Tuesday, August 9, 2016

ጥብቅ ማሳሰቢያ ለአግአዚ ኮ/ክ/ጦር አባላት…….. እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው! እንደ አሳማ ሳይሆን እንደ ሰው እሰብ!


እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው!  እንደ አሳማ ሳይሆን እንደ ሰው እሰብ!
ጥብቅ ማሳሰቢያ አለበል አማረ /ኮሎኔል/
ለአግአዚ ኮ/ክ/ጦር አባላት……..
በተለይም ለአማራና ለኦሮሞ ተወላጆች
ትንሽ ስለእኔ፤
በ1981 መጨረሻ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቴን አቁአርጨ ኢህዴንን ስቀላቀል የኢህዴንን መሰረታዊ አላማ ተረድቸ ሳይሆን ደርግ በተሳሳተ ሁኔታ አድርሶብኝ በነበረው በደል ቁአጥሬው በነበረው ቂም ተገፋፍቸ ነበር። የመጀመሪያውን ወታደራዊና ፖለቲካዊ ስልጠናወች ሙሉ በሙሉ በህወኃት አሰልጣኞች ማይጨው በረሃ ነበር የወሰድኩት። ወታደራዊ ስልጠናወቹን እኔም ሆንኩ ሌላው በደስታ መሰልጠናችን አሁን ድረስ አልዘነጋውም። በፖለቲካዊ ስልጠናወች ላይ ግን ብዙ ክርክርና ፍጭት እናካሂድ ነበር። ከነበሩ ብርቱ ክርክሮች ኤርትራ በኢትዮጵያ ቅኝ ግዛት መያዝ፣ የኢትዮጵያ የመቶ አመት ታሪክ እና የሚኒሊክ ጨፍጫፊነት ለሁላችንም የማይዋጥ ጉዳይ ስለነበር ሰፊ ክርክር እናደርግ ነበር። እነዚህ ነጥቦችም የታጋይነትና አባልነት ዋነኛ መመዘኛ ስለነበሩ ማመን ግድ ነበር፤ ይህን አናምንም ብለው በአቁአማቸው የወጡ ልጆች ወዳልታወቀ ቦታ ተወስደው እርምጃ እንደተወሰደባቸው ዘግይተን ያወቅንበት ሁኔታም ነበር።
ከስልጠና በኃላ ከተራ አባልነት እስከ ኃላፊነት በተለያዩ ቦታወችና ኃላፊነቶች ኢህዴንን በኃላም ብአዴን/ኢህአዴግን በተለይም በብዛት በህዝብ ስራ የሰራው ሲሆን ከ1992 ጀምሮ በዋነኛነት በአግአዚ ኮማንዶ ክ/ጦር በአመራር አባልነት የቆየሁ ስለሆነና የክፍለ ጦሩን አባልና አመራርም በደንብ ስለማውቃቸውና ስለሚያውቁኝ፤ አሁንም በህዝብ ላይ ይቅር የማይባል ግፍ እየፈፀምና አገር እያጠፋ ለሚገኘውና ከአንድ ዘር ለተሰባሰብ ወንጀለኛ ቡድን መጠቀሚያ ሁኖ እየቀጠለ በመሆኑ
ይህንን መልዕክት ለመፃፍ ተገድጃለው። በዚህ በያዝነው ስልጡን አለም ሰውን የሚያክል የተከበረ ፍጡር በየቦታው በፀራራ ፀኃይ በጥይት መግደል እጅግ የሚያሳዝንና ዘግናኝ ነገር ነው።
አግአዚ እንደ ክ/ጦር በ1991 ብላቴ ላይ ከመመስረቱ በፊት መለስ ዜናዊ በቅርብ እየተከታተለው በሌ/ጄኔራል ፃድቃን ገብረትንሳኤ፣ በብ/ጄኔራል ታደሰ ጋውና፣ በጌታቸው አሰፋ /ያንጊዜ የመለስ ዜናዊ የዘመቻ ጉዳዮች ኃላፊ የነበረ ነው/ እንዲሁም የመለስ ዜናዊ የረጅም ጊዜ የጥበቃ ኃላፊ በነበረው በኮ/ል ነጋሲ ወልዳይና በእኔ ኮ/ል አለበል አማረ ሰፊና ተደጋጋሚ ውይይት በኃላ የተመሰረተ ክፍል ነው።አመሰራረቱን በጥልቀት ወደ ፊት የምመለስበት ሁኖ፤
በውይይቱ በክ/ጦሩ አመሰራረት ላይ የተለያየ ሃሳቦች ይነሱ ነበር፤ በነ ጌታቸው አሰፋና ነጋሲ ወልዳይ በኩል በአነስተኛ የሰው ሃይል ሁኖ ከሶስት ሻለቆች ባልበለጠ እንዲደራጅና ግዳጁም ከመደበኛ ውጊያ ውጭ ሁኖ ጠንከር ያሉ የውጭም የውስጥም ስልጠናወች ተሰጥተውት ዘመናዊ መሳሪያ እንዲታጠቅ የፈለጉ ሲሆን በነፃድቃን በኩል ደግሞ በርከት ያለ የሰው ኃይል እንዲኖረ ትጥቁም ብረት ለበስ ተሽከርካሪወችን ጨምሮ ኤሊኮፕተሮች እንዲኖሩት ግዳጁም መደበኛ ውጊያን ጨምሮ ስፔሻል ግዳጆችንም ግምት ያስገባ እንዲሆን ይፈልጉ ነበር።
በመጨረሻ አደረጃጀቱ የሁለቱንም ፍላጎት በአጣጠመ መልኩ በክ/ጦር ደረጃ ሁኖ እንዲደራጅ ሲደረግ የክ/ጦሩ መነሻ ኃይል ቀደም ብሎ በ1982 አጽቢ ላይ በህወኃት በኮማንዶ ደረጃ አዲስ አበባ ስንገባ ለVIP ጥበቃ ያስፈልገናል በማለት 180 የሚሆኑ አባላት አሰልጥነው በሁለት ሻለቆች /ጉና እና ወጋገን/ አደራጅተው በኮ/ል ነጋሲ እየተመሩ ቤተ መንግስት ይጠብቁ የነበሩትን እንደመነሻ ወስደን ክ/ጦሩን እንድናደራጅ ተወሰነ።
የክ/ጦሩን የሰው ኃይል ለማሟላት የምልመላ መመዘኛ ወጥቶ ከእግረኛ ሰራዊት በርካታ ወታደር ተመልምሎ ወደ ደብረዘይትና ብላቴ ስልጠና እንዲገባ ተደረገ። በዚህ ዝግጅት ላይ እያለንም ኮ/ል ነጋሲ ወልዳይ ሸሸቢት /አዲሃኪም ላይ/ በሻቢያ መድፍ ተመቶ ሞተ። ከነጋሲ ሞት በኃላ ብ/ጄ ገብረኪዳን የሚባል / አሁን የመከላከያ ኢንዶክትሬሽን ኃላፊ/ በአዛዥነት ተመድቦ መጣ። ገብረ ኪዳንም ብዙ ሳይቆይ ሌላ ብ/ጄ ገብረመድን ፈቃዱ የሚባል በም/አዛዥነት ተመድቦ መጣ /አሁን ክ/ጦሩን እያዘዘ ያለ የአድዋ ተወላጅ/ በነገራች ላይ ከመጀመሪያው ጀምሮ አግአዚን በአዛዥነት እንዲመሩ የተመደቡት ሁሉም የአድዋ ትግሬወች ናቸው ። ከእግረኛ ተመልምሎ ወደ ማሰልጠኛወቹ የገባው ኃይል ስልጠና በኃላ በነበረን በርካታ ሰው ኃይል በብርጌድና በክ/ጦር አደራጀን። በአደረጃጀት ጊዜ መነሻ የነበሩት የህወኃት /ሁለት ሻለቆች/ ሰወች ሙሉ በሙሉ በየደረጃው አመራርነቱን ያዙት። ከአደረጃጀት በኃል ብ/ጄ ፍስሃ ኪዳኔ በአዛዥነት ተመድቦ መጣ፣ እንዲሁም ብ/ጄ ሙሉጌታ በርሄና ብ/ጄ መሃመድ ኢሻ በቅደም ተከተል እየተቀያየሩ ክፍለ ጦሩን አዘውታል።
የክ/ጦሩ ስያሜና የነበረው ፍጭት፤
በርከት ያሉ አዳዲስ አባላት በደብረ ዘይትና ብላቴ የኮማንድ ስልጠና ካጠናቀቁ በኃላ ከነባሮቹ የህወኃት ሻለቆች ጋር ውህደት ተደርጎ ክ/ጦር ሲመሰረት ስሙን እኛ እንድናወጣ ተነገረን፤ ይህንን የማስፈፀም ሃላፊነትም በተለይ ለኔ ተሰጠኝ። እኔም ስሙን እና ተያያዥ ጉዳዮችን ለመፈፀም አንድ ኮሚቴ አቆምኩ። ኮሚቴውን ከአማራ ኦሮሞና ትግሬ ተወላጆች በእኩል ደረጃ አደረኩ እና ወደ ስራው ገባን ስሙን በተመለከተ የተለያዩ አማራጩች ከነምክንያቶቹ ቀረቡ፤ ቴወድሮስ፣ ፈንቅል /የኃየሎም የበረሃ ስም ነው/ ፣ አግአዚ፣ ወልወል የተባሉ ስሞች ከነዝርዝር ምክንያታቸውና አስፈላጊነታቸው በኮሚቴው አባላት ቀረቡ። ብዙ ውይይት አደረግንበት በመጨረሻ ሁለቱ ላይ ተጨቃጭቀን ተግባባን እና ሁለቱንም ለበላይ አካል እናቅርብና እነሱ ይወስኑ ብለን ተስማማን / ቴወድሮስና ፈንቅል/። ይህንኑ ለብ/ጄ ታደሰ ጋውና በወቅቱ የመከላከያ አስተዳደርና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ኃላፊ ለነበረው አቀረብኩ። እሱም ከነ ፃድቃን ጋር መክረውና ወስነው በቀጠሮ ጠራኝና ለክ/ጦሩ መጠሪያ አግአዚ እንዲሆን ከነ ምክንያቱ አስረዳኝ እና ይህንኑ ተቀብየ ወደ ክፍሌ ተመልሸ ለሚመለከታቸው ሁሉ ገለፃ አደረኩ።
ክፍለ ጦሩ ከተመሰረተ በኃላ በአገር ውስጥ በደርግ የኮማንዶና አየር ወለድ ባለሙያወች በነ ጄ/ል ተስፋየ ኃብተማሪያምና ሻለቃ ታምሩ እና ሌሎችም እንዲሁም በውጭ በአሜሪካኖች ሩሲያውችና እስራኤሎች በተደጋጋሚ ስልጠና ተሰጥቷል። በተለያዩ ቦታወች በተለያየ ጊዜ በሞያሌ፣ ጅማ፤ ጋምቤላ፤ አሶሳ፤ ጅጅጋ፤ አሰበ ተፈሪ፤ አሩሲ፤ ሻሼ መኔ፤ አዋሳ፤ ጎዴ፤ ቀብዲዳሃር፤ አዲስ አበባ፤ ፍቸ፤ እና በሌሎችም ህዝቡ በመንግስት ላይ የመብት ጥያቄ ባነሳበት ሁሉ የህዝቡን መብት ለማፈን ክፍለ ጦሩ ግዳጅ እንዲፈፅም ተደርጉኣል።
በተለይም ነባር አባሎች እንደምታስታውሱት በ1993 ህወኃት ከሁለት ሲሰነጠቅ ክ/ጦሩ በነፃድቃን ተፅኖ ስር ስለነበር በመለስ ላይ ታስቦ በነበረው መፈንቅለ መንግስት ለመጠቀም አዘጋጅተውት ነበር። ከነ ፃድቃን ውድቀት በኃላም ጀ/ል ሳሞራ የኑስ በክፍለ ጦሩ ላይ ቂም ይዞ ስለነበረ የኮማንዶ ጥቅማጥቅሙን እና የሚገባውን ትጥቅ እንኩአን እንደማይገባው /የፃድቃን ሰራዊት/ እያለ እስከ መተረብ ደርሶ እንደነበረ የምናስታውሰው ነው። ጌታቸው አሰፋም ቤተመንግስት የአሁኑ አዛዥ ብ/ጄኔራል ገብረመድህን ፈቃዱ /ወዲ ነጮ/ ሻለቃ ተስፋማሪያም ተስፋና እኔን ሰብስቦ ክፍለ ጦሩን ሶስት ሻለቆች ብቻ አስቀርተን ማፍረስ እንፈልጋለን፤ እንዴት እንደሚፈርስ አስባችሁ ስጠራችሁ ትመጣላችሁ ካለን በኃላ ምክንያቱን ሳናውቅ ተግባራዊ ሳያደርገው ተወው።
ይህን ሃሳብ ለማንሳት የፈለኩት ክፍለ ጦሩን ከመጀመሪያም ለግል የስልጣን ፍላጎት መጠቀሚያ አስበው ያደራጁት እንደነበር ለማስገንዘብ ነው። መለስ ተቀናቃኞቹን ካስወገደና የሳሞራም ስልጣን ከተረጋጋ በኃላ አግአዚን ባለበት እንዲቀጥል ፈለገው እንዲያውም ከላይ በጠቀስኩአቸው አካባቢወችና በሌሎችም የህዝብ ቁጣ ሲነሳ አጋአዚ በፍጥነት የህዝብን ጥያቄወች በኃይል ማፈን በመቻሉ የአመራር ለውጥ በማድረግ በትጥቅና በስልጠና እንደገና ለማጠናከር ጥረት ተደረገ።
ክ/ጦሩ ከሻለቃ በላይ ያለው አመራር ፍፁም የትግሬ የበላይነት ያለው ቢሆንም ከሻምበል በታችና ተራ ወታደሩ ግን እስካሁን በቀዳሚነት የአማራ ተወላጆችና በተከታይነት የኦሮሞ ተወላጆች በዝተው ይገኛሉ። ይህ ማለት ለመጥፎም ለመልካምም ነገር ዋናውን ስራ የሚሰራውና ጠመንጃውን የያዘው ግንባር ቀደም ተሰላፊው ማን እንደሆነ በግልፅ ለመረዳት ያስችላል።
እንደሚታወቀው በወያኔ ስርዓት አገዛዙን በመቀዋወምና መብቱን በመጠየቅ በቀዳሚነት እየተንቀሳቀሰ ያለው ሰፊው የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ነው። የዚህን ህዝብ መብት በማፈን እና በመግደል ግንባር ቀደም ሚና እየተጫወተ ያለው ደግሞ የአግአዚ ኮ/ክ/ጦር ነው። በሌላ አገላለጽ በክ/ጦር ውስጥ ያላችሁ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው። በስራ ቆይታየ ከትግሬወች አንድ የተማርኩትና አሁን ላሉበት ሁኔታ ጠቅሟቸዋል ብየ የማስበው፤ በብዙ ነገር ሲጨቃጨቁ ሲጣሉ አያለው በትግራይ ህዝብ፤ ትግራዊነትና በድርጅታዊ ጉዳይ ግን አንድና አንድ ናቸው፡ ልዩነታቸውን ትተው መጥፎም ይሁን መልካም በጋራ ጉዳያቸውና ጥቅሞቻቸው ላይ በአንድነት ይሰለፋሉ ይረባረባሉ። በ1993 እነ ጀ/ል ፃድቃን ከመከላከያ በከባድ ሁኔታ ሲወጡ እነ መለስ የሚምሯቸውና በቀላሉ የሚለቁአቸው አይመስሉም ነበር / ሁኔታውም ከባድ ነበር እና/ ከወጡ በኃላ ግን ሁሉም በጡረታ /በክብር/ እና ዳጎስ ባለ ጉርሻ ጭምር ከነክብራቸው መሸኜታቸውን ስንሰማ ገርሞን ነበር። የ1997 ምርጫን ተከትሎ አገዛዙ በምርጫ በደረሰበት ኪሳራ በተለይም የአማራውን ህዝብ ጥርስ እንደተነከሰበት ይታወቃል፤ በህዝቡ ብቻ ሳይሆን በስርዓት ውስጥ በነበርን አማራወች ሁሉ ጥላቻቸው በግልጽ ይታይ ነበር። እኛም ሁኔታቸው ስላላማረን ራሳችን ለመከላከልና ሂደታቸውን ለመኮነን በፀረ-ህወኃትነት ተሰለፍን፤ ህወሃትን መክፈልም ማዳከምና ሂደቱን መቀየር ይቻል ብለን በማሰብ ጀ/ል ፃድቃንን ለማነጋገር ወሰን፤ ጻድቃን ቀደም ሲል በሰርዊቱ የነበረውን ሁኔታ ተጠቅሞ አሁንም ተፅኖ ይፈጥራል ብለን እናስብ ነበር። ሁለት ሁነን ፖሌ መድሃኒያለም ጀርባ ከፍቶት ከነበረው “የግጭትና ጥናት ምርምር” ምናምን የሚባል ቢሮ ከፍቶ ይሰራ ነበር። በደቡብ ሱዳንም የፀጥታ አማካሪ ሁኖ ለUN እና ለደቡብ ሱዳን መንግስት ይሰራ እንደነበር እናውቅ ነበር። ወደ ቢሮው ሂደን ሰውየውን አግኝተን በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ብዙ ከተነጋገርን በኃላ የመለስና የሳሞራ አካሄድ ወደ ጥፋትና ግጭት መንገድ እየሄዱ ስለሆነ ለምን ተባብረን አናስተካክለውም የሚል ጥያቄ አነሳንለት። እሱም ያነሳችሁት ልክ ነው ይገባኛል አሁን ግን ምንም ማድረግ አይቻልም ጊዜ መጠበቅ ይሻላል ይልቁንስ ከመከላከያ ውጡና ደቡብ ሱዳን በጥሩ ደመወዝ ልላካችሁ አለን። በዚያን ጊዜ በርካታ የትግሬ መኮነኖችን እንደላከና ተጠቃሚ እንዳደረገ እናውቃለን። እኛንም ብንፈልግ ሊልከን እንደሚችልም ተረድቶናል ግን ፍላጎታችን ያ ስላልነበረና እንዳልተሳካልን ስለገባን እሱ ባቀረበልን ሃሳብ ጉዳይ አስበን ሌላ ጊዜ እንደምንገናኝ ተነጋግረን ተለያየን። በሌላ ጊዜ አንድ በጣም የምቀርበውና ብዙ ጊዜ አብሬው የሰራውት ትግሬ ጄኔራል ጋር ስናወራ ስለ ፃድቃን አነሳን እና ጻድቃን እኮ በጣም አስተዋይ ነው እነ ገብሩ አስራት ህወኃት ላይ ስራ እንስራና መለስ እንዲወርድ እናድርግ ሲሉት እሱ ግን አይ በአሁኑ ሰዓት ለትግራይ ከመለስ የተሻለ የለም አላቸው። መለስም ይህንን ስለሚያውቅ በደቡብ ሱዳን ለUN አማካሪ መሆን እንደሚችል ፕሮፖዝ አደረገው ብሎ ነገረኝ። ሌላ ነገር ልጨምር በዚያው 93 በነበረው ልዩነት በርካታ ጀኔራሎች ፃድቃንን ተከትለው መለስን በመፈንቅለ መንግስት ለማስወገድ ከነ ተወልደ ወልደማሪያም ጋር ተሰልፈው ነበር፤ እነ ጀ/ል ገዛይ አበራ, ጀ/ል ሳረ መጆነን ጀ/ል ብርሃኔ ነጋሽ ጀ/ል አብርሃ ተወልደ ጀ/ል ዮሃንስ ገብረ መስቀል ኮል ተወልደ ፍስሃ እነዚህ ወሳኝ የአዛዥነት ቦታ ላይ የነበሩ ከነ ፃድቃን ቡድን ተሰልፈው የነበሩ ናቸው። ታዲያ ሁሉም ስህተታቸውን
እንዲያምኑ ከተደረጉ በኃላ ለ3 ወር ብቻ ከነበራቸው ኃላፊነት አንዳንድ ደረጃ ብቻ ዝቅ ብለው ከቆዩ በኃላ ተመልሰው ወደ ነበሩበትና ከዚያም በላይ የኃላፊነት ቦታ ተመለሱ።
በአንፃሩ በውል እውነት መሆኑን ባላረጋገጡት ጉዳይ ላይ የእኛወቹን የአማራ መኮነኖች እነ ጀ/ል ኃይሌ ጥላሁን ጀ/ል ተፈራ ማሞ ጀ/ል አሳምነው ፅጌ ኮ/ል ደምሰው አንተነህ ኮ/ል መኮነን ወርቁ እና ሌሎችም በርካቶችን መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ አስባችኃል በሚል ሰበብ በጭካኔ በምርመራ አቃጥለውና አሰቃተው፤ ለእስር ዳርገው ቤተሰባቸውን በትነዋል። የ1997 ምርጫን ተከትሎ ሰራዊቱ ውስጥ ያለው /በአግአዚም ጭምር/ አማራና ኦሮሞ በጠላትነት ተፈርጆ ስንት ስቃይና መከራ እንደነበር ታውቃላችሁ። በአስር ሽወች የሚቆጠሩ የአማራና የኦሮሞ ተወላጆች የሰራዊት አባላት በጅምላ ታስረዋል፡ በምርመራ ተሰቃይተዋል ያለምንም ጡረታና ድጎማ ተባረዋል። ይህ ሁሉ ሲደረግ የአንተ ዘር የሆነው አማራውና ኦሮሞው ተለይቶ እንጅ አንድም የትግሬ ተወላጅ ላይ የደረሰ ነገር አልነበረም እንዴውም በየቦታው በምርመራ ስራ ተመደበው ያን የመሰለ ዘግናኝ ግፍ የፈፀሙት የትግሬ ተወላጆች ብቻ ነበሩ። ታዲያ ይህ ስርዓት የማን ነው ትላለህ?
እኔም በነበረኝ የኮማንድ የአመራር አባልነቴ የትግሬ አመራሮች በክፍለ ጦሩ ይፈፀሙ የነበሩትን ዘረኝነትን ለመታገል ብዙ ብጥርም በነበራቸው ስብስብና የበላይ አካል ድጋፍ አልተሳካልኝም። የአመራር ምደባና የአደረጃጀት ለውጦች ባደረግን ቁጥር የሰው ኃይል ምደባ ላይ ከባድ ፍጭት እናደርግ ነበር። እነሱ ከላይ እስከ ታች አመራሩን ትግሬ እንዲይዘው ካላቸው ፍላጎት አንፃር በጣም እቸገር ነበር። እንዴውም አንዳንዴ የበላይ አካል ይወስነው ብለው እንድናልፈው ይደረግ ነበር ያው የበላይ አካሉ ሳሞራ ስለነሆነ እሱን ደግሞ እነሱ ስለሚያገኙት ጨዋታው ለነሱ ቀላል ነበር። በነሱ ጥርስ ውስጥም ሁኜ የአማራውን እና የኦሮሞውን ልጆች መብት በተወሰነ ለማስከበር የቻልኩ ቢሆንም ከኔ በኃላ ግን የአማራን እና የኦሮሞን አመራር ጠራርገው የተወሰነውን ወደ እግረኛ እንደላኩትና የበዛውን ደሞ ካለምንም ክፍያ እንዳሰናበቱት እናንተም ታውቃላችሁ። ይህ ተጠራርጎ ወደ እግረኛና ወደ ቤቱ የተባረረው አመራር በብቃት ወይም በስነ-ምግባር ጉድለት ሳይሆን በዘሩና በማንነቱ ስላልተፈለገ ነበር።
የትግራይ ገዥ መደብ የጭቆና አገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም በዋነኛነት አንተን በመሳሪያነት በመጠቀም ለመብቱና ለነፃነቱ ሰላማዊ ጥያቄ ያነሳውን የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ጥያቄን ዕድታፍንና ወገንህን እንድትገድል እያደረገህ ነው። እነሱ እንወክለዋለን እንጠብቀዋለን እናበልፅገዋለን ብለው የተነሱለን የትግራይን ህዝብ በሰላም እያኖሩ አንተ የተፈጠርክበት የአማራና የኦሮሞ ህዝብ ግን በአንተና በአገዛዙ ታጣቂወች በየቀኑ ይገረፋል ፣ይታሰራል ፣ይገደላል። ለምን ብለህ ማሰብና ማሰላሰል ይኖርብሃል። ከጨካኞች የባዕድ ገዥወች ወግነህ የራስክን ወገን ከመጨፍጨፍ ወገንህን መከላከል ታሪካዊ ግዴታህ ነው። እንደምትረዳው በአሁኑ ሰዓት የዘረኛው የወያኔ አገዛዝ በመንኮታኮት ላይ ሲሆን በአንፃሩ የህዝቡ የነፃነት ትግል ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህንን እየሞተ ያለ ብስባሽ ጨርሶ ለመቅበር ከአንተ ከአግአዚ የአማራና የኦሮሞ አባላት የሚከተሉትን እንድትፈፅም በሚጨፈጨፈው ወገን ስም እጠይቃለው።
1ኛ. አንተም ሆንክ የመከላከያ ሰራዊቱ ዋነኛ ግዳጅ ዳር ደንበር መጠበቅ እንጅ ሰላማዊ ወገንህም መጨፍጨፍ አይደለም። ስለሆነም ከተልኩአችን ውጭ ሰላማዊ ህዝባችን ላይ አንዘምትም በል።
2ኛ. የህዝብ ልጅ ነህና ህዝብ የጠየቀውን የመብት ጥያቄ አንተም ጠይቅ፣ መሳሪያህን አስቀምጠህ ከህዝቡ ጋር አብረህ ጩህ።
3ኛ. በጦር ክፍልህ ውስጥ በእርስትነት /ውርስ/ በትግሬወች የተያዘውን የአመራር ቦታ ይገባኛል በል። በቃ ሁል ጊዜ በትግሬ አልታዘዝም በል።
4ኛ. በየደረጃው ያሉት የትግሬ አዛዞች የሚፈጽሙትን ሙስና እና ብልግና ያለ ምህረት አጋልጥ ታገል።
5ኛ. በየቦታው ህዝብን እንድትጨፈጭፍ የሚሰትህን ግዳጅ እምቢ በል፣ በኃይል ፈፅም ከተባልክ መሳሪያህን በትግሬ አዛዦች ላይ አዙረው።
6ኛ. ከላይ ያልኩአቸውን ነገሮች በድፍረት ተግባራዊ አድርጋቸው፣ በዚህ የማይታረሙ ከሆነ ከሌሎች ከሚመስሉህ ጋር ተነጋገር ከነ ሙሉ ትትቅህ ወደ ህዝብህ ተቀላቀል።
እኔ በበኩሌ የትግሬ ወያኔ ወንጀለኛ ቡድን በአማራና በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ያለውን የጠላትነት አቁአምና ተግባር እንደተረዳሁ ከሌሎች ወንድሞቸ ጋር በመሆን የተቻለውን ያክል የውስጥ ትግል አድርገናል። አሁንም በቻልኩት ሁሉ በአማራ ህዝብና በአገር ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት ለመታደግ ክህዝብ ጎን ሁኜ እየታገልኩ ነው። እናንተም የኔንና ከህዝብ ጎን ሁነው ከሚታገሉ ወገኖቻችን ፈልግ እንድትከተሉ አጥብቄ በድጋሜ እጠይቃችኃለው።
ወገኖቸ እስካሁን አውቃችሁም ይሁን ሳታውቁ ወገናችሁን አድምታችኃል ገድላችኃል፣ አሁን ግን በቃን በማለት የበደላችሁትን ወገናችሁን በመካስ ታሪካችሁን አድሱ። ወያኔ እየተንኮታኮተ ያለ ወንጀለኛ ቡድን ነው፣ ለዚህ ደመኛ የህዝብ ጠላት መጠቀሚያነታችሁ ይብቃ። ዛሬውኑ ወስኑና ንስሃ ገብታችሁ ወደ ህዝባችሁ ወግኑ።
በዚሁ ነፍሰ ገዳይ በሆነ አግአዚ ክ/ጦር ውስጥ ተቀጥረው መጠቀሚያ የሆኑ ወላጆችና ቤተሰቦች፤ ልጆቻችሁ የፋሽስቱ ትግሬ ወያኔ የስልጣን ማራዘሚያ በመሆን በወገናችሁ ላይ ጭፍጨፋ በመፈፀም መጠቀሚያ ሁነው ይገኛሉ። ልጆቻችሁ ከእንዲህ አይነቱ ታሪክ ከማይረሳው ጥቁር ጠባሳ እንዲቆጠቡና በአስቸኩኣይ ወደ ህዝቡ እንዲወግኑ የበኩላችሁን ተፅኖና ምክር በልጆቻችሁ ላይ ልታሳድሩ ይገባል።
አለበል አማረ /ኮሎኔል/




     
:)

No comments:

Post a Comment