Saturday, November 5, 2016

መንግስታዊ ኣሸባሪውን ቴድሮስ ኣድሃኖምን የምንቃወመው በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው።Minilik Salsawi

መንግስታዊ ኣሸባሪውን ቴድሮስ ኣድሃኖምን የምንቃወመው በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው።
Image may contain: one or more people

 – ቴድሮስ አድሃኖም የአምባገነኖች ቁንጮ የደም መጣጦች አውራ ለ አለም የጤና ድርጅት ወንበር መንበር ለመሆን እየተወዳደረ ያለው የሕወሓት ዘረኞች ቁንጮ የሆነው ቴድሮስ ኣድሃኖም በተመለከተ ተቃውሞዎች በርትተው ቀጥለዋል።ግለሰቡ በመጀመሪያ ደረጃ ለቦታው የማይመጥን ሰው ነው።ያለው የትምህርት ደረጃ ለመወዳደር ደፍሮ የሃገርን ገንዘብ ለጉቦ የሚያፈስበት መንገድ እጅግ ኣደገኛ ነው።ዋናው ነጥብ ይግ ግለሰብ የኣምባገነኖች የገዳዮች የደም መጣጮች ዋናው ኣባልና ኣስተባባሪ የነበረ ግለሰብ ሲሆን ዘርን ኔትወክ ኣድርገው ጥቅም ካካበቱ ዘራፊዎችም ኣንዱ ነው።
ቴድሮስ ኣድሃኖም በተመለከተ ሁለት የማጭበርበሪያ ምላሶች ከሁለት ወገን እየተዘረጋጉ ይገኛሉ ኣንደኛው ወገን በጦፈ የጎሳ ፖለቲካ ጣዖት ኣምላኪ የሆኑ ዘረኞች ግለሰቡ ትግሬ በመሆኑ ብቻ ተቃውሞ በዛበት ሲሉ ሌሎች ለዘብተኛ መሳይ ኣስመሳዮች ደግሞ በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ተሸሽገው ሕዝብን ለማታለል ይሞክራሉ። እነዚህ ሁለቱም ወገኖች በፍጹም ከእውነት የራቁ መሆናቸው በገሃድ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተደረገ ያለው መንግስታዊ ኣሸባሪነት ይመሰክራል። ቴድሮስ ኣድሃኖም ላይ እየቀረበ ያለው ተቃውሞ ትግሬ ስለሆነ ኣሊያም ከመልካም ገጽታ ሃገራዊ እደምታ ጋር በተያያዘ ኣይደለም።
ግለሰቡ ለኣለም ጤና ድርጅት መወዳደር የለበትም የሚለው ተቃውሞ የሚነሳው ግለሰቡ ከሕወሓት ኣመራሮች ኣንዱ በመሆኑ ሲሆን ሕወሓት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚፈጽመው የሰብዓዊ መብት ጥሰት እጅግ ኣደገኛ ከመሆኑም በላይ የገዳይ የኣፋኝ የእስር እና የኣሳዳጆች ቡድን ነው ግለሰቡ ደግሞ የዚህ ኣደገኛ መንግስታዊ ኣሸባሪ ማፍያ ቡድን ኣባል ነው፤ ግለሰቡ የጤና ጥበቃ ሚንስትር በነበረበት ወቅት በከፍተኛ ሙስና የተዘፈቀ ካለሙያው ስልጣን ላይ የተቀመተ ነበር። በዚህ ሰሞን ብቻ የሚሰራቸው ስራዎች በየሚዲያውና በየስብሰባው የሚያደርጋቸው ተግባራት ሃገርን ወክሎ ለመወዳደር ኣይደለም በቦታው ላይ ለመወዳደር መቅረቡ ራሱ ኣሳፋሪ ከመሆኑም በላይ ለቦታው የማይመጥን ግለሰብ ነው።
ግለሰቡ ወደፊት የኢትዮጵያ ሕዝብ ነጻነቱን በሚያረጋግጥበት ወቅት በወንጀል የሚፈለግ በዘር ማጥፋት የሚከሰስ ግለሰብ ነው።ቴድሮስ ኣድሃኖም ለመወዳደር ብቁ ነው ተብሎ በወያኔ ኣገዛዝ የተላከው የስርዓቱ ኣመራር ስለሆነ እንጂ ኢትዮጵያን ወክለው ለመወዳደር የሚችሉ በቂ እውቀት ያላቸው የጤና ዶክተሮች ሞልተዋል፤ ይህ ግለሰብ በሃገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ እና በኣፍ መፍቻው ቋንቋ ስለሚያፍር ብቻ እንግሊዘኛን የሃገሩ ቋንቋ ኣድርጎ ቢናገርም ለተጠየቀው ጥያቋ በቂ መልስ መስጣት ካለመቻሉም በላይ ጥያቄዎች ደጋግሙልኝ ኣልገባኝም በማለት ሲደናበር ተስተውሏል። https://youtu.be/Aql-s_GjTKU የሃገሪቱን ሃብት ለሎቢ በመጠቀም ከፍተኛ ገንዘብ ድምጽ ለመግዛት በመክፈል ኢትዮጵያን ኪሳራ ላይ ጥሏታል። ይህ ግለሰብ ኢትዮጵያን በማዋረድ ስራ ላይ ስለተሰማራ በጋራ ተረባርበን ለኣለም ልናጋልጠው ይገባል። መንግስታዊ ኣሸባሪውን ቴድሮስ ኣድሃኖምን የምንቃወመው በኢትዮጵያውያን ላይ በፈጸመው ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው። #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment