Tuesday, August 9, 2016

ትግሉን ለህዝባዊ ድል ለማብቃት……..!!!



ትግሉን ለህዝባዊ ድል ለማብቃት……..!!!

አሁን ያለው ህዝባዊ አመጽ በመላው ሀገሪቱ ለመቀጣጥጠል የበቃው የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ቀጥፎ፣ ለእስር፣ ለስደትና ለምድራዊ ስቃይ ዳርጎ ነው። የ’ስካሁኑ ትግል ለድል ያለበቃው፤ ወያኔ የፈነጨውና ሀገራችን እስከማፈራረስ ደረጃ የተቃረበበት ዋና ምክንያት ተደራጅተን የጋራ ሀይል ያለመያዛችንና የወያኔን ማንነት ያለመረዳታችን ነው። ወያኔን መነሻውን፣ አሁን ያለበትንና የአጭር ግዜና የረጅም ግዜ መረሀ ግብሩ ካላወቅነው፤ እንዳለፈው የትግል ዓመታት ሁሉ ዛሬም ርስ በርስ መጠላለፍ…… ተበደልኩኝ ባዩ፣ ሎሌ – አዳሪው በዝቶ የችግራችንም ፣.ውል -ማሰሪያው ጠፍቶ፤ የሄደው – ሲመጣ፣ የመጣው – ሲሄድ መውጫና መውረጃው፣ ሆኖ የአገር መንገድ፤ ብዘራው አይበቅል፣ ቢበቅል አያፈራ መጠላለፍ ሆኖ፣ ቀረ የ’ኛ ስራ።…………… አሁንም ከዳር እስከዳር የተቀጣጠለውን የህዝብ አመጽ ካልተድራጅንና ካላደራጀነው፤ ካለመራነው፣ ካላቀነባበርነው፤ ሀገራዊ ዓላማ ይዘን በአንድነት እስካልታገልን ድረስ ውጤቱን መገመት አያዳግትም።

በርግጥ ከጎንደሮች ህዝባዊ አመጽ ብዙ የምንማረው አለ። ስለዚህም፤ – ማንም ኢትዮጵያዊ ማወቅ ያለበት ነገር ወያኔ የመጨረሻ ግብ ኢትዮጵያ የተባለች ሀገር በማፈራረስና ኢትዮጵያዊ የሚባል ዜጋ በማጥፋት ‘ርስ በርሳችን ተባልተን እንድንተላለቅ ነው። ለዚህ ዓላማቸው ደግሞ ማንኛውንም ሰይጣናዊ ምግባር ሁሉ በዚች ሀገርና ህዝብ ላይ ይፈጽማሉ፤ እየፈጽሙም ነው። እናም ‘ርስ በርስ አባልቶና በልቶ ሀገር ሳያሳጣን…. እንተባበር! ……እንደርጅ! – ወያኔ እንጅ ኢህአዲግ የሚባል ነገር ባለመኖሩ ”የወያኔን” ስም ብቻ በማንኛውም ቦታን ጊዜ መጠቀም። – ወያኔ ገዥ እንጅ መንግስት ስላልሆነ መጠቀም ያለብን የኢትዮጵያ መንግስት በማለት ሳይሆን የወያኔ ገዥዎች ፤ ወያኔዎች በማንኛውም መስፈርት የኢትዮጵያን ህዝብ አይደልም ታገልንለት ያሉት ቀበሌ አይወክሉም።
—1– –
ወያኔ የሚጠቀምበትን የጎሳ (የክልል) አጠራራ አለመጠቀም፤ ምክንያቱም ዛሬም ሆነ ነገ የምንተላልቅበትንና ተያይዘን ገደል የምንገባበት የወያኔ ወጥመድ ብቻ ሳይሆን ትግሉ አድነት አንዳይኖረው በአካባቢው እንዲወስን ከማደረጉም በላይ ለወያኔ እየነጣጠል ለመምታት ያመቸዋል። – በየቦታው የተነሳው አመጽ እያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ የሚመለከት በመሆኑ፤ ትግሉ የመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል መሆኑን እንቀበል። በማህበራዊ መገናኛወችም የኢትዮጵያ ህዝብ ትግል እያልን እንጠቀም:: – የተነሳውን ህዝባዊ አልገዛም ባይነት የተለያየ ዓላማ እንዳለው አደርገን ማቅረባችንና የመንደር ወይም የጎጥ ስም በመስጠት ለወያኔ ስራ መተባባራችን አቁመን ፤ ትግሉ የሁሉሙ ፍትህ ፈላጌ በመሆኑ ኢትዮጵያዊ ስምና አንድምታ እንስጠው። – ህዝባዊ አመጽ ለማካሄድ ማሳወቅ እንጅ ወያኔ እንዲፈቅድልን መጠበቅ የለብንም። ፈቃድ መጠየቁን የወያኔ ተቃዋሚ ነን ለሚሉ እተወው:: – የአንድ አካባቢ ህዝብ ሰላማዊ ሰልፍ ሲጠራ፤ የትብብር ጥሪው ወያኔ ላሰመረው ክልልና መንደር መወሰኑ ቀርቶ ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይሁን። – የወያኔ ተቃዋሚ ነን የሚሉት በዚህ ወሳኝ ሰዓት ፤ የህዝብ ደም እንደጎርፍ እየፈሰሰ፤ አንዳንዶቹ እንደሰጎን ራሳቸውን አሸዋ ውስጥ ለመደበቅ እየሞከሩ ሲሆን፣ አንዳዶቹ ደግሞ ባህርማዶ ጉብኝት ላይ ናቸው። ሁለትም፤ ሶስትም ….በመሆን .እራሳችን በራሳችን አናደራጅ እንጅ ከነሱ ምንም አንጠብቅ። – ከወያኔ ባልተናነስ “ተቃዋሚወች “ ትግሉን ስለሚያደናቅፉና በወያኔ ሆድ አደሮች የተሞሉ በመሆኑ፤ በምንም መንገድ ከነሱ ጋር ግንኙነት ማደረግ ወይም ራስን ከማሳወቅ መጠንቀቅ ያስፈልጋል። – የተደራጅን ግለስቦች በተቻለንና ጥናቃቄ በተሞላበት መንገድ በሀገሪቱ ውስጥ ከመሀል እስከዳር፤ ከዳር እስከመሀል ካሉ የትግል አጋሮች ጋር መረብ መዘርጋትና ትግሉን ማቀናጀት። በተለይም አዲሳባ ውስጥ ህዝባዊ አመጽ ማቀጣጠል ወሳኝነት አለውና በመደራጅት የተበታተነውን ህዝባዊ አመጽ ማአከላዊነት እንዲኖረው ማደርግ ይጠበቅብናል። – ጥላቻን ማስወገድ! …. በማንኛውም መስፈርት ቢሆን ከጥላቻ የሚሰበሰብ መከር ጥላቻ ነው። ወያኔያዊነት ነው። አካባቢን ወይም አመለካከተን መሰረት ያደረገ ጥላቻን በየትም ቦታና ሰዓት ቢሆን ማሰወገድ። ትግላችን ወያኔ ተወልዶ ያደገበትንና የሀገራችን ህልውና አደጋ ላይ የጣለበትን ጥላቻንና ጎጠኝነትን መታገል ነውና።
—2— –
ህዝባዊ አመጽ በምናደርግበት ወቅት በተቻል መጠን በሰው ህይወት ላይም ሆነ በህዝብ ንብራት ላይ ጉዳት እዳይደርስ ስሜታችን መቆጣጠርና ርስ- በርሳችን መጠባበቅ ይጠበቅብናል። – በህዛባዊ አመጽ ወቅት የሚጎዱ ወጎኖቻችን ለመርዳት የህክምና ባለሞያወች የህክምና መሳሪያወችንና አስፈላጊ መደሀኒቶችን ይዘው እንዲገኙ ማደርግ። – የገዥው ወታድሮች የሚፈጸመው ግፍ በወገናቸው ላይ መሆኑን ተረድተው በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ከመተኮስና ደም ከማፍሰስ እንዲታቀቡ ና ህዝባዊ አመጹን እንዲቀላቀሉ ያለያም ገለለተኛ በመሆን የወያኔን ውድቀት እንዲያፋጥኑ በተለያየ መንገድ ጥሪ ማድርግና የውስጥ ስራ መስራት። – ከዚህ በፊትም ሆነ ወደፊት ከውያኔ ጋር ሲታገሉ መሰዋ’ትነት ለከፈሉና በእስር ለሚገኙ ቤተሰቦች የተቻለውን እርዳታና ትብብር የሚደረግበትን መንገድ መፈለግ። – ህዝባዊ አመጹ እስከ አፍንጫው ከታጠቀ እንደ ወያኔ ካለ ኢትዮጵያኖችንና ኢትዮጵያን ማጥፋት አላማ አድርጎ ከተነሳና በገደለና ባሰቃየን ቁጥር ርካታ ከሚያገኝ መንደርተኛና ባንዳ ቡድን ጋር የሚደረግ ትግል በመሆኑ፤ ትግሉ በጦርነት ከሚካሄድ ትግል የከበደና የከፋ ቢያደርገውም፤ ለሀገራችን ከጠበጃ ሀይል ነጻ የሆነ ትግል በማካሄድ ለድል ማባቃት እንድሚቻል፤ ለኛ ብቻ ሳይሆን ለመጭው ትውልድም ፈር ቀዳጅ ማደርግ መቻል አለብን። – በየአካባቢው የሚገኙ ሆድ አደር የባንዳ ምስለኔዎችን በማህበራዊ ድህረ-ግጾች ፎቶግራፋቸውንና ማነንታቸውን ማጋለጥ። – ወያኔወችና ሆድ አደሮቻቸው ለሚፈጥሩትና ለሚነዙት ተራ የዘረኝነና ማወናበጃ ጊዜም ሆነ ቦታ አለመስጠት። – በቡድንም ሆነ በግል የምንታገል ዜጎች ራሳችን ለማንኛውም ለሚገጥመን ወያኔያዊ ፈተና በመንፈስም ሆነ በስሜታችን ሙሉ ዝግጅት ማድርግ፤ አልበገር ባይነታችንና ቆራጥነታችን ይረዱት። – በየአጋጣሚው ሁሉ በወያኔ ስር ሆነው አገልግሎት የሚሰጡትን ዜጎቻችን የውስጥ ስራ እንዲሰሩና ወያኔን እንዲቦረቡሩት ማግባባትና ሀገራችን ያለችበትን አስከፊ ሁኔታ ማሰርዳት የትግሉ አጋር እንዲሆኑ ማግባባት። – ህዝባዊ አምጽ ለማካሂድ ስንነሳ በቂ ዝግጅት ማድረግ፤ እንደችሎታንና አንደ አቅማችን የስራ ክፍፍል ማደርግ ብቻ ሳይሆን መደማመጥና መተሳሰብ ከየአንዳንዱ ዜጋ የሚጠብቅ ነው።
—3— –
ከሌላው ዓለም ምንም አንጠብቅ፤ እንዲያውም የውጭ መንግስታት የወያኔን ዕድሜ ለማራዛም ማንኛውም ሀገራዊ ትግል ከምደናቀፈና ከማዳፈን ወደ ኋላ አይሉም። እነሱ ለነሱ የሚሰግድላቸውና ጥቅማቸው እስከተጠበቀላቸው ድረስ፤ ከቻሉ ለወያኔ” ኒውከለር” ያበድሩታል። እኛ ጠንካራና በሁለት እግራችን ከቆምን፤ ብሎም ወያኔን እንደምናስወግደው ከተረዱ፤ እኛ ሳንሆን እነሱ ወደ እኛ ይመጣሉ። ያኔ ድግሞ የሀገራችንና የህዝባችን ጥቅም በማስቀደም ግንጡነት ማድረግ እንችላለን። – ትግላችን አንድነትና ሀገራዊነት እንዲኖረው ወያኔ ሰፍቶ የሰቀለውን ጨረቅ ከማውለብለብ እንታቀብ። – መረጃ የዘመኑ አንዱና ዋና የትግል መሳሪያ በመሆን፤ ጠቃሚ መረጃወችን በተገቢው ቦታንና ሰዓት መጠቀም፤ መለዋወጥ። – የህዝባዊ አምጽ መሪዎችና አዘጋጆች ፤ ሊደርስባቸው የሚችለው አደጋ ከፈተኛ በመሆኑ፤ እነሱን ሊተኩ የሚችሉ በቅድሚያ ማዘጋጅት ለትግሉ ቀጣይነት ወሳኝነት አለው። – በራስ በመተማማን ለድል እንደምንበቃና ኢትዮጵያ ሁላችንም በጋራና በኩልነት የምኖርባት፤ የህግ የበላይ የሚከበርባት ሀገር እንደምነደርጋት ማመን። – ከወያኔ ጋር ድርድርና የመሳስሉት ነገሮች ቦታ ስሌለላቸው፤ ወያኔን መጠየቅም ሆነ መታገል ያለብን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ስልጣኑ እንዲለቅና ለህዝብ እንዲያስረክብ ነው። ለዚህ ለመብቃት ደግሞ እኛ ተደራጅተንና ብቁ ሆኖ መገኘት ይጠበቅብናል። ኢትዮጵያ……… እናት- አራስ መሆን እወቂበትና ማሀጸንሽን ባርኪው፤ አልመከንሽምና፤ ላንች ክብር ዝና፣ ለህዝብሽ ልዕልና ሞቼ እየተነሳው፣ ልሙት እንደገና፤ አንድ ሞት ለሀገሬ፣ አልበቃትምና የሚል ታደርሻለሽ፣ ዛሬም ቀና አለና።……..

No comments:

Post a Comment