Wednesday, November 9, 2016

የባሕርዳር ሕዝባዊ ትግል ተጋድሎ የ ኢወተን እና የ አሕን ቅስቀሳ . ቆንጅት ስጦታው  



የባሕርዳር ሕዝባዊ ትግል ተጋድሎ
የ ኢወተን እና የ አሕን ቅስቀሳ
==================
ጥቅምት 26 ለ 27 አጥቢያ በሁለት ተባባሪ ድርጅቶች ማለትም በ “አማራ ሕዝብ ንቅናቄ (አ.ሕ.ን)” እና በ “የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋድሎ ንቅናቄ (ኢ.ወ.ተ.ን) በጋራ በባህርዳር ቀበሌወች እና ኩታ ገጠም አጎራባች ቀጠናወች የቅስቀሳ ወረቀት ሲበተን አድሯል። በነጋታው በየአካባቢወች ነዋሪ የሆነው ሕዝብ የተበተነውን የቅስቀሳ ወረቀት ለማንበብ እና ለማስተላለፍ ተችሏል። እንደሚታወቀው ወያኔ በጥድፊያ ባወጀችው ወታደራዊ አዋጅ፤ ዜጎች ኢንተርኔት አገልግሎት እንዳያገኙ፣ የማህበራዊ ገጾችን እንዳይጠቀሙ በመፈለግ የወሰደቻቸው እርምጃወች ምንም የሕዝብን ድካም እና መከራ ቢጨምርበትም ትግሉን ግን እየገታችው እንዳለሆነ የገለጸው ይህ የቅስቀሳ ሊፍሌት፤ ትግሉ እስከ ድል የሚቀጥል መሆኑን እና በሁለቱ ድርጅቶ ማለትም በ አ.ሕ.ን እና ኢ.ወ.ተ.ን መካከል የትብብር እና በአንድነት የአማራ ተጋድሎ ቀጣይነቱን፣ ለጋራ ነጻነት በጋራ መሰዋት የሚያስፈልግ መሆኑን አብስሯል። በዚህ የተበተነ ሊፍሌት የኢትዮጵያ ወጣቶች ተጋድሎ ከአማራ ሕዝብ ንቅናቄ ጋር በመሆን በአለፉት ቀናት መጠነ ሰፊ የሆነ እስከ አፍጢሙ የታጠቀውን የጠባቧ የወያኔ አጋዚ እና መደበኛ ጦር በየቀየው ሲያራውጡት እንደሰነበቱም በተከታታይ በወጡ ዜናወች አሳውቀዋል። ወልቃይት የአማራ ነው!!! በሚል መፈክር የታጀበው ይህ የቅስቀሳ እና ትብብርን በተጨባጭ በትግሉ አውድማ ያሳየን ጽሁፍ በእውነትም እየታገሉ መሰዋትን ገሎ መሞትን ለነጻነት ሲባል የሚከፈል ከባድ ዋጋ በጸጋ የሚቀበል መሆኑን የሁለቱ ታጋይ ንቅናቄወች አስነብበውናል።
አይጥ በበላ ዳዋ ተመታ እንዲሉ ከዘመን ዘመን ለአገር መሞትን፣ ለአገር ዘብ መቆምን እንጅ አገር እኔ ልግዛ ብሎ በብቸኝነትም አገር ገዝቶ የማያውቅ ሕዝብ በትምክህት ሲፈረጅ እንደኖረ የምናውቀው ሲሆን። ወያኔዋ ዛሬም ድረስ ይህን ሕዝብ በዋና ጠላትነት ፈርጃ የዘመተችበት ቢሆንም ታጋይ ልጆቹ በቃን አንገዛም። ዘራችንን ከማጥፋት እናድን በሚል በጎበዝ አለቃ ተደራጅተው መታገልን፣ ታግሎ መሞትንም እያደረጉት ነው። ምንም ቢሆን የዚህ የጀግና ሕዝብ ትግል ግቡን እንዲመታ ሳይታለም የተፈታ በመሆኑ ሕወሐት እና ባንዳ ተከታዮቿ የግዜ ጉዳይ እንጅ የመጨረሻዋን የችንፈት ጽዋ የሚጎነጩበት እሩቅ እንደማይሆን በእርግጥ እንናገራለን።
ድል ለተገፋው ሕዝብ!!!
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

No comments:

Post a Comment