Sunday, October 2, 2016

በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል



አሁን ባለው ቁጥር ከ295 በላይ ሰዎች በቢሾፍቱ ተረሽነዋል፡፡ 120 አስክሬኖች ወደ ቢሾፍቱ ሆስፒታል ሲሄዱ 175 የሚሆኑት አስክሬኖች ወደ አዲስ አበባ ተጭነዋል፤ወደ ቢሾፍቱ ሀይቅ ውስጥ ከአስለቃሽ ጪስ እና ከጥይት ሸሽቶ የሰጠመ ህዝብ ቁጥር ብዛት ግን ገና አልታወቀም፡፡
በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል፤፤
#Ethiopia #Oromoprotests #Irreecha2016 #MinilikSalsawi #Shashemene
በደብረዘይት በኢሬቻ በዓል ላይ የተፈጸመውን ወታደራዊ እርምጃ ተከትሎ በሻሸመኔ ህዝቡ ለተቃውሞ ወጥቶ በአደባባይና በየቀበሌው ከታጣቂ ኃይል ጋር ተፋጦ ይገኛል፤፤ ወጣቶች ወገኖቻችን ደም ፈሶ አይቀርም፣ የእኛም ደም ነው የፈሰሰው፡፡ ክብራችን፣ መብታችንና ነጻነታችን እስከሚመለስ ትግሉ ይቀጥላል፡፡
በተመሳሳይ የአጄ ከተማና አካባቢቀው ነዋሪዎች ለኢሬቻ በዓል በሄዱ ወገኖቻቸው ላይ በደረሰው አሰቃቂ ወንጀል ለመቃወም አደባባይ ወጥቶ በከተማ መስተዳድር ግቢ የተሰቀለውን ባንዲራ አውርደው ኮከብ ጠሌለበትን የኢትዮጵያ ሰንደቅና የኦነግ ዓርማ በቦታው ሰቅለዋል፡፡ ይህን ተከትሎ ታጣቂ ኃይሉና ነዋሪው ከፍተኛ ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው፡፡

No comments:

Post a Comment