Monday, September 26, 2016

አቡነ አብርሀም ታሪክ ሰሩ! ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል።



Image may contain: 1 person , beard
አቡነ አብርሀም ታሪክ ሰሩ! ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። #Ethiopia #Meskel #BahrDar #AmharaResistance #MinilikSalsawi
የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ጳጳስ አቡነ አብርሐም ታሪክ ሰሩ። ከፋሽስት ወያኔ ነፍሰ በላዎች ፊት ለፊት እውነትን ተጋፍጠዋል። ጳጳሱ የደመራ በዓሉ ላይ ባደረጉት ንግግር ህዝባዊ ብሶቱን አስተጋብተዋል። እንዲህም አሉ…
«ችግር የሚፈጠር በመሪ እንጅ በተመሪ አይደለም፤ የህዝቡ ጥያቄ መመለስ አለበት፤ ወታደር ከዚህ በኋላ የሰላምን ምላጭ እንጅ የመሳሪያን ምላጭ መሳብህን አቁም፤ በየ ሀገሩ በስደት ያለው ወገናችን መመለስ አለብት፤ እኛ አባቶች የምናገረውን በተገቢው መልኩ ለህዝብ የማታቀርቡ የመንግስት ሚድያ ካላስተካከላችሁ ከዚህ በኋላ አደባባዩ አትገቡም ፤ ያለ በደላቸው የታሰሩት ወንድሞቻችን መፈታት አለባቸው፤ ጠላትን እንዳላንበረከኩ አባቶቻችን ፤ዛሬ ለምን እርስ በእርስ ተከፋፈልን?፤ መንግስት የተሸከምነው መሳሪያ ከክርስቶስ መስቀል አይበልጥም፤ ወታደሮችና ድንበር ጠባቂዎች ስለ እናንተ ቤተክርስቲያን ስለምትጸልዩ የሷ ልጆች ናችሁና ደም አታፍሱ» ብለዋል። ህዝብ ክርስቲያኑ አቡነ አብርሀም ይንን ንግግር ሲያደርጉ በእልልታና በጭብጨባ ድጋፉን ገልጧል።
ባህር ዳር ላይ «የተከበረው» የደመራ በዓል ጸሎትና ሀዘን ታስቦ ውሏል። የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቱ ወረብ፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ደግሞ ወቅቱን የተመለከተ መዝሙሮችን አቅርበዋል። የበገና ደርዳሪው እንዲህ ብሏል፦
«ማዕበሉን አይቶ ልባችን አይፍራ፣
“ሁሉን ቻዩ አምላክ አለ ከኛ ጋራ፤ የሚል ነበር።
በመጨረሻም በየቤተክርስቲያኑ ይደረግ የነበረው የምህላና ጸሎት በጋራ መሀል ባህር ዳር ከተማ መስቀል አደባባይ ተስተጋብቷል። አባታችንን አቡነ አብርሀምን፣
የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንቶቻችንን፣የሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎችን፣ የማኅበረ ቅዱሳንና የቅዱስ ያሬድ የበገና ተማሪዎችና መዘምራን ቃለ ህይወት ያሰማልን። ረጅም እድሜ ይስጥልን።
ሁሉም መርሀ ግብር ካለቀ በኋላ አቡነ አብርሐም መጀመሪያ «ሕዝቡ ወደቤቱ ሳይገባ እኔ አልንቀሳቀስም» በማለታቸው እዚያው መስቀል አደባባይ ከቀሩ በኋላ፤ በመጨረሻ ላይ የአማራ ፖሊስ ዩኒፎርም በለበሱ የትግራይ ወታደሮች ከታት በሚታየው መልኩ በፖሊስ መኪኖች ታጅበው እሳቸው ግን በእግራቸው ወደ ባዕታቸው ተመልሰዋል።

No comments:

Post a Comment