Tuesday, October 31, 2017

በህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት ብሶበታል ተባለ source zehabesha



በህወሓት/ኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረው አለመግባባት እየባሰበት እንደመጣ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ፓርቲው አጣብቂኝ ላይ በወደቀበት በዚህ ሰዓት፣ ባለስልጣናቱ የተለያየ አስተሳሰብ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ በተለይ በኦሮሚያ ክልል የተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ በፓርቲው አመራሮች ዘንድ የሚወሰነውን ውሳኔ ጉራማይሌ እንዲሆን እንዳደረገው የጠቆሙት ምንጮች፣ ፓርቲው ትልቅ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ አክለው ገልጸዋል፡፡ ፓርቲው ከፍተኛ መናጋት እና ክፍፍል እየገጠመው እንደመጣ ከዚህ ቀደም ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ የህወሓት/ኢህአዴግ አመራሮችን ለሁለት ከከፈሉ ጉዳዮች መካከል አንደኛው የፖለቲካ እስረኞችን የተመለከተው እንደሆነ ታውቋል፡፡
በተለይ በፖለቲካ ጉዳይ የታሰሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን መፍታት በኦሮሚያ ክልል ለተከሰተው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደ ማብረጃ ይጠቅማል ብለው ያሰቡ የፓርቲው አመራሮች፣ እስረኞቹ እንዲፈቱ ሀሳብ ማቅረባቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡ በሌላ ወገን ያለው አመራር ግን አንደኛው አመራር ያቀረበውን ሀሳብ እንደማይቀበለው መግለጹን ምንጮች ያስረዳሉ፡፡ በአንደኛው ወገን ‹‹ከመሬት ተነስቶ የፖለቲካ እስረኞቹን መፍታት ከባድ ሽንፈት ነው የሚያስከትልብን›› የሚል አመለካከት የያዘ ሲሆን፣ በሌላኛው የፓርቲው ወገን ደግሞ፣ ‹‹እስረኞቹን መፍታት ከመጣብን መዓት አይበልጥም፡፡›› የሚል አመለካከት መኖሩንም ከምንጮች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡
በተለይ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ጨምሮ አቶ በቀለ ገርባ እና ሌሎች በፖለቲካ ጉዳይ የታሰሩ የኦሮሞ ፖለቲከኞችን መፍታት፣ በኦሮሚያ የተፈጠረውን ቀውስ በመጠኑም ቢሆን ሊያበርደው ይችላል የሚል አቋም የያዙ የህወሓት/ኢህአዴግ አመራሮች፣ ሃሳባቸው የበላይነት እየያዘ እንደመጣ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሆኖም እስረኞቹን በነጻ ከመልቀቅ ይልቅ፣ ጉዳዩ የፍርድ ሂደቱን የተከተለ እንዲመስል በዋስ መልቀቁ እንደሚሻል በአንደኛው የፓርቲው ወገን ስምምነት ላይ መደረሱን የቢቢኤን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዛሬው ችሎቱ፣ አቶ በቀለ ገርባን በዋስ የፈታበት ምስጢርም አንደኛው የህወሓት/ኢህአዴግ አመራር ቡድን በደረሰበት ስምምነት መሆኑን የሚገልጹት መረጃዎች፣ በቀጣይም ከኦሮሞ ፖለቲከኞች ውስጥ ከእስር ሊፈታ የሚችል ሰው እንደሚኖር ከወዲሁ ጠቁመዋል፡፡ ሆኖም በቀጣይ ማን ከእስር እንደሚፈታ ለማረጋገጥ አልተቻለም፡፡

Sunday, October 29, 2017

አንዳርጋቸው ጽጌ ዛሬ በዚህ ሰአት  – መስቀሉ አየለ  source zehabesha


ገና ለጋ ሳለ በማርክሲዝም አስተሳሰብ ርቆ የሄደው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ኢንጂነሪንግ ተማሪ የነበረው አንዳርጋቸው ጽጌ ከኢህአፓ ትግል መክሸፍ በኋላ እንደማንኛውም የዘመኑ ወጣት በሱዳን በኩል ወደ አውሮፓ በማቅናት ዱር ቤቴ ብሎ ወደ ኤርትራ በራሃ እስከወረደበት ግዜ ድረስ በዚያው ቆይቷል።

ሆኖም ግን አንዳርጋቸው በአውሮፓ የዩኒቨርሲቲ ቆይታው በወጣትነቱ ከተማረው የኢንጂነሪንግ ትምህርት በማፈንገጥ ነፍሱን ሲበላው ለከረመውና የርሱን ትውልድ በዚያ ደረጃ እንደዛ አድርጎ ያሰከረው ነገር ምን እንደሆነ ሚስጥሩን ፍለጋ ቢረዳኝ በሚል ፍልስፍና ተማረ። ሆኖም ግን ትምህርቱን ከጨረሰም ቦሃላም እንደ ማንኛውም ስደተኛ ቤትና ትዳር ወደሚል የግል ሩጫ ሳያዘነብል ከሰው ገለል ብሎ ብሎ ብዙ በማንበብና ብዙ በማሰብ በተመስጦ ውስጥ ቆይቷል።

ግለ ታሪኩ እንድሚያስረዳው አንዳርጋቸው በብዙ መልኩ አውሮፓ ውስጥ የተባህትዎ ኑሮው የእርሱ መገለጫው እንደነበርና ለዚህም አስረጅው ነገር ከባእቱ ሳይወጣ እረጅም ግዜ የሚያሳልፍ ፣ ብዙ ባለመብላት ይልቁንም ከእፍኝ ቆሎ ጋር ትንሽ ቡና በመጠጣት ሰውነቱን ድካም ሳይሰማው ብዙ የሚያነብና ብዙ ከመናገር አርምሞን የሚመርጥ ሰው ነበር።
በዚህም የተነሳ በአንድ ነገር ላይ ብቻ ሳይወሰን ዘ ስካይ ኢዝ ዘሊሚት በሚል ስሌት ፈርጀ ብዙ እውቀቶችን ለማዳበር የቻለ ሰው ነው አንዳርጋቸው። አንዳርጋቸው ጽጌ ሁሌም ተማሪ፣ በየትኛውም የእውቀት ዘርፍ ላይ መናገር ሲጀምር የሚያስደምም አንደበተ ርትኡ፣ ከምንም በላይ ከሰዎች በታች ዝቅ ብሎ ማንንም ለመስማት ትእግስት ያለው ነገር ግን አንድ ግዜ ላሰመረበት መስመር የማይደራደር እንደ ፌሮ የማይታጠፍ የመርኽ ሰው በሉት እልከኛ ነው።
አንድ ምሳሌ ላንሳ፤
አንዳርጋቸውን በአንድ ወቅት አንድ የሆነ አፍሪካ አገር ውስጥ አግኝቸው በራሱ አንደበት እንዳጫወተኝ ሲጋራ ያጨስ እንደነበር፤ ያም ሆኖ ግን ይህንን ስሜቱን እንደማይወደው ለዚህም እንዲረዳው ወደ ህክምና ማእከል ሄዶ ሲጋራ ለማቆም የሚያስችል ልዩ ልዩ ቴራፒ ለመውሰድ ሞክሮ አንዱም አይነት መንገድ ሊሰራለት እንዳልቻለ ፤ ነገር ግን ባንድ ምሽት ላይ አንዲት ኩነት እንደተፈጠረች እንዲህ ሲል አጫወተኝ። ግዜው አለ አልጎርደን ብራውን የተባለ የቀድሞው የብሌየር ዘመን ቻልስለር የበጀት ሪፖርት የሚሰጥበት ቀን ነበር። በበጀት ሪፖርቱ ዙሪያ ለቻንስለሩ ከቀረቡለት ጥያቄዎች አንዱ የሲጋራን ታክስ የሚመለከት ሲሆን ጋዜኛው እንዲህ ሲል ጠየቀ፣
“ሚር ቻንስለር እርስዎ ወደ ዳውኒንግ ስትሪት ከመጡ ግዜ ጀምሮ የሲጋራ ዋጋ በመቶዎች ፐርሰንት እጥፍ እያደገ ነው፣ ለዚህ ምላሽዎ ምን ይሆን?” የሚል ነበር።
ቻንስለር ብራውን፤ “አየህ እኛ በሁለት መቶ ያህል አገሮች ለምናካሂደው የውጭ ፖሊሲ (በየሃገሩ ያሉትን ኤምባሲዎቻችንን እና የእርዳታ ሰጭ ድርጅቶቻችንን ) እንዲሁም ሌሎች የሁለት አንስተኛ የሚኒስቴር መስሪያ ቤት በጀት ሙሉ ለሙሉ የሚሸፈነው ከሲጋራ በሚገኝ ታክስ ነው በመሆኑ አማራጭ የለንም” ብሎ ቁጭ አለ።
ጋዜጠኛውም በማስከተል ገና ለገና “ሰው ሲጋራ ያጨሳል ብላችሁ ይህን ያህል በመቶ ቢሊዮን ፓውንድ የሚቆጠር በጀት ስትይዙ ሰው ሁሉ ተነጋግሮ ሲጋራውን ማጨስ ቢያቆም ምን ሊውጣችሁ ነው?” ሲል ይጠይቃል፤ ነገር ግን ቻንስለሩ መልሳቸው አጭር ነበር። “አያቆምም!!!” የሚል፤ “ለዚህም” አሉ ቻንስለሩ፣ “ለዚህም በደንብ ወጥነት ያለው (ፓተርንድ) የሆነ መረጃ አለን። ማጨስ የጀመረ ሰው ማለት በራሱ ላይ ስልጣን የሌለው እስቱፒድ ነው ..” የሚል ነበር። ይኽን በቀጥታ ለእግሊዝ ህዝብ ሲተላለፍ የነበረ ቃለ ምልልስ ቤቱ ውስጥ ሆኖ ሲከታተል የነበረው አንዳርጋቸው የመጨረሻውን መልስ ሲሰማ ፈገግ ነበር ያለው። እጁንም ወደ ደረት ኪሱ ሰደድ ሲያደርግ አስር ያህል ሲጋራ የያዘ አንድ የሲጋራ ፓኮ ነበረው፤ አውጥቶም ቅርጥፍጥፍ አደረገና ከፊት ለፊቱ ባለው የብርጭቆ ውሃ ውስጥ ነከረው። “በእርግጥም..!!!” አለ አንዳርጋቸው “ከእንግዲህ የኽን ቃለምልልስ ሰምቸ የሲጋራን ዘር ዳግም ወደ አፌ ብመልሰው አንተ እንዳልከው በእርግጥም እስቱፒድ መሆኔን በእራሴው ግዜ አረጋገጫለሁ ማለት ነው” አለ። ነገሩ ወዲህ ነው፤ የሚገርመው ነገር ከዚያች ቀን ጀምሮ የአንዳርጋቸው ጽጌ ሲጋራ ማቆም መቻሉ ብቻ አልነበረም። እርሱ ሲጋራውን ሲያቆም ማዛጋት፣ ማፋሸግ እራስ ምታትም ሆነ እንቅልፍ እንቅልፍ ማለት ሳያስፈልገው እንደማንኛውም ሱስ እንደሌለበት ሰው እንዲሁ ጽድት ባለ መንፈስ ከብሩህ ፈገግታ ጋር ነበር ከእቅልፉ የነቃው። በዚህም አንድ ሰው ከውስጡ ሲወስን ምን ያህል አቅም መፍጠር እንዲሚቻለው ቀላሉ ማሳያ ሆኖ አልፏል።
እንዲህ ያሉት በመርህ የመጽናት ባህሪዎቹ ለአንዳርጋቸው በጸጥታ ውስጥ በኖረባቸው የጽሞና ግዜያት ያዳበራቸው የሞራል መሰረቶቹ ናቸው። በዚህ የተነሳ ማንም ሰው አንዳርጋቸውን ቀርቦ ለማወቅ እድል ቢገጥመው እርሱ ማለት ከራሱ ጋር የታረቀ፣ ፍጹም ሰላማዊ፣ እንደ ሱናሜ በሚገነፍል ማእበል ላይ ተረጋግቶ መራመድ የማይሳነው፣ የማይሞቀው የማይበርደው፤ በአለም ሳለ እራሱን የካደ ትሁት ሰው ነው።
ዛሬ አንዳርጋቸው ጽጌ በፍልስፍና ውስጥ ያዳበረውን ወደ ውስጥ የማየት ክህሎት በሌላ ገጽታው በመመርመር ያሳልፋል። ወያኔዎች ባዘጋጁለት ከመሬት በታች በተሰራች በጣም ጠባብና አየር አለባ መስኮት አልባ ክፍል ውስጥ የብሉያትን እና የሃዲስ ኪዳንን እንዲሁም የነገረ መለኮትን ትርጉዋሜዎች አዳርሷል። ሰባቱን አጽዋማት ሲጾም በቀን አንድ ግዜ ምግብ ይቀምሳል።የያኔው የማርክሲስት ባህታዊ ፍልስፍና እና ነገረ መለኮት ሳይጣረሱ የት ላይ እንደሚገናኙ ዛሬ በስልሳዎቹ መጀመሪያ እድሜው ላይ ነጥቡን አግኝቶታል።ይዅውም በፍልስፍና ፒውር ሰብጀክቲቪቲ የሚባለው በመጸሃፍ ከንጻሃ ስጋ ወደ ንጻሃ ነፍስ፤ ከንጻሃ ነፍስ ወደ ንጻሃ ልቡናና፤ ነጽሮ ስላሴና አይምሮ መንፈሳዊ እያሉ ባለቤቱ ክርስቶስን እስኪያክሉት በመንፈስ ማደግ ነው። ዛሬ አንዳርጋቸው በዚያ ጎዳና ላይ ነው። ማን ያውቃል፤ እንደ ጳውሎስ ቀናኢ ነገር ግን በራሱ መንገድ ይጏዝ የነበረ፤ በዚያው ልክ ከሰማይ በታች ለሰው ልጆች ሰላም የማይገደው ነገር የሌለና ለዚህም እርሱ በወቅቱ በገባው መስመር ፤ለራሴ ሳይል ከልጅነት እስከእውቀት እራሱን አሳልፎ የሰጠለት ይኽ የእንጨት ለቃሚ ልጆች ጎስቋላ ህይወትን የመታደግ ትግል፤ እንዲሁም የደም ንኪኪው ካለባቸው የሰቃሊያነ ክርስቶስ ተረፈ አይሁድ እጅ ከወደቀበት ቀን ጀምሮ በእያንዳንዷ ደቂቃ የከፈለውን ስቃይ ከጾም ከጸሎት ከንሳሃ ቆጥሮለት እርሱ ብቻ ባወቀው የገለጠለት ወይንም የተገለጠለት ነገር አለመኖሩን ማን ያውቃል?፣ ቅዱስ አውግስጢኖስ “ቤተከርስቲያናችን በቅዱስ እስጢፋኖስ ጸሎት ቅዱስ ጳውሎስን ያህል ሃዋርያ አገኘች” ሲል ቅዱስ ጳውሎስን ኋላ ለደረሰበት የብቃት ደረጃ የጠራችው ቀዳሜ ሰማእት ቅዱስ እስጢፋኖስ በዲንጋይ ሲወገር በጸአት ነፍሱ ግዜ “ጌታ ሆይ ይቅር በላቸው ብሎ የጸለያት ጸሎት ነበረች” ማለቱ ነበር። የመድሃኒዓለም ስራው ሰዎች ለክፋት የሚያደርጉትን ክፉ ስራ ሁሉ ወደ በጎ መለወጥ ነው፣ ውሃውን ወደ ወይነጠጅ እንደለወጠው፤ አንዳርጋቸው ጽጌ ወስመ ጥምቀቱ ዘእየሱስ ዛሬ በመንፈስ ከፍታ ላይ ሆኖ ፓትሪያርኩን ጨምሮ ጥቃቅኖቹን ጭንጋፎች በማይክሮስኮፕ ያያቸዋል።

Friday, October 27, 2017

አቶ ኃይለማርያም መንግስት የአባ ዱላ ገመዳን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ እየመረመረው ነው አለ source zehabesha


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አቶ አባዳላ ገመዳ ያቀረቡትን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ እየመረመረው ይገኛል አሉ፡፡ በተቃራኒው ደግሞ አቶ በረከት ስምዖን ያቀረቡትን የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ መንግስት እንደተቀበላቸው ተናግረዋል፡፡ በዛሬው ዕለት በኢህአዴግ ፓርላማ ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ እሳቸው በተገኙበት የአዲስ አፈ ጉባኤ ምርጫ ይካሔዳል ተብሎ ተጠብቆ ነበር፡፡ ሆኖም ባልታወቀ ምክንያት ምርጫው እንዲራዘም ተደርጓል፡፡
አፈ ጉባኤ አባዱላ ገመዳ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ያስገቡት ከአቶ በረከት ስምዖን ቀደም ብለው ቢሆንም፣ የእሳቸው ጉዳይ ተቀምጦ የአቶ በረከት ጥያቄ ተቀባይነት አግኝቷል ተብሏል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለዚህ እንደ ምክንያት የሰጡት ደግሞ፣ አቶ በረከት ከዚህ ቀደምም ተደጋጋሚ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ማቅረባቸውን ነው፡፡ የአባ ዱላ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ግን የመጀመሪያው በመሆኑ፣ መንግስት እየመረመረው ወይም እየመከረበት ይገኛል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አቶ አባዱላ ገመዳ የስልጣን መልቀቂያ ጥያቄ ያቀረብኩት ‹‹የህዝቤ እና የድርጅቴ ጥቅም ስለተነካ ነው፡፡›› ማለታቸው አይዘነጋም፡፡ አቶ አባዱላ ገመዳ አሁንም በስራቸው ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ከመቼ ጀምሮ ከስራቸው እንደሚሰናበቱ የታወቀ ነገር የለም፡፡ መንግስት ያቀረቡትን ጥያቄ መርምሮ መቼ ምላሽ እንደሚሰጣቸውም ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የገለጹት ነገር የለም፡፡ በአሁን ሰዓት በገዥው ፓርቲ ውስጥ ከፍተኛ መከፋፈል የተፈጠረ ሲሆን፣ አለመደማመጥ መስፈኑም እየተገለጸ

“በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ላለ ሰው ትንቢት አትናገር !” – ዳንኤል ሽበሽ source zhabesha

ዛሬ ጥቅምት 16 ቀን፡ 2010 ዓም ጠቅላይ ሚኒስትራቸው የፕ/ት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ለሕ/ተ/ም ያደረጉትን መክፈቻ ንግግር ተከትለው የሰጡትን ማብራሪያ (brief) አዳመጥኩኝ ፡፡ አንድ ሪፖርት የሚቀዳው ከዕቅድ እስከ ድርጊት ካለው ክፍል ውስጥ መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ ካልዋሸን ወይም ካልተሳሳትን በስተቀር ሪፖርት እውነት መሆን አለበት ፡፡ ከዚህ ሀሳብ ስንነሳ አንገት ስላስደፋን የመንግሥታቸው ሪፖርት ለፓርቲያቸው አባላት (ለፓርላማው) አቅርበውታል ፡፡ የማብራሪያቸው ይዘት ለኔ በብዙ ውሸቶችና በጥቂት አጃቢ እውነታዎች የታጨቀ ነበር ፡፡
እጅግ የመሰጠኝ ግን በፖሊስ አባላት ላይ የሰነዘሩት አስተያየት ነው፡፡ በተለይ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል ስለተፈጠረው ቀውስ በተመለከተ በቀውሱ ውስጥ የተሳተፉ የፖሊስ ሠራዊት የአመለካከት ችግር እና ኪራይ ሰብሳቢ ጥገኞች ናቸው በማለት ነበር የገለጹት ፡፡ እኛ ባለን መረጃ ግን የፖሊስ አባላት አፈሙዙን ወደ መንግሥትና መንግሥት ፖለቲካል አቅጣጫ ላይ ማዞራቸውን እንጂ አንዱ ሌላውን ሕዝብ ለማጥቃት አይመስለኝም ፡፡ ክቡርነታቸው (አጎቴ lol) እንዳሉትም ከሆነም ማለቴ ነው፡፡
“ልጅን ለማረም አስቸጋሪ የሚሆነው ችግሩ ከወላጆቻኀው ጋር ሲኖር ነው” እንደሚባለው ሁሉ የፖሊሶቹ ችግር ነው የተባለው ችግርም የሚቀዳው ከተቀረጹበት ከአብዮታዊ ዴሞክራሲ አለመለካከታቸው መሆኑ ግልጽ ነው ፡፡ በሊብራል አስተሳሰብ ቢቀረጹ ኖሮ ሊብራልና ዴሞክራቲክ ይሆኑ ነበር እንደ ማለት ፡፡ እንደሚታወቀው ፖሊሶቹ (ልዩ ኃይል) ዕድሜ ክልላቸውን ብናይ እንኳ የሩብ ምዕተ ዓመታት ውጤቶች ናቸው፡፡ በኢሠፓ ወይም በኢህአፓ ማላከክ የሚቻል አይመስለኝም፡፡ ፖሊሶቹ ኪራይ ሰብሳቢ፤ ፀረ ዴሞክራቲክ ወዘተ ከሆኑ ተጠያቂው አሳዳጊዉም ጭምር እንጂ ታዳጊዉ ብቻ አለመሆኑ ሊሰመር ይገባል ፡፡ አሳዳጊው የትግራይ ነፃ አውጪ እና የእጁ ሥራው #አዴ ናቸው ፡፡ የአንድ ወንዝ ምንጩ በየጊዜው ድፍርስ ከሆነ ወራጁ ውሃው እንደት ሊጤራ ይችላል ? ውሃው እንዲጠራ ከተፈለገ የግልና የጋራ ጥረት ያስፈልገዋል ፡፡ በሁሉም በኩል ጥረቱም ትግሉም አሁን የተጀመረ ይመስለኛል ፡፡
ፖሊሶቻችን የኛ ናቸው ፡፡ እንደ ማንኛው ሰው ሁሉ ዕኩልነትንና ፍትሐዊነትን ይፈልጋሉ ፡፡ እንደ ዜጋ ፍትህንና ዘላቂ ተጠቃሚነትን ይናፍቃቸዋል ፡፡ ጥሩ ኑሮ መኖር ይፈልጋሉ ብቻም ሳይሆን ያስፈልጋቸዋልም፡፤ በሰው’ ታቸውም በማዕረጋቸውም መከበርን ይፈልጋሉ ፡፡ ያሠማራቸው ሥርዓቱ ከሕዝብ ጋር ባጣላቸው ቁጥር እንደተጣሉ መኖር አይፈልጉም ፡፡ ማንም ተራ ዜጋ እንደሚረዳው በሀገራችን ለተራ እግረኛ ወታደር ይቅርና ለትላልቆቹ ለባለ መሥመር መኮንኖችም ካለው ክብር ይልቅ ለአንድ ቻይናዊ ጉልበት ሠራተኛ ያለው ክብር ይልቃል ፡፡ ለአንድ ኢንስፔክተር፣ ሱፐርኢንተዳንት፣ ኮሎኔልና ወዘተ ከሚሰጠው ሥፍራ ይልቅ ለተራ ጆሮ-ጠቢ ያለው ታአማኝነት ጎልቶ ይታያል … ፡፡ በኀወሓት ዕዝ ሰንሰለት ሥር ተጠርንፈው የሚተነፍሱበትን አጥተው መኖራቸውን ለማንም ግልጽ ነው ፡፡ ነጋ ጠባ ግምገማ ተብየ አውጫጭን ያረሩ ፖሊስ አባላት’ኮ ሁሌም አንገት ደፍተው ይኖራሉ ማለት ለኔ ይከብደኛል ፡፡ ሰዎች ናቸውና አንድ ቀን <… ግን ለምን?…> ብለው መጠየቃቸው አይቀረ ነው ፡፡

በላይ ላያቸው የተቆለሉትና በድሃው ገበሬ ልጅ ደምና በመሬታቸው ቱጃር የሆኑ ዛሬ ላይ የጨዋታ ህጋቸውን ወደ #ቢሊዮኖች ቤት ከፍ ሲያደርጉ (የሠራዊቱን አዛዦችንም ይጨምራል) እነዚህ ሚስክኖቹ ደሞ የታክሲ ሣንትም ጭምር አጥተውና ተርበው በየመንደሩ ሲያዛጉ እንደት ስለሰላም ሊያወሩ ይቻላል? ግዙፉ ሕገመንግሥት ይቅርና የቅርቡን የአለቃ ትዕዛዝ እንደት ብለው ያከብራሉ?፤ ጠ/ሚሩ እንዳሉት ከሆነም ማለቴ ነው ፡፡ በከባድ ሀዘን ውስጥ ላሌ ሰው ትንቢት አትናገር ይባል የለ!? በከባድ አስተዳደራዊ ጭቆና ውስጥ ያለ ሰራዊት፤ የቤት መክፈያ አጥቶ በየካምፑ የሚከራተት ነው ፡፡ የልፋታቸውን ዋጋ በአንፃራዊነት እንኳ መቅመስ ያልቻለ ሠራዊት ፤ ስለ ሰብዓዊነት እየተሰበከላቸው ግን ሰብዓዊ ክብራቸውን ለተነፈጉ ሠራዊት፤ በቅድሚያ ሕገ መንግሥቱን ለመጠበቅም በሕገ መንግሥቱ የተደነገጉ መብቶቻቸው መጠበቅ ይገባል ባይ ነኝ ፡፡ እንዲያውም የሀገራችን ፖሊሶች በባሕልና በሃይማኖት ተፅዕኖ ውስጥ ያደጉና የኖሩ መሆኑ በጀን እንጂ፤ በሥርዓቱ ከሚደርሰባቸው በደል ልክ ቢሆን ኖሮ ምን ሊመፈጠር እንደምችል መገመት አያቅትም ፡፡
በደርግ ጊዜ ከነበረው ከኢት/ያ ሠራዊትም እንዳየነው ከሆነ፤ ቢቸገር ቢቸገር እንኳ መሣሪያ ቢሸጥ ወይም ቢለምን እንጂ መሣሪያውንና ሙያውን ተጠቅመው በእኩይ ተግባር ላይ የማይሳተፍ ነው ፡፡ ይህ ከኢት/ዊ ጨዋነት፣ ከአስተዳደጋቸውና ከግላዊ ባሕርያቸው የሚመነጭ እንጂ ከሙሰኛው፤ ከጨቋኙ፤ ከዘረኛው እና እንዲተኩሱት ከሚያዘው ኃይል አስተሳሰብ የሚመነጭ አይደለም ፡፡ በርግጥ ከሠራዊቱ በኩል ወደ ሕዝቡ ይተኮስ የነበረው ጥይት ለምንና እንደት እንደሆነም አይጠፋብንም ፡፡ ከዚህ በኀላ ግን ሕዝቡም የሠራዊቱ፤ ሠራዊቱም የሕዝቡ ነው !!
በ2005 ዓም በአንዱ ጹሁፌ ላይ ርዕስም ትኩረትም ያደረኩት <ለፖሊስና ለመከላከያ ሠራዊቱ ማን አለላቸው?> የሚል ነበር ፡፡
የጠ/ሚ ኃ/ማርም ንግግር የሀገራችንን ነባራዊና ወቅታውዊ ሐቁን ያላገናዘቤ፤ እውነታውን በደንብ ያልዳሰሰ ነበር ፡፡ ሰላም !!

Thursday, October 26, 2017

የሰው ሕይወት የተቀጠፈበት የአምቦ የተቃውሞ ውሎ በቢቢሲ ዘገባ source zehabesa

በግጭቱ ቢያንስ 10 ሰዎች እንደተገደሉ የአይን እማኞች ይናገራሉ
(Photo credit – BBC)
ስለአምቦው ውሎ የቢቢሲ ዘገባ እንደወረደ:-
በስልክ ያነጋገርናቸው የአምቦ ከተማ ነዋሪዎች እንደነገሩን ስኳር ጭነው በከተማው የሚያልፉ መኪኖች እንዳሉ መረጃ ለአካባቢው በመድረሱ ፤ መኪኖቹን ለማስቆም በመጠባበቅ ከትናንት ጀምሮ መንገድ መዝጋት ጀምረው ነበር።
ምክንያታቸው ደግሞ በሀገሪቱ የሚታየው የስኳር እጥረት በአምቦም የሚስተዋል መሆኑ ነው።
በከተማዋ አንድ ኪሎ እሰከ 70 ብር ድረስ ይሸጣል ይላሉ።
እናም በዚህ ሁኔታ ስኳር ተጭኖ ወደሌላ ቦታ መሄዱን በመቃወም ነው መንገድ መዝጋት የጀመሩት።
” ከተማዋን አቆርጠው የሚሄዱ ዋናና መጋቢ መንገዶች በመዘጋታቸው የክልሉ ፖሊስና እኛ ሆነን በህገወጥ መንገድ ሊያልፍ የነበረውን ስኳር ስንጠብቅ አድረናል”ይላሉ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለገ አንድ የአካባቢው ነዋሪ።
ዛሬ ግን ከማለዳው አንድ ሰዓት አካባቢ የፌደራል ፖሊስና የመከላከያ ሰራዊት መለያ የለበሱ በተቃዋሚዎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ቢያንስ 10 ሰዎች መገደላቸውን ተናግሯል።
“እኔ በአይኔ ያየሁት አምስት ሰዎች ሲገደሉ ነው።ግን የሞቱት በጣም በርካታ ሰዎች ናቸው” ያለን ደግሞ ሌላው የከተማዋ ነዋሪ ነው።
” ሁለት የፌደራል ፖሊስ ልብስ የለበሱ በድንጋይ ተደብድበው እንደሞቱ አይቻለሁ” ብሎናል።
ቢቢሲ ግን የሟቾቹን ትክክለኛ ቁጥር ለማረጋገጥ አልቻለም።
ከግጭቱ ጋር ተያይዞ በንብረት ላይም ጉዳት የደረሰ ሲሆን የዳንጎቴ ሲሚንቶ ፋብሪካ ንብረት የሆኑ ሁለት የጭነት መኪናዎች ተቃጥለዋል።
በከተማዋ ስኳር እንዳይዘዋወር መንገዶች እንዲህ ተዘግተዋል
የአሮሚያ ክልል የመንግስት ቃል አቀባይ አቶ አዲሱ አረጋ በፌስ ቡክ ገጻቸው የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በሌሎች ሰዎች ላይም የአካል ጉዳት መደረሱን የሚገልጽ መረጃ አስፍረዋል።
” ከሰላማዊ ሰልፍና ከስኳር ፍተሻ ጋር በተያያዘ ወጣቶችን በማነሳሳትና ስርዓት አልበኝነት እንዲስፋፋ በማድረግ ለግጭቱ መንስዔ የሆኑትን አካላት እናወግዛለን” ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ከተማዋ በአንጻራዊነት የተረጋጋች ትመስላለች፤ ነገር ግን መንገዶች እንደተዘጉ ሲሆን ሰልፈኞቹም ወደየቤታቸው አልተመለሱም።
ከዚህም የተነሳ ብዙዎች አሁንም ተጨማሪ ጉዳት ሊደርስ የሚችል ስጋት እንዳላቸው ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የሀገሪቱ ጦር እና ደህንነት የህወሓትን ስልጣን በማዳን ስራ ላይ አተኩሯል source zehabesha

(ቢቢኤን) በኢትዮጵያ የሚገኙው ማንኛውም ዓይነት ጦር እና የደህንነት አካል የህወሓትን ስልጣን ለመታደግ አተኩሮ እየሰረ እንደሚገኝ ምንጮች ጠቆሙ፡፡ የሀገሪቱ የደህንነት እና የመከላከያ ሰራዊት ቁልፍ ቦታዎች በህወሓት እጅ ውስጥ እንደመገኘቱ፣ የፓርቲውን ዕድሜ ለማራዘም ከመቼውም ጊዜ በላይ እየተሰራ እንደሚገኝ ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡ ለዚህም ሲባል መደበኛ ስራቸው ሀገር መጠበቅ የሆነ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ህዝባዊ ተቃውሞ በተነሳባቸው ቦታዎች ጭምር እየሔዱ በህዝብ ላይ ጥቃት እየፈጸሙ እንደሚገኙ መረጃዎች በመጠቆም ላይ ናቸው፡፡

ከሁለቱ አካላት በተጨማሪ ደግሞ በህወሓት ርዕዮተ-ዓለም ቅርጽ የተመሰረተው የአጋዚ ጦርም እንደተለመደው፣ የስርዓቱን ዕድሜ ለማስቀጠል ግድያን ጨምሮ ማንኛውንም ዓይነት አረመኔያዊ እርምጃ እየወሰደ ይገኛል፡፡ የኦሮሚያ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ከነበረው አኳኃኑ የተወሰነ መሻሻል ማሳየቱ እና ለተቃውሞ አደባባይ ከሚወጡ ሰዎች ጋር መግባባት መፍጠሩ ህወሓትን አላስደሰተውም ይላሉ- ታዛቢዎች፡፡ ለዚህም ሲባል የአጋዚ ጦር ተቃውሞ በሚነሳባቸው የኦሮሚያ ከተሞች እየገባ ግድያ እንዲፈጽም እየተደረገ ይገኛል ብለዋል-ታዛቢዎቹ፡፡
የህወሓት መንግስት ጀምበር እየጠለቀችበት እንደሚገኝ የሚናገሩ አስተያየት ሰጪዎች፣ ስርዓቱ የባከነ ሰዓት ላይ የሚገኝ እንደመሆኑ ማንኛውንም ዓይነት እርምጃ ከመውሰድ እንደማይመለስ ያክላሉ፡፡ ቀስ በቀስም ሀገሪቱን ወደ ወታደራዊ ስርዓት ሊወስዳት እንደሚችልም አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ በተለይ በህወሓት እጅ የሚገኙት ዋና ዋና የደህንነት እና የመከላከያ ቦታዎች፣ አሁን ላይ ስርዓቱ እንዴት ብሎ ከመጣበት ህዝባዊ መዓት ማምለጥ እንዳለበት በሰፊው እየመከሩ እንደሆነ ከምንጮች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ በየቀኑ እየተካሔዱ ባሉ ተቃውሞዎች የተነሳ ፋታ ያጣው የህወሓት መንግስት፣ አሁን ላይ ሌሎችን ገድሎ ራሱን ለማዳን እየተፍጨረጨረ ይገኛል፡፡

Tuesday, October 24, 2017

የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ከህዝባዊ ተቃውሞ ጋር በተያያዘ ዶክመንተሪ ፊልም ሊሰራ ነው

የገዥው ፓርቲ ልሳን የሆነው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዶክመንተሪ ፊልም ሊሰራ መሆኑን ምንጮች ጠቆሙ፡፡ ዶክመንተሪው የሚያተኩረው ሰሞኑን በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተካሔዱ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ ሲሆን፣ ፊልሙ ህዝቡ ያነሳውን የነጻነት ጥያቄ ሌላ መልክ ሰጥቶ ጥላሸት የመቀባት ዓላማ እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የገባው የህወሓት መንግስት፣ በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተስተዋለ የሚገኘው የብሔረሰቦች አብሮ የመታገል ሁኔታ በእጅጉ እያስፈራው እንደመጣ ይነገራል፡፡ ቡድኑ ይህን ሁኔታ ለመሰባበር ወይም የአንድነቱን ጉዞ ለማሰናከልም ደፋ ቀና እያለ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ህዘቡ የመብት ጥያቄውን እያቀረበ የሚገኘው በግልጽ እና በማያሻማ መንገድ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በኩል ሊሰራ የታቀደው ዶክመንተሪ ፊልም ግን፣ አንዱ ብሔር በሌላው ላይ በጠላትነት እንደተነሳ ተደርጎ ለማቅረብ ታቅዷል፡፡ ለዚህ ዓላማ ሲባልም አስቀድሞ በሰልፎች ውስጥ ጣልቃ እንዲገቡ ተደርገው፣ ሰልፉ ሌላ ዓላማ ያነገበ እንዲመስል ጥረት እያደረጉ ያሉ ካድሬዎች መኖራቸው ታውቋል፡፡ የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ፣ በተደጋጋሚ በሰጠው መግለጫ፣ ሰልፎቹን ወደ ሁከት ለመቀየር ሲሞክሩ የነበሩ ሰዎች ተያዙ የሚል ቃል ሲደጋግም ቆይቷል፡፡ ይህም የፊልሙ አንድ ግብዓት መሆኑንም የመረጃ ምንጮች ይጠቁማሉ፡፡
የተቃውሞ ሰልፍ በተካሔደባቸው የኦሮሚያ ከተሞች፣ ቪዲዮ ካሜራ የያዙ የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሰራተኞችን መመልከታቸውንም የዓይን እማኞች ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ በየከተሞቹ የተደረጉ ሰላማዊ ሰልፎችን ቀርጾ ያስቀመጠው የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን፣ በቀጣይም ሁከት ተነስቶባቸዋል በተባሉ የተቃውሞ ሰልፎች ላይ በመመስረት አዲስ ፊልም ሊሰራ ማቀዱን ከመረጃዎች ገለጻ ለመረዳት ተችሏል፡፡ ቴሌቭዥን ጣብያው ከዚህ ቀደም የተለያዩ አካላትን እና ሰዎችን ስም ለማጥፋት ዶክመንተሪ ፊልም ሲሰራ መቆየቱ ይታወሳል፡፡ ጣብያው ምንም እንኳን ፊልም የመስራት አባዜ ቢኖርበትም፣ የሰራቸው ፊልሞች ግን አንድም ቀን በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት አግኝተው እንደማውቁ ታዛቢዎች ይናገራሉ፡፡

Monday, October 16, 2017

አባዱላ ገመዳ የለቀቁበትን ምክንያት በዝርዝር አስረዱ source zehabesha

ምክንያት በዝርዝር አስረዱ
 



ከላይ በቀረበው የአባዱላ ንግግር ላይ ጋዜጠኛ ጌታቸው ሸፈራው የሚከተለውን ምላሽ ሰጥቷል::
ስለ ኦህዴድ ብዙ ብዙ እየተባለ ነው። አባዱላ የህዝብና ድርጅት ክብር ስለተነካ ለቅቄያለሁ ብሏል። በመሰረቱ የህዝብ ክብር አሁን አይደለም የተነካው። ብዙ ሳንርቅ በ2008 እነ አባይ ፀሃዬ፣ እነ ጌታቸው ረዳ በህዝብ ላይ ምራቅ ሲረጩ እነ አባዱላ ጭጭ ብለው ነበር። ዛሬ ነቃን፣ መረረን፣ በዛ ካሉም መልካም ነው።
በ2008 የተነሳው ህዝባዊ ንቅናቄ ትንፋሽ ሲያሳጣቸው ሚዲያውን መግለጫ በመግለጫ አድርገውት ነበር። በዋነኛነት ችግሩ የህዝብ ሳይሆን የኢህአዴግ ነው ብለዋል። ይህን ብለው ግን በዚሁ ንቅናቄ ሰበብ የታሰሩትን አልፈቱም። እንዲያውም የሀሰት ክስ ቀርቦባቸዋል። የኢህአዴግ ችግር ነው በተባለው ጉዳይ የሀሰት ክስ ከቀረበባቸው መካከል እነ አቶ በቀለ ይገኙበታል!
እነ አቶ በቀለ የቀረበባቸውን የሀሰት ክስ ተከላከሉ ተብለው ለጥቅምት 27፣ 28 እና 29 ቀጠሮ ተይዟል። ለዚህ የሀሰት ክስ በምስክርነት የጠሩት ደግሞ ችግሩ የህዝብ ሳይሆን የእኛ ነው ብለው ህዝብን ይቅርታ የጠየቁትን እነ አባዱላ ገመዳ እና እነ ለማ መገርሳን ነው!
እነ አቶ በቀለ የተከሰሱት እነ አባዱላ ገመዳ ክብሩ ተነክቷል ያሉትን ህዝብ አነሳስታችሁዋል፣ አሳምፃችሁዋል ተብለው ነው። ጥቅምት27፣ 28ና 29 እነ በቀለ የሚያስመሰክሩት ለራሳቸው ብቻ ሳይሆን በገዥዎቹ ስለተፈረጀው፣ ሽብር፣ አመፅ ፈጥሯል ተብሎ ለሚከሰሰው፣ አሁንም በየ ፍርድ ቤቱ ስሙ ሲነሳና ክብሩ ሲነካ ለሚውለው ህዝብ ነው!
እውነት እነ አባዱላ ፣ እነ ለማ ስለ ህዝብ ክብር ካሰቡ ጥቅምት 27፣ 28ና 29 ፍርድ ቤት ቀርበው እውነታውን፣ ቢያንስ ያኔ መግለጫው ላይ የሰጡትን ቃል ማስረዳት ይጠበቅባቸዋል! ባለስልጣናት በምስክርነት ተጠርተው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተልኮላቸዋል ተብሎ ያልቀረቡበት ጊዜ አለ።
ሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያው ብዙ ለተባለላቸው የኦህዴድ ፖለቲከኞች ጥቅምት 27፣ 28ና 29 ከባድ ፈተና ይገጥማቸዋል! የመጀመርያው ለምስክርነት መቅረብ አለመቅረባቸው ነው! አይቀርቡም እንጅ ከቀረቡ ለመስቀለኛ ጥያቄው ከአሁኑ ፀሎት፣ ምህላ ማስደረግ ይጠበቅባቸዋል! ምክንያቱም ምስክርነቱ ከህዝብ ወይንም ከትህነግ ጋር እንደሚያቀያይማቸው እሙን ነው!

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከ እስር ከተፈታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃለምልልስ ሰጠ – “እናቴን በደህና በማግኘቴ ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል


ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከእስር ከተፈታ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ቃለምልልስ ሰጠ – “እናቴን በደህና በማግኘቴ ከፍ ያለ ደስታ ተሰምቶኛል”

Thursday, October 5, 2017

ተመድ የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር አቶ አንዷለም አራጌ እንዲፈታ ጠየቀ


የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራር የነበረው አቶ አንዷለም አራጌ እንዲፈታ ጠየቀ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት አቶ አንዷለምን ያሰረው ዓለም ዓቀፍ ድንጋጌዎችን በመጣስ እንደሆነ የገለጸው ተመድ፣ በመሆኑም መንግስት ፖለቲከኛውን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ አሳስቧል፡፡ ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ ላይ እንደገለጸው ከሆነ፣ አቶ አንዷለም አራጌ ለእስር የተዳረገው ያለ ምንም ጥፋት እና በደል ነው፡፡
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የእስረኞችን ጉዳይ የሚከታተለው ቡድን ባወጣው መግለጫ ላይ፣ የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብር አዋጁን በመጠቀም ህጋዊ የፖለቲካ ሰዎችን እያጠቃ እንደሚገኝ ገልጿል፡፡ መግለጫው ይቀጥልና፣ አቶ አንዷለም አራጌ ለእስር የተዳረገውም የጸረ ሽብር ህጉን በመቃወሙ እንደሆነም ያትታል፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ አቶ አንዷለም አራጌ ብቻ ሳይሆን ባልንጀሮቹ ጭምር ከእስር እንዲፈቱ የኢትዮጵያ መንግስትን አሳስቧል፡፡
በኢትዮጵያ የሚገኘው ስርዓት እጅግ አስከፊ መሆኑ በተለያየ ወቅት ሲገለጽ ቆይቷል፡፡ ይህን ጉዳይ የሀገሬው ህዝብ ብቻ ሳይሆን ዓለም ዓቀፍ ተቋማት እና መንግስታት ጭምር እየመሰከሩት ያለው ሐቅ ከሆነም ሰነባብቷል፡፡ በሕወሓት የሚመራው ይኸው ስርዓት፣ ለስልጣኑ የሚያሰጉትን ፖለቲከኞች ሁሉ እስር ቤት አስገብቷል፡፡ ከአንጋፋ ፖለቲከኞች ጀምሮ ገና ወጣት የሆኑ ፖለቲከኞችን እስር ቤት በማስገባት እየተበቀላቸው የሚገኘው አገዛዙ፣ ሰብስቦ ባሰራቸው ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ታጋዮች የተነሳ ከዓለም ዓቀፍ የመብት ተከራካሪዎች ከፍተኛ ውግዘት እየገጠመው ይገኛል፡፡