Saturday, August 20, 2016

እሁድ ነሐሴ 15 የአዲስ አበባ ሕዝብ ተዓምር መስራት ይችላል – #ግርማ_ካሳ



14079672_1166966676677922_3985789490660935716_n
አገር መለስተኛ የርስ በርስ ጦርነት ዉስጥ እየገባች ነው። ሲሪያም፣ ሊቢያም ሲጀመር እንደዚህ ነበር….ከጎንደር እና ከጎጃም አልፎም፣ ወታደሮችን በሸዋና በወሎ መገደል ተጀምሯል። የመንግስት የደህነነት ወይንም የመከላከያ ሰራዊት አባል መሆን አደገኛ የሆነበት ወቅት ነው። በርካታ የአማራው ክልል ፖሊሶችና የጸጥታ ሃይሎችም አንታዘዝም እያሉ ነው። በብዙ የአማራው ክልል የገጠር ከተሞች ወልቃይት ጠገዴንም ጨመሮ መንግስት የለም። በጎበዝ አለቃ ነው የሚተዳደሩት።
በኦሮሚያ ክልል ላለፉት 9 ወራት ሲደረግ የነበረው ተቃዉሞ መልኩ መቀየር አለበት፣ ወደ አመጽ መሄድ አለበት የሚሉ ቁጥራቸው እየጨመረ ነው። ምናልባት ሰልፍ እያደረጉ ተቃዉሞ ከማሰማት ባለፈ፣ የሃይል እርምጃዎች በአገዛዙ አገልጋዮችና በአጋዚ ጦር ላይ ሊጀመርም ይችላል። ወለጋ፣ ሃረርጌ፣ ምእራብ አርሲ የመሳሰሉት አካባቢዎች በቀላሉ ከመንግስት ቁጥጥር ዉጭ የመሆን እድላቸው የሰፋ ነው።
ከላይ እንደተዘረዘረው ሁኔታው የበለጠ እየከፋ እንዳሄድ  ወያኔዎች በሁሉም አቅጣጫ ለብሄራዊ እርቅ እንዲዘጋጁና የሽግግር መንግስት ይመሰረት ዘንድ ገለል እንዲሉ ግፊት እየተደረገባቸው ነው። እንደዚያም ሆኖ ግን ወያኔዎች በግትርነታቸው እንደቀጠሉ ነው። ምክንያቱም አዲስ አበባ መሸሸጊያና መፈንጫ ስለሆነቻቸው።
የአዲስ አበባ ሕዝብ ግን ይሄን ሁኔታ በመቀየር በአገራችን ለሁሉም የሚበጅ መሰረታዊ ለውጥ እንዲመጣ ማድረግ ይችላል። ወያኔዎች አገርን ድምጥማጧ እንድትወጣ ከማድረጋቸው በፊት የአዲስ አበባ ህዝብ ሊያስቆማቸው ይገባል።
የአዲስ አበባ ህዝብ ለትግሉ ዋጋ የከፈለ ህዝብ ነው። በጎንደር ለተደረገው ሰልፍ አጋርነቱን ለማሳየት ሐምሌ 30 ቀን በአዲስ አበባ ሰልፍ ተደረጎ ነበር። ህወሃቶች ሃይል ተጠቅመው የሕዝቡን ድምጽ አፈኑ። ያን ያደረጉት ለማስፈራራት ነበር። “ከደበደበነው፣ ከገረፍነው፣ ካሰርነው፣ የአዲስ አበባ ሕዝብ ፈሪ ህዝብ ነውና አርፎ ይቀመጣል” በሚል ስሌት።
ግን አልሆነላቸውም። እንደገና በአዲስ አበባ ሰልፍ ተጠርቷል። ነሐሴ 15 ቀን እሁድ። የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ድምጻቸውን እንደገና የሚያሰሙበት ሌላ አጋጣሚ ከፊታቸው ቀርቦላቸዋል።
አዲስ አበባ ተቀምጠው ፣ በአዲስ አበባ ዊስኪ እየተራጩ በየ ከፍለ ሃገራቱ የወገኖቻችንን ደም በግፍና በጭካኔ ሲያፈሱ ዝም የምንልበትና የምንታገስበት ጊዜ ማብቃት አለበት። አንድ ለአምስት የሚሉት ነገር አለ። አንዱ የወያኔ ካድሬ ለአመታት አምስታችንን ሲያሰር ቆይቷል። አሁን ግን መንቃት አለብን። ከአንድ አምስት እንደሚበልጥ መረዳት አለብን። እኛ አምስት ሆነን እንዴት አንዱ አንገታችንን ሊያስደፋን ይችላል ?
የአዲስ አበባ የሸገር ወገኔ አንተ ከጎንደርና ከባህር ዳር ወንድምህ አታንስምና ለመብትህ ተነሳ። በሁሉም ቀበሌውዎች፣ እድሮች፣ ክፍለ ከተማዎች ህዝብ ከተነቃነቀ አጋዚ በሁሉም ቦታ መሆን አይችልም። ጉለቴ፣ ሳሪስ፣ ላፍቶ፣ ኮልፌ፣ አየር ጤና ፣ ስድስት ኪሎ፣ ፈረንሳይ ….ሁሉም በፊናቸው ከተነሱ አስደናቂ የነጻነት ችቦ በርቶ እናያለን።
የአዲስ አበባ ፣ የሸገር ወገኔ ሆይ፣ ከቤትህ ስትወጣ ቀይ ፊኛዎች ይዘውህ ውጣ። ፊኛዉን ወደ ሰማይ ልቀቀው። ያ ም ቀይ ካርድ ለአገዛዙ መስጠትህን የሚያሳይም ሌላ ምልክት ይሆናል።
ያለ ምንም ደም፣ ኢትዮጵያ ትቅደም!!!

No comments:

Post a Comment