Thursday, March 30, 2017

“ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አሁንም ጸረ ሰላም ሃይሎች ይንቀሳቀሳሉ” ብለው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አራዘሙት | ዜና ትንታኔ

ከፋሲል የኔዓለም | የኢሳት ጋዜጠኛ
ዛሬ የኢህአዴግ ፓርላማ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ለተጨማሪ 4 ወራት እንዲራዘም ወስኗል። አቶ ሲራጅ ለአዋጁ መራዘም እንደ ምክንያት ያቀረቡት “ ክልሎች በሚዋሰኑባቸው አካባቢዎች አሁንም ጸረ ሰላም ሃይሎች ይንቀሳቀሳሉ” የሚል ነው። በመላ አገሪቱ በተደረገው የዳሰሳ ጥናት ህዝቡ አዋጁ እንዲራዘም መጠየቁና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መርማሪ ቦርድም “አዋጁ ቢራዘም መልካም ነው” የሚል አስተያየት መስጠቱ ተገልጿል።

ህወሃታውያን በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ “ ጸረ-ሰላም ሃይሎችን” በቁጥጥር ስር ማዋል ይችሉ እንደሆን እናያለን። ግን የገረመኝ የአርበኞች ግንቦት7 ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ የሚሰሩ ስራዎችን ለይቶ ውሳኔ ማሰለፉን በሰማሁ በሰዓታት ውስጥ አዋጁ ለ4 ወራት የመራዘሙን ዜና መስማቴ ነው። ያጋጣሚ ነገር ይሆን ወይስ …?
ለማንኛውም ህወሃት/ኢህአዴግ አካሄድኩ የሚለውን የዳሰሳ ጥናት በተመለከተ ኢሳት የካቲት 14 ቀን 2009 ዓም ባወጣው ዜና እንዲህ ብሎ ነበር- “ በተለያዩ የጎንደር ቀበሌዎች በተካሄዱ የህዝብ ስብሰባዎች፣ የአገዛዙ ካድሬዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በማንሳት በኩል የህዝቡ አስተያየት ምንድነው በሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም፣ ህዝቡ ግን በቀጥታ ከመናገር ይልቅ በጽሁፍ ፣ “ እናንተን አንቀበላችሁም፣ አናውቃችሁም፣ ከህዝብ ውጭ ሆናችሁዋል” የሚል መልስ በብዛት መስጠቱ ካድሬዎችን አስደንግጧል። አንዳንድ ሰዎች “ አዋጁን ስታውጁ እኛን አላማከራችሁንም፣ ሁሌም በራሳችሁ ከላይ ወስናችሁ ከጨረሳችሁ በሁዋላ ነው እኛን የምትጠይቁን፣ እኛ ደግሞ ኮማንድ ፖስት ተነሳ አልተነሳ ከግድያና አፈና አትታቀቡም፣ ብትፈልጉ አንሱት ባትፈልጉ ተውት፣ ጥቅሙን መጨረሻ ላይ ታገኛላችሁ” የሚሉ አስተያየቶችም በብዛት ተሰጥተዋል።”
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቡድን አዋጁ እንዳይነሳ አስተያየት መስጠቱን በተመለከተም ኢሳት በጥር 30 ዘገባው ላይ እንዲህ ብሎ ነበር – “በአማራ ክልል የሚታየውን የጸጥታ ሁኔታ ለመገምገም ከፌደራል የተላከው የኮማንድ ፖስቱ አጣሪ ቡድን ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ቢነሳ ህዝቡ በቀጥታ በመንግስት ላይ ከእስካሁኑ የከፋ ጥቃት ሊሰነዝር ይችላል ሲል አስጠንቅቋል። ኮማንድ ፖስቱ “ የክልሉን ህዝብ ገትቶ የያዘው መሳሪያ ነው” ያለ ሲሆን፣ አዋጁ ቢነሳ ከእስካሁኑ በከፋ ሁኔታ አመፁን ለማስቀጠል ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠናል” ብሎአል፡፡ለአንድ ወር ያክል በጎንደር፣ በባህርዳር እና በአዊ ዞን የተለያዩ ቦታዎች ተዘዋውሮ የህዝቡን ሁኔታ ማጥናቱን የሚገልጸው የፌደራል ኮማንድ ፖስት ቡድን፣ በአማራ ክልል የተካሄደው ተሃድሶ የይምሰል እና ስር ያልስደደ ነው ሲል አጣጥሎታል።”
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የተራዘመው በድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የነጻነት ሃይሎችን ለመደምሰስ አይመስለኝም። ይህ እንደማይሆን እነሱም ያውቁታል፤ ባለፉት 6 ወራት ታጋዮቹ ራሳቸውን በማጠናከር በኩል ብዙ ስራዎችን ሰርተዋል፤ “ሳይቃጠል በቅጠል” የሚባልበት ጊዜ አልፏል። አዋጁን ለማራዘም የተገደዱት በተለይ በ2 ምክንያቶች መሆኑን አምናለሁ። ጥልቅ ተሃድሶ ብለው ባዘጋጁዋቸው መድረኮች ላይ የህዝቡ ቁጣ በቀላሉ እንደማይበርድ አረጋግጠዋል። በመድረኮች ላይ የተሰጡት አስተያየቶች ፍርሃት ለቆባቸዋል። አንድም ሰው እነሱን የሚደግፍ አስተያየት አለመስጠቱ ግራ አጋብቷቸዋል። በእኔ እምነት ህወሃታውያናንን እያስፈራቸው ያለው በድንበር አካባቢ ከሚንቀሳቀሱ ሃይሎች በበለጠ የመሃል አገሩ ህዝብ ቁጣ ነው። ሰሞኑን በተደረገ አንድ ስብሰባ ላይ ፣ “መሃሉ ዳግም ከተነሳ ከእንግዲህ በመሳሪያ አናቆመውም” የሚል አስተያየት በከፍተኛ ባለስልጣን ተነግሯል። በጎንደር አንድ የመኮንኖች ስብሰባ ላይም እንዲሁ መኮንኖች ” ፖለቲካዊ መፍትሄ ካልተገኘ በስተቀር የህዝቡ ተቃውሞ በጉልበት የሚቆም አይሆንም” የሚል አስተያየት ሰጥተዋል። ወታደሩ ሰልችቷል።
ሌላው ምክንያት ደግሞ በድርጅቶች ውስጥ ያለው መከፋፈል እየጨመረ መሄዱ ነው። በተለይ ኢህአዴግን ከመሰረቱት 4 ድርጅቶች ውስጥ የሁለቱ ህልውና አዳጋ ላይ ወድቋል። በእነዚህ ድርጅቶች ውስጥ በማንኛውም ጊዜ “ውስጣዊ ፍንዳታ” ሊከሰት ይችላል። አዋጁ በሚቀጥሉት 4 ወራት ውስጥ እነዚህን ድርጅቶች ከውስጣዊ ፍንዳታ ይታደጋቸው አይታደጋቸው የምናየው ይሆናል።
ለማንኛውም ግን አዋጁ፣ በአንድም ይሁን በሌላ፣ አገዛዙን ዋጋ እያስከፈለው ነው። የገጽታ ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ፣ የአመኔታ ወዘተ።

Monday, March 27, 2017

የዴሞክራሲ አብዮትን “በኢኮኖሚ አብዮት” ማጨናገፍ አይቻልም!

ስዩም ተሾመ

ባለፈው ሳምንት “የኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት፡ በስህተት ላይ ስህተት በመድገም ስህተትን ማረም” በሚል ርዕስ አንድ ፅሁፍ አውጥቼ ነበር። በፅሁፉ ዙሪያ ከተሰጡኝ አስተያየቶች ውስጥ በአብዛኛው “ፅሁፉ የኢኮኖሚ አብዮቱን ዓላማና ግብ በትክክል አይገልፅም” የሚሉ ነበሩ። በመሆኑም ጉዳዩ በዝርዝር ለማብራራት እየተዘጋጀሁ ሳለ የአማራ ክልል ተመሣሣይ የኢኮኖሚ አብዮት ለመጀመር በዝግጅት ላይ መሆኑን የሚገልፁ ዘገባዎች ወጡ። በዘገባው መሰረት የአማራ ክልል “ዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበር” የተሰኘ ግዙፍ አክሲዮን ማህበር እየተቋቋመ መሆኑንና በተለያዩ የኢንዱስትሪ ዘርፎች 22 ፕሮጀክቶችን ለይቶ ወደ ሥራ ሊገባ እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ ፅኁፍ በሁለቱ ክልሎች “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል የተጀመረውን እንቅስቃሴ ከአጠቃላይ የሀገሪቱ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ ጋር አያይዤ በዝርዝር ለመዳሰስ እሞክራለሁ።


በመሰረቱ ባለፉት ጥቂት አመታት የኢትዮጲያ የውጪ ንግድ እያሳየ ያለው ማሽቆልቆል እየተባባሰ መጥቷል። በዘንድሮው ግማሽ ዓመት ከውጪ ንግዱ ዘርፍ ይጠበቅ የነበረው የውጪ ምንዛሪ ገቢ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተገኘው ግን 1.4 ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ሊገኝ ከታቀደው 56% ብቻ ነው። በ2008 የበጀት ዓመት ሊገኝ ከታቀደው ውስጥ 67.7% ብቻ የተገኘ ሲሆን ይህም በ2007 የበጀት ዓመት ከተገኘው በ139.3 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ ነበር።
ከጥቂት ቀናት በፊት መንግስት ችግሩን ለመፍታት ከላኪዎች ጋር ስብሰባ አድርጎ ነበር። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከፍተኛ አማካሪ አቶ አርከበ ዕቁባይ (ዶ/ር) መሪነት በተካሄደው በዚህ ስብሰባ ላይ ለውጪ ንግዱ ማሽቆልቆል በምክንያትነት ከተጠቀሱት ነጥቦች ውስጥ የመንግስት ቢሮክራሲያዊ አሠራር የፈጠራቸው ችግሮች ትልቁን ድርሻ ይዘዋል። ከዚህ በተጨማሪ፣ በሀገሪቱ የተከሰተው የውጪ የፀጥታ ችግር፣ በፀጥታው መናጋት የተፈጠረው ሥጋት ለውጪ ንግዱ መቀዛቀዝ ዋቢ መደረጋቸውን የሪፖርተር ዘገባ ያስረዳል።
በጠ/ሚ ፅፈት ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ ተሳታፊ የነበሩት የኢትዮጲያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ፕሬዚዳነት አቶ ሰለሞን አፈወርቅ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፤ “ዋናው መሰረታዊ ለውጥ ትርፍ ምርት እንዲመጣ ማድረግ፣ አዲስ ምርት ወደ ኢኮኖሚው ማምጣት መቻል እንዲሁም ከውጪ የሚገቡ ምርቶች የሚተኩ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ማምረት መቻል ነው’ ብለዋል። አያይዘውም “ስንዴ ከውጪ እያስመጡ ያንን ለዱቄት ፋብሪካዎች ሰፍሮ በመስጠት ለውጥ አይመጣም” ብለዋል። እንደ እሳቸው አገላለፅ፣ ችግሩን ለመቅረፍ የግብርና ጥሬ ዕቃዎችን በላክ ላይ የተመሰረተውን የውጪ ንግድ ወደ ኢንዱስትሪ ምርቶች ማሸጋገር አስፈላጊ ነው። ነገር ግን፣ የንግድ ሚኒስቴር ባወጣው ሪፖርት የኢንዱስትሪ ምርቶች የውጪ ንግድ እየቀነሰ መሆኑንና ለዚህም የግብዓት አቅርቦት፣ የጥራት ችግር፣ የመንግስት አገልግሎቶች የአሰራር ቅልጥፍና አለመኖር እና የገዢ ኩባኒያዎች በተለያየ ምክንያቶች ውል መሰረዝን በምክንያትነት ጠቅሷል።
በአጠቃላይ፣ የሀገሪቱ የውጪ ንግድ በየአመቱ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት የተጠቀሱትን ነጥቦች በሦስት ከፍሎ ማየት ይቻላል። አንደኛ፡- የመንግስት ቢሮክራሲያዊ አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች፣ ሁለተኛ፡- በሀገሪቱ የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር፣ ሦስተኛ፡- አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ናቸው።
በተለይ የውጪ ንግዱ ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ በመምጣቱ ምክንያት ውጥረት ውስጥ የገባው የኢህአዴግ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት መጋቢት 14/2009 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ “የአማካሪ ምክር ቤት” ለማቋቋም ወስኗል። ከዚህ ጎን-ለጎን፣ የአማራና ኦሮሚያ ክልሎች በየፊናቸው “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል ትላልቅ የኢንዱስትሪ ፕሮጀክቶችን ለይተው ወደ ስራ ገብተዋል። ስለዚህ፣ መንግስት በፌደራልና በክልል ደረጃ የሚያደርገው እንቀስቃሴ ከውጪ ንግድና የኢንዱስትሪ ዘርፍ ልማት ጋር በተያያዘ የተጠቀሱትን ችግሮች በዘላቂነት መቅረፍ ይችላል? ይህን ጥያቄ በአግባቡ ለመመለስ ከላይ የተጠቀሱት ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ከወቅታዊ የሀገሪቱ ፖለቲካዊ ሁኔታ አያይዞ መመልከት ያስፈልጋል።
በተለይ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በሀገሪቱ ለተፈጠረው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ዋናው ምክንያት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች የታየው የአመፅና ተቃውሞ እንቅስቃሴ ነው። ከ60% በላይ የሀገሪቱ ሕዝብ በሚኖርባቸው እነዚህ ሁለት ክልሎች የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር የኢህአዴግ መንግስትን የአስቸኳይ ግዜ አዋጅ እንዲያውጅ አስገድዶታል። ለአመፅና ተቃውሞ አንቅስቃሴው ዋናው ምክንያት የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብትና ነፃነት ባለመከበሩ፣ የመንግስት ሥራና አሰራር በአብዛኛው የሕብረተሰብ ክፍል ዘንድ የእኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ጥያቄ በማስነሳት ነበር። ስለዚህ፣ በሀገሪቱ ለተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ዋናው ምክንያት የኢህአዴግ መንግስት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክበርና ማስከበር፣ እንዲሁም በመንግስታዊ ሥርዓቱ ውስጥ የሚስተዋለውን ስር-የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ ስለተሳነው ነው።

​ሀገሪቱ የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር የተዳረገችበት ምክንያት የኢህአዴግ መንግስት በዴሞክራሲና መልካም አስተዳደር ረገድ ከሕዝቡ የለውጥና መሻሻል ፍላጎት ጋር አብሮ መሄድ ስለተሳነው። ስለዚህ፣ የኢህአዴግ መንግስት መልካም አስተዳደርና ቀጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ ሥርዓት መገንባት ስለተሳነው፣ እንደ ማንኛውም የሕብረተሰብ ክፍል፣ ለንግድና ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሃብቶችና ድርጅቶች አስፈላጊውን አገልግሎትና ድጋፍ እየሰጠ አይደለም። የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት ከተጠቀሱት ሦስት መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ አንደኛው “የመንግስት ቢሮክራሲያዊ አሠራርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግር” ነው። ስለዚህ፣ አንደኛው ችግር ዋና መንስዔ ራሱ የኢህአዴግ መንግስት ነው።
በተመሣሣይ፣ በመልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ግንባታ ረገድ የሚደረገው ጥረት ሲጨናገፍ ሕዝቡን ለአመፅና ተቃውሞ፣ ሀገሪቱን ለፀጥታና አለመረጋጋት ችግር ዳርጓታል። የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት ከተጠቀሱት መሰረታዊ ችግሮች ውስጥ ሁለተኛው “በሀገሪቱ የተከሰተው የፀጥታና አለመረጋጋት ችግር” ነው። በድጋሜ ለሁለተኛው ችግር ዋና መንስዔ ራሱ የኢህአዴግ መንግስት ነው።
እስካሁን ድረስ የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ የመጀመሪያ ሁለት ችግሮች ዋና መንስዔ ራሱ የኢህአዴግ መንግስት እንደሆነ ተመልክተናል። በመቀጠል ደግሞ በሦስተኛ ለይ የተጠቀሰው “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግርን የኦሮሚያና አማራ ክልላዊ መስተዳደሮች ተግባራዊ ማድረግ ከጀመሩት የኢኮኖሚ አብዮት ጋር አያይዘን በዝርዝር እንመለከታለን።
የኦሮሚያና አማራ ክልሎች በሀገሪቱ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ተዓምራዊ ለውጥ ያመጣል፣ ለብዙ ሺህ ወጣቶች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል፣ …ወዘተ በሚል እሳቤ በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ ገብተዋል። ለምሳሌ፣ የአማራ ክልላዊ መስተዳደር “የዓባይ ኢንዱስትሪ ልማት አክሲዮን ማህበርን” 25 በመቶ ድርሻ የአክሲዮን ድርሻ እንደሚገዛ ተጠቅሷል። በተመሣሣይ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደር በኢኮኖሚ አብዮቱ ከሚቋቋሙት የአክሲዮን ድርጅቶች ውስጥ እስከ 35% የአክሲዮን ድርሻ ሊኖረው እንደሚችል በማህበራዊ ድረገፆች ላይ እየተገለፀ ይገኛል። እንደ ማንኛውም መንግስት ሁለቱም ክልላዊ መስተዳደሮች ከሕዝብ ከሚሰበሰበው በስተቀር የራሳቸው የሆነ የገቢ ምንጭ የላቸውም። ስለዚህ፣ ሁለቱም የክልል መንግስታት ከሕዝቡ በግብርና ቀረጥ መልክ የሰበሰቡትን ገንዘብ የቢዝነስ ተቋማት አክሲዮን ድርሻ ለመግዛት አውለውታል።
በኢኮኖሚ አብዮቱ የሚቋቋሙት በአገልግሎት፣ ማምረቻና ግንባታ ዘርፍ የሚሰማሩ የቢዝነስ ድርጅቶች ናቸው። የአማራና ኦሮሚያ ክልል መንግስታት የእነዚህን ድርጅቶች የአክሲዮን ድርሻ በመግዛት በኢኮኖሚው ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ ስለመግባታቸው ጥርጥር የለውም። ስለዚህ፣ ይህ ጣልቃ ገብነት የኢህአዴግ መንግስት ከሚያራምደው የኢኮኖሚ ፖሊሲ አንፃር ምን ያህል ተቀባይነት አለው?፣ የኢንዱስትሪ ዘርፉን ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ከማሻሻል አንፃር ምን አስተዋፅዖ ያበረክታል? ከዚህ ቀጥሎ፣ እነዚህንና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎችን ከሀገሪቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲ እና ከገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት (market economy) አንፃር የአማራና ኦሮሚያ ክልል መንግስታትን ጣልቃ ገብነትና ውጤታማነት በዝርዝር እንመለከታለን።
ከገበያ መር ኢኮኖሚ (market economy) ስርዓት አተገባበር ጋር ተያይዙ ብዙ አከራካሪ ጉዳዮች መኖራቸው እርግጥ ነው። በዋናነት ግን፤ “መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባት የለበትም” እና “መንግስት በተመረጡ የኢኮኖሚ መስኮች ጣልቃ መግባት አለበት” የሚሉት አመለካከቶች የሚጠቀሱ ናቸው። የኢህአዴግ መንግስት የመጀመሪያውን የኒዮ-ሊብራሊዝም አቀንቃኞች አመለካከት እንደሆነ በመጥቀስ “መንግስት በተመረጡ የኢኮኖሚ መስኮች ጣልቃ መግባት አለበት” የሚለውን አመለካከት እንደሚያራምድ ይታወቃል። ስለዚህ፣ የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት በኢኮኖሚው ውስጥ እያደረጉት ያለውን ጣልቃ ገብነት ከኒዮሊብራሊስቶች እይታ ሳይሆን ከራሱ ከኢህአዴግ መንግስት እይታ አንፃር መመልከት ይኖርብናል።
ከላይ እንደተገለፀው፣ የኢህአዴግ መንግስት የኢኮኖሚ ፖሊሲ “መንግስት በተመረጡ የኢኮኖሚ መስኮች ጣልቃ መግባት አለበት” የሚለው ነው። በኢኮኖሚ አብዮቱ በሚቋቋሙት ድርጅቶች አማካኝነት የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት በሀገሪቱ ኢኮኖሚ የአገልግሎት፣ ማምረቻና ግንባታ ዘርፎች ውስጥ ጣልቃ በመግባት ላይ ይገኛሉ። ነገር ግን፣ የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ጣልቃ መግባት ያለባቸው መቼ ነው?
በገዢው ፓርቲ የኢኮኖሚ ፖሊስ መሰረት መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባት ያለበት “የገበያ ውድቀት” (market failure) ሲኖር ነው። አንዳንድ የዘርፉ ምሁራን ሁኔታውን፤ “Government legitimacy in a market economy arises from market failures” በማለት ይገልፁታል። “የገበያ ውድቀት መቼ ነው የሚኖረው?” ለሚለው ደግሞ አራት ዋና ዋና ምክንያቶችን መጥቀስ ይቻላል። እነሱም፣ 1ኛ፡- የምርትና አገልግሎቶች ማምረቻ/ማቅረቢያ ወጪ ከተጠቃሚዎች የመክፈል አቅም በላይ ሲሆን (Incomplete markets)፣ 2ኛ፡- የትክክለኛ መረጃ አቅርቦት ችግር ሲኖር (Information failures)፣ 3ኛ፡- የሕዝብ የአገልግሎት መስጫ ተቋማትን ለመገንባት ሲሆን (Public goods)፣ እና 4ኛ፡- ውጫዊ የሆኑ አሉታዊ ወይም አዎንታዊ ተፅዕኖዎችን በምርቱ የገበያ ዋጋ መመለስ የማይቻል ሲሆን (Negative/ positive Externalities) ናቸው።
ከላይ ከተጠቀሱት አራት መሰረታዊ ምክንያቶች አንፃር፣ የኦሮሚያና አማራ ክልላዊ መንግስታት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ለመግባት በወሰኑባቸው የአገልግሎት፣ ማምረቻና ግንባታ ዘርፎች “የገበያ ውድቀት (market failure) አለ” ማለት አይቻልም። ምክንያቱም፣ የግልና የማህበር ቢዝነስ ተቋማት በተጠቀሱት የኢኮኖሚ መስኮች ለመሰማራትና ተወዳዳሪ ለመሆን የሚያግዳቸው የገበያ ችግር የለም። ስለዚህ፣ የሁለቱም ክልል መንግስታት “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ለመግባታቸው የገበያ ውድቀትን በምክንያትነት መጥቀስ አይችሉም። ስለዚህ፣ የአማራና ኦሮሚያ ክልል መንግስታት “የኢኮኖሚ አብዮት” በሚል በኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴው ውስጥ ጣልቃ የገቡት የገበያ ውድቀት በሌለበት ሁኔታ ነው።
የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት የገበያ ውድቀት በሌለበት ሁኔታ በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ መግባታቸው እንደተባለው በኢንዱስትሪው ዘርፍ ተዓምራዊ ለውጥ ማምጣት ይችላሉ? የአክሲዮን ድርሻ ለመግዛት ያዋሉት የሕዝብ ገንዘብ የዘርፉን ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት ወደ ተሻለ ደረጃ ያሳድገዋል? በዘርፉ ካሉት የሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በምርትና ጥራት ተወዳዳሪ ሆነው ትርፋማ ይሆናሉ? በአጠቃላይ፣ የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እያሽቆለቆለ ለመሄዱ በምክንያትነት የተጠቀሰውን “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግርን መቅረፍ ይችላሉ? በዚህም፣ እንደተባለው ለብዙ ሺህ የአማራና ኦሮሚያ ክልል ወጣቶችና አርሶ አደሮች የስራ ዕድልና የገበያ ትስስር ይፈጥራሉ?
በመሰረቱ፣ መንግስት ከምንም ይሻላል እንጂ ከማንም ግን አይሻልም። ምክንያቱም፣ ምንም ነገር ከባዶ ይሻላልና ምንም ዓይነት የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ በሌለበት የገበያ ውድቀት (market failure) ውስጥ መንግስት ጣልቃ ቢገባ ይመረጣል። ነገር ግን፣ የገበያ ውድቀት በሌለበት መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ ሲገባ ግን በፍፁም ውጤታማና ተወዳዳሪ ሊሆን አይችልም። ምን ግዜም ቢሆን መንግስት በምርታማነትና ጥራት ከግል ተቋማት የተሻለ ሊሆን አይችልም። ስለዚህ፣ የኦሮሚያና አማራ ክልል መንግስታት የኢኮኖሚ አብዮት ለውጪ ንግድ ማሽቆልቆል ምክንያት የሆነውን “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግር ከመቅረፍ አንፃር የጎላ አስተዋፅዖ አያበረክትም።
የገበያ ውድቀት በሌለበት ሁኔታ የመንግስት ሥራና ድርሻ ለሀገር ውስጥና ለውጪ ቢዝነስ ተቋማት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ነው። በዚህም፣ የመንግስት ዋና የሥራ ድርሻ የፀጥታና አለመረጋጋት ችግሮችን በዘላቂነት በመቅረፍ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ሁኔታ መፍጠር እና የመንግስትን ሥራና አሠራር ወደ ላቀ ደረጃ በማሻሻል የተቀላጠፈ የአገልግሎትና ድጋፍ አሰጣጥ ሥርዓት መዘርጋት ነው። የሀገሪቱ የውጪ ንግድ እንዲያሽቆለቁል በምክንያትነት ከተጠቀሱት ውስጥ ሦስተኛው “አነስተኛ የሆነ የኢንዱስትሪ ምርት፣ ምርታማነትና ተወዳዳሪነት” ችግር ነው። በመሆኑም፣ ለሀገሪቱ የውጪ ንግድ ከግዜ ወደ ግዜ እያሽቆለቆለ የሄደበት ምክንያት የፌደራልና ክልል መንግስታት ድርሻና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ስለተሳናቸው ነው። በተለይ የአማራና ኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳደሮች እንደ መንግስት የሚጠበቅባቸውን ሥራና ኃላፊነት በሚገባ ባለመወጣታቸው ምክንያት ተፈጠረ ችግር ነው። አሁንም ከህዝብ ከተሰጣቸው ስልጣንና ኃላፊነት ውጪ በኢኮኖሚው ውስጥ ጣልቃ በመግባት ለችግሩ መፍትሄ ለመስጠት ጥረት በማድረግ ላይ ናቸው።
በመጨረሻም፣ አብዛኞቹ የአማራና ኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ደጋፊዎችና አቀንቃኞች ከላይ ከተገለፀው የሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሁኔታ ይልቅ የአብዮቱ ዓላማና ግብ ላይ ማተኮር ይቀናቸዋል። ስለዚህ፣ አብዛኞቹ “የኢኮኖሚ አብዮቱ ከተቀመጠለት ከግብ (objective) አንፃር መታየት አለበት” የሚል መከራከሪያ ሊያቀርቡ ይችላሉ። ወይም ደግሞ ከላይ በኢኮኖሚ አብዮቱ አማካኝነት የሁለቱ ክልል መንግስታት ጣልቃ በሚገቡባቸው የኢኮኖሚ ዘርፎች ውስጥ “የገበያ ውድቀት አለ” የሚል መከራከሪያ ሊቀርቡ ይችላሉ። ነገር ግን፣ “Market Efficiency and Government Intervention” በሚል ርዕስ የቀረበ ጥናታዊ ፅሁፍ በጉዳይ ዙሪያ የሚከተለውን ሃሳብ አስቀምጧል፡-
“Though the presence of, market failure implies that there may be a scope for government intervention, it does not imply that a particular government program aimed at correcting the market failure is necessarily desirable. To evaluate government program one must not only take into account their objectives but how they implement it.” Journal of International Business and Economics, Vol. 3(1), June 2015
በእርግጥ በኢኮኖሚ አብዮት አማካኝነት ለብዙ ሺህ የአማራና ኦሮሚያ ወጣቶች የሥራ እድል እና የገበያ ትስስር ለመፍጠር የተቀመጠው ግብ አስፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም። ነገር ግን፣ የሁለቱ ክልላዊ መስተዳደሮች በኢኮኖሚው ውስጥ የሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት መመዘን ያለበት ካስቀመጡት ግብ አንፃር ብቻ ሳይሆን ከፕሮግራሙ አተገባበር ጭምር መሆን አለበት። ለብዙ ሺህ የአማራና ኦሮሚያ ክልል ወጣቶች የሥራ እድል ለመፍጠር የሚቻለው እንዴት ነው?፣ የመንግስት ዕቅድና ፕሮግራም በምን ላይ ማዕከል ያደረገ ሊሆን ይገባል? ሁለት የዘርፉ ምሁራን “Human Capital and Sustainability” በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጥናታዊ ፅሁፍ እንዴት ተጨማሪ የሥራ ዕድሎችን መፍጠር እንደሚቻልና የመንግስት ዕቅድና ፕሮግራም ትኩረት በምን ላይ መሆን እንዳለበት እንደሚከተለው ይገልጻሉ፡-
“Contrary to popular belief, the principal source of new jobs is social development, not economic policy. Public stimulus programs, manipulation of the money supply and interest rates can certainly have short-term impact, but it is the growth and development of society that serves as the foundation and context for economic growth. Full employment can be achieved by broad-based social strategies that accelerate social development, including measures that improve the quality and quantity of education and training, promote entrepreneurship and self-employment, increase the speed of communication and transportation, encourage research and innovation, and more fully utilize the power of social organization, e.g., the Internet.” Journal of Sustainability ISSN 2071-1050
ከላይ በጥቅሱ ውስጥ እንደተገለፀው፣ ለወጣቶች ተጨማሪ የሥራ እድል ለመፍጠር መሰረቱ “ማህበራዊ ልማት” (social development) ነው። ለዚህ ደግሞ መንግስት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ዋና ትኩረት በሰው ሃብት ልማት ላይ መሆን አለበት። በመሆኑም፣ የመንግስት ሥራና ኃላፊነት፤ ተግባር ተኮር ትምህርትና ሥልጣና መስጠት፣ ሥራ ፈጣሪነትን ማበረታታት፣ የተቀላጠፈ የብድር አገልግሎት መስጠት፣ የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ አቅርቦት ጥራትና ተደራሽነትን ማሳድግ፣ የጥናትና ምርምር ሥራዎች ማበረታታት፣…ወዘተ የመሳሰሉ የድጋፍ ተግባራትን በማከናወን በሀገሪቱ ወይም በክልሉ የሰው ኃብት ልማት ማረጋገጥ ነው።
ስለዚህ፣ ለብዙ ሺህ ወጣቶች የሥራ-ዕድል ከመፍጠር አንፃር የመንግስት ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ትኩረት ማድረግ ያለባቸው የሰው ሃብት ልማት ነው። ነገር ግን፣ የአማራና ኦሮሚያ የኢኮኖሚ አብዮት ከሰው ሃብት ልማት ይልቅ በኢኮኖሚ እንቅስቃሴው ውስጥ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት ላይ ማዕከል ያደረገ ነው። በመሆኑም፣ የሁለቱም ክልሎች የኢኮኖሚ አብዮት ግቡን አይመታም።
በአጠቃላይ፣ በኢኮኖሚ ውስጥ ለሚስተዋለው ችግር ዋና መንስዔው ያለው የሀገሪቱ ፖለቲካ ነው። የኢትዮጲያ ፖለቲካ መሰረታዊ ችግር ደግሞ የኢህአዴግ መንግስት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክብር/ማስከበር አለመቻሉ ነው። በተለይ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች እየታየ ያለው ሕዝባዊ አመፅና ተቃውሞ ዋና መነሻ ምክንያቱ የኢህአዴግ መንግስት የዜጎችን ዴሞክራሲያዊ መብትና ነፃነት ማክበርና ማስከበር፣ እንዲሁም በመንግስታዊ ሥርዓቱ ውስጥ የሚስተዋለውን ስር-የሰደደ የመልካም አስተዳደር ችግር መቅረፍ ስለተሳነው ነው። “3ኛው ማዕበል፡ የልማታዊ መንግስት ፈተና” በሚለው ፅሁፌ በዝርዝር እንደገለፅኩት ይህ የአመፅና ተቃውሞ እንቅስቃሴ በትክክለኛው ግዜና ሁኔታ ውስት የተነሳ የዴሞክራሲ አብዮት ነው።
ይህን የዴሞክራሲ አብዮት አስፈላጊውን ለውጥና መሻሻል በማድረግ በተገቢው ሁኔታ ማስተናገድ ከተሳነን ሀገሪቷን ወደ ባሰ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ይከታታል። ሕዝቡ ዴሞክራሲያዊ መብቱና ነፃነቱ እንዲከበር፣ የመንግስት ሥራና አሰራር እንዲሻሻል፣ ስር የሰደደው የመልካም አስተዳደር ችግር እንዲቀረፍና የብዙሃኑን እኩልነትና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጥ የሚያነሳቸውን ፖለቲካዊ ጥያቄዎች በኢኮኖሚ አብዮት ምለሽ ለመስጠት መሞከር ችግሩን ከማባባስ የዘለለ ፋይዳ የለውም።
በአጠቃላይ፣ አንደኛ፡- የኢኮኖሚ አብዮቱ የዴሞክራሲ አብዮቱን ለማጨናገፍ ያለመ ነው፣ ሁለተኛ፡- የኢኮኖሚ አብዮቱ ግቡን አይመታም፣ ሦስተኛ፡- የኢኮኖሚ አብዮቱ አለመሳካቱ የዴሞክራሲ አብዮቱን መልሶ ያቀጣጥለዋል። ምክንያቱም፣ የዜጎች ሕገ-መንግስታዊ መብትና ነፃነት እስካልተከበረ እና የመልካም አስተዳደር ችግር በዘላቂነት እስካልተቀረፈ ድረስ፣…ወዘተ አሁን በውጪ ንግዱ ላይ እየታየ ያለው ማሽቆልቆል ወደ አጠቃላይ የሀገሪቱ ኢኮኖሚ ይስፋፋል። የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ሲቀዛቀዝ ፖለቲካዊ ችግር ያስከትላል፣ በዚህም ሕዝቡ ለአመፅና ተቃውሞ አደባባይ ይወጣል። ስለዚህ፣ የዴሞክራሲ አብዮት በኢኮኖሚ አብዮት አይጨናገፍም!

Thursday, March 23, 2017

በመኪና አደጋ የ41 ሰዎች ሕይወት አለፈ source zhabesha

አቢሰሎም ፍሰሐ
ከደሴ ወደ ባሕር ዳር ሲጓዝ የነበረ ISUZU የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከ20 ሜትር በላይ ወደ ሆነ ገደል መንገድ ስቶ በመግባቱ ለ41 ሰዎች ሕይወት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡
መጋቢት 13 ቀን 2009 ዓ.ም ረፋድ ላይ አደጋው እንደደረሰ የነገሩን ምንጮች አውቶቡሱ ይዟቸው ከነበሩት 65 ሰዎች መካከል በሕይወት የተረፉት 24ቱ ብቻ ናቸው ተብሏል፡፡
ከአደጋው የተረፉት አብዛኛዎቹ ተጎጅዎች በከባድ ሁኔታ የተጎዱ ሲሆን በወልዲያ ሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው ቢሆንም ሕይወታቸው አስጊ ነው ተብሏል፡፡
የወልዲያና አካባቢው ሕዝብ ደም በመለገስና ተጎጂዎችን በሚችለው ሁሉ ቢረዳ መልካም እንደሆነም መረጃውን የሰጡን ሰዎች ተናግረዋል፡፡

Tuesday, March 21, 2017

ለሚኒስትሮች፣ጀነራሎች፣የደህንነት ሹሞች፣ዲፕሎማቶች በሙስና ለቤት መሥሪያ የተሠጠ መሬትና ቤት ይመለስ source zhabesha


ክፀ/ት ፂዩን ዘ/ማርያም

‹‹ምላሳዊው መንግሥት በ12 ዓመታት ውስጥ ቤት ሠርቶ ያስረከበው ለ175,000 ሰዎች ብቻ ሲሆን ለተመዘገቡት 800 ሽህ ሰዎች ለማዳረስ 55 ዓመታት ይፈጅበታል!!!››

‹‹በአዲስ አበባ በ1997ዓ/ም እና በ2005ዓ/ም 800 ሽህ በተደረጉ ሁለት የጋራ መኖሪያ ቤት ምዝገባዎች ከ800 መቶ ሽህ በላይ የከተማ ነዋሪዎች ቤት ለማግኘት ተመዝግበው እድላቸውን እየተጠባበቁ ነው፡፡ የህወሓት የቤት ልማት ፕሮጀክት ፕሮግራም ከጀመረ 12 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤት ሠርቶ ያስረከበው ለ175,000 ሰዎች ብቻ ነው፡፡ የቤት ግንባታ በዚህ ፍጥነት ከቀጠለ የተመዘገበውን ከ800 ሽህ የሚልቅ ነዋሪ የቤት ባለቤት ለማድረግ 55 ዓመታት ይፈጃል ማለት ነው፡፡›› የካቲት 22 ቀን አዲስ ዘመን ጋዜጣ
በከተሞች ከሚኖረው ህዝብ መካከል ከ50 እስከ 60 በመቶ ቤት አልባ መሆኑ፣ የቤት ፈላጊ ቁጥርም በዓመቱ በ150 ሽህ እየጨመረ መምጣቱና የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ቤቶች የመገንባት ፍጥነት አዝጋሚ መሆን መጪውን ጊዜ አስፈሪ ድቅድቅ ጨለማ እንደሚያደርገው የዘርፉ ባለሙያዎች ጥናት ይመሠክራል፡፡
መንግሥት በቅንጅት ምርጫ በተሸነፈ ማግስት የአዲስ አበባ ህዝብን ለማማለልና ድጋፍ ለማግኘት በ1997 ዓ/ም የመኖሪያ ቤትን እጥረት ለመቅረፍ መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ይፋ አደረገ፡፡ በአዲስ አበባ  400 ሽህ ተመዝጋቢዎች ቤት ልማት ፕሮጀክት ፕሮግራም ከጀመረ 12 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤት ሠርቶ ያስረከበው ለ140,000 ሰዎች ብቻ ነው፡፡
ኮንዶሚኒየም ቤቶች
የአዲስ አበባ ቤቶች ፕሮጀክት ቢሮ 335,000 ቤቶች በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ማለትም በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት አቅዶል፡፡ ቢሮው 6.3 ቢሊዩን ብር በአመታ ለቤቶች ግንባታ በመመደብ ለተመዘገበው 860 ሽህ ህዝብ ቤት ማዳረስ አቅዶል፡፡ የቤቶች ኤጀንሲ 25 ቢሊዩን ብር ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ገቢ ለመሰብስብ አቅዶል፡፡ በአጠቃላይ በሁለተኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 750,000 ኮንዶሚኒየም ቤቶች በመላ ሃገሪቱ ለመሥራት ታቅዶል፡፡ በሁለተኛው እቅድ ዘመን 190,000 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ለነዋሪዎች ለማስተላለፍ ከዚህም ውስጥ ለልማት ተነሽዎች 50,000 ነዋሪዎች ድርሻ አላቸው፡፡
በ2005 ዓ/ም መኖሪያ ቤትን እጥረት ለመቅረፍ  መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ለሁለተኛ ግዜ ምዝገባ ይፋ አደረገ፡፡ በ10/90፣ በ20/80 እና በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ተመዝጋቢዎች እንደየአቅማቸው ማለትም በ10/90፣የተመዘገበ የቤቱን ግንባታ ወጪ 10 በመቶ መቆጠብ ሲሆርበት 90 በመቶውን ከኢትዩጵያ ንግድ ባንክ ብድር ተመቻችቶለት በየወሩ በመክፈል የቤት ባለቤት ይሆናል፡፡ በ20/80 ተመዘገበ 20 በመቶ በመቆጠብና 80 በመቶውን ብድር ባንክ ይሸፍንለታል እንዲሁም  በ40/60 የተመዘገበ 40 በመቶ መቆጠብ ሲኖርበት 60 በመቶ ከባንክ ብድር በማግኘት የቤት ባለቤት ይሆናል፡፡ በቤታቸው ውስጥ እየኖሩ በየወሩ እንደ ቤት ኪራይ ለባንክ በመክፈል ሲጨርሱ የቤት ባለቤት ካርታ ይወስዳሉ ነበር የተባለው፡፡ አንድ ሰው በ100/100 ከከፈለ በዚህ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ውስጥ አይካተትም ሙሉውን የከፈሉ ሰዎች ከባንክ ጋር ምንም ብድር ስለማይሹ በዚህ ፕሮግራም ሊጠቃለሉ አይገባም፡፡ ለነዚህ ሰዎች አስተዳደሩ በ100/100 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት መዝግቦ ቦታ በመስጠት ልዩ  መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት መንደፍ አለበት፡፡
‹‹በ10/90፣ በ20/80 እና በ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ከ800,000 (ስምንት መቶ ሽህ ) በላይ ቤት ፈላጊዎች ተመዘገቡ፡፡ በዚህ ፕሮግራም በድምሩ 317,863 ቤቶችን የገነባና እየገነባ በ653.3 ሄክታር መሬት ከሊዝ ነፃ ማቅረቡንና 17.5 ቢሊዩን ብር ቀጥታ ድጎማ ማድረጉን ከንቲባው ገልጧል፡፡››
 Approximately 860,000 people are registered across the three housing schemes – 10/90, 20/80 and 40/60 In addition to the ongoing construction of low cost houses, the Addis Abeba Saving Houses Development Enterprise (AASHDE) has embarked on the construction of new condominium houses at a cost of more than one billion Birr, Fortune learnt
‹‹More than 862,000 residents open special saving accounts for housing፡- ADDIS ABABA, June 28, 2013-A total of 862,216  Addis Ababa residents opened special saving  accounts for 10/90 and 20/80 housing schemes at the Commercial Bank of Ethiopia. The CBE will finance from 80% to 90% of the total cost of the houses while the rest will be covered by residents as down payment. ››
የ40/60  የጋራ መኖሪያ ቤቶች
  • በ2005 ዓ/ም የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች 160,000 (መቶ ስልሳ ሽህ) ሲሆኑ ለባለአንዱ መኝታ ቤት 162,000 ብር፣ለባለሁለት መኝታ ቤት 250,000 ብር እና ለባለሦስት መኝታ ቤት 386,000 ብር ዋጋ ተተምነዋል፡፡ ከመቶ ስልሳ ሽህ ተመዝጋቢ ሰዎች 154 ሥህ ሰዎች በየወሩ በባንክ ተቀማጭ ገንዘብ ያደርጋሉ፡፡ ከዚህ ውስጥ 29 ሽህ ሰዎች ወይም 40 በመቶው የኮንዶሚኒየም ቤቱን የግንባታ ውጪ ከፍለዋል እንዲሁም 13 ሽህ ሰዎች ሙሉውን ክፍያ ፈፅሟል፡፡
  • የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ግባታቸው በመጠናቀቅ ላይ ሚገኙት በአቃቂ ክራውን ሆቴልና በሠንጋ ተራ በተገነቡት 1,292 ቤቶች ተገነቡ፡፡ 96.12 በመቶ ተጠናቀዋለወ፡፡ አስተዳደሩ የገነባውን ቤቶች ለኢትጵያ ንግድ ባንክ ያስረክባል፡፡
የ10/90 እና 20/80  የጋራ መኖሪያ ቤቶች
  • በ2005 ዓ/ም የ10/90 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ተመዝጋቢዎች 700,000 (ሳባት መቶ ሽህ) ሲሆኑ ለባለአንዱ ፣ለባለሁለት እና ለባለሦስት መኝታ ቤት ለመገንባት ተመዝግበዋል፡፡
  • የ10/90 እና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት በአራት ኣመታት ውስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቁ  39,249 ቤቶች ብቻ ናቸው፡፡ ይህም  6 በመቶ ተጠናቀዋል ማለት ነው፡፡ አስተዳደሩ የገነባውን ቤቶች ለኢትጵያ ንግድ ባንክ ያስረክባል፡፡የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ ኃላፊ ኃይሌ ቀንአ ለዋልታ ሬዲዩ እንደገለፁት፡፡
  • የልማታዊው መንግሥት የቤት ግንባታ በዚህ የቀንድ አውጣ ፍጥነት መጎዝ ከቀጠለ የተመዘገበውን 700 ሽህ ነዋሪዎች የቤት ባለቤት ለማድረግ ግማሽ ክፍለ ዘመን 55 ዓመታት በላይ ዓመታት ይፈጃል ማለት ነው፡፡
ማጠቃለያ
በአዲስ አበባ በ2005ዓ/ም 860 ሽህ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ቤት ለማግኘት ተመዝግበው እድላቸውን እየተጠባበቁ ነው፡፡ የህወሓት የጦር አበጋዞች መንግሥት ቤት ልማት ፕሮጀክት ፕሮግራም ከጀመረ 4 ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በእነዚህ 4 ዓመታት ውስጥ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ40/60  የጋራ መኖሪያ ቤቶች 1,292 እንዲሁም የ10/90 እና 20/80 ቤቶች 39,249 በድምሩ  40,541 ኮንዶሚኒየም ቤቶች ወይም 4.7 በመቶ ብቻ  ተገንብቶል ማለት ነው፡፡የልማታዊው መንግሥት የቤት ግንባታ በዚህ የቀንድ አውጣ  ፍጥነት መጎዝ ከቀጠለ የተመዘገበውን 860 ሽህ ነዋሪዎች የቤት ባለቤት ለማድረግ ብዙ ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ ይፈጃል ማለት ነው፡፡
በአዲስአበባ ከተማ ከተማው ነዋሪዎች አንገብጋቢ መኖሪ ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር ሊጣጣም አልቻለም፡፡ በዚህም ተነሳ ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት እጥረት መኖሩ ይታወቃል፡፡ ዜጎች የመኖሪያ ቤቱን ዋጋ 10 በመቶ፣ 20 በመቶ 40 በመቶ መቆጠባቸውን፣ ቅድመ ሁኔታዎችን ማሞላታቸውን፣ ለብድር ብቁ መሆናውን እንዲሁም  ሂሳባቸውን በባንክ ማስቀመጣቸው ሲረጋገጥ ባንኩ የሚያቀርበው ብድር የመኖሪያ ቤቱን ዋጋ  90 በመቶ፣ 80  በመቶና 60 በመቶ ብድር ያዘጋጃል፣ብድሩንም ባንኩ ይፈቅዳል፡፡
ዜጎች የመኖሪያ ቤቱን ዋጋ 10 በመቶ፣ 20 በመቶ 40 በመቶ ቆጥበው ልክ ዕጣው ሲደርሳቸው የ10፣20 እና 40 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ መክፈል ግዴታ አለባቸው፡፡ከምግብ፣ ከልብስ፣ከልጆች ትምህርት ቤትና ከሌሎች ተጨማሪ ወጪዎች ባሻገር ማለት ነው፡፡
‹‹ሆኖም በዋጋ ግሽበት ወይንም በውጭ ምንዛሪ ልዩነትና በሌሎች በማንኛውም ምክንያት በቤቱ መነሻ ዋጋ ላይ የሚመጣ የዋጋ ጭማሪ 40 በመቶ ቁጠባውን ተጠቃሚው የሚሸፍን ሲሆን 60 በመቶ ተመጣጣኝ ብድር ባንኩ ይሸፍናል፡፡››….‹‹ለብድሩም 7.5 በመቶ የብድር ወለድ በዓመት ይታሰባል፣ሆኖም የወለድ ስሌቱ በኢትዩጵያ ንግድ ባንክ የተመን ክለሳ ሊያደርግበት ይችላል፡፡›› ይላል፡፡
ኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ የዋጋ ንረት ተሸካሚው ማን ነው መንግሥት በዚህ ዋጋ ኮንዶሚኒየም ቤት በሁለት አመት ሠርቼ አስረክባለሁ ብሎ ብዙ አመታት ከፈጀበት ጥፋቱና የዋጋ ግሽበቱ ተጠያቂ የሚሆነው ማን ነው፡፡
‹‹However, due to inflation of construction material, labor costs and design changes, the prices had to be increased to an unspecified amount.››. The price for each condominium unit will increase by an unknown amount. According to Addis Ababa housing enterprise official Ato Yidnekachew Walelign, the 40/60 condominium lottery will be handled by Commercial Bank of Ethiopia.››
‹‹Currently, 38,709 condominium units are under construction on 12 sites around Addis Abeba. However, most of the projects are behind schedule which has brought serious backlash from people saving money.
ችግሮች
  • የመንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት መንግስት ባጀት እየመደበና ዜጎችም እየቆጠቡ ከፍተኛ መዋለነዋይ የሚፈስባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በጣም አዝጋሚ በሆነውና አቅም በሌለው የመንግስት ቢሮክራሲ መከናወን አይችልም፡፡ የመንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት እየተገነቡ ያሉት ቤቶች ጥራት አጠያያቂ ሆኖል፡፡ ሥራ ተቆራቾችና አማካሪ ድርጅቶች በህጉ መሠረት ኃላፊነታቸውን አልተወጡም፡፡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች አሠጣጥ ግልፅነት የጎደለውና አድሎዊ መሆኑ የአደባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ለፖለቲካ ካድሬዎች፣ ለመከላከያና ለፖሊስ ሠራዊት፣ለደህንነት አባሎችና እንዲሁም በዘር ላይ የተመሠረተ መጠቃቀምያ፣ በአጠቃላይ የአፓርታይድ ስርዓት መዘርጋቱን ዜጎች በማስረጃ ይመሠክራሉ አሊያም ይህን ሙስና ጊዜ ያወጣዋል፡፡
  • መንግሥት ‹‹በልማት ስም!›› የዜጎችን መሬት በመንጠቅ በጨረታ መሬቱን በመሸጥ ዜጎቹን ንብረት የማፍራት መብት ህገ-መንግስታዊ መብት በመግፈፍ፣ ነባር የመኖሪ መንደሮች ‹‹በልማት ምክንያት›› በሚፈናቀሉ ዜጎች ሁኔታውንና የቤት ችግሩን ይበልጥ አባብሶታል፡፡
  • በፊዴራል ደረጃ ካሉ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል 77 ቢሮዎች፣ የራሳቸው ቢሮዎች/ህንፃ የሌላቸው ስለሆነ የግለሰብ ህንፃን እንደ ቢሮዎች ተከራይተው 380 ሚሊዩን ብር በዓመት ይከፍላሉ፡፡ መንግሥት የራሱን ቢሮዎች ሳይሰራ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት አከናውናለሁ ማለት ውሃ አይቆጥርም፡፡
  • የህወሓት መንግሥት ለዝቅተኛው ህብረተሰብ የኮንዶሚኒየም የመኖሪያ ቤት ግንባታ ሳያመቻች ለመካከለኛና ለኃብታሞች የሪል እስቴት የቤቶች ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ የህዝቡን መሬት በመንጠቅ ለእነዚህ የሪል እስቴት ዲቨሎፐርስ ሽርካነት በሙስና የሸጠ መንግሥት ነው፡፡
  • የቤቶችና ቁጠባ ባንክ፣(ሞርጌጅ ባንክ) መክሰርና ወደ ንግድ ባንክ ጋር መዋሃድ የህወሓት መንግሥት በባንኩ ብዙ ሚሊዩን ብር ተበድረው ባለመክፈል ባንኩ የደረሰበት ኪሳራና ታላቅ ሴራ ጊዜ ያወጣዋል፡፡
ሞርጌጅ ባንክ (የቤቶችና ቁጠባ ባንክ)
በኢትዩጵያ  ውስጥ የመኖሪያ ቤቶች እጥረትና ችግር በዜጎች በቅድሚያ ከሚነሱት ችግሮች መካከል ናቸው፡፡የቤቶችና ቁጠባ ባንክ፣(ሞርጌጅ ባንክ) ለህብረተሰቡ በረጅም ጊዜ የሚከፈል የብድር አቅርቦት ተደራሽ በማድረግና የህብረተሰቡን የገንዘብ ቁጠባ ባህል ለማሻሻል፣ ዜጎች በግላቸው ተደራጅተው ያለአንዳች አድሎ በግልፅነት፣ ሁሉም ባለድርሻ አከላት ማለትም የቤት ገንቢዎች ገንዘብ በመቆጠብ፣የቤቶችና ቁጠባ ባንክ ብድር በማመቻቸት፣ መንግስታዊ የከተማ አስተዳደር መሬት በማመቻቸት ሁሉም በተሳተፉበት የመኖሪያ ቤቶች ልማት ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ የተሠራበት ወርቃማ ጊዜ ነበር፡፡ በአሁኑ ጊዜ፣የቤት ኪራይ ዋጋ አንድ ተከራይ ከሚያገኘው ገቢ ከ40 እስከ 50 በመቶ ደርሶል፡፡ በከተማ የሚኖሩ ዜጎች ለምግብ ፍጆታ 55 በመቶ ከገቢያቸው ያወጣሉ፡፡ እንዲህም ሆኖ አንድ መኖሪያ ቤት ለማግኘት የተመዘገበ ዜጋ በየወሩ ከሚያገኘው ላይ መቆጠብ አለበት፡፡ ይህ ሁሉ መሥዋትነት የከፈሉ ዜጎች ገንዘባቸውን ቆጥበው ቤቶቹ ሳይሠሩ በትንሹ ከ4 እስከ 12 ዓመታት በቤት ኪራይ ችግርና በቁጠባ ሲሰቃዩ ምን ዓይነት በሙስና የተጨማለቀ መንግሥት እንዳለን መረዳቱ አያዳግትም፡፡

የቤቶችና ቁጠባ ባንክ ዓላማዎች
  • ዝቅተኛ ኑሮ ደረጃ ያላቸው ዜጎች በማህበር ተደራጅተው፣ ከገቢያቸው ፣በዝግ አካውንት በየወሩ ገንዘብ በመቆጠብ፣ በረዥም ጊዜ ሞርጌጅ ቤቶች እንዲገነቡ ማድረግ
  • መካከለኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በማህበር ተደራጅተው፣ ከገቢያቸው፣በዝግ አካውንት በየወሩ ገንዘብ በመቆጠብ፣ በማህበር ተደራጅተው እንዲገነቡ ማድረግ
  • ከፍተኛ ገቢ ያላቸው ዜጎች በማህበር ተደራጅተው፣ ከገቢያቸው፣በዝግ አካውንት በየወሩ ገንዘብ በመቆጠብ፣ በማህበር ተደራጅተው እንዲገነቡ ማድረግ
  • ባንኩ ለቤት አልሚዎች ብርድ በማመቻቸት ለተለያዩ ህብረተሰብ ክፍሎች እንደ ገቢአቸው መጠን የረዥም ጊዜ ብድር በማበደር ከተበደሩበት ዓመት እስከ ጡረታ ሊወጡ አንድ አመት እስኪቀራቸው ድረስ ማለትም በትንሹ ከ25 እስከ 30 ዓመታት ጊዜ ውስጥ የሚከፈል ብድር ያመቻች ነበር፡፡ የባንኩ ዋነኛ ዓለማ ህብረተሰቡ ካለው ገቢ ቆጥቦ ቤት እንዲሰራ ሁሉንም ነገር ማመጫቸት ነበር፡፡
  • የባንኩ ተበዳሪ ማሳወቅ ያለበት ወርሃዊ ገቢውን የደሞዙን አንድ አራተኛ በወር እየከፈለ በቡዙ አመታት ውስጥ የሚከፈል ብድር ማመቻቸት ነው፡፡ የባንኩ ደንበኛ የህይወት ኢንሹራንስና የእሳት ኢንሹራንስ እንዲገባ ባንኩ ያደርጋል፡፡ የወለድ ምጣኔው 4 በመቶ ነበር፡፡ወያኔ ዛሬ 7.5 በመቶ የወለድ ምጣኔ ይጠይቃል፡፡
  • መንግስት የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ለመቅረፍ የፖሊሲና የስትራቴጂ ለውጥ ማድረግ ይጠበቅበታል ማለትም ሞርጌጅ ባንክን ማፍረስ አልነበረበትም፡፡ የቤቶችና ገንዘብ ቁጠባ ባንክ ከ15 እስ 30 ዓመታት ለሚደርስ ጊዜ በማበደር በአለማችን አሥራሩ ይታወቃል፡፡ የንግድ ባንክ ለንግድና ለማኑፋክቸሪንግ ሥራዎች ከ5 እስከ 10 ዓመታት ጊዜ የሚቆይ ብድር ለደንበኞቹ ያመቻቻል፡፡
  • የቤት አልሚዎች መጠነ ሠፊ ተሳትፎ የነበራቸው በመሆኑ ግልፅ አሠራር፣ ተጠያቂነት፣ የባለቤትነት ስሜትና ከቤቱ ግንባታ ጀምሮ እስከ ፍፃሜው ድረስ በጋራ ቤቶች ግንባታ ሥራ ላይ ይሰማሩ ነበር፡፡ እንደዛሬው ግልፅ ያልሆነ ለአድሎ በር ከፋች የሆነ ሎተሪ ብሎ ጨዋታ የለም፡፡ ቤት ሠሪው ተጀምሮ እስከሚጨረስ መብትና ግዴታውን ያውቃል፡፡
  • ሞርጌጅ ባንክ (የቤቶችና ቁጠባ ባንክ) በሃገሪቱ ያለውን የቤት ልማት ችግርን ለመቅረፍ መልሶ ማቆቆም ብቸኛው ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡ የቤቶችና ገንዘብ ቁጠባ ባንክ ሠራተኞች ምስክርነታቸውን ይስጡበት፡፡
የቤቶች አቅርቦትና ፍላጎት፡- (Housing Supply and Demand)
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤት ሠርቶ ያስረከበው ለ175,000 ሰዎች ብቻ ነው የቤት ልማት ፕሮጀክት ፕሮግራም ከተጀመረ 12 ዓመታት ተቆጥረዋል፣በሃገሪቱ በየአመቱ 150,000 (መቶ ኃምሳ ሽህ) የቤት ፈላጊዎች አሉ፡፡ የወያኔ መንግስት እየሄደበት ያለው መንገድ የቤት ችግርን በፍጽም አይፈታውም፡፡ የህብረተሰቡን የቤት ፍላጎት ከማሞላት አንጻር ጉዞው የዔሊ ነው፡፡ የቤት ግንባታ ፕሮጀክቶቹ በሁለት ዓመት ለማጠናቀቅ የታቀደ ግንባታ አራት ዓመታት ይፈጃል፣ የግንባታ ሂደቱም ሙያዊ ያልሆነ ቢሮክራሲ የበዛበት ነው፡፡ አሁን ባለው ግንባታ ሂደት ከቀጠለ የህዝቡን የቤት ፍላጎት በፍጽም ማርካት አይቻለውም፡፡ ማለትም የዜጎችን የቤት ፍላጎት ከመፍታት አንጻር በጣም ቀርፋፋ ነው፡፡ ለዚህም ዋነኛ ማስረጃ በሃገሪቱ የከተማና የገጠር ከተሞች የህዝብ ብዛት ያገናዘበ የቤቶች ልማት ጥናት ባለመኖሩ የቤት ፈላጊዎች ቁጥር ፍላጎትና አቅርቦት ሰማና ምድር መሆኑ እሙን ነው፡፡የጋራ መኖሪያ ቤቶች ፈላጊዎች በከፍተኛ ትምህርት ተቆም በየዓመቱ ከ100,000 ሽህ በላይ ተመራቂዎች ይወጣሉ፡፡ መንግሥት ሌላ ዙር ምዝገባ ቢያካሂድ የቤት ፈላጊው ቁጥር የትዬለሌ በመሆኑ ሌላ ምዝገባ እንደማይካሄድ ከንቲባ ድሪባ ኩማ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም የቤት ግንባታ ፕሮግራም ለሥራ ዕድል ፈጠራ ስኬት ማምጣቱና የአገር ውስጥ የግንባታ አቅምን ከመፍጠር አንፃር በጎ ጎኖች አሉት፡፡
አማራጭ መፍትሄዎች፣- መንግሥት አሁን እየተጎዘ ባለበት ረዥም መንገድ የተለየ አጭር አቆራጭ አማራጭ መንገድ ካልፈለገ የቤት ችግሩ በአጭር ጊዜ አይፈታም፡፡
  • ሞርጌጅ ባንክ፣-ለዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና፣ መካከለኛ ገቢ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ቤት እንዲያለሙ ፣አቅም ላላቸው የአገር ውስጥ ሥራ ተቆራጮችና አማካሪ ድርጅቶችን ሙሉ ለሙሉ ኮንትራት ሰጥቶ እየተከታተለ ቤቱ እንዲገነባ ማድረግ
  • ሞርጌጅ ባንክ በኩል መንግሥት ለሪል እስቴት አልሚዎች መሬት በዝቅተኛ የሊዝ ዋጋ በማቅረብና፣ መሠረተ ልማት መንገድ መብራት፣ውኃ የመሳሰሉትን በማሞላት፣ከሞርጌጅ ባንክ ጋር ትስስር በመፍጠር አልምተው ሲያበቁ በተተመነላቸው ዋጋ ቤቶቹን ሞርጌጅ ባንክ ለደንበኞቹ እንዲያስረክብ ማድረግ፣
  • ሞርጌጅ ባንክ፣ የአገር ውስጥና የውጭ ተቆራጮችና የሪል እስቴት አልሚዎች በተናጥል ወይም በሽርክና እንዲሠሩ ማነጋገርና መጋበዝ፣አለበት እንላለን፡፡
ኮልፌ ቀራንዩ ክፍለ ከተማ የቁሻሻ መጣያ አደጋ፡-ወረዳ አንድ ላለፉት 50 ዓመታት በተከለለው 37 ሄክታር የደረቅ ቁሻሻ መጣያ፣ ከፍታው 13 ሜትር፣ ጥልቀቱ 40 ሜትር ተደርምሶ የ113 ዜጎች ህይወት ቀጥፎል፡፡  ይህ የቁሻሻ መጣያ አደጋ ሊያስከትል ይችላል በሚል ስጋት አገልግሎት እንዳይሰጥ ታሽጎ ነበር፡፡መንግሥት ሰንዳፋ የቁሻሻ ማስወገጃ በ1 ቢሊዩን ብር አስገንብቶ በኦሮሚያ ህዝባዊ እንቢተኝነት ትግል ህዝቡ በመከልከሉ ቆሞል፡፡ ከዛም በበፊቱ ቦታ በድጋሚ ቁሻሻ መጣል ተጀመረ፡፡
የምዕራብ አፍሪካ ሃረራቶች ከፍተኛ የከተማ ነዋሪዎች እድገት፣ በከተማ መሬት ይዞታ ፖሊሲና የከተማ አስተዳደራዊ ጥገናዊ ለውጥ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ አስከትሎል፡፡ የከተማ ነዋሪዎች ቁጥር መጨመር፣የገጠር የከተሞች ነዋሪዎች ቁጥር  እድገትና፣የገጠር ነዋሪዎች ህዝብ ቁጥር እንዲጨምር አድርጎል፡፡ በአብዛኛው የከተማዎች እድገት ዋነኛ ምክንያት ከገጠር ወደ ከተማ የሚፈልሠው ህዝብ ቁጥር ማሻቀብን አስከትሎል፡፡ መንግሥታት በአጭርና በረዥም ጊዜ የከተማ መሬት ይዞታ ፖሊሲ መንደፍና  የገጠር ነዋሪዎች የመሬት ይዞታ ፖሊሲ መንደፍ  ችግር ለመቅረፍ ዋነኛ መፍትሄ ነው፡፡
Table 4: Urban Slums in Eastern Africa
CountrySlum Annual Growth RatePopulation Slum 1990(‘000s)Population Slum 2001(‘000s)
Ethiopia4.85,98412,315
Kenya5.93,9859,620
Madagascar5.32,5625,696
Sudan5.25,70812,441
Tanzania6.25,60114,113
Source: Habitat (2006).
አብዛኛው የምዕራብ አፍሪካ ሃረራቶች የከተማ ነዋሪዎች የሚኖሩት በቁሻሻ ሥፍራች (Slums Areas) ማለትም በከተማው ውስጥ በሚገኙ የማይፈለጉ ለሰው ልጆች መኖሪያነት የማይመቹ የተለያዩ ቁሻሻ ሥፍራዎች ነው፡፡ የከተማ ደሃ ነዋሪዎች በነዚህ ቁሻሻ ቦታዎች ላይ ሠፍረው ይኖራሉ፡፡ ቦታዎቹ በመንግሥትና በሃብታም ግለሰቦች የማይፈለጉ ገደላማ፣ወንዞች  ዳር፣ረግራጋ ሥፍራዎች በመሆናቸው የፋብሪካዎች ኬሜካሎች ዝቃጭ መፍሰሻ ሥፍራ፣የቁሻሻ መጣያ ቦታዎች በመሆናቸው ለጤና ተስማሚ ስላልሆኑ ነዋሪዎቹ በተለያየ በሽታ ተጠቂዎች ናቸው፡፡  በቁሻሻ ሥፍራዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች አመታዊ ዕድገት ምጣኔ ከአመት አመት በመጨመር ላይ ይገኛል፡፡ ከሰንጠረዡ መረዳት እንደሚቻለው በኢትጵያ  በቁሻሻ ሥፍራዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች አመታዊ ዕድገት ምጣኔ 4.8 በመቶ ሲሆን በ1990 እኤአ አምስት ሚሊዩን 984 ሽህ ሰዎች ይኖሩ ነበር፡፡ በ2001 እኤአ አስራ ሁለት ሚሊዩን 315 ሽህ ሰዎች  በቁሻሻ ሥፍራዎች እንደሚኖሩ በጥናት ተረጋግጦል፡፡ ከ1990 እኤአ እስከ  2001እኤአ ባለው አስራ አንድ አመታት ውስጥ በ48.6 በመቶ የነዋሪዎች ቁጥር ጨምሮል፡፡ በ2017 እኤአ ምን ያህል ሊደርስ እንደሚችል በግምት ስናሰላው የትየለሌ ስለሚሆን የከተማ መሬት ይዞታ ፖሊሲና የከተማ አስተዳደር ይህን ችግር ለመቅረፍ እውቀትም፣አቅምም፣ ብቃትም የለውም፡፡  በኮልፌ ቀራኒዬ የቁሻሻ ሥፍራ የሚኖሩ 113 ነዋሪዎች ሞትና የአካል ጉዳት መድረሱ በከተማው አስተዳደርና መንግሥት ንዝህላልነትና ለዜጎቹ ደንታ እንደሌለው ያሳያል፡፡ ሥራቸው በየግዜው የከተማ መሬት ከህዝብ እየነጠቁ በጨረታ በመሸጥ ላይ ያተኮሩ ስው ሰው ያልሸተተ የከተማ ልማት ፖሊሲ ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡ አሁንም ገደል ስር ቤቶች ሠርተው የሚኖሩ አደዋ አደባባይ ወደ ሃያ ሁለት መሄጃ ኮንጎ ሠፈር ነዋሪዎች ህይወት ትኩረት ሊሠጠው ይገባል፡፡ እንዲሁም በግንፍሌ፣ ቀበናና ቡልቡላ ወንዞች ዳርቻ ቤት ቀልሰው የሚኖሩ ዜጎች በአደጋ ላይ መሆናቸው ሳይታለም የተፈታ ነው፡፡ የከተማ አስተዳደሩና ከንቲባ በአዲስ አበባ የሚገኙ በፈንጅ ወረዳ ላይ በሚኖሩ ዜጎች ህይወትን ከአሁኑ መታደግ ኃላፊነት አለባቸው፡፡
ለሞች ቤተሰቦች መፅናናትን እንመኛለን!!!
ሥርዓቱ ካልተለወጠ የቤቶች ችግር አይፈታም!!!
ለሚኒስትሮች፣ጀነራሎች፣የደህንነት ሹሞች፣ዲፕሎማቶች በሙስና ለቤት መሥሪያ የተሠጠ መሬትና ቤት ይመለስ!!!
የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!!! አስቸኮይ ጊዜ አዋጁ ይነሳ!!!

የአማራ ህዝብ የሚፈልገው ቅሪላ የሚጠልዝበት ሜዳ ሳይሆን ዳቦ የሚያስገኝለት ፋብሪካ ነው (ቬሮኒካ መላኩ) 


 






ለዚህ ፅሁፍ የተጠቀምኩት ርእስ ሞገደኛና ስፖርትን ጠል ሊያስመስልብኝ ይችላል። እውነታው እሱ አይደለም። እኔ ራሴ ስፖርት የምወድና ስፖርት ለአንድ ህዝብ የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ የምገነዘብ ነኝ። ለዚህ ፅሁፌ መነሻ የሆነኝ ብአዴን ሰሞኑን በአማራ ክልል ውስጥ 12 የኳስ ሜዳ ለመገንባት ቃል እንደገባ በመሃበራዊ ሚዲያ ማንበቤ ነው ።
ህውሃት በከባድ በፋብሪካ ቁንጣን በምትሰቃየው ብይ በምታክለው ትግራይ ክልል ኢንዱስትሪዎችን ለመገንባት እቅድ ሲይዝ ። ኦህዴድ ” የኢኮኖሚ አቢዮት ” በሚል መሪ ቃል ለክልሉ ወጣት ስራ የሚያስገኝ የመአድን ማውጫ እና ሰርቪስ ሴክተሮችን ለመገንባት እቅድ ይዞ ሲተገብር ሎሌው ብአዴን የአማራ ወጣት በባዶ ሆዱ ስራ ፈትቶ ኳስ የሚጠልዝበት 12 ስታዴየም እሰራለሁ እያለ ነው።

የብአዴን ነገር ይገርመኛል። ብአዴን አንድ “ታዋቂ ” መዝሙር አለው። ” ያልተንበረከክነው! ” ይባላል  :) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች ታሪክ ውስጥ እንደ ብአዴን ተንበርካኪና ለአሽከርነት የተመቼ ድርጅት የትም አይገኝም ። ብአዴን መንበርከክ ብቻ ሳይሆን በትከሻው የህውሃትን የአንባሻ ዱቄት ተሸክሞ በእንብርክኩ የሚሄድ ድርጅት ነው።

የህውሃት የፖለቲካ ሃሊዮት በፖለቲካው ለዘመናት የበላይነትን ለመቆየት ኢኮኖሚውን እና ሚሊቴሪውን መቆጣጠር የሚል ነው። ይሄን ሃሊዮት ተግባራዊ ለማድረግ ባለፉት 25 አመታት ፍትሃዊ ያልሆነ የሃብት ማግበስበስ ላይ ሲሰማሩ ሌላውን ደግሞ በተለይም አማራውን በድህነት ይማቅቅ ዘንድ የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል እያደረጉም ነው ።

CSA (የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታስቲክ ኤጀንሲ) በቅርቡ ባወጣው መረጃ ትግራይ ላይ እስካሁን 300 ከፍተኛ ፣ከባድና መካከለኛና ኢንዱስትሪዎች (Medium & Large Scale Industries) የተገነቡ ሲሆን፤ በአማራ ክልል ግን 100 መካከለኛና ዝቅተኛ ኢንዱስትሪዎች (Medium & small scale Industries ) ብቻ ተከፍተዋል። ነገር ግን የአማራ ህዝብ የትግራይን ህዝብ ከ7 እጥፍ በላይ የሚበልጥ ከመሆኑም በተጨማሪ በጥሬ ዕቃ አቅርቦትም ሆነ ለኢንዱስትሪ ቦታ ምቹነት አማራ ክልል ከትግራይ እጅግ በላቀ መልኩ ተመራጭ የሚያደርጉ ብዙ ሁኔታዎች አሉት፡፡

ለምን እንዲህ ሆነ ተብለው ሲጠየቁ “በኦሮሚያ ክልል እኮ ከትግራይ የበለጠ 320 ኢንዱስትሪዎች ተሰርተዋል” ብለው ይነግሩናል::
ይገርማል! ብይ የምታክለውን ትግራይን ቋጥኝ ከሚያካክሉ ክልሎች አስበልጦና ነፋፍቶ በማሳየት ፍትሐዊ ባልሆነ መልኩ ያገሪቱን ሐብት ለክልላቸው ብቻ ያጋብሳሉ፡፡
አስቡት እስኪ የትግራይን 7 እጥፍ የሚበልጠው ኦሮሚያ 320 ስላለው፤ 7 እጥፍ ያነሰችው ትግራይ ላይ 300 መከፈቱ ፍትሐዊ ነው ብሎ ግግም ማለት ምን አይነት ደረቅነት እና ስግብግብነት ነው ?!

ባለፈው ጆሯችንን እስኪታመም እና አይናችን ሊጠፋ እስኪደርስ በየሚዲያው METEC (የብረታብረት ኮርፖሬሽን) ውቅሮ ላይ በኢትዮጵያ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ትራክተርን ሙሉ በሙሉ የሚፈበርክ ፋብሪካ ሲከፍት፤ ደብረ-ብርሐን ላይ ደግሞ መገጣጠሚያውን በመክፈት ሜቴክም በበኩሉ ፍትሀዊነት ሰብኮልናል፡፡ እናወዳድርስ ብንል አቅልጦ ማምረትንና የተመረተው መገጣጠም ምን አገናኘው? እንኳን ሊወዳደር የደብረ ብርሐኑ፤ ፋብሪካ ተብሎ ሊጠራ እንኳን አይገባውም!
ያው እንደተለመደው ከትግራይ ፊት concave mirror ደቅነን፤ ከአማራ ፊት ደግሞ convex mirror በማስቀመጥ በአብየታዊ ዲሞክራሲ ወልጋዳ ሚዛን ፍትሃዊነቱን እንድናደንቅ እንገደዳለህ፡፡

ህውሃት የሚመራው መንግስት አላማው አገሪቱንና ህዝቡን በኢኮኖሚ ለማሳደግ ቢሆን ኖሮ እንደ አማራ ክልል ለኢንደስትሪ አመች የሆነ ክልል የትም አይገኝም ነበር ። ለማንኛውም ከባድ ኢንደስትሪ የደም ስር የሚባለው የኤሌክትሪክ ሃይልን ብንመለከት ክልሉ እምቅ ሃይል ያለው ነው ። በአባይ ዋናው ወንዝ ላይ ብቻ 12 ግድቦችና በድምር ወደ 50,000 ሜጋ ዋት የሚደርስ ኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት አቅም ያለው ክልል ነው ።
ኢትዮጵያ 27 የመስኖና አነስተኛ የኤሌክትሪህ ማመንጫ ፕሮጀክቶችን በአባይ ገባር ወንዞች ላይ በመገንባት 2 ሚሊዩን ሄ/ር መሬት በመስኖ ማልማትና ተጨማሪ ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ በማመንጨት ይቻላል።

እውነታው ከላይ የተጠቀሰው ሆኖ እያለ በወያኔ ግልፅ የአፓርታይድ ፖሊሲና በአሽከሩ በብአዴን አስፈፃሚነት የአማራ ህዝብ ከድህነት እንድወጣ አይፈለግም። ህውሃት ከሮም እና ከሌሎች የጣሊያን ከተማ ላይብረሪዎች ፋሽስት ጣሊያን ትከተለው የነበረውን ፖሊሲ ከሸልፍ እያወረደች መተግበር ከቆየች 25 አመታት አለፋት ።

ወያኔ ኢትዮጵያን ከተቆጣጠረ በኋላ ያደረገው ነገር ከሁሉም ክልል ተመርጠው ወደ ስልጣን እንድመጡ የሚደረጉት መመዘኛቸው በአማራው ላይ ከፍተኛ ጥላቻ ያላቸው በመሆናቸው እና ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር መኖር እና ያለመኖር ደንታ የማይሰጣቸው ሰዎች በመሆናቸው ብቻ ነው።
ብአዴንም ውስጥ ወደ ስልጣን እንድመጣ የሚፈለገው ” በአማራው ላይ ጥላቻ አለው ወይ? ” የሚል ፈተና ከተሰጠው በኋላ ያንን ፈተና ማለፍ ከቻለ በኋላ ነው። አሁን በተግባር እንደሚታየው አለምነው መኮንን የተባለ አሳማ ወደ ስልጣን እንድመጣ የሚደረገው ትግል ይሄን መመዘኛ በመቶ ፐርሰንት ስለሚያሟላ ነው ።

ከአሻንጉሊቱ እና በኢትዮጵያውያን ” ጠ/ሚ አቡሽ ” የሚል ቅፅል ስም በተሰጠው ሃይለማርያም ደሳለኝ ጀምሮ በሁሉም ክልል ያሉት በኦሮሞ በጋንቤላ በሱማሌ በትግራይ በቤንሻንጉል በደቡብ ክልል ያሉት የኢሃዴግ ኣመራሮች ምርጫ በኣማራ ላይ ባላቸው ጥላቻ ብቻ የተመረጡ ናቸው እስካሁን ድረስም ቢሆን ያ አሰራር ቀጥሏል በየትኛውም ክልል በኣማራውም ቢሆን ለአማራው ቀና ኣመለካከት ያለው ሰው ወደ ስልጣን በፍጹም ሊመጣ አይችልም።

አሁን የሚታየው የተቀነባበረና በፖሊሲ የታገዘ አማራውን አንገት የማስደፋት ፖሊሲ ለ40 አመታት በደንብ የተሰራበት ነው። አንድ ሁሉም ግንዛቤ ሊወስድበት የሚገባው የአማራ ህዝብ ይህንን በደሉን ለመርሳት/ ለመተው ቢቸገር እና ቀኑ ሲደርስ ሂሳብ ላወራርድ ቢል ሰው እንጂ መልዓክ አለመሆኑን ማወቅ አለባችሁ ።

Monday, March 20, 2017

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት (የጉዞ ማስታወሻ) አዲሱ አረጋ ቂጤሳ source mereja.com

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት (የጉዞ ማስታወሻ)
አዲሱ አረጋ ቂጤሳ
FB_IMG_1490016477525
================================
እነሆ ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ነዉ…
ቦረና የምሄደዉ የዴሞክራሲ መሰረት የሆነዉን አስደናቂዉን የገዳ ስርዓት ምንነት ለማወቅና ለመመርመር አይደለም፡፡ ቦረና የምሄደዉ ለጉብኝት አይደለም፡፡ የቦረና ኦሮሞን የስነ ክዋክብትና ሌሎች ሀገር በቀል ዕዉቀቶችን ለመቅሰም አይደለም፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ዛሬ የቦረና ላይ ሰማዩ ጨክኗል፡፡ ዝናብ የለም፡፡ ከብቶች የሚግጡት የላቸዉም፡፡ ወተት የለም፡፡ የህጻናት ቡረቃና ፈንጠዝያ የለም፡፡ የብዙ ዕሴቶችና እዉቀቶች ባለቤት የሆነዉን የቦረናን ኦሮሞ ድርቁ ጎድቶታል፡፡ የከብቶቹ መክሳትና የመሞት ስጋት፣ የልጆቹና የቤተሰቦቹ ዕጣ ፈንታ የቦረናን አባ ወራ የኦሮሞነት ኩራቱን ፈተና ዉስጥ ከትቶታል፡፡ ጭንቀት ወጥሮታል፡፡ በነገራችን ላይ በቦረና ኦሮሞ ባህል፣ እጅ ሲያጥር፣ ድርቅ ሲከሰት በእርዳታም የተገኘ ቢሆን አባ ወራ በቅድሚያ የተገኘዉን ሁሉ ህጻናትን ይመግባል፡፡ ቀጥሎም ሴቶችን… ከተረፈ ራሱ ይመገባል፡፡ ካልተረፈ በረሃብ የመጨረሻዋን እስትንፋስ ይተነፍሳታል እንጂ ምንም ቢራብ ከህጻናት ልጆቹ እና ከሴቶች አስቀድሞ አንዲት ጉርሻ እንኳ አይጎርስም፡፡ በረሃብ የመጨረሻዋን እስትንፋስ ተንፍሶ ይሞታታል እንጂ! ይህ የቦረናነት፣ የኦሮሞነት ህግ ነዉ!!
……………………………………………………………………………………………………………………
እነሆ ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ነዉ…
ቦረና በድርቅ ምክንያት ለድርቅ በመጋለጡ፣ የሀረር ፣ የባሌ እና የጉጂ ቆላማ ቦታዎች ለድርቅ ተጋልጠዉ ወገኖቼ ለረሃብ በማጋለጠቸዉ ቅስሜ ተሰብሯል፡፡ ወገኖቼን ድርቅ ከሚያስከትለዉ ረሃብ መታደግ ያልቻልኩ “እኔ እንደ ፖለቲካ አመራር ሚናዬ ምንድ ነዉ?” የሚል ሀሳብ እየሞገተኝ እንቅልፍ ይነሳኛል፡፡ ከዉስጤ የሚሰማኝ ድምጽ “አንተን ብሎ አመራር i፣ አንተን ብሎ ፖለቲከኛ! ኦሮሚያን የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር ዕምቅ የዉሃ ሀብት ተጠቅማችሁ ህዝቡን ከድርቅ ስጋት ማላቀቅ ያልቻላችሁ፣ ወንዝ ዉስጥ ቆማችሁ የምትጠሙ ትዉልዶች!” የሚል ስላቅ በጆሮዬ ሹክ እያለ ያስጨነቀኛል፡፡ እንቅልፍ ይነሳኛል፡፡ የተጠያቂነት መንፈስ ይጠዘጥዘኛል፡፡ በሳርና በዉሃ እጥረት የከሱ ከብቶች፣ የከሱ ህጻናት በአይነ ህሊናዬ እየመጡ ህሊናዬ ዕረፍት ያጣል፡፡ የእልህና የቁጭት ዕንባ በአይኔ ሞልቶ ይፈሳል፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ያለሁት ከአማራ ክልል ከመጡ ጓዶቼ ጋር ነዉ፡፡ ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ያለሁት የአማራ ክልል ህዝብ እና መንግስትን ድጋፍ ይዘዉልን ከመጡት ከወዳጆቼ ንጉሱ ጥላሁን (የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዋና ዳይሬክተር) አቶ አሰፋ በላይ (የአማራ ክልዊ መንግስት አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ)ጋር በመሆን ነዉ፡፡ ከኦሮሚያ ክልል አቶ መኮንን ሌንጂሶ ( የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር) አቶ ወርቁ ጫላ (የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ) አብረዉኝ አሉ፡፡
ዛሬ፣ ሰማዩ በመጨከኑ፣ የኦሮሞ ህዝብ እና የሁላችን ኢትዮጵያዉያን የኩራት ምንጭ ሆነዉን የገዳ ስርዓትን ሳይበረዝ ጠብቀዉ ያኖሩልን የቦረና ኦሮሞዎች የዕለት ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ መሆኑን በሰሙ ጊዜ የአማራ ህዝብ ወንድሞቻችን፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አቅም የፈቀደዉን ድጋፍ ይዘዉ ከኛ ጋር ወደ ቦረና እየተጓዙ ነዉ፡፡
ወንድም ህዝብ የሆነዉ የአማራ ህዝብ፣ የዓላማ አጋራችን የሆነዉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ቆላማ ቦታዎች ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቅ በመከሰቱ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የፌዴራል መንግስት እና የተራድኦ ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን ሰብዓዊ የድጋፍ እንቅስቃሴ ለመደገፍ የልዑካን ቡድኑ ከባህርዳር ተነስቶ የክልሉ ህዝብና መንግስት የለገሱትን ድጋፍ ለምዕራብ ጉጂ እና ለቦረና ዞን የድርቅ ተጠቂዎች ለማድረስ አብረን በጉዞ ላይ እንገኛለን፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
የአማራ ክልል ወንድም ህዝብ እና መንግስት ያበረከቱትን 5000 ኩንታል የድጋፍ እህል በአስራ ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች አስጭነዉ፣ ለተረጂዎች፣ ለሰዎች እና ለእንስሳት ዉሃ መመላሻ ይሆኑ ዘንድ የለገሱት ሁለት የዉሃ ማመላሻ ቦቴዎች ከኛ ቀድመዉ በ9/7/09 አመሻሽ ዲላ ከተማ ደርሰዋል፡፡ እኔ እና ጓደኛዬ ንጉሱ ጥላሁን ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር በመሆን ወደ ቦረና ለምናደርገዉ ጉዞ አዳራችንን ሻሸመኔ አድርገናል፡፡ እራት እየተመገበን ስለሁለቱ ህዝቦች ወዳጅነት እያወጋን እየተጫወትን አመሸን፡፡ የጨዋታችን ጭብጥ የሚከተለዉ ነዉ፡፡
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድርቅ ላጠቃቸዉ አካባቢዎች የአማራ ክልል ህዝብና መንግስት ከ20 በላይ የጤና ባለሙያዎችንና የዉሃ ቦቴዎችን አሰማርቶ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ንጉሱ ጥላሁን አጫዉቶኛል፡፡ የሚመሰገን ተግባር ነዉ!
የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ ትናንትም ሆነ ዛሬ የኢትዮጵያ አንድነት ምሰሶ እንደሆኑ እያነሳን አዉግተናል፡፡ በርግጥ ባለፉት ስርዓቶች የነበሩት ገዢ መደቦች የኦሮሞ እና የአማራ ወንድም ህዝቦችን ግንኙነት ለማዛባት ያልተገቡ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ዛሬም የፖለቲካ አኪቲቪስት ነን ባዮች በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለዉን ወንድማዊ ግንኙነት ለማበላሸት ሌት ተቀን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን የሁለቱ ህዝቦች ወንድማዊ ግንኙነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ከነበሩት ገዢ መደቦችም ሆነ ዛሬ ካሉት የፖለቲካ አክቲቪስቶች ፍላጎት በጣም የተሻገረ እና በፍቅር እና በፍጹም ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ትናንት የነበሩት የገዢ መደቦች በህዝብ ስም በመነገድ ጥቅማቸዉን ለማስከበር ሲሉ የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት ለማዛባት የተቻላቸዉን ጥረት ብያደርጉም አልተሳካላቸዉም፡፡ ዛሬም አንዳንድ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ አኪትቪስት ነን ባዮች ህዝቦችን በማጋጨት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲወተረተሩ ማየት የተለመደ የሰርክ ተግባር ሆኗል፡፡ ሁለቱ ህዝቦች የትናንት የገዢ መደቦች ሆነ የዛሬ ፖለቲከኛ የፖለቲካ አክቲቪስቶችን ነን ባዮች ፍላጎቶችን ወደ ጎን በመተዉ ፍቅራቸዉን አጽንተዋ፡፡ ተጋብተዉ ተዋልዳወል፡፡ አንዱ የሌላዉን ቋንቋ ይናገራል፡፡ በነገራችን ላይ በአማራ ብሄራዊ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር እና በሌሎች አካባቢዎች በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች በሰላምና በፍቅር በአብሮነት ይኖራሉ፡፡ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች (የንጉሱ ጥላሁንንቤተሰቦች ጨምሮ)
በኦሮሚያ ክልል በሰላምና በፍቅር በአብሮነት ይኖራሉ፡ ወንድሜ ንጉሱ ጥላሁን አርሲ ተወልዶ ያደገ በመሆኑ አፋን ኦሮሞን አንደኔዉ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ እኔም በአማርኛ ቋንቋ ክህሎት፣ ሳልስና ሳድስን ኣዛብቶ ከመጠቀም በስተቀር ብዙም አልታማም፡፡ ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ኢትዮጵያ ሀገራችን በባዕድ ሃይሎች ስትወረር ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን በጋራ ዘምተዉ አኩሪ ገድል ፈጽመዋል፡፡ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በተደረጉ ዉጊያዎች ደማቸዉ ተቀላቅሎ በአንድ ላይ ፈሷል፡፡ የመስዋዕትነት አጽማቸዉ በአንድ ጉድጓድ ተቀብሯል፡፡ በከፈሉት መስዋዕትነትም ልዕልናዋ የተጠበቀ በቅኝ ያልተገዛች ኩሩ ሀገርን አስረክበዉናል፡
ወጋችን ቀጥሏል…
እራት እየተመገበን ስለሁለቱ ህዝቦች ወዳጅነት እያወጋን እየተጫወትን ነዉ፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ዛሬም ቢሆን የአማራ እና የኦሮሞ ወንድማማች ህዝቦች አንዲሁም ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች የህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችን ምሶሶና ዋስትና እንደሆኑ እያስተማሩን ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት በህዝብ ፍላጎት ጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ መሆኑን እያሳዩን ነዉ፡፡ ፖለቲከኛ ፈለገ አልፈለገ፣ አፍራሽ የፖለቲካ አክቲቪስት ቀሰቀሰ አልቀሰቀሰ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የአንዱ መጠቃትና መከራ የሌላዉ መጠቃትና መከራ አንደሆነ፤የአንዱ መደሰት የሌላዉ ህዝብ መደሰት እንደሆነ በተግባር እያሳዩን ነዉ፡፡
ለዚህ ነዉ የቦረና ኦሮሞ በድርቅ መራብና መጠማት፣ የአማራዉ ህዝብ እና መንግስት መራብና መጠማት መሆኑ ተሰምቷቸዉ በዚህች ቀዉጢ ቀን ከጎናችን የቆሙት፡፡
ከዉይይታችን አንድ ጨብጥ ላይ ተግባባን፡፡ ባለፉት ስርዓቶች የነበሩት ገዢ መደቦች በሁለቱ ወንድም ህዝቦች ላይ አስከፊ ጭቆና እያደረሱም ቢሆን የሁለቱ ወንድማማቾች ህዝቦች ፍቅር እና አንድነት የገዢ መደቦችን ከፋፋይ ፍላጎት አሸንፎ ዘልቋል፡፡ ዛሬም የፖሊተካ አክቲቪስት ነን ባዮች የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነትና ፍቅር ጥላሸት ለመቀባት ቢጥሩም ህዝቡ ሳይቀበላቸዉ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም የህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችን በማይናወጥ መሰረት ላይ መቆሙን፣ በህዝቦች ወንድማማችነትና አብሮ የመኖር ፍላጎት ጽኑ መሰረት ላይ መቆሙን ተግባባን፡፡ ከዚህ በኋላ ማንኛዉም ፖለቲከኛ ሆነ አክቲቪሰት ነኝ ባይ የፈለገዉን ቢመኝ፣ የፖለቲካ አክቲቪስት በፈለገዉ መንገድ ቢቀሰቀስ፣ የህብረብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችን በህዝቦች በፍቅር፣ በእኩልነት በወንድማማችነት እና በዴሞክራሲያዊ አንድነት ጽኑ መሰረት መቆሙ ላይ ተግባባን!!
……………………………………………………………………………………………………………………
በቀዉጢ ቀን የደገፉንን ወንድም የአማራ ወንድም ህዝብ እና መንግስትን እጅግ አድርገን እናመግናለን፡፡ መቼም ቢሆን አንረሳቸሁምም!! የችግር ቀን ባለዉለታችን ናችሁና!!
……………………………………………………………………………………………………………………
ከወንድሜ ከንጉሱ ጥላሁን አና ከባልደረቦቹ ጋር በኦሮሚያ ክልል በተለይ በቦረና ይህ ቀን አልፎ አንደገና ብንገናኝ ደስ ይለኛል፡፡ ሆኖም ንጉሱ የድጋፍ እህልና የዉሃ ማጓጓዣ ቦቴዎችን ይዞልን አንዲመጣ አልመኝም፡፡ እኔ አስጎብኚ ሆኜ የኦሮሞ ባህል የሆነዉ እና በየስምንት አመቱ ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ርክክብ የሚደረግበት፣ በዓለም ወካይ ቅርስነት የተመዘገበዉን የገዳ ስርዓትን ባስጎበኘዉ፣አሊያም የቦረና የዉሃ ኔትዎርክ ፕሮጀክት ተጠናቆ ወገኖቼ ድርቅ ከሚያስከትለዉ ስጋት ተላቀዉ ቀየአቸዉ ጥጋብና አማን ሆኖ ባስጎበኘዉ ምኞቴ ነዉ፡፡ ዛሬ በድርቁ ምክንያት ከስተዉ ሞት አፋፍ ላይ የሚገኙት የቦረና ከብቶች አገግመዉ የቦረና ከብት ዝርያ ኮርማ ብሸልመዉ ደስ ይለኛል፡፡
እንዲሁም ከወንድሜ ከንጉሱ ጥላሁን አና ከባልደረቦቹ ጋር በአማራ ክልል በሌላ ፕሮግራም ብንገናኝ ደስ ይለኛል፡፡ የአማራ ክልል ወንድም ህዝብ ከችግር ተላቆና በልጽጎ፣ ህዝቡ ከችግር የተላቀቀበትን ሚስጥር ንጉሱ ጥላሁን አስጎብኚ ሆኖ በአማርኛና አፋን ኦሮሞን በመጠቀም መግለጫ እየሰጠ ቢያስጎበኘኝ ምኞቴ ነዉ፡፡
በመጨረሻም በግሌ አንድ ነገር ተገነዘብኩ፡፡ ስርዓቶች ይመጣሉ ያልፋሉ፡፡ በመከራም ሆነ በመልካሙ ጊዜ ግን የህዝቦች ፍቅር እና ወንድማማችነት ለዘመናት ይዘልቃል፡፡
የኦሮሞ እና አማራ ህዝቦች ፍቅርና ወንድማማችነት ለዘለዓለም ይኑር!
ቸር እንሰንብት!!

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት (የጉዞ ማስታወሻ) አዲሱ አረጋ ቂጤሳ source mereja.com

የአማራ እና የኦሮሞ ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ወዳጅነት (የጉዞ ማስታወሻ)
አዲሱ አረጋ ቂጤሳ
FB_IMG_1490016477525
================================
እነሆ ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ነዉ…
ቦረና የምሄደዉ የዴሞክራሲ መሰረት የሆነዉን አስደናቂዉን የገዳ ስርዓት ምንነት ለማወቅና ለመመርመር አይደለም፡፡ ቦረና የምሄደዉ ለጉብኝት አይደለም፡፡ የቦረና ኦሮሞን የስነ ክዋክብትና ሌሎች ሀገር በቀል ዕዉቀቶችን ለመቅሰም አይደለም፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ዛሬ የቦረና ላይ ሰማዩ ጨክኗል፡፡ ዝናብ የለም፡፡ ከብቶች የሚግጡት የላቸዉም፡፡ ወተት የለም፡፡ የህጻናት ቡረቃና ፈንጠዝያ የለም፡፡ የብዙ ዕሴቶችና እዉቀቶች ባለቤት የሆነዉን የቦረናን ኦሮሞ ድርቁ ጎድቶታል፡፡ የከብቶቹ መክሳትና የመሞት ስጋት፣ የልጆቹና የቤተሰቦቹ ዕጣ ፈንታ የቦረናን አባ ወራ የኦሮሞነት ኩራቱን ፈተና ዉስጥ ከትቶታል፡፡ ጭንቀት ወጥሮታል፡፡ በነገራችን ላይ በቦረና ኦሮሞ ባህል፣ እጅ ሲያጥር፣ ድርቅ ሲከሰት በእርዳታም የተገኘ ቢሆን አባ ወራ በቅድሚያ የተገኘዉን ሁሉ ህጻናትን ይመግባል፡፡ ቀጥሎም ሴቶችን… ከተረፈ ራሱ ይመገባል፡፡ ካልተረፈ በረሃብ የመጨረሻዋን እስትንፋስ ይተነፍሳታል እንጂ ምንም ቢራብ ከህጻናት ልጆቹ እና ከሴቶች አስቀድሞ አንዲት ጉርሻ እንኳ አይጎርስም፡፡ በረሃብ የመጨረሻዋን እስትንፋስ ተንፍሶ ይሞታታል እንጂ! ይህ የቦረናነት፣ የኦሮሞነት ህግ ነዉ!!
……………………………………………………………………………………………………………………
እነሆ ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ነዉ…
ቦረና በድርቅ ምክንያት ለድርቅ በመጋለጡ፣ የሀረር ፣ የባሌ እና የጉጂ ቆላማ ቦታዎች ለድርቅ ተጋልጠዉ ወገኖቼ ለረሃብ በማጋለጠቸዉ ቅስሜ ተሰብሯል፡፡ ወገኖቼን ድርቅ ከሚያስከትለዉ ረሃብ መታደግ ያልቻልኩ “እኔ እንደ ፖለቲካ አመራር ሚናዬ ምንድ ነዉ?” የሚል ሀሳብ እየሞገተኝ እንቅልፍ ይነሳኛል፡፡ ከዉስጤ የሚሰማኝ ድምጽ “አንተን ብሎ አመራር i፣ አንተን ብሎ ፖለቲከኛ! ኦሮሚያን የከርሰ ምድር እና የገጸ ምድር ዕምቅ የዉሃ ሀብት ተጠቅማችሁ ህዝቡን ከድርቅ ስጋት ማላቀቅ ያልቻላችሁ፣ ወንዝ ዉስጥ ቆማችሁ የምትጠሙ ትዉልዶች!” የሚል ስላቅ በጆሮዬ ሹክ እያለ ያስጨነቀኛል፡፡ እንቅልፍ ይነሳኛል፡፡ የተጠያቂነት መንፈስ ይጠዘጥዘኛል፡፡ በሳርና በዉሃ እጥረት የከሱ ከብቶች፣ የከሱ ህጻናት በአይነ ህሊናዬ እየመጡ ህሊናዬ ዕረፍት ያጣል፡፡ የእልህና የቁጭት ዕንባ በአይኔ ሞልቶ ይፈሳል፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ያለሁት ከአማራ ክልል ከመጡ ጓዶቼ ጋር ነዉ፡፡ ወደ ቦረና እየተጓዝኩ ያለሁት የአማራ ክልል ህዝብ እና መንግስትን ድጋፍ ይዘዉልን ከመጡት ከወዳጆቼ ንጉሱ ጥላሁን (የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ዋና ዳይሬክተር) አቶ አሰፋ በላይ (የአማራ ክልዊ መንግስት አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና መስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ)ጋር በመሆን ነዉ፡፡ ከኦሮሚያ ክልል አቶ መኮንን ሌንጂሶ ( የክልሉ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽነር) አቶ ወርቁ ጫላ (የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ ምክትል ሃላፊ) አብረዉኝ አሉ፡፡
ዛሬ፣ ሰማዩ በመጨከኑ፣ የኦሮሞ ህዝብ እና የሁላችን ኢትዮጵያዉያን የኩራት ምንጭ ሆነዉን የገዳ ስርዓትን ሳይበረዝ ጠብቀዉ ያኖሩልን የቦረና ኦሮሞዎች የዕለት ዕርዳታ የሚያስፈልጋቸዉ መሆኑን በሰሙ ጊዜ የአማራ ህዝብ ወንድሞቻችን፣ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት አቅም የፈቀደዉን ድጋፍ ይዘዉ ከኛ ጋር ወደ ቦረና እየተጓዙ ነዉ፡፡
ወንድም ህዝብ የሆነዉ የአማራ ህዝብ፣ የዓላማ አጋራችን የሆነዉ የአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በኦሮሚያ ክልል ቆላማ ቦታዎች ዝናብ ባለመዝነቡ ድርቅ በመከሰቱ በሰዎች እና በእንስሳት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት፣ የፌዴራል መንግስት እና የተራድኦ ድርጅቶች እያደረጉ ያሉትን ሰብዓዊ የድጋፍ እንቅስቃሴ ለመደገፍ የልዑካን ቡድኑ ከባህርዳር ተነስቶ የክልሉ ህዝብና መንግስት የለገሱትን ድጋፍ ለምዕራብ ጉጂ እና ለቦረና ዞን የድርቅ ተጠቂዎች ለማድረስ አብረን በጉዞ ላይ እንገኛለን፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
የአማራ ክልል ወንድም ህዝብ እና መንግስት ያበረከቱትን 5000 ኩንታል የድጋፍ እህል በአስራ ሁለት የጭነት ተሽከርካሪዎች አስጭነዉ፣ ለተረጂዎች፣ ለሰዎች እና ለእንስሳት ዉሃ መመላሻ ይሆኑ ዘንድ የለገሱት ሁለት የዉሃ ማመላሻ ቦቴዎች ከኛ ቀድመዉ በ9/7/09 አመሻሽ ዲላ ከተማ ደርሰዋል፡፡ እኔ እና ጓደኛዬ ንጉሱ ጥላሁን ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር በመሆን ወደ ቦረና ለምናደርገዉ ጉዞ አዳራችንን ሻሸመኔ አድርገናል፡፡ እራት እየተመገበን ስለሁለቱ ህዝቦች ወዳጅነት እያወጋን እየተጫወትን አመሸን፡፡ የጨዋታችን ጭብጥ የሚከተለዉ ነዉ፡፡
ሰሞኑን በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ድርቅ ላጠቃቸዉ አካባቢዎች የአማራ ክልል ህዝብና መንግስት ከ20 በላይ የጤና ባለሙያዎችንና የዉሃ ቦቴዎችን አሰማርቶ እገዛ እያደረጉ መሆኑን ንጉሱ ጥላሁን አጫዉቶኛል፡፡ የሚመሰገን ተግባር ነዉ!
የኦሮሞ እና የአማራ ህዝብ ትናንትም ሆነ ዛሬ የኢትዮጵያ አንድነት ምሰሶ እንደሆኑ እያነሳን አዉግተናል፡፡ በርግጥ ባለፉት ስርዓቶች የነበሩት ገዢ መደቦች የኦሮሞ እና የአማራ ወንድም ህዝቦችን ግንኙነት ለማዛባት ያልተገቡ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡ ዛሬም የፖለቲካ አኪቲቪስት ነን ባዮች በሁለቱ ህዝቦች መካከል ያለዉን ወንድማዊ ግንኙነት ለማበላሸት ሌት ተቀን እየተፍጨረጨሩ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን የሁለቱ ህዝቦች ወንድማዊ ግንኙነት ትናንትም ሆነ ዛሬ ከነበሩት ገዢ መደቦችም ሆነ ዛሬ ካሉት የፖለቲካ አክቲቪስቶች ፍላጎት በጣም የተሻገረ እና በፍቅር እና በፍጹም ወንድማማችነት ላይ የተመሰረተ ነዉ፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ትናንት የነበሩት የገዢ መደቦች በህዝብ ስም በመነገድ ጥቅማቸዉን ለማስከበር ሲሉ የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት ለማዛባት የተቻላቸዉን ጥረት ብያደርጉም አልተሳካላቸዉም፡፡ ዛሬም አንዳንድ ፖለቲከኞች እና የፖለቲካ አኪትቪስት ነን ባዮች ህዝቦችን በማጋጨት የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ሲወተረተሩ ማየት የተለመደ የሰርክ ተግባር ሆኗል፡፡ ሁለቱ ህዝቦች የትናንት የገዢ መደቦች ሆነ የዛሬ ፖለቲከኛ የፖለቲካ አክቲቪስቶችን ነን ባዮች ፍላጎቶችን ወደ ጎን በመተዉ ፍቅራቸዉን አጽንተዋ፡፡ ተጋብተዉ ተዋልዳወል፡፡ አንዱ የሌላዉን ቋንቋ ይናገራል፡፡ በነገራችን ላይ በአማራ ብሄራዊ ክልል በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር እና በሌሎች አካባቢዎች በርካታ የኦሮሞ ተወላጆች በሰላምና በፍቅር በአብሮነት ይኖራሉ፡፡ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የአማራ ተወላጆች (የንጉሱ ጥላሁንንቤተሰቦች ጨምሮ)
በኦሮሚያ ክልል በሰላምና በፍቅር በአብሮነት ይኖራሉ፡ ወንድሜ ንጉሱ ጥላሁን አርሲ ተወልዶ ያደገ በመሆኑ አፋን ኦሮሞን አንደኔዉ አቀላጥፎ ይናገራል፡፡ እኔም በአማርኛ ቋንቋ ክህሎት፣ ሳልስና ሳድስን ኣዛብቶ ከመጠቀም በስተቀር ብዙም አልታማም፡፡ ሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች ኢትዮጵያ ሀገራችን በባዕድ ሃይሎች ስትወረር ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔረር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ጋር በመሆን በጋራ ዘምተዉ አኩሪ ገድል ፈጽመዋል፡፡ የሀገርን ሉዓላዊነት ለማስከበር በተደረጉ ዉጊያዎች ደማቸዉ ተቀላቅሎ በአንድ ላይ ፈሷል፡፡ የመስዋዕትነት አጽማቸዉ በአንድ ጉድጓድ ተቀብሯል፡፡ በከፈሉት መስዋዕትነትም ልዕልናዋ የተጠበቀ በቅኝ ያልተገዛች ኩሩ ሀገርን አስረክበዉናል፡
ወጋችን ቀጥሏል…
እራት እየተመገበን ስለሁለቱ ህዝቦች ወዳጅነት እያወጋን እየተጫወትን ነዉ፡፡
……………………………………………………………………………………………………………………
ዛሬም ቢሆን የአማራ እና የኦሮሞ ወንድማማች ህዝቦች አንዲሁም ሌሎች የሀገራችን ብሔር ብሔረሰቦች የህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችን ምሶሶና ዋስትና እንደሆኑ እያስተማሩን ይገኛሉ፡፡ የኢትዮጵያ አንድነት በህዝብ ፍላጎት ጠንካራ መሰረት ላይ የቆመ መሆኑን እያሳዩን ነዉ፡፡ ፖለቲከኛ ፈለገ አልፈለገ፣ አፍራሽ የፖለቲካ አክቲቪስት ቀሰቀሰ አልቀሰቀሰ የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦች እና ህዝቦች የአንዱ መጠቃትና መከራ የሌላዉ መጠቃትና መከራ አንደሆነ፤የአንዱ መደሰት የሌላዉ ህዝብ መደሰት እንደሆነ በተግባር እያሳዩን ነዉ፡፡
ለዚህ ነዉ የቦረና ኦሮሞ በድርቅ መራብና መጠማት፣ የአማራዉ ህዝብ እና መንግስት መራብና መጠማት መሆኑ ተሰምቷቸዉ በዚህች ቀዉጢ ቀን ከጎናችን የቆሙት፡፡
ከዉይይታችን አንድ ጨብጥ ላይ ተግባባን፡፡ ባለፉት ስርዓቶች የነበሩት ገዢ መደቦች በሁለቱ ወንድም ህዝቦች ላይ አስከፊ ጭቆና እያደረሱም ቢሆን የሁለቱ ወንድማማቾች ህዝቦች ፍቅር እና አንድነት የገዢ መደቦችን ከፋፋይ ፍላጎት አሸንፎ ዘልቋል፡፡ ዛሬም የፖሊተካ አክቲቪስት ነን ባዮች የሁለቱን ወንድማማች ህዝቦች ግንኙነትና ፍቅር ጥላሸት ለመቀባት ቢጥሩም ህዝቡ ሳይቀበላቸዉ ቀርቷል፡፡ በመሆኑም የህብረ ብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችን በማይናወጥ መሰረት ላይ መቆሙን፣ በህዝቦች ወንድማማችነትና አብሮ የመኖር ፍላጎት ጽኑ መሰረት ላይ መቆሙን ተግባባን፡፡ ከዚህ በኋላ ማንኛዉም ፖለቲከኛ ሆነ አክቲቪሰት ነኝ ባይ የፈለገዉን ቢመኝ፣ የፖለቲካ አክቲቪስት በፈለገዉ መንገድ ቢቀሰቀስ፣ የህብረብሄራዊ ፌዴራላዊ ስርዓታችን በህዝቦች በፍቅር፣ በእኩልነት በወንድማማችነት እና በዴሞክራሲያዊ አንድነት ጽኑ መሰረት መቆሙ ላይ ተግባባን!!
……………………………………………………………………………………………………………………
በቀዉጢ ቀን የደገፉንን ወንድም የአማራ ወንድም ህዝብ እና መንግስትን እጅግ አድርገን እናመግናለን፡፡ መቼም ቢሆን አንረሳቸሁምም!! የችግር ቀን ባለዉለታችን ናችሁና!!
……………………………………………………………………………………………………………………
ከወንድሜ ከንጉሱ ጥላሁን አና ከባልደረቦቹ ጋር በኦሮሚያ ክልል በተለይ በቦረና ይህ ቀን አልፎ አንደገና ብንገናኝ ደስ ይለኛል፡፡ ሆኖም ንጉሱ የድጋፍ እህልና የዉሃ ማጓጓዣ ቦቴዎችን ይዞልን አንዲመጣ አልመኝም፡፡ እኔ አስጎብኚ ሆኜ የኦሮሞ ባህል የሆነዉ እና በየስምንት አመቱ ዴሞክራሲያዊ የስልጣን ርክክብ የሚደረግበት፣ በዓለም ወካይ ቅርስነት የተመዘገበዉን የገዳ ስርዓትን ባስጎበኘዉ፣አሊያም የቦረና የዉሃ ኔትዎርክ ፕሮጀክት ተጠናቆ ወገኖቼ ድርቅ ከሚያስከትለዉ ስጋት ተላቀዉ ቀየአቸዉ ጥጋብና አማን ሆኖ ባስጎበኘዉ ምኞቴ ነዉ፡፡ ዛሬ በድርቁ ምክንያት ከስተዉ ሞት አፋፍ ላይ የሚገኙት የቦረና ከብቶች አገግመዉ የቦረና ከብት ዝርያ ኮርማ ብሸልመዉ ደስ ይለኛል፡፡
እንዲሁም ከወንድሜ ከንጉሱ ጥላሁን አና ከባልደረቦቹ ጋር በአማራ ክልል በሌላ ፕሮግራም ብንገናኝ ደስ ይለኛል፡፡ የአማራ ክልል ወንድም ህዝብ ከችግር ተላቆና በልጽጎ፣ ህዝቡ ከችግር የተላቀቀበትን ሚስጥር ንጉሱ ጥላሁን አስጎብኚ ሆኖ በአማርኛና አፋን ኦሮሞን በመጠቀም መግለጫ እየሰጠ ቢያስጎበኘኝ ምኞቴ ነዉ፡፡
በመጨረሻም በግሌ አንድ ነገር ተገነዘብኩ፡፡ ስርዓቶች ይመጣሉ ያልፋሉ፡፡ በመከራም ሆነ በመልካሙ ጊዜ ግን የህዝቦች ፍቅር እና ወንድማማችነት ለዘመናት ይዘልቃል፡፡
የኦሮሞ እና አማራ ህዝቦች ፍቅርና ወንድማማችነት ለዘለዓለም ይኑር!
ቸር እንሰንብት!!

Netsanet Le Ethiopia Radio Interview With Professor Ezekiel Gebissa 

Netsanet Le Ethiopia Radio Interview With Professor Ezekiel Gebissa 






Netsanet Le Ethiopia Radio Interview With Professor Ezekiel Gebissa

Friday, March 17, 2017

አምባጊዮርጊስ ላይ ጥቃት ማን ፈፀመ? – አስናቀው አበበ source ሳተናው

 28
ከቦታው በጥንቃቄ ጊዜ ወስደን እንዳጣራነው ጎንደር/ወገራ አውራጃ በአምባጊዮርጊስ ከተማ የፖሊስ ጣቢያ ላይ እሮብ እለት ድንገተኛ ተኩስ ከፍተው የነበሩት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ተወርዋሪ ሃይል መሆኑን ለመረዳት ችለናል። ይህ ነው የሚባል ጉዳት መድረሱን ማረጋገጥ ባይቻልም ከሰሞኑ የጎንደር ሆስፒታል በተጎዱ ወታደሮች መጨናነቁን መዘገባችን ይታወቃል።
በሁኔታው የወያኔ ተላላኪ የአካባቢው ባለስልጣናት ክፉኛ መደናገጣቸው ታውቋል። እየተደናበረ ያለው ወያኔ የጎንደር ከተማ ፖሊስ መምሪያ ም/ኮሚሸነርን እና የመምሪያዉ ም/ሀላፊን በተመሳሳይ ወቅት ይዞ ማሰራቸውን መረጃወች ይጠቁማሉ።
አምባጊዮርጊስ ከጎንደር ወደ 40 ኪ.ሜ. ገደማ የምትርቅ ከተማ ስትሆን ወያኔ በቅርብ ጊዜ በጅምላ ህዝብ የፈጀባት ቦታ ናት። አካባቢውን መሰረት ያደረገው የከፋኝ ሃይል ተደጋጋሚ ጀብዱና ድል የፈፀመባት የእንቃሽ አካባቢ መገኛ ናት።
ድል የህዝብ ነው©!

ህዝባችን የሚሻው መሰረታዊ ለውጥን እንጂ ቀጣይ ወታደራዊ አገዛዝንና ባዶ ተስፋን  አይደለም – ሽንጎ source zhabesha

ሕወሀት/ ኢህአዴግ እንደተሽመደመደና መግዛት አንዳቃተው በተዘዋዋሪ አመነ።፤ይህ ሁኔታ ሰፊ የህዝብ መነሳሳትን ይቀስቅሳል ብሎ የፈራው ሕወሀት/ኢህአዴግ ከስድስት ወራት በፊት የጀመረውን ወታደራዊ አገዛዝ በመላ ኢትዮጵያ ይቀጥላል ሲል በጠቅላይ  ሚኒስቴር ሐይለማርም ደሳለኝ በኩል  በዛሬው እለት ለ”ፓርላማ” በቀረበው  ሪፖርት አረጋግጧል። አስቂኝ የሆነው ይህ ንግግር፣ 82% የኢትዮጵያ ህዝብ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲቀጥል ይፈልጋል ይላል። በአማራና ኦሮሚያ ክልል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን (65% ኢትዮጵያውያን) ስርአቱን ሙሉ በሙሉ እየተቃወሙት እንደሆነ እየታወቀ 82%  ድጋፍ ከየት እንደሚመጣ የህወሀት/አህአዴግ በለስልጣኖች ብቻ ናቸው የሚያውቁት፡፡ እነርሱ የኢትዮጵያ ህዝብ የሚሉት የህወሀት/ ኢህአዴግን አባላት ብቻ ከሆነ ሌላ ነገር ነው።
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ንግግራቸው በተለይ ኢኮኖሚውንና እድገትን በተመለከተ  እጅግ የተምታታና መጨበጫም የሌለው ነው፣ ባንድ  በኩል የኢትዮጵያን  ህዝብ ተጨባጭነት የሌለው “እናድጋለን” የሚል ባዶ  ተስፋ ሊመግቡ የሞከሩ ሲሆን  በሌላ በኩል ግን በተጨባጭ የእርሻ ምርት እንደቀነሰ፣ የውጭ ንግድ ገቢ ለሶስት ተከታታይ አመታት እንዳሽቆለቆለ፣ የዋጋ ግሽበት እንዳሻቀበ ከውጭ የሚገኝ እርዳታ እንደወደቀ፣የግብርና ምርት ኤክስፖርት እንደደቀቀ ፤ ድርቅ በየቦታው እንደተስፋፋ፣የሀገሪቱ እዳ እየጨመረ እንደሆነ ስርአቱ ከ26 አመት ስልጣን በሓላ ሀገሪቱን በምግብ ራሷን ማስቻል እንዳልቻለ አምነዋል። ባጠቃላይ ሚዛን ሲታይ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ስርአቱን እድገት ሳይሆን ውድቀት አሽመድምዶ እንደያዘው አምነዋል።
የፖለቲካ ድርድርን በሚመለከት የተናገሩትም እንዲሁ እጅግ አሳዛኝ ፤ ሀገራዊ ሀላፊነት የጎደለው  ነው፡ “ማንም አስገድዶን አይደለም ለድርድር የቀረብነው” “ተጽእኖ ሲደረግብን በፍጹም ፍንክች አንልም” በማለት በግልጽ ቋንቋ ይህ መንግስት እጅግ ችክ ያለ ደረቅ አንደሆነ፣ እና ከሁኔታወች ጋር መጓዝ እንደማይችል፣ ለእውነተኛ ለውጥ የተዘጋጀ እንዳልሆነ ሰጥቶ መቀበልን ሳይሆን በራሱ መስመር ብቻ መጓዝን እንደሚገፋ አረጋግጠዋል። የተጀመረው ድርድር እሩቅ እደማይሄድም የጥርጣሬ ጥላ አጥልተውበታል። ይህ ታዲያ ሀላፊነት የጎደለው ለፍጥጫና ለቀጣይ ግጭት የሚጋብዝ እንጂ ለሰላም በር ከፋች አይደለም፡፡
ያው እንደተለመደው አሁንም ፖለቲካዊ ተቃውሞን በወታደራዊ ሀይል ለመጨፍለቅ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን እንደሚያራዝሙ ከመግለጽ ውጭ፤ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ በዚህ ንግግራቸው በሀገራችን የተከሰቱትን ዋና ዋና የፖለቲካ ግጭቶች  ለመቅረፍ ምን እንደሚያደርጉ ያቀረቡት ምንም ተጨባጭ የፖለቲካ መፍትሄ የለም።
በራሳቸው ጭንቅ የተወጠሩት ጥቅላይ ሚኒስቴሩና  ንግግራቸው ሁሉ ያተኮረው በድርኢጅታቸው የውስጥ ፡ተሀድሶ” ላይ ነው። ይህ አይነቱ ንግግር ለፓርቲያቸው የውስጥ ስበሰባ እንጂ ለህዝብ የሚቀርብ አይደለም፣፡ ምክንያቱም  ከ 26 አመት ስልጣን በሓላ የኢትዮጵያ ህዝብ ስለ ህወሀት/ኢህአዴግ መታደስ ቅንጣት ያክል ስሜት የለውም። የሚፈልገው ግፈኛውንና ከፋፋዩን የኢህአዴግ /ህወሀትን ስርአት በማስወገድ የስርአት ለውጥን እውን ማድረግ  ነውና።
ባጠቃላይ ሙሉውን ንግግር አንገታቸውን ደፍተው የፈጸሙት  ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ከቃላት ይልቅ በድምጻቸውና  በሰውነታቸው ሁኔታ  (ቦዲ ላንጉጅ) ምን ያክል የተጨነቁና ተስፋም የቆረጡ  አንደሆነ ግልጽ አድርገዋል።
እጅግ ገላጭ የሆነው ሌላው ጉዳይ ደግሞ ተሰባሳቢዎቹ “የፓርላማ ተወካዮች”  ግማሾቹ ሲያንቀላፉ የታዩ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ “ምን ማለቱ ነው” የሚል በሚመስል ሁኔታ እርስ በርስ ሲንሾካሾኩ ተስተውሏል።
ከዚህ ውጭ ግን የሚገርመው በሙሉ ንግግሩ መሀል የተለመደው ረጂም ተከታታይ ጭብጨባ እንኳ አለመደመጡ ጠቅላላ ታዳሚዎቹ ምን ያክል በጭንቅ ላይ እንደሆኑ አሳብቆባቸዋል።
አዎ ስርአቱ የሚገኝበት ሁኔታ በውነትም የሚያሰጨንቅ ነው። የእርሻ ምርት  ከወደቀ፣ ኑሮ ውድነት ከጨመረ፣ የውጭ ምንዛሬ ማግኘት ካልተቻለ፣ የውጭ እርዳታ ከቀነሰ፣ ድርቅ ከተስፋፋ ፣ ኮንትሮባንድ ንግድ ሀገሪቱን ካጥለቀለቀ፤ ምርታቸውን የሚገዛ እየቀነሰ ከሄደ   የፖለቲካ ግጭቱ ከቀጠለ ህዝቡ ስቃዩ ይጨምራል ማለት  ነው፤ ህዝብ ይራባል  ማለት ነው ። ህዝብ የመብት ማጣቱ ይጨምራል ማለት ነው። ታዲያ ባለፈው አመት በኢትዮጵያ እንዲሁም  ከጥቂት አመታት በፊት  በግብጽ ሊቢያና የመን እንዳየነው፤ የተከፋ ህዝብ፣ የተራበ ህዝብ መሪዎቹን ይበላል። ይህ ማንም የማይገታው የተፈጥሮ ህግ ነው።
እኛ የምንለው  መፍትሄው መቆዘምና መጨነቅ ወይም እውነታውን መካድ፣ በጨለማ ውስጥ መደናበርና  ባዶ ተስፋ ለመመገብ መሞከር ሳይሆን ሀገራችንንና ህዝባችንን ገደል እየጨመረ ያለውን የህወሀት/ኢህአዴግ ፖሊሲ አሽቀንጥሮ መጣል ነው። በሙሉ ቅንነት ለሁሉም የሚጠቅመውን ሁሉን አቀፍ የሆነ ብሄራዊ መግባባት እና ብሄራዊ እርቅን ተግባራዊ አሁኑኑ ማድረግ ነው።
ለዚህም
  • በተለያየ ሰበብ አስባብ  ለእስር የተዳረጉትን የፖለቲካ እስረኞች ሁሉ በተለይም ደግሞ አንደ አንዱአለም አራጌ፣ በቀለ ገርባ፤ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲናና ኮሎኔል ደመቀን የመሳሰሉ የፖለቲካ መሪዎች፣ እንደ እስክንድር ነጋና ተመስገን ደሳለኝ፣ የመሳሰሉት ጋዜጠኞች  ወዘተ አሁኑኑ እንዲፈቱ  ማድረግ እጅግ አስፈላጊ ይሆናል። ባጠቃላይ የህሊናና የፖለቲካ እሥረኞች ሁሉ አላንዳች ቅድመ ሁኔታ  ከእሥር ነጻ ሊሆኑ ይገባል።
  • መሰረታዊ የሆኑ የዴሞክራሲ መታፈንን፣ የሰብአዊ መብት መገፈፍን፣ የህግ የበላይነት መጥፋትን የመሰሉት ጉዳዮች በግልጽ ውይይት ተደርጎባቸው እነዚህን እውነታዎች ለ26 አመታት ያስቀጠለው ሁኔታ የሚወገድበትን መንገድ በጋራ መሻት የግድ ይላል፡። በግፍ የተጎዱ ሁሉ ሊካሱ የሚችሉበትን ሁኔታም ማመቻቸት ተገቢ ነው።
  • መሰረታዊ መብትን የሚገድቡና የሚጥሱ ህግጋቶችን ለምሳሌ የሲሺክ ማህበራትን፣ የፖለቲካና  የመብት ታጋይ ድርጅቶችን እንዲሁም መስል  እንቅስቃሴዎችን የሚያኮላሸውን ህግ፣ የጸረ ሽብርተኝነት ህግ፤ የሚዲያ ሕግ ወዘተ መሰረዝ አስፈላጊ ነው። ህገ መንግስቱም የሀገራችንን ህዝብ ፍላጎት በሚያንጸባርቅ መልኩ የሚሻሻልበትን ሁኔታ መመርመርና መተግበር ይኖርበታል።
  • በቅርቡ በአማራ በኦሮሞና ሌሎችም ክልሎች የተነሱትን የብዙ ወገኖቻችን ህይወት የተገበረባቸው መሰረታዊ የህዝብ ጥያቄዎች በጥሞናና በሀገራዊ ሀላፊነት መመርመር መወያየትና መፍትሄ መፈለግን የግድ ይላል፡ በነዚህ አካባቢዎች የሚካሄደውን ወታደራዊ ዘመቻም ባሰቸኳይ መስቆም የግድ ነው፡
  • በህዝባችን ላይ የተጫነውን የጭንቅ ቀንበር ማስወገድ አስፈላጊ ነው። ለዚህም በመላ ሀገሪቱ የታወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ኮማንድ ፖስት ባሰቸኳይ ማንሳት ያስፈልጋል። ማንም ኢትዮጵያዊ  አሁንም ከየሰፈሩ እየተጎተተ የማይታሰር በወታደርና ደህንነት ሰራተኞች የማይደበደብ፣ እንደፈለጉ የማያስሩት እንደሚሆን ከቃላት ባለፈ በተጨባጭ ማሳየት አስፈላጊም አጣዳፊም ሆኖ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር መሆን አለበት።
  • በሀገሪቱ መሰረታዊ የፍትህ ሥርአት፣ የምርጫ ቦርድ፣ የምርጫ ሂደት፣ የሰራዊት እዝ፤ የደህንነት ቢሮ፤ ወዘተ ከፖለቲካዊ ወገንተኝነትና የፓርቲ ተቀጽላነት ወጥተው መላ ህዝብን ሊያገለግሉ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ማካሄድና መሰረታዊ የእርምት እርምጃም መወሰድ ይኖርበታል።
  • የጋራ ችግሮቻችንን ከስር መሰረቱ ለመፍታትና ብሄራዊ መግባባትና እርቅ ውጤታማ እንዲሆን ከተፈለገ፣ አግላይነትን አስወግዶ በሀገር ጉዳይ ያገባኛል የሚሉ ሁሉ የሚሳተፉበት ሂደትን ተግባራዊ ማድረግ የግድ ይላል። ብሄራዊ መግባባትና እርቅ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ፣ ስብስብ ወይም ድርጅት የፈለገውን ወስኖ በሌላው ላይ የሚጭነው ወይም “ከፈለጋችሁ ተቀበሉ ካልፈለጋችሁ ተውት “ የሚባል ሳይሆን፣ ሁሉም ወገን የሂደቱም ሆነ የውጤቱ ባለቤት ሊሆኑ የሚችሉበት መሆን ይኖርበታል። ያሁኑ አካሄድም ገና ከጅምሩ ሁሉንም ባለድርሻዎች ያሳተፈ እንዲሆን ማድረግ ያስፈልጋል።
ሽንጎ ደግሞ ደጋግሞ እንደገለጸው ፍላጎታችን በሀገራችን ውስጥ ህገ መንግስታዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ እንዲሁም አንድነት፣ እኩልነት፣ የህግ የበላይነትና ዴሞክራሲያዊ መብትን ተግባራዊ ማድረግ ሲሆን፣ ይህን በማድረግም የአመጽ፣ የጦርነት፣ የአሳሪና ታሳሪ አዙሪት፣ ቂም በቀልና ቁርሾ  እንዲያከትም ማድረግ ነው።
በ26 አመት ተሞክሮ እንደማይሰራ የተረጋጋጠን አካሄድ ለማስቀጠል መሞከር ትርፉ ይበልጥ ግጭትንና ሁከትን መጋበዝ ብቻ ነው።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

Thursday, March 16, 2017

ውክልናቸውን በግላቸው ያፀደቁ የብሄር ፖለቲከኞች – ዳንኤል ሃይሌ

ሁሉም ሊባል በሚችል መልኩ በብሄር ተደራጂተናል የሚሉት ድርጅቶች ገና ከስልጣን ደጃፍ ሳይደርሱ ድፍረታቸው እና ንቀታቸው ማንነታቸውን ፍንትው አርጎ እያሳየነው።
ዛሬ ማውራት የምፈልገው እኔ ስለወጣሁበት አማራ ነው የሌሎቹን በይደር እንያዘው። የአማራን ህዝብ መደራጀት ከቶ ማንም የሚቃወም ይኖራል ብዬ አላስብም ምክንያቱም ስለዲሞክራሲ የምናልም ከሆነ ሰዎች በምንም ይሁን በምንም የመደራጀት መብታቸውን ልናከብር ይገባል እንዲሁም እነሱም የሌላውን የማክበር ግዴታ አለባቸው ብለን እናምናለን። ፍትህ እና ዲሞክራሲ በጠፍባት ሀገር ዜጎች በማንኛውም መልኩ የመደራጀትና ሀሳባቸውን በነፃነት ገልፀው መኖር በማይቻልበት ሁኔታ ውስጥ ሆነን እኮ በምን ስሌት ነው እኔ የዚህ ቢሄር ተወካይ ነኝ ወይም በግልፅ ቋንቋ “እኔ የአማራ ብሄር ተወካይ ነኝ እደራደርለታለሁ” የምንለው?
አዎ እውነት ነው የአማራ ህዝብ የሞት አዋጅ የታወጀበት ባልሰራው በደል ባለፋት 25 ዕመታት የዘር ማጥፍት ሲፈፅምበት ቆይቷል። ለዛም ነው ተደራጅቶ እራሱን መታደግ አለበት የምንለው ሆኖም ባሳለፍነው አንድ አመት ውስጥ የተፈለፈሉት ታላቁን የአማራ ህዝብ እንወክላለን የሚሉን ድርጅቶች ህዝባችን ብለው የተነሱለትን ህዝብ ስነልቦና እንኳን ማንበብ የማይችሉ ከራሳቸውም የተጣሉ ሆነው አግኝተናቸዋል። አብዛኛዎቹ የተፈበረኩት በወያኔ የውጭ የፓለቲካ እስትራቴጂክ መዋቅር ውስጥ መሆኑን በግዜ ተጉዘን መረዳት ችለናል ፤ እደውም አንዳንዴም “አግ7 ወደስልጣን ከሚመጣ ከብአዴን ጋር ተስማምተን እንሰራለን” ትዕግስታቸው ሲያልቅ ብለው የሚናገሩም አሉ። ምን እሚሉት ፈሊጥ ነው ከገዳይ ጋር እሰራለሁ ማለት?
የህዝብ ውክልና ምንድነው?
ኢትዮጵያ አሁን ባለችበት የፓለትካ አጣብቂኝ ውስጥ ሆነን ስለህዝብ ውክልና ማውራት ማለት አላዋቂነት ነው ተብሎ ሊታለፍ አይገባም በማንአለብኝነት የተሞላ የስልጣን ጥማት የነገሰበት አስተሳሰብ ነው።
አምባገነኑን የወያኔ አፓርታይድ ስርአት ሳንጥል እና በነፃነት አገራችን የፖለቲካ ሜዳ ላይ ፖሊሲያችንን አቅርበን ቆሜልሀለው የምንልውን ህዝብ ይሁኝታ ሳናገኝ አይ እኔ የተወለድኩት ጎጃም፣ጎንደር፣ወሎ…ወዘተ ስለሆነ እኔነኝ ተወካይህ በማንነትህ ላይ እደራደራለሁ ማለት የጠገበውን ወያኔን አዉርዶ የራበውን ምትኩን ማንገስ ነው የሚሆነው። ለዛም ነው ምንም እንኳን የአስተሳሰብ ልዩነት ቢኖረንም አምባገነኑን የወያኔን ስርአት በጋራ ጥለን በነፃነት ለተጨቆነው ህዝብ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሀሳባችንን አቅርበን ውክልናን የምንረከበው። በተቃራኒው ግን አሜሪካ አገር ቁጭ ብሎ አገር ቤት ወያኔ ሲወድቅ ስልጣን እንደሚያገኝ እርግጠኛ መሆን የሚፈልጉ ቆሜለታለው የሚሉት ወገን ሞት ምንም የማይመስላቸው ሆነው አግኝተናቸዋል።
አግ7 እንኳን እግር በሌላቸው የወያኔ ድርጅቾች በወያኔም አይፈርስ! አግ7 ውስጥ ምንያህል አማሮች እንዳለን እናንተም ታውቃላችሁ አሁን እናንተም ደረታችሁን ነፍታችሁ እየታገልን ነው የምትሉት ትግል ወልዶ ያሳደገው አሁን ላለንበት ያንገዛም እቢተኝነ ማዕበል ያበቃው አግ7 ነው! እኛም አማራ ነን የህዝባችን ሞት የሚገለን።
አልመሸም ገና ብዙ መንገድ ይቀረናል አብረን ብንጟዝ ቶሎ ያሰብንበት እንድርሳለን የወገኑ ስቃይ የሚያመው ሁሉ ልዩነቱን አቻችሎ ለአንድ ጠላት ወያኔ በጋራ ይነሳ!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ዳንኤል ሃይሌ

ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ከተከዜ በታች ያለ ኢትዮጵያዊ ያላለቀሰበት ጊዜ የለም፤ በአንጻሩ ከተከዜ በላይ ያሉ ዜጎች ዘመናቸው ሁሉ የፍስሃ ሆነ source zhebesha


ከሙሉቀን ተስፋው
ለቀስተኛው፤ ከተከዜ በታች ያለ ሕዝብ:
ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ ከተከዜ በታች ያለ ኢትዮጵያዊ ያላለቀሰበት ጊዜ የለም፤ በአንጻሩ ከተከዜ በላይ ያሉ ዜጎች ዘመናቸው ሁሉ የፍስሃ ሆነ፡፡
እስኪ ትንሾቹን እንይ፤
 ከ1983-86 ዓ.ም በሐረርጌ እስከ 20 ሺህ የሚደርስ ዐማራ በአንድ ዓመት ሲታረድ፣ አጥንታቸው ወደ ወንዝ ሲወረወር፣ አብያተ ክርስቲያናት ሲወድሙ ከተከዜ በላይ ዳንኪራ ይረገጥ ነበር፡፡ በምስራቅ አርሲ የአምስት ወረዳ ዐማራ ቤትና ንብረት ተቃጥሎ ከነነፍሳቸው ወደ ገደል ሲጣሉ፤ በዘንጋዳ ጉድጓድ በጅምላ ሲቀበሩ እየየ ብለን አልቀሰናል፡፡ ወላድ እናቶች ልጃቸው በሳንጃ ከሆዳቸው ላይ የወጣበት ጊዜ በዚሁ በወያኔ ዘመን ነው፡፡ የማይሞላ ገደል ውስጥ የተጨመሩት ዐማሮች፣ ዐይናቸው ተጨፍኖ ወደ ገደል የተወረወሩት መነኮሳትን ማናችንም አልረሳንም፡፡ የመተከልና የወለጋ ጫካዎች በዐማራ አስከሬኖች ሲሞሉ የገዥው ቡድን ዘመዶች አስረሽ ምቺው እያሉ ነበር፡፡
 ከ1972 ዓ.ም ጀምሮ የወልቃይት ዐማራ እናቶች ስለልጆቻቸውና ባሎቻቸው ያላዘኑበት ጊዜ የለም፤ በዚህ ጊዜ ከወንዝ ወዲያ ማዶ ያሉ ሰዎች ምን ይሉ እንደነበር ማንም መገመት አያቅተውም፡፡
 በ1998 ዓ.ም የኮፈሌና የቆሬ ወረዳ ዐማሮች ቤት ንብረታቸው በጨለማ ነዶ ከቀያቸው ሲፈናቀሉ ማንም ምንም ያለ የለም፡፡

 በ1992/3 ዓም በወለጋ የተለያዩ አካባቢዎች ከአንድ ሺህ በላይ ዐማሮች ቤት እየተዘጋባቸው ሲቃጠሉ ሕጻናት ከታዘሉበት እናታቸው ጀርባ እየተቀሙ ወደ ሚነደው እቶን ሲጣሉ መከላከያ ሠራዊት የሚያመልጡትን ዐማሮች በጀርባ ሆኖ ይጨርስ ነበር፡፡ 14000 (ዐሥራ አራት ሺህ) ዐማሮች ተፈናቅለው ቡሬ ላይ ሲቀመጡ የእለት ጉርስ እንኳ የሰጣቸው የመንግሥት አካል አልነበረም፡፡ ጃዊ ላይ ከ800 በላይ በወባ ሲያልቁ የወባ መድኃኒት ያቀረበ የጤና ባለሙያ እንኳ አልነበረም፡፡

 በ1990ዎቹ መጀመሪያ በወያኔና በሻቢያ ጦርነት ከ70 ሺህ በላይ ወንድሞቻችን በጦር በጦርነት ተማግደው አልቀዋል፡፡
 በ1999 ዓ.ም በጂማ ከነቤተክርሲያናቸው ዐማሮች ቤት ተዘግቶባቸው ሲነዱ ማንም ምንም አላለም፡፡
 በ2004-7 በቤንች ማጂ፣ በከማሽ፣ በመተከል፣ ከ32000 በላይ ዐማሮች ቤት ንብረታቸው ወድሞ ሲባረሩ ከተከዜ ማዶ ያሉ ሰዎች ደን ጨፍጫፊ ትምከተኞች ናቸው በማለት ነበር የተሳለቁት፡፡
 በ2007 ዓ.ም በመተከል በአንድ ቀን ሌሊት 160 በላይ ዐማሮች ታርደው ሲያደሩ የተባለ ነገር የለም፤
 በ2007 ዓ.ም በጎንደር ማረሚያ ቤት ከ70 በላይ ሰዎች በእሳት ሲቃጠሉ ምን ተባለ! ምንም፡፡
 በ2008/9 ከ300 በላይ ዐማሮች በጎንደርና በጎጃም በጥይት ተደፍተዋል፤ ገዥው ቡድን ምን አለ! ምንም፡፡
 በደብረዘይት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተጠቅጥቀው ሲሞቱ እንኳ ከተከዜ ማዶ አሸንዳ ሲጨፈር ነበር፡፡
ምኑን ተናግረን ምኑን መተው እንችላለን? ከተከዜ በታች ያለን ዜጎች ኑሮ እንዲህ ነው፡፡ በእኛ ላይ ይህ ሁሉ ሲሆን ከተከዜ ማዶ ባለፉት ሃያ አምስት ዓመታት ምን መቅሰፍት ደርሶ ይሆን ብየ አሰብኩ፤ ምንም!
ደግነቱ ጊዜ ፈራጅ ነው፤ የሚያለቅሱ የሚስቁበት ጊዜ የሚስቁም የሚያለቅሱበት ዘመን ብዙ ሩቅ አይደለም፡፡

አቶ ለገሰ ወልደሃና እና አንድ የደብረ ብርሃን ባለሀብት ታሰሩ by: Zehabesha


 





ከሙሉቀን ተስፋው
በአቶ ማሙሸት አማረ የሚመራው የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ለገሰ ወልደሃና መጋቢት 6 ቀን 2009 ዓም ከቤቱ በደኅንነት ታፍኖ ተወስዷል። በደብረ ብርሃን ከተማ ጠባሴ አካባባቢ የፍቅረ ሰላም ሆቴል ባለቤት የሆኑ ባለሀብት ባካባቢው በመገኘታቸው አብረው ታስረዋል። በደኅንነቶችና በፖሊስ አባላት ድብደባ እንደደረሰባቸው ታዛቢዎች የገለጹ ሲሆን ወደ ማዕከላዊ መዛወራቸውን ዛሬ ለማወቅ ችለናል።
አቶ ለገሰ ወ/ሃና ከፓርቲ ሥራው በተጨማሪ የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ሀሳብ በመሰንዘርና መረጃ በማድረስ የታወቀ ነው። በተለይ በሸዋ አካባቢ ያለውን የዐማራ ተጋድሎ ለሕዝብ ሳያሳልስ የሚያቀርብ ታታሪ ፖለቲከኛ ነው።

የአርበኞች ግንቦት 7 ታጣቂዎች በሰሜን ጎንደር ዞን የተለያዩ ስፍራዎች ማክሰኞ ምሽት ጥቃት ፈጸምሁ አለ

ከአይን ምስክሮችና ከንቅናቄው ምንጮች ለመረዳት እንደተቻለው በጭልጋ፣ ደንቢያና በጎንደር ዙሪያ ወረዳዎች በተመሳሳይ ቀንና በተቀራራቢ ሰዓት በመንግስት ሃይሎችና ተቋማት ላይ ጥቃት ተፈጽሟል።

በትግል ላይ እያሉ መስዋዕትነት በከፈሉት ሻለቃ መሳፍን ጥጋቡ ወይንም ገብርዬ እንዲሁም በታጋይ ጎቤ መልኬ እና በአበራ ጎባው ስም የተሰየሙት ወታደራዊ ዘመቻዎች፣ ማክሰኞ መጋቢት 5 ፥ 2009 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን መግደልና መቁሰል ጭምር ማስከተላቸውንም ለመረዳት ተችሏል።
ዘመቻ “ዋዋ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚሁ ጥቃት ከጎንደር 80 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በመከላከያ ሰራዊት ካምፕ ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል። በጭልጋ ወረዳ ነጋዴ ባህር ከተማ በሰፈረው የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ በተሰነዘረ ድንገተኛ ጥቃት 3 ወታደሮች ሲገደሉ፣ 15 መቁሰላቸው ተመልክቷል። በአምስቱ ላይ የደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ጎንደር ሬፈራል ሆስፒታል ሲወስዱ፣ ቀላል ጉዳት የደርሰባቸው 7 ወታደሮች በመተማ ገንዳ ውሃ ሆስፒታል በህክምና ላይ መሆናቸውን የተገኘው ዜና ያስረዳል።
በቅርቡ በትግል ሜዳ ላይ እያሉ የተሰውትን ጎቤ መልኬን ለማስታወስም በስማቸው መጠሪያ “ዋዋ” የተሰየመው ዘመቻ ተሳታፊ የሆኑት የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊዎች ጥቃቱን ፈጽመው ወደ ነበሩበት መመለሳቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በመከላከያ ሰራዊት በኩል በቡድን መሳሪያ የተደገፈ የአጻፋ ምላሽ መሰጠቱም ተመልክቷል። በመትረየና ላውንቸር የተደገፈውን የአጸፋ ምላሽ ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱንና የትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡም ተመልክቷል።
በዚሁ በጎንደር ዞን ደንቢያ ወረዳ በተመሳሳይ ቀን ዘመቻ ገብርዬ በሚል በተሰየመው ወታደራዊ ዘመቻ በቆላ ድባ ከተማ በሚገኝ የከተማው አስተዳደር ጽ/ቤት ላይ በተከፈተ ዘመቻ የአስተዳደር ጽ/ቤቱ በከፊል ሲወድም፣ የአስተዳዳሪው መኪና መቃጠሉንም የመጣው ዜና ያስረዳል። በተመሳሳይ ጯሂት ከተማ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በካምፕነት በሚጠቀሙበት ቁጥር 2 በተባለው ጽ/ቤት ላይ በተሰነዘረ ጥቃት በወታደሮቹ ላይ የቃጠሎ ጉዳት ደርሶባቸዋል።
በአብራጅራ ከተማ አብራጅ ጽ/ቤት በሰፈሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ እንዲሁም በቸንከር ቀበሌ የከተማዋ ኮማንድ ፖስት ማዘዣ ላይ ጥቃት ተፈጽሟል። በጥቃቱ የቸንከር ቀበሌ ኮማንድ ፖስት ማዘዣ ጣቢያ ሲወድም፣ አንድ የኮማንድ ፖስቱ አባል መጎዳቱንና አንድ መጋዘን መቃጠሉን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።
በሰሜን ጎንደር አካባቢዎች መሳሪያ አንስተው በትግል ላይ ከነበሩት አንዱ በነበረውና መስዋዕትነት በከፈለው በአበራ ጎባው ስም በተመሳሳይ ቀን በጎንደር ዙሪያ የአርበኞች ግንቦት 7 ሃይሎች ጥቃት መፈጸማቸውም ተመልክቷል።
የአርበኞች ግንቦት 7 ተዋጊዎች ማክሰኞ መጋቢት 5 ፥ 2009 እኩለ ሌሊት አካባቢ በጎንደር ዙሪያ ወረዳ በደጋማ ከተማ በወህኒ ቤት እንዲሁም ኮማንድ ፖስቱ በሚጠቀምባቸው ቢሮዎች ላይ ጥቃት መፈጸሙ ታውቋል። እንዲሁም የአማራ ክልል ምክር ቤት አባል በሆኑት በአቶ ደሴ ዘገየ መኖሪያ ቤት ላይም ተመሳሳይ ጥቃት መከተሉንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

Wednesday, March 15, 2017

ለሥልጠና ወደ አድዋ የተወሰዱ የወልቃይት ዐማሮች በድብደባ ጉዳት ደረሰባቸው ከሙሉቀን ተስፋው source zhabesha


ከሙሉቀን ተስፋው
የ10ኛ ክፍል ትምህርታቸውን የጨረሱ የወልቃይት ወጣቶችን አሰልጥኜ ሥራ አስይዛችኋለሁ በማለት ነበር ሕወሓት ወደ አድዋ የወሰዳቸው፡፡ ከወልቃይትና ጠገዴ አካባቢዎች ተመልምለው የተወሰዱ ወጣቶች አድዋ ሲደርሱ ግን የጠበቁትን ሥልጠና አላገኙም፡፡
አብረዋቸው በሚማሩ የትግራይ ተማሪዎችና አስተማሪዎች ‹‹ስለምን ዐማራ ነን አላችሁ፤ ትግሬ የተጠላው በእናንተ ምክንያት ነው!›› የሚል ወከባና ጥያቄ ይደርስባቸዋል፡፡ ከዚያ ወጣቶቹ ‹‹ታዲያ ምን ልንል ነው፤ እኛ እኮ ዐማራ ነን›› የሚል የማያወላዳ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡
ትናንት መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ለሥልጠና የሔዱት ሁሉም ወጣቶች ያለምንም ረዳት በሰው አገር የተደበደቡ ሲሆን ሐጂ የተባለ ወጣት ከፍተኛ የአከርካሪ ጉዳት ደርሶበታል ተብሏል፡፡ በድብደባው ጉዳት የደረሰባቸው ዐማሮች እስካሁን ምንም ዓይነት ሕክምና ካለማግኘታቸውም በተጨማሪ ወደ ወልቃይት እንዳይመለሱ ከፍተኛ ጥበቃ እየተደረገባቸው ነው ተብሏል፡፡ ወደ ወልቃይት ከተመለሱ ለበለጠ አደጋ እንደሚጋለጡና እንደሚታሰሩም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል፡፡

ኖርን እና ሞትን! Posted by: Zehabesh 

ኖርን እና ሞትን!










Tuesday, March 14, 2017

መንግስታዊ ቸልተኝነት እና ብሔራዊ የሐዘን ቀን! – (ይድነቃቸው ከበደ) source zhabesha


መንግስት በደረሰበት ከፍተኛ ተጽዕኖ እንዲሁም ፣ በማህበራዊ ድረ ገጾች በተለያየ መንገድ ይደረግ የነበረው ቅስቀሳ ባሳደረው ግፊት፣ ብሔራዊ የሐዘን ቀን በኢትዮጵያ ሊታወጅ ችሏል።በዚህም መሰረት ፣ ከመጋቢት 3 እስከ መጋቢት 5 ቀን 2009 ዓ.ም ለሦስት ቀን ብሔራዊ የሃዘን ቀን እንዲሆን ተወስኖል።

በመንግስት ግዴለሽነት ምክንያት ብቻ ! በደረሰው የቆሻሻ ክምር መናድ ፣ከ75 ሰው የማያንስ ለሞት የተዳረገ ሲሆን በመቶ የሚቆጠሩ ለከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ተዳርገዋል ። እንዲሁም ከ250 የማያንሱ ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ሲሆን በጊዚያዊ መጠለያ እንዲቆዩ ተደርጓል ። በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የደረሰው አደጋ፣ የዓለማችን ታላላቅ የመገናኛ ብዙሃን በፊት ገጻቸው ሰፊ የዜና ሽፍና ሰጥተውታል ።

መንግስት አደጋው ከደረሰ ከሦስት ቀን በኋላ ፣ በደረሰበት ከፍተኛ ግፊትና ተጽዕኖ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ከማወጁ በፊት ፣ በአዲስ አበባ የጀርምን ኢምባሲ በደረሰው አደጋ የተሰማውን ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ ፣ በኢምባሲው የጀርመን እና የአውሮፓ ህብረት ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ በማድረግ ለኢትዮጵያውያን የጀርመን መንግስት አጋርነቱን አሳይቷል ። ዓለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ተቋማት ፣በደረሰው አደጋ ማዘናቸውን በመግለጽ ፣ ለአደጋው መንስኤ መንግስትን ተጠያቂ አድርጓል ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፣የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ፣ አደጋው በደረሰበት አካባቢ በመሄድ ፣ የሟች ቤተሰቦችን እያጽናኑ የሚገኝ ሲሆን፣ ከነፍስ አድን ሰራተኞች ጋር በመተባበር ፣ በቆሻሻ ክምር ውስጥ በህይወት የተረፈ እና ጉዳት የደረሰባቸውን በማፈላለግ ላይ ይገኛሉ። አደጋው በተከሰተበት ቦታ የተገኘው የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወንድም ፣ አቶ ታሪኩ ደሳለኝ (ሚኪ) በቦታው ተገኝቶ በማህበራዊ ድረ ገጹ እንደገለጸው ከሆነ ፣ “ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ የሞቱት ነብስ ይማራ ለማለት ቤተሰቦቻቸውን ለማፅናናት ተገኝቻለሁ። በየአምስት ሜትሩ ድንኳን ተተክሎ ማየት ያሰደነግጣል። አንዳንዱ ጋር ለሦስት ለአራተ ሰው በአንድ ድንኳን ሀዘን ተቀምጠዋል። አሁንም ከቆሻሻው ክምር አስክሬን እየወጣ ነው። እኔ ከደረስኩበት ከ12 እስከ 3 ሰዓት ብቻ 12 አስክሬኖች ወጥተዋል። ነዋሪዎቹ እንደሚናገሩት ይሄ ከላይ ያለው ናዳ ቆሻሻ ውስጥ የተገኙ ናቸው ገና የታቸኛወ ውስጥ ይቀራል ብለዋል። አሁንም ውሃ መብራት የለም።አሁንም በዙ ሰው አልወጣም ብዙዎች ያለመጠለያ ቀርተዋል።የተቻላችሁን የሀል ድግፍ እንድታደርግ “በማለት የተሰማውን ገልጸዋል ።

ሌላው የዓይን እማኝ የሆነው ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን ፣ በትላንትናው ዕለት በተካሄደው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተገኝቶ ሃሳብን እንደሚከተለው ገልጸዋል ።”50ዎቹ በደብረ ከዋክብት አቡነ አረጋዊ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈጽሟል ። የሟቾቹ ቁጥር 65
ደርሷል። ፍለጋው እንደቀጠለ ነው። ከሟቾቹ ውስጥ የአንድ ቤት አምስት የቤተሰብ አባላት ይገኙበታል ። ኮልፌ እስላም መቃብር ሀዘንተኛው ነስሩ ሁሴን ተጠጋሁት፣ “እህቴን፣ የእህቴ ሁለት ልጆች፣ የወንድሜ ሚስት ከነልጇ ይሄው ቀበርናቸው” ኡኡታውን አቀለጠው።” በማለት የተሰማውን ሃዘን አጋርቷናል። በመንግስት ግዴለሽነት ምክንያት ብቻ በደረሰው አደጋ ፣የተለያዩ ሰዎች የተለያየ አሰተያየት እየሰጡ ይገኛል

ህይወታቸውን ላጡ ፈጣሪ ነፍሳቸውን ይማር ፤ ለቤተሰቡና ለወዳጅ ዘመድ መጸናናት ፈጣሪ ይስጥልን ፤አሜን!!!

በአምቦ የጥይት ማምረቻ ፋብሪካ ውስጥ የሚፈፀም በደል ተጋለጠ source zhabesha ከሙሉነህ ዮሐንስ


ከሙሉነህ ዮሐንስ
በእውነት ምስክርነት የተዘበ ነውና በጥሞና አንብባችሁ እራሳችንን ለትግል አናዘጋጅ። ቢያንስ እንኳ እግዚአብሔር ይህን ድብቅ ያጋልጥ ብላቹህ ፀልዩ።
በጥይት ማምረቻው ውስጥ እውነት እላቹሃለሁ አንድ አንኳ የትግራይ ሰው በዕለት የማምረት ተግባሩ ውስጥ የሉበትም፡፡ ነገር ግን በሰው ኃይል ምደባ ተቆጣጣሪነት ..ወዘተ ድርሻ እነሱ እና እነሱ ብቻ ናቸው፡፡ ለምን ጥይት በማምረቱ ስራ ትግሬዎቹ የሉም? ለምትሉ መልሱ እና እውነታው ይኸውላችሁ፡-
፨፨፨ ጥይትን ለማምረት የሚጠቅመው የፖታስየም ናይትሬት ኮምፓውንድ(KNO3) /ውህድ እጅግ በጣም ለካንሰር የሚያጋልጥ በርካቶችንም ከዚህ በፊት ለሞት እና ለመካንነት የዳረገ ነው፡፡ በምሬት አንድ ወታደር ያለችኝም ይህ የማምረቱን ስራ የምንሰራው ሁላችንም ሴቶች ነን በቀን እስከ 15 ካርቶን እያንዳንዳችን እናመርታለን፡፡
አንድም የትግራይ ሴቶች የሉም። በአብዛኛው የአማራ ሴቶች ሲሆኑ ቀጥሎ የኦሮሚያና የደቡብ ናቸው፡፡ እጅግ በጣም የሚያሳዝነው ግን እያለቀሰች የነገረችኝ፦
እኔ ባጋጣሚ የትግል አጋሬን አግብቸ አንድ ሴት ልጅ ወደ ዚህ ከመግባቴ በፊት ወልጃለሁ ከቤተሰቦቸ ጋርም ትኖራለች፡፡ ሌሎች ግን የወሊድ ምርመራ ያውም በግል ሲመረመሩ ከ11 ጓደኞቸ 9ኙ በጥይት ማምረቻው የተለያዩ ኬሚካሎች ምክንያት መክነዋል። ጡቶቻቸው አካባቢ ሙሉ በሙሉ ጥላሸት/ማድያት የሚመስል መልክ አንደወጣባቸው በለቅሶ ያስረዳሉ፡፡ ምክንያቱም የሚሰሩት ያለ ሴፈቲ/የአዳጋ መከላከያ አልባሳትና ትጥቅ ስለሆነ፡፡ የሚሰጥ ወተት አንኳ ካቆመ ቆየ በማለት የአረመኔ ተግባራቸውን ሀገር ይስማው ብለው አስረድተዋል ፡፡
ለደህንነታቸው ሲባልም ነው ስማቸውንና ጠቋሚ መረጃ ያልጠቀስኩት፡፡ ታድያ ትግራዮች እውን ኢትዮጲያዊ ስሜት አላቸው፡፡ የውጭ ሀገር ዜጎች እንኳ በዚህ መልኩ የረቀቀ ዘር የማጥፋት ዘመቻ አልሰሩብንም፡፡ ወገን ስለዚህ አባባሉ የሚለው ማወቅ ስለሰዎች መኖር ነው ይላል፡፡ ስለዚህ ካወቅን የአቅማችንን ሁላችንም ወደ ትግል መግፋት አለብን፡፡ ቢያንስ እነሱን በድርጊታቸው እንኳ ልንጥላቸው ይገባል።
ቋሚ አምደኛችንን ከልብ እናመሰግናለን።

Saturday, March 11, 2017

ድርቁ መቶ ሺዎችን አፈናቅሏል፤ ከ250 ሺ በላይ ህፃናት ትምህርት አቋርጠዋል


Image result for ethiopian drought 2017


ድርቁን ተከትሎ አስከፊ ረሀብ ሊከሰት እንደሚችል ተመድ አስጠንቅቋል
መንግሥት የእርዳታ ጥሪ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አላገኘም
እስከ 15 ሺህ ብር ይሸጡ የነበሩ ከብቶች፣ 500 ብር ድረስ እየተሸጡ ነው
Addis Admass
በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል የድርቅ አደጋ በመቶ ሺዎች የሚገመቱ ሰዎችን ያፈናቀለ ሲሆን ከሩብ ሚሊዮን በላይ ህፃናት ትምህርታቸውን እንዲያቋርጡ ውጪ ማድረጉንም የተባበሩት መንግስታት የእርዳታና የሰብአዊ ድጋፍ ድርጅት (UNOCHA) ሰሞኑን ባወጣው ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል በድርቅ ከተጎዱ አካባቢዎች አንዱ በሆነው የኦሮሚያ ክልል፣ ቦረና ዞን ያሉ አርሶ አደሮች በህይወት የተረፉ ከብቶቻቸውን በርካሽ ዋጋ እየሸጡ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ አድማስ ጠቁመዋል፡፡
ድርቅ ባጠቃቸው የቦረና አካባቢዎች በጉዳዩ ላይ ጥናት በማድረግ ላይ የሚገኙ ባለሙያዎች እንደሚሉት፤ በደህናው ጊዜ እስከ 15 ሺህ ብር ይሸጡ የነበሩ በሬዎች፤ በአሁን ወቅት ከ500 እስከ 1 ሺህ ብር ድረስ እየተሸጡ ሲሆን ከ500 እስከ 1 ሺህ 500 ብር ይሸጡ የነበሩ በጎችና ፍየሎች ደግሞ በ80 እና በ90 ብር እየተሸጡ ነው ተብሏል፡፡
ከብቶቹ በአብዛኛው በአካላዊ ቁመናቸው የተጎዱ በመሆኑ፣ ፈላጊ ስለሌላቸው አርብቶ አደሮቹ በርካሽ ዋጋ ለመሸጥ መገደዳቸውን ባለሙያዎቹ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡፡፡
የከብቶች ሞትም እንደቀጠለ መሆኑን የጠቆሙት አጥኚዎች በተለይ የመጠጥ ውሃ ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ገልፀው፤ መንግስት በቦቴ ውሃ እያቀረበ ቢሆንም በበቂ መጠን አለመሆኑን አመልክተዋል፡፡
ወቅታዊ ሪፖርቱን ሰሞኑን ይፋ ያደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በበኩሉ፤ በተለይ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልል የሚሊዮኖችን ህይወት አደጋ ላይ ለጣለው ድርቅ መንግስትና የእርዳታ ለጋሽ ተቋማት ውሃና ምግብ በማቅረብ እየተረባረቡ ቢሆንም ከአደጋው አስከፊነት አንፃር በቂ አይደለም ብሏል፡፡
በድርቁ ምክንያት 228 ሺህ ህፃናት ትምህርት ማቋረጣቸውን ይፋ ያደረገው ሪፖርቱ፤ ከእነዚህ ውስጥ 183 ሺህ 090 የሶማሌ ክልል ህፃናት ሲሆኑ 44 ሺህ 571 የሚሆኑት ደግሞ የኦሮሚያ ክልል መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡ በሁለቱ ክልሎች ማለትም በኦሮሚያ በድርቁ ምክንያት 141 ት/ቤቶች፣ በሶማሌ ክልል 437 ት/ቤቶች በድምሩ 578 ትምህርት ቤቶች መዘጋታቸውን ሪፖርቱ አስታውቋል፡፡
ምግብና ውሃ ፍለጋ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አባወራዎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸውን የጠቆመው የተመድ የእርዳታና ሰብአዊ ድጋፍ ድርጅት ሪፖርቱ፤ ከተፈናቀሉት ውስጥ 163 ሺህ ያህሉ ለትምህርት የደረሱ ህፃናት መሆናቸውን አመልክቷል፡፡ እነዚህን ተፈናቃይ ህፃናት ለ75 ቀናት ሊመመገብ 5.9 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልግም ተገልጿል፡፡
በእርዳታ አሰጣት ደንብ ለአንድ ሰው በቀን ውስጥ 5 ሊትር ውሃ መቅረብ ያለበት ቢሆንም በአሁን ወቅት ለአንድ ሰው በቀን እየቀረበ ያለው በአማካይ 2.1 ሊትር ውሃ መሆኑን የተመድ ሪፖርት ጠቁሞ፤ የውሃ ክፍፍሉም ፍትሃዊ አለመሆኑንና ከወረዳ ወረዳ እንደሚለያይ አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይ ለ5.6 ሚሊዮን የተረጂዎች 1 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ እርዳታ እንደሚያስፈልግና ይህ እርዳታ በአፋጣኝ ካልተገኘ ሁኔታው ወደ አስከፊ ረሃብ ሊቀየር እንደሚችል አሳስቧል፡፡
ተመድ መንግስት ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመሆን የእርዳታ ርብርብ እያደረጉ ነው ቢልም መንግስት በበኩሉ፤ ለድርቁ አደጋ የእርዳታ ጥሪ ቢያቀርብም እስካሁን ምላሽ አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡
በሌላ በኩል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አፍሪካን በተመለከተ ባወጣው ሪፖርቱ፣ ኢትዮጵያን ጨምሮ በድርቅ በተጎዱ፣ ከሠሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሃገራት፣ በአሁኑ ወቅት ከ20 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የእርዳታ ርብርብ እንደሚፈልጉ አስታውቆ፤ አለማቀፉ ማህበረሠብ እጁን እንዲዘረጋ ጥሪውን አስተላልፏል

ብአዴን የህውሃት የትሮይ ፈረስ – (በቬሮኒካ መላኩ )

በቬሮኒካ መላኩ
……………………
ሰሞኑን የትግሬ ብሄርተኞች ” ብአዴን እንደዚህ አለ እንደዚያ አለ ” እየተባለ ሴቱ በየወፍጮ ቤቱ ወንዱም በየቀንዶ ቤቱ እያወራ እየፈነጠዘ ነው ።
ለአማራ ህዝብ ብአዴን የሚባል ድርጅት ባእዱ ነዉ ። የአማራ ህዝብ ብአዴን አማረኛ ተናጋሪ ህወሀት ናቸሁ ተላላኪ ናቸሁ ብሎ ፊቱን ካዞረባቸው ብዙ አመታት ተቆጠረ ።
ብአዴን ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት የሚል የሆዳሞች ስብስብ የህዋት ተላላኪ ድርጅት ነው ተብሎ አቋም የተያዘበት ድርጅት እንደሆነ የአደባባይ ሚስጥር ነው ። መቸም ትግሬዎች በራሳችሁ አምሳል ጠፍጥፋችሁ የሰራችኋቸውነን ተላላኪዎቻችሁን እያወቃችሁ ብአዴን እንዲህ አለ እያላችሁ ጮቤ ምትረግጡት እና ህዝቡን ለመሸወድ የምትሞክሩት ነገር አስገራሚም አስቂኝም ነው።
እንደት ትግሬ የራሱን ድምፅ እንደገደል ማሚቶ ኤኮ እያደረገ መልሶ በሚዲያው መስማቱ እንደት ሊያስፈነጥዘው ቻለ? ይሄ የሰዎቹን ንቃተ ህሊና የት ደረጃ እንደደረሰ አመላካች ስለሆነ አይገርምም ።

“ብአዴን ማነው ? ” የሚል ጥያቄ በማንሳት አንባቢን ማዛግ የሚያስፈልግ አይመስለኝም ። ነገር ግን አንዳንድ ጥያቄዎችን ማንሳት ጥሩ ይመስለኛል ።
ለመሆኑ ግማሽ ትግሬው እና የአማራን ህዝብ በፀያፍ ስድቡ የዘለፈው አለምነው መኮንን እንዴት ለአማራ ሊያስብ ይችላል?
የትግሬ ተወላጁ ካሳ ተ/ብርሀን እንዴት ለአማራ መሬት ሊጨነቅ ይችላል? ኤርትራዊው በረከት ስሞን እንዴት የሚጠላውን አማራ ሊያስብለት ይችላል?
የእድሜውን ከግማሽ በላይ ሀረር እና ትግራይ ውስጥ ሲርመጠመጥ ያሳለፈው እና ትግሪኛ ተናጋሪው አዲሱ ለገሰ በምንም ተአምር ለአማራ ሊቆረቆር ይችላል?
ትግሬው ህላዊ ዮሴፍ እንደት ለአማራ ሊጨነቅ ይችላል?
የትግሬን የአምባሻ ዱቄት ተሸከም ቢሉት የማያቅማማው ሎሌ ደመቀ መኮንን እንደት አማራን ሊወክል ይችላል?

የአማራ ህዝብ ብአዴን ወልቃይት እና ሌሎች በማን አለብኝነት የተወሰዱ የአማራ መሬቶች ማስመለስ እንደማይችል አሳምሮ ያውቀዋል። ማስመለስ ቢችልማ መጀመሪያውን እንዴት አሳልፎ ይሰጥ ነበር?

አዲሱ ለገሰ የተባለው የህውሃት ሎሌ በወልቃይት ጉዳይ ላይ ባደረገው ኢንተርቪው ሳያስበው አንድ እውነት አምልጦታል ። Smart ብትሆኑ ኖሮ የሰውየው ንግግር ሊያሳዝናችሁ እንጅ ሊያስፈነጥዛችሁ ባልተገባ ነበር ። ሎሌ አዲሱ ለገሰ ምን አለ ? ” የወልቃይት ጉዳይን የብአዴን ጥያቄ አይደለም አለ ።” እውነቱን ነው ። ከመነሻውም የወልቃይት ጥያቄ የ 40 ሚሊዮን የአማራ ወልቃይት ህዝብ ጥያቄ እንጂ ብአዴን የተባለው ድርጅት ጥያቄ አልነበረም ። የአማራ ህዝብ እኮ እየታጋለ ያለው ህውሃትን ብቻ ሳይሆን አማርኛ ተናጋሪ የህውሃት ክንፍ የሆነውን ብአዴንንም ጭምር ነው ።

ባለፉት 25 አመታት የወልቃይት ህዝብ እያለ ያለው ጨዋታው በየብሄርህ ከሆነ እኛን ለምን ከብሄራችን ትነጥሉናላችሁ ነው። ይሄ ደግሞ መብታቸው ነው። ቋንቋቸውን ባህላቸውን ለመጠበቅ ወደ ክልላቸው መመለስ አለባቸው።
የወያኔ አስተዳደር ስምምነት ይሄው ስለሆነ የወልቃይት ህዝብ ማንነቱን ከመሬቱ ጋር ኣያይዞ እየጠየቀ ስለሆነ መመለስ አለበት።
ዘረኛው ወያኔ አልተረዳውም እንጂ የትግራይ ህዝብ ድንበሩ ተከዜም ወልቃይትም አልነበረመም። ድንበሩ ከኢሉባቦር እስከ ኦጋዴን እስከ ሞያሌ እስከ ባድመ ነው። ነገር ግን ወያኔ የዘር ጨዋታውን ፊሽካ በማስነፋት ስለጀመረው በስግብግብነት እንደ አሳማ ከጎንደር እና ከወሎ የዋጠውን መሬት ማንቁርቱን ተይዞ መትፋቱ አይቀርም ። በመጀመሪያ በዚህ ጉዳይ ላይ ወደ ስምምነት መምጣት አለባት። ሁላችን ወሰናችን ይሄ መሆኑን መስማማት አለብን። አለበለዚያ ወያኔ በአንድ በኩል የቋንቋ መንግስት አምሮት በሌላ በኩል ደግሞ ትንሽ ለም መሬት ሲያይ ከቤንሻንጉልም ከአማራም ቦጨቅ ማድረግ እያማረው ኣይሆንም። ትክክልም አይደለም።

በብዙ መልኩ ስንገመግመው የትግሬ ወያኔ ባህሪ የክረምት ጅብ አይነት ነው ።
በአንድ በኩል በትግሬ ውስጥ ያሉ ሃብቶችን የኢፈርትንም ጭምር ፣ተፈጥሮ ሃብቱንም የኛ የትግራይ ህዝብ ብቻ ነው ይልና በአንድ እጁ ይዞ ይታያል። ንብረትነቱ የኛ ብቻ ነው ይላል። በሌላ በኩል ደግሞ የአባይን ወንዝ ፣ የጣናን ተፋሰስ እና ለም መሬት ፣ የጉጂዎችን ወርቅ ፣የጅማውን ቡና የሁላችን በማለት አብሮ ይበላል። የሌላውን በአንድ ገበታ አርገን እንብላ ይልህና የራሱን ብቻውን ይውጣል ። የራሱን በጁ ይዞ እያደለበ የሌላውን ያጫርሳል። ይሄ ጥሩ አይደለም። ለሃቹ ለሃገራችን ኣይበጅም። ብንገነጠልም እንኳን ለጉርብትና አይሆነንም። ታሪካዊ እሴቱም ጥሩ ኣይደለም።

የአማራ ህዝብም ሆነ የሌላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባለፉት ወራቶች ጥያቄውን በግልፅ አስቀምጧል፡፡ ይህም ከተከዜ ማዶ ያለን ቦታ ለጎንደር መመለስን ጨምሮ የህወሃትን የበላይነት፣ ጣልቃ ገብነትና ዝርፊያ ጨርሶ መቆምንም ይጨምራል፡፡ ይህን በመናቅ ግን ጥያቄውን ሳይመልሱ መቅረት በጉልበት መሞከር ሁኔታውን የሚያብስ ሲሆን በሚሊዮን የሚቆጠር ሀይል እንኳ ቢኖራቸሁ ህዝብን ማሸነፍ እንኳን በእውን በህልማችሁ እንኳን ሊሳካላቸውሁ የማይችል ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ዘመን እንዳለፉት 25 አመታት አይደለም። አማራ አሁን ከልሂቅ እስከ ደቂቅ ሁሉንም ያውቃል ። ወቅቱ እጅግ የተለየና ለህዝብ ምቹ የሆነ ሲሆን የፈለገውን ያህል አጋዚ ያሰማራ በመጨረሻ ላይ ግን ዘመኑ የወያኔን ፍፃሜ ማብሰሪያ ዘመን የሚሆን ነው፡፡

ወያኔ እና መሰሎቹ አንድ መገንዘብ ያለባቸው ነገር አለ ። ጥያቄዎች በሰላም መንገድ ካልተፈቱ ስንፋጅና ስንጎዳዳ ኖረን ወያኔ በጉልበት እንደወሰደው ሁሉ ከነወለዱ በጉልበት ይመለሳል ።

ማጠቃለያ
የአማራ ህዝብ ምን ማድረግ አለበት?

1~ የአማራ ህዝብ በታሪክ ታይቶ በማያውቅ ሁኔታ የተጋረጠበትን ችግር ለመፍታት እርስ በእርስ መረጃ እየተለዋወጡ በወንድማማችነት መንፈስ መደራጀት ያስፈልጋል ።አማራ በማንም እንዳይጠቃ እርስ በርስ እየተጠባበቁና እየተከላከሉ ወንድማማችነትን ማዳበር ።

2~ የገበሬውን ነገር አደራ፡፡ ከማንኛውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ በመረጃ እያጠነከሩ በስራው መበርታት ይኖርብታል፡፡
ዛሬ ካልተሰራና ነገ ካልተመረተ ከነገ ወዲያ ችግር ሲፈጠር ህወሃት በእርዳታ መልክ የፖለቲካም ሆነ የኢኮኖሚ ጥገኛ ለማድረግ እንዳትችል ዛሬውኑ ሁሉም በእጃችን ያለና የሚቻል ስለሆነ ሁሉም በያለበት በስራ መበርታት አለበት፡፡ በስራ የሚበረታና ራሱን የሚችል ህዝብ ምን ጊዜም አሸናፊ መሆኑ ታወቆ አርሶ አደሩ በስራው እንድበረታ መርዳት ።

3 ~ሌላው ቁልፍ ነጥብ የአማራ ቲቪ እንደ OMN መቁዋቋም አለበት።
አባቶቻችን ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው ያሉት ትልቅ ስትራቴጂ ነው ።”ህዝቤ እውቀት በማጣት ጠፋ” ይላል ነብዩ ሆሴ።ያማራ ህዝብ የጠፋው እውቀት፣መረጃ፣ በማጣቱ ነው።መረጃ የደምስር ነው።መረጃ የሌለው ማህበረሰብና ከባህር እንደ ወጣ አሳ መጨረሻቸው “ሞት” ነው ። አማራ ለህዝቡ መረጃ የሚሰጠው የራሱ የሆነ ሚዲያ እንደሚያስፈልግ ታውቆ ለተግባራዊነቱ ጥረት ማድረግ ።
ልብ ያለው ልብ ይበል!

Friday, March 10, 2017

በደብረታቦር ከተማ የህወሓት ወታደሮች ተገድለው ተገኙ | ሕወሓት በከተማዋ የጦር መሳሪያ ገፈፋ ሲያደርግ ዋለ. ከናትናኤል መኮንን ደብረታቦር ከተማ

ደብረታቦር ከተማ
ከናትናኤል መኮንን
በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ ቀበሌ 02 ልዩ ስሙ ወይብላ ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ (ወይብላ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ) ከእስር ቤቱ ጀርባ ሁለት ወታደሮች ተገለው ተገኝተዋል ።በማንና እንዴት እንደተገደሉ ሊታወቅ ባይችልም በወታደሩ ውስጥ የነገሰው እርስ በርስ አለመተማመን ለግድያው ቀራቢ ምክንያት ሁኗል።
ወታደሮቹ ተገለው መገኘታቸውን ተከትሎ የካቲት 30 ለመጋቢት 1 /2009 ዓ.ም አጥቢያ ጀምሮ በከተማዋ የሚገኝ በህጋዊ ፍቃድ ያስመዘገቡ ታጣቂወች ጨምሮ ቤት ለቤት ገፈፉ ተጀምሯል። በቴወድሮስ አደባባይ ከቴሌው አጠገብ የሚገኘው አዳራሽ ውስጥ የሚኖሩት ወታደሮች በተለያየ የከተመዋ አቅጣጫ ለፍተሻ ተሰማርተዋል።
በድንገተኛው የመሳሪያ ገፈፉ በቀበሌ 04 ቀበሌ ውስጥ 4 በህጋዊ ፈቃድ ያስመዘገቡ ነዋሪወች መሳሪያ መገፈፉቸው ታውቋል

ዶክተር መረራ የዋስ መብታቸው እንደተከለከለ ሲገለጽላቸው በፍርድ ቤት ይህን ተናገሩ

ዶክተር መረራ የዋስ መብታቸው እንደተከለከለ ሲገለጽላቸው በፍርድ ቤት ይህን ተናገሩ:-
“ 1) ከእነጄኔራል መንግስቱ ንዋይና ጄኔራል ታደሰ ብሩ ዘመን ጀምሮ ከአንድ ትውልድ በላይ ገዳዮችና ሟቾች አሳሪዎችና ታሳሪዎች በበዛበት የሀገራችን የፖለቲካ ድራማ ውስጥ በመቆየት አንድ አንድ ከሆዱ በላይ ለሀገሩ የሚያስብ ምሁር ማድረግ እንዳለበት ሁሉ ከአርባ አምስት አመታት በላይ ለሀገሬ የተሻለ ለውጥ እንዲመጣ በታማኝነት መታገሌ እየታወቀ ወደ ጎን መገፋቱ፡-
2) ለሁላችንም የምትሆንና በእኩልነት የምታስተናግደን ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እንድትፈጠርና ነፃ የፍትህ ሥርዓት በሀገራችን እንዲሰፍን ላለፉት ሃያ አምስት አመታት በመታገሌ መከሰሴ አንሶ የአገሪቱ ፓርላማ አባል የነበርኩ ሰው ለተራ ወንጀለኛ የሚፈቀድ የዋስ መብት በመከልከሌ የተሰማኝ ጥልቅ ሀዘን ለራሴ ብቻ ሳይሆን እኛም ሆን ልጆቻችን በሰላም ይኖሩበታል ለምንለው መከረኛ ሀገራችንና አላልፍለት ብሎ ስታመስ ለሚኖር መከረኛ ሕዝባችን ጭምር መሆኑን እንዲታወቅልኝ ነው፡፡







Wednesday, March 8, 2017

እስከመቼ ሃይለማሪያም በነሳሞራ እየተናቀ ይኖራል ? #ግርማ_ካሳ


የአፍሪካ ኢንተሊጀንስ ጠቅሶ ዘሃበሻ የሚከትለዉን ዘግቧል። አፍሪአ ኢንተሊጄንስ የሚታመን ምንጭ ነው። ኢሕአዴእግ ስልጣን እንደያዘ ገና የአዲስ አበባ ቻርተር ሳይጸድቅ የኢትዮጵያ አወቃቀር ምን እንደምትመስል አፍሪካ ኢንተሊጀንስ ነበር ያወጣው። ብዙም አልቆይም በቻርተሩ ጸደቀ።
 
ይሄ ሜዲያ ብዙዎቻችን ለአንባቢያን ለምሳየት ስንሞክር የነበረውን ነገር ነው በግልጽ ያስቀመጠው። በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለው ሁለት መንግስት ነው። አንደኛው በሃይለማሪያም ደሳለኝ የሚመራው ሲሆን፣ ሁለተኛ በጥቂት ህወሃቶች የሚመራውው፣ ደህንነቱን እና ሰርራዊቱን የሚቆጣጠረውው፣ እነ ኃይለማሪያም የማይታዘዝ ብቻ ሳይሆንን የሚንቅንና መመሪያዎች በጎን እየላከ ዉሳኔያቸውን የሚሰርዝ አካል ነው።
 
እና ሃይለማሪያም የአገር ችግር በድርድር እንዲፈታ ያለው ፖለቲካ እንዲለዝብ የሕዝብ ጥያቄ እንዲፌታ ይፈልግጋሉ። ይህ አሁኡንን ይደረጋል የተባለውንን ድርድር ያመቻቹት እነርሱ ናቸው። ግን የሕወሃቱ ሁለተኛው መንግስት ድርድር የሚባል ነገር አይፈለግም። እያሰረ፣ እየገድደለ፣ እያፈናቀል በጥጋብና በ እርብሪት መግዛት ነው የሚፈለገው። ለዚህ ነው ተቃዋምሚዎች ከድርድሩ እዲወጡ አመራሮችን እያሰረ ያለውና የሚከሰው።
 
ህወሃት ለ547 መቀመጫ 38 ብቻ ነው ድምጽ ያለው። በኢሕአዴግ ዉስጥ ደግሞ አንድ አራተኛ ብቻ ነው መቀመጫ ያለው። ታዲያ እንዴት በዚህ መልክ እየተዋረዱና መሳቂያ እየሆኑ ዝም ብለው ያያሉ ? እስከ መቼ ነው እነዚህ የታሪክ አተላዎችን ይታገሳሉ ? እስከመቼ ነው፣ ግድ የለም ለሌላው አይቁሞ ለራሳቸውና ለክብራቸው እንኳን የማይቆሙት ? እስከ መቼ እነ ሶሞራ እንደ ዉሻ እያዩዋቸው ዝም የሚሉት ?
 
አንድ ጊዜ በብአዴን ጉባዬ አባላቱ “እነርሱ ባልፎቅ ሲሆኑ እኛ ሎተሪ ሻጮች ነው የሆንነው” እያሉ ሲያማረርሩ ነበር። እስከመቼ ነው የሚያማርሩት ?