Friday, August 5, 2016

የኣዲስ አበባ ወጣቶች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተውን የሰላማዊ ሰልፍ መልዕክት የያዘ በራሪ ወረቀት በራሳቸው ተነሳሽነት አሳትመው እያሰራጩ ነው



የኣዲስ አበባ ወጣቶች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተውን የሰላማዊ ሰልፍ መልዕክት የያዘ በራሪ ወረቀት በራሳቸው ተነሳሽነት አሳትመው እያሰራጩ ነው
#‎AddisAbaba‬ ‪#‎Demonstration‬ የኣዲስ አበባ ወጣቶች ከዚህ ቀጥሎ የተመለከተውን መልዕክት የያዘ በራሪ ወረቀት በራሳቸው ተነሳሽነት አሳትመው እያሰራጩ ነው
ጉዳዩ: ሰላማዊ ሰልፍ ማወጅን ይመለከታል፡፡‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Amharaprotests‬
በ25 አመታት የኢህአዴግ አገዛዝ ዉስጥ ከስርአቱ ተጠጊዎችና ከስርአቱ አቀንቃኞች ዉጪ አንድም የተጠቀመ ሰዉ እንደሌለ እሙን ነዉ፡፡”በመሆኑም ብሄራዊ ክብሬ ተነክቷል፤ ሰበአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቴ ተጥሷል፤ በሀገሬ ሰርቼ መኖር አልቻልኩም፤ ድግሪን የሚያህል የት/ርት ደረጃ ይዤ ድንጋይ እንድፈልጥ ነዉ የተፈረደብኝ፤ በአንጻሩ ምንም ያልተማረ ድልብ መሃይም ካድሬ ኢህአዴግን ስለተጠጋ ብቻ በአንድ ለሊት ባለጸጋ ለመሆን በቅቷል፤ እኔ ነጻነት አጥቻለሁ፤ ዴሞክራሲን በስሙ እንጂ አይቼዉም አላዉቅም፤ እኩልነት ምን እንደሆነ ብገነዘብም በኢህአዴግ አገዛዝ ዘመን ሲተገበር አላየሁም፤ ለራሳቸዉ ከቀረጥ ነጻ አስገብተዉ በቅናሽ ዋጋ ሲሸጡ እኔ ላይ ግብር ከምረዉ ከስራ ዉጪ ሆኛለሁ-ነግጄ ለመንግስት ነዉ ስሰራ የከረምኩት
Image may contain: text, one or more people and outdoor
ራሴን መለወጥ አልቻልኩም፤ መሬቴ በጉልበት ተወርሶብኛል፤ በሀገራቸዉ ስራ መስራት ባለመቻላቸዉ እህትና ወንድሞቼ ስራ ፍለጋ እንደወጡ በባህር ሰጥመዉ፤ በአሸባሪ ተገድለዉብኝ ልቤ ቆስሏል፤ እንደ እንስሳ እንጂ እንደ ሰው እየታየሁ አይደለም፤ ሁለተኛ ዜጋ እንደሆንኩ ነዉ የሚሰማኝ፤ ቤቴ ፈርሶ ሜዳ ላይ ተጥያለሁ፤ ቤታችን ለምን ይፈርሳል ብለዉ የተቃወሙ የቤተሰብ አባላቶቼ እስር ቤት ናቸዉ፣ በፖለቲካ አመለካከቴ ምክንያት ከመስሪያ ቤቴ ተባርሬአለሁ፣ ንብረት ለማፍራት ምንም ዋስትና የለኝም፤
ሀገሬን ባለግዜዎች ነጥቀዉኛል፣አማራ በመሆኔ ትምክህተኛ መርዝ ለሃጫም፣ ኦሮሞ በመሆኔ ጠባብ ዘረኛ ተብዬ ተሰድቤአለሁ የዘር ግንዴ ተሰልቶ አድልኦ ተደርጎብኛል፤ በኑሮ ዉድነት ምክንያት እንኳን ለመኖር ኑሮን ራሱ ሳስብ የተፈጠርኩበትን ቀን እርግማለሁ ይሄንንም የፈጠረዉ የመንግስት የቢሮክራሲ አሰራር እንደሆነ ቢገባኝም ፈርቼ ወይም ብቻዬን ሆኜ እስከ ዛሬ ታግዣለሁ፣ ፍርድ ቤት፣ የመከላከያ ሰራዊት፤ ፖሊስ የአንድ ድርጅት ዙፋን ጠባቂ እንጂ ነጻ ተቋማት ሆነው የህዝብ ወገኝተኝነታቸውን በግዢው ፓርቲ ተነጥቀዋል።
የምትል በሙሉ ቅዳሜ ሐምሌ 30/2008 ዓ/ም ማለዳ ጀምሮ መስቀል አደባባይ እንገናኝ፡፡ ክልል ላይ የምትኖር ከሆነ ደግሞ ወደ አንዱ የኦሮሚያ ክልል ወረዳና ዞን ጎራ በል በዕለቱ ህዝቡ ብሶቱን ያሰማል።
ድል የህዝብ ነዉ፡፡”
 

No comments:

Post a Comment