
የወያኔ ታጣቂዎች በሸዋሮቢት ከተማ ትናንት እና ዛሬ ህዝቡ ሰልፍ እንዳይወጣ ለማስፈራራት ሲሞክሩ ውለዋል። ከሸዋሮቢት የደረሰን ሪፖርት እንደሚለው፣ ህዝቡን ስለትራፊክ ደህንነት እንወያይ በሚል ሽፋን ስብሰባ ጠርተዋል። ከተማ ውስጥ መትረየስ የታጠቁ የፈደራል ፖሊስ አባላት በፒካፕ መኪና ሲዘዋወሩ ይታያሉ። ደሴ ውስጥ ከትላንት ማታ ጀምሮ የወሎ ተወላጅ የሆኑ የአማራ ፖሊስ አባላት ሁሉ መሳሪያ እንዲያስረክቡ እየተደረገ ነው። ወልድያ ውስጥ በክፍለጦር ደረጃ የሚገመት የወያኔ ሰራዊት ሰፍሯል። በጎንደርና ጎጃም የተነሳው ህዝባዊ አመጽ ወደወሎ ከተዛመተ ወያኔ ሊያበቃለት እንደሚችል ስለገመተ ይመስላል የፊታችን እሁድ ወሎ ውስጥ የተጠራውን ሰልፍ የወያኔ ታጣቂዎች በእያንዳንዱ ቤት እየተዘዋወሩ ልጆቻችሁ ከቤት እንዳይወጡ እያሉ በማስጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።
No comments:
Post a Comment