Saturday, August 6, 2016

” አማራና ኦሮሞዎች በመቀናጀት ከህወሃት ነጻ የሆነችዉን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በሚገነቡበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን ::” የኦሮሞ አክቲቪስቶች=



የኦሮሚያ ተቃዉሞ ይዘቱን ሊቀይር ይችላል ተባለ
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Oromoprotests‬ ‪#‎Amharaprotests‬ ‪‬
 
” አማራና ኦሮሞዎች በመቀናጀት ከህወሃት ነጻ የሆነችዉን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በሚገነቡበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን ::” የኦሮሞ አክቲቪስቶች============================ ===========================================ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ በነበረዉ የተቃዉሞ ሰልፍ ላይ የተሳተፉ አክቲቪስቶችን ቢቢኤን አነጋግሮ ለመረዳት እንደቻለዉ ህወሃት መራሹ መንግስት ቀይ መስመርን በማለፉ የትግል ስትራቲጂን መቀየሩ ተገቢ መሆኑ በኦሮሞ አክቲቪስቶች ዘንድ ታምኖበታል።ህገ መንግስታዊ መብት ይተግበር ያሉ ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች እጃቸዉን ወዳላይ ባነሱበት በጥይት ተመተዋል።መሬት ላይ በወደቁበት በከስክስ ጫማ ተረግጠዋል። ይህ መቀጠል የለበትም ህዝብ የበላይነቱን ሊአስከብር ይገባል ሲሉም ተጣርተዋል አክቲቪስቶቹ።በኦሮሚያ ዉስጥ ዛሬ የንጹሗን ደም መፍሰሱን የሚያስረዱት አክቲቪስቶች ሰልፍ ተሰልፎ ተግድሎ መመለሱ ያበቃል፤የእስትራቴጂ ለዉጥ በቅርቡ ይኖራል ሲሉም ገልጸዋል።
 
የኦሮምያ ክልላዊ መንግስት በተለያዩ ቦታዎች በአጋዚ ቁጥጥር ስር መዋሉን ለቢቢኤን የገለጹት አክቲቪስቶች ኦሆዴድ አይደለም ህዝቡን ከጥቃት ሊከላከል ቀርቶ እራሱን ማዳን ያልቻለ በመሆኑ ህዝቡ እዉቅናዉን ነፍጎታል። አጋጣሚዉንም በመጠቀም ከህዝብ ጋር መደባለቅ አለበት ሲሉም ጥሪ እቸዉን አቅርበዋል።የኦሮሞ ህዝብ በተላላኪዎች መመራቱ ማብቃት አለብት የሚሉት አክቲቪስቶች ህዝቡ ህወሃት አምጥቶ በሚጭንበት ሆድ አደሮች ሳይሆን እራሱን የማስተዳደር ብቃት ያለዉ በመሆኑ እራሱን ለማስተዳደር የሚያደርገዉ ተጋድሎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አሳዉቀዋል።
 
ሰማኒያ ከመቶ ከሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ህወሃት መራሹ መንግስት ተጣልቷል። አማራና ኦሮሞን ከአመራር መዋቅር ለማራቅ ህወሃት ብዙ ሞክሯል። አማራና ኦሮሞዎች በመቀናጀት ከህወሃት ነጻ የሆነችዉን አዲሲቷን ኢትዮጵያ በሚገነቡበት ታሪካዊ ወቅት ላይ እንገኛለን ሲሉ አሳዉቀዋል። ህዝቡ ነጻነትን ለመቀዳጀት ያለዉ ፍላጎት የላቀ ነዉ የሚሉት አክቲቪስቶች ህዝቡ ቀድሞ እየተጓዘ መሆኑን ገልጸዋል። የህዝቡን ፍላጎት በመጠበቁ ረገድ፣ አክቲቪስቱም ሆነ ምሁራኑ ቀድሞ መገኘት እንዳለበት ዛሬ በአዲስ አበባ ዉስጥ ታሪካዊ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ አክቲቪስቶች ለቢቢኤን አሳዉቀዋል። ቢቢኤን ነሐሴ 1/2008

No comments:

Post a Comment