Thursday, August 4, 2016

ሕዝብ በማያውቀው ሕግ ገዢ ነን ባዮች ሊመሩት አይችሉም። ሰልፉ ኣይቀሬ ነው።

ሕዝብ በማያውቀው ሕግ ገዢ ነን ባዮች ሊመሩት አይችሉም። ሰልፉ ኣይቀሬ ነው።

በኦሮሚያ ክልል ለቅዳሜ ሐምሌ 30 2008 ታላቅ ሕዝባዊና ሰልማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ተጠርቷል። ይህን ጥሪ ተከትሎ የኦሮሚያው ክልል የወያኔ ወኪል ሙክታር ከድር በኦሮምያ ክልል እውቅና የሰጠነው ስልፍ የለም በማለት መናገሩ ተሰምቷል። ሰልፉ ኣልተፈቀደም በሚል ብቻ የሕዝብን መብት እጋፋለሁ የሚል የሕወሓት ኣገዛዝ ኣካል ቢኖር ዋጋ ያስከፍለዋል፥ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ሕዝቦች ነጻነታቸውን እና መብታቸውን ለማስከበር የምንንም ድጋፍ እና ፈቃደኘት ኣይፈልጉም በጎንደር የተካሄደው እና በሚሊዮኖች የተሳተፉበት ሰልፍ ኣልተፈቀደም በሚል ሕወሓትና ኣሽከሮቹ ቢደነፉም የሕዝብ የበላይነት በኣሸናፊነት ገኖ ሕወሓት እንደሚመኘው በደም መፋሰስ ሳይሆን በሰላማዊነት ተጠናቋል።
Image may contain: text
በኦሮሚያ ክልልም ሕዝብ በገዛ ኣገሩ ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ ከፈለገ የምንም ፈቃድ እና ድጋፍን ኣይፈልግም የህዝብ ሃይል ታላቅ ድልን እንደሚያጎናጽፍ ዛሬ ላይ በመሳሪያ ሃይል የሚመኩ ነገን እንደሚዋረዱ ሊያውቁና ሕዝብም የድል ባለቤት እንደሆነ ሊያውቁ ግድ ይላቸዋል። ሰልፉ ኣልተፈቀደም በሚል ብቻ የሕዝብን መብት እጋፋለሁ የሚል የሕወሓት ኣገዛዝ ኣካል ቢኖር ዋጋ ያስከፍለዋል፥ እያስጠነቀቅ ያለነው በጎንደር እንደተካሄደው ሁሉ በኦሮሚያ እና በባህር ዳርም የሚካሄደው ሰልፍ በሕዝብ የበላይነት ስለሚመራ ሰላማዊ እና እንከን የሌለበት ታላቅ ሰልፍ ነው፤ይሆናልም።
ስለዚህ ሕወሓትም ሆኑ ኣሽከሮቹ ብአዴንና ኦሕዴድ በሕዝብ ላይ የሚያደርጉትን ዛቻ ኣቁመው እጃቸውን ሰብስበው በመቀመጥ የሕዝብን ጥያቄ ኣድምጠው ስልጣን ለሕዝብ እንዲያስረክቡ ይፈለግባቸዋል።የወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ኣገሪቷል ለመበጥበጥ የማይቆፍረው ጉድጓድ እንዳሌለ ይታውቃል በዚህ ጉድጓድ ግን የሚቀበረው ራሱ ወያኔ መሆኑን ሊያውቅ ይገባል። የፊታችን ቅዳሜ በመላው ኦሮሚያና እሁድ በባህር ዳር እና በሌሎች ከተሞች የሚደረጉ ሰልፎች በተያዘላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ይፈጸማሉ።ሞት ለወያኔና ኣሽከሮቹ። ‪#‎

No comments:

Post a Comment