Wednesday, November 23, 2016

የጎሳ ፖለቲካ የዘረኝነት አስፋፊ የሆነውን አካል ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል።Minilik Salsawi



Image may contain: text
የጎሳ ፖለቲካ የዘረኝነት አስፋፊ የሆነውን አካል ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል።
Minilik Salsawi – mereja.com – ከላይ ቅርንጫፉን ስትለመልሙት እንደገና ማቆጥቆጡ ኣይቀርም። የለውጥ ሃይሉ ችግር በጉያው ያሉትን የዘር ፖለቲከኞች መዋጋት ያልቻለው ምክንያቱ የችግሩ የጎሳ ፖለቲካው ምንጭ የሆነውን ወያኔን ክፍተት እየሰጠው ስለሚያግዘው ነው። ካሁን ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ሃገር ወዳድ የሆኑ ኢትዮጵያውያን የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ በቀደደላቸው ቦይ መፍሰስ ችለዋል። ከመሰዳደብ ከማንጓጠጥና ከመፈራረጃችን በፊት ራሳችንን እንመርምር!!!
ሊጠራ የሚገባው ኣለ የሚባለው የለውጥ ሩጫ የአደፍራሾች የስግብግቦች የሐሰተኞች የድብብቆሽ ፖለቲካ መሆኑ ሲሆን ሌላው ደግሞ አውቅልሃለሁ የሚሉ ኣካላት በአንድነት ሃይሉ ውስጥ እንደ አሸን መፍላታቸው የብሄር ፖለቲካው እንዲቀድም በር ከፍቷል። የጎሳ ፖለቲካው ዋና ምንጭ ሕወሓት ነው። ሕወሓትን ከስሩ መንግሎ ማፍረስ እስካልተቻለ ድረስ በአሁኑ ወቅት የምንመለከታቸው ኣስቀያሚ የፖለቲካ ሂደቶች ተስፋፍተው ይቀጥላሉ። በአሁኑ ወቅት በተለይ በዲያስፖራው ዘንድ የሚራመደው የጎሳ ፖለቲካ የሚመሩት እንዲሁም ትግሉ ሞተ ትግሉ ተነሳ እያሉ የሚዘባርቁት ይብልጡኑ ከወያኔ ጋር ጥቅመኞች የነበሩ የሆኑና የሚሆኑ ግለሰቦችና ከባቢዎቻቸው መሆናቸውን ስናስብ ልንነቃ ይገባል።
የተቃዋሚው\የለውጥ ሃይሉ የፈለገው ፕሮፓጋንዳ አሳሳቢ አይደለም። የፖለቲካ ድርጅቶችና የግለሰቦች ጉዳይ ኣስፈላጊ ኣይደለም። እያጠሩ መሄድም የሚቻለው በጋራ አጀንዳ ላይ የተመሰረተ የጋራ ጠላትን የማጥፋት ስራ ሲሰራ ብቻ ነው። ሌላው ይደረስበታል ዝም ብለን ወያኔን እንታገል የሚል መርሕ አልባነት ምንም ስለማይፈይድ ሁሉን ሊያሰባስብ የሚችል ስራ ሊሰራ ይገባል።ካልሆነ ትግሉ በስድብና በሹፈት ታጅቦ ሁልግዜ ሆያሆዬ እንደሆነ ይቀጥላል። ካለምንም መዘናጋት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ቢኖር በየቦታው የሚፈሉትን የጎሳና የመንደር ድርጅቶችና ግለሰቦች ከመዋጋት ይልቅ የጎሳ ፖለቲካ የዘረኝነት አስፋፊ የሆነውን አካል ሕወሓትን ከምንጩ ማድረቅ ያስፈልጋል። ከመሰዳደብ ከማንጓጠጥና ከመፈራረጃችን በፊት ራሳችንን እንመርምር!!! #ምንሊክሳልሳዊ

No comments:

Post a Comment