Wednesday, August 31, 2016

አሜሪካ የአደራ መንግስት ስለማቋቋም ከተቃዋሚዎች ጋር ተማከረች



አትላንቲክ ካውንስል ለአፍሪካ Atlantic Council for Africa የተሰኘው የአሜሪካ የመንግስታትና የአለም አቀፍ ተቋማት ምክር ቤት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ሊቀመንበርና የመድረክ ም/ሊቀመንበር ዶ/ር መረራ ጉዲናን እና የሰማያዊ ፓርቲን ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነትን በማነጋገር ላይ ናቸው። ለስብሰባ የተጠሩት በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው አሳሳቢ የፖለቲካ ቀውስና ሀገሪቷን ያለምንም አማራጭ የፖለቲካ አመለካከት በወታደር ሀይል በመቆጣጠር በውጥረት ላይ ስለሚገኘው የኢህአዴግ ስርዓት ማብራሪያ ሰጥተዋል። የዩናትድ ስቴትስ መንግስት ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዴሞክራሲና የሰብዓዊ መብት ችግር እና በተለይ በነፃ ሚዲያውና ተቃዋሚዎች ላይ ሰለሚደርሰው ወከባ ሙሉ ግንዛቤ እንዳለው አሳውቀዋል።

በስብሰባው ለይ ከተገኙትና ስማቸው በተቋሙ ይፋ ከሚደረጉት መካከል በዩናይትድ ስቴትስ የወጪ ጉዳይ አማካሪዎች፣ የፔንታጎን መካላከያ አማካሪዎች፣ የፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ የጸጥታ ዋና አማካሪ በቦታው የተገኙ ሲሆን በቦታውም ሌሎች የአሜሪካን ምሁራን ተገኝተዋል። ከዚህ በፊት ስማቸው የሚታወቁት አምባሳደር ዴቪድ ሺን፣ ሃርማን ኮኸን እና የግጭትና ስትራቴጂ ምሁር Terrence Lyons (Conflict Analysis and Resolution expert) እና ሌሎች ስማቸው እንዳይጠቀስ የሚፈልጉ ዲፕሎማቶች በቦታው ተገኝተዋል። የውይይቱ ርዕስ ያተኮረው ዩናይትድ ሰቴትስ ከኢትዮጵያ የሚታገኘው ስትራቴጂክና ወታደራዊ ጥቅሞች ሳይነኩ እንዴት አዲስ የአደራ መንግስት (Caretaker Government) ለማቋቋም እንደታሰበና በሂደት በምን አይነት ሁኔታ ሰላማዊ የስልጣን ክፍፍልና ሽግግር ማድረግ እንደሚቻል ለመምከር መሆኑን ምንጮቹ ገልጸዋል። መረጃውን ምክር ቤቱ በከፊል ይፋ እንደሚያደርገው ተነግሯል።

Image result for Atlantic Council for Africa

ከባድ መሳሪያ አይደለም ከአይሮፕላን ቦምብ ቢዘንብ ለውጥ አይቀርም ፡፡” የአዲስ አበባ ሕዝብ



ከባድ መሳሪያ አይደለም ከአይሮፕላን ቦምብ ቢዘንብ ለውጥ አይቀርም ፡፡” የአዲስ አበባ ሕዝብ
በ11ኛው ሰዓት አጣብቂኝ ውስጥ የገባው በፍርሃት የተወጠረው ሕወሓት በአዲስ አበባ መንገዶች ከባድ መሳሪያዎችን ቢኮለኩል የአዲስ አበባ ሕዝብ ከመጨረሻዎቹ የደርግ ውድቀት ጋር በማመሳሰል ታሪክ ራሱን ደገመ ብሏል ። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)
Mereja.com's photo.
Mereja.com's photo.
Mereja.com's photo.

የኢትዮጵያ ነብሮች ሲበሳጩ ያጉረመርማሉ!



ከፕሮፌሰር አለማየሁ ገብረማርያም 
ትርጉም በነጻነት ለሀገሬ 
Cheetah 14አሜሪካውያን የጀግንነት በላይነት የላቸውም፣  ማለትም  የኦሎምፒክ ጀግንነት ጠቅላይነት፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 የ26 ዓመቱ የኢትዮጵያ የረዥም ርቀት ማራቶን ሯጩ ፈይሳ ሌሊሳ በአንድ ወቅት በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክ “የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የፖለቲካ እንቅስቃሴ መግለጫ መድረኮች ሊሆኑ አይችሉም” በማለት ይገለጽ የነበረውን ሕግ ወደ ጎን አሽቀንጥሮ በመጣል በሪዮ ኦሎምፒክ ውድድር አስደናቂ የሆነ ታሪካዊ ድርጊትን ደግሟል፡፡
እ.ኤ.አ ጥቅምት 16/1968 በሜክሲኮ ኦሎምፒክ ተደርጎ በነበረው የ200 ሜትር የአጭር ርቀት የሩጫ ውድድር ቶሚ ስሚዝ እና ጆን ካርሎስ የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ አሸናፊዎች ሆነው ነበር፡፡ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት መድረኩ ላይ አድርገውት የነበረው ታሪካዊ ድርጊት በአሁኑ ጊዜ ትልቅ የመነጋገሪያ አጀንዳ ሆኖ ይገኛል፡፡ የእጆቻቸውን ቡጢዎች ከፍ አድርገው ከራሳቸውበ በላይ ወደ ላይ በማንሳት የጥቁር ሕዝቦችን አይበገሬነት ምልክትነት በይፋ አሳይተዋል፡፡
ፈይሳ ከውድድሩ ማጠናቀቂያ መስመር ላይ ሲደርስ ሁለቱንም እጆቹን አጣምሮ ከእራሱ በላይ ከፍ አድርጎ በማንሳት የኢትዮጵያን ወጣቶች የአይበገሬነት የኃይል ምልክት እንቅስቃሴ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ አሳይቷል፡፡
ይህ ምልክት በዓለም ላይ የሚገኝ 3.5 ቢሊዮን ሕዝብ እንዲመለከተው የተደረገ ነበር፡፡
በዚያች ቅጽበታዊ ኩነት ፈይሳ ከያዘው እውነታ ጋር ተገናኘ፡፡ ያገኘውን የብር ሜዳሊያ ምርጫ ለዝና፣ ለዕድል እና ለታዋቂነት አውሎታል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ምንም ዓይነት የተለየ ችሎታ እንደሌለው እና እንደማንኛውም ተራ የዓለም ሕዝብ ሆኖ የመቀጠል ምርጫ ማድረግ ሲችል አርሱ ግን  የበለጠ ነገር ማድረግ ፈቀደ፡፡
ሆኖም ግን ፈይሳ የኩነቱን አጋጣሚ ለመያዝ መረጠ እና በዚህ መልኩ ተረጎመው፡፡
የኩነቱን አጋጣሚ ለመወሰን ጆሴፍ ካምፕቤል በመጽሐፋቸው እንደጻፉት እና ምዕናባዊ ገጽታን የሚላበሱ በሺዎች የሚቆጠሩ ጀግኖች እንዳሉ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳም ለህይወቱ ዘላለማዊ ጀግና ሆኗል፡፡
ፈይሳ የኢትዮጵያ የጀግንነት አንጸባራቂ ገጽታ ለመሆን በቅቷል፡፡
እጆቹን ከጭንቅላቱ በላይ ከፍ በማድረግ አጣምሮ በመያዝ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን እያቋረጠ በነበረበት ጊዜ ፈይሳ የዓለምን ጀግንነት ነው ያቋረጠው፡፡
ለመሆኑ ፈይሳን ከተራ የማራቶን ውድድር ሯጭነት እንደዚህ ያለውን የጀግንነት እርምጃ ለመውሰድ እና የጀግንነት ስብዕናን እንዲላበስ ያደረገው ምክንያት ምንድን ነው?
መልሱ አየር የመተንፈስን ያህል ቀላል ነው! ሌላ ምንም ሳይሆን የአስተሳሰብ አድማሱን አእምሮውን መለወጡ ብቻ ነው፡፡
ጆርጅ በርናንድ ሻው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ነበር፣ “ያለለውጥ ምንም ዓይነት እድገት ሊኖር አይችልም፣ እናም አእምሯቸውን መለወጥ የማይችሉ ምንም ዓይነት ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም“ ነበር ያሉት፡፡
ፈይሳ በአሁኑ ጊዜ በሀገሩ ውስጥ ስርነቀል ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ በሚገባ ግንዛቤ ወስዷል፡፡ በዚያች ውሱን በሆነች የኩነት አጋጣሚ ፈይሳ በእርሱ ጨቋኞች ጫማ ስር ወድቆ እና ሁለተኛ ዜጋ ሆኖ እየተጨቆነ የእድሜ ልክ ክብር እና ሀብት እያገኘ ከመኖር ይልቅ የአንድ ሴኮንድ ነጻነት ይሻለኛል በማለት አእምሮውን ለውጧል፡፡
በሪዮ የማራቶን ውድድር ፈይሳ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን በሚያቋርጥበት ጊዜ የአትሌቲክሱን ድል አድራጊነት አይደለም ያቋረጠው፡፡ በምንም ዓይነት ይኸ አይደለም!
ሆኖም ግን ፈይሳ ፍርሀትን፣ ተስፋ የማጣት ጨለምተኝነትን፣ ሀዘንን፣ ብስጭትን፣ መጥፎ ዕድልን እና ጥርጣሬን አሽቀንጥሮ በመጣል የድፍረትን፣ የመስዋዕትነትን፣ የዓላማ ጽናት ቁርጠኝነትን፣ የአይበገሬንትን እና የተጨባጭ ተግባርን መስመር ነው በይፋ ያቋረጠው፡፡
በሩጫው የመጨረሻዎቹ ሰከንዶች ላይ ፈይሳ የጥሩምባ ጥሪ ድምጽ ሰማ፡፡
እንደ ጆሴፍ ካምፕቤል ባለ አንድ ሺ ፊት ምዕናባዊ ጀግንነት ፈይሳ ከተራው የዓለም ሕዝብ ለታላቅ ቁምነገር አድናቆትን እንዲፈጽም ጥሪ ቀረበለት፡፡
ፈይሳ ለጥሪው አውጥቶ እና አውርዶ በሚገባ አሰበበት፡፡ ለብዙ ጊዜ ሲያደርገው የነበረውን አሰበ፡፡ እንደ ካምፕቤል ጀግና ወሳኙ ጊዜ በሚመጣበት ጊዜ ፈይሳ ውሳኔ የማይሰጥ ልፍስፍስ  ወይም ደግሞ ወላዋይ አልሆነም፡፡ ቆራጥ ሆነ ።
ጥርት ባለ የእውነታ መንገድ እና በዓላማ ጽናት ላይ በመመስረት ከእራስ ወዳድነት፣ ከማን አህሎኝነት ስሜት እና ጥሩ የዓለም ህይወትን  ከመውደድ ይልቅ ማንኛውንም አደጋ በጽናት ተቋቁመው ለመልካም ነገር ለማህበረሰቡ መስዋዕትነትን ከፍለው ድልን የሚያቀዳጁ ጀግኖች መስመርን ነው ያቋረጠው፡፡
እንደ ካምፕቤል ምዕናባዊ ጀግና ማንኛውንም የጀግንነት አደጋዎች መጋፈጥ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳም ለሕዝቦቹ፣ ለሀገሩ፣ ለወጣት ወገኖቹ፣ ለባለቤቱ እና ለጥቅላላው ለዘመድ አዝማዶቹ የእራሱን ህይወት በመስዋዕትነት ሰጥቷል፡፡
ግን ለምንድን ነው ይህን ያረገው!?
Cheetah 8እ.ኤ.አ በ1968 በሰሜን ካሊፎርኒያ ከሳን ጆሴ ስቴት ዩኒቨርስቲ ሁለት የኮሌጅ ተማሪዎች የእጆቻቸውን ቡጢዎች ወደ አየር ከፍ አድርገው ከራሳቸው በላይ በመያዝ በአይበገሬነት የጀግንነት መስመሩን እንደዚሁ አቋርጠዋል፡፡
ካርሎስ እድሜው 23 እና ስሚዝ ድግሞ የ24 ዓመት ወጣቶች የነበሩ ሲሆኑ የስኬት፣ የዝና፣ የዕድል እና የታዋቂነትን የወጥመድ አደጋዎች ሁሉ ያለምንም ማወላወል ፊት ለፊት ተጋፍጠዋል፡፡ በአደባባይ ተንቀዋል፣ ተወግዘዋል፣ ተዋርደዋል፣ የማስፈራሪያ ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፣ ተዘልፈዋል እናም የማጃጃል ድርጊት ተፈጽሞባቸዋል፡፡ ከዚህም አልፎ እንዲያውም በውድድሩ አሸናፊ ሆነው ያገኟቸውን ሜዲሊያዎች ለዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴው እንዲመልሱ ተደርገዋል፡፡
ለመሆኑ እንደዚህ ያለ መስዋዕትነትን የከፈሉት ለምንድን ነው!?
የካርሎስ እና የስሚዝ ፎቶ ለጥቁር ኃያልነት ምልክት ሆኖ እንዲኖር ለመሆኑ ለዘላለም በአእምሮዬ ውስጥ ፍንትው ብሎ ይታየኛል፡፡
በአፍሪካ ቀንድ እምብርት እንደ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪ እኔ በግሌ በአሜሪካ የሲቪል መብቶችን እና የወጣቶችን የተቃውሞ ንቅናቄዎችን በተለይም ደግሞ በወጣት አማጺያን በ”ሕዝባዊ ሬፐብሊኮች” በካሊፎርኒያ በበርክለይ እና በኦክላንድ ይደረጉ የነበሩትን እንቅስቃሴዎች አስታውሳለሁ፡፡
ግን ለምን?
ሸክስፒር አስራሁለተኛው ሌሊት/Twelfth Night በሚለው መጽሐፋቸው እንዲህ በማለት ጽፈው ነበር፣ “ጥቂቶች ታላቆች ሆነው ተፈጥረዋል፡፡ ጥቂቶች ደግሞ በሂደት ታላቅነትን ተጎናጽፈዋል፣ ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ በእነዚህ ታላቆች ላይ እምነቶቻቸውን ጥለዋል፡፡
ሸክስፒር ከዚህም በተጨማሪ ጥቂት ሰዎች ደግም ሁልጊዜ ተጎጂ የሆኑ ሕዝቦችን መብቶች ለማስጠበቅ ሲሉ እውነትን በመናገር ሌሎችን ሰዎች በመጨቆን ጉዳት በሚያስከትሉ ሰዎች ላይ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው እንዲያወግዙ እና እንዲጮኹ ሆነው ተፈጥረዋል የሚል ቢጨምሩበት ኖሮ እንዴት ደስ ባለኝ ነበር፡፡
በጣም የሚገርመኝ ጉዳይ ነው፡፡
የወርቅ እና የብር ሜዳሊያዎችን በእጅ ለማስገባት እንደ ነብር የሚወረወረውን የስሚዝን እና የካርሎስን የቪዲዮ ምስል እና በቀጣይነት ቀርቦላቸው የነበረውን ቃለ መጠይቅ ፈይሳ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን ቆርጦ ሲገባ እንደተደረገው ሁሉ ለብዙ ጊዜ ደጋግሜ ተመልክቸው እና አዳምጨው ነበር፡፡
ሁለቱ የኦሎምፒክ ጓደኛሞች በግዋንቲ የተሸፈኑ ሁለት ቡጢዎቻቸውን ወደ ላይ ወደ አየር ከጭንቅላታቸው በላይ ከፍ በማድረግ በሚያማምሩ ጌጣጌጦች ያሸበረቀውን ባለኮከብ የጽሑፍ ሰሌዳ ጨርቁን/ባነር በመበጠስ ውድድሩን አጠናቀዋል፡፡
ግን አወዛጋቢ የሆነው የጥቁሮች ኃይለኝነት በነበረበት ወቅት እጆቻቸውን ወደ ላይ ወደ አየር ከፍ አድርገው ያንን ምልክት ያሳዩበት ምክንያት ለምን ነበር?
ፈይሳ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን በሚያቋርጥበት ጊዜ ሁለት እጆቹን በማጣመር ከራሱ በላይ ወደ አየር ከፍ በማድረግ ያንን ምልክት ያሳየበት ምክንያት ምንድን ነው?
ካርሎስ እና ስሚዝ የዓለምን የኦሎምፒክ መድረክ አጋጣሚን በመጠቀም በአፍሪካ አሜሪካውያን ላይ እየተፈጸመ እና እያሰቃያቸው የነበረውን ዘረኝነትን፣ ድህነትን እና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነትን በመቃወም ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ለማሳወቅ ነበር፡፡
ሆኖም ግን አይበገሬው ድርጊታቸው ወደላይ ከጭንቅላታቸው በላይ በተጣመሩት ቡጢዎቻቸው ብቻ ተወስኖ አልቀረም፡፡ ሆኖም ግን በርካታ በሆኑ አፍሪካ አሜሪካውያን ላይ ዕለት በዕለት በላያቸው ላይ የሚያናጥርባቸውን አውዳሚ የሆነ ድህነት የውድድሩን ፍጻሜ ተከትሎ ሲከናወን በነበረው የሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ ጽኑ አቋማቸውን በግልጽ አሳይተዋል፡፡ በተለይም ደግሞ ካርሎስ ቀደም ሲል ላለቁት ወይም ደግሞ ለተገደሉት  እና ደመ ከልብ ሆነው ለቀሩት ሰዎች ማንም ምንም ዓይነት ጸሎት ያላደረገላቸው እና ያላሰባቸው በመሆኑ ጥቁር ነጠብጣብ ያለበትን ከረባት አስሮ ነበር፡፡ ይህም ማለት በጀልባ በመጓዝ ላይ የነበሩ ሰዎችን በጉዞው አማካይ ርቀት ላይ ሲደርሱ በውኃው አካላ ላይ እንዳሉ ከጀልባው ወደ ባህሩ ውስጥ እንዲወረወሩ እየተደረጉ እልቂት ስለተፈጸመባቸው ሰዎች ነበር፡፡
ፈይሳም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወይም ደግሞ በትክክለኛው እና ገላጭ በሆነው የባህሪ አጠራሩ መሰረት የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ (ዘ-ህወሀት) እየተባለ በሚጠራው ሕገወጥ የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የግፍ አገዛዝ በወገኖቹ በኢትዮጵያ ሕዝቦች ላይ እየደረሰ ያለውን ጭቆና እና የሁለተኛ ደረጃ ዜግነትን በመቃወም እጆቹን በማጣመር ወደ ላይ ከራሱ በላይ ከፍ አድርጎ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በይፋ አሳይቷል፡፡
በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ እንደዚህ ያለውን አስደናቂ የሆነውን እርምጃ ለምን እንደወሰደ ጥያቄ በቀረበለት ጊዜ ፈይሳ እንዲህ ነበር ያለው፣ “የኢትዮጵያ መንግስት የኦሮሞ ሕዝቦችን ይገድላል፡፡ እናም መሬቶቻቸውን እና ሀብታቸውን ሁሉ ይወስዳል፡፡ ስለዚህ የኦሮሞ ሕዝብ በአሁኑ ጊዜ ድርጊቱን በመቃወም ላይ ይገኛል፣ እኔም የኦሮሞ ማህበረሰብ ተወላጅ ስለሆንኩ ድርጊቱን በመቃወም ደጋፊነቴን ለማሳየት ነው፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ወገኖቼን በየቦታው በመግደል ላይ ይገኛል፣ እናም እኔም የኦሮሞ ጎሳ አባል ስለሆንኩ ድርጊቱን በመቃወም ከወገኖቼ ጎን መቆሜን በግልጽ ለማሳየት ነው፡፡ የእኔ ዘመዶች በእስር ቤት ውስጥ በመማቀቅ ላይ ይገኛሉ፣ ስለዴሞክራሲያዊ መብቶቻቸው ከጠየቁ ይገደላሉ፡፡ እጆቼን ከፍ በማድረግ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ያሳዬሁበት ምክንያት የኦሮሞን ተቃውሞ መደገፌን ለማሳየት ነው፡፡“
ፈይሳ የተናገረው ነገር ዋና ፍሬነገር/ ዳህራው እ.ኤ.አ በ1968 ስሚዝ እና ካርሎስ ተናግረውት ከነበረው እንዲህ ከሚለው ቃለመጠይቅ ብዙም የሚለይ አይደለም፡፡
ቃለመጠይቅ አድራጊ፡ እንደዚህ ዓይነቱን ድርጊት በዓለም አቀፍ መድረክ ላይ በኦሎምፒክ ጨዋታዎች መድረክ ላይ ማሳየት ትክክለኛ ቦታው ነው ብላችሁ ታስባላችሁ?
ስሚዝ፡ እኛ አትሌቶች ነን፡፡ እኔ መምህር ነኝ ሆኖም ግን የፖለቲካ ሰው አይደለሁም፡፡ ይህንን ድርጊት የፈጸምነው የዓለም ሕዝብ በአሜሪካ በጥቁር ሕዝቦች ላይ የተንሰራፋውን ድህነት እንዲመከለተው እና ግንዛቤ እንዲወስድ በማሰብ ነው፡፡
ቃለመጠይቅ አድራጊ፡ ሜዳሊያ በማግኘት በሕዝብ ዘንድ ታዋቂነትን እና ዝናን ተጎናጽፊያለሁ ብለህ ታስባለህ ወይስ ደግሞ መስዋዕትነት ከፍያለሁ ነው የምትለው?
ካርሎስ፡ እኔ ሜዳሊያውን ምግብ ሆኖ አልበላውም፡፡ በእኔ የእድሜ የዕኩያነት ደረጃ ላይ ያሉት ታዳጊ ወጣቶችም ቢሆኑ ይህንን ሜዲሊያ አይበሉትም፡፡ ከእነዚህ ልጆች በኋላ የሚመጡት እና የሚያድጉት ልጆችም ቢሆኑ ሊበሉት አይችሉም፡፡ የወርቅ ሜዳሊያዎችን ሊበሏቸው አይችሉም፡፡ ሁላችንም የምናቀርበው ጥያቄ ቢኖር የሰው ለጆች ለመሆናችን ዕኩል እድል ይሰጠን የሚል ነው፡፡ እናም አሁን እንደማየው ከሆነ ከመሰላሉ በ5 ደረጃዎች ዝቅ ብለን እንገኛለን፡፡ እናም ሁልጊዜ መሰላሉን ለመንካት በምንሞክርበት ጊዜ እግሮቻቸውን በእጆቻችን ላይ ይጭናሉ፣ እናም በመሰላሉ ወደላይ እንድንወጣ አይፈልጉም፡፡
በእርግጥ ካርሎስ እና ስሚዝ በሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓቱ ወቅት እጆቻቸውን በአይበገሬነት መንፈስ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ቡጢዎቻቸውን ጠበቅ በማድረግ ዘረኝነትን እና የአፍሪካ አሜሪካውያንን የሁለተኛነት ደረጃ ዜግነትን ሲቃወሙ ብቻቸውን አልነበሩም፡፡ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩት የአሜሪካ ወጣቶች እና በዓለም ላይ የሚገኙ ሕዝቦች ሁሉ ከጎናቸው ነበሩ፡፡
ፈይሳ ሁለት እጆቹን በማጣመር ከጭንቅላቱ በላይ ወደ ላይ ከፍ በማድረግ የውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩን ሲያቋርጥ ብቻውን አልነበረም፡፡ የ100 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ወገኖቹ መንፈሳዊ ድጋፎች፣ ፍቅር እና አድናቆት ነበረው፡፡
በአየር ላይ ከፍ ብለው በምስል ይታዩ የነበሩት በግዋንት የተጠቀለሉት የካርሎስ እና የስሚዝ እጆች የአንድ ሺ ቃላት ያህል ትርጉም ሊሰጡ ይችሉ ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን ለእኔ ይኸ ታሪካዊ ድርጊታቸው አንድ ቃል ብቻ ይወክላል፡ እምቢተኝነት!
የእነርሱ እምቢተኝነት ጨቋኝ ለሆነው እና ለዘረኛው ስርዓት ውድቀት ጽናት ያለው እና ሰላማዊ የሆነ መገዳደርን/አይበገሬነት ይወክላል፡፡
የእነርሱ እምቢተኝነት በአሜሪካ ውስጥ ለሚደረጉ የሲቪል መብቶች ንቅናቄ እና ለብዙሀን የማንነት ትግል እና ለሙሉ የዜግነት ጥያቄ እውቅና ውክልና ይሰጣል፡፡
ስሚዝ በዚያን ጊዜ የነበረውን የእንቆቅልሽ ሁኔታ አቅሎ ባለመመልከት እንዲህ ብሎ ነበር፡ “ውድድሩን የማሸነፍ ከሆነ አሜሪካዊ እንጅ ጥቁር አሜሪካዊ አይደለሁም፡፡ ሆኖም ግን አንድ የሆነ መጥፎ ነገር ሰርቼ ከሆነ እኔን ባሪያ/Negro ነው ይላሉ፡፡ እኛ ጥቁሮች ነን፣ እናም ጥቁሮች በመሆናችን እንኮራለን፡፡ ጥቁር አሜሪካውያን በዛሬው ምሽት ምን እንደሰራን በውል ይገነዘባሉ“ ነበር ያለው፡፡
በአሜሪካ ውስጥ ጥቁር አሜሪካዊ የመሆን እና ያለመሆን የሸክስፒር ዘላለማዊ ተቃርኖ እንዲህ የሚል ነው፡ መሆን ወይም አለመሆን… ወይም ደግሞ መሆን ይችላልን… ጥቁር እስከሆነ ድረስ?
ካርሎስ እና ስሚዝ በዚያ ገጻቸው ለዓለም ሕዝብ እንዲህ በማለት ነበር ያወጁት፣ “ላመንንበት ዓላማ በጽናት እንቆማለን፡፡ በምንም ዓይነት ሁኔታ ወደኋላ አናፈገፍግም፡፡“
የውድድሩ አሸናፊ የውድድር መስመሩን ሲያቋረጥ የሚበጥሰውን ባለነጠብጣብ የኮከብ ጨርቅ/ባነር በሚበጥሱበት ጊዜ የአፍሪካ አሜሪካውያንን መንፈስ በመላበስ እንዲህ በማለት ነበር የሚዘምሩት፣ “ከዚህ አቋሜ አንዲትም ጋት ንቅንቅ አልልም“ ነበር ያሉት፡፡
ፈይሳ ሌሊሳ በካርሎስ እና በስሚዝ አስደማሚ ድርጊት እጅግ ተመስጦ እንደነበር ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡
እንደ ካርሎስ እና ስሚዝ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የእርሱ ድፍረት ለሕዝቦቹ ይናገር ነበር፡፡ የእነርሱን የማጎሪያ እስር ቤቶች እና የማሰቃያ ክፍሎች እንደማይፈራቸው ፈይሳ ዘ-ህወሀት በሚገባ እንዲገነዘብ አድርጓል፡፡ ዘ-ህወሀት የእርሱን ቤተሰቦች ገሀነም እንደሚያስገባቸው በሚገባ ይገነዘባል፡፡ በእርግጥ ከገሀነም ጌቶች ከዚህ ያነሰ ሊጠበቅ አይችልም፡፡
ሆኖም ግን በዚያ ብቸኛ የእምቢተኝነት ቅርጹ ፈይሳ በኢትዮጵያ ውስጥ በዘ-ህወሀት የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን እጅ እየተገደሉ እና እልቂት እየተፈጸመባቻው፣ በቁጥጥር ስር እየዋሉ፣ ወደ እስር ቤት የሚጋዙት እና ስይቃ እየተፈጸመባቸው ለሚገኙት ወጣት ወንድሞቹ እና እህቶቹ ፍጹም የሆነ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
ፈይስሳ ወደ ውድድር ማጠናቀቂያ መስመሩ እየተቃረበ በመጣ ጊዜ ለኦሎምፒክ ዝና እና የበላይነት ክብር እንዲሁም ከዚያ ጋር ተያያዞ ሊገኝ ስለሚችለው መልካም ዕድል ምንም ዓይነት ፍላጎት እንዳልነበረው ለዚያች ቅጽበት ምስክር ሊሆኑ ለሚችሉ ሰዎች ሁሉ ጉዳዩ ግልጽ ነበር፡፡
ፈይሳ የህይወቱን የማራቶንን የሩጫ ውድድር ለወገኖቹ ህይወት እና ክብር ሲል ሮጦታል፡፡
አሸንፎ ሜዳሊያ ለማግኘት ሳይሆን የእርሱን ወገኖች ከስቃይ እና ከውርደት ለማዳን ሲል የማራቶንን ሩጫ ሮጦታል፡፡
ለዚህች ለአንድ ጊዜ አልባ ለሆነች አጋጣሚ ለበርካታ ዓመታት በኮረብታዎች እና በሸለቆዎች እንደ ውኃ ቀጅ በመመላለስ ያለምንም መሰላቸት ሰልጥኗል፡፡
አፉ በዘ-ህወሀት ባይለጎም እና ባይሸበብ ኖሮ እንዲህ ብሎ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እና ለወገኖቹ አይናገርም ነበር፡፡
ሆኖም ግን የሚያምነበትን አቋሙን በእግሮቹ ተናግሯል፡፡ ከአፍ ይልቅ እግር እንዴት ድምጹን ከፍ አድርጎ ይናገራል እባካችሁ!
ካርሎስ እና ስሚዝም የሮጡት ለእራሳቸው ጥቅም ሲሉ ሳይሆን ለሰው ልጆች ዘር ሁሉ መብቶች መከበር ሲሉ ነበር፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 በሳን ጆሴ ስቴት ዩኒቨርስቲ እ.ኤ.አ በ1968 ካርሎስ እና ስሚዝ ፈጽመውት በነበው ታሪካዊ ድርጊት ምክንያት ለመታሰቢያነት በተገነባው ሀውልት የምረቃ ስነስርዓት በሚደረግበት ጊዜ ዶ/ር ካርሎስ እንዲህ ብለው ነበር፡
“በሚክሲኮ ሲቴ ምንም እናድርግ ምን በጣም ውድ እና እንቁ, የተከበረ፣ ቆጥቋጭ፣ አስደንጋጭ እና ገላጭ  የሆነ ነገር፣  አድርገናል፡፡ አመልካች ጣታችንን በሰዎች ላይ አልቀሰርንም፡፡ ምንም ዓይነት ግፊት አላደረግንም፡፡ ሰንደቅ ዓላማችንን በራሳችን ላይ አልጠቀለልንም ወይም ደግሞ እንደ ህጻናት የሽንት መምጠጫ ጨርቅ/ዳይፐር አላሰርንም፡፡ ክብርን በሚያዋርድ መልኩ እዚያ አልቆምንም፡፡ እዚያ የቆምነው እንዲህ ለማለት ነው፣ ‘ሰዎች ጉድ እኮ ነው፡፡ እኔ አሜሪካዊ ነኝ፡፡ የአንተ ልጅ ነኝ፡፡ ቆስያለሁ፡፡ ለእራሴ ስል አልቆሰልኩም ምክንያቱም ከአንተ ጀግኖች መካከል እኔ አንዱ ነኝ፡፡ በአሎምፒክ ላይ ነኝ፡፡ ለውድድሩ ስል ቆስያለሁ፡፡ ስለ 200 ሜትር የርቀት ሩጫ ውድድር አይደለም እያወራሁ ያለሁት፡፡ እየተናገርኩ ያለሁት ስለሰው ልጆች  ሰባዊ መብት ነው፡፡ ለዚህም ነው ሜክሲኮ ሲቲ የሄድነው’” ነበር ያለው፡፡
እጆቹን ወደ ላይ ከፍ በማድረግ ፈይሳ ዘ-ህወሀት እየተባለ በሚጠራ ወንጀለኛ የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የኢትዮጵያ የማስመሰያ መንግስት ተብዬ ድርጅት (አሁን በቅርቡ “ኢትዮጵያ ከጭፍን የጎሳ ጥላቻ ባሻገር“ በሚል ርዕስ ያዘጋጀሁትን ትችት ይመልከቱ፡፡) በሕዝቦች ላይ እያደረሰ ያለውን ስቃይ፣ መከራ፣ የመጥፎ ነገሮቸ ሁሉ መሞከሪያነት እና ከባድ ችግር ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የህሊና ዳኝነት ለአደባባይ እንዲደርስ አድርጓል፡፡
እንደ ስሚዝ እና እንደ ካርሎስ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳ የእርሱ ወገኖች፣ ልጆች፣ ቤተሰቦች እና ጎረቤቶች የብር ሜዳሊያ ሊበሉ አይችሉም በማለት ላይ ይገኛል፡፡ የብር ሜዳሊያው ክብር፣ ነጻነት እና የሰብአዊ መብቶችን አይገዛላቸውም፡፡
እንደ ስሚዝ እና ካርሎስ ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳ ወገኖቹ በሙሉ ዕኩል በሆነ አንድ ዓይነት እድል መስተናገድ እንዲችሉ ፈልጓል፡፡ እንደ ሁለተኛ ደረጃ ዜግነት እንዲስተናገዱ አልፈለገም፡፡ እንደ ወንጀለኞች እና አሸባሪዎች ተደርገው እንዲፈረጁ አልፈለገም፡፡ ፈይሳ የፈለገው በአምላክ አምሳል እንደተፈጠረ እንደማንኛውም ሰብአዊ ፍጡር፣ አምላክ ካጎናጸፋቸው የህይወት ሙሉ ዘላለማዊ መብት፣ ነጻነት እና ደስታን ከማግኘት መብት ጋር  በሰላም እና በድሎት እንዲኖሩ ነው የሚፈልገው፡፡
ፈይሳ የእርሱ ሕዝቦች በመሰላሉ ላይ እንደማንኛውም ሰው እንዲወጡ ይፈልጋል፣ እናም በምንም ዓይነት መልኩ መሰላሉ በዘ-ህወሀት፣ በአባሎቹ እና በግብረ አበሮቹ በክልከላ በመያዝ ከላይ ከቁንጮው ላይ እግራቸውን አንፈራጥጠው በመቀመጥ ሌላው ዜጋ ለመውጣት ሙከራ በሚያደርግበት ጊዜ እየኮረኮሙ በመከልከል የኢትዮጵያን ሕዝብ መሰላል የእነርሱ ብቻ መሰላል አድርገው እንዳይቀመጡ ይፈልጋል፡፡
እ.ኤ.አ ነሐሴ 21/2016 በሪዮ የማራቶን ውድድር የሜዳሊያ አሰጣጥ ስነስርዓት ላይ ፈይሳ ሌሊሳ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) ማለት ምን ማለት እንደሆነ እና የኩሩ ትወልድ ዝርያ ኩሩ እንደሆነ ኢትዮጵያውያንን በሙሉ እንደሚያኮራ ወይም ደግሞ እንደ ኩሩ አንበሶች የኮራ ጀግና የህብረተሰብ ክፍል መሆኑን ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በሚገባ አሳይቷል፡፡
ሆኖም ግን ፈይሳ ለአቻ ጓደኞቹ ያስተላለፈው እንደህ የሚል ግልጽ መልዕክት ነበር፣ “በዘ-ህወሀት የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ እየተፈጸመ ያለውን የእናንተን ስቃይ፣ የመሞከሪያ ዕቃ ስለመሆናችሁ እና ስለሚያደርስባችሁ መከራ እና ስቃይ ሁሉ 3.5 ቢሊዮን ለሚሆኑ የዓለም ሕዝቦች በሚገባ ተናግሪያለሁ“ የሚል ነው፡፡
ፈይሳ ለኢትዮጵያ በግዴታ ገዥዎች በምንም ዓይነት መንገድ፣ መለኪያ እና መስፈርት ሊመጥን የማይችለውን አሸባሪ እና የማፊያ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብ የሆነውን እራሱን ዘ-ህወሀትን እንኳ “የኢትዮጵያ መንግስት” ብሎ ጠርቶታል፡፡
ፈይሳ እንደዚያ ዓይነቱን ደም የተጠማ የወሮበላ ዘራፊ እና የእራሱን ዜጎች ጨፍጫፊ ቡድን ስብስብ ታላቅ ቸርነትን በማሳየት በባህሪ እና በግብር ከማይገናኘው ጋር “መንግስት” ብሎ ጠርቶታል፡፡ ድንቄም መንግስት፣ መንግስት እንዳይባል የለ! የዱርዬ መንግስት እንጂ !
ዘ-ህወሀትን “መንግስት” ብሎ መጥራት ቦቅቧቃዎችን እና ፈሪ የሆኑትን ጥንብ ሲያዩ የሚያሽካኩትን ጅቦች “ኩሩ አንበሳ” ብሎ ከመመጥራት ጋር መሳ ለመሳ ነው፡፡
ማንም ቢሆን አካፋን አካፋ ብሎ መጥራት አለበት፡፡ እንደዚሁም ጅብን ጅብ ብሎ መጥራት አለበት፡፡
ዘ-ህወሀት ለዘራፊዎች በዘራፊዎች የተቋቋመ የዘራፊዎች መንግስት ነው (እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 “ዘራፊነት፡ የአፍሪካ አምባገነኖች ከፍተኛ ደረጃ“ በሚል ርዕስ አቀርቤው የነበረውን ትችቴን ይመልከቱ፡፡)
ዘራፊዎች ምን ወርቅ ቢለብሱ ምንጊዜም ቢሆን ያው ዘራፊዎች ናቸው፡፡ ጅቦችም እንኳ ቢሆኑ ምንም እንኳን ነገር እንደገባው ሰብአዊ ፍጡር ቢሽከመከሙም (ጧ ብሎ መሳቅ) ያው ምንጊዜም ጅቦች ናቸው፡፡
አንበሶች ምንጊዜም ቢሆን ያው አንበሶች ናቸው፣ እናም ጅቦች የአንበሶቹን ማግሳት እና የአቦ ሸማኔዎችን ማጉረምረም በሚገባ ያውቃሉ፡፡
Cheetah 10ሆኖም ግን ፈይሳ በአንድ ላይ የተጠቃለለ አንበሳ እና አቦ ሸማኔ ነው፡፡
በዚያው ተመሳሳይ ቀን ፈይሳ የብር ሜዳሊያውን አሸናፊ በሆነበት ዕለት በሀገሪቱ ዋና መናገሻ በሆነችው በአዲስ አበባ ውስጥ ሊደረግ የነበረውን ሰላማዊ ተቃውሞ ለመከላከል ሲል ዘ-ህወሀት አፋኝ የደህንነት መንጋዎቹን፣ የፖሊስ ኃይሉን እና ወሮበላ ዘራፊ ወታደሮቹን በከተማይቱ አሰማርቷል፡፡
እንዴት ዓይነት በተቃርኖ የተሞላ ጊዜ ነው እባካችሁ! በሚሊዮን የሚቆጠሩትን ሰላማዊ ተቃዋሚዎች በመከልከል እቤታቸው ውስጥ እንዲቀመጡ በማስገደድ ዘ-ህወሀት ሕዝቦች የእነርሱን ስራ ከመካከላቸው የእነርሱ በሆነ አንድ ሰው አማካይነት ቆንጆ በሆነ መልኩ 3.5 ቢሊዮን ሕዝብ እንዲመለከተው ሲደረግ ደስታ በተመላበት ሁኔታ ተቀምጠው ተመልክተዋል፡፡
ፈይሳ ወደ ውድድሩ ማጠናቀቀቂያ መስመር ላይ ሲያቃርብ የሚያሳየውን የቪዲዮ ምስል በምመለከትበት ጊዜ እ.ኤ.አ ሰኔ 1989 በቻይና ዋና ከተማ አንድ ግለሰብ በከተማይቱ እምብርት በታንኮቹ ፊት ተገትሮ በመቆም “በምንም ዓይነት ሁኔታ ከቆምኩባት ቦታ ንቅንቅ አልልም“ በሚል ሞገደኛ እና እልኸኛ ስሜት ዓላማውን የገለጸውን ወጣት አስታወሰኝ፡፡
ኃይለኛ በሆኑት በቻይናውያን ወታሮች እና የደህንነት ኃይሎች እብሪተኝነት በመቶዎች በሚቆጠሩ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ላይ እልቂትን እየፈጸሙ ባሉበት በዚያ ቅጽበታዊ ጊዜ አንድ ትንሽ የሆነ አሞተ ቆራጥ ጀግና ሰው እምቢኝ አሻፈረኝ ካለሁባት ቦታ ጋት አልንቀሳቀስም በማለት ያሳየው ተጋድሎ የሚደነቅ እና የሚገርም ትይንት ነበር፡፡
ያ ተዋቂነትን ያልተጎናጸፈ ተራ ሰው የቻይና የጦር ማሽን/ፋብሪካ በእርሱ ላይ ምን ሊያደርስ እንደሚችል ምንም ዓይነት ፍርሀት አልነበረውም፡፡
ዘ-ህወሀት በእርሱ ላይ ሊያደርግ ስለሚችለው ሁኔታ ፈይሳ ይፈራልን?
ፈይሳ ቀጥተኛ በሆነ መልኩ በግልጽ እንዲህ በማለት ተናግሯል፣ “ባይገድሉኝ እንኳ በእስር ቤት ያማቅቁኛል፡፡ እስከ አሁን ድረስ ምንም የወሰንኩት ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን ምናልባትም ወደ ሌላ ሀገር የምንቀሳቀስ ይሆናል“ ነበር ያለው፡፡
የፈይሳ እናት ምንም ዓይነት ፍርሀት ሳያሳዩ ለቀረበላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እንዲህ ብለዋል፣ “መንግስት እየተናገረ ባለው ነገር ያምናሉን? እዚያው ባለበት ይቆይ፡፡ እዚያው እንዲቆይ ነው እኔ የምፈልገው፡፡ ደህና እንዲሆን ነው የምመኘው“ ነበር ያሉት ከመጣ ደህንነቱ እንደማይጠበቅ እርግጠኛ በመሆን መንፈስ፡፡
የፈይሳ ባለቤት የእርሷ ባለቤት ምን ዓይነት ጠንካራ እንደሆነ እንደምታውቅ እንዲህ ብላለች፣ “በወቅቱ ፈርቸ ነበር፣ ሆኖም ግን ይህ ሁኔታ የሚያስደንቀኝ አይሆንም ምክንያቱም እኔ እርሱን አውቀዋለሁና፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጾች የሰዎችን ሬሳዎች በሚያይበት ጊዜ፣ ሰዎች በቁጥጥር ስር ሲዉሉ በሚመለከትብት ጊዜ እና ሰዎች ሲደበደቡ በሚመለከትበት ጊዜ በውስጡ ይቃጠል ነበር፡፡ ስለሆነም እኔ በዚህ ጉዳይ ላይ አልተደነቅሁም ነበር ምክንያቱም በውስጡ በርካታ ብስጭቶች በውስጡ ታምቀው ነበርና“  ነበር ያለችው፡፡
ፈይሳ የህወሀት ወሮበላ ዘራፊዎች እንደፈለጉ በጫማቸው ስር አድርገው የፈለጋቸውን ነገር እንዲፈጽሙበት እና በእነርሱ ስር ለመውደቅ የሚያስችል አቋም የለውም፡፡ ፈይሳ ባለው ፍጥነት ወደፊት በፍጥነት መገስገስ እንጅ በእነዚህ እርባናቢስ ቅጥር ነብሰገዳዮች እጅ ስር መውደቅን አልፈለገም፡፡
ፈይሳ በቀላል አገላለጽ ዘ-ህወሀትን ምንም ዓይነት ልብስ ሳይለብስ በሕዝብ አደባባይ ላይ ቆሞ የለበሰ መስሎት ያልለበሰ መሆኑን ሳያውቅ ራቁቱን ተገትሮ ይታይ የነበረውን የንጉስ አፈ ታሪክ በተጨባጭ አሳይቷል፡፡ ወይም ደግሞ ፈይሳ ይህንን በማድረጉ በእውኑ ዓለም በአሁኑ ጊዜ ሕዝብን እያሰቃዩ እና እየዘረፉ ያሉትን ደም መጣጮች በተጨባጭ ለዓለም ሕዝብ በሚገባ አሳይቷል፡፡
ፈይሳ በአሸናፊነቱ ስለሚያጣው የብር ሜዳሊያ እና የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ስለሚጭንበት ቅጣት የሚያሳስበው ጉዳይ ነበርን?
ለዚህ ትንሽ ክብ ቁራጭ ብረት ምንም ዓይነት ደንታ ሊኖረው አይችልም ወይም ደግሞ ከዚህ ጋር በተያያዘ ስለሚያገኘው ዝና እና መልካም ዕድል ሁሉ ደንታው እና ጉዳዩ አይደለም፡፡ መቋጫ በሌለው መልኩ የእርሱ ጭንቀት እና በበለጠ መልኩ ያሳስበው የነበረው ስለወገኖቹ ደህንነት ነበር፡፡ እንዲህ ብሎ ነበር፣ “ስለዚያ ነገር ምንም ማድረግ አልችልም [የዓለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ/ዓኦኮ ስለሚያደርገው ነገር]፡፡ የእኔ ስሜት ይህ ነበር፡፡ በሀገሬ ውስጥ ትልቅ ችግር አለ፡፡ በሀገሬ ውስጥ ተቃውሞ ማሰማት እና በተቃውሞ መንቀሳቀስ እጅግ አደገኛ የሆነ ነገር ነው:: ዓኦኮ እነዚያን ሁለት ቁራጭ ብረቶች መውሰድ እና  እኔን መገፍተር ይችላል…የእኔ ክብር እና የሕዝቦቼ ክብር በኦሎምፒክ ገበያ ወይም ደግሞ በሌላ በማናቸውም ገበያ ቢሆን ለሽያጭ ለድርድር የሚቀርብ አይደለም“ ነበር ያለው፡፡
ፈይሳን እና ቤተሰቡን እግዚአብሄር ይባርካቸው!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም፣
እ.ኤ.አ ግንቦት 2011 “የአፍሪካ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡
ያ ትችት ያጠነጥን የነበረው ስለሙባረክ አገዛዝ ተፈረካክሶ መውደቅ ጉዳይ እና አምባገነኖች በስልጣናቸው ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው ለመቆየት ስለሚወስዱት የኃይል እርምጃ ነበር፡፡ ያ ኃይልን የመጠቀሙ እርምጃ የደካሞች ዋና መሳሪያ እንደነበር ግልጽ አድርጌ ነበር፡፡ ምንም ዓይነት መሳሪያ ያልታጠቁትን ሰላማዊ ዜጎች በመንገዶች ላይ ተኩሶ መግደል እና አካለ ጎደሎ ማድረግ የጥንካሬ ምልክት አይደለም፣ ይልቁንም በተቃራኒው የፍርሀት፣ የደካማነት እና የቦቅቧቃ ፈሪዎች ዋና መለያ ምግባር ነው ነበር ያልኩት፡፡
እ.ኤ.አ ሰኔ 2010 “ስለኢትዮጵያ ወጣቶች እውነታውን መናገር“ በሚል ርዕስ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ ትችቴ በቁጣ ተሞልተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙት የኢትዮጵያ ወጣቶች በጊዜ የተሞላ የስነሕዝብ ቦምብ ነው የሚል የክርክር ጭብጥ ማስረጃዬን አቅርቤ ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች ተስፋ እያጡ የመምጣት፣ የደስታ እጦት፣ የተሳሳተ እምነት መኖር እና ለብዙ ጊዜ በቆየ የኢኮኖሚ ቀውስ ሳቢያ ብርታትን ማጣት፣ የኢኮኖሚ ዕድሎች ያለመኖር እና የፖለቲካ ጭቆና ግልጽ ሆኖ እየገዘፈ መከሰቱ የማይካድ መሆኑን በማብራራት የክርክ ጭብጤን አቅርቤ ነበር፡፡ ወጣቶች ለነጻነት እና ለለውጥ ያላቸው ጥልቅ ፍላጎት በእራሱ ገላጭ ነው፡፡ ብቸኛ ሆኖ የሚቀርበው ጥያቄ ግን የሀገሪቱ ወጣቶች ለውጡን ሊያመጡት የሚችት እየጨመረ የመጣውን የኃይል እርምጃን በመጠቀም ነው ወይስ ደግሞ በሌላ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ነው የሚለው ነው፡፡
እ.ኤ.አ ጥር 2013 “ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2013፡ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ዓመት“ በሚል ርዕስ ለኢትዮጵያ ወጣቶች መልዕክት በማስተላለፍ ትችት አቅርቤ ነበር፡፡
በዚያ መልዕክቴ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ይፋ ባልሆነ መልኩ የውይይት መድረክ በእራሳቸው በወጣቶቹ መካከል ማድረግ እና በብሄራዊ ዕርቅ የእነርሱ ሚናዎች ምን መሆን እንዳለባቸው አስቀድመው መወሰን እንዳለባቸው ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ በዚያ መልዕክቴ ወጣቶች  ከምንጊዜውም በላይ እራሳቸውን ማጠናከር እና የእራሳቸውን የፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ምህዳር መፍጠር እና አንድ በአንድ ከጎሳ፣ ኃይማኖት፣ ቋንቋ፣ ጾታ፣ ክልል እና የመደብ መስመርን ሳይለይ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር መነጋገር እንደሚያስፈልግ የተማጽዕኖ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡ እንደዚሁም ሁሉ ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ወጣት ትውልድ ብዝሀነታቸውን እንደ ጥንካሬ መውሰድ እንዳለባቸው እና ብዝሀነታቸው እራሳቸውን ለመከፋፈል እና ለጥቃት ሊዳርጋቸው እንደማይገባ የተማጽኖ ጥሪ አቅርቤ ነበር፡፡
በዚያ ትችቴ ላይ የጾታ ልዩነት ክፍተትን ማስወገድ እና ሰላማዊ የእምቢተኝነት ጥረቶችን አጠናክሮ በመቀጠል የወጣት ሴቶችን ተሳትፎ ማስፋት እና ማጠናከር አስፈላጊ እንደሆነ አስምሬበት ነበር፡፡
እ.ኤ.አ ጥር 2014 “እ.ኤ.አ 2014፡ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው እና የጉማሬው (የቀድሞው) ትውልድ ዓመት“ በሚል ርዕስ አቅርቤው በነበረው ትችት በኢትዮጵያ ውስጥ በወጣቶች ላይ ተጋርጠው ስለሚገኙት ተግዳሮቶች በዝርዝር ጽፌ ነበር፡፡ በዚህ ትችቴ የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ ወጣቶች አደገኛ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ በማለት አውጀ ነበር፡፡
የ21ኛው ክፍለ ዘመን ኢትዮጵያ ዋናው ችግር የወጣቱ ችግር ነው የሚል የክርክር ጭብጥ አቅርቤ ነበር፡፡ እንደ ዩኤስ የሕዝብ ቆጠራ ቢሮ ከ34 ዓመታት ባነሰ ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በሶስት እጅ በመጨመር 278 ሚሊዮን እንደሚሆን እና ሀገሪቱ ከፍተኛ የሕዝብ ብዛት በማስመዝገብ ላይ ከሚገኙት 10 የመጀመሪያ ደረጃ ላይ ከሚገኙት ሀገሮች ምድብ ውስጥ ትመደባለች የሚል ትንበያ የሰጠ መሆኑን በመጥቀስ የክርክር ጭብጤን አቅርቤ ነበር፡፡
በአሁኑ ጊዜ ወደ አንድ መቶ እና ከዚያም በላይ ሊሆን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር ውስጥ ወደ 70 በመቶ የሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ35 ዓመት በታች እድሜ (66 ሚሊዮን) ያለው የህብረተሰብ ክፍል ነው፡፡
ኔልሰን ማንዴል በአንድ ወቅት እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “የእኛ ልጆች የእኛ ታላቅ ሀብቶች ናቸው፡፡ ልጆቹ የእኛ የወደፊት ጸጋዎች ናቸው፡፡ በእነርሱ ላይ ከሕግ አግባብ ውጭ የሚፈጸም ማንኛውም ድርጊት ሁሉ የማህበረሰባችንን የአንድነት ክር ይበጥሳል፣ እናም ሀገራችንን ያዳክማል“ ነበር ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች የሀገሪቱ ታላቅ ሀብት የሆኑት እና የኢትዮጵያ የወደፊት ጸጋዎች  በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ አደጋ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ ሀብቶች የሆኑት ወጣቶች ፍጹም በሆነ መልኩ ተረስተዋል፣ ከሕግ አግባብ ውጭ ጭቆና ይፈጸምባቸዋል፣ ውድ የሆነው ጉልበታቸው በከንቱ እየጠፋ እና በከንቱ በመባከን ላይ ይገኛል፡፡
እንደ የአፍሪካ ሕዝቦች እና የጤና ምርምር ማዕከል/African Population and Health Research Center ዘገባ ከሆነ ኢትዮጵያ በዓለም ላይ በጣም ዝቅተኛ የሆነ ጠቅላላ የትምህርት ሽፋን መጣኔ/Gross Enrollment Rate ካላቸው ሀገሮች መካከል አንዷ ናት…ዝቅተኛ የትምህርት ጥራት እና ከፍተኛ የሆነ የማቋረጥ መጣኔ እንደዚሁም ሁሉ በገጠር እና በከተማ መካከል ከፍተኛ የሆነ የጾታ ልዩነት መኖር ዋና የሀገሪቱ ችግሮች ሆነው ቀጥለዋል፡፡ እንደምንም ብለው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለመግባት በጣም የጠበቡ ዕድሎች እንዳሏቸው ወይም ደግሞ የስራ ዕድል እንደማያገኙ ዘገባው ግልጽ አድርጓል፡፡
እ.ኤ.አ በ2012 በዩኤስኤአይዲ የወጣው ዘገባ እንዲህ ይላል፣ “ኢትዮጵያ የከተማ ወጣት የስራ አጥነት የተንሰራፋባት ሀገር ናት፡፡ ይህም የስራ አጥነት መጣኔ 50 በመቶ እንደሆነ እና ከፍተኛ የሆነ የስራ አጥነት ችግር ተንሰራፍቶ እንደሚገኝ እንዲሁም 85 በመቶ የሚሆነውን ሕዝብ በሚይዘው በገጠሪቱ ኢትዮጵያም የስራ አጥነቱ ችግር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሮ ይገኛል“ ነበር ያለው፡፡
ሌላው በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center እ.ኤ.አ በ2012 በወጣት ስራ አጥነት ላይ የተደረገ ጥናት የግኝት ጭብጥ እንዲህ ይላል፣ “በአሁኑ ጊዜ ያለው (እ.ኤ.አ 2010/11 – 2014/15) የ5 ዓመት የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገዥው አካል የወጣቶችን ስራ አጥነት ችግር ጉዳይ በቀጥታ አላካተተም…“ ነበር ያለው፡፡ ያ ጥናት እንዲህ የሚል የጥናት ውጤት አግኝቷል፣ “እ.ኤ.አ በ2011 38 በመቶ የሚሆኑት ወጣቶች አብዛኛውን ጊዜ ዝቅተኛ የጥራት ጉድለት በሚታይባቸው እና ዝቅተኛ ክፍያን በሚከፍሉ የግል ዘርፉ ውስጥ ተቀጥረው ይገኛሉ“ ነበር ያለው፡፡
በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ውስጥ ያሉት ከፍተኛ ብዛት ያላቸው ወጣቶች ስራ አጥ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን መሰረታዊ የሆኑ ክህሎቶችን በተገቢው ስልጠና ያላገኙ በመሆናቸው ወደፊትም እንኳ የስራው ዕድል ቢፈጠር ተቀጥረው ለመስራት የማይችሉ ናቸው፡፡ በመንግስት ቁጥጥር ስር የሚገኙት የስራ ዘርፎች በብቃት ወይም ደግሞ በውድድር ላይ በተመሰረተ መስፈርት መሰረት ባለሞያዎችን የሚቀጥሩ ሳይሆን በፖለቲካ የመንግስት ወገንተኝነት እምነታቸው እና በማህበራዊ ግንኙነቶች እንደዚሁም ደግሞ  የገዥው ፓርቲ አባል ለሆኑት ስራ ፈላጊዎች ብቻ ተደራሽ የሆኑ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለ ማንኛውም ወጣት አባልነትን የሚገልጽ ካርድ ከገዥው ፓርቲ መያዝ ትክክለኛ በሆነ የግል ጥረት ከተያዘ የዩኒቨርስቲ ዲፕሎማ በላይ ጠቃሚነት አለው፡፡ ከዚህም በላይ የገጠር ወጣቶች መሬት አልባነት ለዚህ ለተፈጠረው ቀውስ እና ወደ ከተማ ለሚደረገው ከፍተኛ የሆነ የሰው ፍልሰት፣ ስራ አጥነት እና ተስፋየለሽነት እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
በኢትዮጵያ ወጣቶች ላይ ተጋርጠው የሚገኙ አደጋዎች ሙሉ በሙሉ በህብረተሰቡ ውስጥ ተንሰራፍተው የሚገኙ ማህበራዊ ቀውሶች ናቸው፡፡
እ.ኤ.አ በ2010 እንደወጣው የዘ-ህወሀት ዘገባ 150 ሺ ህጻናት የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎች ሆነዋል፣ ከእነዚህም ውስጥ 60 ሺ የሚሆኑት በሀገሪቱ ዋና መናገሻ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ልጆቹ በመጀመሪያ ቤት አልባ የሚሆኑበት አማካይ እድሜ 10 እና 11 ዓመት እንደሆነ ተዘግቧል፡፡
ከኤች አይቪ ኤይድስ እና ከሌሎች በግብረ ስጋ ከሚተላለፉ በሽታዎች ጋር በተያያዘ መልኩ የወጣቶች የጤንነት አደጋዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ ይገኛሉ፡፡ ምንም ዓይነት ዕድል የሌላቸው በርካታ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች አንደንዛዥ እጾችን በመውሰድ፣ አልኮልን በማዘውተር፣ በዝሙት አዳሪነት እና በሌሎች በወንጀል ድርጊቶች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡፡ በከተሞች አካባቢ ያለምንም ስራ እና የትምህርት ዕደል በርካታ የሆኑ ወጣቶች ስራ አጥ፣ ቤት የለሽ፣ ረዳት የለሽ እና ተስፋየለሽ ሆነው ይገኛሉ፡፡
እ.ኤ.አ በ2004 ዘ-ህወሀት ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲን አወጀ፡፡ እናም ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ዘገባ መሰረት እንዲህ የሚል ግኝት ተመዝግቦ ነበር፣ “44 በመቶ የሚሆነው ሕዝብ ከድህነት ወልል በታች ነው፡፡ በዚህ ዓይነት የድህነት ሁኔታ ወጣቱ በከፍተኛ ደረጃ ተጠቂ የሆነ የማህበረሰብ ከፍል ነው…አብዛኞቹ ስራ አጥ የሆኑት ሴት ወጣቶች የመሆናቸው ጉዳይ ደግሞ የዚህ ችግር ሰለባ የመሆናቸውን እውነታነት የበለጠ ተጨባጭ ያደርገዋል“ የሚል ነበር፡፡ ሰነዱ የፖሊሲውን ተፈጻሚነት ሲያብራራ “መንግስት፣ የመምራት፣ የማስተባበር፣ የማቀናጀት እና የአቅም ግንባታ ስራዎችን የመስራት ኃላፊነትን ይወስዳል” የሚል ነበር፡፡
ሆኖም ግን እ.ኤ.አ በ2012 በዓለም አቀፍ የዕድገት ማዕከል/International Growth Center  በወጣት ስራ አጥነት ላይ የተደረገ ጥናት የግኝት ጭብጥ እንዲህ ይላል፣ “በአሁኑ ጊዜ ያለው (እ.ኤ.አ 2010/11 – 2014/15) የ5 ዓመት የኢትዮጵያ የዕድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ገዥው አካል የወጣቶችን ስራ አጥነት ችግር ጉዳይ በቀጥታ አላካተተም…“ የሚል ነበር፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ብሄራዊ የወጣቶች ፖሊሲ እየተባለ የሚጠራው ለዘ-ህወሀት ወጣቶችን ለይስሙላው ምርጫ መጠቀሚያነት ከመሆን ባለፈ ለወጣቱ አንዳችም የፈጠረው ፋይዳ የለም፡፡
እ.ኤ.አ በ2014 የወጣ ዘገባ አስከፊውን የገጠር ድህነት ለማምለጥ ወጣቶች እንዴት አድርገው የውስጥ ፍልሰትን እንደሚጠቀሙ ያመላክታል፡፡
ለበርካታ ዓመታት የኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ አንድ ቀን ሊነሳ እንደሚችል እና ያችንም ቀን እንሚጠብቃት ስናገር ቆይቻለሁ፡፡ ኢትዮጵያን ከዘ-ህወሀት ጅቦች ጠብቁ፡፡
ሳስተላልፈው በቆየሁት መልካም መልዕክት ሁሉ በጣም ኩራት ይሰማኛል!
እ.ኤ.አ የካቲት 2016 “ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ የጥርሙስ ውስጥ መልዕክት፡ ነጻ ሆናችሁ ተወልዳችኋል፣ ነጻ ሆናችሁ ኑሩ!“ በሚል ርዕስ ስለሚመጣው ሁኔታ እንዲህ በማለት አስጠንቅቄ ነበር፡
“የኢትዮጵያ ወጣቶች ሙሉ በሙሉ ግንዛቤው አላቸው፡፡ ጥቂት የአቦ ሸማኔው ትውልድ አባላት በንዴት እና በከፍተኛ ቁጣ በመነሳሳት በእምቢተኝነት ከዘ-ህወሀት ፊት ለፊት ይቆማሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ድምጾቻቸውን ከፍ አድርገው ያንሾካሹኩ እና ያጉረመርማሉ፡፡ የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች ደስተኞች አይደሉም” በማለት አስጠንቅቄ ነበር፡፡ ለዚህም ነው በአሁኑ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ ውስጥ ከጅቦች ጋር ፊት ለፊት በመጋፈጥ እና በማጉረምረም ላይ የሚገኙት፡፡
እ.ኤ.አ ጥር 2016 ዘ ኢኮኖሚስት የተባለው መጽሄት ለበርካታ ዓመታት በአእምሮዬ ውስጥ ሲመላለስ የቆዬ እንዲህ የሚል አንድ ጥያቄ አቅርቦ ነበር፡፡ ጥያቄውን በሰማሁበት ጊዜ መብረቅ እንደመታው ዛፍ ድርቅ ብዬ ነበር የቀረሁት፡፡ እንዲህ የሚል ጥያቄ ነበር፣ “አትዮጵያውያን ነጻ ቢሆኑ ኖሮ የት ይደርሱ ነበር?“ ዘ ኢኮኖሚስት ለእራሱ ጥያቄ መልስም እራሱ እንዲህ በማለት ነበር የሰጠው፣ “የኢትዮጵያ መንግስት ሕዝቦች በነጻነት እንዲተነፍሱ ቢፈቅድ ክንፍ አውጥተው ሊበሩ ይችላሉ፡፡“
“ብሪሪ፣ ኢትዮጵያ ብረሪ…“ በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው በነበረው ትችቴ የምዕናባዊ በረራዬን አከናውኘ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ መብረር የምትችል ቢሆን ኖሮ ለመሞት በባህር ላይ አይጣሉም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገሮች በእርግጠኝነት ባሮች ለመሆን አይበሩም ነበር፡፡ በረሀዎችን በማቋረጥ ደም ለጠማቸው አሸባሪዎች የጥቃት ሰለባ አይሆኑም ነበር፡፡ ወደ ስደት አያመሩም ነበር፡፡ ለመብረር የሚችሉ ቢሆን ኖሮ እንደ አፍሪካ ዓሳ ይንሰፈፉ ነበር፡፡ ክንፎቻቸውን ወደ ሰማይ ከፍ በጣም ከፍ ያደርጉ ነበር፡፡ እንደ ድምጻዊዋ ወፍ ያዜሙም ነበር፡፡
የኢትዮጵያ ወጣቶች እንዲበሩ እፈልጋለሁ፡፡
በምዕናባቸው በረራ እንዲያደርጉ እፈልጋለሁ፡፡
የእነርሱ የሆነች እና ከጎሳ ፖለቲካ፣ ከኃይማኖት ጽንፈኝነት እና ከጭፍን ጥላቻ ነጻ  የሆነች አዲስ ኢትዮጵያን እንዲያልሙ እፈልጋለሁ፡፡
በእራሷ ለእርሷ እና ለጎረቤቶቿ ሰላሟ የተጠበቀ፣ ከጭቆና እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ የሆነች ኢትዮጵያን ለማየት እፈልጋለሁ፡፡
እያንዳንዱ የአቦ ሸማኔ ትውልድ የህንጻ ንድፍ ባለሞያ፣ ንድፍ ሰሪ፣ ፈጣሪ፣ ለኪ፣ ገንቢ እና ዜጎቿ እርስ በእርሳቸው ስለጎሳዎቻቸው ሳይሆን ስለሰብአዊ ፍጡርነታቸው፣ ስለእኩልነት ዕድሎቻቸው፣ ከሙስና፣ ከጭቆና እና ከወሮበላ ዘራፊዎች ነጻ ስለሆነች ኢትዮጵያ በአንክሮ የሚያስቡ የነጻ ኢትዮጵያ ስራ ፈጣሪ ዜጋ እንዲሆኑ አጥብቄ እጠይቃለሁ፡፡
ኢትዮጵያን በምዕናባቸው እንዲያንጿት እፈልጋለሁ፡፡
ማሸነፍ ልብን እና አእምሮን እንጂ ሜዳሊያዎችን አይደለም፣
እኔ ሁልጊዜ ከኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትወልድ ጠርዝ ወይም ጫፍ ላይ እንደምቆም ግልጽ አድርጊያለሁ፡፡ (እ.ኤ.አ ጥር 2013 “የአቦ ሸማኔ – ጉማሬው ትውልድ መነሰሳሳት” በሚል ርዕስ አዘጋጅቸው የነበረውን ትችቴን ይመልከቱ፡፡)
በዚያ ትችቴ ላይ በኢትዮጵያ ለነጻነት፣ ለዴሞክራሲ እና ለሰብአዊ መብጥ ጥበቃ የሚደረገው ትግል ዋናው ምስሶ እንደሆነ እና የኢትዮጵያን ሕዝቦች ልብ እና አእምሮ ለመቆጣጠር በሚደረገው ጦርነት ላይ ትልቅ ጉዳይ እንደሆነ ለኢትዮጵያ የአቦ ሸማኔው ትውልድ በዝርዝር ገልጨ ነበር፡፡ ልብን እና አእምሮን ለመቆጣጠር በሚደረግ የጦር ሜዳ ትግል ውስጥ ጠብመንጃዎች፣ ታንኮች እና የጦር አውሮፕላኖች ዋጋቢሶች ናቸው፡፡ ይህንን ጉዳይ ታሪክ በተጨባጭ አረጋግጧል፡፡ ዩኤስ አሜሪካ በቬትናም ጦርነት ድልን አጥታለች ምክንያቱም አውዳሚ የጦር መሳሪያዎች ኃይል፣ የአየር ኃይል፣ የኒኩሌር ኃይል፣ የገንዘብ ኃይል ሳይንሳዊ ወይም ደግሞ የቴክኒክ ኃይል ስላጡ አልነበረም፡፡ ዩኤስ አሜሪካ በጦርነቱ የተሸነፈችበት ዋናው ምክንያት የቬትናማውያንን እና የአሜሪካውያንን ሕዘቦች ልቦች እና አእምሮዎች ማሸነፍ ባለመቻላቸው ነበር፡፡
ህይወት ሜዳሊያ ስለማሸነፍ ጉዳይ አይደለም፡፡
ይልቁንም ህይወት ልብን እና አእምሮን ስለማሸነፍ ጉዳይ ነው፡፡
የዓለም አቀፍ ኦሎምፒክ ኮሚቴ የሚያብረቀርቁ ሜዳሊያዎችን ከስሚዝ እና ከካርሎስ ቀምቶ ወስዷል፡፡  እነዚህ ሁለት ጓደኛሞች ከአራት አስርት ዓመታት በላይ ይበገሬ የሰብአዊ መብት ተሟጋችነታቸውን በተግባር አረጋግጠዋል፡፡
ዓለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ የፈይሳን ሜዳሊያ ይወስደው ወይም አይወስደው ለመሆኑ ገና ግልጽ አይደለም፡፡
እንደ ስሚዝ እና ካርሎስ በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳ እ.ኤ.አ በ2016 የእርሱን ሕዝቦች ልቦች እና አእምሮዎችን የተቆጣጠረውን ሜዳሊያ ብቻ አይደለም የወሰደው ሆኖም ግን በእርገጠኝነት የወሰደው በዓለም ላይ የሚገኙትን በቢሊዮኖች የሚቆጠሩትን የሌሎችን የነጻነት አፍቃሪዎች ሕዝቦች ልቦች እና አእምሮዎች ጭምር እንጅ፡፡
ፈይሳ ልክ እንደ ስሚዝ እና ካርሎስ በተመሳሳይ መልኩ ለበርካታ ጊዚያት የዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተሟጋች በመሆን ሲወደስ እና ሲዘከር ይኖራል፡፡
ስሚዝ፣ ካርሎስ እና ፈይሳ የፈጸሙት ድርጊት እውነተኛ የአሜሪካ መስራች አርበኞች የፈጸሙት እውነተኛ የመንፈስ እና ቃላት ድርጊት እንደሆነ አምናለሁ፡፡
ወጣቱ አሌክሳንደር ሀሚልተን (አንዱ ያሜሪካ ቆርቅዋሪ) እንዲህ በማለት ጽፎ ነበር፣ “የሰውን ባህሪ ከእራሱ በላይ አድርጎ በቆራጥነት እና በጀግንነት እንዲወጣ ሊያደርግ የሚያስችል በነጻነት ውስጥ አንድ ልዩ የሆነ የማድረግ ጉጉት አለ“ ነበር ያለው፡፡ ሀሚልተን የእንግሊዝ በሙያ ክህሎት የተካነው የጦር ኃይል በአንድ የማድረግ ጉጉት በተጠናውተው ቆራጥ እና ጀግና አማጺ ሊሸነፍ እንደሚችል ያምናል፡፡ ካርሎስ እና ስሚዝ በዝቀተኛው የህብረተሰብ ክፍል የሚገኙት የሲቪል ማህበረሰቡን መብት የማስከበር ጉጉት ያደረባቸው ጀግኖች የመብት ተሟጋቾች በአሜሪካ ውስጥ ዘረኝነትን እና ድህነትን ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ያምናሉ፡፡ ፈይሳ ለነጻነት ያለውን ጉጉት ቆራጥነት እና ጀግንነትን በተላበሰ መልኩ በዓለም አቀፍ ደረጃ በቢሊዮኖች እንዲታይ በማድረግ ወደ ተጨባጭ ተግባር ተርጉሞታል፡፡
ወጣት ጀምስ ማዲሰን (የአሜሪካ ሕገ መንግስት መስራች አባት) አብዮታዊ በሆነ ብሄራዊ የአንድነት እና የዓላማ መንፈስን በመተግበር እንዲህ የሚል ዝናን ተጎናጽፏል፡ “የነጻነት መንፈስ እና አርበኝነት ሁሉንም የሰው ልጆችን የደስታ መጠን እና ዋጋዎች ግኡዝ ያደርጋሉ፡፡“  እንደዚሁም ሁሉ ካርሎስ እና ስሚዝ እ.ኤ.አ በ1968 እንዳደረጉት ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የነጻነት መንፈስ እና አርበኝነት ፈይሳን እ.ኤ.አ በ2016 ግኡዝ አድርገውታል፡፡
የምክንያታዊነት ደጋፊና አምፅ አንቀሳቃሽ  የሆኑት ሳሙኤልሰን አዳምስ በአንድ ወቅት እንዲህ በማለት አስጠንቅቀው ነበር፣ “ለእውነተኛ አርበኞች ዝምታን መምረጥ አደገኛ ሁኔታ ነው“ ነበር ያሉት፡፡
እውነተኛ የአሜሪካ አርበኞች ስሚዝ እና ካርሎስ እና የኢትዮጵ አርበኛ ፈይሳ ሌሊሳ በኦሎምፒክ መድረክ ዝምታን መርጠው ነበር፣ ሆኖም ግን ወደ ላይ ከፍ ያሉት ቡጢዎቻቸው እና የተጣመሩ እጆቻቸው ስለዘርኝነት፣ ስለጎሳ ጥላቻ፣ ስለኢፍትሀዊነት እና ስለአድልኦ በርካታ ነገሮችን ተናግረዋል፡፡
የኢትዮጵ የአቦ ሸማኔዎች ግድያ ለመጣል በማዛጋት ያጉረመርማሉ፣
“የአቦ ሸማኔ – ጉማሬ” መጽሐፍ ደራሲ የሆኑት የጋናው ኢኮኖሚስት ጆርጅ አይቴይ በአፍሪካ ውስጥ የሚታየውን የአመራር ቀውስ ለመግለጽ  የአቦ – ሸማኔን ተመሳስሎ በመውሰድ እንዲህ የሚል ምልከታ አድርገው ነበር፣ “የአፍረካ አቦ ሸማኔዎች በለውጥ የታጀቡ ጠንካሮች ናቸው፣ ምሁራዊ የአእምሮ የማድረግ ቅልጥፍና እና በተግባራዊ ውጤታማነት ላይ ልዩ የሆነ ትኩረት አላቸው፡፡ እረፍትየለሽ ትውልዶ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ሆኖም ግን የአፍሪካ አዲስ ተስፋዎቸ ናቸው፡፡ ስለሙስና፣ ስለውጤት አልባነት፣ ስለክህሎት የለሽነት እና ስለብቃትየለሽነት ወይም ደግሞ ስለእርባናቢስ ባህሪ ትዕግስቱ ፈጽሞ የላቸውም“ ነበር ያሉት፡፡
አቦ ሸማኔ ፈይሳ ሌሊሳን ተመልከቱት!
የኢትዮጵያ ተስፋዎች የሆኑትን የኢትዮጵያውን ወጣት አቦሸማኔዎችን ተመልከቱ፡፡
ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር እና እንደ ሕዝብ የመቀጠል የህልውና ዕድል ቢኖራቸው ያ የመኖር ህልውና ሁልጊዜ በእራሷ ወጣቶች የመፍጠር ችሎታ፣ የማይበገር የአካል፣ የአእምሮ ጥንካሬ የማሳየት ብቃት፣ ጽናት፣ መልካም ፈቃድ፣ የመፈጸም ብቃት፣ እና መስዋዕትነት በመክፈል ሁኔታ ላይ የሚወሰን ነው እላለሁ፡፡ ይኸ ሁኔታ በወጣቶች ላይ ታላቅ ሸክምን አስቀምጧል፡፡ ከባዱን ነገር ለማንሳት፣ ከባድ ስራዎችን ለመስራት እና መስዋዕትነትን በመቀበል የአንበሳውን ድርሻ (የአቦ ሸማኔውን ሳይሆን) ማድረግ አለባቸው፡፡
እንደዚሁም ሁሉ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ወጣቶች እንደ ወጣት መቀጠል ቢችሉ እና የመኖር ዕድል ቢኖራቸው በቀድሞው ትውልድ ለመጭው ትውልድ ንቁ እና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ በማድረግ ጥንካሬ ላይ የሚወሰን ነው፡፡
የኢትዮጵያ የጉማሬው (የቀድሞው ትውልድ) አቦ ሸማኔዎቻችን ተስፋ እንዳያጡ እና እንዳይወድቁ የምንችለውን ሁሉ ማድረግ አለብን፡፡ ይህንን ማድረግ ከቻሉ በአንጸባራቂነት እንዲወጡ እና ደግመው እና ደጋግመው እንዲያደርጉት ማስቻል አለብን፡፡
እኛ የቀድሞው ትውልድ አባላት የቱንም ያህል ጊዜ ቢፈጅም፣ ገሀነም ወይም የቱንም ያሀል በከፍተኛ ደረጃ ላይ ደረሰ ቢሆንም በማንኛውም መንገድ ከአቦ ሸማኔዎቻችን ጎን በጽናት መቆም አለብን፡፡ ከእነርሱ ጋር የውይት መድረኮችን በመክፈት መወያየት እና እነርሱን እንደምንደግፋቸው እና እንደምንወዳቸው፣ በአዲሲቷ ኢትዮጵያ ግንባታ ውስጥ ተሰማርተው እስካሉ ድረስ እኛ በደስታ የእነርሱ ውኃ አቀባይ እንደሆንን ልናረጋግጥላቸው ይገባል፡፡
አብዛኞቻችን እኛ የጉማሬው ትውልድ አባላት ታላላቅ ነገሮችን ለመስራት ሊያመልጡን የማይገቡ ዕድሎች በፍጹም ሊያመልጡን የማይገቡ ዕድሎች ናቸው፡፡ (ውይ እንዴት የሚያም ነገር ነው! እውነት እንዴት እንደሚጎዳ!)
ታላላቅ ነገሮችን ለእራሳችን መስራት ማለትም አይደለም፡፡ ለሌሎች ነው መስራት ያለብን፡፡ መስራት ያለብን ኃይል ለሌላቸው፣ መከላከያ ለሌላቸው፣ ለተስፋ የለሾች፣ ለመጠለያ የለሾች፣ ለሀገር አልባዎች እና ለምቾት የለሾች ነው፡፡
ከአቦ ሸማኔዎች ጎን በመቆም አቦ ሸማነኔዎቻችንን በመርዳት ይህንን ቅዱስ የሆነ አጋጣሚ እንዳናጣው ጥረት እናድርግ፡፡
የጀግና ጉዞ፣
ሺ ፊቶችን የሚጋፈጠው የጆሴፍ ካምፕቤል ጀግና በዓለም አቀፍ ደረጃ ጀግንነትን ለመስራት እና ድልን በወሳኝነት እስከመጨረሻው ለመቀዳጀት ሁሉንም ዓይነት ስቃዮች፣ መከራዎች መጋፈጥ አለበት፡፡ ማናቸውንም ፍርሀት ከሚያስከትሉ ነገሮች፣ ከሚያበሳጩ እና መከራ ከሚያስከትሉ ነገሮች ጋር ሁሉ ፊት ለፊት ይጋፈጣል፡፡ ሞትንም ሊጋፈጥ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን ጅግና በሁሉም ጉድለቶች ሳቢያ አይንበረከክም፡፡
ፈይሳም እንደዚሁ በተመሳሳይ መልኩ በእርሱ የዓለም ጀግንነት ከታላላቅ ተግዳሮቶች እና የህይወት አጋጣሚዎች ጋር መጋፈጥ አለበት፡፡
ያለምንም ጥርጥር ከእራስ መተማመን ጥርጣሬ፣ በእራስ ከማዘን፣ ከራስ ትችት፣ ከሀዘን፣ ከጥፋት፣ ከጸጸት፣ ከሀሜት፣ ከሀዘን እና ከብስጭት እራሱን ነጻ እንደሚያደረግ የሚያጠራጥር ጉዳይ አይለም፡፡
ቃላት ሊገልጹት ከሚችሉት በላይ ልጆቹን እና ባለቤቱን ሊያጣ እንደሚችል የሚያጠራጥር ጉዳይ አይደለም፡፡ ሆኖም ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለእውነተኛ የሰው ልጆች ስጋ ለለበሱ ሰይጣኖች ሳይሆን ለሁሉም የሰው ልጆች መለያ ባህሪያት ናቸው፡፡
እነዚህ ነገሮች ለረዥም ርቀት ሯጩ ታላቅ ሸክም ናቸው፡፡
ሆኖም ግን ፈይሳ በማወቅ ሁሉንም የእርሱን ምቾት በመሰዋት ለልጆቹ፣ ለባለቤቱ፣ ለወላጆቹ፣ እና ለእርሱ ሕዝቦች እንደ ሰብአዊ ፍጡር ክብር እና ነጻነት አግኝተው እንዲኖሩ በማሰብ ያደረገው ጉዳይ ስለሆነ የሚጸጸትበት ነገር አይሆንም፡፡
ፈይሳ እና ሁላችንም ከእርሱ ጎን የቆምን እና በኢትዮጵያ ውስጥ ለዴሞክራሲ፣ ለነጻነት እና ለሰብአዊ መብት መከበር የማራቶን ሩጫ ለመሮጥ የተዘጋጀን ሰዎች ሁሉ በመጨረሻ የወርቅ ሜዳሊ አሸናፊዎች እንደምንሆን ምንም ዓይነት ጥርጣሬ የለኝም፡፡ ማራቶን መንፈስ አይደለም፣ ስለሆነም የፍጥነት ምህዋራችንን ጠብቀን መሮጣችንን መቀጠል አለብን፡፡
የጀግኖች ጉዞ በፍጹም ቀላል አይደለም፡፡ ለዚህም ነው በዓለም ላይ እንደዚህ ያለውን ከባድ ሸክም ለመቀበል ፈቃደኛ የሆኑ በጣም ጥቂት እውነተና ጀግኖች ብቻ ያሉን፡፡
አብዛኞቻችን ለውጥን እንፈራለን፣ እናም በይበልጥም ደግሞ የእራሳችንን አእምሮ ለመለወጥ እንፈራለን፡፡ ስለሆም በፍርሀት ብርድ ልብስ ውስጥ በመወሸቅ ፍጹም በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ወድቀን እንገኛለን፡፡
እንደ ጀግና ኢትዮጵያዊ የፈይሳ ገጽታ ለሁሉም ኢትዮጵያውን እንደ ነጻነት ጠባቂ፣ ዘብ፣  የዴሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ተሟጋችነት ሚና እውነታነት ተተርገሟል፡፡
እንደ ካምፔል ምዕናባዊ ጀግና በተመሳሳይ መልኩ ፈይሳም ሁሉንም ነገር መስዋዕት ያደረገለትን ጉዳይ አጥብቆ በመያዝ የሁሉም ፈዋሽ መድሃኒት እና ሀብት በመያዝ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ ሀገሩ ይመለሳል፡፡
ምናልባትም ፈይሳ ስለሰራው ቆራጥነት እና ጀግንነት ትልቅ አክብሮት ላንሰጥ እንችል ይሆናል፡፡
የእርሱ ቀደምት አባቶች ኢትዮጵያን ከውጭ ወራሪዎች፣ ከቅኝ ተገዥነት እና ከኢምፔሪያሊዝም ተጽዕኖ ለዘመናት የሀገራችንን ነጻነት ለመጠበቅ በደማቸው፣ በላባቸው እና በእንባዎቻቸው ክቡር ዋጋ የከፈሉ ሲሆን ፈይሳ ግን በእግሩ እና በእጆቹ ብቻ በመጠቀም ፈጽሞታል፡፡
ብቸኛው ልዩነት ግን ፈይሳ በሀገሩ በስልጣን ኮርቻ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የሚገኙትን የማፊያ ወንጀለኛ ወሮበላ የዘራፊ ቡድን ስብስብን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማስወገድ የከፈለው መስዋዕትነት የመሆኑ ጉዳይ ነው፡፡
የፈይሳ እንደ እውነተኛ ኢትዮጵያዊ አርበኛ ሆኖ እንደገና የመወለድ ሁኔታ የሚመጣው ሀገሩ ኢትዮጵያ  ከዘራፊዎች፣ ወሮበሎች እና ከወንጀለኞች አፈና ነጻ ከሆነችው ምድር ላይ ከቤተሰቡ ጋር እንደገና መገናኘት ሲችል ነው፡፡
ፈይሳ ወደ ሀገሩ በሚመለስበት ጊዜ እርሱን ሰላም ለማለት ሚሊዮኖች መንገዶችን ሁሉ በሰልፍ እንደሚያጣብቡ አልጠራጠርም…
አቤት ጉድ እኮ ነው፣ መላዕክቶች ወደ ሀገራቸው በሚመለሱበት ጊዜ…ሰይጣኖቹ በቀጥታ ወደ ገሀነም ይወርዳሉ፡፡
እ.ኤ.አ በ2011 ያስተላለፍኩትን መልዕክት እንደገና በ2016 ለኢትዮጵያ ወጣቶች እናገራለሁ፣
እ.ኤ.አ በ2011 እንዲህ የሚል መልካም የሆነ መልዕክት ለኢትዮጵያ ወጣቶች አስተላልፌ ነበር፡
“የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋርጠውባቸው ስላሉት ማናቸውም ችግሮች መፍትሄ ሊሆን የሚችል ታምራዊ ቀመር በፍጹም የለኝም፡፡ ለሁሉም ወጣት ኢትዮጵያውያን ለማስተላለፍ የምፈልገው ዋና ጉዳይ እንዲህ የሚል ቀላል ነገር ነው፡፡ ‘በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ፣ በፍጹም!’ አእምሮዎቻችሁን ከአእምሮ ባርነት ነጻ አውጡ፡፡ የመፍጠር ኃይላችሁን አሳድጉ፡፡ እርስ በእርሳችሁ ተማሩ፣ አስተምሩ፡፡ እንደ እናት ኢትዮጵያ ልጆችነታችሁ ተባበሩ፣ እናም በጎሳ፣ በቋንቋ፣ በአካባቢያዊነት ወይም በመደብ መሰረትነት የሚከፋፍላችሁን ማንኛውንም ርዕዮት ዓለም አስወግዱ፡፡ ስለሳይንስ እና ስለማህበረሰብ ትምህርታችሁ ብቻ ሳይሆን ከዚህም በተጨማሪ ስለ ሕጋችሁ፣ ስለሕገ መንግስት እና ስለሰብአዊ መብትም አጥኑ፡፡“ 
እ.ኤ.አ በ2016 እንደገና ይህንኑ መልዕክት በድጋሜ በአስቸኳይ እንዲህ በማለት ላክሁ፡
የኢትዮጵያ የወጣት ኃይል በምንም ዓይነት መንገድ የሚቆም እንዳልሆነ በእያንዳንዱ የሰውነታችን ክፍል ይታወቃል፡፡
በፍጹም እጅ እንዳትሰጡ! በፍጹም!
እንደ እናት ኢትዮጵያ ልጅነታችሁ ሁላችሁም ተባበሩ፡፡
ዘርን፣ ቋንቋን፣ ኃይማኖትን፣ አካባቢያዊነትን ወይም ደግሞ መደብን መሰረት በማድረግ የሚመጣን ርዕዮት ዓለም ወይም ጥረት አስወግዱ፡፡
እጆቻችሁን በማጣመር ወደ ቤተሰማያት አቅጣጫ በማድረግ ጉዟችሁን ቀጥሉ፡፡ በሰላማዊ መንገድ፡፡
መላዕክት ጉዟቸውን አጠናቅቀው በሚደርሱበት ጊዜ ሰይጣኖቹ ውር ብለው እንደሚበሩ እመኑ፡፡
የእናንተ ትግል ማተኮር ያለበት ከተራው ዓለም ሕዝብ ጋር ያለመሆኑን አስታውሱ፡፡
የእናንተ ትግል በገሀነም ውስጥ ካለው ከሰይጣናዊ ኃይል ጋር ነው፡፡
የእናንተ ትግል እንደገና ህይወት ዘርቶ የጭቆና ህልውናውን ለማስቀጠል የሞት ሽረት ትግል ከሚያደርገው ከጨለማው ልዑል ሠራዊት ጋር ነው፡፡
ሆኖም ግን እናንተ አሸናፊዎች እንደምትሆኑ ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ምክንያቱም አምላክ ከእናንተ ጎን ተሰልፏልና፡፡
እመኑ!
የሀሰት ልዑሎች ይወድቃሉ፣ አፈር ትቢያም ይሆናሉ፣ እናም ኢትዮጵያ እጆቿን ወደ እግዚአብሄር ትዘረጋለች ተብሎ በቅዱሱ መጽሐፍ ተጽፏልና፡፡
የሰላም እጆቻችሁን ለኢትዮጵያውያን ወገኖቻችሁ ዘርጉ!
እጆቻችሁን ወደ ላይ ወደ አየር ከፍ በማድረግ አጣምሩ፣ እናም ሰይጣኖች በምንም መንገድ ሊያቋርጧቸው አይችሉም፡፡
ለቅሶ ለዛሬ ማታ ብቻ ህልውና ሊኖረው ይችላል፣ ሆኖም ደስታ እና ሀሴት ከነገ ጠዋት ጀምሮ ይመጣል፡፡
አሁን የጧቱ ጊዜ ነው!
የኢትዮጵያ ወጣቶች በአንድነት ወደፊት! ጉዟችሁን በቆራጥነት እና በጽናት ቀጥሉ!
የኢትዮጵያ አቦ ሸማኔዎች ማጉረምረማችሁን የበለጠ አጠናክራችሁ ቀጥሉ!
ድል በእጆቻችሁ መዳፍ ውስጥ ነው! ድል በእጆቻችሁ መዳፍ ውስጥ ነው!
እመኑ!
የኢትዮጵያ ወጣቶች ተባብረዋል በፍጹም ሊሸነፉ አይችሉም!!!
ኃይል ለኢትዮጵያ ወጣቶች!  
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!  
ነሐሴ 25 ቀን 2008 ዓ.ም

አስቸኳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደር እያመሩ




አስቸኳይ በሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን የጫኑ ወታደራዊ ተሽከርካሪዎች በውጫሌ ዞረው ወደ ሰሜን ጎንደር እያመሩ ነው
አብዛኛዎቹ ኤርትራዊያን የሆኑ 6,500 ስደተኞች ሜዲተራንያን ባህር ውስጥ ከመስመጥ መትረፋቸው ተገለጸ

የጋይንት ህዝብ ጨጨሆ ላይ መንገድ ዘግቶ እየተፋለመ እንደሆነ ታውቋል ።



Minilik Salsawi : ሰኣቱ ያለፈባቸው የሕወሓት ኣምባገነኖች ሕዝብን የመፍጀት ነጋሪታቸውን በመጎሰም ሕወሓት ሰራዊትን በኣማራ ክልል ለማስገባት የሚያደርጉት ግብግብ ሕዝቡ ያለውን ሃይል በመጠቀም እያከሸፈባቸው ሲሆን በጨጨሆ በተደረገው ውጊያ ሕዝቡ መስመሩን ኣሳብሮ ባደረሰው ጥቃት የሕወሓት ሰራዊት እንዲያፈገፍግ ኣድርጎታል።
የጋይንት ህዝብ ትናንት ከሌሊቱ አስር ሰአት ጀምሮ እስካሁን ድረስ ከአግዓዚ ወታደሮች ጋር ጨጨሆ ላይ መንገድ ዘግቶ እየተፋለመ እንደሆነ ታውቋል ።

በፈንታሌ ወረዳ በከረዩ ኦሮሞዎችና በአግዓዚ ወታደሮች መሃከል ከባድ ጦርነት ተደረገ




በፈንታሌ ወረዳ በከረዩ ኦሮሞዎችና በአግዓዚ ወታደሮች መሃከል ከባድ ጦርነት ተደረገ Minilik Salsawi
በምስራቅ ሸዋ ፈንታሌ ወረዳ ጡጢ በተባለ ቦታ ላይ ከረዩ ኦሮሞውችን ከአማራ ጎረቤቶቹ ሊያጋጭ ተልኮ የነበረው የአጋዚ ጦር ከከረዩ አርብቶ አደሮች ጋር ባደረገው ውጊያ 4 አጋዚዎች ተገድለው 13 ቆስለው ወደ አዳማ እና አዲሳበባ ሆስፒታሎች ተወስደዋል። ከ አርብቶ አደሩ 3 ሰው የተሰዋ ሲሆን 6 ቆስሏል።

በወገራ የሕወሓት ወታደሮች ሕጻናትን ሁሉ እየጨፈጨፉ ነው – ሽንዲ ወያኔዎች ከዐማራው ላይ ይፋ ጦርነት እያካሄዱ ነው፡፡



በወገራ የሕወሓት ወታደሮች ሕጻናትን ሁሉ እየጨፈጨፉ ነው፤በሰሜን ጎንደር የሕወሓት ወታደሮች ሁሉንም ዐማራ በእድሜ ሳይለዩ እየጨፈጨፉ ሲሆን ሕጻናት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ እስካሁን ድረስ ባለን መረጃ የ፮ ሕጻናት አስከሬን ጎንደር ዩንቨርሲቲ ሆስፒታል እንደገባ እና ከ፳ በላይ የሚሆኑ ምንም የማያውቁ ልጆች ሆስፒታል እንደገቡ የተጎጅ ቤተሰቦች አረጋግጠዋል፡፡
በወንበርማ (ሽንዲ) ወረዳ ወያኔዎች ከዐማራው ላይ ይፋ ጦርነት እያካሄዱ ነው፡፡ እስካሁን ሦስት ወንድሞቻችን ተሰውተዋል፡፡ የወንበርማ (ሽንዲ) ሕዝብ ለሁለት ተከታታይ ቀናት አደባባይ በመውጣት ከአገዛዙ ጋር እየተጋደለ ነው፡፡ መንገዶች ዝግ ናቸው፡፡በምእራብ ጎጃም ቡሬ ባለቤትነቱ የሕወሓቱ ቀንደኛ አባልና ሰላይ የሆነ ትንሳኤ የሚባለው ሆቴል ግቢ ውስጥ ሁለት ዐማሮች ተገድለውና ሸንኮራ አገዳ ቅጠል በላያቸው ላይ ተደርጎ ተገኘ፡፡ የሕወሓት ሰዎች ንብረት በሆኑ በዐማራው አካባቢ ተመሳሳይ ግድያዎች እንደሚኖሩ ይጠበቃል፡፡

Tuesday, August 30, 2016

በአማራ ክልል የሕዝቡ ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው።




በአማራ ክልል የሕዝቡ ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል።ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው።
#Ethiopia #Amharaprotests #BahrDar #AmharaResistance #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) በባህር ዳር ተቃውሞ ዛሬም ተቀጣጥሎ መቀጠሉ ታውቋል።ከባሕር ዳር 45 ኪሎ ሜትሮችን በምትርቀው የጉማራ መንደር እስከ ዛሬ ሌለት ድረስ በቆየ የተኩስ ልውውጥ 8 የወያኔ ፌደራሎች ተገድለዋል። 2 ዐማሮች በተጋድሎው ተሰውተዋል። የ8 ፌደራል ሙሉ ትጥቅ ገበሬው ተከፋፍሏል። መንገዶች ዝግ ሲሆኑ ሕዝቡም ራሱን እያስተደዳረ ነው።በባህር ዳር እና አዋሳኝ በሆኑ ከተሞች በህዝብና በወያኔ ቅልብ ወታደሮች መካከል ውጊያ እየተካሄደ ነው፡፡
Minilik Salsawi's photo.
ከባህር ዳር ወደ ጭስ አባይና አዴት ሞጣ ቢቸና በሚወስደው መንገድ ላይ በምትገኘው ሰባታሚት ላይ የአማራ ህዝብ ወያኔን በአኩሪ ጀግንነት እየተፋለመ ነው፡፡በባህር ዳርም ቀበሌ 7 እና 17 ከፍተኛ የተኩስ እሩምታ እየተሰማ ነው። ወያኔ በማንኩሳ ዐማሮች ላይ ሙለ ጦርነት አውጇል።ከማንኩሳ አካባቢ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው የወያኔ ነፍሰ ገዳይ ወታደሮች ሕጻናትን ጨምሮ በደካሞችና አዛውንቶች ላይ ሁሉ እያነጣጠሩ እየተኮሱ ነው።ማንኩሳ ማንኛውም ዓይነት መረጃ መለዋወጫ መንገድ ተዘግቷል። #ምንሊክሳልሳዊ
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.


ኢትዮጵያ ማለት አዲስ አበባና እና መቀሌ ብቻ ነው እንዴ ? የዛሬው የአማራው ክልል ዉሎ – #ግርማ_ካሣ

  


14192647_1171562736235660_8754010325640618866_n
ባህር ዳር ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ያለች ትልቋ ከተማ ናት። በአሁኑ ጊዜ ባባህር ዳር መንግስት የለም ማለት ይችላል። ሕዝቡ በድጋሚ በሕወሃት ላይ ያለውን ጥላቻ ሲገልጽ ነው የዋለው።
በባህር ዳር ብቻ አይደለም በድፍን ጎጃም፣ በድፍን ጎንደር ነው ተቃዉሞ እየተቀጣጠለ ያለው። ዛሬ ብቻ ተቃዉሞዎችን ከተቀላቀሉ ከተሞች መካከል ቻግኒ እና መራዊ ይገኙበታል።
ሕወሃት ለነ አቶ ኃይይለማሪያም ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት፣ ከኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚና፣ ከኢሕአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ የሚል ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው መግለጫዎችን አወጥቷል። እንኳን የሕዝብ ጥያቄ ሊመልስና ለብሄራዊ እርቅ ሊዘጋጅ ቀርቶ፣ ለሚቀጥሉት በርካታ አመታት ጥገናዊ የማስመሰል ለዉጦችን በማድረግ፣ የተወሰኑ አመራር አባላትን፣ ምናልባትም አምባሳደሮች አድርጎ በመሾም ለሚቀጥሉት አመታት “ልማትዊ ዲሞክራሲ” የሚሉትን ግን ልማታዊም ሆነ ዴሞክራሲያዊ ይልሆነ አገዛዛቸዉን ለማስቀጥል መወሰናቸውን ነው የገለጽት።
ሆኖም ግን እነርሱ ግትር በሆኑ ቁጥር የሕዝብ ተቃዉሞ ግለትም በሁለት ሶስት እጥፍ እየጬመረ ነው የመጣው። ሕወሃት ለሰላም በሮቹን በዘጋና የሕዝቡን ጥያቄ በሃይል ለመጭጨፍለቅ በሞከረ ቁጥር፣ ዜጎች ራሳቸውን መመከት ስላለባቸው፣ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ እየተገባ ነው:
ሕወሃቶች አዲስ አበባና መቀሌ ብቻ መረጋጋት ስላላ ሁሉም አማን ነው ፣ ሌላ ቦት ያለው ተቃዉሞ ይበርዳል ከሚል ይሆናል ጊዜ እየወሰዱ ያሉት። ሆኖም ግን በአሁኑ ጊዜ በብዙ የአማራው ክልል ከተሞች የኢሕአዴግ መንግስት የፈረሰበት ሁኔታ ነው ያለው። በቅርብ ጊዜ ዉስጥ ደሴ፣ ደብረ ብርሃኑ፣ ፍቼ፣ ሸኖ እያለ አዲስ አበባ መድረሱ አይቀሬ ነው። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ወደ መቀሌ የሚወስዲ መስመሮችም ሙሉ ለሙሉ ይዘጋሉ። ከሕዝብ ጋርር ተጣልቶ እየቀለዱ መኖር ክዚህ በኋላ አይቻልም። ለሕወሃት መሽቶበታል። ስልጣን በስላም ለሽግግር መንግስት አስርክብሩ ከመሄድ ዉጭ ሌላ የተሻለ አማራጭ የላቸውም:
በአማራው ክልል እየሆነ ስላልለው ነገር ጋዜጠኝ ሙሉቀን ተስፋው ፣ ዛረ ነሐሴ 23 ቀን በሁለት ክፍል ያቀረበውን አንድ ላይ አደርጌ እንደሚከትለው አቅርቤዋለሁ። ጋዜጥጠኛ ሙሉቀን “አማራ” ብሎ ቢጠራም በአምራው ክልል ተቃዉሞ እያሰሙ ያሉ አገዎች፣ ቅማንቶች ፣ የተለያዩ ብሄረሰብ አባላትም፣ ያሉበት መሆኑ መረሳት የለበትም። አገራችን የብዙ ብሄር ብሄረሰቦች አገር እንደመሆኗም፣ በተቻለ መጠን የተናጥን ማንነታችንን ከምንጠቀም የጋራ ማንንታችንን መምጠቀሙን ብንጀመር ጥርኡ ሊሆን ይችላል ብዬ አስባለሁ።
========================
ባሕር ዳር
——–
በባሕር ዳር ከተማ በሕዝብ የተጠረውን የቤት ውስጥ አድማ ለማደናቀፍ በሞከሩ የወያኔ አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ንብረት ላይ ዐማራው እርምጃ እየወሰደ ነው፡፡ የዐማራው ሕዝብ ቆራጥነቱን በተግባር ያሳየበት ከዛሬ የበለጠ ቀን አልነበረም፡፡ ጠዋት አካባቢ አድማውን ችላ በማለት ሥራ የጀመረ አንድ የከተማ አውቶቡስ ሾፌር መኪናውን ሰባብረው ልጁን እንዲማር መጠነኛ አካላዊ ጉዳት ደርሶበት አሰናበቱት፡፡ ሥራ የጀመረው የንግድ ባንክም ሕንጻ መስኮቶች ተሰባብረዋል፡፡ በሕዝብ አስቀድመው የተለዩ የሕወሓት አባላት እና የዐማራ ቅጥረኛ ባንዳ ሰዎች ስም ዝርዝር አስቀድሞ የተሰራ ሲሆን ተራ በተራ ሲቃጠል ውሏል፡፡ ባሕር ዳር አሁን ከዝናቡ ጋር በጭስ ታፍናለች፡፡ ከቦታው አስተያየቱን እንዲሰጠን የጠየቅነው የከተማዋ ነዋሪ ‹‹የጥይት ሩምታው ይሰማሃል? የቤት ጣራ ላይ ሆኜ ነው የማወራህ አንድ ሁለት… ወደ ዘጠኝ ቤት ሲቃጠል ይታየኛል እኛ ሰፈር እንኳ፡፡ የአምቡላንስና የጥይት ድምጽ እየረበሸኝ ነው›› ሲል የነበረበትን ሁኔታ ገልጦልናል፡፡ ቀበሌ 08 የሚባለው ሰፈር በርካታ ቤቶች የተቃጠሉበት ነው ተብሏል፡፡
በባሕር ዳር በዛሬው የዐማራ ተጋድሎ ቀበሌ 06 ሦስት ዐማሮች ተሰውተዋል፡፡ ቀበሌ 14 ኤፍራታ እሚባለው አካባቢ ደግሞ ለታጋይ ዐማሮች ውሃና ምግብ ለማቅረብ ሲሄዱ የነበሩ እናት ወድቀው መሰዋታቸውን ሰምተናል፡፡ በርካታ ተሸከርካሪዎች የተቃጠሉ ሲሆን ዐማራው በየሰፈሩ የጎበዝ አለቃዎችን እየመረጠ በመታገል ላይ መሆኑን ሰምተናል፡፡ ያልተዘጋ መንገድ የለም፡፡ የዐማራ ፖሊስ ሕዝብን በመጠበቅ ያደረገው ተጋድሎ የሚደነቅ መሆኑን ሰምተናል፡፡ በባሕር ዳር ዛሬ የተደረገው ተጋድሎ እጅግ የሚያኮራና ከተማዋን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ ሕዝቡ የተቆጣጠረበት ሁኔታ እንዳለ ሰምተናል፡፡ የባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢ የዐማራን ተጋድሎ ሲያንጸባርቁ ውለዋል፡፡
ከባሕር ዳር ከተማ 17 ኪሎ ሜትር አካባቢ ያለችው የመሸንቲ ከተማና የይባብ ኢየሱስ ቀበሌም የዐማራ ተጋድሎ ከዋለባቸው ቦታዎች ውስጥ ናቸው፡፡ መሸንቲ ያለው የሕወሓት አባል የድንጋይ ጠጠር ማምረቻ ፕላንትም ተቃጥሏል ተብለናል፡፡
መራዊ፤
——
በመራዊ ከተማ የዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ የወጣው በጠዋት ነበር፡፡ የሜጫዋ መራዊ ከተማ እንደ ባሕር ዳር ሁሉ በጢስ ታፍና ውላለች፡፡ ለተጋድሎ የወጣው የዐማራ ሕዝብ ከጉያው ተሸጉጠው ሲያንገላቱት የነበሩትን የሕወሓት አባላትና ቅጥረኛ ባንዳዎች ሀብትና ንብረት ተለቅሞ ተቃጥሏል፡፡ የገብረ ሥላሴ ኃይለማርያም ክሊኒክና ፋርማሲ፣ የገ/ድህን ክሊኒክ፣ ፒታ ዳቦ ቤት፣ ኃይሌ ፎቅ፣ የኢትዮጵያ እህል ንግድ ድርጅት፣ ብአዴን ጽ/ቤትና በርካታ የሰላዮች መኖሪያ ቤትና ንብረት ወድሟል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ከተማዋን ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ጊዜ ድረስ ተቆጣጥሯት ይገኝ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
አዴት
—–
የይልማና ዴንሳዋ አዴት ከተማ በዐማራ ተጋድሎ ስትናጥ ውላለች፡፡ ከአዴት ከተማ የሚገኘው ሪፖርተራችን የላከልን መረጃ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ የአዴት ሕዝብ በነቂስ ወጥቶ ወያኔን ሲቃወም ዋለ፡፡ በአዴት ከተወለዱ በጤና እያለ አንድስ እንኳ እቤት የዋለ የለም፡፡ ከወጣት እስከ ሽማግሌ፣ ሴትና ወንድ፣ እስላምና ክርስቲያን ሁሉ በቁጣ ገንፍሎ ወጥቷል፡፡ ሰልፉን የሰሙ የይልማና ዴንሳ አርሶ አደሮችም ከወንዳጣ ድረስ እየመጡ በወኔ ተጋድሎውን ተቀላቅለው ውለዋል፡፡
‹‹ወያኔ ሕወሓት ሌባ ነው፤ ቅጥረኛው ብአዴን አይወክለንም፤ ድንበራችን ተከዜ ነው፤ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ በዐማራ ላይ የሚደርሰው ጭቆና ይቁም፤ የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ይቁም፤ …›› እና ሌሎችም መፈክሮች ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የዐማራው ሕዝብ ወደ ባሕር ዳር በኩል 2 ኪሎ ሜትር መንገድ በመጓዝ አቦላ ተራራ አካባቢ ያለውን መንገድ መዝጋት ቅድሚያ የሠጠው መርሃ ግብር ነበር፤ ይህም የወያኔን አልሞ ተኳሾች እንዳይመጡ መንገዱን ማበላሸት ሲሆን ይህን የሰሙት የባሕር ዳር አናብስት ወጣቶች ሰባታሚት አካባቢ መንገዱን ጠርቅመው በመዝጋት የአዴት ዐማሮችን ተባብረዋል፡፡ ሰልፈኞች ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩ ወጣቶችን ሰብረው በመግባት አስፈትተዋል፤ የአስተዳደር ቢሮው ተሰባብሯል፡፡ የገንዘብና ኢኮኖሚ ጽ/ቤት ኮምፕዩተሮች በእሳት ጋይተዋል፡፡ አካለ መንግሥቱ የሚባለው የወያኔ ቅጠረኛ ዐማሮችን ሲሰልልና ሲያሰቃይ የሰነበተ ሲሆን የሕንጻ መሣሪያ መደብሩ ወድሞበታል፡፡
ክሊኒክና ፋርማሲ በመክፈት የአዴት ዐማራን ጊዜው ባለፈበት መድኃኒት ሲበዘብዙና ሲሰልሉ የነበሩት የገ/እግዚአብሔር ቤተሰቦች ከሳምንታት ቀደም ብለው ከአዴት ቢወጡም ንብረታቸውና መኖሪያ ቤታቸው በእሳት ከመጋየት አልዳነም፡፡ የገ/እግዚአብሔር ልጅ የሆነው አቶ አማኑኤል ዐማሮችን በሽጉጥ ሲያስፈራራ የሰነበተ ሲሆን ዛሬ ተፈልጎ የገባበት ሳይታወቅ ቀርቷል፡፡ ይህ በዚህ እንዳለ የወያኔ ቀኝ እጅ የሆኑት የሃይማኖት አባቶች ሰልፉን ለመገላገል ቢገቡም እናንተን አንሰማም ብሎ አሳፍሮ መልሷቸዋል፡፡ ይልማና ዴንሳ በህዝብ ቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ ለዘጋቢያችን ምስጋና ይድረሰው፡፡
ዳንግላ
——
የአገው ምድሯ ዳንግላ ከተማ የዐማራን ተጋድሎ የተቀላቀለችው ትናንት ነበር፡፡ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. ከጠዋቱ 1፡00 ጀምሮ የዳንግላ አገው ዐማራ ሕዝብ ለተጋድሎ ወጣ፡፡ የዐማራውን ጥያቄዎች አንግቦ ወደ ወኅኒ ቤቱ አቅጣጫ ሲሄድ መዘጋጃ ቤት አካባቢ ሲደርስ የወያኔ አባል የሆነው የመዘጋጃ ቤት ሠራተኛ አቶ ሀብተወልድ ወደ ሕዝብ በመተኮስ ሁለት ሰዎችን አቆሰለ፡፡ ሕዝብ ተቆጣና የአቶ ሀብተወልድን ቤት ሙሉ በሙሉ አቃጠለው፡፡
ወደ መሃል ከተማ ሲመጣ አንድ ቅጥረኛ የሆነ ያረጋል የሚባል ፖሊስ የዳሸን ቢራ ማስታወቂያን ከሚቀዱት የአገው ዐማራ ወጣቶች ላይ ጥይት አርከፈከፈ፡፡ ፖሊሱ የቤቱን አጥር ጉድብ ይዞ ሁለት ሰዎችን ገደለ፡፡ ከሕዝብ ጋር በሚያደርገው ትንቅንቅ ጥይት ጨረሰ፡፡ ሕዝቡ ሊይዘው ሲል ጎረቤቱ አንድ ካዝና ጥይት ሲሰጠው አናብስቶቹ አዩት፡፡ ባንዳው ጎረቤቱ ተጨፍጭፎ ተገደለ፡፡ ፖሊሱ ቢያመልጥም ቤቱ ከመቃጠል አላመለጠም፡፡ ይህ ሙሰኛ ፖሊስ መኖሪያ ቤት ውስጥ 50 ኩንታል ስኳርና 20 ጀሪካ ዘይት ተደብቆ ተገኘ፡፡ ሁሉም ንብረት አብሮ እንዲወድም ተደረገ፡፡ መኪናም ነበረችው፤ ወደመች፡፡
ዳንግላዎች ወደ ቤታቸው ገቡ፡፡ ነሃሴ 23 ቀን ጠባ፡፡ ዳግም ለተጋድሎ ተሰለፉ፡፡ ከዚያም ዳንግላ ከተማ ከክረምት ጉም እኩል የእሳት ጭስ አፈናት፡፡ የህወሓት አባላትና የቅጥረኛ ባለሥልጣናት ቤት ሙሉ በሙሉ ወደመ፡፡ ከተማዋም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆነች፡፡ የከንቲቫው (አቶ ሙላት እሸቴ) በሙስና የተከማቹ ሦስት ቤቶች፣ የጥቃቅን ኃላፊው አቶ ያለው ዘለቀ፣ የብአዴን ኃላፊው አቶ ዳዊት ብርሃኑ፣ የማዘጋጃ ኃላፊው አቶ መንግሥቴ ቢተው፣ የትራፊክ ፖሊሱ አቶ አይተነው፣ የደኅንነቱ አቶ ይመኑ፣ እና ሌሎችም ዛሬ ወደ አመድነት ከተለወጡ በቶች ጥቂቶቹ ናቸው፡፡
የአጋዚና የፌደራል ፖሊስ አባላት ከተማዋን ቢወሯትም ሕዝብን ግን እስካሁን ማሸነፍ አልተቻለም፡፡
እንጅባራ
——–
በእንጅራባራ ከተማ ትናንት ነሃሴ 22 ቀን 2008 ዓ.ም. በተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ ከመቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ወጥቷል፡፡ የሕዝቡን ብዛት ሲገልጹ በባሕር ዳር፣ በጃግኒና በአዲስ አበባ መውጫ መንገዶች እስከ ሦስት ኪሎ ሜትር ድረስ የሚረዝም የሰው ጎርፍ ነበር ብለዋል መረጃዎቻችን፡፡ ወልቃት ዐማራ ነው፤ የታሠሩ ኮሚቴዎቻችን ይፈቱ፤ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፤ የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች ተሰምተዋል፡፡
በእንጅባራ በዞኑ ጸጥታ ዘርፍ የሚሠራ አንድ ታፈረ የሚባል አገው ዐማሮችን በማሰቃየት የታወቀ ቅጥረኛ በሕግ አምላክ እየተባለ አንድ ሰው ገደለ፡፡ ከዚያ የትግሬ አጋዚ ሠራዊት ደርሶ ሌሎች 5 አገው ዐማሮችን የገደለ ሲሆን 19 ሰዎችን ደግሞ አቁስሏል፡፡ ሕዝቡ በንዴት እና በደም ፍላት አቶ ታፈረ የተባለውን ባንዳ ሊገድል ቢሞክርም በማምለጡ ልጁ ተገድሏል፡፡ ሕዝብ በንዴት ወደ ቤት ሳይገባ በውጭ አድሯል፡፡
የእንጅባራ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን በርካታ የሕወሓት አባላትና የቅጥር ባንዳዎች መኖሪያ ቤቶችና ንብረቶች ተቃጥለዋል፡፡ እንጅባራም በጭስ ታፍነው ከዋሉ ከተሞች አንደኛ ሆናለች፡፡ የአገዚ ጦር ዛሬ ሌሎች 6 ወንድሞቻችን በሞት ነጥቆናል፡፡ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ ዛሬም እየተውለበለበ ሲሆን የእንጅባራ ከተማ አሁንም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ነው፡፡ በርካታ መኪናዎች እየተቃጠሉ ነው፡፡
የተጋድሎው መቀጠል አለመቀጠል በተመከተ ለአንድ የእንጅባራ ነዋሪ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹ገና ገና ገና ይቀጥላል!›› ሲሉ በሙሉ ልብና በእርግጠኛነት ተናግረዋል፡፡ እኚሁ አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ‹‹የዐማራ ጥያቄ ሳይመልስ መቼም ቢሆን እኛ አናቆምም፤ መንግሥቱን አፍርሰነዋል፤ ቀጣይ ሥራችንም የጎበዝ አለቆችን መምረጥ ነው፤ ወቅቱ የአዝመራ ጊዜ ቢሆንም ገበሬው ከነጻነት በኃላ ይደርሳል እያለ እየተቀላቀለን ነው›› ሲሉ አክለው ገልጸዋል፡፡
ስማዳ
—–
የስማዳዋ ወገዳ ከተማ ዐማሮች ዛሬ በጠዋት ነበር ተጋድሏቸውን የጀመሩት፡፡ ዛሬ ሦስት አካበቢ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ የዐማራውን ሕዝብ ጥያቄ ሲያስጋባ ከዋለ በኋላ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ በክብር ተውለብልባለች፡፡ በወረዳው የወያኔ ቅጥረኛ የሆነ አንድ ፖሊስ ሦስት ያክል ሰዎችን ገድሎ ከዐሥር በላይ ደግሞ ማቁሰሉን ከቦታው አረጋግጠናል፡፡ ዛሬ በስማዳ የተሰው ዐማሮች ጠቅላላ አምስት ደርሷል፡፡ የአስተዳደር ቢሮ ተሰብሮ ቅጥረኛው ኃላፊ ከከተማዋ ተሰውሯል፡፡ ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ የቆመ ሲሆን በአቅራቢያ ባሉ የሙጃና የሦስቻም የገጠር ቀበሌዎችም ላይ ተጋድሎ እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ቻግኒ/ መተከል
—————
ዛሬ በጃግኒና በመተከል ባሉ ከተማዎች የዐማራ ተጋድሎ ቀጥሎ የዋለ ቢሆንም በስልክ ችግር የተሟላ መረጃ ማቅረብ አልቻልንም፡፡
አንዳቤት/ጃራ ገዶ
—————
የአንዳቤት ዐማሮች ዛሬ ሳይነጋ ሌሊት ዘጠኝ ሰአት ነበር የዐማራውን ተጋድሎ የጀመሩት፡፡ የጃራ ገዶ ከተማ ከወልሽ ከተማ 10 ኪሎ ሜትር የምትርቅ ሲሆን በሌሊት የወጣው ዐማራ አንዳቤት ወረዳን ድብልቅልቅ አድርጓት ውሏል፡፡ የወልሽ ከተማ ነዋሪዎች ወደ ጃራ ገዶ በመሄድ የጃራ ገዶ ደግሞ ወደ ወለሽ በመምጣት አዳማ የሚባለው አካባቢ ተገናኝተዋል፡፡ የአንዳቤት ዐማሮች የጎበዝ አለቆችን እየመረጡ ሲሆን ቀጣይ ቀናት ወረዳው ሙሉ በሙሉ በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በአንዳቤት 5 ዐማሮች በቅጥረኛ ታጣቂዎች የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ቢሆንም የሰው ሕይወት አለመጥፋቱን ሰምተናል፡፡
እስቴ መካነየሱስ
—————
የእስቴዋ መካነየሱስ ከተማ በቤት ውስጥ አድማ መመታቷን ሰምተናል፡፡ የእስቴ መካነየሱስ መንገዶች በሰውና በመኪና ድርቀት ተመተው ውለዋል፡፡ የእስቴን ጤፍ ዘርገቶ የሚይዘው የመካነየሱስ ገበያ አእዋፋት ብቻ ወረውት ውለዋል፡፡ የመካነየሱስ የቤት ውስጥ አድማ ነገም ይቀጥላል፡፡
ጋይንት/ ነፋስ መውጫ
———————-
ትናንት ነሃሴ 22 ቀን የተጀመረው የቤት ውስጥ አድማ በጽጥታ አካላት ጣልቃ ገብነት ደፈረሰ፡፡ የጋይንት አናብስት ተቆጡ፡፡ ተኩስ ተጀመረ፡፡ አንድ ቅጥረኛ ፖሊስ ሦስት ዐማሮችን በጥይት አቆሰለ፡፡ ሕዝቡ ሊገድለው ሲል አመለጠ፡፡ ቤቱ ሔዱ፡፡ ተከራይ ሆኖ አገኙት፡፡ የቤቱን ሙሉ እቃ አውጥተው አስፓልት ላይ አቃጠሉት፡፡ ዐማሮች ከተማዋን ተቆጣጠሩ፡፡
የጋይንት ዐማሮች ተቃውሞ ዛሬም ቀጥሎ ዋለ፡፡ በጨጭሆ በኩልና በደብረ ታቦር መምጫ መንገዶች በሚገባ ተዘግተዋል፡፡ የነፋስ መውጫ ከተማ ሙሉ በሙሉ በዐማሮች እጅ ከሆነች ሁለተኛ ቀኗን አስቆጥራለች፡፡ የጋይንት ወጣቶች በአድማው የሚበሉትን ላጡ ሰዎች የምግብ እና የመጠጥ እርዳታ አድርገዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ የታች ጋይንት ዐማሮችም ለተጋድሎ መውጣታቸውን ብንሰማም ከቦታው ያገኘነው መረጃ ባለመኖሩ ማካተት አልቻልንም፡፡
ደብረ ታቦር
————
የደ/ታቦር ዐማሮች የቤት ውስጥ አድማ ከመቱ ሁለተኛ ቀናቸው ነው፡፡ አንዳንድ ቅጥረኞች ሥራ ለመጀመር ትናንት እንቅስቃሴ ሲያደርጉ ያን የተቃወሙት የታቦር ልጆች በቅጥረኛ ወታደሮች ሁለት ወንድሞቻችን ተነጥቀዋል፡፡
በደብረ ታቦር 94 ቅጥረኛ ሰላዮች የተለዩ ሲሆን በሚቀጥሉት ቀናት ዐማራው ሕዝብ እርምጃ እንደሚወስድ ይጠበቃል ሲሉ አስተያየት የሠጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡ የታቦር ዐማሮች የፌደራል ፖሊሶችን መሣሪያም መንጠቃቸውን ሰምተናል፡፡ በጎበዝ አለቆችም መደራጀት ተጀምሯል፡፡ ደብረ ታቦር ግማሽ ነጻነት ላይ ያለች ከተማ ናት፡፡
የጋሳይና የክምር ድንጋይ
————————
የጋይላንን ክምር ድንጋይ ዐማሮች የካቢኔ አመራሮችን በሙሉ ማስወገዳቸውም ተገልጧል፡፡ ጋሳይና ክምር ድንጋይ መንገዶች ዝግ ናቸው፡፡
ወረታ/ ጉማራ
———-
የወረታ ከተማም ትናንት ጀምሮ የቤት ውስጥ አድማ ላይ ናት፡፡ ትናንት ቅጥረኛ የሆኑ ሥጋ ቤታቸውን የከፈቱ 2 ግለሰቦች የወረታ ዐማሮች አዘግተዋል፡፡ መከላከያ ሠራዊት አስለቃሽ ጪስ በመጠቀም ወጣቱን የበተነ ቢሆንም መንገዶችን ሙሉ በሙሉ በመዝጋት የገባውን መከላከያ እንዳይወጣ አስጨንቀውት ሰንብተዋል፡፡ ትናንት ለዛሬ ሌሊት ጉማራ ላይ በገበሬውና በትግሬ መከላከያ መካከል ከፍተኛ ተኩስ አድሯል፡፡ በተኩስ ልውውጡ ሦስት የፎገራ ዐማሮች የተሰው ሲሆን ከሦስት በላይ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ተገድለዋል፡፡ ጉማራ ድልድይ መንገድ ተዘግቷል፡፡
ደባርቅ/ ጃናሞራ
—————
ከደባርቅ ከተማ እስከ ጃናሞራና ደረስጌ ያለው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ከመንግሥት ቁጥጥር ውጭ መሆኑን ዛሬ ሰምተናል፡፡ የፖርክ ጠበቂ የነበሩ ሚሊሻዎችን በማባረር ዐማራው ራሱን በራሱ እያስተዳደረ ነው፡፡
በለሳ/ አርባያ
———-
የአርባያ በለሳ ሕዝብ መንግሥትን ካባረረ ዛሬ ሦስተኛ ቀኑ ነው፤ ሆኖም በስልክ ችግር ምክንያት የተሟላ መረጃ ማቅረብ አልቻልንም፡፡
በየቦታው መረጃ በማቅረብ ለምትተባበሩን ቁርጥ የዐማራ ልጆች ሁሉ በዐማራ ሕዝብ ስም ምስጋናችን ከፍ ያለ ነው፡

ትናንትና የኢህአደግ ሥ/አ ኮሚቴ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ድርጅቱ ፍርክስክሱ መውጣቱ መታየት ጀምሯል

  
The EPRDF house of cards
አገሪቱ ያለችበትን ውጥረት ተከትሎ ትናንትና የኢህአደግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የሚያወጣው መግለጫ በጉጉት ይጠበቅ የነበረ መሆኑ ብቻ ሳይሆን የአመራር ብቃት የሚፈተሽበት ነው ተብሎ ነበር፡፡ ነገር ግን የተሰጠው መግለጫ በአባላቱ ዘንድ ኢህአደግ ለመንኮታኮቱ ማረጋገጫ እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል፡፡
ከመግለጫው ይጠበቅ የነበረው በወልቃይት አማራ ማንነት በተመለከተ የሚወሰን ምን ይሆናል የሚለው ነበረ፡፡ አባላቱ የጠቁት
1. የአማራ ክልል ሕዝብ ጥያቄ ምለሽ ተሰጥቶበታል
2. የፈዴራል መንግስት ከትግራይ ክልልና ከአማራ ክልል መንግስታትን በመምራት የሚያስተካክለው ይሆናል
3. የወልቃይት አማራ ማንነት ኮሚቴ ከእስር እንዲፈቱ ተወስኗል
4. በወልቃይት አማራ ማንነት ጥያቄ ምክንያት የታሠሩት በሙሉ እንዲለቀቁ ተወስኗል
5. የሕዝቡን እንቅስቃሴ ተጠቅመው ሕገ ወጥ ድርጊት ላይ የተሠማሩ ግለሰቦችን ለመከላከል ሲባልበተወሰደው እርምጃ አንዳንድ ንጹሀን ሰዎች ላይ ስለደረሰው ሟቿች ቤተሰብ መንግስት መጽናናትን የሚመኝ ሲሆን እንደአስፈላጊነቱ የሚክስ ይሆናል፡፡
6. ከዚህ በኋላ መንግስት በወልቃይት ጉዳይ የሕዝቡን ይሁንታ ያገኘ ውሳኔ ይሰጣል የሚለውን ያካተተ ውሳኔ እንደሚገለጽ ከመጠበቁም በላይ እንዲህ ያለ ውሳኔ እንዲሰጥ ከፍተኛ ግፊት ሲደረግ ነበር፡፡ ነገር ግን ሥራ አስፈጻሚው የወልቃይትን ጥየቄ መፍታት ለትግራይ ክልል የሰጠ መግለጫ አውጥቷል፡፡
በመሆኑም በኢህአደግ አባላት የሚከተለው ታምኖበታል፡፡
1. ብአዴን በአማራ ክልል እግሩን የሚያሳርፍበትን ሥፍራ አጥቷል
2. ትግራይ ክልል አማራን በመውረር ማስተዳደር አትችልም
3. የአማራን ሕዝብ ገድሎ መጨረስ አይቻልም
4. የወልቃይት ጉዳይ ለዘላለም የማይፈወስ ካንሰር ነው
5. አማራ ክልል ለነፃነት ኃይል ነን ለሚሉት የጸዳ ነፃ ቀጠና ሆኗል
6. ኦሮሚያ በጥቂት ጊዜ የአማራን መንገድ ይዞ ነጻ ቀጠና ይሆናል
7.የመንግስት ባለሥልጣናት በየፊናው ለመሸሽ ተዘጋጅተዋል የሚል ታምኖበታል፡፡
በመሆኑም የኢህአደግ አባላት ወዴት እንደሚሸሹ ግራ ከመጋባቱም በላይ ፍርክስክሱ መውጣቱ መታየት ጀምሯል፡፡ የየአዲስ አበባ ሕዝብም ዘሎ ለመያዝ እንዳደፈጠ ነብር ተገምቷል፡፡ ይህ እንፎርሜሽን ከወደ ፓርላማ አባላት የተሰበሰበ ነው፡፡

Monday, August 29, 2016

ኢህአዴግ ቀባሪ እንጂ መካሪ አይሻም – ስዩም ተሾመ



Seyoum Teshome
ስዩም ተሾመ
በዘንድሮው ዓመት በተለያዩ የሀገራችን አከባቢዎች የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር መከሰቱ ይታወቃል። የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍሎች በተደጋጋሚ የተቃውሞ ሰልፍ በማድረግ ጥያቄዎቻቸውን አቅርበዋል። በዚህ አጋጣሚ ከፀጥታ ኃይሎች ጋር በተፈጠረው ግጭት ምክንያት በዜጎች ላይ የአካል ጉዳት፣ የሕይወት መጥፋት እና የንብረት ውድመት ደርሷል። በመሆኑም፣ ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት የሚከተሉትን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ ማድረግ ያሻል፡፡
1ኛ፡- ነፃ ምርጫ በማካሄድ ሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር ማድረግ፣
2ኛ፡- ገለልተኛ የምርጫ አካሄድ መዘርጋት፣
3ኛ፡- ለታሰሩ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ምህረት ማድረግና የፖሊቲካ እስረኞችን መፍታት፣
4ኛ፡- የሰብዓዊ መብቶች አያያዝን ማሻሻል፣
5ኛ፡- የፕሬስና ሃሳብን የመግለፅ ነፃነትን ማረጋገጥ፣
6ኛ፡- በየአከባቢው ከፖለቲካ ነፃ የሆነ አደረጃጀትና አስተዳደር ለመዘርጋት፣
7ኛ፡- በኃላፊነትና በመግባባት ላይ የተመሰረተ የፓርቲ ፖለቲካ፣ እና
8ኛ፡- በማህበራዊ ግንኙነት ረገድ ያሉ ግድፈቶች በማስወገድ ጤናማ ግንኙነት እንዲኖር ማስቻል።
ከላይ የቀረቡት ስምንት ነጥቦች ዛሬ ላይ በኢትዮጲያ ላለው ችግር ትክክለኛ መፍትሄዎች ቢሆንም እኛ ግን ለእንደዚህ ዓይነት የሰለጠነ ፖለቲካዊ መፍትሄ አልታደልንም። ይህ “June 29 Proposal” በመባል የሚታወቀው የመፍትሄ ሃሳብ የቀረበው እ.አ.አ. ሰኔ 29/ 1987 ዓ.ም በደቡብ ኮሪያው ገዢ ፓርቲ “Democratic Justice Party” ዋና ሊቀመንበር በነበሩት “Roh Tae Woo” ነበር። በእርግጥ በወቅቱ ደቡብ ኮሪያ የገጠማት ችግር አሁን ኢትዮጲያ ከገጣማት ችግር ጋር ፍፁም ተመሳሳይ ነበር። ከተወሰነ የአውድ ልዩነት በስተቀር የመፍትሄ ሃሳቡም ተመሳሳይ እንደሆነ በፅሁፉ መጨረሻ ካለው እንግሊዘኛ ቅጂ ጋር ማመሣከር ይቻላል።
ከግዜና ቦታ በስተቀር በደቡብ ኮሪያ እና በኢትዮጲያ የተነሳው ጥያቄ ልዩነት የለውም። በዚህ ጉዳይ ላይ ልማታዊ መንግስትና የ3ኛው ምዕራፍ መንታ መንገድ በሚል ርዕስ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥቼበታለሁ። ስለዚህ፣ በዚህ ፅሁፍ ዋና ትኩረቴ በልማታዊ ዴሞክራሲ አቅጣጫን በሚከተሉት ሁለቱ ፓርቲዎች ለተመሳሳይ ችግር ባቀረቡት የመፍትሄ ሃሳብ ላይ ይሆናል። ከላይ የተጠቀሱትን የመፍትሄ ሃሳቦች ተግባራዊ በማድረጉ የደቡብ ኮሪያ መንግስት ከአምባገነንነት ወደ ዴሞክራሲያዊነት፣ ሀገሪቱን ከታዳጊነት ወደ የበለፀጉ ሀገራት ተርታ አሸጋግሯታል። ከዚህ አንፃር፣ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ውስጥ የቀረበው የመፍትሄ ሃሳብ ግን ራሱንና ሀገሪቷ ለባሰ ውድቀት የሚዳርግ ነው፡-
“… በአሁኑ ጊዜ ልማታዊ ዴሞክራሲያዊ ስርዓቱን ከሚፈታተኑት ችግሮች መካከል አንዱ የመንግስት ስልጣን የህዝብን ኑሮ ለማሻሻልና አገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል እንዲሆን ከማድረግ ይልቅ የግል ኑሮ መሰረት አድርጎ የመመልከትና በአንዳንዶችም ዘንድ የግል ጥቅም ከማስቀደም ጋር የተያያዘ እንደሆነ አረጋግጧል፡፡ …. መላ የአገራችን ህዝቦች …በዚህ ወቅት በድርጅትና በመንግስት አካላት ዘንድ የታየው ይህ ስህተት ተስፋቸውን እንዳያጨልመው ያደረጉትን ትግል ከታላቅ አክብሮት ጋር ይመለከተዋል። …እነሆ ዛሬ ድርጅታችን በዚህ ችግር ምክንያት የተፈጠረውን አደጋ መሰረታዊ መንስዔዎች በሌላ በማንም ሳያሳብብ በመንግስትና በድርጅት ማዕቀፍ እንደሚታይ ቀዳሚ ችግር እንደሆነ ተገንዝቦ ይህንኑ ለማስተካከል የሚያስችል እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡”
በመሰረቱ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ግምገማ ውጤት፡- የችግሩ መንስዔና መፍትሄ ፍፁም ስህተት ነው። ሕዝቡ ላደረገው ትግል “ታላቅ አክብሮት” እንዳለው መግለፁም ቢሆን “የአዞ እምባ” ነው። ምክንያቱም፣ አሁን ሀገሪቷ ያጋጠሟት ችግሮች መሰረታዊ መንስዔና መፍትሄ ከላይ በፅሁፉ መጀመሪያ ላይ በተጠቀሱት ስምንት ነጥቦች ያለው ነው። ስለዚህ፣ ያለ ምንም መዛነፍ፣ በእነዚህ ስምንት ነጥቦች ላይ ተገቢው ምላሽ እስካልተሰጠ ድረስ ችግሩ ይበልጥ እየተባባሰ ይሄዳል። ምክንያቱም፣ “ልማታዊ መንግስትና የ3ኛው ምዕራፍ መንታ መንገድ” በሚለው ፅሁፌ በዝርዝር ለማብራራት እንደሞከርኩት፣ እ.አ.አ. በ1987 ዓ.ም በደቡብ ኮሪያ የነበረውና ዛሬ ላይ በኢትዮጲያ እየታየ ያለው የሕዝብ እንቅስቃሴ መነሻውና መድረሻው መዋቅራዊ ለውጥ (structural change) ነው።
በእርግጥ ላለፉት ስምንት ወራት ተከታታይ ፅሁፎችን በማውጣት የኢህአዴግ መንግስትን ስመክርና ስተች ነበር። የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፤ “የአብዮት እና የዴሞክራሲ ትውልድ ግጭት” የተቃውሞ እንቅስቃሴው የተወሰኑ ቡድኖች ጥያቄ ሳይሆን የትውልድ ጥያቄ እንደሆነ፣ “ኢህአዴግና ፅንፈኞች፡- ባሉበት የቆሙና ባለፈው የቆዘሙ” በሚል ርዕስ ደግሞ ገዢው ፓርቲ ከአዲሱ ትውልድ ጋር አብሮ መሄድ እንደተሳነው፤ “ኢህአዴግ፡ አፍን ይዞ ከኋላ መጫን ለማፈንዳት” የ2007ቱን ምርጫ ውጤት አመፅ ቀስቃሽ እንደሆነ፤ “ኢህአዴግ፡ ይሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ”ኦሮሚያን ለአመፅ፣ አዲስ አበባን ለቆሻሻ የዳረገች አንቀፅ እና አርሶ-አደርን ከመሬቱ ከማስነሳት ይልቅ ማጠጋጋት” በሚሉት ፅሁፎች ደግሞ ኢህአዴግ ከሕዝቡ ለሚነሱ የመብትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄቆች ምላሽ መስጠት እንደተሳነው፤ “ሕገ-መንግስታዊ ፅንፈኝነት በኢትዮጲያ” በሕገ-መንግስት ስም የዜጎችን መብትና ነፃነት እየጣሰ እንደሆነ፤“ኢህአዴግና የሰይጣን ጠበቆች እና ከጓንታናሞ እስከ ማዕከላዊ፡ ክፍል-3 የአሸባሪዎች ሕግ” የፕሬስና ሃሳብን የመግለፅ ነፃነት፤ ኢህአዴግ አሸነፈም ተሸነፈም ለውጥ አይመጣም እና የደሞወዝ እድገት ቀርቶብኝ የአካዳሚክ ነፃነቴን ስጡኝ” የማህበራት አደረጃጀትና የሀገሪቱን ሲቪል ሰርቪስ ከገዢው ፓርቲ ተፅዕኖ ስር ነፃ እንዲወጣ፣…ወዘተ።
ልክ እንደ እኔ ኢህአዴግን ብዙ ሰዎች መክረውታል። የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ ያወጣውን መግለጫ ስመለከት ግን የእኔም ሆነ የሌሎች ሰዎች ምክር ውሃ እንደበላው ነው ተሰማኝ። መጀመሪያ ላይ ችግሩ ሲነገረው ሳይቀበል ይቆይና፣ የብዙ ሰው ሕይወትና ንብረት ከጠፋ በኋላ ልክ እንደ ሰሞኑ፤ “ጥፋቱ የእኔ መሆኑን ተቀብዬለሁ” ብሎ መግለጫ ይሰጣል። “ከዘገየም በኋላ ቢሆን ጥፋትህን መቀበልህ ጥሩ፣ መፍትሄው ደግሞ ይኸውልህ…” ሲባል ደግሞ አይሰማም። በራሱ መፍትሄ ነው ያለው ነገር ሌላ ስህተት ይሆንና፣ እንደገና የብዙ ሰው ሕይወትና ንብረት ከጠፋ በኋላ፣ “በመጀመሪያ የወሰድኩት የመፍትሄ እርምጃ በጥናት ላይ የተመሰረተ አልነበረም” ይላል። እንዲህ እያለ፣ በስህተቱ ላይ ሌላ ስህተት እየደገመ ሀገሪቷን ለከፋ ውድቀት ሊዳርጋት ተቃርቧል። “ይኼ ምን የሚሉት አባዜ ነው?” እያልኩ ሳስብ የሚከተለው ውይይት ትዝ አለኝ።
“ጃንሆይ ሩሲያን ለመጎብኘት ሲሄዱ አብሬ ሄጄ ነበር፡፡ ከዚያም በባቡር ከሌኒንግራድ ወደ ሞስኮ ከተማ ለመሔድ ብዙ ሰዓት የፈጀ ጉዞ በማድረግ ላይ እንዳለን ጃንሆይን ብቻቸውን በቂ ጊዜ አግኝቼ ያነጋገርኩበት መልካም አጋጣሚ ስለነበር፤ በአገራችን በአስተዳደር፣ በፍርድ፣ በምጣኔ ሀብትና በመሬት ስሪቱ ያለውን ብልሽትና ባለስልጣኖች በጠቅላላው በህዝብ ላይ የሚፈጽሙትን በደል በሠፊው ዘርዝሬ ገለጽኩላቸው፡፡
ከዚያም ይህ ሁኔታ ቶሎ መግቻ ካልተደረገበት የጉዳቱ ብዛት ይህ ነው የማይባል እልቂት የሚያመጣ፣ የብዙ ሰው ህይወት የሚያጠፋ፣ ብዙ ደም የሚያፋስስ፣ ንብረት የሚያወድም፣ የግርማዊነቶን ታሪክ የሚያጎድፍና የዘውድ አስተዳደር ቀጣይነት ገትቶ ለውጥ የሚያመጣ ብርቱ እንቅስቃሴ ስለሚያስነሳ፤ ግርማዊነቶ ይህን ሥርዓት አንስቶ ሥልጣኑን ለአልጋ ወራሹ ሰጥቶ ግርማዊነቶ ከኋላ ሆኖ በመምከርና በመቆጣጠር፣ እንደ እንግሊዝና ጃፓን ያለ የመንግስት አስተዳደር ሥርዓት በኢትዮጵያ ቢዘረጋ፤ ዘውዳዊውን ሥርዓት የሚያስቀጥልና ኢትዮጵያን ከጥፋት በማዳን ስምዎ፣ ክብርዎና ታሪክዎ እንደተወደደና እንደተከበረ ለዘላለም እንዲኖር የሚረዳ ነው፡፡ እንዲህ ቢያደርጉ ኢትዮጵያን ከመከራና ከብጥብጥ ያድኗታል ብዬ ንግግሬን ሳቆም፤
ዝም ብለው ቆይተው ‘አይ ! አይ! ወርቅነህ! እኔ የበሰልክ ይመስለኝ ነበር፤ ለካስ ልጅ ነህ! ከልጅ ጋር ነው የምንሰራው! እግዚአብሔር የሰጠንን ሥልጣን እስካለን እንሰራበታለን፡፡ ከዚያ በኀላ እሱ እንደፈለገ ያድርጋት፡፡ ለመሆኑ ማን ስልጣኑን ለሌላ አሳልፎ የሰጠ አይተሀል?’ አሉኝ፡፡” – (ብርሃኑ አስረስ – የታህሳሱ ግርግርና መዘዙ፡ ገጽ 145)
ቀዳማዊ ኃይለስላሴ የኮ/ል ወርቅነህ ገበየሁን ምክር ስላልሰሙ፤ በመጀመሪያ እንደ ጄ/ል መንግስቱ ነዋይ ያለ ቀባሪ መጣባቸውና ለትንሽ ተረፉ። ብዙም ሳይቆዩ ግን ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማሪያም መጥቶ ቀበራቸው። መንግስቱ ኃይለማሪያም ስልጣኑን እንደ ተቆጣጠረ በዙሪያው እንደ ኢህአፓና ሚኢሶን ያሉ መከሪዎች ነበሩት። በኋላ ላይ ኢህአፓ በጥይት ሊቀብረው መሞከሩን ተከትሎ በሀገሪቱ ያሉትን የተማሩ ሰዎች ለሞት፣ ለስደት፣ ለጦርነትና ለእስር-ቤት በመዳረግ ሀገሪቷን ምሁር-አልባ አደረጋት። ከእነዚህ ውስጥ በሕይወት የተረፉት በወቅቱ ቀድመው የትጥቅ ትግል የጀመሩት እና ከሀገር የተሰደዱት ወጣቶች ብቻ ነበሩ። ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከታህሳሱ ግርግር በኋላ እንዳደረጉት፣ ደርግም በቀይ-ሽብር ወቅት መካሪዎቹን ገድሎና አስሮ ሲጨርስ ኢህአዴግ ሊቀብረው መጣ።
ከኢህአዴግ በፊት የነበሩት ዘውዳዊው አገዛዝና ደርግ የሚያመሳስላቸው ነገር ቢኖር ለፖለቲካ ልሂቃን (Political Elites) ያላቸው ጥላቻ ነው። በአንድ ሀገር ውስጥ የዳበረ ፖለቲካዊ ሥርዓት ለመገንባቱ በሚደረግ ጥረት ውስጥ የፖለቲካ ልሂቃን የማይተካ ሚና አላቸው። ንቁ ተሳትፎ የሚያደርጉ ልሂቃን ባሉበት ሀገር በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ የጋራ ዕውቀት (shared knowledge) እና ሀገራዊ መግባባት ይዳብራል። ቀይ-ሽብር በመንግስት እና ሕዝብ መካከል ያለው የመተማመን መንፈስ (social contract) እንዳይኖር አደረገው። ከዚህ በተጨማሪ፣ በሀገሪቱ የፖለቲካ ልሂቃን ላይ የፍርሃት ድባብ በማስፈን በጋራ ጉዳዮች ላይ ግልፅ የውይይት የማድረግ ባህልን ሙሉ-ለሙሉ አጠፋው።
የተማሩ ልጆቿን ለሞት፣ ለስደት፣ ለጦርነትና ለእስር-ቤት በመዳረግ ኢትዮጲያን የወላድ መሃን ያደረጋትን ደርግ ያስወገደው ኢህአዴግ ወደ ስልጣን በመጣ ሁለተኛ ዓመት ምን ቢያደርግ ጥሩ ነው? ከደርግ ጭፍጨፋና እስር የተረፉትን ከ40 በላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራንን ከሥራ በማባረር መካሪዎቹን ማጥፋት ጀመረ። የኢህአዴግን መንግስት ሲተቹትና ሲቃወሙት የነበሩትን ቀስ-በቀስ ለእስርና ስደት ሲዳርግ ከከረመ በኋላ በ1997 ዓ.ም ቅንጅት የሚባል ቀባሪ መጣበት። እንደ አፄ ኃይለስላሴ እና መንግስቱ ኃይለማሪያም የመጀመሪያውን ሙከራ እንደ ምንም ተንገዳግዶ ተረፈ። ከዚያ በኋላ፣ እሱን የሚቃወም ፖለቲከኛ እና የሚተች ጋዜጠኞች አንድ በአንድ ለእስርና ስደት ከዳረገ በኋላ፣ ይኼው ዛሬ ላይ ኢህአዴግ ቢጠሩት አይሰማ፣ ቢመክሩት አይለማ። መካሪዎቹን አባሮና አስሮ ቀባሪዎቹን እየጠበቀ ነው። እንደው በቃ ግን ሁሉም የኢትዮጲያ መንግስታት ቀባሪ እንጂ መካሪ አይሹም?

በአዊ ዞን አንከሻ ጔጉሳ ወረዳ ግምጃቤት ማርያም ከተማ ከባድ የሆነ ሰልፍ ነበረ፡።




Minilik Salsawi – mereja.com በአዊ ዞን አንከሻ ጔጉሳ ወረዳ ግምጃቤት ማርያም ከተማ ከባድ የሆነ ሰልፍ ነበረ፡። ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ሰልፍ ነበረ፡። መፈክሩም፡። 1ለወያኔ አንተዳደርም ወይም አንገዛም 2ወያኔ ሌባ ነው በማለት 3ወያኔ ከግምጃቤት ማርያም የወሰደውን ስልካችንን ይመልስ በማለት 4ወልካይት የጎንደር ኔት 5ወልቃይት የአማራ ናት 6ወያኔ በንፁሐን ዜጎች ላይ የሚያደርገውን ግድያ እና አፋና ይኩም 7የአዮን መሬት 25 አመት በአላሙዲ ስም ነግዶባታል ተንግዲ ግን የአዮን ህዝብ አፈናቅሎ ላባረሬቸው ይመልስ፡። በማለት አሰምተዋል የወያኔ ምክር ቤት በደንጋይ ተወግሯል። ወደ ፓሊስ ታቢያዎች ህዝቡ ደንጋይን ወርውረዋል ህዝቡ በግምጃቤት ማርያም አደባባይ ላይ ከመሀል ኮከብ ወይም አርማ የሌለውን ሰንደቅ አላማ ሰክለዋል ፡። By Minilik Salsawi

በባህር ዳር የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተለውጦ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቷል።ባለስልጣናት ተደብቀዋል።



በባህር ዳር የቤት ውስጥ የመቀመጥ ኣድማ ወደ ተቃውሞ ሰልፍ ተለውጦ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቷል።ባለስልጣናት ተደብቀዋል።

በዳንግላ ከተማ የወረዳው አስተዳዳሪ ቤት ተቃጥሎአል። አንድ ዋና ሳጅን አየነው የሚባል በህዝብ ላይ በመተኮሱ የእሱም ቤቱ ተቃጥሎአል ። በአዴት ከተማ ፖሊሶች ከህዝብ ጋር በማበር እየተቃወሙ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ተባብረው ከተማዋን በማስተዳደር ላይ ናቸው። በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ አርብ ገበያ አድማው ለሁለተኛ ቀን እየተደረገ ሲሆን፣ መንገዶች በመሉ በድንጋይና በግንድ ተዘግቷል። ህዝቡ የጎበዝ አለቃውን ነገ ተሰብስቦ ይመርጣል። በቋሪት አራት የጎበዝ አለቆች ከተማዋን እንዲያስተዳድሩ ተመርጠዋል። …ይልማና ዴንሳ(አዴት) ከተማ ሙሉ በሙሉ ከመንግስት ቁጥጥር ውጪ ህዝቡ ስልጣን ተቆጣጥሯል።  ባሁኑ ሰአት ከተማዋ በጎበዝ አለቃ እየተመራች ነው። ቄሶችና ባለሃብቶች ከተማዋን ተረክበዋል።

ውስጥ ውስጡ ሚኒስትሮች እየተነሱ ነው፤ የከተማ ልማት ሚኒስትሩ ተነስተው ወደ ጠ/ሚ ቢሮ በኣማካሪነት ተዘዋውረዋል።



የከተማ ልማት ሚኒስትሩ ተነስተው ወደ ጠ/ሚ ቢሮ በኣማካሪነት ተዘዋውረዋል።Minilik Salsawi
ውስጥ ውስጡ ሚኒስትሮች እየተነሱ ነው፤ ወያኔ በለመደው ፕሮፓጋንዳ መሰረት በራስ ፈቃድ ያሰኛል። ዛሬ በከተማ ልማት ሚ/ር ወርሃዊ የሠራተኞች ስብሰባ ላይ ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ‹‹ከሌላ ከምትሰሙ ልንገራችሁ፣ ከስልጣኔ በራሴ ጥያቄ ለቅቄ ወደ ጠ/ሚ/ሩ አማካሪነት ተዛውሬኣለሁ ›› ሲሉ በተሰበረ ልብ የኑዛዜ ቃላቸውን አሰምተው ‹ጠንክራችሁ ሥሩ› የሚል ማሳሰቢያ ተናግረዋል፡፡ ይህ ማለት አቶ መኩሪያ ከአገርና ህዝብ ጥቅም የራሳቸውን ጥቅምና ድሎት ካስቀደሙ –ሥልጣናቸውን ለኪራይ ሰብሳቢነት ከተጠቀሙ ለኢህአዴግ መበስበስ ምክንያት ከሆኑ ባለሥልጣናት አንዱ ናቸው ማለት ነው– በወያኔያዊ መግለጫው መሰረት፡፡ #MinilikSalsawi
Image result for ministry mekuria
 

Sunday, August 28, 2016

እናመሰግናለን ዶር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ – #ግርማ_ካሳ

  


14064305_1676870739298231_595808815460356192_nከዚህ በታች ያለውን ለማሰራት ከአርባ ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል። የሕወሃት ተላላኪ ሙክታር ከድር ነው በቦታዉ ሄዶ ያስመረቀው። ዶር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ በመጽሃፋቸው እንደገለጹት ፣ ሕወሃት፣ ኦህዴድን አዞ ይሄን ሃዉልት ያሰራበት ታሪክ, ምንም አይነት የጽሁፍ ማስረጃ የሌለበት አፈታሪክ ብቻ ሳይሆን ዉሸትም እንደሆነ ነ ያስቀመጡት።
እንግዲህ ሕወሃት ዉሸትን እየፈጠረ ( እንደ ተስፋዬ ገብረ አብ ያሉትን በመጠቀም) ነው በአማራኛ ተናጋሪዎች እና በኦሮሞኛ ተናጋሪዎች መካከል መቃቃር እንዲኖር ለማድረግ ነው የሞከረው።
ምን ችግር ነበረው ይሄንን የጥላቻ ሃዉልት ከሚሰሩ፣ ክሊኒክ፣ ትምህርት ቤት የመሳሰሉት እዚያ አካባቢ ላለው ማህብረሰብ ቢሰሩበት ? እዚህ ሃዉልት ይሰራ ከተባለ ደግሞ በገዳ ስርዓት ጊዜ መቼም ጀብሩ የፈጸሙ ታላላቅ የኦሮሞ አባቶች ይኖራሉ። ሌላውም ከታሪክ እንዲማር፣ የበለጠ ስለ ኦሮሞ ባህል እንዲያወቅ፣ የአንዳቸውን ሃዉል ለምን አያቆሙም ?
ይህ ሃዉልት የተሰራው ሊከፋፍለን፣ ሊያጣላን ነው። ጎንደር እና ጎጃም “የኦሮሞዎች ደም የኛ ደም ነው” ሲሉ ነበር። ኦሮሞዎች በአዳማ “አማራ የኛ ነው” እያሉ ነው። ከዚህ በኋላ አንፈራራም። ከዚህ በኋላ አማርኛም እንማራለን፣ አፋን ኦሮሞም እንማራለን። አማርኛም የኛ ነው፤ አፋን ኦሮሞም የኛ ነው። ሁለቱንም እንይዛለን። በቋንቋ አንከፋፈልም።
የተማረ ይግደለኝ ነው የሚባለው። እናመሰግናለን ዶር ፍቅሬ ፣ ታላቅ የኦሮሞ ልጅ፣ የኢትዮጵያ ልጅ …
“የኦሮሞ እና የአማራ እውነተኛው የዘር ምንጭ”
ፕሮፌሰር ፍቅሬ ቶሎሳ ጂግሳ
ገፅ ፡152-153
“አፄ ምኒልክ ደም መፈሰስን እናስቀር ብለው ንጉሥ ጦናን ለመኑት።ንጉሥ ጦና ግን ኃይሉን አሟጦ መዋጋት ስለመረጠ በምኒልክ ሠራዊት ላይ ከባድ ጉዳት አደረሰ። በመጨረሻ ግን ቆሰለና ተማረከ።ዳግማዊ ምኒልክ ጦናን አይቀጡ ቅጣት ከመቅጣትና መንግስቱንም አሽቀንጥረው ጥለው ሥልጣኑን ለጦር መሪዎቻቸው ከመስጠት ይልቅ ደግነት የተሞላበት ምህረት አድርገውለት እንደሚገብርላቸው ቃል ካስገቡት በኃላ ወደ ሥልጣኑ መለሱት። ምኒልክ ተበቃይ አልነበሩም ።ይቅር በይ፣ በተጨባጭ እውነታ ላይ የተመሰረተ ምክንያታዊ አስተሳሰብ የነበራቸው እና ራሳቸውን እነደ ጥሩ ክርስቲያን የሚያዩ ሰው ነበሩ።በጦርነት ላይ የሴት ልጅ ጡት መቁረጥ ፍጹም ከባሕሪያቸው ውጪ ነው።እንዲህ ዓይነቱ ውንጀላ መሰረተ―ቢስ እና ከተንኮለኞች የመነጨ ነው።የጎጃሙ ንጉሥ ተክለሃይማኖት አምጸው ጦርነት አነሱና ቆስለው ተማረኩ።ምኒልክ የቆሰለውን ምርኮኛ ገድሎ በመጨረስ ፈንታ ቁስላቸውን ራሳቸው አክመው ፣አጠገባቸው አስቀምጠው አብረዋቸው እንዲመገቡ በማድረግ ፍቅር ነው ያሳዪአቸው።ሥልጣናቸውንም አልወሰዱባቸው፤ ያለማመንታት መልሰውላቸዋል። በርግጥ ዳግማዊ አጼ ምኒልክ ሩኅሩኅ ነበሩ።አገራቸውን ለመውረር የመጡ ምርኮኞች ጣልያኖችን እንኳ በርኅራኄና በደግ አያያዝ ነበር የያዟቸው።እኝህን ሰው ጡት ቆርጠዋል/አስቆርጠዋል/ ብሎ መፈረጅ አግባብነት የሌለው ትንሽ የፓለቲካ ጠቀሜታ ለማግኘት የሚነዛ ርካሽ ፕሮፓጋንዳ ነው።ምኒልክን ጡት ቆርጠዋል ብለው ለማስጠላት ሀውልት ያቆሙ አካላት በድርጊታቸው ማፈር እና ያንን አሳፋሪ ሀውልትም ማፍረስ ይገባቸዋል። ምኒልክ በግላቸው እንደዚያ ዓይነት ተግባር ጨርሶ አይፈጽሙም።”

በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው



 በብዙ የዐማራ አካባቢዎች የመንግሥትን መዋቅር ሕዝቡ ተረክቧል፤ የጎበዝ አለቃዎች ጸጥታ የማስከበሩንና የመሪነት ሚናውን በሚገባ እየተወጡ ነው፡፡ የአርባያ በለሳና የቋሪት አንበሶች ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡ በድፍን ጎጃምና በድፍን ጎንደር ሕዝብ አገዛዙን አሽቀንጥሮ ለመጣል እየታገለ ነው፡፡ በወሎና በሸዋ ያሉ ዐማሮችም ተነስተዋል፡፡ ከ60 በመቶ በላይ በሚሆነው የዐማራ አካባቢ ወያኔ ለእግሩ መርገጫ የሚሆን ቦታ የለውም፤ ይህ ተጋድሎ በትንሽ ውጤት ሕዝቡ ሳይዘናጋ እስከ መጨረሻው መቀጠል አለበት፡፡ ዛሬ ያለው ግማሽ ድል ሙሉ እስኪሆን ድረስ ዐማራ ተጋድለውን ይቀጥላል፡፡ ዛሬ በተጋድሎ ያሉ ወንድሞቻችን ብዛት አይደለም አካባቢያቸውን ሁሉ ሙሉ በሙሉ መቁጠር አንችልም፤ ደባርቅ፣ ዳባት፣ ገብደብየ፣ አምባጊወርጊስ፣ ጎንደር፣ ደምቢያ፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ፣ ወረታ፣ ዓለም በር፣ ደብረ ታቦር፣ ጋሳይ- ክምር ድንጋይ፣ ነፋስ መውጫ፣ ሳሊ፣ ጨጭሆ፣ ጎብጎብ፣ ፍላቂት፣ ደራ ሐሙሲት፣ ባሕር ዳር፣ ፒኮሎ፣ ዱርቤቴ፣ አቸፈር፣ ዳንግላ፣ ቲሊሊ፣ ግምጃ ቤት፣ እንጅባራ፣ ቋሪት፣ ፍኖተ ሰላም፣ ብርሸለቆ- ጃቢጠናን፣ ቡሬ፣ ሽንዲ፣ ደምበጫ፣ የጨረቃ፣ አንበር፣ ሎማሜ፣ ፈረስ ቤት፣ አዴት ይልማና ዴንሳ፣ ጎንጅ ቆለላ፣ ሞጣ፣ ጉንደወይን…… በነዚህ ቦታዎች ሁሉ የዐማራ ሕዝብ ከወያኔ ጋር ግብግብ ነው፤ ለነጻነት ልጆቹን መስዋት እያደረገ ነው፡፡

በዚህ ሁሉ መካከል ግን ሊወሰዱ የሚገባቸው ነገሮች አሉ፡፡ የዐማራው ሕዝብ መንግሥት መፍረሱን ተቀብሎ የሰላም ማስጠበቁን የመረከብ ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ አዳዲስ የወረዳ አስተዳዳሪዎችና የጦር አበጋዞች መመረጥ አለባቸው፡፡ ሕዝቡ ደግሞ በመረጣቸው የጎበዝ አለቆች የመመራት ባሕሉን አጠናክሮ መሄድ አለበት፡፡ በጥቂት ቀናት ውስጥ ምርጥ መሪዎች ሕዝቡን ወደ ፊት ይዘው መሔዳቸውን እናያለን፤ የቋሪትና የበለሳ ተመክሮ እንደሚስፋፋ እሙን ነው፡፡
የዐማራው ገበሬ ለማይወክሉት የወያኔ ተላላኪዎች የመሬት ግብርና የማዳበሪያ፣ የአብቁተ ብድር ምናምን መክፈል የለበትም፡፡ ሁላችንም የዐማራ ልጆች ለገበሬ ዘመዶቻችን የማስረዳት ኃላፊነት አለብን፡፡ ሁሉም ገበሬ በየበቀበሌውና በየወረዳው አስተዳደር የሥልጣን እርከኖችን በልጆቹ የማስያዝ ሥራ አሁኑ መጀመር አለበት፡፡


በቀጣይ ቀናት ማናቸውም የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በመላው የዐማራ አካባቢ እንደሚቋረጥ ይጠበቃል፡፡ የስልክና የኢንተርኔት መቋረጥ በውጭ ያለውን የአክቲቪዝም ሥራ የሚጎዳው ቢሆንም በአገር ውስጥ ያለውን ትግል ግን ወደ ኋላ አይመልሰውም፡፡ የዐማራ ሕዝብ የወያኔን ቂመኛነት ከማንም በላይ ያውቀዋል፤ በዚህም ወያኔ ይቅር ለእግዜር የሚባልበት የይቅርታ ዘመን አልፏል፡፡ የመጨረሻው መጀመሪያ እንዲህ ነው!!
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል!!

የኢሕአዴግ የተሃድሶ ጥሪ ማዘናጊያ እና የለውጥ ትግል መግደያ ነው። በተሃድሶ ስም አዲስ በጀት መድበው ለመዝረፍ ኣሰፍስፈዋል።



#Ethiopia #EPRDF የኢሕአዴግ የተሃድሶ ጥሪ ማዘናጊያ እና የለውጥ ትግል መግደያ ነው። በተሃድሶ ስም አዲስ በጀት መድበው ለመዝረፍ ኣሰፍስፈዋል።#MinilikSalsawi #EthiopiaProtests
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ) – የሕዝብ ችግር ኢሕአዴግና ፖሊሲው እንጂ መግለጫ እና የምክር ቤት ውሳኔ ኣይደለም ።መፍትሄው ስልታን ለሕዝብ ማስረከብ ብቻ ነው። የወያኔ መግለጫ (በማር የተለወሰ መርዝ)የሕዝብ ትግል ስላሽመደመደው በለመደው የውሸት መግለጫው ሕዝብን እያታለለ ለመኖር እንጂ ምንም ለውጥ እንደማያመጣ መግለጫው በራሱ ምስክር ነው።በልማት እና በተሃድሶ ስም በመነገድ ላይ የሚገኘው ወያኔ የሕዝብን ትግል ለማኮላሸት የሚያደርገውን ማዘናጊያ እነ የሃሰት መግለጫውን ሳንሰማ እግላችንን ኣቀጣጥለን መቀጠል ኣለብን።
‹‹ከ2009 ዓ/ም ጀምሮ በአዲስ መንፈስና ጉልበት ተጠናክረን እንመጣለን፤›› የሚለው ወያኔ ሕዝብን ለመፍጀት ራሱን በማጠናከር ላይ መሆኑን እየነገረን ነው ስለዚህ ሳይቀድሙን በመቅደም ድምጥማጣቸውን ልናጠፋው ይገባል፤ እንደገና በኣዲስ ኣመት ኣዲስ መንግስት ለማቋቋም የሚያስበው ወያኔ መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች ኣይነት ሆኖበታል፤ወያኔ ራሱ በሚፈጥረው ሽብርና በራሱ ፍርሃት ራሱ በሚሰራው ወንጀል የውጭም ሆነ የውስጥ ጽንፈኛ፣ ፀረ ሰላምና ፀረ ልማት ኃይሎች በማለት መወንጀሉን ተያይዞታል።
የወልቃይትን ጉዳይ በተመለከተ ሕገመንግስቱ መሰረት ኣድርጎ የትግራይ ክልል ሊፈታው ይገባል በማለት ጉዳዩን ለጨፍጫፊዎቹ ሕወሓቶች በመስጠት ብ አዴንን ደካም ድርጅት ሲል ፈርጆታል። የወልቃት ጉዳይ በኣስቸኳይ መፍጤ ኣግኝቶ የሕዝብ ጥያቄ ካልተመለሰ ትግሉ እንደተቀጣጠለ ይቀጥላል፥ የኣማራው ክልል የሕዝብ ብሶት የፈነዳው የወልቃይትን ጥያቄ ተከትሎ መሆኑን ለማመን ያልፈለገው ወያኔ ኣሁንም የወልቃይትን ጉዳይ ከሕወሓት ጉያ ለመምዘዝ ኣልፈለገም ሕወሓት በጉያዋ እሳት እንደታቀፈች ልታውቅ ይገባታል፤ወልቃይት ኣማራ ኢትዮጵያዊ ነው። ሰበበኛው ወያኔ የሚሰጠው መግለጫ የሚያደርገው ድርድር ሁሉ ሕዝብን ለማዘናጋት የለውጡን ትግል ለመግደል የሚሰራው ሴራ ኣንዱ አካል ነው።በተሃድሶ ስም አዲስ በጀት መድበው ለመዝረፍ ኣሰፍስፈዋል።
ስለዚህ የኢትዮጵያ ሕዝብ በየኣቅጠጫው የጀመረውን ትግል በመቀጠል በወያኔ መግለጫ ሳይዘናጋ በጀመረው የለውጥ ጉዞ ወያኔን ወደ ከርሰ መቃብሩ የመክተት የዜግነት ግዴታ ኣለብን፤ ድል የሰፊው ሕዝብ ነው። #ምንሊክሳልሳዊ
Image may contain: text

ጎጃም ጀግናው የዱርቤቴ ሕዝብ ትግሉን በመቀላቀል ወያኔን በቃኸኝ ብሎታል ።ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማ ደብረታቦር፣ ወረታ እና አዲሥ ዘመን


ከጎንደር ወልድያና ባሃርዳር መንገዶች ተዘግተዋል። ጎጃም ጀግናው የዱርቤቴ ሕዝብ ትግሉን በመቀላቀል ወያኔን በቃኸኝ ብሎታል ።ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማ ደብረታቦር፣ ወረታ እና አዲሥ ዘመን
Minilik Salsawi
በቲሊሊ ከተማ ህዝቡ እስረኞችን አስፈትቷል። በህዝቡና በፖሊስ መካከል የተፈጠረውን ፍጥጫ ቄሶቹ ታቦት ይዘው መሀል ላይ በመግባት ህዝቡ እስረኞችን ይዞ እስካሁኗ ሰአት ተቃውሞውን እያቀረበ ይገኛል ።በደብረታቦር፣ በወረታ እና በአዲሥ ዘመን ከተሞች ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀን የስራ ማቆም አድማው የተጀመረ ሲሆን ደብረታቦር ከተማ ፀጥ ረጭ ብላለች።በአገው ምድር እንጅባራ አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ ከፍ ተደርጎ ተሰቅሏል።ዳንግላ፣ ዱርቤቴ፣ ኮሶበር ተቃውሞ በማድረግ ላይ ናቸው፥፥ በኮሶበር ፌደራሎች በህዝብ ላይ እየተኮሱ ነው፥፥ ኣንድ ሰው መገደሉንና ሶስት መቁሳላቸውን መረጃ ደርሶናል፥፥ በዳንግላ የመዘጋጃው ዘበኛ በህዝብ ላይ በመተኮሱ ቤቱ ተቃጥሏል፥፥ የደንበጫ ህዝብ የወታደሮችን እንቅስቃሴ ለመግታት ድልድይ በመዝጋት ተቃውሞውን እየገለፀ ነው::


የበላይ ልጆች በጎጃም የሚገኙ ድልድዮችን በሙሉ እየዘጉ ነው። ወያኔ ወገቡ ተቆርጧል። ከዚህ በኃላ ወደ ጎጃም ጎንደር በመኪና የሚደረገው ጉዞ ቆሟል። ጎንደር ወሎ ሸዋም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቱን ጨርሷል። ድሉ በእጃችን እየገባ ነው!
የደቡብ ጎንደሯ እሥቴ(መካነ እየሡሥ) ከተማ የአማራ ተጋድሎውን በሥራ ማቆም አድማ ተቀላቀለች። በመካነ እየሡን ከተማ አገልግሎት ሠጭ ተቋማት በሙሉ ተዘግተዋል። በነገራችን ላይ መካነ እየሡሥ ከተማ ከዚህ በፊት የአማራ ተጋድሎን በመቀላቀል ግንባር ቀደሟ ነበረች። ከዚህ በፊት በሠላማዊ ሠልፍ የተጀመረው ተቃውሞ ዛሬ ከቤት ባለመውጣት ተቃውሞ ተደግሟል!በደቡብ ጎንደር ወረታ ከተማ የሥራ ማቆም አድማውን ተከትሎ ሱቆችንና ሆቴሎችን ለማሥከፈት የተደረገው ሙከራ ወደ ግጭት ማደጉን ከቦታው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በአሁኑ ሠዓት የከተማው ህዝብ ወደ አደባባዮች የወጣ ሲሆን በአጸፋው የመንግሥት ታማኞች በየአቅጣጫው እየተኮሡ እንደሆነ ለማወቅ ችለናል ወረታ፤ ሃሙሲትና አመድበር ቀውጢ ተፈጥሯል!
የጉማራና ርብ ድልድዮች በተጋድሎ ወጣቶች ቁጥጥር ስር ወድቀዋል። ከጎንደር ወልድያና ባሃርዳር መንገዶች ተዘግተዋል። የገጠሩ ህዝብ ከነትጥቁና ፈረሱ እየፎከረና እየሸለለ ወደ ከተሞቹ ገብቷል፤ ከከተማው ወጣቶች ጋር በመሆንም አካባቤውን ተቆጣጥሯል። ሁኔታው ሁሉ በቃ ተቀይሯል።
ደብረታቦር አሁንም ፀጥ ብላለች። ምንም አይነት እንቅስቃሴ የለም።ፎገራ ወረታ ከተማ ታሪክ ተቀየረ፡፡ ጦርነቱ ተጀምሯል፡፡ ተደራጅተው የቆዩ ወጣቶች የገጠሩም የከተማውም ዝናሩን እያገማሸረ ታጥቆ ወጥቷል፡፡ጉጅሌና ፖሊስ ድራሹ ጠፍቷል፡፡ እየተቧደነ መደበቂያ ፍለጋ ላይ ነው፡፡ ሀሙሲቶችና የጉማራ ገበሬ ታጥቆ እየገባ ነው፡፡ ከደብረታቦር የታጠቁ ወጣቶች ወረታ ገብተዋል፡፡
 አዊ ዞን ከፍተኛ ተቃውሞ እየተካሄደ ነው ፤በጣም ከልክ ያለፈ ተኩስ አለ። ምን ያህል ሰው እንደሞተ እና እንደቆሰለ ኣልታወቀም።


የሰማያዊ ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ በኦዲት ኮሚሽኑ ተበተነ

  


የሰማያዊ ፓርቲ ኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን በተነ፡፡ አዲስ የሥራ አስፈጻሚ ለመምረጥና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ለመወያየት አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ መስከረም 2009 ዓ.ም. እንደሚያደርግ፣ የፓርቲው የኦዲትና ምርመራ ኮሚሽን ሰብሳቢ አቶ አበራ ገብሩ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ፓርቲው ነሐሴ 8 ቀን 2008 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ የሥራ አስፈጻሚው ጉዳይ ተነስቶ ውይይት መደረጉን ያስታወሱት አቶ አበራ፣ ‹‹ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በቁጥር የተጓደለ  ነው፡፡ በተጓደሉ አባላት ምትክ መርጦ ማሟላት አልቻለም፡፡ በዚህ ሁኔታ ደግሞ የማስፈጸም አቅም አይኖረውም፡፡ ስለዚህ ኮሚሽኑ ሥራ አስፈጻሚውን በትኖ ጠቅላላ ጉባዔ ለማድረግ ወስኗል፤›› በማለት አክለው አስረድተዋል፡፡
ጠቅላላ ጉባዔው እስከሚሰበሰብ ድረስ የፓርቲው እንቅስቃሴና የዕለት ተዕለት ሥራው አይታጐልም ወይ በሚል ከሪፖርተር ለቀረበ ጥያቄ፣ ‹‹አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ የተጠራበት አንደኛው ምክንያት ይኼ ነው፡፡ እስከዚያው ድረስ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ምክትል ፕሬዚዳንቱ እየሠሩ ይቆያሉ፡፡ በዚህ አሠራር ሙሉ በሙሉ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴውን ሥራ ሸፍኖ መሥራት እንደማይቻል የታወቀ ነው፡፡ ይህ የራሱ የሆኑ እንቅፋትና ችግሮች አሉት፡፡ እስከዚያው ድረስ የሚሸፈኑ ነገሮች ካሉ ይሸፈናሉ፡፡ መሸፈን የማይችሉት ነገሮች ደግሞ እንቅፋት እንደሆኑ ይቀጥላሉ፤›› በማለት አስረድተዋል፡፡
በተመሳሳይ የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ነገሠ ተፈረደኝ የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መበተኑን ለሪፖርተር ያረጋገጡ ሲሆን፣ ቀጣይ ጠቅላላ ጉባዔ እስከሚሰበሰብ ድረስ የፓርቲውን ሥራ እያከናወኑ እንደሚቆዩ አስረድተዋል፡፡
በሰማያዊ ፓርቲ መተዳደሪያ ደንብ መሠረት የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ 11 አባላት እንደሚኖሩት ይገልጻል፡፡
ነገር ግን ባለፈው መስከረም በተካሄደው የሥራ አስፈጻሚ ምርጫ ፕሬዚዳንቱ ካቀረቧቸው ዕጩዎች መካከል፣ ብሔራዊ ምክር ቤቱ ሦስቱን አለመቀበሉን መዘገባችን ይታወሳል፡፡
ስምንት ሆነው ሥራ መጀመራቸውን የሚያስታውሱት አቶ ነገሠ፣ ‹‹ከስምንታችን በልዩ ምክንያት እንደገና አንድ አባል ጐደለ፡፡ ሰባት ሆነን በምንሠራበት ወቅት በፓርቲው ውስጥ የተለያዩ አለመግባባቶች ተፈጥረው ነበር፡፡ ስለሆነም ጠቅላላ ጉባዔ እንዲጠራ ተወስኖ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይከናወን ቀረ፡፡ አሁን በቅርቡ ደግሞ ከሰባቱ አባላት መካከል ሁለቱ በተለያዩ ምክንያት ሳይገኙ ቆዩ፡፡ ሊቀመንበሩ [ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት] ደግሞ ወደ ካናዳ ከሄዱ ሁለት ወር ሊሆናቸው ነው፤›› በማለት የውሳኔውን ምክንያት አስረድተዋል፡፡
‹‹በአራት ሥራ አስፈጻሚዎች የአሥራ አንድ ሰዎች ሥራ መሥራትና ምልዓተ ጉባዔ ማሟላት ያስቸግራል፤›› ሲሉም አሁን በፓርቲው ውስጥ ያለውን ሁኔታ ገልጸዋል፡፡
የፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ የፓርቲው ፕሬዚዳንት በማይኖርበት ወቅት የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተክቶ ይሠራል ስለሚል፣ እስከሚቀጥለው ጉባዔ ድረስ ምክትል ፕሬዚዳንቱ የፓርቲውን ሥራዎች እያከናወኑ ይቆያሉ፡፡

ሕወሓት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል፤ ሕወሓት መስጊድ ውስጥ በተሰበስቡ ወጣቶች ላይ ቦምብ ወረወረ



#Ethiopia #Oromoprotests ሕወሓት በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ጥቃት ማድረሱን ቀጥሏል። ሕወሓት መስጊድ ውስጥ በተሰበስቡ ወጣቶች ላይ ቦምብ ወረወረ። #EthioMuslims #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)ለቅሶ የሚቀመጠው የሞተበትን ሃዘንተኛ የሚያሰቃየው የሕወሓት መንግስት በኦሮሚያ ክልል ግድያውን መቀጠሉን መረጃዎች ሲጠቁም በዛሬው እለት በምእራብ ሃረርጌ ማሳላ ወረዳ ልዩ ስሙ ዋልተሲስ በሚገኘው መስኪድ ላይ የኣግዓዚ ወታደሮች በመስኪዱና ውስጥ በነበሩት ሰዎች ላይ ጉዳት ማድረሳቸው ታወቀ።
በመስኪድ ውስጥ የነበሩ ወጣቶችን በመክበብ ለመያዝ ሲሞክሩ ሲከሽፍባቸው መስጊዱ ላይ ቦምብ በመወርወር ያቃጠሉት ሲሆን በውስጡ የተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱ ሲታወቅ የሞትና የቁስለቱ ጉዳት ብዛት እስካሁን ለማረጋገጥ ኣልተቻለም፤ እስካሁን የታወቀው ኣብዲ ኢማም የተባለው ወጣት ከነሕይወቱ መቃጠሉ ሲሆን በርካቶች ላይ ከፍተኛ የእሳት ኣደጋ ጉዳት ደርሶባቸዋል። #ምንሊክሳልሳዊ

ከአ.አ. ወደ ባህርዳር የሚወስደው መንገድ ደምበጫ ድልድይ ሰልፈኞች ዘግተውታል



አማራ ተጋድሎ ዛሬም ተቀጣጥሎ ቀጥሏል::
ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር የሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘውን ደምበጫ ድልድይ ሰልፈኞች ዘግተውታል። የመንገድ መዝጋቱ ዓላማ የወያኔን ኢኮኖሚ ለማዳሸቅ ነው። የመንገድ መዝጋቱ እንቅስቃሴ በዚህ ሁኔታ ከቀጠለ በነዳጅ እጥረት ምክንያት በቅርብ ጊዜ ውስጥ በአዲስ አበባ የሚንቀሳቀስ ተሽከርካሪ አይኖርም።
እንዲሁም ከባህርዳር ወደ አ.አ የሚያስገባው ሙሉአለም ችግኝ ሀሙሲት ላይ ተዘግቷል::
ብዙ የወያኔ ታፔላወች ተሰባብረዋል።”ወያኔ ሌባ” “ወያኔ ሌባ” ደምቆ የስተጋባል ሰልፈኞች ያስተጋቡት ጩኸት ነበር። የገብያ ቀን ቢሆንም አርሳ አደሮች ወደ ከተማ እንዳይገቡ በሚሊሻዎች ታግደዋል። በርካታ ወጣት እየጨፈረ ነው።ከተለያዬ ሰፈር ሰልፉን ለመቀላቀል አሁንም ህዝቡ እየተመመ ነው



Saturday, August 27, 2016

በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯ ታወቀ



በአሁኑ ሰዓት ደብረማርቆስ ከተማ በአጋዚ ወታደር መወረሯን መረጃ ደርሶናል፡፡ ከፍተኛ ውጥረት ላይ ትገኛለች፡፡ ማርቆስን ጥቁር ደመና ተጭኗታል፡፡ ህዝቡ በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፡፡ ለአጋዚ ወታደር የምግብና የመጠጥ አቅርቦት የሚሰጥ ሆቴል ካለ ህዝቡ እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስጠንቅቋል፡፡ ባለፈው በተደረገው ከፍተኛ ህዝባዊ ተቃውሞ…

Image result for agaze ethiopian soldiers

በጎጃም የደንበጫ ፣ የአማኑኤል ፣ የብር ሸለቆ ህዝብ ተቃውሞውን ተቀላቅሏል!!



#Ethiopia #Amharaprotests : በጎጃም የደንበጫ ፣ የአማኑኤል ፣ የብር ሸለቆ ህዝብ ተቃውሞውን ተቀላቅሏል!! የብር ሸለቆ ወጣቶች አውራ ጎዳናዎችን ተቆጣጥረዋል ፤መንገድ ዘግተዋል ። #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi's photo.
Minilik Salsawi's photo.


የጎጃም ተቃዉሞ ገንፍሏል – #ግርማ_ካሳ



14045683_10210072017307718_7947312963569255026_n
በጎጃም የተለያዩ ቦታዎች ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች እየታዩ ነው። ከደጀን ተነስቶ ወደ ባህር ዳር የሚወስደዉን መንገድ እናበምርጦ ለማሪያም አድርጎ ከደሴ የሚመጣው መንገድ በምታገናኘዋ በግንደ ወይን ከፍተኛ ተቃዉሞ ተነስቷል። ከደጀን በደብረ ማርቆስ አድርጎ ወደ ባህር ዳር በሚወስደዉም መስመር፣ በጅጋ፣ ፍኖት ሰላም ፣ ማንኩሳ የሕዝቡ ቁጣ የተቀጣጠለ ሲሆን፣ ከወለጋ ወደ ወደ ባህር ዳር እና በደብረ ማርቆስ አድርጎ ከደጀን ወደ ባህር ዳር የሚወስዱትን መንገዶች የምታገናኘዋም የቡሬ ከተማ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ ተቃዉሞ ነው የተሰማው።
ከቻግኒ ከሚመጣውና በዳንግላ በኩል አድርጎ ወደ ባህር ዳር ከሚወስደው መንገድ ዉጭ፣ በጎጃም ባሉ ዋና ዋና መንገዶች በሙሉ ሕዝባዊ ተቃዉሞዎች እየተደረጉ ናቸው። በቅርቡ በዳንግላ፣መራዊ በመሳሰሉት ቦታዎች ተቃዉሞ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
ጋዜጠኛ ሙሉቀን ተስፋው በጎጃም ስለነበረዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ እንደሚከተለው አቅርቧል፡
ቡሬ ( በደብረ ማርቆስና በነቀምቴ መካከል ያለች ከተማ)
===
ቡሬ፤ በሬ ዛሬ የዐማራ ተጋድሎ ከተካሔደባቸው ከተሞች ዋነኛዋ ናት፡፡ ከጠዋቱ ሦስት ሰአት አካባቢ የጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እስከ ምሽት 12 ሰአት ድረስ ቆይቷል፡፡ የተጋድሎ ሰልፉ ማዶ በሚባለው የከተማው ክፍል የተጀመረ ሲሆን ከሰላሳ ሺህ በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ተጋድሏቸው ሲያሰሙ ውለዋል፡፡ ወልቃይት ዐማራ ነው፤ ኮ/ል ደመቀ እና የወልቃይት ጠገዴ የዐማራ ማንነት ጥያቄ አቅራቢ ኮሜቴዎች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ይፈቱ፤ መሬታችን ይመለስ፤ 25 ዓመት ታስረናል አሁን ግን በቃን፤ ዐማራነት ወንጅል አይደለም፣ ወያኔ ሌባ ነው፤ ብአዴን እኛን አይወክልም… የሚሉ መፈክሮች ገልተው ሲሰሙ ውለዋል፡፡ የወያኔ ደጋፊ የሆኑ ድርጅቶችና ግለሰቦች ንብረት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ ትንሳኤ ሆቴል (ባለቤቱ ዐማራ ሲያስገድል የኖረ ሕወሓት ነው)፣ ቀበሌ 01 ጽ/ቤት፣ አብቁተ፣ የዓባይና የንግድ ባንኮች መጠነኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክን ሊያወድሙ የሚፈልጉ ተላላኪዎችን ወጣቱ ዐማራ አክሽፎታል፡፡ ኦሮሞ ወገኖቻችን ላይ የሚደርሰው ግፍ መቆም አለበት ሲሉም የዐማራ ሕዝብ አጋርነቱን አሳይቷል፡፡
በሰው ሕይወት ላይ የደረሰ አደጋ መኖሩን በተመለከተ ላቀረብነው ጥያቄ የዐይን ምስክር ሲናገሩ ‹‹እኔ በዐይኔ አንድ ለእረፍት የመጣ የዩንቨርሲቲ ተማሪ አጋዚ ሲገድለው አይቻለሁ፤ ሦስት ዐማሮችም በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል፤ በሕይወት ስለመኖር አለመኖራቸው ያወቁት ነገር የለም›› ብለዋል አንድ እማኝ በስልክ እንዳረጋገጡልን፡፡ የአጋዚ ወታደሮች ያቆሰሏቸው ሰዎች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ በቡሬ ከተማ መግቢያና መውጫ በሮች ሙሉ በሙሉ በወጣቱ ተዘግተዋል፡፡
ጅጋ ( በደብረ ማርቆስና ቡሬ መካከል ያለች ከተማ)
===
ጅጋ፤ የጅጋ ዐማሮች ዛሬ ለሦስተኛ ቀን የዐማራ ተጋድሎ አድርገዋል፡፡ የጅጋ ከተማ ሕዝብ ከነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. ጀምሮ በየቀኑ ወደ አደባባይ እየወጣ ተጋድሎውን እያደረገ ነው፡፡ በጅጋ እስካሁን አንዲት እህታችን ተሰውታለች፡፡ ከተማዋንና አጠቃላይ ወረዳውን ዐማሮች ራሳቸው የተቆጣጠሩ ሲሆን ዛሬ ላይ የሃይማኖት አባቶች ወጣቱን ለመሰብሰብ ሞክረው ነበር፡፡ የዐማራው ወጣትም ከእንግዲህ በኋላ የዐማራ የመኖር መብት ሳይረጋገጥ ተጋድሎው እንደማይቆም እንቅጩን በአንድ ድምጽ ተናግረው ስብሰባው ያለስምምነት መበተኑን ከቦታው በስልክ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በጅጋ ለተከታታይ ሦስት ቀናት ምንም ዓይነት የንግድ እንቅስቃሴም የለም፡፡ ሁሉም ዐማራ የተጋድሎ ጥያቄውን እያስተጋባ ነው፡፡ በስልክ ያነጋገርናቸው ወጣቶች ‹‹ከእንግዲህ በኋላ ዐማራነት ወንጅል ሆኖ የምንኖርበት ምንም ምክንያት የለም፤ የአባቶቻችን የአርበኝነት ታሪክ በዚህ ትውልድ ይደገማል›› ሲሉ በጎበዝ አለቃዎች ጭምር መመራት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
ቋሪት
===
ቋሪት፤ በቋት ወረዳ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ አድማሱን አስፍቶ የወረዳዋ ከተማ ገበዘ ማርያምም በሕዝብ ቁጥጥር ሥር ሆናለች፡፡ ገነት አቦ ከተማ ትናንት ከቀኑ ከ9፡00 እስከ 12፡00 የነበረውን የዐማራ ተጋድሎ ለማደናቀፍ ከወረዳው የወያኔ ተላላኪዎች የተውጣጡ የፖሊስና የሚንሻ አባላት ወደ ገነት አቦ ተላኩ፡፡ የገነት አቦ ዐማሮችም በአንድ ድምጽ ‹‹በመጣችሁበት መኪና አሁኑ ተመለሱ፤ አይ ካላችሁ ሕይወታችሁን ጠልታችኋል ማለት ነው›› አላቸው፡፡ ከመኪና ሳይወርዱ ተመለሱ፡፡ የከተማዋ ነዋሪዎች ለዛሬ ጠዋት ቀጠሩ፡፡ በቃላቸው መሠረት ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የተጋድሎ ሰልፉ ተካሄደ፡፡ የገበዘ ማርያም ከተማ ዐማሮችም ተጨመሩ፡፡ የከተማ ፖሊሶች ዝም አሉ፡፡ ከዞን የመጣ ሁለት መኪና የፌደራል ፖሊስም የቋሪትን ዐማራ መጋፈጥ አልቻለም፡፡ የፌደራል ፖሊሶች ልብሳቸውን ቀይረው ተደብቀው ዋሉ፡፡ ነፍጠኛው ዐማራ ጥይቱን ሲቆላው ዋለ፡፡ ለዚህማ ቋሪትን ማን ብሎት፡፡ በቋሪት ነገም የዐማራ ተጋድሎ ይቀጥላል፡፡
ማንኩሳ
=====
ማንኩሳ፤ በማንኩሳ የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉን ሰምተናል፡፡ በማንኩሳ ትናንት የተካሔደው የዐማራ ተጋድሎ መጠነኛ ቢሆንም ዛሬ ግን ወደ አደባባይ ያልወጣ የከተመዋ ነዋሪ አልነበረም ነው የተባለው፡፡ በማንኩሳ ዝርዝር ጉዳዮችን በስልክ መቆራረጥ ምክንያት ማግኘት አልቻልንም፡፡
ፍኖተ ሰላም
=======
በፍኖተ ሰላም ከተማ የዐማራ ተጋድሎ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል፡፡ ትናንት የአንድ ዐማራ ወጣት ነፍስ ያጠፈው ቅጥረኛ ምንሻ ቤት መቃጠሉንም ሰምተናል፡፡ የፌደራልና የአጋዚ ጦር በፍኖተ ሰላም ከተማ ከመጠን በላይ መግባቱን ሰምተናል፡፡ ዛሬ ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ሰዐት ድረስ መንገዶች ሁሉ ዝግ መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
ጉንደወይን
======
(ጉንደወይን ከደጀኝ አድርጎ በሞጣ፣ ደብረ ወርቅ በኩል አድርጎ ወደ ባህር ዳር በሚወስደው መንገድ ላይ ያለች ከተማ ናት)
በእነሴዎች አገር ጉንደወይን ትናንት ነሃሴ 19 ቀን 2008 ዓ.ም. ታላቅ የዐማራ ተጋድሎ ሰልፍ ተካሒዷል፡፡ የጎንቻ ሲሦ እነሴ ወረዳ ዐማሮች ትናንት ባካሔዱት ተጋድሎ የትግራይ የበላይነት ይብቃ፣ የማንነት ጥያቄያችን መልስ ይሰጥ፣ ዐማራነት ወንጀል አይደለም፣ የወንድሞቻችን ደም መፍሰስ መቆም አለበት… የሚሉ መፈክሮች መሰማታቸውን ዛሬ ከጉንደ ወይን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በተያያዘም ነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም. በብቸና አንድ የአገዛዙ መሣሪያ የሆነ ሰው ተገድሎ መገኘቱንም ሰምተናል፡፡