Sunday, November 27, 2016

በወገራ የዐማራ ገበሬዎች ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅተዋል፤



በወገራ የዐማራ ገበሬዎች ከፍተኛ ድልን ተቀዳጅተዋል፤
የሰሜን ጎንደር ወገራ ወረዳ የእንቃሽና የጃኖራ ቀበሌ ገበሬዎችን ትጥቅ ለማስፈታት በሚል ትናንት ኅዳር 17 ቀን 2009 ዓ.ም. የተንቀሳቀሰው የወያኔ ወታደር በታጋዮቹ የዐማራ ገበሬዎች ሙት፣ ቁስለኛና ምርኮኛ ሆኗል፡፡ ከቦታው ያነጋገርናቸው የዐማራ የጎበዝ አለቆች እንደሚሉት ትናንት ከሰዐት በኋላ ጀምሮ ጃኖራ ከተባለው ቦታ ከፍተኛ ጦርነት ላይ ናቸው፡፡

ትናንት የሄደው የጠላት ወታደር በሞትና በምርኮ በመመናመኑ ተጨማሪ ወታሮች ወደ ቦታው ተልከው እስካሁን ድረስ ተጋድሎ ላይ መሆናቸውን የአካባቢው የጎበዝ አለቆች ተናግረዋል፡፡ የጎበዝ አለቆቹ በርካታ ወታደሮች የሞቱና የተማረኩ መሆኑን ገልጸው በትክክል ቁጥሩን ለመናገር ግን ጊዜ እንደሚያስፈልጋቸው ተናግረዋል፡፡ ከባድና ቀላል የጦር መሣሪያዎችንም በምርኮ በእጃቸው አስገብተዋል፡፡
ከሣምንታት በፊት በእንቃሽ በነበረው ውጊያ በርካታ ወታደሮች ተማርከው በሃይማኖት አባቶች ምልጃ መመለሳቸው የሚታወስ ሲሆን ከባለፈው ስሕተት አሁን እንደተማሩ አያይዘው ገልጸዋል፡፡
የዐማራ ተጋድሎ ያሸንፋል// Muluken Tsfaw

No comments:

Post a Comment