Wednesday, November 30, 2016

ዶ/ር መረራ ጉዲና ከአውሮፓ አዲስ አበባ ሲገቡ መታሰራቸው ታወቀ

  


merera-1
ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ ፕሬዚደንት ዶ/ር መረራ ጉዲና
የአይን ምስክሮች እንደገለጹት ዶ/ር መረራ ጉዲና በቁጥጥር ስር የዋሉት በምን እንደሆነ የታወቀ ነገር ባይኖርም፣ የህወሃት መገናኛ ብዙሃን ዶር መረራ እንዲታሰሩ ሰሞኑን በቅስቀሳ ላይ እንደነበሩ ታውቋል። በአውሮፓ ህብረት ግብዣ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ላይ ምስክርነት ለመስጠት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና ከአትሌት ፈይሳ ለሊሳ ጋር ብራሰልስ የተገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ጥሰዋል የሚል ቅስቀሳ ሲደረግባቸው ቆይቷል። ለዚህም ይቀርብ የነበረው ምክንያት ከፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጋር በአንድ መድረክ መገናኘታቸውና ጎን ለጎን መቀመጣቸው መሆኑን መረዳት ተችሏል። ዶ/ር መረራ ጉዲና አውሮፓ የተጋበዙትም በአንድ መድረክ የተገኙትም በአውሮፓ ፓርላማ ግብዣ ሆኖ ሳለ፣ በጉዳዩ ተጠያቂ መደረጋቸውና በዚህም መወንጀላቸው አነጋጋሪ ሆኗል። ዶ/ር መረራ ጉዲናን የያዟቸው ወገኖች ወዴት እንደወሰዷቸው ይህ ዘገባ እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ የታወቀ ነገር የለም። ዶ/ር መረራ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት ምስክርነት መንግስትን አለማስደሰቱን ለማወቅ ተችሏል። ምንጭ፦ ኢሳት

No comments:

Post a Comment