Friday, November 18, 2016

በቂሊንጦ ማ/ቤት እስረኞች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ ቆንጅት ስጦታው

በቂሊንጦ ማ/ቤት እስረኞች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ


በቂሊንጦ ማ/ቤት እስረኞች ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ገለጹ::በእነ ጉርሜሳ አያኖ የክስ መዝገብ በሽብር ተከሰው ጉዳያቸው በፍ/ቤት እየታየ የሚገኙት የኦፌኮ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሌሎች አብረዋቸው የተከሰሱት 22 ተከሳሾች በዚሁ መዝገብ የተከሰሱት አራት ተከሳሾች፣ ማለትም ገመቹ ሻንቆ፣ ጭምሳ አብዲሳ፣ ገላና ነገራ እና ደረጀ መርጋ በቂሊንጦ ማ/ቤት አስተዳደር ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው መሆኑን በመግለጽ ፍ/ቤቱ ይህን እንዲያስቆምላቸው በጠበቃቸው አማካኝነት በጽሁፍ አቤቱታ አቅርበዋል፡፡
_92468221_ws_new_languages_624_ws
አቤቱታ አቅራቢ ተከሳሾች ከነሐሴ 28/2008 ዓ.ም ጀምሮ ቀን ከሌት እጅና እግራቸው በካቴና ታስረው እንደሚደበደቡና ስቃይ እንደሚደርስባቸው በአቤቱታቸው ላይ ገልጸዋል፡፡ ለዚህ ስቃይ የሚዳረጉትም በ28/12/2008 ዓ.ም በቂሊንጦ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ አቀጣጥላችኋል፣ ወይም ያቃጠሉትን ታውቃላችሁና ተናገሩ በሚል እነደሆነ አስረድተዋል፡፡
‹‹አምናችሁ እሳቱን ያቃጠሉትን ከተናገራችሁ ከወንጀሉ ነጻ ትሆናላችሁ፣ መስክራችሁ ትወጣላችሁ፡፡ ይህን ካልፈጸማችሁ ግን በሙሉ አካልም ሆነ በህይወት አትወጡም›› እነደሚባሉ፣ በካቴና የታሰረው እጅና እግራቸውም ማታ ማታ ከአልጋ ጋር ተቆራኝተው እንደሚታሰሩ በአቤቱታቸው ላይ አስፍረዋል፡፡ በመሆኑም ይህ ኢ-ሰብዓዊና ኢ-ህገ-መንግስታዊ ድርጊትን ፍ/ቤቱ ያስቁምልን ሲሉ አቤቱታቸውን አሰምተዋል፡፡
ፍ/ቤቱም የቂሊንጦ ማ/ቤት ተወካይ አቤቱታው እንዲደርሳቸው በማድረግ ‹‹ወደ ክርክር ሳንገባ ተጠርጠሪዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ ተመልክታችሁ አስተካክሉ፡፡ በተረፈ ግን በቀረበው አቤቱታ ላይ በቀጣይ ሰኞ ህዳር 12/2009 ዓ.ም የጽሁፍ መልስ ይዛችሁ ቅረቡ›› የሚል የተለሳለሰ ማሳሰቢያና ትዕዛዝ አስተላልፏል፡፡ እነዚህ አቤቱታ አቅራቢዎች ከሌሎች በተለየ በሌላ መኪና ወደ ችሎት እንደሚመጡና እንደሚመለሱ፣ እንዲሁም ችሎት እስኪሰየም ድረስ ከሌሎች ተከሳሾች ጋር እንዲገናኙ እንደማይፈቀድላቸው ለመመልከት ተችሏል፡፡

No comments:

Post a Comment