Monday, September 5, 2016

በቂእየተዋከቡ ሲሆን እስረኞች ዝዋይ መድረሳቸው ታውቋል። የኣማራው ሕዝብ ዛሬም ለወያኔ ኣልቀመስ ብሏል።ሊንጦ የእስረኞች ቤተሰቦች በወያኔ ፖሊሶች



በቂሊንጦ የእስረኞች ቤተሰቦች በወያኔ ፖሊሶች እየተዋከቡ ሲሆን እስረኞች ዝዋይ መድረሳቸው ታውቋል። የኣማራው ሕዝብ ዛሬም ለወያኔ ኣልቀመስ ብሏል። #MinilikSalsawi
Minilik Salsawi – mereja.com ኣዲስ ኣበባ በፖሊሶችና ወታደሮች የተወረረች ሲሆን የክልሉ ፖሊሶችና ሚሊሻዎች መሳሪያ እንዲያስረክቡ ተደርጎ የጎማ ዱላ ታጥቀዋል።በቂሊንጦ የእስረኞች ቤተሰቦች በወያኔ ፖሊሶች እየተዋከቡ ሲሆን እስረኞች ዝዋይ መድረሳቸው ታውቋል። ባለው መረጃ መሰረት የእስረኛ ቤተሰቦች ጉዳዩን ለማጣራት እንዳይገኙ ወደ ቂሊንጦ የሚወስዱ መንገዶች ቢዘጉም ሕዝቡ ባገኝው መስመር ወደ እስር ቤቱ ለመድረስ የሞከረ ሲሆን የወያኔ ፖሊሶች የእስረኞች ቤተሰቦችን ሲያንገላቱና ሲያዋክቡ ሲደበድቡ ሲያባርሩ ተስተውሏል ይህ በእንዲህ እንዳለ በ30 መኪና ሙሉ እስረኞች ከቂሊንጦ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ግቢ ከ40 ደቂቃ በፊት ገብተዋል። ማንነታቸውን ለማወቅ አልተቻለም። ዝዋይ እስረኞችን ጥየቃ የሄዱ ቤተሰቦች ከወትሮው አርፍደው ነበር ለመጠየቅ የገቡት። አርፍደው ገብተውም ቶሎ እንዲወጡ ነው የተደረገው።መረጃዎች ከዝዋይ ተገኝተዋል።
የኣማራው ሕዝብ ዛሬም ለወያኔ ኣልቀመስ ብሏል።ሸዋ መሳሪያዬን ልወልውልበት ኣትነካኩኝ የመጨረሻ ሰኣት ላይ ነኝ ሲል በመናገር ላይ ሲሆን ወያኔ በቄሶችና እና በኣገር ሺማግሌዎች ወጣቱን በመንዝ በይፋት በምንጃር በመርሃቢቴ በደብረብርሃን እና በኦሮሚያ ኣማራ ወሰን ላይ የሚኖሩትን በማስለመን ላይ መሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ። በሸዋሮቢት ዘልቀው የገቡ የኣማራ ታጣቂዎች ኣሉ በሚል ስጋት የወያኔ ሰራዊት በፒካፕ ላይ መትረየሱን ጠምዶ ከተማዋን የጦርነት ቀጠና ኣስመስልዋታል።
በተለያዩ የኣማራ ኣከባቢዎች ተቃውሞ የቀጠለ ሲሆን በኣርማጮ ስብሰባ ላይ የነበሩት ገዱ ኣንዳርጋቸውን የቁም እስረኛ መሆናቸውን ተሰብሳቢዎች የነገሯቸው ሲሆን በፍጹም ሽንገላ ኣንፈልግም ነጻነት ፈላጊ ነን ሲሉ በመግለጽ ሕወሓት ወደ ክልላችን እንዳትመጣ መጥፊያዋ ደርሷል ሲሉ የኣርማጮ ጀግኖች ገልጸዋል፥፥ በጎጃም ኣሁንም ሕዝቡ ጥርሱን ነቅሶ መስራት ያለበትን በመምከር ላይ ይገኛል በወሎ ክፍለሃገር የደሴ ከተማ በዛሬው እለት በቤት ውስጥ የመቀመጥ አድማን በሁሉም ንግድ ድርጅቶች ላይ በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል ሆኖም ግን ህዝብን በመናቅ ለህዝብ ደንታ የሌላቸው አንዳንድ ድርጅቶች አሁንም አግልግሎት እየሰጡ መሆኑ ታውቋል።እነዚህ ከዚህ በታች ያሉት ድርጅቶች የህውሀት ተላላኪና ስግብግብ ነጋዴዎች በአማራንና በኦሮሞ ህዝብ ላይ እየፈሰሰ ያለውን
ደም ደጋፊዎች መሆናቸውን አመላካች ነው
1: ግሸን ወርቅ ቤት
2:ስታር ወርቅ ቤት
3:ወልዴ ወርቅ ቤት
4: ቴዲ ሲሊቨር
5:አባይ ካፌ
6: ፒያሳ ካፌ
7: ወሎ ሻይ ቤት
8:አዲስ ዘመን ሆቴል
9:ሜል ቦርን ሆቴል
10:ታይም ሆቴል
11:ጂጂ ባርና ሬስቶራንት
በጋራጅ በቤተ ክርስቲያንና በተለያዩ የኮንደሚኒየም የመኪና ማቆሚያንና የመኪና እጥበት በሚደረግባቸው አካባቢ ፖሊስ በመሄድ እንዲታስነሱና ስራ እንዲሰሩ እያስጠነቀቁ ሲሆን ባለቤት ያልተገኘውን ደግሞ ታርጋ ሲፈቱ አርፍደዋል። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

No comments:

Post a Comment