Sunday, August 7, 2016

የባህር ዳር ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ወያኔን አውግዟል ።




የባህር ዳር ሕዝብ አደባባይ በመውጣት ወያኔን አውግዟል ።የጎጃም ህዝብ ወልቃይትን በተመለከተ ለሃይለማሪያም ምላሽ ሰጠ
ወልቃይት የሚለውን ቃል ሕወሃቶች በጭራሽ እንዲነሳ አይፈለጉም። የብአዴን አመራሮችም የወልቃይት ጥያቄ ሕወሃቶችን የሚያበሳጭ በመህኑ በይፋ አይናገሩትም። “የመልካም አስተዳደር ችግር” ብቻ ብለው ነው የሚያልፉት። ሆኖም የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ማእከል ቦታ ይዟል።
ወንጀለኛና ሽብርተኛ ብለው፣ ኮሎኔል ደመቀን ዘዉዱን ወደ መቀሌ ወይም ወደ ማእከላዊ ለመዉሰድ ሕወሃት ደፋ ቀና እያለ እንደሆነና በአዴንም ጫና በዝቶበት እያንገራገረ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ሆኖም ግን የጎጃም ህዝብ በማያሻማ መልኩ የጎንደር ነዋሪዎችን ድምጽ በድጋሚ በማስተጋባት “ሁላችንም ኮሎኔል ደመቀ ነን” ብሏል።
 ከጥቂት ቀናት በፊት፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆነው የጎንደር ሕዝብ ድምጹን ቢያሰማም፣ የሕዝቡን ድምጽ በመናቅ አቶ ሃይለማሪያም ደሳለኝ እና የብአዴን ከፍተኛ አመራር አባል እና የአማራዉን ህዝብ እወክላለሁ ባይ፣ የፌዴሬሽን ጉዳዮች ሚኒስቴሩ ካሳ ተክለብርሃኑ፣ ለሕዝብ ትልቅ ንቀት በማሳየት “የወልቃይት ጥያቄ ከተፈታ ቆይቷል። ወልቃይት የትግራይ ናት” ማለታቸው በ እጅጉ የጎጃምን ህዝብ አስቆጥቷል።
“ሃይለማሪያም እና ካሳ ተከለ ብርሃን ወልቃይት የትግራይ ናት ማለታቸው በአማራው ህዝብ ላይ ጦርነት አዉጀዋል እንደማለት ነው” በማለት ነበር ተቃዉሟቸውን   ያሰሙት።



Mereja.com's photo.


No comments:

Post a Comment