Tuesday, November 29, 2016

ልዩ ልዩ ዜናዎች – Finote Democracy- EPRP Radio – ፍካሬ ዜና ምኒሊክ ሳልሳዊ



ልዩ ልዩ ዜናዎች – – Finote Democracy- EPRP Radio – ፍካሬ ዜና
 ኢትዮጵያ ከአምስት አመት በታች የሆኑ ህፃናት በተለያዩ በሽታዎች ከሚቀጠፉባቸው ሀገራት ግንባር ቀደምትነቱን መያዟ ታወቀ፡፡ ከሰላሳ ከመቶ በላይ የሚሆኑ ህፃናት የሚሞቱት በተቅማጥና በሳምባ ምች መሆኑም ተነግሯል፡፡ ወያኔ በየጊዜው የህፃናትና የእናቶች ሞትን መቀነስ መቻሉን ቢያቀርብም ሐቁ ግን በወሊድ የሚሞቱ ህፃናት ቁጥር በእጅጉ የጨመረ መሆኑንና ስድስተኛ ልደተቻውን ሳያከብሩ በሞት የሚነጠቁ ሕፃናትም ቁጥር እየናረ በመሄድ ላይ
እንደሆነ ታውቋል፡፡
 የተለያዩ የነዳጅ ምርቶች ማለትም ቤንዚን፣ ናፍጣ፣ የአውሮፕላን ነዳጅና ጋዝ በማቅረብ በኩል ግዙፍ መሆኑ የሚነገርለት የቻይናው ፔትሮቻይና የተባለ ኩባንያ ለመጀመሪያ ጊዜ ጨረታ ማሸነፉ በይፋ ተነገረ፡፡ ይህ በዓለም ግዙፍ ከሆኑት አስሩ ነዳጅ አቅራቢ ኩባንያዎች አንዱ የሆነው ድርጅት ከአመታት በፊት ይህንን እድል ለማግኘት ከወያኔ ቁንጮዎች ጋር ውስጥ ውስጡን ይሠራ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርብ የሆኑ ወገኖች ያስረዳሉ፡፡ ይህ ኩባንያ እስካሁን ነዳጅ ያቀርብ የነበረውን ቪቶል ኦይል የተባለን የባህሬን ኩባንያ ገፍተሮ መግባቱ ቻይናና ወያኔ እጅና ጓንት መሆናቸውን የሚያሳይ እንደሆነ የፖለቲካ አዋቂዎች ያስረዳሉ፡፡
 በአማራ ህዝብ ላይ የተጫነው ብአዴን የተባለው የ ወያኔ ቡድን፣ ተከስቶ የነበረውን ሕዝባዊ አመጽ በማጣጣል ለወልቃይት ጥያቄ የተድበሰበሰ ምላሽ በመስጠት በመጠናቀቁ ሕዝቡን ክፉኛ ያበሳጨና ጥርሱን ያስነከሰ መሆኑ ታወቀ፡፡ የወልቃይት ሕዝብ ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው በማንም ወገን ሳይሆን በወልቃይትና በጎንደር ሕዝብ፣ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ሕዝብ ሆኖ ሳለ የአማራ ፕሬዚደንት ተብየው ገዱ አንዳርጋቸው ይህ ጥያቄ ሊፈታ የሚችለው በትግራይ ገዥዎች ብቻ እንደሆነ መናገሩ ሕዝቡ እያካሄደ ላለው ሕዝባዊ አመጽ ነዳጅ ሆኖ እንሚያቀጣጥለው ለማወቅ ችለናል፡፡ በጎንደር በተለያዩ አካባቢዎች ሕዝቡ በጎበዝ አለቆች እየተመራ ከወያኔ ነፍሰ-ገዳዮች ጋር ፍልሚውን እያደረገ እንደሚገኝ ከተለያዩ አቅጣጫዎች ከሚደርሱን ዜናዎች መገንዘብ ተችሏል፡፡
 በቅሊንጦ እስር ቤት እሳት አያይዛችኋል የተባሉ 38 እስረኞች ክስ የተመሰረተባቸው መሆኑ ተነግሯል። በክሳቸው ውስጥ ከተዘረዘሩት ጉዳዮች መካከል አመጽ ማስነሳት፤ የአሸባሪ ድርጅቶች አባሎች በመሆን ሌሎች ሰዎችን መመልመል የሚሉት የተጠቀሱ ሲሆን እሳቱ ከመነሳቱ በፊትም ያልተግባቧቸውን ሰዎች ይደበድቡ እንደነበር ተጠቅሷል። በቅሊንጦ የተካሄደው የእሳት ቃጠሎ በወያኔ አገዛዝ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሲካሄድ የነበረው ሕዝባዊ አመጽ መልኩን እንዲቀይር ያደረገው እኩይ ተግባር መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን ከእሳቱ በፊት የተኩስ ድምጽ እንደተሰማ የአይን እማኞች ከመመስከራቸውም በላይ በእሳት ቃጥሎ ምክንያት ከሞቱት ዜጎች መካከል
የተወሰኑት በጥይት ተመተው እንደሞቱ የአስከሬናቸው ምርመራ አረጋግጧል።
 በጋምቤላ ታግተው የነበሩና ቪንቴጅ ኤር ራለይ በሚል ስም የሚታወቁ የትናንሽ ሲቪል አውሮፕላኖች አብራሪዎች ተለቀው ጉዟቸውን ወደ ደቡብ አፍሪካ የቀጠሉ መሆናቸውን የዜና ምንጮች ገልጸዋል። የወያኔ አገዛዝ ሰዎችን ያገተበት ምክንያት የአየር ወሰንን አለፈቃድ በመጣሳቸው መሆኑን ጠቅሶ ከማክሰኞ ኅዳር 13 ቀን ጀምሮ ከጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ እንዳይወጡ ያደረገ መሆኑን ገልጿል። ሰዎችን ለማስፈታት በርካታ የምዕራብ አገሮች
ዲፕሎማቶች ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸው ይታወሳል።
 ባለፈው ሳምንት አንዲት ኢትዮጵያዊት 3.1 ኪሎግራም የሚመዝን ወርቅና $10, 000 ዶላር ጥሬ ገንዘብ እንዲሁም የሌሎች አገሮች ገንዝብ ኖቶች ይዛ ወደ ህንድ ለመግባት ስትሞክር ዴልሂ የኢንድራ ጋንዲ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ላይ በፈታሾች ተይዛ የታሰረች መሆኑ ተዘግቧል። የህንድ ባለስልጣኖች በሰጡት መግለጫ ግለሰቧ ከሁለት ወር በፊት ተመሳሳይ ሙከራ ስታደርግ ተይዛ በዋስ የተለቀቀች መሆኑን አስታውሰው በአሁኑ ወቅት የያዘቻቸው ንብረቶች በሙሉ የተያዙ መሆናቸውንና እሷም ወደ እስር ቤት መላኳን ገልጸዋል። ባለፈው ዓመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች እየተካሄዱ የነበሩትን ሕዝባዊ አመጾች በመሸሽ በርክት ያሉ የወያኔ ባለስልጣኖች የዘረፉትን ሀብት በተለያዩ መንገዶች ሲያስወጡ የነበሩ መሆናቸው የሚታወቅ ሲሆን በህንድ ባለስልጣኖች በቁጥጥር ስር የዋለችው ሴት ምናልባት ከወያኔ ባለሥልጣናት መካከል አንዷ ወይም የነሱ ተባባሪ ልትሆን ትችላለች የሚል ግምት እየተሰጠ ነው።
ለዝርዝር ዜናዎች > ከታች ይጫኑ (to listen detail news click below)
To Read: http://www.finote.org/Fikarezena.pdf
To Listen PART 1: http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
Vm
http://www.finote.org/TodayPart1.mp3
00:00
R
p

To Listen PART 2: http://www.finote.org/TodayPart2.mp3
Vm
P

No comments:

Post a Comment