Wednesday, August 24, 2016

ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ይዘው ለመሔድ በፈለጉ የትግራይ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራው ፖሊስ መካከል የተፈጠረውን ፍጥጫ የጎንደር ወጣቶች ተቀላቅለውታል፡




ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱን ይዘው ለመሔድ በፈለጉ የትግራይ መከላከያ ሠራዊትና በዐማራው ፖሊስ መካከል የተፈጠረውን ፍጥጫ የጎንደር ወጣቶች ተቀላቅለውታል፡፡ኮሎኔል ደመቀን እና የጎንደር ማረሚያ ቤት በአሁኑ ሰአት (ትግሬን ከከተመው አስወጥቶ ዐማራን ለመጨረስ የታሰበ እቅድ) ..
ዐማራ እንዴት ዋለ? (ነሃሴ 18 ቀን 2008 ዓ.ም.) ዝርዝር
የፍኖተ ሰላም ዐማሮች የተሳካ የዐማራ ተጋድሎ አካሔዱ
• ኮሎኔል ደመቀን ለመውሰድ መከላከያ ሠራዊት ሙከራ አደረገ
• በጎንደር የቤት ውስጥ አድማ ዳግመኛ ተጀመረ
• በአርማጭሆ የዐማራ ተወላጅ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ከሕዝብ ጋር መሆናቸውን አሳዩ
• በደብረ ታቦር ከነሃሴ 22 እስከ 25 የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ይደረጋል
ፍኖተ ሰላም፤ በፍኖተ ሰላም ከተማ የዐማራ ተጋድሎ በተሳካ ሁኔታ ተከናውኗል
በዳሞቷ ፈርጥ ፍኖተ ሰላም ከተማ ከዛሬ ጀምሮ ለሦስት ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ነበር እቅዱ፡፡ ግን ይህ ከቤት ውስጥ የመቆየት የተጋድሎ አድማ በወያኔዎችና በቅጥረኞቹ እንዲከሽፍ በጠዋት ወደ ሥራ የተሰማሩ ቡድኖችና ግለሰቦች መኖራቸው ታወቀ፡፡ የቆላ ደጋ ዳሞት ዐማራ ከቀናት በፊት ለገጠር ቀበሌ ገበሬ ማኅበራት መልእክት አስተላልፎ ነበር፡፡ ገበሬው በንቃት ጉዳዩን ተከታተለ፡፡
ዛሬ ገበያ ቦታ ላይ አድማውን ትተው ከሕዝብ የተነጠሉትን ሆድ አደር ነጋዴዎች ወጣቶች ሒደው ተነሱ ወደ ቤታችሁ ግቡ አሏቸው፡፡ አልሰሙም፡፡ ተጋድሎው ተጀመረ፡፡ የቤት ውስጥ አድማው ወደ አደባባይ ዞረ፡፡ ከዚያ በኋላማ ለዳሞት ዐማራ ምን ይነገረዋል? ሀምሌ 30 ቀን ተጀምሮ እንዲኮላሽ የተደረገው የተጋድሎ እንቅስቃሴ ቁጭት አለ፡፡ የሰላሟ ከተማ በቆራጥ የዐማራ ጀግኖች ቁጥጥር ሥር ለመዋል ጠዋት ሦስት ሰአት ብቻ ነው የጠበቀችው፡፡
በ3፡00 የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ ሥራ የጀመሩ የንብ፣ የዓባይ፣ የንግድና የዳሸን ባንኮችን ቶሎ በራቸውን እንዲዘጉ በዐማራ ባሕል ነገሯቸው፡፡ አልሰሙም፡፡ በግዴታ ነበልባሎቹ ወጣቶች ሁሉንም እንዲጠረቀም አደረጉ፡፡ የዐማራ ወጣቶች ወደ ማረሚያ ቤት በመሔድ የመኪና መንገድ ዘጉ፡፡ ከወደ ጅጋ በኩል የሚመጣውንም የመኪና መንገድ ጥርቅም አደረጉት፡፡ ወደ አደባባይ ሲሔዱ ‹‹መጪው ጊዜ ከኢሕአዴግ ጋር ብሩህ ነው›› የሚል ፌዘኛ ቢል ቦርድ አገኙ፤ ይህ ቀልድ ዳግም በጎጃም ምድር መኖር የለበትም ሲሉ አጋዩት፡፡
አቶ ብናልፍ አንዱዓለም የሚመካበትን የብአዴን ጽ/ቤት ጋ ሔዱ፡፡ ማንም የሚያቆማቸው አልነበረም፡፡ የብአዴንን ዓርማ አቃጠሉት፡፡ የአባቶቻችን ሰንደቅ ዓላማ በፍኖተ ሰላም ከ25 ዓመታት በኋላ ተውለበለበ፡፡ አደባባይ ላይም ሰቀሉት፤ የቆላ ደጋ ዳሞት ዐማሮች በደስታ እልል አሉ፡፡
የዐማራ ፖሊስ ከእኛ ጋር እንደሆነ ከሕዝብ ጋር ቆመ፡፡ አንድም እንኳ የዐማራ ፖሊስ በዐማራ ሕዝብ ላይ የተኮሰ የለም፤ እንዲያውም ሰልፈኞችን አበረታተዋል፡፡ የሥርዓቱ አገልጋይ የሆኑ የንግድ ቤቶችና ንብረቶች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ከዚህ በኋላ በአንበሳ ባንክ የሚጠቀም ዐማራ የለም፡፡
ወያኔ ከብር ሸለቆ መከላከያ ሲያንቀሳቅስ መንገድ ተዘጋበት፡፡ በእግር ብዛት ያለው መኪና ከብር ሸለቆ እየሔደ እንደሆነ ሰምተናል፡፡ የዳሞት ዐማራ ለቋሪትና ለሰከላ፣ ለእንጅባራና ለጃግኒ መልእክት ልኳል፤ ‹‹የዐማራ ተጋድሎ እስከ ነጻነት ይቀጥላል›› በማለት፡፡
በፍኖተ ሰለም ከተማ ይህ ሪፖርት እስከተሠራበት ጊዜ ድረስ ተጋድሎው እንደቀጠለ ነበር፡፡ ብዙ ወጣቶች ምሳና ቁርስ ሳይበሉ ተጋድሎአቸውን መቀጠላቸው ታውቋል፡፡ ከደብረ ማርቆስ በኩል የመጣ የፌደራል ፖሊስ መንገድ ተዘግቶበት እንደነበር ለማወቅ ችለናል፡፡
ወደ ማረሚያ ቤት በመሔድ መንገድ ዘግቶ ከዚያ የፓርቲው ሰንደቅ አላማ ተቃጥሏል፡፡ አደባባይ ቀይ ቢጫ አረንጓው ሰንደቅ አለማ ተሰቅሏል፡፡ የኢሕአዴግ ደጋፊ ድርጅቶች ሙሉ ጥቃት ደርሷል፡፡ ፖሊስ ከእኛ ጋር ነው፡፡
ግልገል በለስ፤ በግልገል በለስ መምህራን ኮሌጅ ሁለት የአገዛዙ ቅጥረኞች የእጅ ቦንብ ይዘው ግቢው ውስጥ እንዲያዙ ከተደረገ በኋላ ዐማሮች ጉምዞችን ለመጨረስ ሲሉ ተያዙ እያሉ በማስወራት በመተከል ዞን ሁሉም አመራር የዐማራን ጉዳይ ለማየት ስብሰባ መቀመጣቸው ታውቋል፡፡ ይህ ዓይነት ምክንያት ዐማራን ለመጨፍጨፍ በየጊዜው የሚፈበረክ ወሬ በመሆኑ ሁሉም በአካባቢው የሚኖሩ ዐማሮች እንዲጠነቀቁ መልእክት እንዲተላለፍ መረጃውን የሰጡን ሰዎች ገልጸዋል፡፡
ጃግኒ፤ የጃግኒ ከተማ ገበሬው ወደ ገበያ ሲመጣ በመከላከያ ኃይል እንዲመለስ እየተደረገ ነው፡፡ ገበሬዎች ወደ ከተማ ሲገቡ የዐማራውን ተጋድሎ ይቀላቀላሉ በሚል ስጋት ወደ ከተማ እንዳይገቡ እየተመለሱ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ባሕር ዳር፤ የባሕር ዳር ዐማሮች ቤታቸው ውስጥ ከተቀመጡ ዛሬ አራተኛ ቀናቸውን ይዘዋል፡፡ አንዳንድ የባጃጅ ሾፌሮችና የንግድ ቤቶች በግዴታ እንዲከፈቱ የተደረገ ቢሆንም በከተማው ብዙ እንቅስቃሴ እንደሌለው ነው የሚነገረው፡፡ በባሕር ዳርም የዐማራ ፖሊስ ከሕዝብ ጋር መቆሙን አረጋግጧል፡፡
ደብረ ታቦር፤ የደብረ ታቦር ዐማሮች ከነሃሴ 22 እስከ 25 ቀን የሚቆይ የቤት ውስጥ አድማ ይደረጋል፡፡ የደብረ ታቦር ከተማ በተጠቀሱት ቀናት ውስጥ ጭር ብላ ትሰነብታለች፡፡ ሁሉም ሰው ወደ ሥራ ገበታ ባለመሔድ ትብብር እንዲያደርግ የደብረታቦር ከተማ የተጋድሎው አስተባባሪዎች ጠይቀዋል፡፡ የዐማራውን ተጋድሎ ትቶ የሚሔድ ሰው ቢገኝ ግን ዝምድናው ከወያኔ ጋር እንደሆነ ይቆጠርበታልም ብለዋል፡፡ ማንኛውም የንግድ ቤትና የመንግሥት መሥሪያ ቤት ዝግ ሆኖ ይሠነብታል፡፡ ደብረ ታቦርን በእነዚያ ቀናት ታቦር ተራራ ላይ ሆኖ ለሚያያት በውስጧ ሕይወት ያለባትም አትመስል ይሆናል፡፡
ጎንደር፤ ኮሎኔል ደመቀን ለመውሰድ የትግሬ መከላከያ ሙከራ እያደረገ እንደሆነ ዛሬ ከመሸ ያገኘነው መረጃ አመልክቷል፡፡ ከሰአት በኋላ ሁለት ፓትሮል ስናይፐር የያዘ የመከላከያ ሠራዊት ወደ አንገረብ ማረሚያ ቤት ሒደው ነበር፡፡ ለምን እንደሆነ ሲጠየቁም በቂ መልስ መስጠት አልቻሉም፡፡ የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ የመከላከያ ሠራዊቱን ጉድብ በመያዝ የጠበቃቸው ሲሆን ምንም ሳያደርጉ እንደገና ተመልሰዋል፡፡ የዐማራ ልዩ ኃይል ፖሊስ ላደረገው ቁርጠኝነት መረጃውን የሠጡን ሰዎች ገልጸው ሕዝቡም በንቃት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
ይህ በዚህ እንዳለ ለአምስት ቀናት ሊዘልቅ የሚችል የቤት ውስጥ አድማ በጎንደር ከተማ ዛሬ ተጀምሯል፡፡ የጎንደር ከተማ ዐማሮች ትግሉን ከፍ አድርገው ሰቅለውታል፡፡ ዳቦ ቤቶች፣ ክሊኒክና ፋርማሲዎች እንዲሠሩ ተፈቅዶላቸዋል፡፡ ከዚያ ውጭ ያለ ማንኛውም የንግድ እንቅስቃሴ ጸጥ አረጭ ያለ ነው ዛሬ በጎንደር፡፡ በቀን ሥራ የተሠማሩና ሕይወታቸውን በእየለቱ እየሠሩ ለሚመገቡ ዝቅተኛ ኑሮ ለሚኖሩ ዐማሮችም መፍትሔ መኖሩን ነው ያነጋገርናቸው ሰዎች የገለጹት፡፡
ኮሌኑ ጋ መከላከያ ዛሬ ሒደው ነበር፤ ሰውየውን ለመውሰድ እየሞከሩ ነው፡፡ መከላከያዎች ስናይፐር ይዘው በሁለት ፓትሮል ሲሔዱ የክልሉ ልዩ ኃይል ጉድብ ይዘው የጠበቁት፡፡ ሰልፉን እንዴትና በማን እየተመራ ነው ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ ‹‹አንተ ዐማራው በአንድ ልብ ነው የሚተነፍሰው፤ በጣም ተግባብቷል፡፡ ከወያኔወች ሁሉ ቀድሞ ሒዷል፡፡ ምን ቢከሰት ምን እንደሚያደርግ ራሱ ያውቃል›› ሲሉ በመደነቅ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም የዐማራው ሕዝብ ተጋድሎውን ያለማንም ጣልቃ ገብነት እያቀጣጠለው ይገኛል፡፡
በሌላ በኩል ሐምሌ 06 ቀን 2008 ዓ.ም በአጋዚ የተመታው አቶ አዳነ አየነው ከ40 ቀን በኋላ ዛሬ ማረፉን በሐዘን ውስጥ ሆነን ሰምተናል፡፡ የሰማእቱ ወንድማችን ቀብር በቅዱስ ዮሐንስ ቤተ ክርስቲያን የፈጸማል፡፡
ምእራብ አርማጭሆ፤ በምዕራብ አርማጭሆዋ የኩር ዑመር (ጠፈረ ወርቅ) ከተማ ነሃሴ 16 ቀን የተጀመረው የዐማራ ተጋድሎ እስካሁን እንደቀጠለ ነው፡፡ የሥርዓቱ አጋፋሪዎች ንብረት ሙሉ በሙሉ ወድሟል፡፡ የወያኔ ደጋፊዎችም አካባቢውን ለቀው እየወጡ እንደሆነ ነው የሚነገረው፡፡
በሌላ ዜና የዐማራ ተወላጅ የሆኑ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በአርማጭሆ አገዛዙን እየተው ወደ ሕዝብ መቀላቀላቸውን ሰምተናል፡፡ ትናንት አንድ የመቶ አለቃ ሦስት የበታች አባሎቹን ይዞ ከሕዝቡ ጋር ገብቷል፡፡ ወደ አርማጭሆ የተላኩት የመከላከያ ሠራዊት አባለት በቂ ካምፕ ሳይዘጋጅ ወደ ቦታው በመንቀሳቀሳቸው ምክንያትም ወደ ሕዝቡ እንጀራ እንደሚለምኑ ተሰምቷል፡፡ የዐማራ ሕዝብ ደግሞ ምንም እንኳ እንግዳ ተቀባይ ቢሆንም የወያኔ መከላከያ ሠራዊት አባላትን ማየት እንደማይፈልግ እየነገራቸው ነው፡፡
ወልቃይት፤ ባለፈው ሳምንት ከዩንቨርሲቲ ተመርቀው ሥራ ያልያዙና 12ኛ ክፍል የጨረሱ የወልቃይት ዐማሮችን መቀሌ በቀን 500 ብር አበል ለስብሰባ ተጠርተው ነበር፡፡ ሆኖም የወልቃይት ዐማሮችን ዐማራ ነን ማለታችሁን ተው በመባላቸው ምክንያት ስብሰባውን አቋርጠው ተመለሰዋል፡፡ እስካሁን ድረስ በዳንሻ፣ አዲረመጥና ኹመራ አካባቢዎች የትግራይ ተወላጆች ሀብት ንብረታቸውን እያሸሹ እንደሆነ ነው የሚሠማው፡፡

No comments:

Post a Comment