Monday, October 10, 2016

የአማራ ተጋድሎ መሪ አለው፣ የአማራ የጎበዝ አለቆች (አቻምየለህ ታምሩ)



የአማራ ተጋድሎ መሪዎች በጎንደር፣ በጎጃም፣ በሸዋና በወሎ የሚገኙ የጎበዝ አለቆች ናቸው። የፊታችን ጥቅምት ሶስት ወር የሚሆነው ይፋዊ የአማራ ተጋድሎ የጎበዝ አለቆቻችን በብቃት እየመሩት ነው።
የወያኔ ልሳኖቹ ኢቢሲ፣ ሰንደቅና ሪፖርተር ሊያንቃቸው ጋት የቀረውን ተጋድሏችንን «መሪ የሌለው ትግል» አድርገው ሊያቀርቡት ይቃጣቸዋል። እነሱ የሚያውቁት የመሪ ሞዴል ከኮምኒስት ማኒፌስቶ የሚሳብ፤ በአብዮታዊ ዲሚክራሲ የተጠመቀ፤ እንደ ሊቀ መንበር መለስ ዜናዊ አይነት ፈላጭ ቆራጭ ግለሰብ ስለሆነ ከዚያ የተለየ አገርኛ የትግል አመራር ዘዴ ውጤት እንኳ ቢያመጣ «መሪ» ያለው መስሎ ሊታያቸው አይችልም።
የኛ ተጋድሎ የመሪ ሞዴል እንደነሱ ከአውሮፓ ያመጣነው የአንድ ግለሰብ ፈላጭ ቆራጭነት የሚሰፍንበትና ሙታን እድምተኞች ጀሌ ሆነው የሚሰለፉበት ድንግዝግዝ ሳይሆን ከአባቶቻችን የወረስነው፤ ወራሪዎቻችንንም በተደጋጋሚ ያሳፈርበት አገርኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ነው።
የጎበዝ አለቃ መሰረታዊ ጽንሰ ሃሳብ ጎበዞች ከመሃከላቸው አንዱን ጎበዝ አለቃ አድርገው ስራቸውን የሚሰሩበት አገርኛ የአርበኞች አደረጃጀት ነው። የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት እንደ መለስ ዜናዊ አንድ «ጎበዝ» ሺ ነፈዞችን በዙሪያው አሰልፎ የሚነግራቸውን ብቻ የሚደግሙ ደናቁርት የተሰበሰቡበት ስምሪት አይደለም። በጎበዝ አለቃ አደረጃጀች ሁሉም ጎበዞች ስለሆኑ በመካከላቸው የበላይና የበታች የለም። የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት እንደ ወያኔ አንዱ ሲሞት ያለመሪ የሚቀር ስብስብ ሳይሆን ሁሉም በማንኛውም አስፈላጊ በሆነ ጊዜ አለቃ የመሆን ችሎታውም ሆነ ፈቃደኝነቱ ያላቸው ጎበዞች አደረጃጀት ነው።
መለስ ዜናዊ የፈጠረው «የአብዮታዊ ዲሞክራሲ» አደረጃጀት በበሉበት የሚጮሁ፣ በሆዳቸው የሚገዙ ካድሬዎች ጥርቅም ነው። ስለሆነም ኮንትራክታቸው ሆዳቸው እስከሞላ ድረስ ስለሆነ አለመተማመን፣ አለመከባበር፣ ጥላቻ፣ አንዱ ባንዱ ላይ መረማመድ የስብስቡ መገለጫ ነው። የኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ግን የመዋቅሩ መሰረት የቆመው በእኩልነት ላይ በመሆኑ መተማመን፣ መከባበር፣ መፋቀር፣ አንዱ ላንዱ ከኔ ይብስ መባባል ጎልቶ የሚታይ የስብስቡ መገለጫ ነው። መለስ ዜናዊ የገነባው «አብዮታዊ ዲሞክራሲ» ግን የበላይና የበታች ያለበት፤ መጠራጠር፣ ፍራቻ፣ ጥላቻ፣ ቅናትንና ጊዜን ጠብቆ መጠቃቃት መርሁ የሆነ የእፉኝት ልጆች ስብስብ ነው።
መለስ ዜናዊ የፈጠረው አደረጃጀት የአንድ ግለሰብ አስተሳሰብ ያለ ገደብ የሚፈጸምበት ስርዓት ነው። ስለሆነም የሚያኮርፈው፣ የሚከፋው፣ የሚያዝነውና ቂም የሚቋጥረው ሎሌ፣ አሽከርና ጀሌ ቁጥር የትየለሌ ነው። የኛው የጎበዝ አለቃ አደረጃጀት ግን የሁሉም ሃሳብ በእኩልነት የሚስተናገድበት፤ የተሻለው በውይይት ተቀባይነት የሚያገኝበት፤ ከሃሳቦች ሁሉ ምርጥ የሆነው በሁሉም የጎበዝ አለቆች ይሁንታ አግኝቶ በሙሉ ስሜት ተግባራዊ የሚሆንበትና ውጤቱም ሁሉንም የሚያረካ ስርዓት ያነበረ የአባቶቻችን አስተዳደራዊ መዋቅር በሆኑ የሚያኮርፍ፣ የሚከፋ፣ የሚያዝንና ቂም የሚቋጥር አንድም ሰው የለም።
እኩልነት ብሎ ነገር ደብዛው የሌለበት የሊቀ መንገበር መለስ ዜናዊ «የአብዮታዊ ዲሞክራሲ» አደረጃጀት ስብስቡ የሚዘወረው በአንድ ሰው ሃሳብ፣ በአንድ ሰው ፍላጎት ስለሆነ የተሻሉ ሃሳቦች ወደፊት የመምጣት እድል የላቸውም። ሊቀ መንበሩም ከራሱ የስልጣን ጥቅም አንጻር ብቻ ስለሚያስብ ውጤቱ አብዛኛውን የስብስቡን አካላት የማያረካ ይሆናል።ይህ የበለጠ ጥርጣሬ፤ የበለጠ በቀለኝነት ያሰፍናል። ሊቀ መንበሩም ይህንን ስለሚያውቅ ጥርጣሬና በቀልተኝነትን ለመቆጣጠር ሲል ነጻነትን እያፈነ ይሄዳል። «ውስጣዊ ዲሞክራሲ» የሚለው የመለስ ዜናዊ «አብዮታዊ ዲሞክራሲ» አስተሳሰብ በግለሰብ አምባገነንበት የተደመደመው ጥርጣሬና በቀልተኝነትን ለመቆጣጠር ሲል ነጻነትን በማፈኑ ነው።
የአማራን ተጋድሎ መሪ የሌለው አድርጋችሁ የምታስቡ የአማራ ተጋድሎ መሪ እንዳለው ማወቅ ይኖርባችኋል። መሪዎቹ ደግሞ በአባቶቻችን ትውፊት የተደራጁትና በዘመናዊ መልክ የተቀናጁ መሬት ላይ ያሉት የአማራ የጎበዝ አለቆች ናቸው። የአማራ የጎበዝ አለቆች የአማራን ተጋድሎ እየመሩ ያሉት እንደ ወያኔ በሞቀ ቤታቸው ቤተ ሽፍታ [ቤተ መንግስት ላለማለት ነው] ሳይሆን ህዝባችን መሃል እየዋሉ፣ እያደሩና የህዝቡ አካል ሆነው ነው። የጎበዝ አለቆቻችን ትግሉን እየመሩ ያሉት የተሰዋውን አርበኛ በክብር መዝገብ አስፍረው እንደየ ቤተ እምነቱ በክብር እንዲያርፍ በማድረግ እንጂ እንደ መለስ ዜናዊ መለስ ዜናዊ «የሟች ወታደሮችን አሃዝ ይፋ የማድረግ ግዴታ የለብኝም» በማለት የአርበኞችን ሞራል በመግደልና የጠላትን ሞራል ደግሞ ከፍ በማድረግ አይደለም።
ጀግኖች አባቶቻችን ፋሽስትን አምስት አመታት ሙሉ በዱር በገደል የተፋለሙት በመሰረቱት የጎበዝ አለቃ ስርዓት ነው። ጥሊያን የዚህን አገርኛ አደረጃጀት መሪ ቢገድልም ሁሉም የጎበዝ አለቆች መሪ ሊሆኑ የሚችሉ ጎበዞች ስለሆኑ አንድ መሪ የጎበዝ አለቃ ቢሰዋ ትግሉ ነጻነታችንን መልሰን እስክናገኝ ድረስ ሊቆም ያልቻለው ለዚያ ነበር። ይህም በመሆኑ ነጻነታችንን ልናስመልስ ችለናል። አሁንም እየሆነ ያለው ያ ነው።
ወያኔዎችና ሎሌዎቻቸው የሚያውቁት ግን አንድ መሪ ብቻ ስለሆነ አንዱ ሲሞት ሌላውን ደምስሶ የሚገዛ እንደ መለስ ዜናዊ አይነት አንድ ግለሰብ ያለ ስለማይመስላቸው ተጋድሏችን መሪ የሌለው ይመስላቸዋል። ወያኔዎቹ በሙሉ የባንዳ ልጆች ናቸው። ጥሊያን በወረረን ጊዜ የጥሊያን አገልጋይ የነበሩትን ባንዶቹን አባቶቻቸውን ጀግኖቹና አርበኞቹ አባቶቻችን አቧራ አስገስተው ያሸነፏቸው በዚህ አገርኛ የጎበዝ አለቆች ስርዓተ ማህበር ተደራጅተው ነበር። ዛሬም ታሪክ መደገሙ አይቀሬ ነው። የአባቶቻችን ልጆች የሆንን የዛሬ ወጣቶች አባቶቻችን በመሰረቱት የጎበዝ አለቃ ስርዓት ተደራጅተን የባንዶች አባቶቻቸው ልጆች ከሆኑት ከወያኔዎች ነጻ እንወጣለን። እኛም ከአርበኞች አያቶቻችን አናንስም፤ ወያኔዎችም ከባንዶች አባቶቻቸው አይበልጡም። በአንድ ልብ ሆነን ህልውናችንን ሊያጠፋ በመጣ ጠላት ላይ የምናደርገውን ትግል የወያኔ ኢንተርኔት ቢቋረጥ፤ የትግራይ ነፍሰ በላ ጦር ሰራዊት ቢሰማራ ወይንም ሌላ ፋሽስት ወያኔያዊ ምድራዊ ኃይል ቢመጣ የአማራን ተጋድሎ ሊያስቆመው አይችልም።
#የአማራ_ተጋድሎ ይቀጥላል!



No comments:

Post a Comment