Monday, November 28, 2016

በበርካታ አካባቢዎች የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ ተካሄደ ምኒሊክ ሳልሳዊ



በበርካታ አካባቢዎች የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ ተካሄደ
ባሳለፍነው ሳምንት ወያኔ በበርካታ አካባቢዎች ሕዝብን ትጥቅ ለማስፈታት ዘመቻ እያካሄደ መሆኑን ከሚደርሱን ዘገባዎች ተረድተናል፡፡ የአገዛዙ ፌደራል ፖሊስና የየአካባቢ የፖሊስ ኃይሎች የቤት ለቤት አሰሳ በማካሄድ ሕዝቡ እራሱንና ቤተሰቡን ከማንኛውም ዘራፊ ኃይል ለመከላከል በገዛ ገንዘቡ የገዛውን መሣሪያ በኃይል እየነጠቁ መሰንበታቸውን ተገንዝበናል፡፡ በበርካታ አካባቢዎች ሕዝቡ መሣሪያውን ላለማስረከብ ከተሰማራው የወያኔ ኃይል ጋር ግጭት እንደፈጠረም ተሰምቷል፡፡
በጋምቤላ፣ በከረዩ፣ በቦረና፣ በባህር ዳር፣በሐረር፣ በአርሲ፣ በጉጂ፣ በጎንደርና አካባቢው፣ በኮንሶ፣ ፣ …ወዘተ መሣሪያ ላለማስረከብ ሕዝቡ ተቃውሞ በማሰማቱ ሳቢያ በርካታ ሰዎች ለእስር ተዳርገዋል። ከዚህ ቀደም በጋምቤላ ሕዝቡ ከወሮበላና ድንበር ጥሶ ከሚመጣ ኃይል ለመከላከል ባለው አቅሙ የገዛቸውን የነፍስ ወከፍ ማሣሪያዎች ወያኔ ስለወረሰበት ከደቡብ ሱዳን ዘልቀው የመጡትን ሙርሌ የሚባሉትን ለመመከት ሳይችል ቀርቶ ህፃናቱ ተዘርፈው እንደተወሰዱበት የሚታወስ ነው፡፡ ይህን መሰል ሕዝብን በጅምላ ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ መዘዙ ዘርፈ-ብዙ መሆኑን የፖሊቲካ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡ ከመደበኛ ጦር ውጭ ሀገርን ድንበር የሚያስከብረው አርሶ አደሩ በመሆኑ ሕዝብን ካለመሣሪያ ባዶ እጅ ማስቀረት ለድንበር ተሻጋሪ ወራሪዎች የተመቻቸ ሁኔታ ይፈጥራል ይላሉ፡፡ በሌላ አንጻር ትጥቅ በማስፈታት ወያኔ የጭቆና እድሜውን ለማራዘም ቢያልምም ሕዝቡ ክብሩንና ሀብቱን በመገፈፉ ምሬትና ንዴት አድሮበት ወያኔን ለማውረድ በጽኑ ይታገላል የሚሉ በርካቶች ናቸው፡፡ minilik salsawi via finote Democracy

No comments:

Post a Comment