Friday, September 16, 2016

በኢህአዴግ የተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መደረክ የዝምታ አመፅ ውጦታል፡፡



Bilderesultat for eprdf






የከፍተኛ ትምህርት ተቃማት መምህራን እና ሰራተኞች ኢህአዴግ ይታደስ ከምትሉን ይፍረስ እያሉ ነው፡፡
ኦህአዴግ በዚህ በከፍተኛ ትምህርት አመፁ እንዳይቀጥል ለመከላከል መሰረት ያደረገ ቢሆንም መምህራኑ የምትፈሩት አመጽ በትምህርት ቤቶችም ይቀጥላሉ ሲሉ እያስጠነቀቁ ነው፡
በኢህአዴግ የተዘጋጀው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መደረክ የዝምታ አመፅ ውጦታል፡፡
መድረኩ የኢህአዴግ የሩብ ምዕተ ዓመት የ25 ዓመታት ጉዞ የዳሰሰ እና የትምህርት ልማት ሰራዊት እና ጥራት ላይ በማተኮር በሂስ እና ግለሂስ የሚጠናቀቅ ሲሆን ፤ ኢህአዴግ በከፍተኛ ሁኔታ የተቃውሞ እና የዝምታ አመፅ አመፅ እንደገጠመው የትላልንተ ውሎው አመልክቷል፡፡ ከባህር ዳር ፤ ጎንደር ፤ ደሴ ፤ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲዎች በቦርድ አመራሮች እና በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት የተሰጠውን ትንታኔ ተንትርሶ ለውይይት ቢጋበዙም የባህር ዳር ዩኒቨርስቲ መምህራናን እና ሰራተኞች ለውጥ ለማያመጣ መንግስት ሃሳባችንን አንሰጥም ላለፉት ሶስት አመታት አወያይቶናል፡፡ የቀየረው የለም እኛም ከሚገድለን መንግስት ጋር ምንም ንግግር የለንም በማለት ትላንት ከስዓት በኃላ የነበሩ የውይይት መድረኮች በዝምታ አመፅ የተሸበቡ ሰው አልባ መድረኮችን አሰተናግደዋል፡፡

በተቃራኒው በደብረ ማርቆስ እና ደሴ ዩኒቨርስቲዎች ደብረታቦርን ጨምሮ አማራ ላይ ጦርነት ያወጀ መንግስት ጋር መነጋገር እሻም ኢህአዴግ የሚያስራቸው እና የሚገድላቸው ወንድሞቻችንን አይተን ከእናንተ ጋር ካበርን እኛ ምንድነን፡፡ ኢህአዴግ ላለፉት 25 ዓመታት ተኝቷል እኛም ችለነዋል አሁን ግን በቅቶናል የምትፈሩት አመፅ በእርገጠኝነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መቀስቀሱ አይቀርም ብለዋል፡፡


No comments:

Post a Comment