Tuesday, August 23, 2016

ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰደው የሀይል እርምጃ መፍትሄ አይደለም አለች

  


ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያ መንግሥት በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የወሰደው የሀይል እርምጃ መፍትሄ አይደለም አለች
በኢትዮጵያ እየተወሰዱ ያሉት የሀይል እምጃዎችና ሌሎቹ ለሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ መፍትሄ ሊሆኑ አይችሉም ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ረዳት ሚኒስቴር ቶም ማሎንስኪ አስታወቁ።
ረዳት ሚኒስትሩ እንዳሉት የፀጥታ ሀይሎች ከመጠን ያለፈ ሀይል መጠቀም በርካታ ሰዎችን መግደል እና ማቁሰል እንደዚሁም በሺዎች የሚቆጠሩ ማሰር ቀጥለዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ ሰልፎቹ ሰላማዊ አልነበሩም ብሏል።
ከሰልፎቹ ጥቂቶቹ ለብጥብጥ መሳርያነት ጥቅም ላይ ውለው ይሆናል ያሉት በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት የዲሞክራሲ የሰብዓዊ መብቶች እና የሥራ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሎስኪ አብዛኛዎቹ የሰልፉ ተሳታፊዎች ግን በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት የሰፈረውን ሃሳብ የመግለፅ መብት የተጠቀሙ እንደነበር እናምናለን ብለዋል።
ኢትዮጵያ የውጭ ስጋቶች እንዳሉባት እንደሚረዱም ጠቅሰዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
http://av.voanews.com/clips/VAM/2016/08/22/541444a9-7576-410c-9af4-8dd125c60e24.mp3
Vm
P
በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስርያ ቤት የዲሞክራሲ የሰብዓዊ መብቶች እና የሥራ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ቶም ማሎስኪ

No comments:

Post a Comment