Friday, September 30, 2016

አቶ እንደሻው እምሻውና ግብረ አበሮቻቸው የሰማያዊ ፓርቲ ንብቶችንና ሰነዶችን በመዝረፍ ተሰውረዋል፡፡



አቶ እንደሻው እምሻውና ግብረ አበሮቻቸው የሰማያዊ ፓርቲ ንብቶችንና ሰነዶችን በመዝረፍ ተሰውረዋል፡፡
የሰማያዊ ፓርቲ የፅ/ቤትና አስተዳደር ኃላፊነትን በሕገወጥነት ይዘው የቆዩት አቶ እንደሻው እምሻው ከግብረ አበሮቻቸው ጋር በመሆን በተለያዩ ጊዚያት የፓርቲውን ንብረት በድብቅ እያወጡ መሆኑ መረጃ የደረሳቸው የፓርቲው ሊቀመንበር ጊዚያዊ የንብረት አጣሪና ተረካቢ ኮሚቴ በማቋቋም የነገሩን እውነትነት እንዲያረጋግጡና ንብረቶቹና ሰነዶቹ ካሉም በቃለ ጉባኤ መዝግበው እንዲረከቡ አዘዋል፡፡ ኃላፊነት የተሰጣቸው አባላት 1ኛ. አቶ እስክንድር ጥላሁን 2ኛ. አቶ ይድነቃቸው አዲስ 3ኛ. አቶ ማቲያስ መኩሪያ 4ኛ. አቶ ቴዎድሮስ አሰፋ በዛሬው ዕለት መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም በፓርቲው ቢሮ በመገኘት ንብረቶች መኖራቸውን ለማረጋገጥ የሚፈልጉ መሆኑን በመግለፅ አቶ እንደሻው እምሻውን እንዲያሳዩአቸው ቢጠይቁም ወደ ፓርቲው ፅ/ቤት አልመጣም በማለት ፈፅሞ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል፡፡
አቶ እንደሻው እምሻው በቅርብ ቀናት ወደ ፓርቲው ፅ/ቤት መጥተው የማያውቁ መሆኑና የፓርቲውን ንብረቶች ያሉበትን ሁኔታ ለማሳየት ፈቃደኛ አለመሆናቸው የኮሚቴ አባላቱን ጥርጣሬ በማሳደጉ ዋና ዋና ሰነዶችና ንብረቶች የሚገኝበት የፓርቲው የፅ/ቤትና አስተዳደር ኃላፊ ቢሮን ከፍተው ባዩበት ወቅት ሰነዶችና ንብረቶች አለመኖራቸውን አረጋግጠው በምስል ቀርፀውና በቃለ ጉባኤ መዝግበው ሪፖርት አድርገዋል፡፡ ይህ ወንጀል መጣራትና በሕግም መጠየቅ ስለሚገባው ለየካ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ መረጃው ተልኮ ተመዝግቧል፡፡ በነገውም ዕለት በጣቢያው በመገኘት ክስ እንዲመሰረት ፓርቲው የሚጠይቅ መሆኑን ኢንጅነር ይልቃል አስረድተዋል፡፡
አቶ እንደሻው እምሻው የፓርቲውን ማሕተም ከፓርቲው ፅ/ቤት አውጥተው በመውሰድ በግል ቤታቸው ያስቀመጡት መሆኑ በመታወቁ ከፓርቲው የተለየ መግለጫ እስከሚሰጥ ድረስ ከዛሬው ዕለት ጀምሮ በዚህ የፓርቲው ማህተም ተደርጎባቸው የሚወጡ ማንኛውም ሰነዶች ፓርቲውን የማይወክሉ መሆኑንና በፓርቲው ማህተም ሰነዶችን የሚያሰራጩ አካለት በህግ የሚያስጠይቃቸው መሆኑን አውቀው ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

No comments:

Post a Comment