Monday, September 19, 2016

የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለስድስተኛ ጊዜ ወደ መስከረም 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ተዛወረ።



Image may contain: outdoor and one or more people
የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለስድስተኛ ጊዜ ወደ መስከረም 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ተዛወረ።#Ethiopia #Gonder #AmharaResistance #MinilikSalsawi
ለዛሬ ተቀይሮ የነበረው የኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ የፍርድ ቤት ቀጠሮ ለስድስተኛ ጊዜ ወደ መስከረም 18 ቀን 2009 ዓ.ም. ተዛወረ። በጎንደርና በባህር ዳር በቤት ውስጥ የመዋል አድማው እደቀጠለ ነው።
ከኮሎኔል ደመቀ ቀጠሮ ጋር ተያይዞ የግፍ ሒደቱን [የፍርድ ሒደቱን ላለማለት ነው] ለመከታተል የወጡ የጎንደር ወጣቶችን ለመግደልና ለማሳደድ የትግራይ TPLF ወታደሮች ከተማውን አጥለቅልቀውታል።
በተያያዘ ዜና በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፋሽስት ወያኔ ሊያካሂደው የነበረው የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጉባኤ ሳይካሄድ ቀርቷል። ጉባኤው የተቋረጠው ሁሉም የጎንደር ዩኒቨርሲቲ መምህራን ስብሰባውን ቦይኮት በማድረጋቸው ነው። ሁሉም አማራ በአንድነት የአባቶቹን የጀግንነት ታሪክ ይደግማል። ከታች ያለው ፎቶ የትግራይ ነፍሰ በላ ወታደሮች በጎንደር ከተማ የንጹሀንን ደም ለማፍሰው ሲዘዋወሩ የሚያሳይ ነው።

No comments:

Post a Comment