Tuesday, August 23, 2016

አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ አስታውቋል ኢትዮጵያውያን 43 ሺሕ ዶላር አሰባስበውለታል



አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ወደ ኢትዮጵያ እንደማይመለስ አስታውቋል ኢትዮጵያውያን 43 ሺሕ ዶላር አሰባስበውለታል VOA Amharic.

የ26 ዓመቱ ፈይሳ ሌሊሳ በትናንትናው በሪዮ ኦሎምፒክ የወንዶች ማራቶን የብር ሜዳልያ ያሸነፈበትን ሩጫ አጠናቆ ሲገባ በኦሮሞ ተቃውሞ ጊዜ የተጀመረውና በአሁኑ ሰዓት በኢትዮጵያ የተቃውሞ ምልክት የሆነውን እጅ ማጣመር ምልክት እያሳየ ገብቷል።

ይህን በማድረጉም ወደ ኢትዮጵያ ቢመለስ የግድያ ፣ የእስራት እና ፓስፖርት መቀማት ስጋት ስላለበት ወደ ሀገሩ እንደማይመልስ አስታውቋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት በበኩሉ አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ እንደሌሎቹ የኢትዮጵያ አትሌቶች ሜዳልያ ያመጣ ብሄራዊ ጀግና ነው፤ ሃሳቡን በነጻነት መግለጽ ይችላል፤ ወደ ሀገሩ ቢመለስ ምንም ዓይነት ጉዳት አይደርስበትም ብሏል።
አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ በበኩሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ሁሌም ስለሚዋሽ በምን አምነዋለሁ? ብሏል።
በሌላ በኩል በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ፈይሳ ሌሊሳን የሕግ ድጋፍ እንዲያገኝ በሰዓታት ውስጥ ወደ 43 ሺሕ ዶላር ወይም ወደ 1 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር አሰባስበዋል።
ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።
Audio Player
 በ2008 ዓ.ም ሪዮ ኦሎምፒክ በማራቶን ውድድር የብር መዳልያ ተሸላሚ ፈይሳ ሌሊሳ በሽልማት ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት

No comments:

Post a Comment