Saturday, October 1, 2016

ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ለመጄመሪያ ጊዜ በድብቅ ቀረበ ።



Image may contain: 1 person , hat
ኮረኔል ደመቀ ዘውዱ ዛሬ ፍርድ ቤት ለመጄመሪያ ጊዜ በድብቅ ቀረበ ።
ኮረኔል ዛሬ ወደ ፍርድቤት መምጣቱን ህዝቡ ባለመስማቱ እንደ አለፉት ጊዚያት ፍርድ ቤቱ በህዝብ አልተጥለቀለቀም። ይል ቁንም የአማራ ክልል መከላከያ በብዛት ፍርድ ቤቱን በክፍተኛ ጥበቃ ዙሪያውን ከብበውት ነበር።


ኮረኔል ደመቀ ቀደም ሲል በክልሉ የአቃቤ ህግ የተመሰረተበት ሰው የመግደል ክስ በፍርድ ቤቱ ውድቅ የተደረገም ቢሆን ከፌደራል መንግስት የመጣው አቃቤ ህግ አንድ ዘርን በማጥቃት እና በአሸባሪነት ተጠርጣሪ ነው በማለት ክስ መስርቶበታል። ፍርድ ቤቱም ጉዳዩን ለመጭው ጥቅምት ወር ቀጠሮ ሰጥቷል።


የጎንደር ህዝብ እንደ አይኑ ብሌን የሚያየው ኮረኔል ደመቀ ፍርድ ቤት መቅረቡን ዘግይቶ የሰማው የጎንደር ከተማ ነዋሪ በተለይ እናቶች አሁን ነው የገደሉን እያሉ ሰብሰብ ብለው ሲያነቡ ታይተዋል።


በተያያዘ ዜና በጎንደር ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ በርካታ ወጣቶች ታስረው የነበረ ሲሆን በሌሊት የት እንደወሰዷቸው ማዎቅ አልተቻለም። የታሳሪ ቤተሰቦች ስንቅ ለማቀበል ሲሄዱ እዚህ የሉም የት እንደተወሰዱ አናውቅም የሚል መልስ ከጣቢያው ፖሊሶች መሰጠታቸውን ከስፍራው የአይን እማኝ አረጋግጦልኛል

No comments:

Post a Comment