Thursday, November 10, 2016

በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ ተገድለዋል፤Muluken Tesfaw



ከትናንት ጀምሮ በተደረገ ውጊያ በወገራ 50 ወታደሮች ሲማረኩ ቁጥራቸው የበዛ ደግሞ ተገድለዋል፤ Muluken Tesfaw
በሰሜን ጎንደር ዞን በወገራ ወረዳ የእንቃሽ ቀበሌ የዐማራ ገበሬዎችን ትጥቅ ለመንጠቅ የተንቀሳቀሰው የወያኔ ጦር ሙሉ በሙሉ በምርኮና በሞት ተደምስሷል፡፡ ከቦታው በስልክ ያነጋገርናቸው የጎበዝ አለቆች ‹‹ሆን ብለው አዝመራችን በምንሸክፍበት በዚህ ወቅት መሣሪያ ለመግፈፍ መጡብን፤ እኛም ገጥመን ፈጀናቸው›› ብለዋል፡፡ ከትናንት ጥቅምት 30 ቀን 2008 ዓ.ም. ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ሌሊቱን ባደረው ጦርነት 50 የሚሆኑ ወታደሮች ከነሙሉ ትጥቃቸው ተማርከዋል፡፡ ሁለት መትረጊስ፣ አንድ ስናይፐርና ጥቂት የሬዲዮ መገናኛዎችም አብረው ተማርከዋል፡፡
የተገደሉ ወታደሮችን በተመለከተ ላቀረብንላቸው ጥያቄ ‹‹እስከ ምሽት ድረስ የተገደሉት ከ20 በላይ ነበሩ፤ ሌሊቱን ወታደሩ በየቦታው ተፈንድሷል፤ የተገደለው ወታደር ትክክለኛ ቁጥር ለማወቅ ከመሸግንበት ወጥተን በየቦታው የወዳደቀውን አስከሬን መቁጠር ይጠበቅብናል፤ ሆኖም ግን ከማረክናቸው ወታደሮች በእጥፍ ይበልጣል›› በማለት አብራርተዋል፡፡
ራሳቸውን ለመከላከል ባደረጉት ጦርነት ከጎበዝ አለቆች መካከል የሆኑት አቶ ፈንቴ አየልኝ ዛሬ ሌሊቱን ተሰውተዋል፡፡ አቶ ፈንቴ በጠላት ቀጠና ዘለው በመግባት በርካታ ወታደሮችን ካጋደሙ በኋላ መሞታቸው በጓዶቻቸው ዘንድ ቁጭትና እልህ ፈጥሯል፡፡ የጎበዝ አለቆች በአምባ ጊወርጊስ እና በአርማጭሆ አካባቢ ያሉ የዐማራ የጎበዝ አለቃዎች በአስቸኳይ እንዲደርሱላቸውና ትግላቸውንም እንዲያግዙ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ‹‹እኛ ስለሰላም ስንል ነው እንጅ እንኳን ወገራን ድፍን ዐማራን ነጻ ማድረግ አያቅተንም፤ ግን በየአካባቢው ያለው ገበሬ አሁንኑ ይቀላቀላቀለን፤ መንገድ በመዝጋት ወደእኛ የሚመጣውን ወታደር የስቁም ወይም ከእኛ ጋር ይጨመረን፡፡ ይህም በአስቸኳይ መሆን አለበት›› በማለት አብራርተዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ በተለያዩ አካባቢዎች በተለይም በአርማጭሆ፣ በወልቃይት፣ ወገራ፣ ጎንደር፣ ባሕር ዳር፣ ጢስ ዓባይና መራዊ በመሳሰሉ ቦታዎች ወያኔዎች ታካሚ በመምሰል ወደ ሆስፒታሎች ቆስለው የመጡ ገበሬዎችን ለመያዝ በየህክምና ጣቢያዎች መሰማራታቸውን ጥቆማዎች እየመጡ ነው፡፡ ስለሆነም ወደ ሕክምና ተቋማት የሚሔዱ ቁስለኞች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸው ጥቆማውን የሰጡ አካላት አሳስበዋል፡፡
በተያያዘ ዜና በየቦታው የሚታሠሩ ወጣቶች ቁጥራቸው እየጨመረ ሲሆን እንደ ወገራና ጢሳ ዓባይ ወጣቶች ፊትለፊት በመግጠም አገዛዙን እንዲያሽመደምዱት አንዳንድ የጎበዝ አለቆች አሳስበዋል፡፡
(ማሳሰቢያ፤ በየቦታው ያሉ የጎበዝ አለቆች ለወገራ ገበሬዎች እገዛ እንዲልኩላቸው መረጃውን በማሰራጨት እንተባበር)

No comments:

Post a Comment