህንድ ለመግባት ስትሞክር ዴልሂ የኢንድራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፈታሾች ተይዛ የታሰረች መሆኑ ተዘግቧል። የህንድ ባለስልጣኖች በሰጡት መግለጫ ግለሰቧ ከሁለት ወር በፊት ተመሳሳይ ሙከራ ስታደርግ ተይዛ በዋስ የተለቀቀች መሆኑን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት የያዘቻቸው ንብረቶች በሙሉ የተያዙ መሆናቸውንና እሷም ወደ እስር ቤት መላኳን ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄዱ የነበሩትን ሕዝባዊ አመጾች በመሸሽ በርክት ያሉ የወያኔ ባለስልጣኖች የዘረፉትን ሀብት በተለያዩ መንገዶች ሲያስወጡ የነበሩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በህንድ ባለስልጣኖች በቁጥጥር ስር የዋለችው ሴት ምናልባት ከወያኔ ባለሥልጣናት መካከል አንዷ ወይም የነሱ ተባባሪ ልትሆን ትችላለች የሚል ግምት እየተሰጠ ነው።
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
Vm
http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
00:00
R
p

To Listen PART 2: http://www.finote.org/TodayPart2.mp3
Vm
P

የትግል ጥሪ! የጎንደር እና ጎጃም ህዝብ ለመላው ኢትዮጵያዊ ያቀረበው አጭር የትግል ጥሪ !ቆንጅት ስጦታው



የትግል ጥሪ!
የጎንደር እና ጎጃም ህዝብ ለመላው ኢትዮጵያዊ ያቀረበው አጭር የትግል ጥሪ!
የጎንደር እና የጎጃም ህዝብ ከወያኔ ጋር ጉሮሮ ለጉረሮ ተናንቆ እየተፋለመ ይገኛል። መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ይህንን ታሪካዊ ትግል ከጎናችን ተሰልፎ በመፋለም ኢትዮጵያዊ ክብራችንን መልሰን እንጎናፀፉ ዘንድ በምንወዳት አገራችን ስም ጥሪ አስተላልፈናል።
በመላው ኢትዮጵያ ድንበሬ ተደፈረ እያለ ደሙን እያፈሰሰ የኖረው የጎጃም እና ጎንደር ህዝብ ዛሬ ከወያኔ ጋር ትልቅ ፉልሚያ ላይ ይገኛል።
ይህንን ፉልሚያ ህገ-ወጡ ወያኔ የጣለብህን ህገ-ወጥ አስቸኳይ_አዋጅ_አሽቀንጥረህ በመወርወር በያለህበት ሆነህ ወያኔን እና የወያኔን ቅጥረኞች ትፋለማቸው ዘንድ ወገናዊ ጥሪያችንን አስተላልፈንልሃል።”
ድል ለኢትዮጵያውያን!!!

Monday, November 28, 2016

በበርካታ አካባቢዎች የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ ተካሄደ ምኒሊክ ሳልሳዊ



በበርካታ አካባቢዎች የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ ተካሄደ
ባሳለፍነው ሳምንት ወያኔ በበርካታ አካባቢዎች ሕዝብን ትጥቅ ለማስፈታት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ከሚደርሱን ዘገባዎች ተረድተናል፡፡ የአገዛዙ ፌደራል ፖሊስና የየአካባቢ የፖሊስ ኃይሎች የቤት ለቤት አሰሳ በማካሄድ ሕዝቡ እራሱንና ቤተሰቡን ከማንኛውም ዘራፊ ኃይል ለመከላከል በገዛ ገንዘቡ የገዛውን መሣሪያ በኃይል እየነጠቁ መሰንበታቸውን ተገንዝበናል፡፡ በበርካታ አካባቢዎች ሕዝቡ መሣሪያውን ላለማስረከብ ከተሰማራው የወያኔ ኃይል ጋር ግጭት እንደፈጠረም ተሰምቷል፡፡
በጋምቤላ፣ በከረዩ፣ በቦረና፣ በባህር ዳር፣በሐረር፣ በአርሲ፣ በጉጂ፣ በጎንደርና አካባቢው፣ በኮንሶ፣ ፣ …ወዘተ መሣሪያ ላለማስረከብ ሕዝቡ ተቃውሞ በማሰማቱ ሳቢያ በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል። ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ሕዝቡ ከወሮበላና ድንበር ጥሶ ከሚመጣ ኃይል ለመከላከል ባለው አቅሙ የገዛቸውን የነፍስ ወከፍ ማሣሪያዎች ወያኔ ስለወረሰበት ከደቡብ ሱዳን ዘልቀው የመጡትን ሙርሌ የሚባሉትን ለመመከት ሳይችል ቀርቶ ህፃናቱ ተዘርፈው እንደተወሰዱበት የሚታወስ ነው፡፡ ይህን መሰል ሕዝብን በጅምላ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ መዘዙ ዘርፈ-ብዙ መሆኑን የፖሊቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ከመደበኛ ጦር ውጭ ሀገርን ድንበር የሚያስከብረው አርሶ አደሩ በመሆኑ ሕዝብን ካለመሣሪያ ባዶ እጅ ማስቀረት ለድንበር ተሻጋሪ ወራሪዎች የተመቻቸ ሁኔታ ይፈጥራል ይላሉ፡፡ በሌላ አንጻር ትጥቅ በማስፈታት ወያኔ የጭቆና እድሜውን ለማራዘም ቢያልምም ሕዝቡ ክብሩንና ሀብቱን በመገፈፉ ምሬትና ንዴት አድሮበት ወያኔን ለማውረድ በጽኑ ይታገላል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ minilik salsawi via finote Democracy

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 102 ተማሪዎች ታሰሩ ተባለ ቆንጅት ስጦታው



በጎንደር ዩኒቨርሲቲ 102 ተማሪዎች ታሰሩ ተባለ
“የሥራ ዕድሉ በጣም ጠባብ ስለሆነ ዲፓርትመንት ይቀየርልን” ብለው የጠየቁ 102 የጎንደር ዩኒቨርስቲ የእንሳት ፈርማሲ ተማሪዎች ከትናንት በስቲያ አርብ መታሰራቸውን የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች ለአሜሪካ ድምጽ ገለጹ።
የጎንደር ዩኒቨርስቲ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ዓመት ያሉ የእንስሳት ሕክምና ፈርማሲ ትምሕርት ክፍል ተማሪዎች ከእነርሱ ቀድመው የተመረቁ ተማሪዎች ሥራ ማግኘት ስላልቻሉ የትምህርት ክፍላቸው እንዲቀየር መጠየቅ ከጀመሩ ሦስት ሳምንት እንዳለፋቸው ለአሜሪካ ድምጽ የገለጸ ስሙን መናገር ያልፈለገ ተማሪ ይናገራል።
በዩኒቨርስቲው ውስጥ ጉዳዩን በቅርብ ሲከታተል እንደነበር የገለፀው ይኸው ተማሪ ተማሪዎቹ መማር ካልፈለጉ ክሊራንስ ሞልተው ግቢውን ለቀው እንዲወጡ ማስታወቂያ መለጠፉንና በዚህ መሰረት ክሊራንስ ሊሞሉ ሲሄዱ ተሰብስበው እንደታሰሩ ተማሪው ተናግሯል።
በዚህ ጉዳይ ላይ የዩኒቨርስቲውን ፕሬዝዳንት ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።
ጽዮን ግርማ ዝርዝር አላት።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋየል ያድምጡ። http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/11/27/155f8e23-dcb0-49f1-b8e2-fa2479cf0e10.mp3
Vm
P

ለሕዝብ እንቆረቆራለን የሚሉ በስድብ ፖለቲካ ሲናቆሩ ሕወሓት በደቡብ ክልል የኮንሶ ሕዝብ ላይ አዲስ ጭፍጨፋ ጀምራለች።Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)



ለሕዝብ እንቆረቆራለን የሚሉ በስድብ ፖለቲካ ሲናቆሩ ሕወሓት በደቡብ ክልል የኮንሶ ሕዝብ ላይ አዲስ ጭፍጨፋ ጀምራለች።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) የለውጥ ሃይል ነኝ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የብሄር ፖለቲካ ኣራማጅ ነኝ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው አትኩሮቱና ተግባሩ ሁሉ ቢመከር በማይመልስበት የዘለፋና የቅፈላ ፖለቲካ ላይ ባተኮርበት በዚህ ወቅት ላይ ወያኔ በሕዝቦች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃውን ቀጥሏል።ከቃላት ጦርነት ይልቅ ለሕዝብ የሚጮህ የሕዝብን ዋይታ የሚያስማ የሕዝብን ትግል የሚጋራ ወገን ያስፈልጋል። ለአለም ማህበረሰብ ማጋለጥ የለውጥ ሃይሉ ግዴታ ነው።
በኮንሶ ሰዎች አሁንም በጅምላ እንደሚታሰሩ፣የኮንሶን ሕዝብ ወክለው ጥያቄ ያቀርቡ የነበሩ የኮሚቴ አባላት የተወሰኑት መታሰራቸውን አብዛኞቹ ደግሞ መኖሪያ መንደራቸውን ትተው መሰደዳቸውን እኛም በስደት ጫካ ገብተን ነው የምናነጋግራችሁ ሲሉ የኮንሶ ነዋሪዎች ነን ያሉ ሁለት ሰዎች ቤተሰቦቻቸው እንደታሰሩባቸው፣ በኮንሶ የተነሳውን በዞን የመደራቸት ጥያቄ ያነሱ ሰዎች ቀያቸውን ጥለው ጫካ መግባታቸውንና እየተፈጠሩ ባሉት ሁኔታዎች ግራ እንደተጋቡ ለአሜሪካ ድምጽ ተናግረዋል።ወያኔ ሕዝብን እየጨፈጨፈ ባለበት በዚህ ወቅት መነታረክ ለወያኔ ወንጀሎች ሽፋን መስጠት ነው። ለአለም ማህበረሰብ ማጋለጥ የለውጥ ሃይሉ ግዴታ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ

ወታደሮች በየዩኒቨርስቲዎቹ ካምፕ እያቋቋሙ ነው ምኒሊክ ሳልሳዊ


ወታደሮች በየዩኒቨርስቲዎቹ ካምፕ እያቋቋሙ ነው
የተማሪዎችን ተቃውሞ አፍኖ ለመያዝ እንዲያስችል በሚል በርካታ ወታደሮች በየዩኒቭርሲቲዎቹ ግቢ ውስጥ እንዲሰፍሩ ተደርጓል፡፡ ይህ ድርጊት በዩኔስኮ የተደነገገውን የከፍተኛ ትምህርት ነፃነት የሚገፍ በመሆኑ ሊወገዝና ሊጋለጥ ይገባዋል ተብሏል፡፡
ምንም እንኳ ወያኔ የጦር ሜዳ ትጥቅ የታጠቁ ወታደሮችን በየዩኒቭርሲቲ ጊቢዎች ውስጥ ቢያሰማራም በዚህ ባሳለፍነው ሳምንት በአምቦ፣ በወለጋ፣ በነጆ፣ በጂማ ዩኒቭርሲቲዎች “የታሰሩት ይፈቱ” በሚል መሪ ቃል እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ከደረሱን መረጃዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡
በርካታ ተማሪዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፣ እየታፈኑ ወደ አልታወቁ እስር በቶች ተወስደዋል፡፡ ከምሽቱ ሁለት ሰዓት በኋላ ከቤተ መጸሀፍቶችና ከጥናት ክፍሎች ውጪ ሲንቀሳቀሱ የሚገኙ ተማሪዎች እየተደበደቡ መሆናቸውን ተማሪዎች በምሬት ሲገልጹ ተሰምተዋል። Finote Democracy

መረጃ ሙሉ ያደርጋል -የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎች መጣጥፎች ቆንጅት ስጦታው



News Ethiopia Wetatoch Dimts
መረጃ ሙሉ ያደርጋል ለዚህ ደግሞ የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምፅ ሳምንታዊ ዜናዎችን እንዲሁም መጣጥፎችን ለስለስ ካሉ ሙዚቃዎች ጋር ይዘንላችሁ ቀርበናል አብራችሁን ሁኑ

ባሕር ዳር – የዐማራ ሲቪልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በኮማንድ ፖስቱ እየታሰሩ ነው Muluken Tesfaw



ባሕር ዳር – የዐማራ ሲቪልና ልዩ ኃይል ፖሊሶች በኮማንድ ፖስቱ እየታሰሩ ነው፤ Muluken Tesfaw
ከወደ ባሕር ዳር ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው ኮማንድ ፖስቱ በዐማራ ሲቪልና ልዩ ኃይል ውስጥ ያሉ ፖሊሶች እየታሰሩ ነው፡፡ ሰሞኑን 8 ያክል የዐማራ ፖሊስ አባላት የኮማንድ ፖስቱ ሰለባ ሆነዋል ተብሏል፡፡

Sunday, November 27, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይቀጥል ማለት ግድያው አፈናውና እስሩ ይቀጥል ማለት ነው። ኢዴፓ የሕወሓትን የስልጣን ዘመን ለማስረዘም እየተጋ ነው።ምኒሊክ ሳልሳዊ



የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ይቀጥል ማለት ግድያው አፈናውና እስሩ ይቀጥል ማለት ነው። ኢዴፓ የሕወሓትን የስልጣን ዘመን ለማስረዘም እየተጋ ነው። 
 
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) ከወያኔ ታማኝ ተቃዋሚዎች አንዱ ኢዴፓ የተባለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዳይነሳ እያለ ወያኔን እየተማጸነ ነው። ለምን ሲባል የሕዝብ ጥያቄ መመለስ አለበት ብለዋል።የሕዝብ ጥያቄ ለመመለስ ኣስችኳይ ጊዜ አዋጅ ኣስፈላጊ ኣይደለም ፖለቲካ ለሚያውቅ ሰው ከገባው። የሕዝብ ጥያቄ ደግሞ ወያኔ ስልጣን ይልቀቅ ነው፤ የሕዝብ ጥያቄ ይመለስ ማለት ወያኔ ከስልጣን ይውረድ ከሆነ የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኣስፍላጊ ስላልሆነ ወያኔ ስልጣኑን መልቅቅ ኣለበት።
 
አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ወያኔ ሃይልን ተጠቅሞ በስልጣን ለመቆየት በጭንቀት የወለደው መሆኑ ይታወቃል።የኣስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ኣይነሳ ይቀመጥ ማለት በሕዝብ መብትና ነጻነት ላይ መዘባብት ነው። ግድያው አፈናውና እስሩ ይቀጥል ማለት ነው።ይህ አዋጅ ክቀድሞ ኣፈና በበለጠ መልኩ የሕዝብን መብት የሸረሸረ በኣስር ሺዎች የሚቆጠሩትን ወደ እስር ማጎሪያ ካምፖች ያስገባ ገዳይና ጨቋኝ አዋጅ ነው። ይህ አዋጅ ኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆኑ ምእራባውያን ሳይቀር እንዲነሳ እየታገሉ የኢዴፓ የ አ ስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ኣይነሳ ምስጢር ግን ምን እንደሆነ ሕዝብ ይፍታው። #ምንሊክሳልሳዊ

በወገራ የዐማራ ገበሬዎች ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅተዋል፤



በወገራ የዐማራ ገበሬዎች ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅተዋል፤
የሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ የእንቃሽና የጃኖራ ቀበሌ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ትናንት ኅዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. የተንቀሳቀሰው የወያኔ ወታደር በታጋዮቹ የዐማራ ገበሬዎች ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡ ከቦታው ያነጋገርናቸው የዐማራ የጎበዝ አለቆች እንደሚሉት ትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ጃኖራ ከተባለው ቦታ ከፍተኛ ጦርነት ላይ ናቸው፡፡

ትናንት የሄደው የጠላት ወታደር በሞትና በምርኮ በመመናመኑ ተጨማሪ ወታሮች ወደ ቦታው ተልከው እስካሁን ድረስ ተጋድሎ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የጎበዝ አለቆች ተናግረዋል፡፡ የጎበዝ አለቆቹ በርካታ ወታደሮች የሞቱና የተማረኩ መሆኑን ገልጸው በትክክል ቁጥሩን ለመናገር ግን ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡ ከባድና ቀላል የጦር መሣሪያዎችንም በምርኮ በእጃቸው አስገብተዋል፡፡
ከሣምንታት በፊት በእንቃሽ በነበረው ውጊያ በርካታ ወታደሮች ተማርከው በሃይማኖት አባቶች ምልጃ መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን ከባለፈው ስሕተት አሁን እንደተማሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል// Muluken Tsfaw

በታችና ምዕራብ አርማጭሆ ከባድ ጦርነት ተቀስቅሷል Muluken Tesfaw



በታችና ምዕራብ አርማጭሆ ከባድ ጦርነት ተቀስቅሷል Muluken Tesfaw
በከፋኝ የዐማራ ንቅናቄ ሥር የሚንቀሳቀሱ ታጋዮች ከወያኔ ሠራዊት ጋር ትንቅንቅ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡ ዛሬ ኅዳር 18 ቀን 2009 ዓ.ም. የደረሱ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት የዐማራ ታጋዮች በወያኔ ሠራዊት ላይ ድል እየተቀዳጁ ነው፤
በሳምንቱ በነበሩ ከፍተኛ የጦር ሜዳ ውሎዎች ከአገዛዙ በኩል የተገደሉ ወታደሮች ወደ መቶ የሚጠጉ ሲሆን እስካሁን ባለው መረጃ አራት የዐማራ ወጣቶች ሰማዕት ሆነዋል፡፡ የዐማራ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከነሙሉ ትጥቃቸው የከፋኝ እንቅስቃሴን እየተቀላቀሉ እንደሆንም ሰምተናል፡፡
በአካባቢው የመገናኛ ዘዴዎች በመዘጋታቸው ምክንያት የዛሬውን ዝርዝር መረጃ ማግኘት አልተቻለም፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

Saturday, November 26, 2016

በአማራና በትግራይ ክልሎች የወሰንና የማንነት ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱ ዳግም ጥያቄ አስነሳ EthiopianReporter.com  



ከዓመታት ንትርክ በኋላ ለግጭት መንስዔ የሆነው የአማራና የትግራይ ክልሎች የጋራ አዋሳኝ ሥፍራዎችን የመከለልና የማንነት ጉዳይ፣ የመጨረሻ ዕልባት አለማግኘት አሁንም ጥያቄ አስነሳ፡፡
የአማራ ክልል መንግሥት የችግሩን መንስዔ በተመለከተ ግምገማ ተካሂዶ ሁለቱ ክልሎች የጋራ መግባባት መድረሳቸውንና ችግሩን ለመፍታት መስማማታቸውን ገልጿል፡፡ ችግሩ መቼና

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤትን በማቃጠል ለ23 ታራሚዎች ሞት ተጠያቂ ናቸው የተባሉ ተከሰሱ EthiopianReporter.com



–  በቃጠሎው ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት ወድሟል ተባለ
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በፌዴራል ማረሚያ ቤት ቂሊንጦ የእስረኞች ማቆያ ቤትን በማቃጠል፣ የ23 ታራሚዎች ሕይወት እንዲጠፋና ከ15 ሚሊዮን ብር

በጎጃምና በጎንደር 19,847 ወጣቶች መታሰራቸው ተገለጸ፤ • በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች 734 የጦር መሣሪያ ተገፏል Muluken Tesfaw


በጎጃምና በጎንደር 19,847 ወጣቶች መታሰራቸው ተገለጸ፤
• በምዕራብ ጎጃምና አዊ ዞኖች 734 የጦር መሣሪያ ተገፏል  = Muluken Tesfaw
የመንግሥትን ፍርሀት መሸሻና መደበቂያ የሆነውን አስቸኳዋይ ጊዜ አዋጅ የቂም መወጣጫ ያደረጉት የብአዴን የወረዳ ባለሥልጣናት አስካሁን በቻግኒ ከፍጠኛ ቁጥር ያለው ወጣት በቀበሌ ጽ/ቤቶች ታጉሮ እንደሚገኝ መረጃዎች አመለከቱ፡፡

ይህ ከፍተኛ ዘግናኝ ድርጊት የፊድራሉ መንግሥት ሪፖርት ካደረገው ውጭ ሆነው ቁጥር ባለሥልጣናቱ በቀበሌ ሊቀ መናብርቶቻቸው አማካኝነት የአማራን የለውጥ ኃይል ሞራላዊ ጉዳት እና ፖለቲካዊ ተሳትፎ ለማጥፋት በማለም እየተንቀሳቀሱሰ ሲሆን በዞን ደረጃ በአዊ ዞን በሚገኙ ስድስት ወረዳዎች 4967 ወጣቶች ከማንድ ፖስቱ እውቅና ውጭ በአካበቢ ካድሪዎች ታስረው ወራት አልፏቸዋል፡፡ ይህንን ግፍ ላለማየት በሽዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች በመሰደድ ላይ ናቸው፡፡


በምዕራብ ጎጃም 2941፣ በምስራቅ ጎጃም 871፤ በደቡብ ጎንደር 3441 እንዲሁም በሰሜን ጎንደር 4167 ወጣቶች በየቀበሌው የመገኝታቸው ዜና መረጃ የታፈነ ሲሆን የክልሉ አሰተዳደር እና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ እንኳን ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ገልጧል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በአማራ ክልል ከሚገኙ 25489 መደበኛ እስረኞች ላይ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተጨመሩትን 19847 ወጣቶችን መመገብ አልቻልኩም ሲል የክልሉ ማረሚያ ቤት ተቃውሞውን ገለጸ፡፡ በክልሉ ለአንድ ታሳሪ በቀን 9.30 ብር ቁርስ፣ ምሳ እና እራት በጀት የተመደበላቸው ሲሆን እስረኞችም በቂ ምግብ ባለማግኘታቸው እንደተራቡ ተሰምቷል፡፡


በተያያዘ ዜና በምዕራብ ጎጃም ዞን ባህር ዳር ዙርያ እና በአዊ ዞን በዚገም አካባቢ የመሣሪያ ገፈፋ ተጀምሯል፡፡ እስካሁን በምዕራብ ጎጃም በተካሄደው የሌሊት ገፈፋ 534 እንዲሁም በአዊ ዞን ደግሞ 200 ክለሽ እና ቤለጅግ ተገፏል፡፡ መንግሥት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሚኒሻዎችን እያስታጠቀ መሣሪያ እየገፈፈ የሚገኝ ሲሆን ያልተገፈፉ ዐማሮች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ተጠይቋል፡፡
ከአማራ ፖሊስ በተገኝው መረጃ መሰረት ገፈፋው በደቡብ እና ሰሜን ጎንደር አጠናክሮ ለመቀጠል የመከላከከያ አደረጃጀት ተፈጥሯል፡፡

በእጃችን ያለውን ነጻነታችንን የምናረጋግጥበትና የተነጠቅነውን መብት የምናስመልስበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን።የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ምኒሊክ ሳልሳዊ  



በእጃችን ያለውን ነጻነታችንን የምናረጋግጥበትና የተነጠቅነውን መብት የምናስመልስበት ወሳኝ ወቅት ላይ ነን።የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡
 
Minilik Salsawi – mereja.com የወያኔ መንግስት ሁሉም ዜጋ በህግ ፊት እኩል ነው እያለ ሲፅፍና ሲናገር እንሰማለን፡፡ ወያኔ/ኢህአዴግ ይህንን ሲል ምን ማለቱ እንደሆነ ግልጽ ነው፡፡ በአመለካከት ከኔ እስካልተለያየህ ድረስ ማለቱ እንደሆነ እንረዳለን፡፡ በአስተሳሰብ የተለየ እስካልሆንክ ሰው ብትገድል እንኳ በእርቅ ነፃ መውጣት ትችላለህ፡፡ ስልጣንህን ተገን በማድረግ የህዝብ ንብረትና ገንዘብ ብትዘርፍ ዘመነኛ ተብለህ ልትሸለማለህ ትችል እንደሆነ እንጂ ሙሰኛ አያሰኝህም፤ይህ ለኛ ብሄራዊ ውርደት ነው ፤ አንድ ዜጋ የሚከበረው በህገሩ እስከሆነ ድረስ የደርሰብንን ብሄራዊ ውርደት በመቅበር በድል ማንሰራራት የምንችለው ይህንን ወሳኝ ወቅት ተጠቅመን ለኣንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ወያኔን ወደ ከርሰ መቃብሩ ስንከተው ስለሆነ በጋራ ትግል ተባብረን ለድል የምንነሳበት ወቅት ነው።
 
የወያኔ ጁንታ የፍትህና የጸጥታ አካላት ህግን ተመርኩዘው በህገወጥነት እንዲንቀሳቀሱ አድርጓል፡፡ እነዚህ የፍትህ አካላት የተባሉት የሚወስዱት ህገ-ወጥ እርምጃ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ ሳይሆን የወያኔን መንግስት ለሚቃወሙ ግለሰቦች፣ ቡድኖች፣ የፖለቲካ ድርጅቶች በአጠቃላይ የተለየ ሐሳብ የሚያራምዱ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለመጫን የተመሰረቱ ይመስሉኛል፡፡ በማንኛውም ወንጀል የተጠረጠረን ግለሰብ ፖሊስ መጀመርያ ግለሰቡን “ከወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች” አንዱ መሆኑን እና አለመሆኑን ከወያኔ/ኢህአዴግ ባለስልጣናት ይሁንታ ካላገኘ የማሰር አቅም አይኖረውም፡፡ የፍትህ አካላትም ክስ የሚመሰረቱበትን የግለሰቡን ማንነት አስቀድመው ከወያኔ/ኢህአዴግ የፖለቲካ ታማኞች ውጭ መሆኑን ማረጋገጥ የግድ ይላቸዋል፡፡ ዳኞችም እንግዲህ በአንፃሩ ከወያኔ/ኢህአዴግ መንግስት በአመለካከት ያልተለዩ ከሆኑ ወንጀል ቢፈፅምም ተጠርጣሪ ጠያቂ አለበት ማለት ይከብዳል፡፡ የፖለቲካ ታማኝነቱ ሳይታወቅ የተከሰሰ አባል እንኳ በችሎት ላይ እያለም ክሱ እንዲሰረዝለት የሚደረግበት አጋጣሚ አለ፡፡
 
የህግ የበላይነት ባልተከበረበት ሀገር ስለዴሞክራሲያዊ መብቶች ማንሳት ተገቢ አይደለም፡፡ ሁለቱን ለብቻቸው ነጥሎ ማየት ሁኔታውን ጎልቶ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ዴሞክራሲ እየገነባ እንደሆነ በየቀኑ ከመቶ ጊዜ በላይ ራሱ በሞኖፖል ይዞ በሚቆጣጠራቸው የተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን እየነገረን ነው፡፡ በየጊዜው ይህንን ሃሰት እና የውሸት ዲስኩር እየሰማን መሄድ ማለት ሃገርን እና ህዝብን እያላሸቁ መሄድ ስለሆነ እያንዳንዳችን ለዲሞክራሲያዊ መሰረታዊ መብቶች መከበር የራሳችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል::ይህንን ድርሻችንን ልንወጣ የምንችለው ደሞ ወያኒን በጋራ የህዝቦች ትግል ተባብረን በማስወገድ ለሃገራችን አስታውጾ ስናበረክት ብቻ ነው።
 
ወያኔ/ኢህኣዴግ የመንግስትን ስልጣን ተቆጣጥሮ መንግስታዊ ሽብርን እያስፋፋ የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ ጉዳቶችን በህዝብ ላይ እያደረሰ መሆኑ የሚታውቅ ሲሆን ህዝቦች አስፈላጊውን የዜግነት መብቶቻቸውን እንዳያገኙ ሞራላቸውን በሃሰት ፕሮፓጋንዳ በማሸበር እና በሃይል በመግደል የስልጣን መስፋፋቱን ቀጥሎበታል::የህግ የበላይነት እንዲከበር እና የፖለቲካ እና የኢኮኖሚ መብቶችን ለመጎናጸፍ በጋራ በመታገል ሳይውል ሳያድር ወያኔን ከሃገሪቱ ማስወገድ የግድ ነው::አሁንም ወገን ሆይ እንነሳ እንታጠቅ ወቅቱ ወሳኝ እና የድል ብስራት የምናውጅበት ጊዜ ነውና ወድ ትግላችን በመትመም በፍቅር ና በአንድነት ከወያኒ አምባገነኖች መዳፍ ርሳችንን እና ሃገራችንን ልንታደገው ይገባል። ወገኔ እርስ በእርስ መጠዛጠዝ ይብቃ !!!!!!! #ምንሊክሳልሳዊ

Friday, November 25, 2016

በአገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔን እያርበደበዱ ካሉት የአማራ አርበኞች ቆንጅት ስጦታው  



ከታች የሚታዩት ጀግኖች በአገር ውስጥ ፋሽስት ወያኔን እያርበደበዱ ካሉት የአማራ አርበኞች መካከል የተወሱቱ ናቸው።
የአማራ አርበኞች በትናንት እለት የወያኔን ተላላኪዎች ጭኖ ወደ ሣንጃ -ጅንግር ቀበሌ ያመራውን የመብራት ኃይል መኪና ሙሉ ለሙሉ እንዳወደሙ መዘገባችን ይታወሳል። ይህ ዘገባ ከታተመ በኋላ በደረሰን ተጨማሪ ዜና መሰረት በትናንትናው እለት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10:00 ሰዓት አካባቢ በመብራት ኃይል መኪናው ተጨነው ወደ ሣንጃ -ጅንግር ቀበሌ ከሄዱት የወያኔ ተላላኪዎች መካከል 11ዱ ተማርከው በአማራ አርበኞች መታሰራቸው ተረጋግጧል። ተጨማሪ ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ይኖሩናል!

የአማራ ተጋድሎ በጀግኖቻችን ተጋድሎ እስከ ድል ድረስ ይቀጥላል

Thursday, November 24, 2016

በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩና ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉ የውጭ ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት እየተደረገ ነው ተባለ


ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009)
የአሜሪካና የብሪታኒያ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉና በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሃሙስ አስታወቁ።
የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው እነዚሁ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ፓይለቶች አፍሪካን በሚሸፍን የአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ አዘጋጆች ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አንድ ብሪታኒያዊ ፓይለት ከሱዳን ወደ ጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ እንዳለ ደብዛው መጥፋቱን አስታውቆ እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ......
ኢሳት (ኅዳር 15 ፥ 2009) የአሜሪካና የብሪታኒያ ባለስልጣናት ከኢትዮጵያ እንዳይወጡ የተደረጉና በአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ የተለያዩ ሃገራት ዜጎች እንዲለቀቁ ውይይት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሃሙስ አስታወቁ። የተለያዩ ሃገራት ዜግነት ያላቸው እነዚሁ ቁጥራቸው ያልተገለጸ ፓይለቶች አፍሪካን በሚሸፍን የአውሮፕላን ውድድር ላይ የነበሩ አዘጋጆች ለመገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል። የውድድሩ አዘጋጆች ረቡዕ አንድ ብሪታኒያዊ ፓይለት ከሱዳን ወደ ጋምቤላ ክልል በመጓዝ ላይ .....
amharic.ethsat.com

ዜናው ግልፅ አይደለም ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ(ገብርዬ)ራሱን ለማጥፋቱ ምንም ማስረጃ የለም። የሻእቢያ ስለባ ነው የሚሉ በርክተዋል። ( ቆንጂት ስጦታው)



ዜናው ግልፅ አይደለም ነው ያልነው ። እወቁ ካላችሁ በደንብ እንወቅ ! የተነገረንን ሁሉ አንቀበልም ! የተባለው ሁሉ ውሸት ነውም አንልም ! የመመርመር መብት ግን አለን !
ዜናው ግልፅ አይደለም ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ(ገብርዬ)ራሱን ለማጥፋቱ ምንም ማስረጃ የለም። የሻእቢያ ስለባ ነው የሚሉ በርክተዋል። ( ቆንጂት ስጦታው)
በሰሜን ኢትዮጵያ ድንበር ኣከባቢ በተነሳ ግጭት የበላይነቱን ይዣለሁ የሚለው የግንቦት ሰባት ድርጅት የጦር መሪዬ ሻለቃ መሳፍንት ጥጋቡ(ገብርዬ) በወያኔ ጦር ተከቦ እጄን ኣልሰጥም በማለት ራሱን ኣጠፋ ሲል የለቀቀው ዜና ብዙ የሚጣረሱና የሚጋጩ ዘገባዎችን በመያዙ ሻለቃው ራሱን ለማጥፋቱ ምንም ማረጋገጫ ኣለመገኘቱንና ምናልባትም በኣቋማቸው ምክንያት የሻእቢያ ስለባ ከሆኑ ታጋዮች ኣንዱ ነው ሲሉ ጥርጣሬያቸውን ይገልጻሉ።
ሻለቃ መሳፍንት ከዘመነ ካሴ ጋር በመሆን በግንቦት ሰባት ላይ ከፍተኛ ትችት ሲያቀርብ የነበረ ሲሆን እንዲሁም በተለያየ ጊዜ ለጦርነት የሚሆን በቂ ዝግጅት ኣድርገናል ለምን አንንቀሳቀስም በሚል በተዴጋጋሚ ከኮሎኔል ፍጹምና ከሌሎች የሻእብያ ኣካላት ጋር ይጋጭ እንደነበር በኣስመራ የኣርበኞች ግንባር ኣባላት ይናገራሉ። ሻለቃ መሳፍንት ወደ ጦር ሜዳ ተንቀሳቀስ ተብሎ ሲላክ ኣብረዉት በቡድን የተላኩ ጥቂት ሰዎች ከደምህት ተመልምለው የተወሰዱ እንደነበር የኣይን እማኞች ይናገራሉ። ሞተ ተብሎ የተነገረውም ወዲያው ሲሆን የሟቹ ኣስከሬን ግን በማን ቭድዮ እንደተነሳ ፎቶው እንዴት ተደርጎ እንደተገኘ ማብራሪያ ኣልተሰጠም።ይህ ብቻ ሳይሆን ሻለቃው ራሱን ለመግደሉ የሚያረጋግጡ ምልክቶች በሰውነቱ ላይ የለም ወያኔ ከባው ራሱን ካጠፋ ወያኔ ቦታውን ለቃ ሬሳውን ትታ እንዴት ልት ሄድ ቻለች የተገደለበት ቦታስ ድረስ የሻእቢያ ሚዲያዎች እንዴት ሊደርሱ ቻሉ የሚሉ ጥያቄዎች በተከታታይ እየተነሱ ይገኛሉ።
ከዚሁ ጋር በተያያዘ የግንቦት ሰባት ካድሬዎች ሻለቃውን የኛ ጀግና በማለት የኣርበኞች ግንባር ሰዎች የጦር ሜዳ ውሎ እንዳሌላቸው በመናገር ላይ መሆናቸውን የኣርበኞች ግንባር ኣባላትን እያስቆጣ ይገኛል። ይህ የሚያሳየው በኣርበኞች ግንባርና በግንቦት ሰባት መካከል ያለው ገመድ የሃሰት መሆኑን ነው ሲሉ ኣስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
ከዚህ ጋር በተያያዘ ግንቦት ሰባትን እርቃኑን ያወጣው ሄኖክ የሺጥላ እንደሚከተው ጽፏል።
እነ ኮነሬል ፍፁም ሁለት ጓደኞቼን ከገደሉ በኋላ ፥ በወያኔ እጅ ላለመውደቅ ራሳቸው ገደሉ ነበር ያሉን። መሳይ መኮንን ኤርትራ በወረደ ጊዜ ፥ ከአውሮፓ የገቡትን ታጋዮች ቃለ መጠይቅ አድርጎላቸው ነበር ። የነዚያ ልጆች ቃለ መጠይቅ በኮረም ነዋሪ የሆነችው ብርቱካን አሊ ልጇን በራብ ቀብራ ፥ አይ ታሞ ነው የሞተው ብላ ለሁለተኛ ጊዜ በወያኔ ከተቀረፀችው ጋ የሚያመሳስሏቸውን ብዙ ነገሮችን አስተውዬበታለሁ።
ጥያቄ
በወያኔ እጅ ላለመውደቅ ራሱን ሲያጠፋ ፥ በወያኔ ተከቧል ማለት ነው አይደል ? በጥይት ተመቶ ቆስሎ ነበር ?
እሱ ራሱን ባጠፋበት ሰዓት ፥ እሱ ራሱን ሲያጠፋ ያየ ግን ደሞ በወያኔ ያልተያዘ አካል አለ ማለት ነው ? አሁንም ማወቅ እንፈልጋለን ! ግርግር ለሌባ ያመቻል እንዲሉ ሻዕቢያ በአቋማቸው ምክንያት የገደላቸውን ሰዎች መርዶ የምናስተላልፍበት አጋጣሚ ስላለመሆኑ አሁንም ህዝቡ ማወቅ ይፈልጋል ። ይህንን የምለው በተከታታይ ጓደኞቼን ሻዕቢያ እንዴት አድርጎ እንዳጠፋቸው ስለማውቅ ነው !!!! ስለ ሚሽን 1725 በቅርቡ በስፋት ዕፅፋለሁ ። በዚህ ሚሽን እነ ኮነሬል ፍፁም የአማራ ልጆችን ጭልጋ ላይ እንዴት አስከብበው በወያኔ እንዳስደበደቧቸው ለህዝብ የማሳውቅበት ነው።
ዜናው ግልፅ አይደለም ነው ያልነው ። እወቁ ካላችሁ በደንብ እንወቅ ! የተነገረንን ሁሉ አንቀበልም ! የተባለው ሁሉ ውሸት ነውም አንልም ! የመመርመር መብት ግን አለን ! የዚህ ልጅ ቤተሰቦች የልጃቸውን ሞት ( እውነተኛ አሟሟት ) የማወቅ መብት አላቸው። ከዜናው አንፃር ገለፃው ብዥታ አለበት። ይብራራ ነው ያልነው!!! አዎ ይብራራልን የሞተው አማራ ነውና!!!!

የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል የሆነችው ወይንሸት ሞላ ታሠረች።ቆንጅት ስጦታው  




የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባል የሆነችው ወይንሸት ሞላ ታሠረች። አራት ኪሎ አካባቢ ደህንነቶች መጥተው ወደ አልታወቀ ቦታ ወስደዋታል።የእስር ምክንያቷ ደግሞ ” ኢትዮጵያ ትቅደም አቆርቋዧ ይውደም !!! የሚል ፅሁፍ ፌስቡክ ላይ በመለጠፍና ሰማያዊ ፓርቲ ከፈረሰ በዃላ መንግሥትን በግልሽ ለመጣል አስበሻል” የሚል እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።

Wednesday, November 23, 2016

የህወሀት መንግስት በጎንደር ከተማ አፈናዉን ቀጥሎበታል



የህወሀት መንግስት በጎንደር ከተማ አፈናዉን ቀጥሎበታል በተለይ ተፅኖ ፈጣሪ ናቸዉ ተብሎ የሚገመቱ ሰዎች በአብዛኛዉ ወደእስር ቤትእየተጋዙ ብዙ መከራ እና ስቃይ እደረሰባቸዉ ይገኛለ፤
ከነዚህም ዉስጥ ለምሳሌ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ሰዎች ይገኙበታል፡፡
1.ዳኔእል (የዳን ፈርኒቸር ባለቤት ቀበሌ 18 ነዋሪ የሆነ)
2.ትዕግስት ጀምበሩ (ጉንደር የኒቨርሲቲ የምትሰራ የቀበሌ 18 ነዋሪ የሆነች)
3.ሙሉሰዉ ጌታሁን (ባጃጅ ሹፌር ቀበሌ 04 ነዋሪ የሆነ)
4.አቶ ቀለምወረቅ አስመላሽ(ጡረተኛ የሆኑ የታወቁ የሀገር ሽማግሌ ቀበሌ 05 ነዋሪ)
5.ንጉሴ ሽቤ (የአየር መንገድ ሰራተኛ የሆኑ ቀበሌ 04 ነዋሪ)
6.ሚካኤሌ (ባለሀብት የቀበሌ 13 ነዋሪ የሆነ)


እነዲሁም ብዙ የጎንደር ዩኑቨርሲቲ መምህራን በእስር ላይ ይገኛሉ:: Henok Yeshitla


የልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ከኃላፊነታቸው ተሰናበቱ



ባለፉት 30 ዓመታት በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ኢሳያስ ባህረ፣ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዚዳንትነታቸው ተነሱ፡፡
ባለፈው ዓርብ ኅዳር 9 ቀን 2009 ዓ.ም. በመንግሥት የፋይናንስ ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ስንታየሁ ወልደ ሚካኤል ፊርማ በወጣ ደብዳቤ፣ አቶ ኢሳያስ  

የጎሳ ፖለቲካ የዘረኝነት አስፋፊ የሆነውን አካል ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል።Minilik Salsawi



Image may contain: text
የጎሳ ፖለቲካ የዘረኝነት አስፋፊ የሆነውን አካል ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል።
Minilik Salsawi – mereja.com – ከላይ ቅርንጫፉን ስትለመልሙት እንደገና ማቆጥቆጡ ኣይቀርም። የለውጥ ሃይሉ ችግር በጉያው ያሉትን የዘር ፖለቲከኞች መዋጋት ያልቻለው ምክንያቱ የችግሩ የጎሳ ፖለቲካው ምንጭ የሆነውን ወያኔን ክፍተት እየሰጠው ስለሚያግዘው ነው። ካሁን ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሃገር ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ በቀደደላቸው ቦይ መፍሰስ ችለዋል። ከመሰዳደብ ከማንጓጠጥና ከመፈራረጃችን በፊት ራሳችንን እንመርምር!!!
ሊጠራ የሚገባው ኣለ የሚባለው የለውጥ ሩጫ የአደፍራሾች የስግብግቦች የሐሰተኞች የድብብቆሽ ፖለቲካ መሆኑ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውቅልሃለሁ የሚሉ ኣካላት በአንድነት ሃይሉ ውስጥ እንደ አሸን መፍላታቸው የብሄር ፖለቲካው እንዲቀድም በር ከፍቷል። የጎሳ ፖለቲካው ዋና ምንጭ ሕወሓት ነው። ሕወሓትን ከስሩ መንግሎ ማፍረስ እስካልተቻለ ድረስ በአሁኑ ወቅት የምንመለከታቸው ኣስቀያሚ የፖለቲካ ሂደቶች ተስፋፍተው ይቀጥላሉ። በአሁኑ ወቅት በተለይ በዲያስፖራው ዘንድ የሚራመደው የጎሳ ፖለቲካ የሚመሩት እንዲሁም ትግሉ ሞተ ትግሉ ተነሳ እያሉ የሚዘባርቁት ይብልጡኑ ከወያኔ ጋር ጥቅመኞች የነበሩ የሆኑና የሚሆኑ ግለሰቦችና ከባቢዎቻቸው መሆናቸውን ስናስብ ልንነቃ ይገባል።
የተቃዋሚው\የለውጥ ሃይሉ የፈለገው ፕሮፓጋንዳ አሳሳቢ አይደለም። የፖለቲካ ድርጅቶችና የግለሰቦች ጉዳይ ኣስፈላጊ ኣይደለም። እያጠሩ መሄድም የሚቻለው በጋራ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ የጋራ ጠላትን የማጥፋት ስራ ሲሰራ ብቻ ነው። ሌላው ይደረስበታል ዝም ብለን ወያኔን እንታገል የሚል መርሕ አልባነት ምንም ስለማይፈይድ ሁሉን ሊያሰባስብ የሚችል ስራ ሊሰራ ይገባል።ካልሆነ ትግሉ በስድብና በሹፈት ታጅቦ ሁልግዜ ሆያሆዬ እንደሆነ ይቀጥላል። ካለምንም መዘናጋት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር በየቦታው የሚፈሉትን የጎሳና የመንደር ድርጅቶችና ግለሰቦች ከመዋጋት ይልቅ የጎሳ ፖለቲካ የዘረኝነት አስፋፊ የሆነውን አካል ሕወሓትን ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል። ከመሰዳደብ ከማንጓጠጥና ከመፈራረጃችን በፊት ራሳችንን እንመርምር!!! #ምንሊክሳልሳዊ

በገዛ ወገኖቻችን አማካኝነት እህቶቻችን ላይ ስውር ግን ዘመናዊ የባሪያና የወሲብ ንግድ እየተፈፀመ ነው

  


አሳዛኙ ጉዞ ቀጥሏል !
እኛም መጮሀችንን አላቋረጥንም!
Nubiya Kush Kedamawi(መሳይ አክሊሉ)
“እህቶቻችን የባንጋሊ፣ የህንድና፣ የፓኪስታኒ መጫወቻ እየሆኑ ነው,,,”
“በገዛ ወገኖቻችን አማካኝነት እህቶቻችን ላይ ስውር ግን ዘመናዊ የባሪያና የወሲብ ንግድ እየተፈፀመ ነው,,,,”
“የመጡበትንም ሆነ አመጣጣቸውን በጭራሽ የማያውቁ አሉ,,,”
“በኦማን ብቻ ከ40 የማያንሱ ኢትዮጵያውያን ያለ አሻራ በባህር ትገባላችሁ በሚል በራሳችን ሀገር ሆዳምና ህሊና ቢስ ደላላዎች ተታልለው እስር ቤት ከገቡ 4 ወር አልፏቸዋል,,”
ሰላማችሁ ይብዛልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? በናንተ ፀሎት፣ ምርቃትና፣ መልካም ምኞት ይኸው በፈጣሪ ጥበቃ አለሁ።
ላለፉት ሁለት ቀናት በርከት የሉ ጥቆማዎች የመልዕክት ሳጥኔ ውስጥ ተሰትረው አነበብኩ። ሃሳባቸው ስለ ህገወጥ የዱባይ የሰራተኛ ጉዞ ነው።
ከ 2013 ጀምሮ በተለይም በሳኡዲ አረቢያ ሀገር በሪያድ ከተማ መንፉሃ በተሰኘው አካባቢ ውስጥ ከደረሰው አሳዛኝ የኢትዮጵያውያን ሞትና ሰብዓዊ መብት ረገጣ በጟላ ወደ አረብ ሀገራት የሚደረገው የሰራተኛ ጉዞ በሞላ ማለት ይቻለል መዘጋቱ ይታወሳል።
ሆኖም ግን በኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደተለያዩ የአረብ ሀገራት የሚደረገውን ጉዞ እገዳው በፍፁም ሊያስቆመው አልቻለም።
ዛሬም በኢትዮጵያ አየር መንገድ በኩል በመቶዎች የሚቆጠሩ እንስቶች ወደ ዱባይ አየር ማረፊያ መጉረፋቸውን አላቆሙም።
“ከነገ ወዲያ ወደ ዱባይ ልበር ነው,,, ”
ብታምኑም ባታምኑም ከሰዓታት በፊት ይህን መልዕክት በስልክ የላከችልኝ በቅርቡ 20ኛ ዓመቷን ያከበረች በቅርብ የመውቃት ሴት ነት።
በአስተሳሰብ ብስለት፣ በአካላዊ ብቃት እና በማህበራዊ ግንኙነት ክህሎት ብቁ ያልሆኑ ትናንሽ እህቶቻችሁን እና ልጆቻችሁን ከጉያችሁ እየፈለቀቃችሁ ገንዘብ እየሰጣችሁ ወደ ባርነት የምትልኩ ቤተሰቦች ምን አይነት ህሊና ነው ያላችሁ በፈጣሪ?
ዱባይ አየር ማረፊያ ላይ የሚገቡትን ሴቶች እየተቀበሉ የሚወስዱት እነማን ናቸው????
ባንጋሊዎች፣ ህንዶች ፣ ፓኪስታኒዎች እናም ሴቶቻችን ወዴት እንደሚሄዱ ሳያውቁ እንደበግ እየተነዱ ወደማያውቁት የጭለማ ዓለም ይወሰዳሉ ከዛስ ቤተሰብ በስድስት ወሩ ልጄ ድምፇ ጠፋ ብሎ የአዞ እንባ ማንባት አጉል እዬዬ።
የዱባይ መንግስት ለቪዚት ቪዛ እንኳ የዕድሜ ገደብ ወስኗል ለሴት 30 ለወንድ 28 ብሎ የ 20 እና የ18 ዓመት ልጆችን እየወሰዱ በየካፍቴሪያው በየሺሻ ቤቱ መማገድ ከቶ ግፍ አይደለምን?
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ውስጥ የሚገኘው የኢሚግሬሽን ንዑስ ክፍልስ ለምን የሚወጣውን ሰው የእድሜ እና የሂደቱን ምክንያት አይቆጣጠርም? ምኑ ከብዶ ነው?
ስለእውነት እህቶቻችን እያለቁ፣ እየተበላሹ፣ ወደ ጭለማ እየተነዱ ነው በየገጠሩ በየእርሻ ቦታው ቤትና ግቢ ተዘግቶባቸው፣ የረሀቡና የደሞዝ ክልከላው ሳያንስ በፆታዊ ጥቃት የእድሜ ልክ የህሊና ቁስል እየላጡ ከዓለም ተገልለው በስቃይ የሚኖሩትን አምላክ ያያቸዋል።
ሰው ከሀገሩ ወጥቶ አይስራ የሚል አቋም የለኝም ግን ሁሉም በህግና በአግበቡ ይሁን ነው በደህንነትና በሰላም ሰርተው ከራሳቸው አልፈው ለብዙዎች የተረፉ አሉ ግን በዚህ መልክ አይደለም።
አስቸኳይ መፍትሄ ያስፈልጋል ቁጥጥር ሊኖር ግድ ነው
ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ፣
የሴቶች ጉዳይ፣
የውጪ ጉዳይ,,, ሌሎቻችሁም የመንግስት አካላት የናንተ እርምጃዎች ወሳኝ ናቸው የነገ ሀገር ተረካቢ ትናንሽ እህቶቻችንን እንታደግ።
No automatic alt text available.

በዳዳብ ስደተኞች ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኑሯችንን ተረጋግተን መምራት አልቻልንም ይላሉ ቆንጅት ስጦታው  



በዳዳብ ስደተኞች ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ኑሯችንን ተረጋግተን መምራት አልቻልንም ይላሉ

“ኑሯችንን ተረጋግተን መምራት አልቻልንም” በዳዳብ ስደተኞች ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን
በዓለም ትልቁ የሆነው የዳዳብ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ወደ ሌላ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እንደሚዘዋወሩ የኬንያ መንግሥት እንደገለፀላቸውና፤ በአሁኑ ወቅት ኑራቸው በእንጥልጥል መቆየቱን ያስረዳሉ።
http://amharic.voanews.com/a/kenya-ethiopians-daddab-camps-11-21-2016/3606064.html


Tuesday, November 22, 2016

አንድ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በትግራይ ተወላጅ ተማሪ ዘግናኝ ጥቃት ተፈፀመበት።Ayalew Menber



አንድ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ በትግራይ ተወላጅ ተማሪ ዘግናኝ ጥቃት ተፈፀመበት።
በተመሳሳይ ህዳር 21 ያልተጠበቀ ጥቃት ሊፈፅሙ መዘጋጀታቸውን በቅርብ የሚከታተሏቸው ተማሪዎች መረጃውን አውጥተውታል።
የትግራይ ተውላጅ ተማሪዎች ሌሎች ተማሪዎችን መተንኮል ጀምረዋል።በተለይ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ ተደጋጋሚ ትንኮሳዎችን አድርገዋል። ከነዚህም መካከል አክሊሉ መንገሻ የተባለ የ3ኛ አመት ማኔጅመት ተማሪ ትናንት ምሽት ጆሮውን_ቆርጠውታል፤ ልጁም ለህክምና ወደ አዲስ አበባ ተልኳል፤ወንጀል ፈፃሚውም በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል ተብላል።

ቆራጩ ትግሬ ሲሆን አክሊሉ ግን የአቦምሳ (ናዝሬት አካባቢ) ልጅነው ፡፡ ልጁ ለህክምና  ወደ አዲስ አበባ ትናንት የተላከ ሲሆን የኢትዮ ስታር ሆቴል ባለቤት (ትግሬ )  ለማደራደር በሽምግልና ቢመጡም አልተሳካም።ሌላ ደግሞ የአደት ልጅ 3ኛ አመት ማርኬትንግ ተማሪም እንድሁ ጥቃት ሊያደርሱበት ሞክረው ሳይሳካላቸው ቀርቷል ፡፡ በተለይ ትናንትና ዛሬ ብዙ ተማሪዎችን ሲተናኮሉና ሲደባደቡ ነበር።
በዚህ አጋጣሚ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እርስበርሳችሁም ሆነ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ጋር አፋጣኝ መረጃ ትለዋወጡ ዘንድ እንመክራለን።
Ayalew Menber

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እየገፈፈ ነው ተባለ ቆንጅት ስጦታው

  


የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የዜጎችን መብት እየገፈፈ ነው ተባለ

አንዳንድ ከፍተኛ የአመራር አባላቶቻቸውን ጨምሮ በርካታ አባላትና ቁጥራቸው የበዛ ደጋፊዎቻቸው የታሰሩባቸው መሆኑን፤ ከታሰሩባቸው የአካባቢ እስር ቤቶች ዘመድ ጠያቂ ወደማያገኙባቸው ካምፖች አዛውረዋቸዋል ሲሉ ሁለት የፖለቲካ ፓርቲዎች አማረሩ።
በአስቸኳይ አዋጁ ሥም የዜጎች መብት እየተገፈፈ ነው፤ ሲሉ የከሰሱት ተቃዋሚ ፓርቲዎች በእስር ላይ የሚገኙ አባሎቻቸው ያሉበት ያልታወቀ መኖራቸውንም ተናግረዋል።
አዋጁ ከመደንገጉ አስቀድሞ የታሰሩ አንዳንድ የአመራር አባላቶቻችንን
“የታሰሩበት ጉዳይ አያስከስሳቸውም፣ ሊለቀቁ ይገባል” ሲል የክልሉ ፍትሕ ቢሮ ለማረሚያ ቤቱና ለፖሊስ ደብዳቤ ቢፅፍም እስካሁን ያለመለቀቃቸውን፤ እንዲያውም እንደ አዲስ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲታይ እየተደረገ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
Audio Player
Vm
P
Ethiopia's State of Emergency

የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ ቆንጅት ስጦታው 



የጅማ ዩኒቨርስቲ ኪቶ ፉርዲሳ ግቢ ትናንት ማታ ከአምስት ሰዓት እስከ ሠባት ሰዓት ሰልፍ ያደረጉት ተማሪዎች አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሥራ ላይ ከዋለ ወዲህ የፀጥታ ኃይሎች ሌሊት ሌሊት እየገቡ ተማሪዎች ይወስዳሉ፡፡
ዝርዝሩን ከተያያዘው VOA ድምፅ ያዳምጡ።

Monday, November 21, 2016

ግንቦት ሰባት ያለመጠየቅ ህግን አዳብሯል ። ተከታዮቹ የመጠየቅ መብት የላቸውም ! ( ኄኖክ የሺጥላ )


ግንቦት ሰባት ያለመጠየቅ ህግን አዳብሯል ። ተከታዮቹ የመጠየቅ መብት የላቸውም ! ( ኄኖክ የሺጥላ )
ወያኔ ትግሬ ያለመጠየቅ መብትን ህጋዊ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው ። ህዝቡ የመናገር እና የመጠየቅ መብት እንደሌለው ወያኔ ትግሬ በሚያደርገው ነገሮች ሁሉ አሳይቷል። የመ-ፈራት ህግን አጥቷል ። በዚህም ህዝብ ለረጅም ጊዜ ይፈራው ነበር። ጥቂት ደፋሮች ቆርጠው ተነሱ ! የመለስ አምልኮ ብለው ፃፉ! ፊት ለፊት ተጋፈጡት! በመሳሪያ ሳይሆን በሃሳብ ። እስክንድር ጥይት ተኩሶ አይደለም የታሰረው ። የእስክንድር ጥይቱ ብዕሩ ነው ። ተመስገን ወታደር አቁሞ አይደለም የተፋለመው ! የተመስገን ጦሩ ሃሳቡ ነው። አንዷለም በርሃ ስለገባ አይደለም ለወያኔ ጭንቀት የሆነው ፥ የአንዷለም መልዕክቱ ግን ከቦንብ በላይ ወያኔን አቁስሎታል ። ስለዚህ ሃሳብን የሚፈራው ወያኔ ሃሳብን እያሳደደ ያስር ጀምር ።ሃሳብ እና የማሰብ ነፃነት ለዘላለም ይኖራል ወያኔ ግን አይቀጥልም ይወድቃል ! ውድቀት አንድ
ግንቦት ሰባት ያለመጠየቅ ህግን አዳብሯል ። ተከታዮቹ የመጠየቅ መብት የላቸውም ! ሃሳብ ማንሸራሸር ነውር ነው ። ለምን ማለት ክልክል ነው ! ዝም ብለህ ተከተል! ይህ የግንቦት ሰባት ህግ ነው ! እኛ ስራውን እንሰራለን ፥ አንተ ግን ስለምንም ነገር የማወቅ መብት የለህም! ከተከተልህ ትከተላለህ ! እጠይቃለው ፥ አውቃለው ካልህ ገደል ትገባለህ ! በጥያቄ እና በግንቦት ሰባት መሃከል የቻይናን ግንብ የሚያህል ትልቅ ጥርብ ድንጋይ አለ ። ከተወያየህም የምትወያየው ሰላማያወያይ ነገር ነው ። ይህንን ህግ ያፈረሰ በአድማ እንዳይሆኑ ተደርጎ ይዘለፋል! ይወረፋል ! በፍጥነት ከሰውነት ወደ እንስሳነት ( ወያኔነት ) ይሸጋገራል ! ሃሳቡን ከመረዳት ስሙን ማጥፋት ቀላሉ መንገድ ይሆናል ። ይህንንም ሲያደርጉ ለሌሎች ተከታዮቻቸው መቀጣጫም እንደሚሆን እያሳዩ ነው ። የመፈራት ህግን ልክ እንደ ወያኔ እያፀደቁ ነው ። ትዕቢት ነው ! ውድቀት ሁለት!
ኄኖክ የሺጥላ

የእሬቻ በዓል ላይ Down Down Woyane በማለት መፈክር ያሰማው ወጣት ካይሮ ተገኘ።ቆንጅት ስጦታው 



ዳውን ዳውን ወያኔ / Down Down Woyane 2016
ዳውን ዳውን ወያኔ / Down Down Woyane 2016
የቢሾፍቱው የእሬቻ በዓል ላይ መድረክ ላይ ማይኩን ከተናጋሪዎች በመቀማት ዳውን ዳውን ወያኔ / Down Down Woyanee  በማለት ሲያወግዝ የነበረው ወጣት ጉዳይ ብዙዎችን ሲያነጋገር ቆይቶ ነበር::
ይህ ወጣት በሕይወት ይኖር ይሆን? ሲሉ የሚጠይቁ በርካታ ነበሩ:: በተመሳሳዩም የኦሮሞ ሕዝብ የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን ተቃውሞ በወጣበት ወቅት እጆቹን ወደላይ በማድረግ (Say No to The Master Plan) ተቃውሞውን ሲያሰማ ፎቶ ግራፉ በሶሻል ሚድያዎች እና በድረገጾች ላይ በስፋት የሚታየው ወጣት ተቃዋሚ ጉዳይም አነጋጋሪ ነበር::
ዛሬ ከወደ ግብጽ ካይሮ በኦሮሞ አክቲቭስቶች በኩል የተለቀቁ አዳዲስ ፎቶዎች እንደሚያሳዩት ሁለቱም ወጣት ታጋዮች ግብጽ ካይሮ ይገኛሉ::

የኣማራ ተጋድሎ ጦር በቃፍታ ሁመራ ጦር ግንባር ያደረጉት ቃለመጠይቅ ( Video)



የኣማራ ተጋድሎ ጦር በቃፍታ ሁመራ ጦር ግንባር ያደረጉት ቃለመጠይቅ ( Video)

Sunday, November 20, 2016

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሊነሣ ይችላል ተባለ አውሮፓ ህብረት በሚዲያና በሞባይል ኢንተርኔት ላይ ጥያቄ አቅርቧልቆንጅት ስጦታው

  


‹‹ከታሠሩት 70 በመቶ ያህሉ ተለቀዋል››
አውሮፓ ህብረት በሚዲያና በሞባይል ኢንተርኔት ላይ ጥያቄ አቅርቧል
ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች የታሠሩበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሃገሪቱን ሰላምና ፀጥታ ወደ ነበረበት እየመለሠ በመሆኑ ሊነሣ እንደሚችል ጠቅላይ ሚኒስቴር ሃይለ ማርያም ደሣለን ገለፁ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከውጭ ሃገራት አምባሳደሮችና የውጭ ተቋማት ተወካዮች ጋር ሰሞኑን በሃገሪቱ ወቅታዊ ጉዳይ በሰጡት ገለፃ በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በ‹‹ሁከት›› ተሳትፈው ከነበሩት መካከል ከ70 በመቶ በላይ የሚሆኑት ትምህርት ተሠጥቷቸው ምህረት ተደርጎላቸዋል ብለዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ አፈፃፀም መርማሪ ቦርድ ባለፈው ሣምንት ከ11 ሺህ በላይ ሰዎች መታሠራቸውን አስታውቆ የነበረ ሲሆን ተቃዋሚ ፓርቲዎችም በርካታ አባሎቻቸው መታሠራቸውንና ታሣሪዎች ያሉበት ሁኔታ እንደማያውቁ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡
በጠቅላይ ሚኒስትሩ መግለጫ ላይ ማብራሪያ እንዲሰጡ አዲስ አድማስ የጠየቃቸው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሰዒድ፤ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲታወጅ ቅድመ ሁኔታዎች መቀመጣቸውንና ችግሮች ደረጃ በደረጃ ሲቃለሉ ማስተካከያዎች እንደሚደረጉ በግልፅ መቀመጡን ጠቁመው ቀደም ሲልም ዲፕሎማቶች ከአዲስ አበባ 40 ኪ. ሜትር ራዲየስ ውጪ ለሚመለከተው አካል ሳያሳውቁ እንዳይንቀሳቀሱ የሚለው እገዳ ተብሎ የነበረው መነሣቱን ጠቅሰው ሌሎች መሻሻሎችም እየተገመገሙ እንዲነሳ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የአንድ ወር ግምገማው ሲታይ፣ በርካታ መሻሻሎች መታየታቸውን አቶ መሃመድ አብራርተዋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሀገሪቱን ሰላም ለመመለስ፣ የኢንቨስተሮችን ዋስትና ለማስጠበቅና የቱሪስቶችን ደህንነት ለማረጋገጥ የታወጀ መሆኑን በመጠቆም ባለፈው አንድ ወር በነዚህ ጉዳዮች ላይ መሻሻሎች መታየታቸው ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል የአውሮፓ ህብረት በመገናኛ ብዙኃን ነፃነትና በሞባይል የኢንተርኔት አገልግሎት ላይ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥያቄ አቅርቧል፡፡
ህብረቱ በተለይ የአፍሪካ መዲና በሆነችው አዲስ አበባና በመላ ሀገሪቱ የ3ጂ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡ ዘመናዊ ንግድ ወደ ሀገሪቱ ለመሳብ የሚደረገውን ጥረት የውጪ ኢንቨስትመንት ፍላጎትን የሚገታ ነው ብሏል፡፡
ለመገናኛ ብዙኃን በቂ ነፃነት አለመሰጠቱንና ዜጎች ወደ ውጭ ሚዲያዎች ለማማተር መገደዳቸውን የጠቆመው ህብረቱ፤ መንግስት የህዝቡን የመረጃ ጥማትና ፍላጎት እንዲያጤን ጠይቋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁም የፖለቲካ ውይይቶችንና ለችግሮች መፍትሄ ለማበጀት በተለይም የችግሮችን ምንጭ ከስሩ አጥርቶ መሻሻል ለማምጣት የሚደረገውን ጥረት ይገድበዋል የሚል ስጋት እንዳለው ህብረቱ አስታውቋል፡፡

ህወሀት ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ወደ አዲስ አበባ ማእካላዊ እስር ቤት እንዲወሰዱ መወሰኑ ተሰምቷል። ቆንጅት ስጦታው



በትላንትናው እለት ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግሰት የደህንነትና የመከላከያ አመራሮች ባድሩጉት ሚስጥራዊ ስብሰባ ኮ/ል ደመቀ ዘውዴ ወደ አዲስ አበባ ማእካላዊ እስር ቤት እንዲወሰዱ መወሰኑ ተሰምቷል። ESAT

Friday, November 18, 2016

የትግራይ ክልል በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚፈለጉትን.አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ አሳልፌ አልሰጥም አለ ቆንጅት ስጦታው



ኢሳት (ህዳር 8 ፥ 2009)
በባህርዳር ከተማ የጊዮን ሆቴልን ያለጨረታ ተከራይተው ለ20 አመታት ሲጠቀሙበት የነበሩት አቶ ወልዱ ወልደአረጋይ በአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቢታዘዙም የትግራይ ክልል አሳልፌ አልሰጥም ማለቱ ተነገረ። የአቶ መለስ ዜናዊ ዘመድ እንደሆኑ የሚታወቁት አቶ ወልዱ ወልደ አረጋይ ከ1987 ዓም ጀምሮ ለ 20 አመታት የመንግስት የነበረው የባህርዳር ጊዮን ሆቴል ያለጨረታ ተከራይተው ሲገለገሉ ቆይተዋል። ይሁንና አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ የባህርዳር ነዋሪዎች ባደረጉት ጫና ሆቴሉ በ 2007 መጨረሻ ላይ ለመልቀቅ ተገደዋል። በዚሁ ጊዜም ከግብር ማጭበርበር ጋር በተያያዘ በፌዴራል ገቢዎች ቢሮ ባህርዳር ቅርንጫፍ ተከሰው በመጨረሻ የ7 አመታት እስር ቢፈረድባቸውም ይግባኝ ጠይቀው እነ አቶ ስብሃት ነጋ ባደረጉት ጫና በዋስትና ከእስር መለቀቃቸው ይታወሳል።
ጉዳያቸው ከታችኛው ፍርድ ቤት ጀምሮ ይገባኝ እየተጠየቀበት ወደ አማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ደርሶ ውሳኔያቸው ቢፀናባቸውም አቶ ወልዱ ከባህር ዳር ወደ አድዋ በመሄድ ለጊዜው መሸሻቸው ይነገራል። ይህንኑ ተከትሎ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በጋዜጣ ተጠርተው ሊገኙ ባለመቻላቸው በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ በመታዘዙ ይህንን ለማስፈጸም የክልሉ ፖሊሶች ፍለጋ ላይ ቆይተዋል። በዚሁ መሰረት የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ወደ አድዋ በማምራት በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት አቶ ወልዱን በቁጥጥር ስር ለማዋል ቢሞክሩም የትግራይ ክልል አሳልፌ አልሰጥም ማለቱ ተነግሯል።

በጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ግዳጅ የተሰጣቸው የአማራ ክልል ፖሊሶች በትግራይ የጸጥታ ሃይሎች ታስረው ከቆዩ በኋላ ማክሰኞ ተፈተው ተደብድበው መባረራቸውንም ምንጮቻችን ለኢሳት አስታውቀዋል። የባህርዳር ጊዮን ሆቴልን ሲያስተዳድር የነበረው ልጃቸው ብስራት ወልዱ በጣና ዳር የሚገኘውን በ 1999 ዓም ይህን ድርጅት በሊዝ ጨረታ ለመግዛት ሞክሮ ሳይችል በመቅረቱ ከትግራይ ጄኔራሎች ጋር በመመሳጠር በከተማው ከንቲባ ላይ ዛቻና ማስፈራራት ሲያካሄድ እንደነበር ምንጮቻችን አክለው ጠቁመዋል። በታክስ ማጭበርበር በአማራ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሚፈለጉት አቶ ወልዱ አረጋይ በአድዋ ከተማ በከፈቱት የብረታብረት ቶርኖ ቤት ከፍተው እየሰሩ ቢገኙም የትግራይ አስተዳደር ግለሰቡ የክልሌ ተወላጅ በመሆናቸው አሳልፌ አልሰጥም በማለቱ ሊሳካ አለመቻሉን የኢሳት ምንጮች አስታውቀዋል።


የትግራይ የጸጥታ ሃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከአማራ ክልል የሚፈልጉትን ሰው እያፈኑ ሲወስዱ መቆየታቸው ይታወሳል። በቅርቡም ምንም የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖራቸው ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን አፍነው ለመውሰድ ሲሞክሩ የጎንደር ነዋሪዎች ባደረጉት ትግል የአማራ ህዝብ ተቃውሞ ለመነሳት ምክንያት መሆኑ ይታወሳል። በአሁኑ ጊዜ ግን የክልሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት አቶ ወልዱ ሙላት ከአድዋ በፖሊስ ተይዘው እንዲመጡ ትዕዛዝ ቢያስተላልፍም የትግራይ መንግስት የፍ/ ቤቱን ውሳኔ ሳያከብር የአማራ ፖሊሶችን አስሮ ማባረሩ ብዙዎችን እያነጋገረ ነው።

የአርበኞች ግንቦት7 ሃይል ከህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ጋር በቀብትያ ሁመራ እና አጎራባች ቀበሌዎች እየተዋጋ ነው ቆንጅት ስጦታው


የአርበኞች ግንቦት7 ሃይል ከህወሃት/ኢህአዴግ ወታደሮች ጋር በቀብትያ ሁመራ እና አጎራባች ቀበሌዎች እየተዋጋ ነው
ኅዳር ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአርበኞች ግንቦት7 የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ እንደገለጹት፣ አባሎቻቸው በሰሜን ጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ለወራት ሲደራጁና ሲያደራጁ ከቆዩ በሁዋላ፣ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ወታደራዊ ጥቃት በመፈጸም ላይ ናቸው። በተለይ ከትናንት ጀምሮ በቃፍታ ሁመራ እና በአከር አካባቢ ከፍተኛ ውጊያ እያካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል።
አደንድን በሚባል አካባቢ ባለፈው ሳምንት በተደረገው ጦርነት 48 የአገዛዙ ወታደሮች መገደላቸውን የገለጹት አስተባባሪው፣ ከትናንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑንና አንድ የጸረ ሽምቅ ሃላፊ መገደሉን ገልጸዋል። ሃይላቸው ወደ መሃል አገር ለመግባት እየታገለ መሆኑንም ተናግረዋል።
ራሳቸውን በጎበዝ አለቆች አደራጅተው በረሃ ወርደው ሲታገሉ የነበሩትን በማሰባሰብ እና ድጋፍ በማድረግ ወደ አንድነት እንዲመጡ ማድረጋቸውን የገለጹት አስተባባሪው፣ አገሩን ነጻ ለማውጣት የሚፈልግ ሃይል ሁሉ በማንኛውም ጊዜ መጥቶ ሊቀላቀላቸው እንደሚችል ገልጸዋል።
በኢትዮጵያ ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 1 ሰአት ላይ በደረሰን መረጃ ደግሞ በሁለቱ ሃይሎች መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሲካሄድ ከዋለ በሁዋላ፣ አርበኞቹ ከርሰሌት በሚባለው ቦታ ላይ የሚገኘውን አደባይ ተራራን መቆጣጠራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። የመጀመሪያው ጥቃት በአዲ ጎሹና ሁመራ መካከል በምትገኘው እንድሪስ አካባቢ መፈጸሙ የታወቀ ሲሆን፣ በእዚሁ አካባቢ በነበሩ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። ከአርበኞች ግንቦት 7 በኩል 3 ሰዎች መስዋት መሆናቸውንም ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል።
ከሰአት በሁዋላ በ52 መኪኖች የተጫኑ ወታደሮች በሽሬ ፣አድርቃይ፣ ማይጸብሪ፣ ጸለምት አድርገው ታጋዮችን ለመግጠም የተንቀሳቀሱ ሲሆን፣ በዳንሻ አካባቢም በ8 መኪኖች የተጫኑ ወታደሮቸ ሰፍረዋል። ታጋዮቹ ወደ ጠገዴ፣ አርማጭሆ ፣ ቆላ ወገራና ሌሎችም አካባቢዎች ሰንጥቀው ከገቡ ከህዝብ ጋር በመቀላቀል ወደ መሃል ይገሰግሳሉ የሚል ስጋት የገባው አገዛዙ፣ ለትግራይ አካባቢ ህዝብና ሚሊሺዎች “ አርበኞች ግንቦት7 መጥቷልና ራሳችሁን አድኑ “ በማለት ሲቀሰቅስ፣ ለአማራ ተወላጆች ደግሞ “ሽፍቶች ገብተዋል”ና ተነሱ እያለ ነው። በገዢው ፓርቲ በኩል እስካሁን የተሰጠ ይፋዊ መግለጫ የለም።

በቂሊንጦ ማ/ቤት እስረኞች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ ቆንጅት ስጦታው

በቂሊንጦ ማ/ቤት እስረኞች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ


በቂሊንጦ ማ/ቤት እስረኞች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ::በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በሽብር ተከሰው ጉዳያቸው በፍ/ቤት እየታየ የሚገኙት የኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች አብረዋቸው የተከሰሱት 22 ተከሳሾች በዚሁ መዝገብ የተከሰሱት አራት ተከሳሾች፣ ማለትም ገመቹ ሻንቆ፣ ጭምሳ አብዲሳ፣ ገላና ነገራ እና ደረጀ መርጋ በቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን በመግለጽ ፍ/ቤቱ ይህን እንዲያስቆምላቸው በጠበቃቸው አማካኝነት በጽሁፍ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
_92468221_ws_new_languages_624_ws
አቤቱታ አቅራቢ ተከሳሾች ከነሐሴ 28/2008 ዓ.ም ጀምሮ ቀን ከሌት እጅና እግራቸው በካቴና ታስረው እንደሚደበደቡና ስቃይ እንደሚደርስባቸው በአቤቱታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ስቃይ የሚዳረጉትም በ28/12/2008 ዓ.ም በቂሊንጦ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ አቀጣጥላችኋል፣ ወይም ያቃጠሉትን ታውቃላችሁና ተናገሩ በሚል እነደሆነ አስረድተዋል፡፡
‹‹አምናችሁ እሳቱን ያቃጠሉትን ከተናገራችሁ ከወንጀሉ ነጻ ትሆናላችሁ፣ መስክራችሁ ትወጣላችሁ፡፡ ይህን ካልፈጸማችሁ ግን በሙሉ አካልም ሆነ በህይወት አትወጡም›› እነደሚባሉ፣ በካቴና የታሰረው እጅና እግራቸውም ማታ ማታ ከአልጋ ጋር ተቆራኝተው እንደሚታሰሩ በአቤቱታቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ህገ-መንግስታዊ ድርጊትን ፍ/ቤቱ ያስቁምልን ሲሉ አቤቱታቸውን አሰምተዋል፡፡
ፍ/ቤቱም የቂሊንጦ ማ/ቤት ተወካይ አቤቱታው እንዲደርሳቸው በማድረግ ‹‹ወደ ክርክር ሳንገባ ተጠርጠሪዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ ተመልክታችሁ አስተካክሉ፡፡ በተረፈ ግን በቀረበው አቤቱታ ላይ በቀጣይ ሰኞ ህዳር 12/2009 ዓ.ም የጽሁፍ መልስ ይዛችሁ ቅረቡ›› የሚል የተለሳለሰ ማሳሰቢያና ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ እነዚህ አቤቱታ አቅራቢዎች ከሌሎች በተለየ በሌላ መኪና ወደ ችሎት እንደሚመጡና እንደሚመለሱ፣ እንዲሁም ችሎት እስኪሰየም ድረስ ከሌሎች ተከሳሾች ጋር እንዲገናኙ እንደማይፈቀድላቸው ለመመልከት ተችሏል፡፡

ወያኔ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሕልሙ ቅዥት ሆነ ናሆም ግርማ/ከኖርዌይ Nahome Girma



ወያኔ ኢትዮጵያን የማፈራረስ ሕልሙ ቅዥት ሆነ
የወያኔ ፍላጎት የሚሞላው በኢትዮጵያ መፈራረስ ነው። እኛ ኢትዮጵያውያኖች እየገደለንም ቢሆን ዛሬ የመውደቂያው ዋዜማ ላይ እንገኛለን። ለእኛ ለዜጎች ደግሞ እየሞትንም እያዘንም ከፊታችን ያለውን ነፃነት እያየን አለን። የወያኔ መንግስት ዛሬ ከስልጣን ተሰናበተ የሚለው ዜና ቅርብ እንደሆነ ብዙ አመላካች ነገሮችን እያየን ነው። በሌላ በኩል ወያኔ በአምቦ፣ በወለጋ፣ በሻሸመኔ፣ በአላባ፣ በጎንደር፣ በደብረታቦር፣ በጋይንት፣ በባህርዳር፣ በፍኖተሰላም ወዘተ….. የተነሳበት የህዝብ ተቃውሞ ምላሹ በጥይት ግድያና ጭፍጨፋ መሆኑ እያየነውና እየተመለከትነው እንገኛለን። ወያኔ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የተነሱ ህዝባዊ ተቃውሞዎችን ለማኮላሸት የሚወስዳቸው የጭፍጨፋ ተግባራት የተለየ ሽፋን ለመስጠት ምን ምን ዘዴዎችን ይጠቀማል የሚሉትን ከተጨባጭ የወያኔ ተግባራት በመነሳት የሚከተሉትን ማየት ይጠቅማል።
ወያኔ በሚወስዳቸው ግድያና አፈና ጭፍጨፋዎች ህጋዊ ሽፋን ለመስጠት የህዝብ ጥያቄና የህዝብ ግፊት ነው በማለት ሰሚ ያጡ የመገናኛ ብዙሃኖችንና በስም የግል የሆነ በተግባር ግን ወያኔ የሆኑ የግል ሚዲያዎችን ይጠቀማል። ሁሉም የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዝን ሌሎችም የግል ሚዲያዎችን የግል መሳይ ጋዜጦችን ወዘተ… ሁሉም የወያኔ የእምባ አባሾች ናቸው። ስለዚህ በማንኛውም ጊዜና ሰዓት የፈለገውን የፕሮፓጋንዳ ስራ ለመስራት ይጠቀምባቸዋል። እንዲሁም ለተለያዩ የስብሰባ አዳራሾች በሚጠሩ የወያኔ ስብሰባዎች ይህንኑ የሽፍን ተግባር ያንፀባርቃሉ።
ሌላው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በንቃት ሊከታተለው የሚገባ ጉዳይ አለ። በመከታተል ብቻ ሳይሆን ለመርጃ የተደገፈ ምዝገባዎችን እያደረገ የማስቀመጥ ስራን መፈፀም፣ በቴሌቪዝን በራዲዮ እየቀረቡ ለኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት የህዝብ ተቃውሞዎችን የሚወነጅሉ፣ የሚያንቋሽሹ ወዘተ… እንደዚህ አይነት ግለሰቦች በህግ የሚጠየቁበት ጊዜ ይመጣል። እያንዳንዱ ዜጋ ደግሞ እንደነዚህ ያሉ ከሃዲዎችን እየመዘገቡ መያዝ ትልቅ  ግዴታ የመወጣት አካል ስለሆነ በጥንቃቄ ሊሰራ ይገባል። በኋላ የቁርጥ ቀን ሲመጣ ተገድጄ ነው ካለማወቅ ነው… ወዘተ ያደረኩት የሚሉ ተልካሻ ምክንያቶች ከተጠያቂነት የሚያድን አለመሆኑ ማወቅ ይገባል።
እርጅና ጓዙን ጠቅልሎ የመጣባቸው የወያኔ መሪዎች የሚሰሩትን ካለማወቃቸው የተነሳ የማይወዳቸውንና የማይወዱትን ህዝብ የሞት እስራት የግድያ የቶርች ተግባራቸውን እየፈፀሙ በተጠናከረ መልኩ ቀጥለዋል። የህዝባችንን ደህንነት፣ አንድነት የማይፈልገውና የማይጠብቀው ወያኔ በአሁኑ ሰዓት የመከፋፈልን ቁማር ሲከተልና አማራጭ ከማጣትና  የሚሰራውን ስለማያውቅ ሙሉ ለሙሉ ባለማወቅ ሙሉ በሙሉ ወደዘር ጭፍጨፋ ፊቱን አዙሯል።
ሕዝብ ዛሬ ላይ የሚፈልገው ከወያኔ ስርአት መላቀቅ ብቻ ነው። በዜጎች በብሄር፣ በሃይማኖት፣ በፆታ፣ በተለያዩ አመለካከት ምክንያት ፍትህ የማያዛባ መንግስት እንዲመሰረት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ፍላጎት ነው። ሕዝቡን ሁሉ በእኩል ስልጣን የሚገዛ አድሎ የሌለበት የዳርድንበር የሚጠይቅ የሃገርፍቅር የሚያንገበግበው መሪ ይህ አይነቱን ሰው ማስቀመጥ የሁሉም ሰው ሀላፊነት ነው። ኢትዮጵያውያን በአሁኑ ሰአት ካረጁት የወያኔ ባለስልጣናት ማናቸውን ስለመፈለግ አልፈው በሕግ ከለሳ ስር ሆነው ለ25 ዓመታት ውስጥ በፈፀሙት የዘር ማጥፋት ወንጀል እንዲጠየቁ አቋም ነው። እነዚህ ያረጁ የወያኔ ባለስልጣናት በዘመናዊ አመለካከት ዝግ ሆነው ዘርና ጎሳን እየቆጠሩ ለሀገራችን ኢይትዮጵያ ላይ የአንድ ዘር የበላይነት ገኖ እንዲወጣ በፓለቲካውም በኢኮኖሚውም ለ25 ዓመታት ሲሰሩበት ከርመዋል። ዘር ላይ የተፃፈ ታሪክ ደግሞ ከልማት ይልቅ ጥፋት፣ ወደፊት ከመሄድ ይልቅ ጎታችነቱ ያመዝናል።
ወያኔዎች ስልጣንን ሊገለገሉበት እንጂ ህዝቡን ሊያገለግሉበት እንደተቀበሉት ያልገባቸው ደንቆሮዎች ናቸው። በኢትዮጵያ ላይ ህዝብን ደስ የሚያሰኝ መሪ ሊመጣ የግድ ነው። በአዲሱ ትውልድ ለአዲሱ አስተሳሰብ የዳበረና የሰለጠነ ለሀገርና ለወገን የሚበጅ ሁሉን ኢትዮጵያ ተጠቃሚ የሚያደርግ ራእይ ያለው መሪ አስፈላጊ ነው።
ድል ለኢትዮያ ህዝብ
ናሆም ግርማ/ከኖርዌይ

Thursday, November 17, 2016

በቆላ ቃብቲያ ኹመራ ከፍተኛ ጦርነት ተቀስቅሷል፤ War broke out in North West Ethiopia!Muluken Tesfaw



በቆላ ቃብቲያ ኹመራ ከፍተኛ ጦርነት ተቀስቅሷል፤
Muluken Tesfaw
ዛሬ ኅዳር 7 ቀን 2009 ዓ.ም ከቀኑ 11.00 አካባቢ ጀምሮ የወያኔ ጦር ከአማራ ገበሬዎች ላይ ጦርነት ከፍቷል። በአካባቢው የጎበዝ አለቆች የሚመራው የአማራ ገበሬዎች ጦር በአጋዚ ጦር ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ለማጥቃት የሄደው የወያኔ አጋዚ ጦር ከምልባምሻዎች እርዳታ መጠየቁን ሰምተናል።
War broke out in North West Ethiopia!
The TPLF military has launched war against Amhara farmers in North Western Ethiopia in a place called Qabtiya Humera.

Wednesday, November 16, 2016

የሕወሓት ጥልቅ ተሓድሶ :- የአዲስ አበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው።Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)



Image may contain: 2 people , meme and text    የሕወሓት ጥልቅ ተሓድሶ :- የአዲስ አበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው።
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – ሕወሓቶች ጓዳዊና ድርጅታዊ ፍቅራቸው ኣይጣል ነው። በኣደባባይ የተባሉ ይመስላሉ እንጂ ውስጥ ውስጡን ግን ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ዲሲፕሊን እና መደማመጥ ኣላቸው። በደጅ በሚነዙት ፕሮፓጋንዳ ሕወሓት እንዳበቃላት እንደፈረሰች እንደተከፋፈለች ተደሮ የሕዝብን ስሜት ለመሳብ የሚደረጉ ውሸቶች የውስጥ እውነታውን ይደብቁታል ኣደባባይ ላይ ከፍተኛ የሆነ የፖለቲካ ኣስመሳይነት ሲታይባቸው የውስጥ ጥንካሬን ግን በተርታ ሰንሰለት እየገነቡት ይጓዛሉ።
በቅርቡ በኣማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል የሚደረገው የድንበር እና የማንኔት ጥያቄ ፍጥጫዎች ኣቶ ኣባይ ወልዱንና ኣቶ ደጉ ኣንዳርጋቸውን ሲወነጃጅሉ የከረሙት የወያኔ ፕሮፓጋንዲስቶች ስራቸውን ኣጠናቀው ኣዲስ የፕሮፓጋንዳ ኣጀንዳ ለማምጣት እየሰሩ ነው። በመቀሌ እና በባህር ዳር የተካሄደው የፓርቲዎች ግምገማ ተጠናቆ (ችግሮች ?) በሰላም እንደተፈቱ እየሰማን ሲሆን ምን ያህል በሕዝብ ትከሻ ላይ ኣምባገኖች እየዘለሉ እንደሚገኙ የመሰከረ ግምገማ ነበር። በዋናነት የሚነኩትና የሚወገዱት የብአዴን ካድሬዎች ሲሆን ሕወሓት በግምገማዋ ተማምላ እንጂ ተጣልታ ኣልተለያየችም።
በራሳችን የሰጡንን ኣጀንዳ ተከትለን በፈጠርነው የሕወሓት የኣዲስ ኣበባ ኣንጃና የመቀሌ ኣንጃ ንትርኩ በሰላም ተፈቶ ኣባይ ወልዱ ከስልጣን ኣልወርድም ብሎ ምናምን በሚል የደጅ ፕሮፓጋንዳ የውስጥ መሃላ የሕወሓት ግምገማ ተጠናቋል። ለማን ደስ ይበለው ብለን ነው ኣባይ ወልዱን የምናባርረው የሚል ውሳኔ ጸድቋል። ለዚህ ደጋፊ የሚሆን ፕሮፓጋንዳ ደሞ የፌዴራሉ ሕወሓት ኣፍሮ መመለሱ እንዲደሰኮር ተደርጓል። ሕወሓቶችን ማመን ቀብሮ ነው። በኣደባባይ በተላላኪዎቻቸው የሚያስነዙት ፕሮፓጋንዳና በጓዳ የሚሰሩት የፖለቲካ ሴራ የተለያየ ነው።ከሕወሓት ውስጥ ማንም ኣይወገድም ከስልጣን ኣይነሳም።የኣዲስ ኣበባና የመቀሌ ኣንጃ የሚባል ቃል የተቃዋሚን ጆሮ ለማደንቆር የተሰራ ሴራ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ

በእነ ታጋይ በቀለ ገርባ ላይ የተከፈተው ሃሰተኛ ክስ የሕወሓት ዓቃቢ ሕግ ምስክሮቹን በዝግ ችሎት ሊያሰማ ፍርድ ቤቱ የወሰነውን ኣሻሻለ።ቆንጅት ስጦታው



በእነ ታጋይ በቀለ ገርባ ላይ የተከፈተው ሃሰተኛ ክስ የሕወሓት ዓቃቢ ሕግ ምስክሮቹን በዝግ ችሎት ሊያሰማ ፍርድ ቤቱ የወሰነውን ኣሻሻለ።
የሕወሓት ዓቃቢ ሕግ በኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ኣመራሮች በነታጋይ በቀለ ገርባ ላይ የከፈተውን የፈጠራ ክስ ኣስመልክቶ ምስክሮቹን በዝግ ችሎት እንዲሰሙለት ቢጠይቅም ይህንም ጥያቀ ባልተጠበቀና እንግዳ በሆነ መልኩ ፍርድ ቤቱ ተቀብሎ ትእዛዝ መስጠቱ ኣነጋጋሪ ሆኖ ነበር። ቢሆንም በእነ ታጋይ በቀለ ገርባ ላይ የተከፈተው ሃሰተኛ ክስ የሕወሓት ዓቃቢ ሕግ ምስክሮቹን በዝግ ችሎት ሊያሰማ ፍርድ ቤቱ የወሰነውን ለውጦት በክፍት ችሎት እንዲታይ ኣዟል :: ከሕወሓት ፍርድ ቤቶች ፍት ህ ማግኘት የማይቻል ሲሆን ታጋይ በቀለ ገርባ ላይ በእስር ቤት ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሆነ ይታወቃል።
http://mereja.com/network/post/378/news-bekele-gerba-et-al-federal-court-overrules-prosecutor-s-r

Tuesday, November 15, 2016

ወያኔ የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን፤ ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው:: Minilik Salsawi



ወያኔ የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን፤ ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው:: (ምንሊክ ሳልሳዊ)
 – Minilik Salsawi – mereja.com – ስምምነት የጎደለው ትግል ፣ መግባባት የተሳነው ፖለቲካ ፣ በጥላቻ ፖለቲካ የታጀለ ፕሮፕጋንዳ፣ ለጠላት የፖለቲካ ፍጆታ በሩን የበረገደ ጭፍን ኣስተሳሰብ፣ በድቦ የስድብ ፖለቲካ የሚያራምድ መንገኝነትን የለበሰ ባዶ ጩኸት ብዙ ማለት ይቻላል ለዲያስፖራው ፖለቲካ ። እነማን ማን እንዳደራጀቸው የነማን ግርፍ እንደሆኑ ለይተን የማናውቅ የማንነቃ ከትግል ይልቅ ኣፍ መክፈት የሚቀናን እጅግ ልንተች የምንገባ ንፋሳሞች ነን።ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው፥ከወያኔ የማይለይ ኣስተሳሰብ ያነገቡ የወያኔ ግልባጮች ትላንት በእንበታትነዋለን ዛሬ ደግሞ ጥያቄው የቅኝ ግዛት ነው በሚሉ ንፋሳም ኣጀንዳዎች መላተም ሊቆም ይገባል። ብስለት በጣም ያስፈልጋል።ተዋጠልህም አልተዋጠልህም እውነቱ ይህ ነው።
 
በየማህበራዊ ድህረገጹና በየዌብ ሳይቱ ከማውራት መሬት ላይ ወርዶ ተገባራዊ ስራ መስራት ይጠበቃል። ኢትዮጵያን እንበታትናለን ኣሊያም ጥያቄያችን የቅኝ ግዛት ነው የሚሉ ሃይሎችን ማኮላሸት የሚቻለው ተግቶ በመስራት እንጂ በማውራት ኣይደለም። የሚገርመው ስሜታውያን በርክተዋል::ተናግረው እፎይ ብለው የሚተኙ በርካቶች ሆነዋል::ልክ ልኩን ነገርጉት ብለው ሌላውን ደሞ ለማሸማቀቅ (የሚሸማቀቅ ካገኙ) አስበው በየምናምኑ የሚንጎዳጎዱ ጊዜው ይቁጠራቸው::በነፈሰበት የሚነፍሱ ሳያገናዝቡ የሚያራግቡ የፈጠራ እሳት የሚያርገበግቡ በተገኘበት ተደናብረው እና ደንብረው ደንግጠው ለማስደንገጥ የሚርበተበቱ እንዳሉ ሁሉ ሙድ ለመያዝ የሕዝብን ጭንቀት የሚጠቀሙበት ተደምረው ሆዳም በጥቅም የሚደለሉ በጠለዟቸው ሄደው የሚቾመሱ አጀንዳ እና አቋም አልባ ሮቦት ካድሬዎችም በርካቶች ሆነዋል::ይህ ሁላ የግንዛቤ እጥረት ነው::ያለንበትን ጊዜ እና የሚካሄዱ ትግሎችን አለመመዘን ለትግሉ አስታውጾ ለማድረግ ደፋ ቀና ከማለት ይልቅ ተደራሽነት ያሌላቸውን የክፋት ብእር አጀንዳዎችን ይዞ መክለፍለፍ ምም ውጤት የለውም::ለመድገም ያህል ካለፈው ለመማር ያልቻልን የራሳችን ጠላቶች መሆናችንን እንደቀጠልን ነው::
 
ወያኔ ስራዋን ትሰራለች::ጓዳ ጎድጓዳ ገበናውን ስላወቀች በተላላኪዎቿ የሚሰጠውን የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች አሸክማ እሷ የውስጥ ጉዳይውን እያስተካከለች የለውጥ ሃይሎች እያሰረች እየሳደደች እየገደለች ስልጣኗን ታጠናክራለች::እና ከሚዘመሩ የሃሰት መዝሙሮች ተነስተን ወያኔ አብቅቶላታል በሚል የፕሮፓጋንዳ መደምደሚያ ላይ ትተን የሰጠችንን የቤት ስራ እየመነዘርን እዛው ላይ እንደፋደፋለን::ራሳችን ማረም የምንጀምረው መች ይሆን ?አጀንዳ የማታጣው የቤት ስራ ለለውጥ ሃይሎች ማዘጋጀት ስራዋ የሆነው ወያኔ የምታመጣው አጀንዳ እና የቤት ስራ አትኩሮት ባንሰእጠው ያላትን የፕሮፓጋንዳ ሂደት ማኮላሸት እንችላለን::
 
.. ኧረ በስንቱ ልበጥበጥ አለች? በሶ:: ይህንን የሚያራግቡ እና አገር ወዳዱን ርሁሩሁን ዲያስፖራ ሆዱን የሚያንቦጫብጩ አጀንዳዎች ላይ እንዲሽከረከር ማድረግ ምን ያህል የወያኔን አደገኝነት የሚያሳይ ነው::አደባባይ ላይ አተካራ ገጥሞ የለውጥ ሃይሎን በ ነው/አይደለም አተካሮ ለማናከስ ክርክሮችን ፈጥሮ አለመግባባቶች ለማስፋት የሚደረጉ ያልተጣሩ መረጃዎች እና የፈጠራ ማዘናጊያ ጽሁፎች ምን ያህል የትግሉን ወንዝ እንደሚያሻግሩን አላውቅም:;
 
መንገድ ዳር ሰጥሞ ለመቅረት ካልሆነ በስተቀር ወያኔያዊ የፈጠራ አጀንዳ እና መረጃ ላይ ፊት ለፊት እየነጠሩ መጠዛጠዝ የብስለት ስርቆት መካሄዱን ፍንትው አድርጎ ያሳያል::ወያኔን ለመጣል አንድ እና አንድ ነገር ያስፈልጋል ህዝብ ተስፋ የሚያስቆርጡ መረጃዎች የለውጥ ሃይሎች የእርስ በእርስ መናከስ በተገኘ አጀንዳ እንደተፈለገ ንፍስፍስ ማለት የመሳሰሉት ጉዳዮች ሊታሰብባቸው እና ሊወገዱ ይገባል::የሚመጡ መረጃዎች ሃላፊነት የሚወስድ ሰው አሊያም ሚዲያ እስካልተገኘ ድረስ አሊያም ወያኔን ወያኔ አዋረደ በሚል የዋህነት ፈሊጥ መነሳት እንዲሁም ባልበሰለ የዘረኝነት እና የመንደርተኝነት ጽሁፎች ከመቃጠል ራሳችን ማዳን እና ልብ መግዛት ይገባናል:: ሁላችንም በጋራ በሚደረጉ ትግሎች ላይ ልንረባረብ ይገባል::ትግሎችን በማስፋፋት በማስተማር እና በመቀስቀስ በመርዳት ላይ ልንሰማራ ይገባል:ብስለት ማለት ለትግል የሚደረጉ አስታውጾዎችን በማበርከት እና በተረጋገጡ አጀንዳዎች ላይ ስራ መስራት ሲቻል ብቻ ነው::እና እኔም እላለሁ ያለንበት ጊዜ በተገኘው አጀንዳ ላይ የሚነፈስበት ሳይሆን ብስለት የሚጠየቅበት ጊዜ ነው:: ‪#ምንሊክሳልሳዊ
በየማህበራዊ ድህረገጹና በየዌብ ሳይቱ ከማውራት መሬት ላይ ወርዶ ተገባራዊ ስራ መስራት ይጠበቃል። ተዋጠልህም አልተዋጠልህም እውነቱ ይህ ነው።

በኦጋዴን ኣዲስ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመጀመር እና ለመታገል የጋራ ንቅናቄ ተመሰረተ።tቆንጅት ስጦታው



በኦጋዴን ኣዲስ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለመጀመር እና ለመታገል የጋራ ንቅናቄ ተመሰረተ።
 
በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ውስጥ በሕወሓት መንግስት የሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ጭፍጨፋ በመቃውም የሚታገሉ ሃይሎች ኣዲስ እንቅስቃሴ በኦጋዴን ለማድረግ የሶማሌ ክልል የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚባል ድርጅት መመስረታቸውን በቭድዮ ባስተላለፉት ጋዜጣዊ መግለጫ ኣስታውቋል። ዝርዝሩ እነሆ ፡ http://mereja.com/network/post/369/new-movement-in-ogaden-somali-region-justice-and-democracy-move

Thursday, November 10, 2016

ሕወሓት በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው።Minilik Salsawi –



ሕወሓት በመካከለኛ እና ዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ ሊወስድ ነው።

ማፊያው የሕወሓት ቡድን ከኣማራው ሕዝብ ጎን የቆሙ የመካከለኛና ዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ ሊወስድ መሆኑን መረጃዎች ጠቆሙ። በመካከለኛና በዝቅተኛ የብአዴን ኣባላት ላይ እርምጃ እንዲወስድ የሕወሓት ኮማንድ ፖስት ሙሉ ሃላፊነት ተሰቶታል። በክልሉ ውስጥ የተነሳውን የሕዝብ ተቃውሞ ከጎን ቆመዋል ድርጅታችንን ከድተዋል የተባሉትን የብ አዴን ኣባላት ጨምሮ በኣጠቃላይ በመካከለኛ እና ዝቅተኛ ኣባላት ልይ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀቱ ሲጠቆም እርምጃው ከግድያ ጀምሮ እስከ ጅምላ እስር መሆኑን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል።
ምንጮቹ እንዳሉት የብአዴን ኣባላት ቀድመው እርምጃውን ማክሸፍና ሕዝቡ ኣስተባብረው በክልሉ ያለው የሕወሓት ሰራዊትና ኮማንድ ፖስት ብሎ ራሱን የሚጠራው ገዳይ ቡድን ላይ ኣስፈላጊውን እርምጃ እንዲወስዱ መክረዋል።

በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ ተገድለዋል፤Muluken Tesfaw



ከትናንት ጀምሮ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ ተገድለዋል፤ Muluken Tesfaw
በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ቀበሌ የዐማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለመንጠቅ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በምርኮና በሞት ተደምስሷል፡፡ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች ‹‹ሆን ብለው አዝመራችን በምንሸክፍበት በዚህ ወቅት መሣሪያ ለመግፈፍ መጡብን፤ እኛም ገጥመን ፈጀናቸው›› ብለዋል፡፡ ከትናንት ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ሌሊቱን ባደረው ጦርነት 50 የሚሆኑ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ተማርከዋል፡፡ ሁለት መትረጊስ፣ አንድ ስናይፐርና ጥቂት የሬዲዮ መገናኛዎችም አብረው ተማርከዋል፡፡
የተገደሉ ወታደሮችን በተመለከተ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹እስከ ምሽት ድረስ የተገደሉት ከ20 በላይ ነበሩ፤ ሌሊቱን ወታደሩ በየቦታው ተፈንድሷል፤ የተገደለው ወታደር ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ከመሸግንበት ወጥተን በየቦታው የወዳደቀውን አስከሬን መቁጠር ይጠበቅብናል፤ ሆኖም ግን ከማረክናቸው ወታደሮች በእጥፍ ይበልጣል›› በማለት አብራርተዋል፡፡
ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ጦርነት ከጎበዝ አለቆች መካከል የሆኑት አቶ ፈንቴ አየልኝ ዛሬ ሌሊቱን ተሰውተዋል፡፡ አቶ ፈንቴ በጠላት ቀጠና ዘለው በመግባት በርካታ ወታደሮችን ካጋደሙ በኋላ መሞታቸው በጓዶቻቸው ዘንድ ቁጭትና እልህ ፈጥሯል፡፡ የጎበዝ አለቆች በአምባ ጊወርጊስ እና በአርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ የጎበዝ አለቃዎች በአስቸኳይ እንዲደርሱላቸውና ትግላቸውንም እንዲያግዙ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹እኛ ስለሰላም ስንል ነው እንጅ እንኳን ወገራን ድፍን ዐማራን ነጻ ማድረግ አያቅተንም፤ ግን በየአካባቢው ያለው ገበሬ አሁንኑ ይቀላቀላቀለን፤ መንገድ በመዝጋት ወደእኛ የሚመጣውን ወታደር የስቁም ወይም ከእኛ ጋር ይጨመረን፡፡ ይህም በአስቸኳይ መሆን አለበት›› በማለት አብራርተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአርማጭሆ፣ በወልቃይት፣ ወገራ፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳር፣ ጢስ ዓባይና መራዊ በመሳሰሉ ቦታዎች ወያኔዎች ታካሚ በመምሰል ወደ ሆስፒታሎች ቆስለው የመጡ ገበሬዎችን ለመያዝ በየህክምና ጣቢያዎች መሰማራታቸውን ጥቆማዎች እየመጡ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ሕክምና ተቋማት የሚሔዱ ቁስለኞች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ጥቆማውን የሰጡ አካላት አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በየቦታው የሚታሠሩ ወጣቶች ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሆን እንደ ወገራና ጢሳ ዓባይ ወጣቶች ፊትለፊት በመግጠም አገዛዙን እንዲያሽመደምዱት አንዳንድ የጎበዝ አለቆች አሳስበዋል፡፡
(ማሳሰቢያ፤ በየቦታው ያሉ የጎበዝ አለቆች ለወገራ ገበሬዎች እገዛ እንዲልኩላቸው መረጃውን በማሰራጨት እንተባበር)

Wednesday, November 9, 2016

የባሕርዳር ሕዝባዊ ትግል ተጋድሎ የ ኢወተን እና የ አሕን ቅስቀሳ . ቆንጅት ስጦታው  



የባሕርዳር ሕዝባዊ ትግል ተጋድሎ
የ ኢወተን እና የ አሕን ቅስቀሳ
==================
ጥቅምት 26 ለ 27 አጥቢያ በሁለት ተባባሪ ድርጅቶች ማለትም በ “አማራ ሕዝብ ንቅናቄ (አ.ሕ.ን)” እና በ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋድሎ ንቅናቄ (ኢ.ወ.ተ.ን) በጋራ በባህርዳር ቀበሌወች እና ኩታ ገጠም አጎራባች ቀጠናወች የቅስቀሳ ወረቀት ሲበተን አድሯል። በነጋታው በየአካባቢወች ነዋሪ የሆነው ሕዝብ የተበተነውን የቅስቀሳ ወረቀት ለማንበብ እና ለማስተላለፍ ተችሏል። እንደሚታወቀው ወያኔ በጥድፊያ ባወጀችው ወታደራዊ አዋጅ፤ ዜጎች ኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙ፣ የማህበራዊ ገጾችን እንዳይጠቀሙ በመፈለግ የወሰደቻቸው እርምጃወች ምንም የሕዝብን ድካም እና መከራ ቢጨምርበትም ትግሉን ግን እየገታችው እንዳለሆነ የገለጸው ይህ የቅስቀሳ ሊፍሌት፤ ትግሉ እስከ ድል የሚቀጥል መሆኑን እና በሁለቱ ድርጅቶ ማለትም በ አ.ሕ.ን እና ኢ.ወ.ተ.ን መካከል የትብብር እና በአንድነት የአማራ ተጋድሎ ቀጣይነቱን፣ ለጋራ ነጻነት በጋራ መሰዋት የሚያስፈልግ መሆኑን አብስሯል። በዚህ የተበተነ ሊፍሌት የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋድሎ ከአማራ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በመሆን በአለፉት ቀናት መጠነ ሰፊ የሆነ እስከ አፍጢሙ የታጠቀውን የጠባቧ የወያኔ አጋዚ እና መደበኛ ጦር በየቀየው ሲያራውጡት እንደሰነበቱም በተከታታይ በወጡ ዜናወች አሳውቀዋል። ወልቃይት የአማራ ነው!!! በሚል መፈክር የታጀበው ይህ የቅስቀሳ እና ትብብርን በተጨባጭ በትግሉ አውድማ ያሳየን ጽሁፍ በእውነትም እየታገሉ መሰዋትን ገሎ መሞትን ለነጻነት ሲባል የሚከፈል ከባድ ዋጋ በጸጋ የሚቀበል መሆኑን የሁለቱ ታጋይ ንቅናቄወች አስነብበውናል።
አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ከዘመን ዘመን ለአገር መሞትን፣ ለአገር ዘብ መቆምን እንጅ አገር እኔ ልግዛ ብሎ በብቸኝነትም አገር ገዝቶ የማያውቅ ሕዝብ በትምክህት ሲፈረጅ እንደኖረ የምናውቀው ሲሆን። ወያኔዋ ዛሬም ድረስ ይህን ሕዝብ በዋና ጠላትነት ፈርጃ የዘመተችበት ቢሆንም ታጋይ ልጆቹ በቃን አንገዛም። ዘራችንን ከማጥፋት እናድን በሚል በጎበዝ አለቃ ተደራጅተው መታገልን፣ ታግሎ መሞትንም እያደረጉት ነው። ምንም ቢሆን የዚህ የጀግና ሕዝብ ትግል ግቡን እንዲመታ ሳይታለም የተፈታ በመሆኑ ሕወሐት እና ባንዳ ተከታዮቿ የግዜ ጉዳይ እንጅ የመጨረሻዋን የችንፈት ጽዋ የሚጎነጩበት እሩቅ እንደማይሆን በእርግጥ እንናገራለን።
ድል ለተገፋው ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

Tuesday, November 8, 2016

የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል:: Minilik Salsawi


የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል::   Minilik Salsawi
 
የሕወሓት መንግስት ሃገር ውስጥ በሚኖሩ በዲያስፖራው ቤተሰቦች ላይ ታክቲካዊ ጥቃት ይፈጽማል:: ወደ ሃገር ውስጥ የሚገቡ ዲያስፖራዎችንም ቤተሰቦች በዘፍቀደ ያፍናል ሲል አንድ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ገለጸ። ሂዩማን ራይት ስ ዎች የተባለው የሰብዓዊ መብት ድርጅት እንደጠቀሰው በሜልቦርን በስኔ ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ በኣውስትራሊያ ነዋሪዎች የሆኑ ኢትዮጵያውያን ዘመዶቻቸው በጅምላ ታፍሰው እስር ቤት መወርወራቸውን እና እስካሁን ኣለመፈታታቸውን ያብራራል። በምስልና በቪድዮ የተደገፈውን ዝርዝር እዚህ ሊንክ ላይ ያገኙታል ፦http://mereja.com/network/post/320/australia-protests-prompt-ethiopia-reprisals-human-rights-wat

Monday, November 7, 2016

ደባርቅ ሰሜን ጎንደር የጅምላ እስር እየተካሄደ ነው! ቆንጅት ስጦታው


ደባርቅ ሰሜን ጎንደር የጅምላ እስር እየተካሄደ ነው! ለጊዜው የወጣቶች ስም ዝርዝር ደርሶኛል 
1. አግንቸ ማውሻ
2. ሐብታሙ መኮነን
3. መልስ ጌታቸው
4. ይርጋ መኩርያው
5. ለምለም አዲሱ
6. ሰለሞን ክንዴ
7. ቀናው መዝን
ይህንን እኩይ የባንዳ ሎሌነት እያስፈፀሙ የሚገኙት የከተማ አስተዳደሩ የፀጥታ ሐላፊዎች እነዚህ ናቸው፦
1.አዳነ ዳኘው
2. ሻምበል አምባቸው
የደባርቅ መውጫ መግቢያ በወታደር ታጥሯል
እባካችሁ ቤተሰብ ጋር ግንኙነት አርጉ የምትችሉትን መላ ፈይዱ…
ሙሉነህ ዮሃንስ

የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመርቋል ፡፡ በቆንጅት ስጦታው


No automatic alt text available.
የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ምልምል አርበኛ ታጋዮች አሰልጥኖ አስመርቋል ፡፡
የኢትዮጲያን ህዝብ ከጭቆናና የስቃይ ህይወት ለማላቀቅ እና አምባገነኑን የህወሓት አገዛዝ ገርስሶ ለመጣል የትጥቅ ትግል እያደረገ የሚገኘው አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ለወራት ያክል በወታደራዊ ፣ ፖለቲካዊና ሌሎች ተጓዳኝ ትምህርቶች ዙሪያ ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ምልምል አርበኛ ታጋዮች እሁድ ጥቅምት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. በደማቅ ስነ-ስርዓት አስመርቋል ፡፡
በዚህም የምረቃ ስነ-ስርዓት በዓል ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ተጋባዥ እንግዶች የተገኙ ሲሆን የአርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ትምህርትና ስልጠና መምሪያ ሃላፊ አርበኛ ታጋይ ተስፋሁን ተገኝ ለተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ከፊት ለፊታችን ትልቅ ግዳጅና ሃላፊነት ስለሚጠብቀን በምትመደቡበት ቦታ ሁሉ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳትሉ ሃገራዊና ድርጅታዊ ግዴታችሁን ለመወጣት በወታደራዊ ስነ-ምግባር የታነፀ ሰራዊት አስፈላጊ በመሆኑ ለዚህ ለተቀደሰ አላማ መከፈል ያለበትን የህይወት መሰዋዕትነት ለመክፈልና የኢትዮጵያን ህዝብ ከባርነት ህይወትና ከጭቆና ለማላቀቅ በሚደረገው የትጥቅ ትግል የበኩላችሁን ድርሻ መወጣት ይጠበቅባችኋል በማለትና አጠቃላይ የስልጠናውን ሂደት የሚመለከት ሪፖርታቸውን አሰምተዋል፡፡

በዚህ የምረቃ በዓል ላይ ተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የእጅ በእጅ ውጊያን ጨምሮ የተለያዩ ትርኢቶችን በማሳየት ለበዓሉ ድምቀት ሰተውት የነበረ ሲሆን በተመራቂ አርበኛ ታጋዮች የቀረቡ ስነ-ፅሁፎችና መነባንቦች እንዲሁም አዝናኝና ትምህርት ሰጪ ድራማዎችም ልዩ ትኩረት የሳቡ እንደነበርና በቦታው የተገኙትንም ተጋባዥ እንግዶች አስደምመውት ውለዋል ፡፡