Monday, November 21, 2016

ግንቦት ሰባት ያለመጠየቅ ህግን አዳብሯል ። ተከታዮቹ የመጠየቅ መብት የላቸውም ! ( ኄኖክ የሺጥላ )


ግንቦት ሰባት ያለመጠየቅ ህግን አዳብሯል ። ተከታዮቹ የመጠየቅ መብት የላቸውም ! ( ኄኖክ የሺጥላ )
ወያኔ ትግሬ ያለመጠየቅ መብትን ህጋዊ አድርጎ የሚንቀሳቀስ ቡድን ነው ። ህዝቡ የመናገር እና የመጠየቅ መብት እንደሌለው ወያኔ ትግሬ በሚያደርገው ነገሮች ሁሉ አሳይቷል። የመ-ፈራት ህግን አጥቷል ። በዚህም ህዝብ ለረጅም ጊዜ ይፈራው ነበር። ጥቂት ደፋሮች ቆርጠው ተነሱ ! የመለስ አምልኮ ብለው ፃፉ! ፊት ለፊት ተጋፈጡት! በመሳሪያ ሳይሆን በሃሳብ ። እስክንድር ጥይት ተኩሶ አይደለም የታሰረው ። የእስክንድር ጥይቱ ብዕሩ ነው ። ተመስገን ወታደር አቁሞ አይደለም የተፋለመው ! የተመስገን ጦሩ ሃሳቡ ነው። አንዷለም በርሃ ስለገባ አይደለም ለወያኔ ጭንቀት የሆነው ፥ የአንዷለም መልዕክቱ ግን ከቦንብ በላይ ወያኔን አቁስሎታል ። ስለዚህ ሃሳብን የሚፈራው ወያኔ ሃሳብን እያሳደደ ያስር ጀምር ።ሃሳብ እና የማሰብ ነፃነት ለዘላለም ይኖራል ወያኔ ግን አይቀጥልም ይወድቃል ! ውድቀት አንድ
ግንቦት ሰባት ያለመጠየቅ ህግን አዳብሯል ። ተከታዮቹ የመጠየቅ መብት የላቸውም ! ሃሳብ ማንሸራሸር ነውር ነው ። ለምን ማለት ክልክል ነው ! ዝም ብለህ ተከተል! ይህ የግንቦት ሰባት ህግ ነው ! እኛ ስራውን እንሰራለን ፥ አንተ ግን ስለምንም ነገር የማወቅ መብት የለህም! ከተከተልህ ትከተላለህ ! እጠይቃለው ፥ አውቃለው ካልህ ገደል ትገባለህ ! በጥያቄ እና በግንቦት ሰባት መሃከል የቻይናን ግንብ የሚያህል ትልቅ ጥርብ ድንጋይ አለ ። ከተወያየህም የምትወያየው ሰላማያወያይ ነገር ነው ። ይህንን ህግ ያፈረሰ በአድማ እንዳይሆኑ ተደርጎ ይዘለፋል! ይወረፋል ! በፍጥነት ከሰውነት ወደ እንስሳነት ( ወያኔነት ) ይሸጋገራል ! ሃሳቡን ከመረዳት ስሙን ማጥፋት ቀላሉ መንገድ ይሆናል ። ይህንንም ሲያደርጉ ለሌሎች ተከታዮቻቸው መቀጣጫም እንደሚሆን እያሳዩ ነው ። የመፈራት ህግን ልክ እንደ ወያኔ እያፀደቁ ነው ። ትዕቢት ነው ! ውድቀት ሁለት!
ኄኖክ የሺጥላ

1 comment:

  1. በሄኖክ ስም የሚጽፍ ወየኔ መጥቶ መሆን አለበት እንጂ መቼም ሄኖክ የዚህ አይነት አሪትቡርቲ በመክተብ እድሜውን ያባክናል ብዬ ማሰብ ይከብደኛል። የሰማይ ርቀቱን የውቅያኖስ ጥልቀቱን ያክል እወደዋለሁ እያለ ሲያሞካሸው የነበረውን ስብስብ ዛሬ እንዲህ ስብስብ አድርጎ በአንድ ጆንያ በመክተት ወደ ገደል ልወርውር ማለት እንዴት እውነት ነው ብሎ ማመን ይቻልላ? ትናንት ተሳስቼ ነበር ከድርጅቱና ከመሪው ጋር ፍቅር የያዘኝ ከሆነ ደግሞ ምላሹ ትናንት የነገን ለመገመት ያግዛልና የትናንቱ ፍቅር ሙገሳ በስህተት ከሆነ የዛሬውስ ጥላቻና ወቀሳ ስህተት አይደለም ለማለት እንዴት ይቻል ይሆን? እረንእሺቴ እኔ ይህን አላልኩም ይለናል ብዬ በተስፋ እጠብቃለሁ።

    ReplyDelete